en
Feedback
Maya Essentials

Maya Essentials

Open in Telegram

ማያ ዘመናዊ የወጥ ቤት ዕቃዎች መሸጫ

Show more
664
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
#ALERT - ኢራን ከእስራኤል ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ በረራዎች እንዳይደረጉ እና በዚያ መስመር ላይ የሚደረጉ በረራዎች መስመር እንዲቀይሩ ትዕዛዝ ሰጥታለች። @TheNewsReports

#JUST_IN - ኢራን እና ሒዝቡላህ ዛሬ ለሊቱን እስራኤል ላይ ጥቃት ይሰነዝራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በነገራችን ላይ ጥቃት "ጥቃት" የሚባለው ድንገት እና ሳይታሰብ የሚመጣ ሲሆን ነው። አሜሪካ እና እስራኤል፤ ኢራን ዛሬ ልታጠቃ እንደምትችል ያውቃሉ። ይህም ጥቃቱ ባለፈው ከነበረው የዘለለ እንደማይሆን መገመት አያዳግትም። አዳዲስ እና አስቸኳይ መረጃዎችን እዚሁ ገፅ ላይ ይጠብቁ! T.me/TheNewsReports

ዓለም ወደለየለት ቀውስ ውስጥ ትገባ ይሆን ? የፍልስጤም እና እስራኤል ጦርነት መቆሚያ ማጣቱን ተከትሎ በየጊዜው አዳዲስ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ ፤ መካከለኛው ምስራቅ እየታመሰ ነው። ምንም ሰላማዊ መፍትሄ በመጥፋቱ አሁንም በጦርነቱ ሰዎች እያለቁ ነው። " ፍልስጤምን አትንኳት " የሚሉና ሃማስን የሚደግፉ ኃይሎችም እስራኤልን በሮኬት / ሚሳኤል መደብደብ አላቋረጡም። ከሰሞኑን ግን በኢራን ቴህራን ውስጥ ለአዲሱ የኢራን ፕሬዝዳንት በዓለ ሲመት የተገኙት የሐማስ የፖለቲካ ኃላፊ እስማኤል ሃኒያ áŠĽáŠ•á‹˛áˆáˆ ከዛ ቀድሞ የሊባኖሱ ሂዝቦላ ቡድን ከፍተኛ አዛዥ ፉአድ ሽኩር መገደላቸውን ተከትሎ የለየለት ውጥረት አይሏል። እስራኤል የሐማሱን ሃኒያን ግድያ ስለመፈጸም ወይም አለመፈጸሟን በይፋ ያለቸው ነገር የለም። ኢራን ግን እስራኤል ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃት ዝታለች። እስራኤልን ክፉኛ ሳትቀጣት አርፋ እንደማትቀመጥ አሳውቃለች። የእስራኤል ባለልስጣናትም የማይቀር ጥቃት ከኢራን እና ከሂዝቦላህ እንዳለ በመናገር መዘጋጀታቸውን እያሳውቁ ነው። አሜሪካም ፤ እስራኤልም በቀጣዮቹ ሰዓታት የኢራን ጥቃት ሊኖር ይችላል የሚል ግምገማ አላቸው። " እስራኤልን ፍጹም አትንኩብኝ " የምትለው አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ እና አካባቢው የተሰማራውን መከላከያዋን ለማጠናከር የጦር መርከቦች እና ተዋጊ ጄቶችን ልካለች። የተላያዩ ሀገራት ለዜጎቻቸው ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ነው። የሚመጣው ነገር ያስፈራልና ከሊባኖስ ለቃችሁ ውጡ እያሉ ይገኛሉ። በተጨማሪም ለጊዜው ወደ መካከለኛው ምስራቅ እንዳይሄዱና አርፈው እንዲቀመጡ እያስጠነቀቁ ናቸው። በአጠቃላይ ያሉት ሁኔታዎች ከባለፈውም ጊዜ በባሰ መልኩ አስፈሪ ናቸው። አንዳንድ ሀገራት ኢራንን " እባክሽ አረጋጊው ! " ብለው ቢማጸኗትም " ቅጣቱ የማይቀር ነው " የሚል አቋም እንደያዘችና ጥቃቱም ከፍተኛ እንደሚሆን እየተነገረ ነው። በሌላ በኩል ፥ ፍልሥጤም ውስጥ በየዕለቱ ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን እስካሁን በ10 ወራት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 39 ሺህ 583 መሻገሩን በጋዛ የሚገኘው ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል። Š Tikvah-Ethiopia @TheNewsReports

#read የሃማስ መሪ ኢስማኢል ሃኒዬህን ለመግደል ፈንጂዎች ከኢስላሚክ አብዮታዊ ጥበቃ ኮርፖሬሽን (IRGC) በተወጣጡ የኢራን ወኪሎች አጥምደው ነበር። ይህ ኦፕሬሽን የተካሄደው በእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ ትእዛዝ መሆኑን ዘ ቴሌግራፍ ስማቸው ያልተጠቀሱ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። ግድያው መጀመሪያ የታቀደው በግንቦት ወር ነበር። ነገር ግን በጊዜው ሃኒዬህ በቀድሞ የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ረዒሲ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ነበሩ። ይሁን እንጂ በቀብር ስነስርዓቱ ላይ ብዙ ሰዎች በመገኘታቸው እቅዱ እንደከሸፈ የጋዜጣው ምንጮች ገልፀዋል። #MOSSAD #IRAN @TheNewsReports

#ጥንቃቄ አዲስ አበባ ከተማ፤ በከባድ የዝናብ ወቅት የተነሳ ምስል @TheNewsReports

#ይህ ጦርነት የእስራኤል-ሃማስ ጦርነት ሳይሆን የአሜሪካ-ሃማስ ጦርነት ነበር መባል የነበረበት። ለዚህም ነው ከተመረጥኩኝ እስራኤልም ሆነ ዩክሬን ጦርነቱን ለራሳቸው እተወዋለሁ ያለው፤ ዶናልድ ትራምፕ
#ይህ ጦርነት የእስራኤል-ሃማስ ጦርነት ሳይሆን የአሜሪካ-ሃማስ ጦርነት ነበር መባል የነበረበት። ለዚህም ነው ከተመረጥኩኝ እስራኤልም ሆነ ዩክሬን ጦርነቱን ለራሳቸው እተወዋለሁ ያለው፤ ዶናልድ ትራምፕ! @TheNewsReports

#BREAKING - የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ የሐማስ መሪ እስማኤል ሃኒዬህ በቆዩበት ቴህራን በሚገኘው የእንግዳ ማረፊያ ሶስት ክፍሎች ውስጥ ፈንጂ እንዲተክሉ የኢራን የደህንነት ወኪሎችን ቀጥሮ
#BREAKING - የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ የሐማስ መሪ እስማኤል ሃኒዬህ በቆዩበት ቴህራን በሚገኘው የእንግዳ ማረፊያ ሶስት ክፍሎች ውስጥ ፈንጂ እንዲተክሉ የኢራን የደህንነት ወኪሎችን ቀጥሮ ነበር። - THE TELEGRAPH T.me/TheNewsReports

አንዲት ሀገር ሉዓላዊነቷ በተነካ ጊዜ ፈጣን ምላሽ እንደምትሰጥ የታወቀ ነገር ነው። ነገር ግን ኢራን ይህ ሉዓላዊነቷ በተደጋጋሚ ሲጣስ ለዚያውም በእስራኤል ከመግለጫ እና ከዛቻ በስተቀር ምንም የሰጠችው ምላሽ አልነበረም። እሱንም እንተወው፤ እንዴት አንዲት ሀገር ዋና ጄነራሏ ሌላ ሀገር ውስጥ ሲገደል ዝምታን ትመርጣለች..? ለዚያውም ሀገሪቷ ኢራን ስትሆን! @TheNewsReports

በባለፈው በአንድ ለሊት ኢራን እስራኤን ከ300 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ሮኬቶቸን ተጠቅማ የመታች እለት አንድም የተጎዳ ወይም የሞተ ሰው አልነበረም። ያ አጋጣሚ ብቻ አልነበረም። @TheNewsReports

#ኢራን እና እስራኤል ሚስጥራዊ ወዳጅ መሆናቸውን ጊዜ ይፋ ያወጣዋል። በነገራችን ላይ ቦምቡ የተተከለው ግድያው ከመፈጸሙ ሁለት ወራት ቀደም ብሎ ነበር ይላል ዘገባው። በዚህም የሃኒዬህ መገኘት ሲረጋገጥ ከርቀት እንዲፈነዳ ተደርጓል። ግድያውም የተፈፀመው በሰሜን ቴህራን በነሻት ግቢ ውስጥ በሚገኝ የእንግዳ ማረፊያ ውስጥ ነው። ከዚህም በላይ የሚገርመው ግቢው የሚመራው እና የሚጠበቀው በኢስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ሰራዊት ነው። #IRAN #HANIYEH @TheNewsReports

#BREAKING - የሃማስ መሪ ኢስማኢል ሃኒዬህ በቴህራን ባረፈበት የእንግዳ ማረፊያ ውስጥ በድብቅ በተጠመደ ፈንጅ መገደሉን ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል። @TheNewsReports
#BREAKING - የሃማስ መሪ ኢስማኢል ሃኒዬህ በቴህራን ባረፈበት የእንግዳ ማረፊያ ውስጥ በድብቅ በተጠመደ ፈንጅ መገደሉን ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል። @TheNewsReports

"የእስራኤል እና የኢራን ወዳጅነት ከአሜሪካ ጋር ካላት ወዳጅነት በላይ እየጠነከረ መጥቷል። @TheNewsReports

#WHEN_THE_GUARDIANS_FAILS_TO_GARD! ፕሮፌሰር መስዑድ አሊ ሙሐመድ - ፊዚስት (QFT)   - በፈረንጆቹ 2010 በቴህራን ሞተር ሳይክሉ ላይ በተጠመደ ቦምብ የተገደለ፤ መጂድ ሻህሪያሪ - የኒውክሌር ኢንጂነር - በፈረንጆቹ 2010 መኪናው ላይ በተጠመደ ቦምብ የተገደለ፤ ፊሪዱን አባሲ - ኒውክሌር ፊዚስት (P) - በፈረንጆቹ 2010 በቴህራን መኪናው ላይ ተወርውሮ በነበረ ቦምብ የግድያ ሙከራ የተደረገበት ነገር ግን አልሞተም። ጄኔራል ሐሰን ቴህራኒ - የኢራን ሚሳዔል ሲስተም አርክቴክት - በፈረንጆቹ 2011 በቴህራን ከሌሎች 17 የአብዮቱ ጠባቂዎች ጨምሮ የተገደለ፤ ዳርዊሽ ሬዚኒጃድ - ፊዚስት - በፈረንጆቹ 2011 በቴህራን ሞተር ሳይክል ላይ ሆነው በመጡ ተኳሾች የተገደለ፤ ሙስጠፋ አሕመዲ - ፕሮፌሰር - በፈረንጆቹ 2012 በቴህራን መኪናው ላይ በተጠመደ ቦምብ የተገደለ፤ ሙሕሲን ፋኺዛዴህ - የኢራን ኒውክሌር ፕሮግራም ዋና ሃላፊ - በፈረንጆቹ 2020 በዳማቫንድ በሪሞት መቆጣጠሪያ ማሽን የተገደለ፤ ሐሰን ሰዒድ ኾዳዒ - የቁድስ ሃይል ኮሎኔል - በፈረንጆቹ 2022 በቴህራን በጥይት የተገደለ ጀነራል ቃሲም ሱለይማኒ - የኢራን ዋና ጄነራል እና የቁድስ ሃይል ዋና አዛዥ - በፈረንጆቹ 2020 በባጝዳድ በድሮን ጥቃት የተገደለ፤ ኢስማዒል ሐኒዬህ - የሃማስ የፖለቲካ ቢሮ ሃላፊ - በፈረንጆቹ 2024 በቴህራን በአየር ጥቃት የተገደለ እና ሌሎችም አሉ። ታዲያ እነዚህ የኢራን ቁልፍ ሰዎች በኢራን መከላከያ ድክመት ብቻ የተገደሉ ይመስላችኋልን..?! #POLITICS #ASSASSINATION #MOSSAD @TheNewsReports

#NEW - ኔታንያሁ፡ "ፈታኝ ቀናት ከፊታችን ይጠብቀናል፤ ለማንኛውም ሁኔታ ተዘጋጅተናል" ኔታንያሁ ስለ ኢስማዒል ሃኒዬህ ግድያ የሰጠው አስተያየት የለም። @TheNewsReports

#JUST_IN - በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ወደ ሊባኖስና ቴህራን በተላኩት መልእክቶች መሠረት ሌላኛው ወገን እስራኤልን ክፉኛ የሚጎዳ ምላሽ ከሰጠ እስራኤል ሁሉን አቀፍ ጦርነት ለማካሄድ ተዘጋጅታለች። ምንጭ፡ N12 of Israel @TheNewsReports

#ALERT 🚨 - የኢራን ጠቅላይ መሪ ኻሜኒ በቴህራን የሃኒዬህ ግድያን ተከትሎ ኢራን እስራኤልን እንድትመታ ትእዛዝ መስጠታቸው ተሰምቷል። - NYT @TheNewsReports

#JUST_IN - ሒዝቡላህ በይፋዊ መግለጫ፦ "የሒዝቡላህ ዋና አዛዥ ፉአድ ሹክር ተገድለዋል" @TheNewsReports
#JUST_IN - ሒዝቡላህ በይፋዊ መግለጫ፦ "የሒዝቡላህ ዋና አዛዥ ፉአድ ሹክር ተገድለዋል" @TheNewsReports

#NEW - ዩናይትድ አየር መንገድ እና ዴልታ ከዛሬ ጀምሮ ወደ እስራኤል የሚያደርጉትን በረራ ሰርዘዋል። @TheNewsReports

#JUST_IN - በቴህራን ተገድሏል የተባለው የሃማስ ፓለቲካ ቢሮ ሃላፊ ኢስማዒል ሃኒዬህ ስለ ጥቃቱ ወይም ስለአገዳደሉ የተለቀቀ አንድም ምስል እስካሁን አልወጣም። @TheNewsReports

ከሶስት ቀን በፊት የዶላር ምንዛሬ ተመኑ 74 ብር የገባው ብር ዛሬ ጠዋት 77 ገብቶ ነበር፣ አሁን ከሰአት ደግሞ በአንድ ግዜ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80 ደርሷል። Just wow! © Elias Mes
ከሶስት ቀን በፊት የዶላር ምንዛሬ ተመኑ 74 ብር የገባው ብር ዛሬ ጠዋት 77 ገብቶ ነበር፣ አሁን ከሰአት ደግሞ በአንድ ግዜ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80 ደርሷል። Just wow! © Elias Meseret