664
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
#ALERT 🚨 ፡ በጀርመን፣ ጣሊያን፣ ሮማኒያ እና ቡልጋሪያ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ሰፈሮች የሽብር ጥቃት ሊፈጠር ይችላል በሚል የስጋት ደረጃቸውን ወደ "ቻርሊ" ከፍ አድርገዋል።
Share | T.me/TheNewsReports
#BREAKING ፡ የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለሁቲዎች ተዋጊ ፀረ-መርከቦች፣ ባለስቲክ ክሩዝ ሚሳኤሎችን ለመስጠት አስበዋል ሲሉ አንድ የአሜሪካ የስለላ ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣን ለMEE ተናግረዋል።
ቭላድሚር ፑቲን የየመን ሁቲዎችን ለማስታጠቅ ሳውዲ አረቢያን የክሩዝ ሚሳኤሎችን ወደ ሁቲዎች እንድታስተላለፍ ፍቃድ ጠይቋል።
Share | T.me/TheNewsReports
#NEW ፡ የእስራኤሉ ኤል አል አውሮፕላን ዛሬ በድንገተኛ ክስተት ምክንያት በቱርክ አንታሊያ ለማረፍ ተገዶ ነበር።
አውሮፕላኑ ሲያርፍ በቦታው ላይ የነበሩት የቱርክ ባለስልጣናትም አውሮፕላኑን ነዳጅ ለመሙላት ፈቃደኛ እንዳልነበሩ ተዘግቧል።
በመሆኑም አውሮፕላኑ ወደ እስራኤል ከመብረሩ በፊት ነዳጅ ለመሙላት ወደ ሮድስ ግሪክ እየበረረ መሄዱ ነው የተነገረው።
Share | T.me/TheNewsReports
#BREAKING ፡ በሩሲያ ኒዝሂኒ ኖቭጎሮድ ከተማ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ተነስቷል።
የአደጋ ጊዜ ሚኒስቴር እንደገለጸው፣ አንድ ሺህ ካሬ ሜትር አካባቢ የሚሸፍነው የቆሻሻ ማስወገጃ መጋዘን በእሳት እየተቃጠለ ነው ብሏል።
በድንገተኛ አደጋ ወቅት ፍንዳታዎች እንደደረሱ የአካባቢው ሪፖርቶች ያመለክታሉ።
Share | T.me/TheNewsReports
#BREAKING ፡ ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ ጠቃሚ ነገር ይፋ እንደምታደርግ ተናግራለች።
Stay Tuned!
Share | T.me/TheNewsReports
#JUST_IN ፡ አዲስ የእስራኤል ወታደራዊ ማጠናከሪያዎች ወደ ሊባኖስ ድንበር እየተሰማሩ ነው።
Share | T.me/TheNewsReports
#BREAKING ፡ አረብ ሊግ ሒዝቡላህን ከአሸባሪ ድርጅት ዝርዝር ውስጥ ሰርዟል።
የአረብ መንግስታት ሊግ (LAS) ከአሁን በኋላ የሺዓ ፓርቲ የሆነውን ሒዝቦላህን እንደ አሸባሪ ድርጅት አይመለከተውም ሲል አል-አኽባር ዕለታዊ የላስ ረዳት ዋና ፀሀፊ ሆሳም ዛኪን ጠቅሶ ዘግቧል።
የግብፅ ዲፕሎማት በዕለታዊው ጋዜጣ እንደዘገበው ሒዝቡላህ በአሁኑ ፖለቲካ እና በወደፊት የሊባኖስ እጣ ፈንታ ላይ ወሳኝ ሚና ስለሚጫወት ሊጉ የአሸባሪውን መለያ ከሒዝቦላህ ላይ ለማንሳት ወስኗል።
- TASS
Share | T.me/TheNewsReports
#BREAKING ፡ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፦ ሒዝቦላህ ከደቡብ ሊባኖስ ካልወጣ እስራኤል በሒዝቡላህ ላይ በሙሉ ሃይል እርምጃ ትወስዳለች!። የኢራን መንግስትም መጥፋት አለበት!"
Share | T.me/TheNewsReports
#NEW ፡ አብዛኞቹ የአሜሪካ መራጮች ከክርክሩ በኋላ ስለ ባይደን እና ትራምፕ ያላቸውን አስተያየት ቀይረዋል ተብሏል።
46.7% መራጮች ለባይደን ድምጽ ለመስጠት ዝግጁ ሲሆኑ 43.9% ትራምፕን ይደግፋሉ።
የባይደን ደጋፊ መራጮች በጣም እየቀነሱ ነው።
- Ipsos
Share | T.me/TheNewsReports
#BREAKING ፡ ሳውዲ አረቢያ ዜጎቿ በአስቸኳይ ሊባኖስን ለቀው እንዲወጡ አሳስባለች።
Share | T.me/TheNewsReports
#BREAKING ፡ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የቅርብ ዘመዶቹ እና ጓደኞቹ የተሻለ እንደሆነ ከወሰኑ የፕሬዝዳንትነት ውድድሩን ይተዋል ሲል አክሲዮስ ፅፏል።
በፕሬዚዳንቱ ውሳኔዎች ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ቁልፍ ግለሰቦች ከተባሉት ውስጥ ቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን፣ ታናሽ እህታቸው ቫለሪ ባይደን፣ ጓደኛቸው እና አማካሪያቸው ቴድ ካፍማን እና አነስተኛ የዋይት ሀውስ ረዳቶች ይገኙበታል ተብሏል።
- Axios
Share | T.me/TheNewsReports
#NEW ፡ አነጋጋሪ የሆነው የታይም መፅሔት ሽፋን በብዙ ሚዲያዎች እየተዘዋወረ ይገኛል።
ታይም መጽሔት ተሰናባቹን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን በእትሙ ሽፋን ላይ በማድረግ "ሽብር/ድንጋጤ" የሚለውን ቃል አብሮ ፅፏል።
"ነገሮች ጨለማ ናቸው። ዲሞክራቶች ስለ ጆ ባይደን የክርክር አፈጻጸም እየተሸበሩ ነው" ሲል ታይም ሽፋኑን ገልጿል።
Share | T.me/TheNewsReports
#NEW ፡ ሰሜን ኮሪያ የ22 ዓመቱን ወጣት ኬ-ፖፕ ሙዙቃን በመስማቱ በሞት ቀጥታለች።
ወጣቱ ከደቡብ ኮሪያ የመጡ ሙዚቃዎችን ማዳመጥ ብቻ ሳይሆን ፊልሞችን በመመልከት ከጓደኞቹ ጋር በማጋራቱ ነው የተቀጣው ተብሏል። ይህም የሰሜን ኮሪያን ህግ የሚፃረር በመሆኑ የሞት ቅጣት ሊፈረድበት ችሏል።
የደቡብ ኮሪያ ፊልሞች እና ሙዚቃዎች በፊኛዎች ወይም በጥቁር ገበያ ወደ ሀገሪቱ ሊገቡ ይችላሉ።
ዘገባው የዘ-ጋርዲያን ነው።
Share | T.me/TheNewsReports
#BREAKING ፡ የግብፅ ጦር በራፋህ ድንበር ላይ ብዙ ሃይሎችን እየሰበሰበ መሆኑ ተሰምቷል።
ግብፅ ወደ 160 የሚጠጉ ታንኮች እና 140 ጂፕ ተሽከርካሪዎችን ከፀረ-ታንክ ጠመንጃዎች ጋር ማሰማራቷን የእስራኤል ሚዲያዎች ገልጸዋል።
Share | T.me/TheNewsReports
#አንዲት እስራኤላዊት እንስት የሒዝቡላህን ጥቃት እየቀረፀች ባለችበት ወቅት የሒዝቡላህ ሮኬት አጠገቧ ሲፈነዳ የሚያሳይ ምስል ነው።
Share | T.me/TheNewsReports
#NEW ፡ ዘ ጀሩሳሌም ፖስት፦ አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ጋላንት ላይ ሊሰጥ የነበረውን የእስር ማዘዣ አራዝሟል።
Share | T.me/TheNewsReports
