cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ድምፀ ተዋሕዶ

ይህ መንፈሳዊ ቻናል መቀመጫውን እንግሊዝ ለንደን ያደረገ ማንኛውንም ታማኝ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችን እና መንፈሳዊ ክንውኖችን ለምእመኑ በፍጥነት፤ በጥራት ያቀብላል። የእግዚአብሔር ጸጋ እና በረከት በሁላችን ላይ ይደር። ድምፀ ተዋሕዶ ለንደን ለታማኝ መረጃዎ

Show more
Advertising posts
10 708
Subscribers
-1624 hours
+4467 days
+1 58530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
🤔 3👍 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
እውነትም ይሁን ሐሰት ከቤተ ክርስቲያኒቱ የተባለ ነገር የለም።እንዳይሆን እሚያግደው ነገር ባይኖርም፤እንዳይሆን ግን ጸልዩ።
Show all...
🙏 2 1
ጌታችን አዲሱን የዕርገቱን ዜና ለማርያም መግደላዊት ባበሠራት ጊዜ በከፍተኛ የደስታ ስሜት ስለተሞላች ፈጥና ዜናውን ለደቀ መዛሙርቱ እንድትነግር ሲል “አትንኪኝ አላት፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።”  ጌታችን ከዕርገቱ በፊት በቀለዮጳ ቤት ተገኝቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ማዕድን ተካፍሎአል፤ ለቶማስም የተወጋውን ጎኑን አሳይቶታል።   በምን ምክንያት ነው ታዲያ እንዳትነካው ይከለከላት? ጌታችን ማርያም መግደላዊትን፡- “አትንኪኝ” ሲላት እርሱን አለመንካቷ ተግሣጽ እንዲሆናትም በማሰብ ነው። ጌታችን ለማርያም መግደላዊት ወደ ሰማይ እንደሚያርግ በፍጻሜ ዘመንም በዚሁ አካል እንደሚመጣ በመጣም ጊዜ ለእነርሱ የገባውን ቃል እንደሚፈጽም ከሐዋርያት ጋር ሳለ አስተምሮአት ነበር።  ስለዚህ እርሱ ጌታችን እንደሆነ ስታውቅ በአእምሮዋ ዳግም ምጽአቱ የተፈጸመ መስሎአት በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ እንዳለች ቆጥራ ነበርና “ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ' አላት፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ብዙ ሕዝብና ትውልድ ከተዋጡበት ከሲኦል በኵር ሆኖ ተወልዷልና (ተነሥቶአልና) በዚህ ቃሉ በእርሱ ትንሣኤ (ብቻ) አባቶች ወደ ልጆቻቸውም ልጆችም ወደ አባቶቻቸው እንዳይመለሱ ነገር ግን ሁሉም በትንሣኤ ዘጉባኤ ትንሣኤአቸው እንዲፈጽምላቸውና ወደ አባታቸውም ለማረግ የተገባቸው እንደሚሆኑ ሲያስገነዝባት እንዲህ አለ፡፡ አንድ አንባቢ “እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ" የሚለውን ቃል ሲያነብ ጥሬ ቃሉን ይዞ እግዚአብሔር አብ በምድር እንደሌለ በሰማይ እንዳለ አድርጎ እንዳይረዳ፤ እርሱ እግዚአብሔር አብ በምድርም ያለ ከሆነ ስለምን ጌታችን ወደ ሰማይ እሄዳለሁ አለ? ብሎ ይጠይቅ ይሆናል። ልጁ በሰማይ የማይሆንበት አባቱም በምድር የማይኖርበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ጌታችን “እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ” ዮሐ.17:11 ባለው ቃል እውነቱን ገልጦልናል፡፡ “አምላኬ” አላለውም፤ “ቅዱስ አባት ሆይ!” አለው እንጂ። እንዲህም ማለቱ እርሱ ከእርሱ እንደወጣ ለማጠየቅ ነው። መግደላዊት ማርያም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሲልካት ግን “ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ እሄዳሉ" ብሏታል፡፡ እንዲህም ሲላት ከእርሱ ጋር በአምላክነት አንድ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡  ጌታችን እንዲሁ በሌላ ሥፍራ “አብ ከእኔ ጋር ስለሆነ ብቻዬን አይደለሁም።”፣ “እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ”ዮሐ.17:36 “እኔና አብ አንድ ነን” ብሎአልና። ዮሐ.14:11 ጌታችን “ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ” ብለሽ ተናገሪ ብሎአል፡፡ “ወደ አባታችንና ወደ አምላካችን" አላለም ነገር ግን “ወደ አባቴ” አስከትሎም “ወደ አምላኬ" አለ እንጂ። በእርግጥ “ወደ አባታችንና ወደ “አምላካችን” ብቻ ብሎ ቢሆን ኖሮ ለሚቃወሙን መሠረት በኖራቸው ነበር፡፡ ነገር ግን “ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ” ሲል ስለ ሥጋዌው መናገሩ ነው። “ወደ አባቴ እሄዳለሁ” ሲል ስለሥጋዌው እንጂ በእግዚአብሔር ቃልነቱ አይደለም። እንዲሁ “ወደ አባታችሁ” ሲልም ከእኛ ስለነሣው ሥጋ ስለመሆኑ “አባታችን ሆይ! በሰማያት የምትኖር”ብሎ ባዘዘን ቃሉ መረዳት እንችላለን፡፡ ማቴ.6:9 ✅መ/ር ንዋይ ካሳሁን
Show all...
👍 4 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
አትንኪኝ” ዮሐ.20:17 ጌታችን ማርያም መግደላዊነትን “አትንኪኝ" የማለቱ ምክንያት ይህ አካል ከሲኦል በኵር ሆኖ አብቦ ያፈራ ፍሬ ነውና እንደ ሊቀ ካህንነቱ ይህን ፍሬ ከሰው እጅ ንክኪ ጠብቆ ከዚህ ፍሬ ሊቀበልና ዋጋውንም ሊከፍል ለሚችል ሰው ሊያቀብለው ስለሚገባ ነው። አንድም አካሉን እንዳትነካው መፈለጉ ይህ አካል በመክበሩ ነው። እርሱ አስቀድሞ እንደ አገልጋይ በመካከላቸው ሲመላለስ እርሱን ነክተውት ነበር። ኃጢአተኞችና ቀራጮችም ቀርበው ዳስሰውታል፡፡ "ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቱ ንጥር ወስዳ የኢየሱስን እግር ቀባች፤ በጠጕርዋም እግሩን አበሰች፤ ቤቱም ከናርዶስ ሽቱ ሞላ" ዮሐ.12:3 ወደ ቀደመው ክብሩ ሲመለስ ግን እግዚአብሔር አብን እንዲፈሩት እርሱን መፍራትም በእነርሱ ላይ ሰፈነ። አይደለም ጌታችንን ነገሥታትን መሳፍንትን ስናይ እነርሱን ለመንካት እንፈራ የለምን? ጌታችን ማንም እንዳይነካው መፈለጉ ጠላቶች ከእንግዲህ እርሱን ፈጽመው መረዳትም ሆነ ሊይዙት ሥልጣን እንደሌላቸው ለማሳየት ነው።  ወዳጆቹ ግን በሌላ መንገድ እርሱን በመፍራትና በፍቅር ሊነኩት ሥልጣኑ ተሰጥቶአቸዋል።  ይህም በሥርዓተ ቊርባን ከሥጋውና ከደሙ በመቀበል እርሱን ይነኩታል ከሕማሙም ይካፈላሉ፡፡ ከቅዱስ ሥጋውና ከክቡር ደሙ የሚቀበሉ ሁሉ ከሕማሙ መካፈልንም ይወቅ።  እርሱ ለእነርሱ ደስታን እንደሰጠ እርሱም በእነርሱ ደስ ይበለው።  አንዳንዶች ጌታችን ማርያም መግደላዊትን አትንኪኝ ማለቱ ከቅዱስ ሥጋውና ከክቡር ደሙ ስላልተቀበለች ነው ብለው ይተረጕማሉ፡፡ ስለዚህም እንዲህ ሲላት ከቅዱስ ሥጋው ከክቡር ደሙ ሊያቀብላት ስለፈለገ ነው።  አንድም እንዲህ ማድረጉ የአስቆሮቱን ይሁዳን የመሰሉ ጠላቶቹን ብቻ ሳይሆን ወዳጆቹ ጭምር እርሱን ከእንግዲህ ቀርበው ሊዳስሱ እንደማይችል ምሳሌ ሲሰጣቸው ነው፡፡ አንድም ጌታችን ማርያምን አትንኪኝ ማለቱ ሔዋን እናቷ እጆቿን በመዘርጋት ይህን አካል ለሞትና ለልዩ ልዩ መከራዎች አሳልፋ መስጠቷን ለማሳሰብ ነው። ነገር ግን እርሱን የመንካት መብት “በቀኜ ተቀመጥ” መዝ.110:1 ለሚለውና ከዕርገት በኋላ በመልካም ነገሮች ሁሉ ለሚያከብሩት እጆች የተጠበቁ መሆናቸውንም ለማስረዳት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጌታችን ማርያምን አትንኪኝ ማለቱ በመጠራጠሯ ነበር። ክርስቶስ እንደተነሣ ሰምታ ነበር ነገር ግን ጌታችንን ባየችው ጊዜ የአትክልት ጠባቂ መስሏት፡ - “ጌታ ሆይ! አንተ ወስደኸው እንደ ሆንህ ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ" ብላለች። ዮሐ.20:14 በዚህም ቃሏ ትንሣኤውን መጠራጠሯን እንረዳለን፡፡ ስለዚህም ጌታችን “ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።" ዮሐ.20:17 እንዲህም ሲል ወደ አባቱ ከማረጉ በፊት እርሱን የማትነካው ሆና አይደለም። ነገር ግን ስለ ጥርጣሬዋ “ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ” አላት፡፡ ትንሣኤውን በመጠራጠሯ እርሱን እንዳትነካ ከልክሎአት ቢሆን ኖሮ ቶማስ ትንሣኤውን ተጠራጥሮ ነበር ነገር ግን ጌታችንን ነክቶታል፡፡ "ከዚያም በኋላ ቶማስን፦ ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው" ዮሐ.20:27 ይህንን እንደሚከተለው እናብራራው፡- ስለሚቀበለው መከራ አስቀድሞ እንደተናገረ ስለትንሣኤውም አስቀድሞ እንደነገራቸው እንዲሁ ዕርገቱን በሚመለከት አስቀድሞ ለእነርሱ መንገር መፈለጉን እንመለከታለን፡፡ 
Show all...
👍 1
እግዚአብሔር የማመስገን ግዴታ አለብኝ 🤲🙏 ✍በውስጥ መስመር በጠየቃችሁት መሰረት ያስተምሯችኋል የምትሉአቸውን TOP  የቴለግራም ቻናል ይዘን መተናል መርጠው ይቀላቀሉ🙏             ይ🀄️ላ🀄️ሉ ይማሩ                   👇🏾👇🏾👇🏾 https://t.me/addlist/AQPOMxHXz_42NDE0
Show all...
የመዝሙሮች ግጥም
የኦርቶዶክስ ምስለ አድኖ
የኦርቶዶክስ ስብከት
ስንክሳር
የኦርቶዶክስ የዝማሬ መድብል
ይ🀄️ላ🀄️ሉ
Photo unavailableShow in Telegram
ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ ታዟል። የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት እነ ቀሲስ በላይ መኮንን ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ አዟል። በዋስ ጥያቄያቸው ዛሬም ውድቅ ተደርጓል። ቀሲስ በላይ መኮንን በችሎቱ ፥ " ፖሊስ ይዞኝ ሳይሆን እራሴ ነው የሄድኩት " ብለዋል፡፡ " ብዙ የሀገር ጉዳይ በእጄ ስላሉ ጥፋ ብባል እንኳ የምጠፋ ስላልሆንኩ ፤ በጤናዬ ላይ በደረሰው እክልና በቤተሰቦቼ ላይ በደረሰው ችግር ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብት ይጠብቅልኝ " ሲሉ ጠይቀዋል። የብዙ ልጆች አሳዳጊና የቤተሰብ አስተዳዳሪ እንደሆኑ ጠቅሰው በዋስ ከእስር እንዲወጡ ጠይቀው ነበር። ፍርድ ቤት ግን ሁሉም ተከሳሾች በፖሊስ ጣቢያ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ አዟል። ቀሲስ በላይ መኮንን በሀሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ላይ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማውጣት ሙከራ አድርገዋል ተብለው አብረዋቸው ከነበሩት ሰዎች ጭምር መታሰራቸው አይዘነጋም። ✅ዶቼቨለ ቲክቫህ
Show all...
👍 6 2👏 2
ዓለም አቀፍ የመነኮሳት ማኅበር ወቅታዊ ሀገራዊ እና ቤተ ክርስቲያናዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ጠንከር ጠንከር ያሉ አቋሞቹን በመዘርዘር መግለጫ አወጣ። ማኅበሩ በመግለጫው ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያን የገጠማትን ፈተና ለመመከት በሚመጥን ካልተራመደ ሓላፊነቱን ለሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እስከማስረከብ መሔድ አለበት ብሏል። ብፁዕ አቡነ ሉቃስንም በብርቱ ተከላክሏል። ተግሣጻቸው ነቢዩ ኤልያስ ኤልዛቤልና አክዓብን እንደገሰጸበት ያለ ነው ብሏል። ✅አባይነህ ካሴ
Show all...
👍 5👏 2 1
🔔✝ ከመምህራን የማንን ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇 ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ምሕረተአብ አሰፋ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ዘበነ ለማ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ሄኖክ ኃይሌ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ዮርዳኖስ አበበ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 አባ ገብረ ኪዳን ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ያረጋል አበጋዝ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር እዮብ ይመኑ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔መምህር ገብረ እግዚአብሔር ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔መምህር አባ ገብረ ኪዳን ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ 🔗የሁሉንም መምህራን ትምህርት ለማግኘት🔔 🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
Show all...
ትምህርቶችን ለማዳመጥ
Photo unavailableShow in Telegram
ምእመናን በሀገረ እንግሊዝ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን እውቅና ውጭ እየተደረገ ከሚገኘው የሕገወጥ "አጥማቂዎች" እንቅስቃሴ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ ቀረበ ! "ቀሲስ" ሄኖክ በተባለ ግለሰብ አማካይነት በሀገረ እንግሊዝ ከመዋቅሩ ፈቃድና እውቅና ውጭ አዳራሽ በመከራየት "የፈውስ" አገልግሎት እንሰጣለን በሚል እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ተከትሎ በርካቶች አካሄዱን በማውገዝ ግለሰቡ ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ በተለያዩ መንገዶች ጥሪ ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወሳል። ይኸው ግለሰብ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ንዋየ ቅድሳት በመጠቀም እና ምእመናንን በማታለል እያደረገ የሚገኘውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ በመቀጠል የፊታችን ዓርብ ጀምሮ እንደ መናፍቃን ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውጭ አዳራሽ በመከራየት "የፈውስ" አገልግሎት እሰጣለሁ እያለ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው። ግለሰቡ እና በሀገረ እንግሊዝ የሚኖሩ ግብረአበሮቹ በከፈቱት አንድ የማኅበራዊ ትስስር ሚዲያ ግሩፕ ውስጥ በርካታ ምእመናንን በአባልነት በመያዝ በከፍተኛ ሁኔታ የማሳሳት ተግባር ላይ እንደሚገኝ ተ.ሚ.ማ ያገኘው ማስረጃ ያመላክታል። የሕገወጥ አጥማቂያንን እንቅስቃሴ ከብፁዓን አባቶች ጀምሮ በርካቶች እያወገዙት የሚገኘው ተግባር ቢሆንም የቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የሥልጣን አካል በዚህ አደገኛ ተግባር ላይ ያለው ነገር አለመኖሩ አነጋጋሪ ሆኗል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከተ.ሚ.ማ ጋር ቆይታ ያደረጉ በሀገረ እንግሊዝ የሚኖሩ አንዳንድ ካህናት እና ምእመናን ይህ ሕገወጥ ሰው ባዘጋጀው ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ ወደሆነ "የፈውስ" ስም ያለው ተግባር ምእመናን ባለመሳተፍ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል። ✅ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
Show all...
👍 6 2
Show all...
መዝሙር ከ ግጥም ጋር
መዝሙሮችን ለማግኘት
ይቀላቀሉ