en
Feedback
@hakezel hayat

@hakezel hayat

Open in Telegram

اللهم اجعل القرآن ربيع قلوبنا @abuna124

Show more
3 980
Subscribers
-624 hours
-397 days
-13730 days
Posts Archive
ህያው ቀልብ… አንድ የአላህ ወዳጅ እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ፦ «አንድ ሰው አላህ ዘንድ ቅርብ መሆኑን በምን ያውቃል?» እርሱም እንዲህ መለሰ፦ «ቀልቡ አላህን ሲያስታውስ ይረጋጋል፤ ነፍሱ ከኃጢአት ስትርቅ ደስ ይላታል፤ ከሰዎች ጋር ደግሞ በርህራሄ ይኖራል።» የሰው ሕያውነት ከውጭ አይጀምርም፤ ከቀልብ ውስጥ ይጀምራል። በዚክር ቀልብህን አጽዳ። በተውበት ነፍስህን ያሳርፍ። በርኅራኄህ የአላህን እዝነት ጥራ። በነቢዩ [ﷺ] ፍቅር ምግባርህን አሳምር። በደጋጎች ተረክ መንገድህን አቅና። ትኩረትህን የአኺራ ስኬት ላይ አንጠልጥል። ለምትኖርባት ዱንያም መልካምን አበርክት። አላህ ያግዝህ!

ልክ እንደ ዩሱፍ "ህልሜ እኮ እውን ሆነ" የምንልበትን ቀን ቅርብ ያድረግልን!
ልክ እንደ ዩሱፍ "ህልሜ እኮ እውን ሆነ" የምንልበትን ቀን ቅርብ ያድረግልን!

ባንቱ'ኮ ነው ከጉድ የራቅኩት እንኳን ዲኔን ዱንያን ያወኩት ኑር ዊላዳው ሆኖልኝ ዛዴ ባንቱ አይደሎይ ቆሜ መህዴ🥰

መከራን ያረከሰ ፍቅር… የኡሁድ ቀን ነበር። የጦርነቱ ዜና ወደ ሐምና ቢንት ጀሕሽ [ረዲየላሁ ዐንሃ] መጣ። መጀመሪያ አባቷ ጀሕሽ ኢብኑ ሪአብ መሰዋታቸው ተነገራት። እሷም፦ «ነቢዩስ ﷺ ምን ሆኑ?»
መከራን ያረከሰ ፍቅር… የኡሁድ ቀን ነበር። የጦርነቱ ዜና ወደ ሐምና ቢንት ጀሕሽ [ረዲየላሁ ዐንሃ] መጣ። መጀመሪያ አባቷ ጀሕሽ ኢብኑ ሪአብ መሰዋታቸው ተነገራት። እሷም፦ «ነቢዩስ ﷺ ምን ሆኑ?» ብላ ጠየቀች። ከዚያ ወንድሟ ዐብዱላህ ኢብኑ ጀሕሽ [ረዲየላሁ ዐንሁ] መሰዋቱ ተነገራት። እንደገና፦ «ነቢዩስ ﷺ ምን ሆኑ?» ከዚያ ባሏ ሙስዐብ ኢብኑ ዑመይር [ረዲየላሁ ዐንሁ] መሰዋቱ ተነገራት። አሁንም ጥያቄዋ አንድ ነበር፦ «ነቢዩ ﷺ ምን ሆኑ?!»… በመጨረሻም አጎቷ ሐምዛ ኢብኑ ዐብዱልሙጦሊብ [ረዲየላሁ ዐንሁ] መሰዋታቸው ተነገራት። እሷ ግን እንደገና፦ «ነቢዩስ ﷺ ምን ሆኑ?» ነበር ጥያቄዋ።… ከዚያም የአላህ መልእክተኛ ﷺ በሕይወት እንዳሉና ደህና እንደሆኑ ሲነገራት፣ ወደ እርሳቸው በፍጥነት ሄደች። እርሳቸውን ባየች ጊዜም፣ በአትኩሮት ደህንነታቸውን ተመልክታ ካረጋገጠች በኋላ፦ «كل مصيبة بعدك جلل» «ከእርስዎ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም መከራ ትንሽ ነው።» አለች። እስቲ ይህን ፍቅር አስቡ!… አባቷ ሞተዋል፤ ግን የነቢዩ ﷺ ዜናን ትጠይቃለች። ወንድሟ ሞቷል፤ ግን የነቢዩ ﷺ ዜናን ትጠይቃለች። ባሏ ሞቷል፤ ግን የነቢዩ ﷺ ዜናን ትጠይቃለች። አጎቷም ተሰውተዋል፤ እሷ ግን አሁንም የነቢዩን ﷺ ደህንነት ትጠይቃለች! ነቢዩ ﷺ ደህና መሆናቸውን ባወቀች ጊዜ ብቻ ልቧ እረፍት አገኘ። ይህ ነው የሶሐቦች ፍቅር።… ከምንም በፊት እና በኋላ የሚያስቀድሙት የተወዳጃቸውን ጉዳይ ነበር። …እኛም በተራ እንደ ሶሓቦች አደራ ማለት ይህኔ ነው😊 የነርሱን እድል ይስጠን!

በውሸት በጥፋት በኔነት በስሜት ለጉድ ተከብቤ እንዴት ወዳጆህ ተከታዮ ነኝ እላለው ከልቤ...🤕 ያሻፊየል ሙዝኒቢን
በውሸት በጥፋት በኔነት በስሜት ለጉድ ተከብቤ እንዴት ወዳጆህ ተከታዮ ነኝ እላለው ከልቤ...🤕 ያሻፊየል ሙዝኒቢን

አላህ ሆይ! የተሟላ ኢማንን፣ እውነተኛ እርግጠኝነትን፣ መልካም ሥራን፣ ሰፊ ሲሳይን፣ ላንተ የተዋረደና አንተን የሚፈራ ልብን፣ አንተን በማስታወስ የሚጠመድ ምላስን፣ ሐላልና መልካም ሲሳይን፣ ሁሉንም
አላህ ሆይ! የተሟላ ኢማንን፣ እውነተኛ እርግጠኝነትን፣ መልካም ሥራን፣ ሰፊ ሲሳይን፣ ላንተ የተዋረደና አንተን የሚፈራ ልብን፣ አንተን በማስታወስ የሚጠመድ ምላስን፣ ሐላልና መልካም ሲሳይን፣ ሁሉንም መልካም ነገር የሚያካትት በረከትን፣ የሚስሰማና ተቀባይነት የሚቸረው ዱዓን፣ ደህናና ሰላማዊ ቤትን፣ ጤናማ ሰውነትን፣ መልካም መጨረሻን፣ ጀነትን መታደልና በእሳት ከመቀጣት መዳንን እንለምንሃለን። : አላህ ሆይ፣ ሁሉንም ልመናዎቻችንን በችሮታህ ሙላልን። አሚን።

የወለድ አደገኝነት! ከጃቢር (🤎) ተይዞ:  እንዲህ ይላል፦ ﴿لَعَنَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ آكِلَ الرِّبَا، وَمُؤْكِلَهُ، وَكَاتِبَهُ، وَشَاهِدَيْهِ. وَقَالَ : " هُمْ سَوَاءٌ﴾ “የአላህ መልእክተኛ (🤎) ወለድ የሚበላንም፣ የሚያበላውንም፣ ፀሐፊውንም፣ ምስክሮቹንም ተራግመዋል፡፡ ‘ሁሉም በወንጀሉ እኩል ናቸው!!’ ብለዋል፡፡” ሙስሊም ዘግበውታል: 1598

ያልፉ ይሆን ብለን ስንሰጋባቸው የነበሩ ቀናት ሁሉ ኮሽ ሳይሉ እንደዋዛ አለፉ። አልሐምዱ ሊላህ❤️‍🩹

የታላቁ ነቢይ (📿) ስብዕና! ረሱል እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لَوْ دُعِيتُ إِلَى كُرَاعٍ لَأَجَبْتُ، وَلَوْ أُهْدِيَ إِلَيَّ ذِرَاعٌ لَقَبِلْتُ﴾ “በእንስሳ (በበግ እግር የተዘጋጀ መጠነኛ ግብዣም ቢሆን) ብጠራ ኖሮ እቀበል ነበር፤ ክንድም (ስጦታ) ቢበርከትልኝ ኖሮ በእርግጥም እቀበል ነበር።” ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 5178

የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ يا عَائشةُ، لا ترُدِّي المِسكينَ ولو بشِقِّ تَمرةٍ، يا عائشةُ، أحِبِّي المساكينَ، وقَرِّبيهم؛ فإنَّ اللهَ يقرِّبُكِ يومَ القيامَةِ. "ዓኢሻ ሆይ! ምስኪንን (ባዶ እጁን) አትመልሺ፣ የአንድን ተምር ግማሽ እንኳ ቢሆን (ስጪ)። ዓኢሻ ሆይ! ምስኪኖችን ውደጂ፣ አቅርቢያቸውም፤ አላህ በቂያማ ቀን ያቀርብሻልና።" [ሶሒሑ ቲርሚዚይ፡ 2352]

ሀራም ግንኙነት....ልብህን ለማስደሰት ብለህ ከ አላህ ሚያርቅህን ግንኙነት አትያዝ ። ዛሬ የሚያስደስትህ ነገር ነገ ልብህን ሊሰብረው ይችላል። ...ከሀራም መራቅ ማለት ፍቅርን መጥላት ማለት አይደለም ፣ ፍቅርህን ለ አላህ ስትል መጠበቅ እንጂ 🤌 وَلَا تَقْرَبُوا۟ ٱلزِّنَىٰٓ ۖ إِنَّهُۥ كَانَ فَٰحِشَةًۭ وَسَآءَ سَبِيلًۭا "እናንተ ወደ ዝሙት አትቅረቡ ፣ እርሱ በርግጥ አፀያፊ ነው።" (17:32)

❤ስለ ፍቅር ከተነገሩት በጣም ቆንጆ ነገሮች ዉስጥ አንዱ የሰይድና አቡበክር (ረ.ዐ) አባባል... "ረሱል(ﷺ) ጠጡ እኔም በሳቸዉ መጠጣት ጠገብኩ" اللهم صلِ وسلم وبارك عل نبينا مُ
❤ስለ ፍቅር ከተነገሩት በጣም ቆንጆ ነገሮች ዉስጥ አንዱ የሰይድና አቡበክር (ረ.ዐ) አባባል... "ረሱል(ﷺ) ጠጡ እኔም በሳቸዉ መጠጣት ጠገብኩ" اللهم صلِ وسلم وبارك عل نبينا مُحَمَّد (ﷺ)

እልፍ ዘመናት ስሙ ተወስቶ የማይደበዝዝ ታሪኩ አርጅቶ መርሀበን ያ ረሱሉላህ 💚መርሀበን...አንቱዬዋ!💙 مَرْحَبًا يَا رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّم
እልፍ ዘመናት ስሙ ተወስቶ የማይደበዝዝ ታሪኩ አርጅቶ መርሀበን ያ ረሱሉላህ 💚መርሀበን...አንቱዬዋ!💙 مَرْحَبًا يَا رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ 🥰🥰🥰

ነቢን መውደድ ኢማን ነው ነቢን ማውሳት ሁብ ነው ሰለዋት ማውረድ ኑር ነው" ሶሉ አለል ሀቢቢ!
ነቢን መውደድ ኢማን ነው ነቢን ማውሳት ሁብ ነው ሰለዋት ማውረድ ኑር ነው" ሶሉ አለል ሀቢቢ!

💚✨እንኳን ለታላቁ ነቢይ ሙሐመድ ﷺ የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ💚🙌 ይኸው ታላቅ ቀን የሰላም እና የፍቅር ይሁንልን። ✨ የረሱል ﷺ  መወለድ ለዓለማት እዝነት እና ብርሃን ነው! 💚 መልካም የመውሊድ በዓል🥰🥰🥰 🎉ኢሽቅ መደድ👏👏👏👏👏👏

እንኳን ለ1501ኛው የትልቁ ሰው ﷺ የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
እንኳን ለ1501ኛው የትልቁ ሰው ﷺ የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ يا عَائشةُ، لا ترُدِّي المِسكينَ ولو بشِقِّ تَمرةٍ، يا عائشةُ، أحِبِّي المساكينَ، وقَرِّبيهم؛ فإنَّ اللهَ يقرِّبُكِ يومَ القيامَةِ. "ዓኢሻ ሆይ! ምስኪንን (ባዶ እጁን) አትመልሺ፣ የአንድን ተምር ግማሽ እንኳ ቢሆን (ስጪ)። ዓኢሻ ሆይ! ምስኪኖችን ውደጂ፣ አቅርቢያቸውም፤ አላህ በቂያማ ቀን ያቀርብሻልና።" [ሶሒሑ ቲርሚዚይ፡ 2352]

ሰይደል‐ኸልቅ ﷺ ለወዳጆቻቸው እንደ ቅድመ ጀነት ናቸው ፤ ያን የወዳጅነት ጀነት ጥፍጥናውን የቀመሰ‐የለመደ ለቅፅበት ቢያጣው እራሱን በጥፋት አንዳጣ ይቆጥራል። አቡል‐ዓባሰል‐ሙርሲይ "ነብዩﷺ ለቅፅበት ከኔ ቢሰወሩ በሞትኩ ነበር" እንዳሉት መሆኑ ነው።   ሰይዳችንﷺ ለሁሉም አፍቃሪ አዘቦት የሌለው የዘውትር ዒዱ ናቸው። ሼህ አሕመድ ሲራጁዲን ኸይረል‐ወራ ላይ جنة الأحباب عيد كل عاشق «የወዳጆች ጀነት ፤ የአፍቃሪ ሁላ ዒድ» ይሏቸዋል።    ከፍቅሩ ጨፌ አንዴ የተጎነጩት አሕመደል ሃዲ እየተንሰፈሰፉ… አፍቃሪን ሊያንሳፍፉ "ትልቁ የአላህ ጀነት" ይሏቸዋል كيف لا وهو سباني ۔ وجنة الله الأعظم በዛ ፍቅር ተማርኮ የተጠለፈ ማረፊያው ሚሆነው ትልቁ የአላህ ጀነት (ሰዪደል‐ዉጁድ) ውስጥ ነው። ረቢዑልቁሉብ

ብዙ ያለኝ ሚመስለኝ በራህመትህ ምኖር እኔ ያንተ ለማኝ ነኝ❤️‍🩹

እስልምናን ሚአክል ወርቃማ የእምነት እርከን ላይ ሆነን ከእስልምና ወጣ ያለ መንገድ ላይ መገኘት... ነገ እንስተካከላለን እያልን ዛሬአችንን ማጨለም.... ምናልባትም ነገ ብለን ቀን የቀጠርንለት ቀን የሞታችን ድግስ ሊሆን ይችላልና ነገ ማለቱን"ሟች ነኝ" በሚል መሪ ቃል ጭንቅላታችን ላይ እናስቀምጠው እና ከዛሬም አሁንን እናሳምር። ምንአልባት ነገ አንተ የለለህበት ቀን ይሆናል እናም አሁንህን ወርቅ ቀባ!😊 ያረብ በሰጠከኝ ሽልማት ይበልጥ ማምርበት አድርገኝ🤲🖤