cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ድምፀ ተዋሕዶ

ይህ መንፈሳዊ ቻናል መቀመጫውን እንግሊዝ ለንደን ያደረገ ማንኛውንም ታማኝ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችን እና መንፈሳዊ ክንውኖችን ለምእመኑ በፍጥነት፤ በጥራት ያቀብላል። የእግዚአብሔር ጸጋ እና በረከት በሁላችን ላይ ይደር። ድምፀ ተዋሕዶ ለንደን ለታማኝ መረጃዎ

Show more
Advertising posts
11 113
Subscribers
+3424 hours
+817 days
+68930 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
አባ ፍራንሲስ “የሚያስከፋ እስካልሆነ ድረስ ስለ ፈጣሪ መቀለድ ችግር የለውም” አሉ አባ ፍራንሲስ ለኮሜዲያኑ "በፈጣሪ ላይ እንኳን መሳቅ ትችላላችሁ፣ ይህ መናፍቅነት አይደለም” ብለዋል። የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ “የሚያስከፋ እስካልሆነ ድረስ ስለ ፈጣሪ መቀለድ ችግር የለውም” በማለት ለተሰበሰቡት ታዋቂ ኮሜዲያኖች እንዲሁም አርቲስቶች ነበር የተናገሩት። አባ ፍራንሲስ ከመላው ዓለም ከተውጣጡ ከ100 በላይ ኮሜዲያን፣ የፊልም ተዋናዮች እና ጸሃፊዎችን በትናንትናው እለት በቫቲካን አግኝተው አነጋግረዋል። ከአባ ፍራንሲስ ጋር ከተገናኙ ታዋቂ ሰዎች መካከልም የአሜሪካ ታዋቂው የሾው ቢዝ አቅራቢ ውሁፒ ግልድበርግ፣ ጂሚ ፋሎን፣ ካነን ኦበሪየን፣ ክሪስ ሮክ እና ስቴፈን ኮልበርት እንደሚገኙበት ሮይተርስ ዘግቧል። በዚሁ ወቅት በጣሊያንኛ ንግግር ያደረጉት አባ ፍራንሲስ "በፈጣሪ ላይም መሳቅ እችላለን” ያሉ ሲሆን፤ ይህ ስድብ አይደለም እኛ ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር እንደምንጫወት እና እንደቀልድ ሁሉ በፈጣሪ ላይም እንችላለን” ሲሉ ተደምጠዋል። “የሚያስከፋ እስካልሆነ ድረስ ስለ ፈጣሪ መቀለድ ችግር የለውም” ያሉት አባ ፍራንሲስ፣ “እያልኩ ያለሁት ነገር መናፍቅነት አይደለም፤ በአንድ ሰው ከንፈር ላይ እንዴት ፈገግታን መፍጠር እንዳለብህ ካወክ እና አንድን ሰው ፈገግ ካሰኝህ፤ እግዚአብሄርም እንዲስቅ ታደርጋለህ” ብለዋል። የሮማው ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ 30 ደቂቃ ከፈጀው እና ከመስመር ወጣ ያለ ነው የተባለውን ንግግራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ከኮሜዲያኖቹ ጋር እየተጨባበጡ ተቀላልቀደዋል። የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ በተደጋጋሚ በሚሰጧቸው ለየት ባሉ እና አነጋጋሪ አስተያየታቸው ይታወቃሉ። አባ ፍራንሲስ ከቀናት በፊት ቄሶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት በተቻለ መጠን አጭር እንዲያደርጉ ማሳሰባቸው ይታወሳል። አባ ፍራንሲስ አክለውም ለማስቀደስ እና ሌሎች በረከቶችን ለማግኘት ብለው ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጡ የዕምነቱ ተከታዮች በቄሶች አገልግሎት መርዘም ምክንያት እንቅልፍ እየጣላቸው ነው ብለዋል። ቄሶች ስለ ጌታ ከመጽሃፍ ቅዱስ ላይ ለምዕመናን የሚያስተምሩበት ጊዜ ከስምንት ደቂቃ መብለጥ የለበትም ሲሉ ሊቀ ጳጳሱ ተናግረዋል። ✅አል አይን የእግርጌ ማስታወሻ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መስመር ከሳተች ቆይታለች።ይልቅ አሁን ላይ ለተከታዮቻም ሆነ ውጪ ላለው ሰው በመጥፎ ዝንባሌዋ እና ወቅታዊ ልማዷ አስጊ እየሆነች ነው።
2725Loading...
02
አርባ ምንጭ ከተማ እንዲህ ባለ ድምቀት ብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በልጅነት ክብር ተቀብላ ተባርካለች። ሁሌም ሙቀቱ የማይለየው የደቡብ ህዝብ ዛሬም አባቶቹን በክብር ተቀብሏል።በተለይ አርባ ምንጭ ብዙ ያልተደረገለት ብዙ ሊሰራበት የሚገባ ሀገረ ስብከት ነው።
3021Loading...
03
ስርዓተ ጥምቀት ፈጽመው 123 ሰዎች ወደ ከኦርቶዶክሳዊ በረት ተጨምረዋል:: በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ክልል በሸካ ቤንች ሸኮ ምዕራብ ኦሞ ሀገረ ስብከት በቤንች ወረዳ ቤተ ክህነት በምትገኘው በቲሹ ደብረ ገነት ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን በትናንትናው ዕለት ሰኔ 6/2016 ዓ/ም 123 ነፍሳት ሀብተ ወልድ እና ስመ ክርስትናን አገኙ።
4692Loading...
04
ስደተኛው ተመራቂ፤ “ብፁዓን እለ ይሰደዱ በእንተ ጽድቅ፥እስመ ሎሙ ይዕቲ መንግሥተ ሰማያት።ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።”ማቴ፡፭፥፲። ሊቀ ማዕምራን ፈንታሁን ሙጬ የቤተ ክርስቲያኒቱን መደበኛ ትምህርት ዜማውን አቋቋሙን እና ቅኔውን ከሕፃንነቱ ጀምሮ “በእንተ ስማ ለማርያም” እያለ ቁራሽ እንጀራ እየለመነ፥ ከመቃብር ቤት ደንጊያ ተንተርሶ እየተኛ እስከ ጥግ ድረስ ተምሮአል።የእናቱን ፍትፍት እየጎረሰ፥በአባቱ እጅ እየተዳበሰ አላደገም።ያደገው በደጀ ሰላም ፍርፋሪ ነው፥የቤተ ክርስቲያን ፍርፋሪ ደግሞ ስመ እግዚአብሔር የተጠራበት፥ቃለ እግዚአብሔር ያረፈበት፥በመስቀለ ክርስቶስ የተባረከ፥ምእመናን በሃይማኖት ያቀረቡት በመሆኑ መድኃኒት ነው። በዘመናዊም የከፍተኛ ፪ኛ ደረጃ ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት ካጠናቀቀ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መግባት ቢችልም ፈቃደ ነፍሱን በማስቀደም ወደ ቅድስት ሥላሴ ቴኦሎጂ ዩኒቨርስቲ በመግባት የመጀመሪያ ድግሪውን ይዟል።ይህ ለቀለም ቀንድነት የተፈጠረ ወንድማችን በዚሁ ይበቃኛል ሳይል ከውጭ ሀገር የኒቨርስቲዎች ጋር በመጸጻፍ በግል ጥረቱ የነፃ ትምህርት ዕድል በማግኘቱ ወደ አውሮፓ በመጓዝ ሁለተኛ ድግሪውን ሠርቶአል። ከሁሉም የሚደንቀው በዚያው እንዲቀር ብዙ ግፊቶች ቢኖሩበትም “የቤተ ክርስቲያን ውለታ አለብኝ፤”በሚል ቀና መንፈስ ወደሚወዳት ሀገሩና ወደሚመካባት ቤተ ክርስቲያኑ በመመለስ በተለያዩ ሃላፊነቶች እናት ቤተ ክርስቲያኑን አገልግሎአል። እንደሚታወቀው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት አልጋ በአልጋ ሳይሆን በቀኖት ላይ የመረማመድ ያህል ነው። የቀን ዕረፍት የሌሊት እንቅልፍ አይሰጥም።ቢሆንም የጽድቅ ጉዳይ ስለሆነ ሁሉንም በጸጋ ተቀብሎታል። እንደገናም ከቤተሰብ አስተዳደር ጋር ያ ሁሉ ሃላፊነት ቢኖርበትም አሜሪካን ሀገር ከሚገኝ ዩኒቨርስቲ ጋር በመጻጻፍ ዕድሉን በማግኘቱ ሦስተኛ ድግሪውን በኦን ላይን እየተማረ አጠናቅቆ ነበር። በመሆኑም ስደት በወጣ በሦስተኛ ወሩ ኢንዲያና ከሚገኝ Newburgh Theological Seminary ሰኔ ፭ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. የአቡየ ዕለት በዶክተሬት ድግሪ ተመርቋል።በሐዘን ውስጥ ደስታ ያለው እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን።እመ እግዚአብሔር ፀባዖት ድንግል ማርያምም የተመሰገነች ትሁን።በእውነቱ መጋቤ ሃይማኖት መምህር አንዱ ዓለም ዳግማዊ በዕለቱ በስፍራው በመገኘት ብቸኝነት እንዳይሰማው በማድረግህ ልትመሰገን ይገባሃል።ወንድም ማለት እንደዚህ በችግር ጊዜ በጎን የሚቆም ነው።ሌሎቻችንማ “ኩሉ ጻድቅ በጊዜ ርቱዕ፤” ሆነናል። ለምን ተሰደደ? እንደምታስታውሱት በጥር ፳፻፲፭ ታላቋ ቤተ ክርስቲያን ከከባድ ፈተና ውስጥ ገብታ ነበር። በሃላፊው መንግሥት የተመኩ፥የዘረኝነት ጎርፍ የጠረጋቸው ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት ከሃይማኖት አፈንግጠው፥ቀኖና ሐዋርያትን ጥሰው፥መንፈስ ቅዱስ ካሰመረው መስመር ወጥተው በምዕራብ ሸዋ ወሊሶ በሕገ ወጥነት ኤጲስ ቆጶሳትን “ሾምን፤”ብለው ነበር።በወቅቱ ካህናትና ምእመናን እስከ ሞት ድረስ ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።በዚህ ክፉ ሰዓት ጠቅላይ ሚንስትሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን መብት ማስከበር ሲገባቸው፥ሕገ ወጥነትን በመደገፍ በሚንስትሮች ጉባኤ ላይ ንግግር አድርገው ነበር። ንግግሩም “አርፋችሁ ተቀመጡ፤”አይነት ነበር። ወዲያውም የቤተ ክርስቲያን ደጆች በታጣቂዎች እየተሰበሩ፥ካህናትና ምእመናንም እየተገደሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሕገ ወጦቹ ተላልፋ ተሰጠች።አያሌ ምእመናንም ታሰሩ፥ተገረፉ፥ከመንግሥት ሥራቸውም ተፈናቀሉ። በዚያ ቀውጢ ሰዓት ሊቀ ማእምራን ፈንታሁን ሞት ጥላውን ባጠላበት ከተማ እንደሚኖር እያወቀ ፥ራሱ በሥራ አስኪያጅነት በሚያስተዳድረው የቤተ ክርስቲያኒቱ ቴሌቪዢን ቀርቦ፥ጠቅላይ ሚንስትሩ በቤተ ከርስቲያኒቱ ላይ በድፍረት ለተናገሩት ነገር ሁሉ ቃል በቃል መልስ ሰጣቸው።በክፉ ቀን ለቤተ ክርስቲያኑ ጠበቃ ሆኖ በአደባባይ በትሁት ቃል እና በትሁት ሰብእና ተሟገታቸው። ይህንንም ያደረገው ሃይማኖታዊ ግዴታወን ለመወጣት ብቻ እንጂ ማንንም ለማስቀየም ወይም ማንም እንዲያጨበጭብለት አልነበረም።ነገር ግን ከዚያች ቅጽበት ጀምሮ በደኅንነት ክትትል ስር ወደቀ። በመጨረሻም ለቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ ወደ ሰሜን አሜሪካ ለመሄድ አይሮፕላን ውስጥ ከገባ በኋላ አንቀው አስወረዱት።እንዳይሞት እንዳይሽር አድርገው የእግዚአብሔርን ካህን ቀጠቀጡት። በብረት ካቴና አስረውትም ከጨለማ ቤት ጣሉት። እነርሱ አጥንትን እንኳ ሊያደቅ በሚችል በትር እየደበደቡት ውዳሴ ማርያም ይደግም ነበር።”መከራውን ያስቻለችኝ እርሷ ናት፤”ይላል። ከዚህ ሁሉ ሥቅየት በኋላ የጀመረውን የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ ከጫፍ ለማድረስ፥እስከ ቁስሉ ወደ ሰሜን አሜሪካ መጣ።ለመቆም ለመቀመጥ፥ ለመተኛት ለመነሣት መከራ ሆነ።ሁሉ ነገር በሰው ድጋፍ ነበረ።አሁንም ወንድማችን ዶክተር አንዱ ዓለም ከፍተኛ ወጪ በማውጣት በሕክምና እንዲደገፍ በማድረጉ፥ሐዘኑን እስኪረሳ ድረስ በመንከባከቡ፥ለቤተ ክርስቲያኒቱ ቴሌቪዥን መምሪያ የሚያስፈልጉትን ውድ ውድ ቁሳቁሶችን በሟሟላቱና ሀገር ቤት ድረስ አሜሪካዊ ባለሞያ ይዞ በመሄድ ሠራተኞቹ እንዲሰለጥኑ በማድረጉ ሊመሰገን ይገባዋል። ሊቀ ማዕምራን አሁንም “ከሚገባህ በላይ መሥዋዕትነት ከፍለሃል፥ይበቃህል፥በዚሁ ቅር፤”ለሚለው የወዳጆች ምክር ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ሀገር ቤት ተመለሰ።ለአንድ ዓመት ያህልም ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ራእይ ለማሳካት ታገለ።ነገር ግን የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጠላቶች አላንቀሳቅስ አሉት። አንዳንድ ወዳጆችም “እባክህ ለቤተ ክርስቲያንም ቢሆን ከምትሞትባት ብትኖርላት ይሻላል፥ሰላማዊ ዘመን ሲመጣ ታገለግላታለህ።ቃሉም የሚለው ‘ተኀባእ ኅዳጠ ምዕረ እስከ የኀልፍ መዓቱ ለእግዚአብሔር።የእግዚአብሔር ቁጣ እስኪያልፍ ድረስ ጥቂት ተሸሸግ ነው።’”ሲሉት ሳይወድ በግዱ ሀገሩን ጥሎ ተሰደደ።ቤተ ክርስቲያን ግን በመላው ዓለም ስላለች መቼም ቢሆን አያጣትም፥ያገለግላታል።
5334Loading...
05
በዋግሕምራ ዞን አበርገሌ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ 1.53 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነበት ማኅበራዊ ድጋፍ ተደረገ፡፡  ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) ማኅበረ ቅዱሳን ከደጋፊ አካላት ጋር በመተባበር በዋግሕምራ ዞን አበርገሌ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 1.53 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነበት ማኅበራዊ ድጋፍ አድርጓል፡፡  የማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ በሀገራችን እያጋጠሙ ያሉ ሰፊ ማኅበራዊ ቀውሶች በምእመንመናን፣ በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ላይ እያስከተሉት ያለውን ሁለንተናዊ ችግር ለማቃለል ሰፊ የማኅበራዊ ድጋፍ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና በመተግበር በተገቢ ደረጃ ማኅበራዊና ሰብአዊ ሚናውን እየተወጣ እንዳለ ይታወቃል። ማኅበሩ እነዚህን ችግሮች በስፋት በማጥናት ላለፉት 6 ዓመታት በሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያው በኩል በአርሲ፣ በሐረር ፣በባሌ፣ በወሊሶ፣ በሻሸመኔ፣ በዶዶላ፣ በአጋርፋ፣ በጅጅጋ፣ በሲዳማ፣ በመተከል፣ በቤንሻጉል ጉምዝ፣ በፓዊ፣ በቡለን፣ ፣በሽሬ፣ በአክሱም፣ በያቤሎ፣ በጎንደር አዘዞ፣ በአዲግራት፣ በማይ ጨው፣ በሽረ እንደ ሥላሴ ፣በመቐለ፣ በደብረ ብርሃን፣ በደሴ፣ በወልዲያ፣ በላሊበላ ፣በሐይቅ እስጢፋኖስ፣ በወሎ ገራዶ፣ በደባርቅ ፣በጃን አሞራና በሌሎችም የሀገራችን ክፍል ለሚገኙ ተጎጅዎች ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ድጋፍ አድራጊ ምእመናንና ተቋማትን እያስተባበረ የአልባሳት፣ የምግብ እና መሠል አስቸኳይ ድጋፎችን በስፋት ሲያደርግ ቆይቷል። አሁንም አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህ መሠረት በዋግሕምራ ዞን አበርገሌ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖችና በአካባቢው ለሚገኙ ለተመረጡ 3 ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች 1.53 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነበት 202 ኩንታል የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ አድርጓል።  ከዚህ ድጋፍ ውስጥ 1,000, 000 (አንድ ሚሊዮን ብር) ወጭው የተሸፈነው ግሎባል አሊያንስ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በሀገረ አሜሪካ ሜኔሶታ ከሚገኘው የርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ምእመናና አገልጋዮች ጋር በመተባበር ያበረከቱት ነው። ቀሪው ወጭ የተሸፈነው በሀገረ አሜሪካ ከሚገኘው የሲያትል ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው። ሰኔ 05-06 ቀን 2016 ዓ.ም በቦታዎቹ በመገኘት በተደረገው በዚህ የእጅ በእጅ ድጋፍ ርክክብ ወቅትም፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከልና የሰቆጣ ማእከል ልዑካን፣ የግሎባል አሊያንስ ድርጅት ተወካይ እንዲሁም የወረዳው የመንግስት አካላት ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በወረዳው ከ67 ሺህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎች አሁንም ድረስ አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ የሚሹ መሆናቸውን በድጋፍ ሥርጭት ወቅት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ለማኅበረሰቡ ከተደረገው ድጋፍ በተጨማሪ የአማናዊው ዕውቀትና ጥበብ ምንጭ ለሆኑ በአካባቢው ለሚገኙ 3 ገዳማትና ጉባኤ ቤቶች ተመሳሳይ ድጋፎች ተደርገዋል። ማኅበረ ቅዱሳን በቅርብ ጊዜያት ብቻ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅና ጃን አሞራ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ በሰቆጣና አካባቢው ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በደቡብ ኦሞ በናጸማይ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ በሃይማኖት ተኮር ጥቃት ለተጎዱ የቅበት ኦርቶዶክሳውያን፣ በደብረ ብርሃን ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በትግራይ መቐለ ኩሓ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በትግራይ አጽቢ ወንበርታ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ የደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳምን ጨምረ በማኅበራዊ ቀውስ ለተጎዱ 6 ጥንታዊያን ገዳማትና ጉባኤ ቤቶች ከፍተኛ ድጋፎችን አድርሷል። ማኅበረ ቅዱሳን ይህ ሰብአዊ ድጋፍ ለተጎጅ ወገኖች እንዲደርስ የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ አካላትን እያመሰገ፣ በቀጣይ ተመሳሳይ ድጋፎችን ለማድረስ በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን፣ ማኅበራት፣ ልዩ ልዩ ተቋማትና በጎ አድራጊ ድርጅቶች የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲል ጥሪውን ያቀርባል። ድጋፍ ለማድረግ፡- በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡- 1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901 2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458 3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648 4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101 5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 6. በጎ ፈንድ ሚ https://www.gofundme.com/f/uerc8... 7. በወገን ፈንድ ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። ✅የማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ
5022Loading...
06
ምን አይነት መዝሙሮችን ይፈልጋሉ?👇👇👇
911Loading...
07
On this day, we celebrate the Ascension of our Lord, God and Savior Jesus Christ. This Feast is celebrated each year on the fortieth day after the Great and Holy Feast of Pascha (Easter). Since the date of Pascha changes each year, the date of the Feast of the Ascension changes. The Feast is always celebrated on a Thursday. The Feast itself commemorates when, on the fortieth day after His Resurrection, Jesus led His disciples to the Mount of Olives, and after blessing them and asking them to wait for the fulfillment of the promise of the Holy Spirit, He ascended into heaven
10Loading...
08
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ  ዕርገቱ በምድር ላይ የሚሠራውን የትሕትና ሥራ የመፈጸሙ ምልክት ነው፡፡ ዕርገቱም ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት “ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ/ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ (መዝ ፵፮፥፭፡፮) እንዳለው በታላቅ ክብር እልልታና ምስጋና ነው፡፡ ጌታችን የድል ዕርገትን ያረገው ወደ ባሕርይ አባቱ ቀኝ ነው፡፡ በእርሱ ዕርገት የጸጋ መንፈስ ቅዱስና የዳግም ምጽአት ተስፋዎች ተሰጥተውናል፡፡ የእርሱ ዕርገትም ለነፍሣችን ዕርገት /ለዕርገተ መንግሥተ ሰማያት/ አርአያ ሆኖናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ክርስቲያኖች በጻፈው ክታቡ ይህንን ሲያስረዳ፦ « ንሕነ ሕያዋን እለ ንተርፍ አመ ምጽአተ እግዚእነ ንትመሠጥ በደመና ምስሌሆሙ ኅቡረ ከመ ንትቀበሎ ለእግዚእነ ውስተ አየር » « እኛ ሕያዋን ሆንን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉትን አንቀድማቸውም ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክት አለቃ ድምጽ በእግዚአብሔር መለከት ከሰማይ ይወርዳልና በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ። ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ጌታን በአየር ለመቀበል ከእርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን። እንዲሁም ሁል ጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን። ስለዚህ እርስ በእርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ» በማለት የክርስቶስ ዕርገት ለምዕመናን ዕርገት መሠረት መሆኑን ገልጾልናል (፩ተሰ. ፬፡፲፯)። ወደ ልጁ ጢሞቴዎስ በላከው መልእክቱም « በሥጋ የተገለጠ፣  መንፈስ የጸደቀ፣  ለመላእክት የታየ፣  በአሕዛብ የተሰበከ፣  በዓለም የታመነ፣ በክብር ያረገ» በማለት ልደትን እንደ ዘር ዕርገትን እንደ መከር አድርጎ ገልጾልናል። (1ጢሞ.3፥16) ወርሐ ዘር የመከር ጊዜ ነው፡፡ ገበሬ በጎተራ ያለውን እህል እያወጣ ሲዘራ ከላይ ዝናም ከታች ጭቃውን ታግሶ ነው፡፡ በመከር ጊዜ ያን የዘራውን ምርት በጥፍ ሲያገኝ ደስ ይለዋል መከራውን ይረሳዋል፡፡ ምነው በጨመርኩበት ይላል የክርሰቶስም ልደቱ ስለኛ መከራን ለመቀበል ነውና፥ በሥጋ የተገለጠ ብሎ ትሕትናውን አሳየ፡፡ ዕርገቱን ግን በክብር ያረገ ብሎታል፡፡ ምክንያቱም የሰውነትን ሥራ ፈጽሟልና ድል ነስቶአልና ይህን በሥጋ ዕርገቱን ስናስብ ለምን ዕለቱን ተነሥቶ እለቱን አላረገም ለምንስ እስከ አርባ ቀን በምድር ላይ ቆየ ቢሉ ፡ እስከ አርባ ቀን በምድር ላይ የቆየው ትንሣኤው በግልጽ እንዲረዳ ደቀ መዛሙርቱንም መጽሐፈ ኪዳንን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያስተምር ዘንድ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በወንጌሉ ‹‹አልቦ ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘእንበለ ዘወረደ እምሰማይ ወልደ ዕጓለመሕያው፤ ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው፡፡ » ብሏል። (ዮሐ.3፥13) ጌታችን ሞትን በሥልጣኑ ከሻረ፣ ሙስና መቃብርን ካጠፋ፣ የትንሣኤያችን በኩር ሆኖ በዕለት ሰንበት ከሞት ከተነሣ በኋላ በምድር ላይ መቆየቱ የማያምኑ ፈሪሳውያንም ‹‹ትንሣኤው ምትሐት ነው›› እንዳይሉ እየታየ እያስተማረ እስከ 40 ቀን ድረስ በምድር ቆይቷል፡፡ በነዚህም የ40 ቀናት 3 ጊዜያትጉባኤ ዘርግቶ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ ቅዱስ ወንጌል ይነግረናል፡፡ " ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥላቸው ይህ ሦስተኛ ጊዜ ነበረ " እንዲል ወንጌላዊው ዮሐንስ (ዮሐ.21፥14 ) እነዚህንም 3 ጉባኤያት የተባሉትን ሊቃውንት አባቶቻችን፡- 1ኛ በዕለተ ዕሁድ በዕለተ ትንሣኤ 2ኛ በአግብኦተ ግብር /በዳግም ትንሣኤ/ 3ኛ በጥብርያዶስ ባሕር የተገለጡ ጉባኤያት መሆናቸውን አመሳጥረው ያስተምሩናል። ጌታችን በ40 ቀናት ውስጥም መጽሐፈ ኪዳንን ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሯል፡፡ ቅዱስ ያሬድም ዝማሬ በተባለው መጽሐፍ የጌታችንን ማዳን ከፅንሰቱ ጀምሮ እስከ ዕርገቱ ብሎም እስከ ዳግም ምጽአቱ ከብሉያትና ከሐዲሳት እያጣቀሰ አምልቶና አስፍቶ በተናገረበት የምስጋና ክፍል “ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና፤ ለድንግል ዘፈትሐ ማኅፀና፤ ለደቂቀ እስራኤል ዘአውረደ መና፤ ውእቱኬ ዘአድኃና ለሶስና እም እደ ረበናት፤ ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና / በደመና ወደ ሰማይ ዐረገ፤ የድንግልን ማኅፀን የፈታ፣ ለእስራኤል ልጆች መናን ያወረደ፣ ሶስናን ከረበናት እጅ ያዳነ፣ በደመና ወደ ሰማይ ዐረገ/” ብሏል፡፡ ‘ዐረገ’ መባሉ የሌለበት ቦታ ኑሮ ካለበት ቦታ ወደ ሌለበት ቦታ ሔደ ማለት አይደለም፡፡ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ወደ ባሕርይ አባቱ መመለሱን፣ የማዳን ሥራውን መፈጸሙን፣ በሥጋ በክብር ማረጉን ለመግለጽ ነው፡፡ አንድም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደመና ዐረገ ሲል በክብር ማረጉን፣ ልዕልናውን መግለጹ ነው፡፡ ደመና ክብሩ ልዕልናው ነውና። በደመና ዐረገ መባሉ በእመቤታችን ጀርባ መታዘሉንም ለመግለጥ ነው። ደመና ተብላ የተገለጠችው እመቤታችን ድንግል ማርያም ናትና። ከማርያም በነሣው ሥጋ ዐረገ ማለት ነው። ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ “እነሆ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብጽ ይመጣል” (ኢሳ.፲፱፥፩) ብሎ አስቀድሞ በትንቢቱ የተናገረላት ደመና እመቤታችን ናት። ሊቁ ቅዱስ ያሬድም “ደመናሰ ዘይቤ ይእቲኬ ማርያም እንተ ጾረቶ ዲበ ዘባና፤ ደመናስ የሚላት አምላክን በጀርባዋ የተሸከመችው ማርያም ናት” በማለት ያስረዳል። ስለዚህ በደመና ዓምድ ዐረገ ሲል ከድንግል ማርያም በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማይ ዐረገ ማለት ነው። ቤተ ክርስቲያናችንም በሥርዓተ ቅዳሴዋ “ላዕለ ይኩን ኅሊናክሙ በሰማይ የሀሉ ልብክሙ አእምሩ ኀበ ትቀውሙ ስምዑ ቃለ ጽድቅ ወአስምዑ ዜና ሰናይ” እያለች ዕርገቱን ታሳስበናለች። ሃይማኖተ አበው "ዐርገ እግዚአብሔር በቃለ ቀርነ መዊእ ወኢይቤ አዕረግዎ አላ ለሊሁ ዐርገ ወኢፈቀደ መራሔ ፍኖተ፥ እስመ ከመዝ ኢክህለ ኤልያስ ይዕርግ በዝንቱ መካን ነኪር አላ ኀይላት አዕረግዎ ኀበ ተአዘዙ ወቃለ እግዚአብሔርሰ ዋሕድ ለሊሁ ዐርገ በሥልጣኑ እስመ እግዚአ ኀይላት ውእቱ። ወበእንተ ዝ ይቤ ሉቃስ ወንጌላዊ በመጽሐፈ ግብር እስመ አርዳኢሁ ያንቀዐድዉ ኀቤሁ እንዘ የዐርግ ሰማየ ወኢይቤ አዕረግዎ ወኢሂ ጾርዎ እስመ መካን ኀበ ዐርገ ዘዚኣሁ ውእቱ"  ይላል። ሃይ. አበ. ዘዮ. አፈ. ፷፯፡፲፪-፲፬ ሰላም ለዕርገትከ ዘኢይትረከብ መጠኑ ወለንብረትከ ሰላም ለአቡከ ውስተ የማኑ ኢየሱስ ክርስቶስ እለ ኪያከ ተአመኑ ቅዱሳነ ዘእምኀቤከ ወንጹሐነ ይኩኑ ጰራቅሊጦስሃ መንፈስከ ፈኑ። ሰላም ለዕርገትከ በዘባነ መብረቅ ወነጎድጓድ፤ ከመ ትፈኑ መንፈሰከ በአምሳለ ነፋስ ወነድ፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በመንግሥትከ ዋሕድ፤ ይቤሉከ ለለ ዕለቱ ሰማያውያን ነገድ፤ መንግሥቱ ዘለዓለም ወምኩናኑኒ ለትውልደ ትውልድ፡፡ ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ። በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ። (መዝሙር 67፥ 33) መልካም በዓል ‼ 𝐀𝐬𝐜𝐞𝐧𝐬𝐢𝐨𝐧 𝐨𝐟 𝐨𝐮𝐫 𝐋𝐨𝐫𝐝, 𝐆𝐨𝐝 𝐚𝐧𝐝 𝐒𝐚𝐯𝐢𝐨𝐫 𝐉𝐞𝐬𝐮𝐬 𝐂𝐡𝐫𝐢𝐬𝐭 O Christ our God, You ascended in Glory and gladdened Your disciples by the promise of the Holy Spirit. Your blessing assured them that You are the Son of God, the Redeemer of the world. (Apolytikion for Holy Ascension)
5513Loading...
09
☁️ ☁️ ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ☁️ ☁️ ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ መዝ.67(68) ÷ 33 ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና፤ ለድንግል ዘፈትሐ ማኅፀና፤ ለደቂቀ እስራኤል ዘአውረደ መና፤ ውእቱኬ ዘአድኃና ለሶስና እም እደ ረበናት፤ ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና በደመና ወደ ሰማይ ዐረገ፤ የድንግልን ማኅፀን የፈታ፣ ለእስራኤል ልጆች መናን ያወረደ፣ ሶስናን ከረበናት እጅ ያዳነ፣ በደመና ወደ ሰማይ ዐረገ (ማኅሌታይ ያሬድ ኢትዮጵያዊ ) እንኳን ለ1982ኛው የጌታችን ብርሃነ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ ‼ 𝐀𝐬𝐜𝐞𝐧𝐬𝐢𝐨𝐧 𝐨𝐟 𝐨𝐮𝐫 𝐋𝐨𝐫𝐝, 𝐆𝐨𝐝 𝐚𝐧𝐝 𝐒𝐚𝐯𝐢𝐨𝐫 𝐉𝐞𝐬𝐮𝐬 𝐂𝐡𝐫𝐢𝐬𝐭 ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ዕርገቱ ለክርስቶስ እምድኅረ ተንሥአ እሙታን በዓርብአ ዕለት በይባቤ ወበቃለ ቀርን አማን መንክር ስብሐተ ዕርገቱ። ዛሬ በኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ደስታ ሆነ። ከሙታን ከተነሳ በኋላ በአርባ ቀን በእልልታ በመለከት ድምጽ ዐረገ። በእውነት ድንቅ ነው የዕርገቱ ምስጋና። ዮምሰ ዐባይ ትፍሥሕት እስመ ተንሥአ ወዐርገ ውስተ ሰማያት፤ ወነበረ በየማነ አቡሁ፤ ነሢኦ ሥጋ እንተ እምኀቤነ ተለዐለ፤ እምኀበ አቡሁ ተሰብሐ። ( ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ ) ዕርገት ከጌታችና ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ “ዕርገት” የሚለው ቃል “ዐርገ” ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ከታች ወደ ላይ መውጣት፣ ክፍ ከፍ ማለት፣ ማረግ ማለት ነው፡፡ ዕርገት (Ascension) ሲባልም ማረግን፣ ከፍ ከፍ ማለትን፣ ወደ ላይ መውጣትን ያመለክታል፡፡ በዓለ ዕርገትም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም የነበረውን የማዳኑን ሥራ ጨርሶ ወደ ላይ መውጣቱና በቀደመ ክብሩ በአብ ቀኝ መቀመጡ የሚከበርበት በዓል ነው፡፡ ለዚህም መሰረት እንዲሆን አርዮስን ለማውገዝ በኒቅያ የተሰበሰቡት ቅዱሳን አበው “ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ…/ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ…” ብለው ዕርገቱን በቅዱሳት መጻሕፍት ዋቢነት አስረግጠው ደንግገዋል፡፡ በወንጌልም "ወእንዘ ይባርኮሙ ተረኀቆሙ ወዐርገ ሰማየ" እየባረካቸው ራቃቸው፤ ወደ ሰማይም ወጣ። በማለት ተጽፏል (ሉቃ 24÷51)። ጥንተ ዕርገቱ በወርሐ ግንቦት በቀን ስምንት በዕለት ኅሙስ ሲሆን፤ ዘመኑ በ34 ዓ.ም፣ ወንጌላዊው/ዘመኑ ደግሞ በዘመነ ማርቆስ ነው፡፡ የዕርገት በዓል እስከ 4ኛው ክፍለ ዘመን እንደ ዛሬው ኅሙስን ሳይጠብቅ በጥንተ ዕርገቱ ግንቦት ስምንት ቀን ብቻ ይከበር ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህ ግን ትንሣኤ በዋለ በ40ው ቀን ብቻ እንዲከበር የቅዱስ ዲሜጥሮስ ባሕረ ሐሳብ ቀመርን መሠረት በማድረግ በቀኖና ቤተክርስቲያን ተወስኖ በሥራ ላይ ውሎ ይገኛል፡፡ ዕርገቱ የትሕትና ሥራው የመፈጸሙ ምልክት ነው። አምላካችን ምሉዕ በኩለሄ (ሁሉን የሞላ እና በሁሉም ቦታ የሚኖር) ነው። ስለዚህ ጌታችን በባሕርይው መውጣት መውረድ የለበትም። ‘ወረደ፣ ተወለደ’ ሲባል ፍጹም ሰው መሆኑን የትህትና ሥራ መፈጸሙን ከመናገር ውጪ ከዙፋኑ ተለየ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ዐረገ ወጣ ሲባልም ከሰማያዊው ዙፋኑ ተለይቶ ነበር ማለት አይደለም። በምድር ላይ ሊሰራ ያለውን ሁሉ መፈጸሙን ያመለክታል እንጂ። እንዲሁም ጌታችን በዕርገቱ ምክንያት ከቤተክርስቲያን የተለየበት ጊዜ የለም። ነገር ግን ዕርገቱ በሥጋው የተደረገውን ዕርገቱን ያመለክታል። ይህም ዕርገት ቅዱስ ሥጋው በምድር የስበት ቁጥጥር (Gravitational force) የማይዘው ለመሆኑ አስረጅ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ አምላካዊ ስልጣኑን ያሳያል።
4942Loading...
10
Media files
1360Loading...
11
ስድስት ቦትስዋናውያን የቅድስት ሥላሴ ልጅነት አገኙ። በማኅበረ ቅዱሳን የደቡባዊ አፍሪካ ማዕከል የቦትስዋና ግንኙነት ጣቢያ ከደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት እንዲሁም ከጋቦሮኒ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጋር በመቀናጀት የቤተ ክርስቲያንን ሐዋርያዊ ተልዕኮ ተደራሽ በማድረግ ስድስት ቦትስዋናውያንን አስጠምቋል። ከጥቅምት እስከ የካቲት 2016 ዓ.ም ለመጠመቅ የሚያበቃቸውን መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ተከታትለዋል። በሐድያና ሥልጤ ፣ ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ  አቡነ ሕርያቆስ መልካም ፈቃድ በደቡብ አፍሪካ በማፊኬን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ.ም የቅድስት ሥላሴ ልጅነት አግኝተዋል። ሥርዓተ ጥምቀቱ በማፊኬን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሳምሶን እና በአጥቢያው ካህናት የአካባቢው ምእመናን በተገኙበት ተከናውኗል።  በተጨማሪም ሦስት ቦትስዋናውያን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ በማፊኬን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የሚጠመቁ ይኾናል። ✅ዘገባው የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ነው
6291Loading...
12
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ሥርዓትን የጠበቁ  👉ሰዓታት 👉ሥርዓተ ዋይዜማ ወማኅሌት 👉መዝሙር ዘሰንበት 👉ምስባክ ዘዘወትር ወዘሰንበት 👉ዝማሬያት 👉ስንክሳር ዘቅዱሳን፤ከነ ቅዱሳን ሥዕላት 👉መንፈሳዊ ትምህርት 👉ሥርዓተ ቅዳሴ 👉አንድምታ 🎯ለማግኘት ቻናላችንን ይጐብኙ። ኢትዮጵያ ሀገራችንን ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቅልን!     ይ🀄️ላ🀄️ሉ ይማሩ                   👇🏾👇🏾👇🏾 https://t.me/+7-1kD8Wh7TYzYmQ0
570Loading...
13
💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒 💒                                          💒 💒      #የተዋህዶ_ፍሬዎች        💒 💒◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈💒 💒       ከ፩ኛ ዓመት ጀምሮ         💒 💒 መንፈሳዊ ኮርሶችን መማር     💒 💒          ለምትፈልጉ፦              💒 💒       እሄን ጹህፍ ነክተው         💒 💒    ወደ እግዚአብሔር ቤት       💒 💒        መግባት ይችላሉ           💒 💒  💠መልካም ትምህርት💠    💒 💒◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈💒 💒                                          💒 💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒
840Loading...
14
✝❤️ የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ 👇 👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 👤 ሊቀ መዘምራን . ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ 👤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 👤 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ 👤 ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ 👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን 👤 ዘማሪ| በሱፍቃድ አንድአርጋቸው 👤 ዘማሪት ሲስተር ሊዲያ ታደሰ 👤 ዘማሪ ዳግማዊ ደርቤ 👤 ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ 👤 ዘማሪ ዲያቆን ብርሃኑ በቀለ 👤 ዘማሪት አዜብ ከበደ 👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ 👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 👤 ዘማሪት ሰላማዊት በርታ 🔗የሁሉንም ዘማሪዎች ለማግኘት🎚✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
330Loading...
15
በትክክለኛው ፊደል የተጻፈው የቱ ነው?
920Loading...
16
Media files
640Loading...
17
✞ ጥያቄ ✞ ➠ ከአስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርቱ ቀረጥ ሰብሳቢ የነበረው ማን ነው?
740Loading...
18
👇👇👇👇👇👇
900Loading...
19
🔔✝ ከመምህራን የማንን ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇 ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ምሕረተአብ አሰፋ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ዘበነ ለማ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ሄኖክ ኃይሌ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ዮርዳኖስ አበበ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 አባ ገብረ ኪዳን ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ያረጋል አበጋዝ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር እዮብ ይመኑ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔መምህር ገብረ እግዚአብሔር ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔መምህር አባ ገብረ ኪዳን ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ 🔗የሁሉንም መምህራን ትምህርት ለማግኘት🔔 🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
780Loading...
20
✝❤️ የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ 👇 👤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 👤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 👤 ሊቀ መዘምራን . ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ 👤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 👤 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ 👤 ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ 👤 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን 👤 ዘማሪ| በሱፍቃድ አንድአርጋቸው 👤 ዘማሪት ሲስተር ሊዲያ ታደሰ 👤 ዘማሪ ዳግማዊ ደርቤ 👤 ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ 👤 ዘማሪ ዲያቆን ብርሃኑ በቀለ 👤 ዘማሪት አዜብ ከበደ 👤 ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ 👤 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 👤 ዘማሪት ሰላማዊት በርታ 🔗የሁሉንም ዘማሪዎች ለማግኘት🎚✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
840Loading...
21
ለገዳማውያን መነኮሳት አባቶች የተዘጋጀው የሥልጠናና የምክክር መርሐ ግብር ተጀመረ። "መነኮሳት መላእክት ምድራውያን ወሰብእ ሰማያውያን ማለትም መነኮሳት ምድራውያን መላእክት ሰማያውያን ሰዎች ናቸው" በሚል መሪ ቃል ከሰኔ 4- 6 ቀን 2016 ዓ.ም የተዘጋጀው የሥልጠናና የምክክር መርሐ ግብር ተጀመረ። በመክፈቻ መርሐ ግብሩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እንዲሁም ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕርዳርና ሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ሌሎች ብፁዓዠን አባቶች ተገኝተዋል። ቅዱስነታቸው "ቤተክርስቲያን ያላት ሀብት ሰፊ ፤ ታሪካችንም ረጅም ነው ፤ እንደ እኛ ሰፊ የመንፈሳዊ ተግባር የለም እንደዚህም ሆኖ መከራ አለቀቀንም ፤ ሰይጣን በእኛ ላይ ትልቅ ሥራ እየሰራ ነው ስለዚህ በጾም በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት ፣ መጮህ መለመን አለብን ፣ እናንተም ወደዚህ ቤታችሁ ለመመካከር በመምጣታችሁ እናመሰግናለን ፣ ምስጢሩን ይግለጥልን ፣ ገዳሞቻችንን ያቆይልን ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን ፤ እንድትተጉና እንድትበረቱ እንድትጸልዩልንም አደራ እላለሁ" በማለት ቡራኬ ሰጥተዋል። ብፁዕ አቡነ አብርሃም ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር "ይሕ መርሃግብር የተዘጋጀው ገዳማውያን እናቶችና አባቶቻችን ከቅዱስነቶ ቡራኬና ቃለምዕዳን ተቀብለው ወደ ሥራ ለመግባት ነው ፤ ዛሬ በዚህ የተገኛችሁ ገዳማውያን በሙሉ ከልዩ ልዩ ጾር ነፃ ሆናችሁ እንደ አባቶቻችን ቤተክርስቲያንን አስጠብቃችሁ እየኖራችሁ ቢሆንም የደከመ ካለ እንዲነቃ ፣ የሰነፈ ካለ እንዲበረታ ፣ የተበላሸም ካለ እንዲስተካከል ለመነጋገር ቅድስት ቤተክርስቲያን ጥሪ አስተላልፋላችኋለች ፤ የአባቶችን ፈለግ ተከትለን የነገውን ተረካቢ እንዴት እንፍጠር? ዘመኑንስ እንዴት እየዋጀን እንዝለቀው በማለት ተነጋግረን መፍትሔ እንፈልጋለን ፤ የተዘጋጀውን ምክክርና ሥልጠና በአግባቡ ወስደን የምንጠቀምበት ይሑን" በማለት ተናግረዋል። የገዳማት አንድነት መምሪያ ኃላፊ መጋቤ ካህናት ቆሞስ አባ ሀብተጊዮርጊስ ባደረጉት ንግግር "የገዳማት ማስተባበሪያው በቀጣይ ይህን መሰል የምክክር ጉባኤ ከማዘጋጀት ባለፈ እግዚአብሔር ቢፈቅድ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አመራር ሰጪነት የገዳማትን የኢኮኖሚ አቅም በየደረጃው እያጎለበቱ በኢትዮጵያ አንድነት ገዳማት ስም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን፣ በጎ አድራጊ ግለሰቦችንና ባለ ሀብቶችን በአጠቃላይ በውስጥም በውጭም ያሉ ምዕመናንን በማስተባበር በማዕከል ደረጃ አንድ የገቢ ማስገኛ ሁለገብ ሕንጻ ለመግዛት (ለማሳነጽ) የገዳማት አስተዳደር  መምሪያ በዕቅድ አካቶ ሰፊ ጥናት አድርጓል። የጥናቱን መሠረተ ሐሳብ መነሻ በማድረግ ፕሮፌሽናል በሆኑ ባለሙያዎች የፕሮጀክት ፕሮፖዛሉን ለማዘጋጀት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፤ ስለሆነም ይህን በጎ ሐሳብ ወደ ተግባር በመቀየር ገዳማውያን መነኮሳት በመንገድ ዳር ቆመው የሚለምኑበትን አስከፊ ችግር በዘላቂነት ሊቀርፍ የሚያስችል ሥራ እንድንሠራ አባቶች በጸሎታችሁ ፣ በእውቀታችሁና በሐሳባችሁ እንድታግዙን በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን" በማለት ምክክር መርሐ ግብሩን አስጀምረዋል። ✅ተ.ሚ.ማ
8881Loading...
22
➦💦ጸበል ተጠምቄ ለመዳን አስቀድሜ ምን ላድርግ⁉️ ➦🚶‍♂ከጸበል በፊት ንስሐ መግባት ለምን አስፈለገ⁉️ ➦🤶የንስሐ አባት ለምን የነፍስ አባት በመባል ይጠራል⁉️ ➦🤲አብዝቶ መፀለይ ለምን ⁉️ ➦💦ጸበልና የጸበል ቦታ ፈተናዎች👿⁉️ ➦🧞‍♀የመንፈሱ ሴራ በጸበልተኞች ላይ ምን ይመስላል⁉️ 🔗እርሶም በዚህ ዙሪያ እውቀቱ እንዲኖርዎ ከፈለጉ ይህንን መስፈንጠርያ ይንኩ ትምህርቱን ይከታተሉ               👇🏽👇🏽👇🏽 https://t.me/addlist/AQPOMxHXz_42NDE0
1000Loading...
23
ምን አይነት መዝሙሮችን ይፈልጋሉ?👇👇👇
630Loading...
Photo unavailableShow in Telegram
አባ ፍራንሲስ “የሚያስከፋ እስካልሆነ ድረስ ስለ ፈጣሪ መቀለድ ችግር የለውም” አሉ አባ ፍራንሲስ ለኮሜዲያኑ "በፈጣሪ ላይ እንኳን መሳቅ ትችላላችሁ፣ ይህ መናፍቅነት አይደለም” ብለዋል። የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ “የሚያስከፋ እስካልሆነ ድረስ ስለ ፈጣሪ መቀለድ ችግር የለውም” በማለት ለተሰበሰቡት ታዋቂ ኮሜዲያኖች እንዲሁም አርቲስቶች ነበር የተናገሩት። አባ ፍራንሲስ ከመላው ዓለም ከተውጣጡ ከ100 በላይ ኮሜዲያን፣ የፊልም ተዋናዮች እና ጸሃፊዎችን በትናንትናው እለት በቫቲካን አግኝተው አነጋግረዋል። ከአባ ፍራንሲስ ጋር ከተገናኙ ታዋቂ ሰዎች መካከልም የአሜሪካ ታዋቂው የሾው ቢዝ አቅራቢ ውሁፒ ግልድበርግ፣ ጂሚ ፋሎን፣ ካነን ኦበሪየን፣ ክሪስ ሮክ እና ስቴፈን ኮልበርት እንደሚገኙበት ሮይተርስ ዘግቧል። በዚሁ ወቅት በጣሊያንኛ ንግግር ያደረጉት አባ ፍራንሲስ "በፈጣሪ ላይም መሳቅ እችላለን” ያሉ ሲሆን፤ ይህ ስድብ አይደለም እኛ ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር እንደምንጫወት እና እንደቀልድ ሁሉ በፈጣሪ ላይም እንችላለን” ሲሉ ተደምጠዋል። “የሚያስከፋ እስካልሆነ ድረስ ስለ ፈጣሪ መቀለድ ችግር የለውም” ያሉት አባ ፍራንሲስ፣ “እያልኩ ያለሁት ነገር መናፍቅነት አይደለም፤ በአንድ ሰው ከንፈር ላይ እንዴት ፈገግታን መፍጠር እንዳለብህ ካወክ እና አንድን ሰው ፈገግ ካሰኝህ፤ እግዚአብሄርም እንዲስቅ ታደርጋለህ” ብለዋል። የሮማው ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ 30 ደቂቃ ከፈጀው እና ከመስመር ወጣ ያለ ነው የተባለውን ንግግራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ከኮሜዲያኖቹ ጋር እየተጨባበጡ ተቀላልቀደዋል። የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ በተደጋጋሚ በሚሰጧቸው ለየት ባሉ እና አነጋጋሪ አስተያየታቸው ይታወቃሉ። አባ ፍራንሲስ ከቀናት በፊት ቄሶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት በተቻለ መጠን አጭር እንዲያደርጉ ማሳሰባቸው ይታወሳል። አባ ፍራንሲስ አክለውም ለማስቀደስ እና ሌሎች በረከቶችን ለማግኘት ብለው ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጡ የዕምነቱ ተከታዮች በቄሶች አገልግሎት መርዘም ምክንያት እንቅልፍ እየጣላቸው ነው ብለዋል። ቄሶች ስለ ጌታ ከመጽሃፍ ቅዱስ ላይ ለምዕመናን የሚያስተምሩበት ጊዜ ከስምንት ደቂቃ መብለጥ የለበትም ሲሉ ሊቀ ጳጳሱ ተናግረዋል። ✅አል አይን የእግርጌ ማስታወሻ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መስመር ከሳተች ቆይታለች።ይልቅ አሁን ላይ ለተከታዮቻም ሆነ ውጪ ላለው ሰው በመጥፎ ዝንባሌዋ እና ወቅታዊ ልማዷ አስጊ እየሆነች ነው።
Show all...
🤔 2
01:44
Video unavailableShow in Telegram
አርባ ምንጭ ከተማ እንዲህ ባለ ድምቀት ብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በልጅነት ክብር ተቀብላ ተባርካለች። ሁሌም ሙቀቱ የማይለየው የደቡብ ህዝብ ዛሬም አባቶቹን በክብር ተቀብሏል።በተለይ አርባ ምንጭ ብዙ ያልተደረገለት ብዙ ሊሰራበት የሚገባ ሀገረ ስብከት ነው።
Show all...
27.85 MB
4👍 1🙏 1
ስርዓተ ጥምቀት ፈጽመው 123 ሰዎች ወደ ከኦርቶዶክሳዊ በረት ተጨምረዋል:: በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ክልል በሸካ ቤንች ሸኮ ምዕራብ ኦሞ ሀገረ ስብከት በቤንች ወረዳ ቤተ ክህነት በምትገኘው በቲሹ ደብረ ገነት ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን በትናንትናው ዕለት ሰኔ 6/2016 ዓ/ም 123 ነፍሳት ሀብተ ወልድ እና ስመ ክርስትናን አገኙ።
Show all...
10🙏 2👍 1😁 1
ስደተኛው ተመራቂ፤ “ብፁዓን እለ ይሰደዱ በእንተ ጽድቅ፥እስመ ሎሙ ይዕቲ መንግሥተ ሰማያት።ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።”ማቴ፡፭፥፲። ሊቀ ማዕምራን ፈንታሁን ሙጬ የቤተ ክርስቲያኒቱን መደበኛ ትምህርት ዜማውን አቋቋሙን እና ቅኔውን ከሕፃንነቱ ጀምሮ “በእንተ ስማ ለማርያም” እያለ ቁራሽ እንጀራ እየለመነ፥ ከመቃብር ቤት ደንጊያ ተንተርሶ እየተኛ እስከ ጥግ ድረስ ተምሮአል።የእናቱን ፍትፍት እየጎረሰ፥በአባቱ እጅ እየተዳበሰ አላደገም።ያደገው በደጀ ሰላም ፍርፋሪ ነው፥የቤተ ክርስቲያን ፍርፋሪ ደግሞ ስመ እግዚአብሔር የተጠራበት፥ቃለ እግዚአብሔር ያረፈበት፥በመስቀለ ክርስቶስ የተባረከ፥ምእመናን በሃይማኖት ያቀረቡት በመሆኑ መድኃኒት ነው። በዘመናዊም የከፍተኛ ፪ኛ ደረጃ ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት ካጠናቀቀ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መግባት ቢችልም ፈቃደ ነፍሱን በማስቀደም ወደ ቅድስት ሥላሴ ቴኦሎጂ ዩኒቨርስቲ በመግባት የመጀመሪያ ድግሪውን ይዟል።ይህ ለቀለም ቀንድነት የተፈጠረ ወንድማችን በዚሁ ይበቃኛል ሳይል ከውጭ ሀገር የኒቨርስቲዎች ጋር በመጸጻፍ በግል ጥረቱ የነፃ ትምህርት ዕድል በማግኘቱ ወደ አውሮፓ በመጓዝ ሁለተኛ ድግሪውን ሠርቶአል። ከሁሉም የሚደንቀው በዚያው እንዲቀር ብዙ ግፊቶች ቢኖሩበትም “የቤተ ክርስቲያን ውለታ አለብኝ፤”በሚል ቀና መንፈስ ወደሚወዳት ሀገሩና ወደሚመካባት ቤተ ክርስቲያኑ በመመለስ በተለያዩ ሃላፊነቶች እናት ቤተ ክርስቲያኑን አገልግሎአል። እንደሚታወቀው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት አልጋ በአልጋ ሳይሆን በቀኖት ላይ የመረማመድ ያህል ነው። የቀን ዕረፍት የሌሊት እንቅልፍ አይሰጥም።ቢሆንም የጽድቅ ጉዳይ ስለሆነ ሁሉንም በጸጋ ተቀብሎታል። እንደገናም ከቤተሰብ አስተዳደር ጋር ያ ሁሉ ሃላፊነት ቢኖርበትም አሜሪካን ሀገር ከሚገኝ ዩኒቨርስቲ ጋር በመጻጻፍ ዕድሉን በማግኘቱ ሦስተኛ ድግሪውን በኦን ላይን እየተማረ አጠናቅቆ ነበር። በመሆኑም ስደት በወጣ በሦስተኛ ወሩ ኢንዲያና ከሚገኝ Newburgh Theological Seminary ሰኔ ፭ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. የአቡየ ዕለት በዶክተሬት ድግሪ ተመርቋል።በሐዘን ውስጥ ደስታ ያለው እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን።እመ እግዚአብሔር ፀባዖት ድንግል ማርያምም የተመሰገነች ትሁን።በእውነቱ መጋቤ ሃይማኖት መምህር አንዱ ዓለም ዳግማዊ በዕለቱ በስፍራው በመገኘት ብቸኝነት እንዳይሰማው በማድረግህ ልትመሰገን ይገባሃል።ወንድም ማለት እንደዚህ በችግር ጊዜ በጎን የሚቆም ነው።ሌሎቻችንማ “ኩሉ ጻድቅ በጊዜ ርቱዕ፤” ሆነናል። ለምን ተሰደደ? እንደምታስታውሱት በጥር ፳፻፲፭ ታላቋ ቤተ ክርስቲያን ከከባድ ፈተና ውስጥ ገብታ ነበር። በሃላፊው መንግሥት የተመኩ፥የዘረኝነት ጎርፍ የጠረጋቸው ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት ከሃይማኖት አፈንግጠው፥ቀኖና ሐዋርያትን ጥሰው፥መንፈስ ቅዱስ ካሰመረው መስመር ወጥተው በምዕራብ ሸዋ ወሊሶ በሕገ ወጥነት ኤጲስ ቆጶሳትን “ሾምን፤”ብለው ነበር።በወቅቱ ካህናትና ምእመናን እስከ ሞት ድረስ ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።በዚህ ክፉ ሰዓት ጠቅላይ ሚንስትሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን መብት ማስከበር ሲገባቸው፥ሕገ ወጥነትን በመደገፍ በሚንስትሮች ጉባኤ ላይ ንግግር አድርገው ነበር። ንግግሩም “አርፋችሁ ተቀመጡ፤”አይነት ነበር። ወዲያውም የቤተ ክርስቲያን ደጆች በታጣቂዎች እየተሰበሩ፥ካህናትና ምእመናንም እየተገደሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሕገ ወጦቹ ተላልፋ ተሰጠች።አያሌ ምእመናንም ታሰሩ፥ተገረፉ፥ከመንግሥት ሥራቸውም ተፈናቀሉ። በዚያ ቀውጢ ሰዓት ሊቀ ማእምራን ፈንታሁን ሞት ጥላውን ባጠላበት ከተማ እንደሚኖር እያወቀ ፥ራሱ በሥራ አስኪያጅነት በሚያስተዳድረው የቤተ ክርስቲያኒቱ ቴሌቪዢን ቀርቦ፥ጠቅላይ ሚንስትሩ በቤተ ከርስቲያኒቱ ላይ በድፍረት ለተናገሩት ነገር ሁሉ ቃል በቃል መልስ ሰጣቸው።በክፉ ቀን ለቤተ ክርስቲያኑ ጠበቃ ሆኖ በአደባባይ በትሁት ቃል እና በትሁት ሰብእና ተሟገታቸው። ይህንንም ያደረገው ሃይማኖታዊ ግዴታወን ለመወጣት ብቻ እንጂ ማንንም ለማስቀየም ወይም ማንም እንዲያጨበጭብለት አልነበረም።ነገር ግን ከዚያች ቅጽበት ጀምሮ በደኅንነት ክትትል ስር ወደቀ። በመጨረሻም ለቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ ወደ ሰሜን አሜሪካ ለመሄድ አይሮፕላን ውስጥ ከገባ በኋላ አንቀው አስወረዱት።እንዳይሞት እንዳይሽር አድርገው የእግዚአብሔርን ካህን ቀጠቀጡት። በብረት ካቴና አስረውትም ከጨለማ ቤት ጣሉት። እነርሱ አጥንትን እንኳ ሊያደቅ በሚችል በትር እየደበደቡት ውዳሴ ማርያም ይደግም ነበር።”መከራውን ያስቻለችኝ እርሷ ናት፤”ይላል። ከዚህ ሁሉ ሥቅየት በኋላ የጀመረውን የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ ከጫፍ ለማድረስ፥እስከ ቁስሉ ወደ ሰሜን አሜሪካ መጣ።ለመቆም ለመቀመጥ፥ ለመተኛት ለመነሣት መከራ ሆነ።ሁሉ ነገር በሰው ድጋፍ ነበረ።አሁንም ወንድማችን ዶክተር አንዱ ዓለም ከፍተኛ ወጪ በማውጣት በሕክምና እንዲደገፍ በማድረጉ፥ሐዘኑን እስኪረሳ ድረስ በመንከባከቡ፥ለቤተ ክርስቲያኒቱ ቴሌቪዥን መምሪያ የሚያስፈልጉትን ውድ ውድ ቁሳቁሶችን በሟሟላቱና ሀገር ቤት ድረስ አሜሪካዊ ባለሞያ ይዞ በመሄድ ሠራተኞቹ እንዲሰለጥኑ በማድረጉ ሊመሰገን ይገባዋል። ሊቀ ማዕምራን አሁንም “ከሚገባህ በላይ መሥዋዕትነት ከፍለሃል፥ይበቃህል፥በዚሁ ቅር፤”ለሚለው የወዳጆች ምክር ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ሀገር ቤት ተመለሰ።ለአንድ ዓመት ያህልም ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ራእይ ለማሳካት ታገለ።ነገር ግን የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጠላቶች አላንቀሳቅስ አሉት። አንዳንድ ወዳጆችም “እባክህ ለቤተ ክርስቲያንም ቢሆን ከምትሞትባት ብትኖርላት ይሻላል፥ሰላማዊ ዘመን ሲመጣ ታገለግላታለህ።ቃሉም የሚለው ‘ተኀባእ ኅዳጠ ምዕረ እስከ የኀልፍ መዓቱ ለእግዚአብሔር።የእግዚአብሔር ቁጣ እስኪያልፍ ድረስ ጥቂት ተሸሸግ ነው።’”ሲሉት ሳይወድ በግዱ ሀገሩን ጥሎ ተሰደደ።ቤተ ክርስቲያን ግን በመላው ዓለም ስላለች መቼም ቢሆን አያጣትም፥ያገለግላታል።
Show all...
7👍 4👏 1🤔 1
በዋግሕምራ ዞን አበርገሌ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ 1.53 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነበት ማኅበራዊ ድጋፍ ተደረገ፡፡  ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) ማኅበረ ቅዱሳን ከደጋፊ አካላት ጋር በመተባበር በዋግሕምራ ዞን አበርገሌ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 1.53 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነበት ማኅበራዊ ድጋፍ አድርጓል፡፡  የማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ በሀገራችን እያጋጠሙ ያሉ ሰፊ ማኅበራዊ ቀውሶች በምእመንመናን፣ በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ላይ እያስከተሉት ያለውን ሁለንተናዊ ችግር ለማቃለል ሰፊ የማኅበራዊ ድጋፍ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና በመተግበር በተገቢ ደረጃ ማኅበራዊና ሰብአዊ ሚናውን እየተወጣ እንዳለ ይታወቃል። ማኅበሩ እነዚህን ችግሮች በስፋት በማጥናት ላለፉት 6 ዓመታት በሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያው በኩል በአርሲ፣ በሐረር ፣በባሌ፣ በወሊሶ፣ በሻሸመኔ፣ በዶዶላ፣ በአጋርፋ፣ በጅጅጋ፣ በሲዳማ፣ በመተከል፣ በቤንሻጉል ጉምዝ፣ በፓዊ፣ በቡለን፣ ፣በሽሬ፣ በአክሱም፣ በያቤሎ፣ በጎንደር አዘዞ፣ በአዲግራት፣ በማይ ጨው፣ በሽረ እንደ ሥላሴ ፣በመቐለ፣ በደብረ ብርሃን፣ በደሴ፣ በወልዲያ፣ በላሊበላ ፣በሐይቅ እስጢፋኖስ፣ በወሎ ገራዶ፣ በደባርቅ ፣በጃን አሞራና በሌሎችም የሀገራችን ክፍል ለሚገኙ ተጎጅዎች ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ድጋፍ አድራጊ ምእመናንና ተቋማትን እያስተባበረ የአልባሳት፣ የምግብ እና መሠል አስቸኳይ ድጋፎችን በስፋት ሲያደርግ ቆይቷል። አሁንም አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህ መሠረት በዋግሕምራ ዞን አበርገሌ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖችና በአካባቢው ለሚገኙ ለተመረጡ 3 ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች 1.53 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነበት 202 ኩንታል የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ አድርጓል።  ከዚህ ድጋፍ ውስጥ 1,000, 000 (አንድ ሚሊዮን ብር) ወጭው የተሸፈነው ግሎባል አሊያንስ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በሀገረ አሜሪካ ሜኔሶታ ከሚገኘው የርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ምእመናና አገልጋዮች ጋር በመተባበር ያበረከቱት ነው። ቀሪው ወጭ የተሸፈነው በሀገረ አሜሪካ ከሚገኘው የሲያትል ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው። ሰኔ 05-06 ቀን 2016 ዓ.ም በቦታዎቹ በመገኘት በተደረገው በዚህ የእጅ በእጅ ድጋፍ ርክክብ ወቅትም፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከልና የሰቆጣ ማእከል ልዑካን፣ የግሎባል አሊያንስ ድርጅት ተወካይ እንዲሁም የወረዳው የመንግስት አካላት ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በወረዳው ከ67 ሺህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎች አሁንም ድረስ አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ የሚሹ መሆናቸውን በድጋፍ ሥርጭት ወቅት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ለማኅበረሰቡ ከተደረገው ድጋፍ በተጨማሪ የአማናዊው ዕውቀትና ጥበብ ምንጭ ለሆኑ በአካባቢው ለሚገኙ 3 ገዳማትና ጉባኤ ቤቶች ተመሳሳይ ድጋፎች ተደርገዋል። ማኅበረ ቅዱሳን በቅርብ ጊዜያት ብቻ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅና ጃን አሞራ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ በሰቆጣና አካባቢው ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በደቡብ ኦሞ በናጸማይ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ በሃይማኖት ተኮር ጥቃት ለተጎዱ የቅበት ኦርቶዶክሳውያን፣ በደብረ ብርሃን ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በትግራይ መቐለ ኩሓ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በትግራይ አጽቢ ወንበርታ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ የደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳምን ጨምረ በማኅበራዊ ቀውስ ለተጎዱ 6 ጥንታዊያን ገዳማትና ጉባኤ ቤቶች ከፍተኛ ድጋፎችን አድርሷል። ማኅበረ ቅዱሳን ይህ ሰብአዊ ድጋፍ ለተጎጅ ወገኖች እንዲደርስ የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ አካላትን እያመሰገ፣ በቀጣይ ተመሳሳይ ድጋፎችን ለማድረስ በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን፣ ማኅበራት፣ ልዩ ልዩ ተቋማትና በጎ አድራጊ ድርጅቶች የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲል ጥሪውን ያቀርባል። ድጋፍ ለማድረግ፡- በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡- 1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901 2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458 3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648 4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101 5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 6. በጎ ፈንድ ሚ https://www.gofundme.com/f/uerc8... 7. በወገን ፈንድ ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። ✅የማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ
Show all...
2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ምን አይነት መዝሙሮችን ይፈልጋሉ?👇👇👇
Show all...
ቆየት ያሉ ዝማሬዎች
አዳዲስ ዝማሬዎች
የንስሐ መዝሙሮች
የቸብቸቦ መዝሙሮች
ሁሉንም በአንድ ላይ
On this day, we celebrate the Ascension of our Lord, God and Savior Jesus Christ. This Feast is celebrated each year on the fortieth day after the Great and Holy Feast of Pascha (Easter). Since the date of Pascha changes each year, the date of the Feast of the Ascension changes. The Feast is always celebrated on a Thursday. The Feast itself commemorates when, on the fortieth day after His Resurrection, Jesus led His disciples to the Mount of Olives, and after blessing them and asking them to wait for the fulfillment of the promise of the Holy Spirit, He ascended into heaven
Show all...
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ  ዕርገቱ በምድር ላይ የሚሠራውን የትሕትና ሥራ የመፈጸሙ ምልክት ነው፡፡ ዕርገቱም ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት “ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ/ በዕልልታና በመለከት ድምፅ ላረገ ለአምላካችን፣ ለጌታችንና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና አቅርቡ (መዝ ፵፮፥፭፡፮) እንዳለው በታላቅ ክብር እልልታና ምስጋና ነው፡፡ ጌታችን የድል ዕርገትን ያረገው ወደ ባሕርይ አባቱ ቀኝ ነው፡፡ በእርሱ ዕርገት የጸጋ መንፈስ ቅዱስና የዳግም ምጽአት ተስፋዎች ተሰጥተውናል፡፡ የእርሱ ዕርገትም ለነፍሣችን ዕርገት /ለዕርገተ መንግሥተ ሰማያት/ አርአያ ሆኖናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ክርስቲያኖች በጻፈው ክታቡ ይህንን ሲያስረዳ፦ « ንሕነ ሕያዋን እለ ንተርፍ አመ ምጽአተ እግዚእነ ንትመሠጥ በደመና ምስሌሆሙ ኅቡረ ከመ ንትቀበሎ ለእግዚእነ ውስተ አየር » « እኛ ሕያዋን ሆንን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉትን አንቀድማቸውም ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክት አለቃ ድምጽ በእግዚአብሔር መለከት ከሰማይ ይወርዳልና በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ። ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ጌታን በአየር ለመቀበል ከእርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን። እንዲሁም ሁል ጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን። ስለዚህ እርስ በእርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ» በማለት የክርስቶስ ዕርገት ለምዕመናን ዕርገት መሠረት መሆኑን ገልጾልናል (፩ተሰ. ፬፡፲፯)። ወደ ልጁ ጢሞቴዎስ በላከው መልእክቱም « በሥጋ የተገለጠ፣  መንፈስ የጸደቀ፣  ለመላእክት የታየ፣  በአሕዛብ የተሰበከ፣  በዓለም የታመነ፣ በክብር ያረገ» በማለት ልደትን እንደ ዘር ዕርገትን እንደ መከር አድርጎ ገልጾልናል። (1ጢሞ.3፥16) ወርሐ ዘር የመከር ጊዜ ነው፡፡ ገበሬ በጎተራ ያለውን እህል እያወጣ ሲዘራ ከላይ ዝናም ከታች ጭቃውን ታግሶ ነው፡፡ በመከር ጊዜ ያን የዘራውን ምርት በጥፍ ሲያገኝ ደስ ይለዋል መከራውን ይረሳዋል፡፡ ምነው በጨመርኩበት ይላል የክርሰቶስም ልደቱ ስለኛ መከራን ለመቀበል ነውና፥ በሥጋ የተገለጠ ብሎ ትሕትናውን አሳየ፡፡ ዕርገቱን ግን በክብር ያረገ ብሎታል፡፡ ምክንያቱም የሰውነትን ሥራ ፈጽሟልና ድል ነስቶአልና ይህን በሥጋ ዕርገቱን ስናስብ ለምን ዕለቱን ተነሥቶ እለቱን አላረገም ለምንስ እስከ አርባ ቀን በምድር ላይ ቆየ ቢሉ ፡ እስከ አርባ ቀን በምድር ላይ የቆየው ትንሣኤው በግልጽ እንዲረዳ ደቀ መዛሙርቱንም መጽሐፈ ኪዳንን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያስተምር ዘንድ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በወንጌሉ ‹‹አልቦ ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘእንበለ ዘወረደ እምሰማይ ወልደ ዕጓለመሕያው፤ ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው፡፡ » ብሏል። (ዮሐ.3፥13) ጌታችን ሞትን በሥልጣኑ ከሻረ፣ ሙስና መቃብርን ካጠፋ፣ የትንሣኤያችን በኩር ሆኖ በዕለት ሰንበት ከሞት ከተነሣ በኋላ በምድር ላይ መቆየቱ የማያምኑ ፈሪሳውያንም ‹‹ትንሣኤው ምትሐት ነው›› እንዳይሉ እየታየ እያስተማረ እስከ 40 ቀን ድረስ በምድር ቆይቷል፡፡ በነዚህም የ40 ቀናት 3 ጊዜያትጉባኤ ዘርግቶ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ ቅዱስ ወንጌል ይነግረናል፡፡ " ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥላቸው ይህ ሦስተኛ ጊዜ ነበረ " እንዲል ወንጌላዊው ዮሐንስ (ዮሐ.21፥14 ) እነዚህንም 3 ጉባኤያት የተባሉትን ሊቃውንት አባቶቻችን፡- 1ኛ በዕለተ ዕሁድ በዕለተ ትንሣኤ 2ኛ በአግብኦተ ግብር /በዳግም ትንሣኤ/ 3ኛ በጥብርያዶስ ባሕር የተገለጡ ጉባኤያት መሆናቸውን አመሳጥረው ያስተምሩናል። ጌታችን በ40 ቀናት ውስጥም መጽሐፈ ኪዳንን ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሯል፡፡ ቅዱስ ያሬድም ዝማሬ በተባለው መጽሐፍ የጌታችንን ማዳን ከፅንሰቱ ጀምሮ እስከ ዕርገቱ ብሎም እስከ ዳግም ምጽአቱ ከብሉያትና ከሐዲሳት እያጣቀሰ አምልቶና አስፍቶ በተናገረበት የምስጋና ክፍል “ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና፤ ለድንግል ዘፈትሐ ማኅፀና፤ ለደቂቀ እስራኤል ዘአውረደ መና፤ ውእቱኬ ዘአድኃና ለሶስና እም እደ ረበናት፤ ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና / በደመና ወደ ሰማይ ዐረገ፤ የድንግልን ማኅፀን የፈታ፣ ለእስራኤል ልጆች መናን ያወረደ፣ ሶስናን ከረበናት እጅ ያዳነ፣ በደመና ወደ ሰማይ ዐረገ/” ብሏል፡፡ ‘ዐረገ’ መባሉ የሌለበት ቦታ ኑሮ ካለበት ቦታ ወደ ሌለበት ቦታ ሔደ ማለት አይደለም፡፡ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ወደ ባሕርይ አባቱ መመለሱን፣ የማዳን ሥራውን መፈጸሙን፣ በሥጋ በክብር ማረጉን ለመግለጽ ነው፡፡ አንድም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደመና ዐረገ ሲል በክብር ማረጉን፣ ልዕልናውን መግለጹ ነው፡፡ ደመና ክብሩ ልዕልናው ነውና። በደመና ዐረገ መባሉ በእመቤታችን ጀርባ መታዘሉንም ለመግለጥ ነው። ደመና ተብላ የተገለጠችው እመቤታችን ድንግል ማርያም ናትና። ከማርያም በነሣው ሥጋ ዐረገ ማለት ነው። ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ “እነሆ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብጽ ይመጣል” (ኢሳ.፲፱፥፩) ብሎ አስቀድሞ በትንቢቱ የተናገረላት ደመና እመቤታችን ናት። ሊቁ ቅዱስ ያሬድም “ደመናሰ ዘይቤ ይእቲኬ ማርያም እንተ ጾረቶ ዲበ ዘባና፤ ደመናስ የሚላት አምላክን በጀርባዋ የተሸከመችው ማርያም ናት” በማለት ያስረዳል። ስለዚህ በደመና ዓምድ ዐረገ ሲል ከድንግል ማርያም በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማይ ዐረገ ማለት ነው። ቤተ ክርስቲያናችንም በሥርዓተ ቅዳሴዋ “ላዕለ ይኩን ኅሊናክሙ በሰማይ የሀሉ ልብክሙ አእምሩ ኀበ ትቀውሙ ስምዑ ቃለ ጽድቅ ወአስምዑ ዜና ሰናይ” እያለች ዕርገቱን ታሳስበናለች። ሃይማኖተ አበው "ዐርገ እግዚአብሔር በቃለ ቀርነ መዊእ ወኢይቤ አዕረግዎ አላ ለሊሁ ዐርገ ወኢፈቀደ መራሔ ፍኖተ፥ እስመ ከመዝ ኢክህለ ኤልያስ ይዕርግ በዝንቱ መካን ነኪር አላ ኀይላት አዕረግዎ ኀበ ተአዘዙ ወቃለ እግዚአብሔርሰ ዋሕድ ለሊሁ ዐርገ በሥልጣኑ እስመ እግዚአ ኀይላት ውእቱ። ወበእንተ ዝ ይቤ ሉቃስ ወንጌላዊ በመጽሐፈ ግብር እስመ አርዳኢሁ ያንቀዐድዉ ኀቤሁ እንዘ የዐርግ ሰማየ ወኢይቤ አዕረግዎ ወኢሂ ጾርዎ እስመ መካን ኀበ ዐርገ ዘዚኣሁ ውእቱ"  ይላል። ሃይ. አበ. ዘዮ. አፈ. ፷፯፡፲፪-፲፬ ሰላም ለዕርገትከ ዘኢይትረከብ መጠኑ ወለንብረትከ ሰላም ለአቡከ ውስተ የማኑ ኢየሱስ ክርስቶስ እለ ኪያከ ተአመኑ ቅዱሳነ ዘእምኀቤከ ወንጹሐነ ይኩኑ ጰራቅሊጦስሃ መንፈስከ ፈኑ። ሰላም ለዕርገትከ በዘባነ መብረቅ ወነጎድጓድ፤ ከመ ትፈኑ መንፈሰከ በአምሳለ ነፋስ ወነድ፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በመንግሥትከ ዋሕድ፤ ይቤሉከ ለለ ዕለቱ ሰማያውያን ነገድ፤ መንግሥቱ ዘለዓለም ወምኩናኑኒ ለትውልደ ትውልድ፡፡ ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ። በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ። (መዝሙር 67፥ 33) መልካም በዓል ‼ 𝐀𝐬𝐜𝐞𝐧𝐬𝐢𝐨𝐧 𝐨𝐟 𝐨𝐮𝐫 𝐋𝐨𝐫𝐝, 𝐆𝐨𝐝 𝐚𝐧𝐝 𝐒𝐚𝐯𝐢𝐨𝐫 𝐉𝐞𝐬𝐮𝐬 𝐂𝐡𝐫𝐢𝐬𝐭 O Christ our God, You ascended in Glory and gladdened Your disciples by the promise of the Holy Spirit. Your blessing assured them that You are the Son of God, the Redeemer of the world. (Apolytikion for Holy Ascension)
Show all...
2🕊 2👍 1🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
☁️ ☁️ ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ☁️ ☁️ ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ መዝ.67(68) ÷ 33 ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና፤ ለድንግል ዘፈትሐ ማኅፀና፤ ለደቂቀ እስራኤል ዘአውረደ መና፤ ውእቱኬ ዘአድኃና ለሶስና እም እደ ረበናት፤ ዐርገ ሰማያተ በዐምደ ደመና በደመና ወደ ሰማይ ዐረገ፤ የድንግልን ማኅፀን የፈታ፣ ለእስራኤል ልጆች መናን ያወረደ፣ ሶስናን ከረበናት እጅ ያዳነ፣ በደመና ወደ ሰማይ ዐረገ (ማኅሌታይ ያሬድ ኢትዮጵያዊ ) እንኳን ለ1982ኛው የጌታችን ብርሃነ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ ‼ 𝐀𝐬𝐜𝐞𝐧𝐬𝐢𝐨𝐧 𝐨𝐟 𝐨𝐮𝐫 𝐋𝐨𝐫𝐝, 𝐆𝐨𝐝 𝐚𝐧𝐝 𝐒𝐚𝐯𝐢𝐨𝐫 𝐉𝐞𝐬𝐮𝐬 𝐂𝐡𝐫𝐢𝐬𝐭 ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ዕርገቱ ለክርስቶስ እምድኅረ ተንሥአ እሙታን በዓርብአ ዕለት በይባቤ ወበቃለ ቀርን አማን መንክር ስብሐተ ዕርገቱ። ዛሬ በኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ደስታ ሆነ። ከሙታን ከተነሳ በኋላ በአርባ ቀን በእልልታ በመለከት ድምጽ ዐረገ። በእውነት ድንቅ ነው የዕርገቱ ምስጋና። ዮምሰ ዐባይ ትፍሥሕት እስመ ተንሥአ ወዐርገ ውስተ ሰማያት፤ ወነበረ በየማነ አቡሁ፤ ነሢኦ ሥጋ እንተ እምኀቤነ ተለዐለ፤ እምኀበ አቡሁ ተሰብሐ። ( ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ ) ዕርገት ከጌታችና ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡ “ዕርገት” የሚለው ቃል “ዐርገ” ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ከታች ወደ ላይ መውጣት፣ ክፍ ከፍ ማለት፣ ማረግ ማለት ነው፡፡ ዕርገት (Ascension) ሲባልም ማረግን፣ ከፍ ከፍ ማለትን፣ ወደ ላይ መውጣትን ያመለክታል፡፡ በዓለ ዕርገትም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም የነበረውን የማዳኑን ሥራ ጨርሶ ወደ ላይ መውጣቱና በቀደመ ክብሩ በአብ ቀኝ መቀመጡ የሚከበርበት በዓል ነው፡፡ ለዚህም መሰረት እንዲሆን አርዮስን ለማውገዝ በኒቅያ የተሰበሰቡት ቅዱሳን አበው “ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ…/ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ…” ብለው ዕርገቱን በቅዱሳት መጻሕፍት ዋቢነት አስረግጠው ደንግገዋል፡፡ በወንጌልም "ወእንዘ ይባርኮሙ ተረኀቆሙ ወዐርገ ሰማየ" እየባረካቸው ራቃቸው፤ ወደ ሰማይም ወጣ። በማለት ተጽፏል (ሉቃ 24÷51)። ጥንተ ዕርገቱ በወርሐ ግንቦት በቀን ስምንት በዕለት ኅሙስ ሲሆን፤ ዘመኑ በ34 ዓ.ም፣ ወንጌላዊው/ዘመኑ ደግሞ በዘመነ ማርቆስ ነው፡፡ የዕርገት በዓል እስከ 4ኛው ክፍለ ዘመን እንደ ዛሬው ኅሙስን ሳይጠብቅ በጥንተ ዕርገቱ ግንቦት ስምንት ቀን ብቻ ይከበር ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህ ግን ትንሣኤ በዋለ በ40ው ቀን ብቻ እንዲከበር የቅዱስ ዲሜጥሮስ ባሕረ ሐሳብ ቀመርን መሠረት በማድረግ በቀኖና ቤተክርስቲያን ተወስኖ በሥራ ላይ ውሎ ይገኛል፡፡ ዕርገቱ የትሕትና ሥራው የመፈጸሙ ምልክት ነው። አምላካችን ምሉዕ በኩለሄ (ሁሉን የሞላ እና በሁሉም ቦታ የሚኖር) ነው። ስለዚህ ጌታችን በባሕርይው መውጣት መውረድ የለበትም። ‘ወረደ፣ ተወለደ’ ሲባል ፍጹም ሰው መሆኑን የትህትና ሥራ መፈጸሙን ከመናገር ውጪ ከዙፋኑ ተለየ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ዐረገ ወጣ ሲባልም ከሰማያዊው ዙፋኑ ተለይቶ ነበር ማለት አይደለም። በምድር ላይ ሊሰራ ያለውን ሁሉ መፈጸሙን ያመለክታል እንጂ። እንዲሁም ጌታችን በዕርገቱ ምክንያት ከቤተክርስቲያን የተለየበት ጊዜ የለም። ነገር ግን ዕርገቱ በሥጋው የተደረገውን ዕርገቱን ያመለክታል። ይህም ዕርገት ቅዱስ ሥጋው በምድር የስበት ቁጥጥር (Gravitational force) የማይዘው ለመሆኑ አስረጅ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ አምላካዊ ስልጣኑን ያሳያል።
Show all...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
5500
5515
7515
2016