en
Feedback
Maya Essentials

Maya Essentials

Open in Telegram

ማያ ዘመናዊ የወጥ ቤት ዕቃዎች መሸጫ

Show more
664
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Attracting Subscribers
October '25
October '25
+1
in 0 channels
September '250
in 0 channels
Get PRO
August '250
in 0 channels
Get PRO
July '250
in 0 channels
Get PRO
June '250
in 0 channels
Get PRO
May '250
in 0 channels
Get PRO
April '250
in 0 channels
Get PRO
March '250
in 0 channels
Get PRO
February '250
in 0 channels
Get PRO
January '250
in 0 channels
Get PRO
December '24
+2
in 0 channels
Get PRO
November '24
+11
in 0 channels
Get PRO
October '24
+9
in 0 channels
Get PRO
September '24
+21
in 1 channels
Get PRO
August '24
+51
in 1 channels
Get PRO
July '24
+70
in 1 channels
Get PRO
June '24
+51
in 1 channels
Get PRO
May '24
+105
in 1 channels
Get PRO
April '24
+157
in 3 channels
Get PRO
March '24
+143
in 2 channels
Get PRO
February '24
+71
in 2 channels
Get PRO
January '24
+275
in 1 channels
Get PRO
December '23
+381
in 2 channels
Channel Posts
#BREAKING_ALERT - ኢትዮጵያ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ወደ ሶማሊያ ድንበር አስጠግታለች! T.me/TheNewsReports

2
#NOW - ብሊንከን በቴልአቪቭ: "እስራኤልን ለመከላከል ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅተናል" @TheNewsReports
#NOW - ብሊንከን በቴልአቪቭ: "እስራኤልን ለመከላከል ሙሉ በሙሉ ተዘጋጅተናል" @TheNewsReports
1 205
3
በሀገራችን በኢትዮጵያ እየተሰሙ እና በሚዲያው እየተንሸራሸሩ የሚገኙት ዜናዎች እንኳን ለመስማት ለማጋራት ራሱ እጅጉን ሰቅጣጭ ሆነዋል። ሰይጣናዊ ድርጊቶችን መስማት ቀላል እየሆነ መጥቷል። ፍርዶች እየ
በሀገራችን በኢትዮጵያ እየተሰሙ እና በሚዲያው እየተንሸራሸሩ የሚገኙት ዜናዎች እንኳን ለመስማት ለማጋራት ራሱ እጅጉን ሰቅጣጭ ሆነዋል። ሰይጣናዊ ድርጊቶችን መስማት ቀላል እየሆነ መጥቷል። ፍርዶች እየተዛቡ ነው። በፊት በፊት እንዲህ ያሉ ነገሮች ከስንት አንዴ እንኳ ሲሰሙ እጅጉን ያስደነግጥ ነበር። አሁን አሁን ያ ሰዋዊ ባህሪ ጠፍቶብናል። 'ሰው'ነታችንን ጥለነው መጥተናል። ለእያንዳንዱ እንዲህ ያለ ድርጊት እያንዳንዱ ዜጋ ሐላፊነት ይውሰድ። እንደ ሀገር ወድቀናል። @TheNewsReports
1 225
4
#BREAKING_ALERT 🚨 የዓለም ጤና ድርጅት በዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ ምክንያት ዓለም አቀፍ ድንገተኛ አደጋን አውጇል። @TheNewsReports
1 193
5
ዛቻ እና ፉከራ መገለጫዋ እየሆነ የመጣችው ኢራን እስራኤል ላይ የበቀል እርምጃ እወስዳለሁ ካለች ይሄው ሁለት ሳምንታት ተቆጠሩ። በትላንትናው እለት በሩሲያ ኤግዚቢሽን ላይ ያለ የሌላትን የረጅም ርቀት ድሮኖቿን ስታሳይ እና አቅሜን እዩ እያለች የነበረችው ኢራን በነዚህ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በጠላት ግዛት አንድም የረባ ጥቃት ለማድረስ እንደማትሞክር ራሷ ታውቃለች። የኢራን ፉከራ "ፍልስጤምን መደገፍ" በሚለው መስመር በመካከላኛው ምስራቅ ከሚገኙ አረብ ሀገራት በላይ ብቅ ብላ ለመታየት ብቻ ያለመ ይመስላል፤ ልክ እንደ ቱርክ! ቱርክ የጦር ሃይሏን እጅጉን እያዘመነች ብትመጣም በጦርነቱ ፍልስጤማውያንን ለመርዳት የሚያስችል በቂ ድፍረት የላትም፤ የኔቶ አባል ነችና! ነገር ግን ባትሆን ኖሮም አሁን ከምታደርገው ነገር የዘለለ ምንም እንደማትፈይድ እርግጥ ነው። ሳውዲና ጆርዳን ነገሩን በዝምታ ማየታቸው ብዙሃኑን እያስጮኸ የነበረ ቢሆንም አሁን ያለውን ሁኔታ ያየ ሰው ሀገራቱ በትክክል ምን እየሰሩ እንደነበር መረዳት ይችላል። አንድ እውነታን መረዳት አለብን። አሜሪካ በተቃራኒ በኩል ያለችበት ነገር ላይ ማንም ምንም ሊፈይድ አይችልም፤ ተዓምር ካልተፈጠረ በስተቀር። ዩክሬንን፣ እስራኤልን እና ታይዋንን በአንድ ግዜ አንድላይ የመደገፍ እና የመርዳት አቅም ያላት አሜሪካ ብቻ ናት! @TheNewsReports
1 249
6
ባለፉት ሳምንታት በእንግሊዝ የተጀመረው የፀረ-ስደተኞች እና የፀረ-ኢስላም ተቃውሞ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል። በሀገራችን ሚዲያዎች ብዙም እየተወራለት ባይሆንም ተቃውሞው በዝምታ የሚታለፍ አይደለም። በ
ባለፉት ሳምንታት በእንግሊዝ የተጀመረው የፀረ-ስደተኞች እና የፀረ-ኢስላም ተቃውሞ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል። በሀገራችን ሚዲያዎች ብዙም እየተወራለት ባይሆንም ተቃውሞው በዝምታ የሚታለፍ አይደለም። በቤልፋስት፣ በርሚንግሃም፣ ካርዲፍ፣ ግላስጎው፣ ለንደን እና በሌሎችም የእንግሊዝ ከተሞች የተስፋፋው ይህ ተቃውሞ ሙስሊሞችን ለማጥቃት እና መስጂዶችን ለመውረር ብዙ ሙከራዎች ተደርገዋል። በሀገሪቱ ያሉ የእስልምና እምነት ተከታዮችም በቀላሉ የሚቀመሱ ሆነው አልተገኙም። ህብረት እና አንድነታቸውን ያሳዩት ሙስሊሞች እና ጥቁር ስደተኞች ከተቃዋሚዎቹ በበለጠ መልኩ ሃይላቸውን አጠናክረዋል። በነገራችን ላይ አንዳንድ ጥናቶችን እንዳየሁት እስልምና ምዕራባውያን ዘንድ እጅግ ፍጥነት ባለው መልኩ እየተስፋፋ ያለ ሐይማኖት ነው። ይህ ተቃውሞ ጊዜያዊ ቀውስ ከመፍጠር በዘለለ እዚህ ግባ የሚባል ቁምነገር የሚያመጣ አይመስልም። ለተቃውሞ እጅጉን ረፍዷል! Share | T.me/TheNewsReports
1 178
7
#ALERT ⚠️ - በአለም ላይ ላሉ የሲቪል አቪዬሽን ኩባንያዎች ከኢራን ባለስልጣናት በተላለፈ ማስታወቂያ መሰረት፣ በወታደራዊ ልምምድ ምክንያት በኢራን የአየር ክልል ላይ መብረርን አስወግዱ ብላለች። - Al Qahera News @TheNewsReports
1 305
8
#ቴህራን እና ሒጃብ | (Latest News) ምስሉ ፖሊሶች ሂጃብ በመባል የሚታወቀውን የራስ መሸፈኛ ያልለበሱ ልጃገረዶችን ሲደበድቡ፣ ሲያስሩ እና ጎትተው ወደ መኪናው ሲያስገቧቸው ያሳያል።    ዛሬ በሚዲያው አለም መነጋገሪያ የነበረው ይህ የህግ አስከባሪ ሀይሎቹ ድርጊት አለምን አስቆጥቷል። የ14 አመት ልጇ ተጎጂ የሆነችባት እናት ለኢንሳፍ ኒውስ ድረ-ገጽ እንደተናገሩት፤ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት የልጇ ጭንቅላት በኤሌትሪክ ምሰሶ እንደተመታ እና ድብደባውም በመኪና ውስጥ እንደቀጠለ ትናገራለች።    የተጎጂዋ እናት በልጇ ላይ ስለደረሰው ጉዳት ቅሬታ ብታቀርብም ወታደራዊ አቃቤ ህግ በሲሲቲቪ የተቀረፀው ምስል እንድታገኝ ቢፈቅድላትም ፍትህን ለማግኘት ያደረገችው ጥረት ብዙም አልተሳካም ትላለች። እናትየው ከታሰሩ በኋላ የልጃቸውን ሁኔታ ሲገልጹ ታዳጊዋ ፊቷ፣ ከንፈሯ እና አንገቷ ላይ ጉዳት የደረሰባት ሲሆን አለፍ ሲልም የመናገር ችግር እንዳጋጠማት ተናግራለች። በዚህም በዛሬው እለት ምላሽ የሰጠው የቴህራን የፖሊስ ሃይል መረጃ ማእከል ቪዲዮው ከ2 ሳምንታት በፊት የተቀዳ ነው ብሏል።    ፖሊስ በመግለጫው ታዳጊዎቹ ተገቢ ያልሆነ ልብስ እንዳይለብሱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ነበር ሲል ገልጿል።  ክስተቱ በኢራን ጥብቅ የአለባበስ ህግ እና የማስፈጸሚያ ዘዴዎቹ ላይ የነበረውን ክርክር አቀጣጥሏል ተብሏል። ብዙ የፋርስ ቋንቋ ተናጋሪ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በታዳጊዎቹ አያያዝ ላይ ቁጣ እና ብስጭታቸውን ሲገልጹ አዲሱን የኢራን ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን እንዲ አይነት ነገሮችን እንዲያስቆሙ ብዙዎች ጠይቀዋል። ፕሬዝዳንት መስዑድ በፕሬዝዳንትነት ዘመቻው ወቅት የግዴታ የሂጃብ ህግጋትን ባለማክበር የህግ አስከባሪ ፖሊሶች በኢራን ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ስላላላቸው አያያዝ በተደጋጋሚ ሲወቅስ ታይቷል።     በመላው ኢራን የአለባበስ ደንብን ጥሰዋል በሚል ምክንያት ሴቶች መታሰራቸውን እና የኃይል እርምጃ እንደተወሰደባቸው በርካታ ሪፖርቶች ቀርበዋል።   ይህም በበርካታ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ተቃውሞው እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል። - AL ARABIYA , ENSAF @TheNewsReports
1 417
9
No text...
964
10
#NEW - ጆርዳን፣ ኳታር እና ሳዑዲ አረቢያ ከጦርነቱ በኋላ በጋዛ ሰላም አስከባሪ ሃይል ለማሰማራት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተሰምቷል። ግብፅ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ጦር በማሰማራቱ ላይ የመሳተ
#NEW - ጆርዳን፣ ኳታር እና ሳዑዲ አረቢያ ከጦርነቱ በኋላ በጋዛ ሰላም አስከባሪ ሃይል ለማሰማራት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተሰምቷል። ግብፅ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ጦር በማሰማራቱ ላይ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል። አንድ የአረብ ባለስልጣን እንዳብራሩት፣ ከጦርነቱ በኋላ ጋዛ ውስጥ ሃይል ማሰማራት ለእስራኤል መከላከል ተደርጎ ስለሚታይ ጆርዳን፣ ኳታር እና ሳዑዲ አረቢያ ያን ማድረግ አይፈልጉም። - Times of Israel @TheNewsReports
1 156
11
#JUST_IN - ኒጀር ማሊን ተከትላ ከዩክሬን ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጠች። ካለፈው አመት መፈንቅለ መንግስት በኋላ ወደ ስልጣን የመጣው የሀገር ውስጥ ጥበቃ ብሄራዊ ምክር ቤት ኪ
#JUST_IN - ኒጀር ማሊን ተከትላ ከዩክሬን ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጠች። ካለፈው አመት መፈንቅለ መንግስት በኋላ ወደ ስልጣን የመጣው የሀገር ውስጥ ጥበቃ ብሄራዊ ምክር ቤት ኪይቭ አሸባሪ ቡድኖችን ትደግፋለች ሲል ከሰዋል። @TheNewsReports
975
12
#RAPE - አንድ የደህንነት ካሜራ የእስራኤል ወታደሮች አንዲት ፍልስጤማዊትን እስረኛ አስገድደው ሲደፈሩ ቀርጿል። ሌሎች አብረው የነበሩ ጠባቂዎችም መከላከያቸውን ተጠቅመው ካሜራውን ለመሸፈን ሲሞክሩ
#RAPE - አንድ የደህንነት ካሜራ የእስራኤል ወታደሮች አንዲት ፍልስጤማዊትን እስረኛ አስገድደው ሲደፈሩ ቀርጿል። ሌሎች አብረው የነበሩ ጠባቂዎችም መከላከያቸውን ተጠቅመው ካሜራውን ለመሸፈን ሲሞክሩ ይታያል። እንስቷ በከባዱ የተጎዳች ስትሆን የፊን** መቀደድ፣ የአንጀት እና የሳንባ ጉዳት እና የጎድን አጥንት መሰበር አጋጥሟታል ተብሏል። - N12 T.me/TheNewsReports
1 015
13
#BREAKING - ካናዳ ነገ ዲፕሎማቶቿን ከእስራኤል ልታስወጣ ነው። @TheNewsReports
1 004
14
የዛሬ 79 ዓመት በዛሬዋ እለት፡ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 6 ቀን 1945 ዩናይትድ ስቴትስ በጃፓን ሂሮሺማ ላይ "Little boy" የሚል ቅጽል ስም የተሰጠውን የዩራኒየም ቦምብ ጣለች። - ቦምቡ ከ15,00
የዛሬ 79 ዓመት በዛሬዋ እለት፡ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 6 ቀን 1945 ዩናይትድ ስቴትስ በጃፓን ሂሮሺማ ላይ "Little boy" የሚል ቅጽል ስም የተሰጠውን የዩራኒየም ቦምብ ጣለች። - ቦምቡ ከ15,000 ቶን ቲአረንቲ (TNT) ጋር የሚመጣጠን ፈንጂ ምርት የነበረው ሲሆን ከተማዋን አውድሞ 70 በመቶ የሚሆነውን አቃጥሏል። - በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራት ውስጥ በሂሮሺማ የቦምብ ፍንዳታው 140,000 የሚገመቱ ሰዎች ተገድለዋል። - ከሃይፖሴንተር በ1.2 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኙት መካከል 50% ያህሉ የሞቱት በዚያ ቀን ሲሆን በሉኪሚያ፣ ካንሰር እና ሌሎች በሽታዎችን ጨምሮ በጨረር መጋለጥ ምክንያት በሚቀጥሉት አመታት በርካቶች ሞተዋል። ከላይ ምስሉ የሚያሳየው የሂሮሺማ ከተማ ከቦምብ ጥቃቱ በፊት እና በኋላ ነው። @TheNewsReports
1 103
15
#JUST_IN - በኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ በደረሰ የሮኬት ጥቃት በርካታ የአሜሪካ ወታደሮች ቆስለዋል ሲል ምንጮች ለሮይተርስ ገልፀዋል። @TheNewsReports
775
16
#BREAKING - ሁለት ሮኬቶች በኢራቅ የአሜሪካ ወታደሮች በሚገኙበት በአይን አል አሳድ የጦር ሰፈር ላይ ተተኩሷል።  - REUTERS @TheNewsReports
859
17
#JUST_IN - ዮርዳኖስ የአየር ክልሏን ለማንኛውም አካል እንዲጠቀሙ እንደማትፈቅድ ለአሜሪካ፣ ለእስራኤል እና ለኢራን አሳውቃለች። - SKY NEWS ARABIA @TheNewsReports
936
18
#BREAKING - ጀርመን ዜጎቿን ከሊባኖስ ለማስወጣት መዘጋጀቷን ስፒጌል የዜና ምንጭ ዘግቧል። - Spiegel @TheNewsReports
938
19
መካከለኛው ምስራቅን በተመለከቱ የተለያዩ አዳዲስ መረጃዎች እየወጡ ነው። ፈጣን መረጃዎችን እናደርሳችኋለን፤ ቻናላችንን ይቀላቀሉ! @TheNewsReports
817
20
አንድ ትልቅ የሚድያ ተቋም ስለ አንድ ፋውንቴን ዘገባ ሲሰራ በግሌ እንደማስበው ህዝብ በእንደዚህ አይነት ዘገባዎች በእጅጉ ተሰላችቷል። አንድ፣ ሁለት፣ አምስት፣ አስር፣ ሀያ... ዘገባዎች ችግር ላይኖ
አንድ ትልቅ የሚድያ ተቋም ስለ አንድ ፋውንቴን ዘገባ ሲሰራ በግሌ እንደማስበው ህዝብ በእንደዚህ አይነት ዘገባዎች በእጅጉ ተሰላችቷል። አንድ፣ ሁለት፣ አምስት፣ አስር፣ ሀያ... ዘገባዎች ችግር ላይኖረው ይችላል። ስንት በርካታ የሚነገሩ፣ ህዝብ የሚጮህባቸው እና መፍትሄ የሚፈልጉ ጉዳዮች እያሉ ሚድያው በሳምንት በመቶ የሚቆጠሩ ዘገባዎችን ስለ ኮሪደር ሲዘግብ መዋሉ ይባስ ህዝቡ ስለ ፕሮጀክቱ ሌላ አተያይ እንዲኖረው እያደረገው እንዳለ እየተገነዘብን ነው። ዝም ተብሎ ቢሰራ ህዝብም "ድምፃቸውን አጥፍተው እየሰሩ ነው" ብሎ ያደንቃል። በዚህ መልኩ ህዝብን ማሰላቸት ተገቢ ነው ተብሎ ከታመነበት... አጠናክረህ ቀጥል፣ ብሎን ሲታሰር እና ጡብ ሲቀመጥም ዘግብ። ግን ህዝብ ሰልችቶት ሀሳቡ ሁሉ የኑሮ ውድነት፣ የፀጥታ ስጋት እና የብልሹ አሰራር ማማረር ላይ ነው። © Elias Meseret @TheNewsReports
830