cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ካቦድ የኪነ ጥበብ ቤተሰብ🎭🎭

‹‹ ለተጠሩት ግን…የእግዚአብሔር ሀይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነዉ ክርስቶስ ነዉ፡፡ ›› 1ኛ ቆሮ 1፤26 በመንፈስ ቅዱስ እየተመራን ጠቢብ የሆነዉን ክርስቶስን በጥበብ እንገልጣለን፡፡ ከሥነ ፅሁፍ ወደ ኪነ ጥበብ! ማንኛዉንም ጥያቄና አሰተያየት ካላችሁ በዚህኛዉ በ @kabodartfamily_bot ላይ ማቅረብ ትችላላችሁ።

Show more
Advertising posts
233
Subscribers
No data24 hours
-77 days
+830 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
ተደርጎልኝ ነው ምህረት በዝቶልኝ ድንቅ ልብን የሚነካ ቀጥታ ከሰማይ የተቀዳ ድንቅ መዝሙር ነውና አንድትሰሙት ዘንደሰ ግብዣችን ነው @kabodartfamily @kabodartfamily
270Loading...
02
https://youtube.com/shorts/Uq2Ji4EntmI?si=jkPqKLWcSVaDYPxb
260Loading...
03
https://youtu.be/sGYTtjJWHj0?feature=shared
240Loading...
04
Media files
321Loading...
05
ድብቁ ድል በኢትዮጵያ ✍️ by Abate the great presented by #KABOWDARTFAMILY ክፍል 11 "ቆራጡ ታደሰ ~1~" ¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤ በተገደሉ ወይም በተፈቱ እስረኞች ምትክ አዳዲስ እስረኞች መተካት ጀምረዋል። በዚህ ሁኔታ ከተተኩት አንዱ ከጋሞ ጎፋ የመጣው ወጣት ታደሰ ነው። ታደሰ በቁመቱ ከንጉሤ እምብዛም አይልቅም። የታሰረው በአዲስ አበባ ጎዳናዎች እየተዘዋወረ ክርስታነዊ ፅሁፍ በማሰራጨቱ ነው። በነበረበት የአገሪቱ ደቡብ ክፍል ያሉ ክርስቲያኖች ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ይልቅ እስራትና ስደት ደርሶባቸዋል። የሻሸመኔው አሊ ሙሳ ግን ከሌሎች ባለስልጣናት ይልቅ ክርስቲያኖች ላይ ሳይከፋ አይቀርም። ሻሸመኔ ውስጥ ሰዎችን በሕይወት ሳሉ ቀብሯቸዋል። የሻሸመኔው የስጋ ደዌ ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶክተር ሙላቱ ከጅምላ ጭፍጫው ያመለጡት ለጥቂት ነበር። የጋሞ ጎፋው ተወላጅ ታደሰ በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት አምኖ ክርስቲያን የሆነው ገና በለጋ ወጣትነቱ ነው። ብዙም ሳይቆይ በአከባቢው በነበሩ ሰዎች ላይ ክርስቲያናዊ ተጽዕኖ ማሳደር ጀመረ። በየገጠሩና በየገበያው እየተዘዋወረ ስለ ክርስቶስ በመመስከር ብዙ ሰዎችን ክርስቲያኖች አድርጓቸዋል። ወጣቶችን እያደረጀ በማስተማር ኃይል የተሞላውን የክርስቶስ የምስራች ለሌሎች እንዲየዓዳርሱ አበረታታቸው። ይህ የ15 ዓመት ለጋ ወጣት በድርጊቱ ማርክሲስቶችን አበሳጫቸው። ለአብዮታዊ ዓላማቸው ሊመለምሉ ያሰቧቸውን ወጣቶች እንዴት እያደረገ ነው የሚያሳምናቸው? ማለትን ጀመሩ። ታደሰ ለሚሰማው ሁሉ ሕያው ስለሆነው ኢየሱስ መመስከሩን ገፋበት። በዚህ ድርጊት የተበሳጩት ማርክሲስቶች...... ይቀጥላል .... @kabodartfamily @kabodartfamily
380Loading...
06
ድብቁ ድል በኢትዮጵያ ✍️ by Abate the great presented by #KABOWDARTFAMILY ክፍል አስር  ደብዳቤ በደረሳት ጊዜ ፈራች። ሆኖም መርማሪዎችኣ ካቀረቡላት ጥያቄ አንፃር ንጉሴ ላይ ክስ ለመመስረት የሚያስችል ማስረጃ አለማግኘታቸውን ተረዳች። ይህም ስጋትዋን አቀለለው። የንጉሴ ከሳሾችም «በሲ አይ ኤ ወኪልነት መጠርጠር» ብለው ብለው ክሳቸውን አቀለሉት።» ይሄም ክስ ቢሆን መሰረት አልነበረውም። ለማስረጃነት የቀረቡት ደብዳቤዎች ከአብሮ አደጉና ከወዳጁ ጆን ጋር ለረጅም ጊዜያቶች የተለዋወጣቸው ደብዳቤዎች ነበሩ። የንጉሴና የእስር ቤት ጓደኞቹ ዕለታዊ መከራ በቂ አየር በሌለበት ጠባብ ክፍል ውስጥ መታጎራቸውና የመታጠቢያ ውሃ አለማግኘታቸው ነበር። እስረኞቹ ከጠባቧ ክፍል የሚወጡት በተወሰነላቸው ጊዜ ወደ መፀዳጃ ቤት ሲሄዱ ብቻ ነበር። ሌሊት የሚርመሱት አይጦች ደሞ የእስረኞችን እረፍትና ሰላም ይነሳሉ። በመጨረሻም ንጉሴ ስድሳዎቹ የቀድሞ መንግስት ባለስልጣናት ወደ ተረሸኑበት ወደ ዋናው ወኅይኒ ቤት ተላከ።  ጠያቂዎች በተወሰነላቸው በሽቦ አጥር የታጠረ ስፍራ ሆነው እስረኞች ደግሞ በሌላ ወገን ተሰብስበው ጎብኚ ዘመዶቻቸውን በጉጉት ሲጠባበቁ ፋንታዬ ተመለከተች። በዚህ መኃል ነው የንጉሴን እህት አልማዝን ያየቻት። እንዳትታይ ፈጠን አለችና ወደ ኋላ አፈገፈገች። የቆመችበት ሆና አልማዝን በዓይኖቿ ተከታተለቻት። ወሊሶ ከተገናኙ ወዲህ ፋንታዬ ንጉሴን እንደገና አየችው። ልቧም በደስታ ሰከረ። አልማዝ ንጉሴን አነጋግራና የያዘችለትን ሰጥታው ስትመለስ ፋንታዬ እንድትታይ ወደ ፊት ራመድ ብላ የያዘችውን ፍራፈሬ ወደ ላይ ከፍ አድርጋ ያዘች። ንጉሴ ፋንታዬን አያት! ለአንድ አፍታ ትንፋሹ በደስታ ብዛት ቁርጥ አለ። ያን ዕለት የተፈጠረበትን ስሜት ምንጊዜም አይረሳውም። የወሰደችውን ፍራፍሬ በመካከላቸው ባለው የሽቦ አጥር ላይ ተንጠራርታ ሰጠችው። ሰው ከሚያየው ምግብ የበለጠ ነገር ነበር የተከዋወጡት። ከዚያን እለት ጀምሮ ንጉሴ በጉጉት የሚጠብቀው በየሳምንቱ እሁድ ለአጭር ጊዜ የሚኖራቸውን መተያየት ሆነ። ያኔ አይኖቻቸውና ልቦቻቸው ይገናኛሉ፤ ለጥቂት ጊዜ ይነጋገራሉ። አንዳቸው ስለሌላው በሕይወት መኖር እርግጠኖች ይሆናሉ። ንጉሴ እስር ቤት ውስጥ በቆየባቸው ጊዜያት የመፈታት እድል ካልገጠማቸው ሰዎች ጋር በሞት ጥላ ስር  ተጉዟል አንድ እስረኛ ንጉሴ በቅንነትና በተደጋጋሚ የነገረውን የሕይወት ቃል አልቀበልም «እምቢ» በማለት ለረጅም ገዚ ቆየ። ሰላም የለውም፤ የራሱን ተስፋ ቢስ ሁኔታ የንጉሴ ህይወት ከሚገልፅለት እውነት ጋር ያነፃፅር ጀመር። በመጨረሻ ግን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ማመንን በመምረጡ በእስረኛው ሕይወት ታላቅ ለውጥ ይታይ ጀመር። እንዲያ ባለ ሁኔታ ውስጠዕ ሳለ ይገጥመኛል ብሎ ያላሰበውን ሰላም አገኘ። ዘግየት ብሎ ወዳመነበት ጌታ የሚሰበሰብበት ሰዓት ደረሰ። እንዲረሸን ተወሰነ። አዲስ ጓደኞቹ ወደ ሆኑት ክርስቲያኖች ሄደና «ልገደል ነው። ቢሆንም የምሄድበትን ስለማውቅ የሚደንቅ ሰላም አለኝ» አላቸው። ይህን ከነገራቸው በኋላ እንደሚገናኙ ተስፋ በማድረግ አቅ ፎ ሳማቸውና ወደ መገደያው ስፍራ አመራ። . . . . ይቀጥላል.... @kabodartfamily @kabodartfamily
470Loading...
07
መጽሐፍ ቅዱስ በራስ መታመንን ሳይሆን በክርስቶስ ብርታት መታመንን ይናገራል። ሰዎች እንደመሆናችን መጠን የአቅማችንን መገደብ መቀበል አለብን፣ እና የኢየሱስ ኃይል በእኛ እንዲሠራ  መፍቀድ አለብን። ከዚያም ፍርሃትን በጠንካራ እምነት እና ድካማችንን በኃይሉ እንተካለን። በክርስቶስ ከአሸናፊዎች በላይ ነን።  አምላክ እያንዳንዱን እርምጃችንን እንደሚረዳ እርግጠኞች እንሁን። @kabodartfamily @kabodartfamily
460Loading...
08
ብቻ እየሱስ ቤቴ ካለ ሙሉ ነው ይበቃኛል ።
520Loading...
09
ድብቁ ድል በኢትዮጵያ ✍️ by Abate the great presented by #KABOWDARTFAMILY ክፍል ዘጠኝ "ከፀጋ ወደ ፀጋ" ¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤ ፋንታዬ «ንጉሤ በተከሰሰበት ነገር ይግባኝ ስለጠየቀ ወደ አዲስአበባ አዛውረውታል» የሚለውን ዜና በሰማች ጊዜ አንዳች ነገር ልቧን አዘለለው። ለእግዚአብሔር እየነገረች ሸክሟን ብቻዋን ነበር የተሸከመችው «እኔ ያለሁት ከተማ ውስጥ ነው፤ ሴቶች ደግሞ ለእስረኛ ዘመዶቻቸው በየቀኑ ምግብ ይወስዱላቸዋል። በድብቅም ቢሆን እኔም እሄዳለሁ።» አለች ለራሷ። ካድሬዎች አዲስ የምርመራ ዘዴ በመጀመራቸውና ሕጋዊ አሰራርም እየጠፋ ስለሄደ ጉዳዩን በይግባኝ ወደ ማዕከላዊ መንግስት መውሰዱ የተሻለ ጥበብ ነው ብሎ ንጉሴ ወሰነ። በዚህም ምክንያት ነበር በጥር 1971 ዓ.ም ንጉሴ ወደ አዲስአበባ ተዛውሮ ፒያሳ አከባቢ በሚገኘው ማዕከላዊ እስርቤት ውስጠዕ እንዲቆይ የተደረገው። ማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ የሚከናወነው ግርፋት ቀለል ያለ ቢሆንም ጥበቃው ግን የሚያፈናፍን አይደለም። ንጉሴን ለመጎብኘት ወደዚያ መሄዱ የሚያስጠርጥር መሆኑን ፋንታዬ ተገነዘበች። በንጉሤ ላየዕ ከቀረቡት ክሶች መሃል «ሚስቱ፣ እህቱ፣ እናቱ ወይም አክስቱ ካልሆነች ሴት ደብዳቤዎች ይላኩለታል» የሚል ነበረ። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፋንታዬን ከአዲስአበባ ውጭ በሸዋ ክፍለሀገር ቡታጅራ ውስጥ መደባት። ፒያሳ በሚተራመሰው ሕዝብ መሀል ሆና አሳቧ ሁሉ ንጉሴ ወደታሰረበት አስርቤት ይሄድ ነበረ። ወደ እስር ቤቱ ለመሄድ በተነሳች ቁጥር ወሊሶ ሳለች ፀጥታ አስከባሪዎች «ይጠይቁሽ ይሆናል ተዘጋጂ » ብሎ ንጉሴ የነገራት ነገር ትዝ ይላታል እናም ወደ እስርቤቱ ሄዳ ነገሮችን ከማወሳሰብ ብላ አስር ቤቱን በሩቁ መመልከት ምርጫዋ አድርጋለች። እንደጠረጠችው ለጥያቄ የምትፈለግ መሆኗን የሚገልጠው የጥሪ ደብዳቤ በደረሳት ጊዜ ፈራች። ይቀጥላል ........ @kabodartfamily @kabodartfamily
600Loading...
10
ጥቂት ቆይታ አገልጋይ በሱፍቃድ ደሳለኝ || Besufekad Desalegn || Bishoftu Emmanuel Unit... https://youtube.com/watch?v=Q-R_29jsbnY&si=hD2OD4oHIcErHhfz
600Loading...
11
ድብቁ ድል በኢትዮጵያ ✍️ by Abate the great presented by #KABOWDARTFAMILY ክፍል ስምንት ....ሲደበድበው ቆይቶ ሲደክመው ጊዜ ንጉሴ አፍ ውስጥ የነበረውን ጨርቅ አወጣና ለማመን ተዘጋጅተሃል?» አለው የውስጥ እግሮቹ ደም የቋጠሩት ንጉሤ እንደ ማቃሰት አለና «ስለጌታዬ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመሞት ዝግጁ ነኝ ብትፈልግ ስጋዬን እየቆራረጥክ ለአሞራ ስተው እንጂ ጌታዬን አልክድም።» አለ በዚህ ንግግሩ የተናደደ ሌላ ካድሬ የንጉሴን ራስ እንደኳስ ይረግጠው ጀመር። ገራፊው ደግሞ የገመዱን ጫፍ በንጉሴ ጣቶች መካከል አስገብቶ በማቁሰል ኃይል ሳበው። የአውራ ጣቶቹን ጥፍርም ነቀላቸው። ከዚያም የተቋጠረው ደም እስኪፈነዳ ድረስ እንደገና በዱላ ይደበድበው ጀመር። ሰውነቱ በደም ረጠበ። ካድሬው በሰይጣናዊ ንዴት መቀጥቀጡን ሲቀጥል፤ ሌሎቹ ገራፊዎች ንጉሤን ይሞት ይሆናል ብለው ሰጉ። በጨለማ የሚቀብሩት እሬሳ እንዲኖር አልፈለጉም። የንጉሤ እግር ግነድ እስኪያህል ስላበጠ ካድሬው መደብደቡን አቆመ። የተቀጠቀተው ንጉሤ ህሊናውን ወደ መሳቱ ተቃርቧል፤ ለመቆም አልቻለም። በመሆኑም በሸክም ወስደው እስር ቤቱ ወለል ላይ ጣሉት። ንጉሤ አሳቡን አዳኙ ላይ ባደረገ ጊዜ ነፍስና ስጋው እንደገና አነሰራሩ። መራመድ ሳይችል ለብዙ ሳምንታት ቆየ። በታሰረበት ጽዳር የለሽ እስር ቤት ውስጠዕ እያለ ወደ ሽንት ቤት እንኳን የሚሄደው በሸክም ነበር። ለመግለጠዕ የሚያዳግት መከራ ደረሰበት። ሊጎበኘው የሚመጣ ወዳጁ እንኳን ከአጥር ቆሞ በጎበጠው ወገቡ ካልሆነ በቀር ሊለየው አይችልም ነበር። ንጉሤ በግርፋቱ ጊዜ በተዓምራዊ መንገድ ሕመሙ እንዳይሰማው የተደረገለት መሆኑን እንዲህ ብሎ ነበር የመሰከረው «የሞትኩ መስሎኝ ነበር፤ አምላኬ ግን እንድኖር ፈለገ።» ንጉሴ እንደምንም ብሎ የት መሆኑን የሚገልጥ ደብዳቤ ለፋንታዬ እንዲደርሳር አደረገ። እርሷም እንደርሱ ታስራ እንደነበር አላወቀም። ፋንታዬ የት መሆኑን በማወቋ እፎይታ ቢሰማትም ያለበትን ቦታ ስትረዳ ግን ተሸማቀቀች። ምቹ ሀኑታ እንደተፈጠረላት ፍራፍሬዎችን ይዛ በምስጢር ወደ ወሊሶ ተጓዘች። እስር ቤቱ ስትደርስ ንጉሤ መኖሩን ቢገልጡላትም ከእርሱ ጋር መገናኘቱን አልፈቀዱላትም። ምርር ብላ እያለቀሰች «ወንድሜ ነው ሳላየው አልሄድም» አለችና ለመነቻቸው በመጨረሻም ፋንታዬ ንጉሴን ለአምስት ደቂቃ ያህል እንድታናግረው ፈቀዱላት። ንጉሴ ፋንታዬን ሲያያት ትዕይንቱን ማመን አቃተው። ከደስታው የተነሳ አለቀሰ። ከመለያየታቸው በፊት «ሊጠይቁሽ ይፈልጋሉ ተዘጋጂ» አላት በሽክሹክታ። በተፈቀደላቸው አጭር ጊዜ ውስጥ የተነጋገሩትና ስለደረሰበት ስቃይ የተረዳቸው ነገር ብዙ ሁኔታዎችን አስገነዘቧት። በደረሰበት መጎሳቆል አዝና ልትረዳው ባለመቻሏ  ልቧ ቆስሎ ከእስር ቤቱ ቅጥር ግቢ በመውጣት በፍጥነት ወደ አዲስ አበባ ተመለሰች። አለሁልሽ የሚላትና የሚረዳት አልነበረም። ለማድረግ የምትችለው የልቧን ሀዘን የልብ ወደጇ ለሂነው ጌታ መንገርና መጠበቅ ብቻ ነበር ...... ይቀጥላል ... @kabodartfamily @kabodartfamily
690Loading...
12
ድብቁ ድል በኢትዮጵያ ✍️ by Abate the great presented by #KABOWDARTFAMILY ክፍል ሰባት ....አሁን ግን "ፀረ አብዮታዊ "ዝንባሌ ያለውን ሰው የሚደብቅ ፖለቲካዊ ተቋም እንደሆነ ተቆጥሯል። ንጉሤ በታሰረበት ምሽት አሳሪዎቹ ወንዝ ያሻገሩት የወደቀን ግንድ እንደ ድልድየዕ በመጠቀም ነው። በጊዜው የእጅ ባትሪ የዕዞ የተገኘው ንጉሤ ብቻ ነበር። እርሱ እያበራላቸው ነበር ሌሎቹ አንድ በአንድ በግንዱ ላይ የተሻገሩት። ከከሳሾቹ መሀል አንድ በእድሜ ጠና ያሉ የኦርቶዶክስ ቄስ ነበሩ። ንጉሤ ባትሪውን እያበራ አሻገራቸው፤ በኢትዮጵያዊ ባህል መሰረት ለአንድ በዕድሜ ለሚልቅ ሰው ሊሰጥ የሚገባን ክብር ሰጣቸው። በማግስቱ ቄሱ ንጉሤ ያለበት እስር ቤት ድረስ በመሄድ የከሰሱት በስህተት መሆኑንና በእስራቱ ወስጥ እጃቸውን በማስገባታቸው ማዘናቸውን ገልጠው ይቅርታ ጠየቁት። ቄሱ ክሳቸውን ቢተውም የወሊሶ አከባቢ አስተዳደር ግን ንጉሤን መቀጣጫ ሊያደርገው ወሰነ። ንጉሤ በቀረበባቸው የአውጃው ቢሮዎች ሁሉ ከውጭ መንግስት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ገልጦ የእግዚአብሔር መንግስት አባል መሆኑን ግን አረጋገጠ «ይህን መጤ ኃይማኖት ብታስተባብል ትፈታለህ።» አሉት «ጌታዬን ከምክድ ሞቴን እመርጣለሁ» ብሎ መለሰ በድፍረት ንጉሤን የሚመረምሩት መርማሪዎች ወፍራም እንጨት የተጋደመባቸው ሁለት ጠረጴዛዎች ወዳሉበት ክፍል ወሰዱት። እንደደረሱም ለተለመደው ግርፊያቸው ያዘጋጁት ጀመር። መጀመሪያ ሁለት እግሮቹን አጣመሩና ቁርጭምጭሚቱ ላይ አሰሩት። ቀጥሎ ደግሞ እጆቹን ወደፊት አጣምረው አሰሩና አስጎንብሰው ከቁርጭምጭሚቱ ጋር ጠፈሯቸው። ከዚህ በኋላ ስራውን ለመጀመር የተዘጋጀ ገራፊ ቡድን አባላት እንዲናገር የመጨረሻ እድል ሰጡት። የፈለጉትን ስላላገኙ የተጠቀለለ ጨርቅ አፉ ውስጥ ጠቀጠቁና «የምትናገረው ነገር ሲኖር ከእጆችህ ጣቶች አንዱን ታሳየናለህ። ግርፊያውን የምናቆመው ስታምን ብቻ ነው።» አሉት ገራፊዎቹ ወፍራሙን እንጨት ተጣምረው በታሰሩት እግርና እጆቹ መሃል አሳለፉና በዚያ ከግራ ከቀኝ በያዝ አንስተው የእንጨቱን ጫፍና ጫፍ ጠረጴዛዎቹ ጠርዞች ላይ አሳረፏቸው። በዚህ ጊዜ ንጉሴ እራሱ ወደመሬት እግሮቹ ደግሞ ወደላይ ሆኑና ተንጠለጠለ። ከወታደሮቹ ባለማዕረግ የሆነው ሰው ወደ ላይ የተገለበጡትን የንጉሤን የውስጠዕ እግሮች በዱላ ይመታቸው ጀመር። ሲደበድበው ቆይቶ ሲደክመው ጊዜ ንጉሴ አፍ ውስጥ የነበረውን ጨርቅ አወጣና ........ ይቀጥላል ..... @kabodartfamily @kabodartfamily
760Loading...
13
ግራ ቀኝ በማየት ትጥቅሽ አይላላ የልቦናሽ አይኖች አይሂዱ ወደሌላ ኢየሱስን ይዞ ከቶ ማነው ያፈረው ስፍራውን ለቆ እንጂ ሰነፍ የከሰረው🙏🥰
720Loading...
14
ያየሁህ  እለት አንተን ፊት ለፊት እንዴት እንደሚሆን ባላውቅም ደስታዬ ፍፁም ይሆናል 😭😭 ህይወቴም ፍፁም ይሆናል😭😭 የኢየሱስ ዳግም መምጣት አይናፍቃችሁም? ማራናታ !!!!! @kabodartfamily @kabodartfamily
761Loading...
15
ኢየሱስ በቀራንዮ የጀመረው ፤ እኛ የምንጨርሰው ደህንነት የለም። ኢየሱስ ከፍሎ ጨርሶታል ። @kabodartfamily @kabodartfamily
1100Loading...
16
ይቀዳ መልዕክቴ ለትውልድ ይለፍ እንደምትረዳ እንደምታሳርፍ ይፃፍልኝ ቃሌ ይተረክ ለሌላ የህይወት ቃል እንደሆንክ እንደምትበላ
991Loading...
17
ድብቁ ድል በኢትዮጵያ ክፍል ስድስት "የመከራው ጅማሬ - በወጥመድ መያዝ-" «ስለጌታዬ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመሞት ዝግጁ ነኝ ብትፈልግ ስጋዬን እየቆራረጥክ ለአሞራ ስተው እንጂ ጌታዬን አልክድም።» ¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤ ንጉሤ ጊንዶ ወደተባለው አዲስ ስፍራ ከሄደ ስድስት ወር ሆኖታል። በዚህም ምክንያት ለፋንታዬ ደብዳቤ ሊልክላት አልቻለም። ንጉሤ አዲስ አበባ ውስጥ ከፋንታዬ ትራክቶችና በኪስ የሚየዓዙ አዲስ ኪዳኖችን ተቀብሎዋት ነበር ወደ ወሊሶ ያመራው። ወሊሶ ጊንዶ እያለ አንድ ቀን ማታ ሁለት ተማሪዎች ወደርሱ መጡ። ሻይ ከተጋበዙ በኋላ የወንጌልን የምስራችና የራሱን ምስክርነት ነገራቸው። ሁለት አዲስ ኪዳን መፃህፍት ሲሰጣቸው በጉጉት ነበር የተቀበሉት። ወዲያው ሁለት መምህራን መጥተው «ለሁለቱ ተማሪዎች እንደሰጠሃቸው ለእኛስ ለምን አዲስ ኪዳን አትሰጠንም?» አሉት በወቅቱ መምህራን አብዮቱን የሚቃወመውን ወይም በሙሉ ልቡ የማይደግፈውን እንዲያጋልጡ ጫና ይደረግባቸው ነበር። በዚሁ መሠረት በሚቀጥለው አርብ በተደረገው ፖለቲካዊ ሰልፍ ላይ ሁለቱ መምህራን «መጤ ኃይማኖት ያስፋፋል» ብለው ንጉሴን ከሰሱት። የክሳቸው መነሻ «አዲስ ኪዳን የማደል ፀረ አብዮታዊ ድርጊት» የሚል ነው። ካድሬዎች ንጉሴን እየገፈታተሩ ወደ እስር ቤት ወሰዱት። የፋንታዬና የጆን ደብዳቤዎች ያሉባቸውን እቃዎቹንም በረበሩት። ወሊሶ ወደሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ በተላከ ጊዜ ምንም እንኳን ጆን ካናዳዊ እንጂ አሜሪካዊ ባይሆንም ደብዳቤዎቹ «ከአሜሪካን የስለላ ድርጅት ጋር ግንኙነት» ያለው መሆኑን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ሆኑ። የፋንታዬ ደብዳቤዎች «ግብረገባዊ ባልሆነ መንገድ ከሴት ጋር መገናኘት» ብለው ለመሠረቱት ክስ ማረጋገጫዎች ሆነው ቀረቡ። ይህ ሁሉ ለፖለቲካዊ ክሳቸው ማጠናከሪያ የሚሆን ስም ማጥፋት ነበር። «ጴንጤነቱም» ከወንጀሎች አንዱ ሆኖ ተመዘገበ። «ጴንጤነት» ከአብቱ በፊት የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች መለያ ስም የነበረ ቢሆንም አሁን ግን «ፀረ አብዮታዊ» ዘንባሌ ያለውን ሰው የሚደብቅ ፖለቲካዊ ተቋም እንደሆነ ተቆጥሯል። ይቀጥላል..... @kabodartfamily @kabodartfamily
1070Loading...
18
እነሆ አዲስ😊😊 👉 በአባቴ አበራ አዘጋጅነት እና በ @kabodartfamily አቅራቢነት በሳምንት ሁለቴ ሲቀርብላችሁ የነበረው "ድብቁ ድል በኢትዮጵያ "የተሰኘው ፅሑፍ በብዙዎቻችሁ ዘንድ ተወዳጅነትን ማትረፉን ፤ በብዙ እየተማራችሁ ደግሞም ለካ እንዲህ አይነት ነገርም አለ?ብላችሁ እየተደነቃችሁ መሆኑን በውስጥ መስመር እንደነገራችሁን የሚታወስ ሲሆን አንዳንዶቻችሁ ደግሞ ለምን በየቀኑ አይለቀቅም? ብላችሁ ጠይቃችሁናል።እኛም ስለ ሀሳብ አስተያየታችሁ እያመሰገንን አንድ ደስ የሚል ዜና ይዘንላችሁ ከተፍ ብለናል። እሱም ማክሰኞ እና ሐሙስ እየቀረበላችሁ የነበረውን ከዚህ በኋላ በተከታታይ ከሰኞ እስከ አርብ እንደምንልክላችሁ ስንገልጽ ታላቅ ደስታ ይሰማናል!! ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ @zogracia በኩል ማቅረብ ትችላላችሁ!! @kabodartfamily @kabodartfamily
920Loading...
19
ደሙ እንደ ውሃ(2×) ጎረፈ፤ የጌታ ጀርባ በጅራፍ ተገረፈ፤ እግሩ እስኪነቃ ተራራውን ነጎደ፤ እስከሞት ድረስ ጌታ እኔን ወደደ። @kabodartfamily @kabodartfamily
820Loading...
20
ዮሐንስ 3 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁸ እናንተ፦ እኔ ክርስቶስ አይደለሁም፥ ነገር ግን፦ ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ እንዳልሁ ራሳችሁ ትመሰክሩልኛላችሁ። ²⁹ ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ። ³⁰ እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል። ³¹ ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሚሆነው የምድር ነው የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው። ³² ያየውንና የሰማውንም ይህን ይመሰክራል፥ ምስክሩንም የሚቀበለው የለም። ³³ ምስክሩን የተቀበለ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ። ³⁴ እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና። ³⁵ አባት ልጁን ይወዳል ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል። ³⁶ በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።
941Loading...
21
ድብቁ ድል በኢትዮጵያ ክፍል አምስት "ፍቅርና ሰቀቀን" ¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤ ፋንታዬ ከተማ አደግ ወጣት ስትሆን የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን አጠናቃ እድል የሚከፍትላትን በር በመጠበቅ ላይ ናት። አዲስ አበባ ቦሌ አከባቢ ተወልዳ ያደገችው ፋንታዬ ከኦርቶዳክሳውያን ቤተሰብ የተገኘች ሲሆን። በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ስርዓትና እምነት ያደገች ወጣት ነች። ፋንታዬ መልካም ቁመና ኮስታራ ፊትና ረጋ ያለ አስተያየት ያላት ልጅ ስትሆን ደረቱ ላይ መስቀል የተጠለፈበት የሀገር ልብስ ለብሳ ስትታይ ውበቷ ይደምቃል። ደርግ ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ካለው የፐለቲካ ግለት አንጻር  በዙሪያዋ ያሉትን ማህበረሰቦች በጽሞና እየተመለከተች «ከዚህ ሀሉ ነገር የእኔ ስፍራ የት ይሆን?» እያለች ራስዋን ትጠይቃለች። የእግዚአብሔር ቃል ከሆነው መጽሐፍቅዱስ ለመማር ባላት ፍላጎት በብስራተ ወንጌል ሬድዮ አማካይነት በአማርኛ የሚተላለፈውን ትምህርት ክፍሏ ውስጠዕ ለብቻዋ በመሆን ትከታተል ነበር። በሬዲዮ ስርጭቱ አማካይነት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በተደጋጋሚ አደመጠች። የኢየሱስን ጌትነት ተረዳች። «እግዚአብሔርንና ሰውን ያስታረቀ» ብቻ ሳይሆን በኃጢአጠኞች ላይ የነበረውን የሞት ፍርድ ለመሻር ሕይወቱን የሰጠ መሆኑን ተገነዘበች። የእርስዋ ኃጢአት ይቅር የመባሉ ዋስትና ተሰማት። ይህን ከእግዚአብሔር ቃል የቀረበ ምስክርነት በማመን ኢየሱስ ክርስቶስ «ሥጋ እንደሆነ ቃል» ተቀበለችው። የብሥራተ ወንጌኦእ ሬድዮ መልእክት ነፍሷን መገበው። አንድ ቀን ግን ማርክሳውያን ባለስልጣኖች ወደ ሬድዮ ጣቢያው ገብተው እነኛን በጣም የሚፈሩዋቸውን የማስተማሪያ ቴፖች አወደሟቸው። ድርጊቱ ፋንታዬንና ሌሎች እጅግ ብዙ ሰዎችን አንድ ትልቅ ነገር አሳጣቸው። እንደሌሎቹ ሁሉ ፋንታዬም መንፈሳዊ ጽናት ለመሻት ወደ ሕቡዕ ስብሰባዎች ትሄድ ጀመር። በ1970 ዓ.ም አንድ ምሽት ከሌሎች አማኞች ጋር አንድ ቤት ውስጠዕ እንደ ተሰበሰበች ከወሊሶ የመጣ አንድ ሰውዬ ወዳነበሩበት ጎራ አለ። ያን ምሽት ጎብኚ የሆነው የንጉሤ አይኖች በማግኔት እንደ ተሳበ ብረት ፊት ለፊት ወደተቀመጠችው ወጣት ተወረወረ። ያን ቀን ምሽት ፋንታዬ ወደ ቤትዋ የተመለሰችው ቀድሞ በማታውቀው ሁኔታ መደናገርና መታወክ እየተሰማት ነበረ። ከወሊሶ የመጣው እንግዳ አጭር ነው። ያን ጊዜ አይኖችዋን ወደ ሌላ አቅጣጫ ልትልካቸው ብትሞክርም አንዳች መስህብ የጎተታቸው ይመስል እምቢ እያሏት ወደ እርሱ ይመለሳሉ። እርሱም ድርጊቷ ያስደሰተው መሆኑን በፈገግታ ይገልጥላታል። የቁመቱ ማጠር ባያስደስታትም አልናቀችውም። የሰውነቱ ቅርጽ ያልተመጣጠነ መሆን፣ የእግሮቹ መርዘም እንዲሁም ፊቱ ከእድሜው በላይ የጸና ሰው ፊት መምሰሉ አስገርሟታል። ከምንም በላየዕ የሳባት ግን ውስጣዊ እርሱነቱ በቅርቡ የወደደችውና የተማረከችለትን ውዷን ኢየሱስን የሚያንጸባርቅ ነበር። ያን ምሽት ፋንታዬም ሆነ ንጉሴ ለዘላለም ያስታውሱታል። በሚቀጥለውም የአዲስ አበባው ጉዞ  ወቅት ለአጭር ጊዜም ቢሆን ተገናኙ። እንደቀድሞው ሞገስን ተጎናጽፋ ፊት ለፊት ተቀምጣ ነበር። በሕብረት የመሆንን ልምድ ተጋሩ። ጣቶቹ በሚወደው የጊታር ክር ላይ እየተርመሰመሱና ልቡ እያዜመ ከእርሷ ጋር በዝማሬ ለማምለክ በመቻሉ ብቻ ደስተኛ ነበር። «ከእኔ ጋር ደብዳቤ ለመለዋወጥ ትፈቅጂ ይሆን?» ብሎ ጠየቃት ንጉሤ ፈራ ተባ እያለ «አዎ እፈቅዳለሁ» አለችው **** በተለያየ ጊዜ ከጆን ሆነ ከፋንታዬ የሚላኩለትን ደብዳቤዎች ለማግኘት አልፎ አልፎ ወሊሶ ከተማ ወደምትገኘው ትንሽ ፖስታ ቤት ብቅ ይላል። ከእለታት በአንዱ ቀን የደረሰው ፖስታ ግን ልቡን በሀዘን የወጋው ነበር። የልጅነትና የትምህርት ቤት ጓደኛው ተስፋዬ ምጽዋ አከባቢ በተደረገው ጦርነት ውስጠዕ መሞቱን የሚገልጥ ነበር። ንጉሤ መርዶውን እንደ ሰማ አለቀሰ። ከፋንታዬ ጋር የነበራቸው ግንኙነት ቀስ በቀስ እያደገ መጣ። ግንኙነታቸውንም በጌታ ፊት ማስቀመጥ ጀመሩ። * ንጉሴ በመንግስት ሹማምንት እምነቱን እንዲሸሽግ ለሚደረግበት ጫና ላለመንበርከክ ወሰነ። ለተለያዩ ሰዎችም በጥንቃቄ ስለክርስቶስ ይመሰክርላቸው ነበር። ይህን ድርጊቱን የአከባቢው ካድሬዎች አልወደዱለትም። በዚህም ምክንያት እርሱን የሚከሱበትን ወንጀል ወይም እርሱን የሚያስወግዱበትን አጋጣም ይፈልጉ ጀመር። ንጉሴም ቢሆን ወጥመዱ የተዘጋጀለት መሆኑን ጠርጥሯል «መቼ ይሆን ወጥመዱ የሚያገኘኝ?» እያለ መስጋቱ አልቀረም።  ወጥመዱ ተመቻቸለት። ወደ አንዲት የገጠር መንደር ከማዛወር ይልቅ እንዴት ቢቀጣ ይሻላል? ንጉሤ ወደ አዲስ አበባ በመጣ ጊዜ ጊንዶ ወደምትባልና ከወሊሶ ደቡብ ምዕራብ ወደምትገኝ የገጠር ከተማ ተዛውሮ እዚያ እምትገኝ ትንሽ ትምህርት ቤት ውስጥ ዝቅ ማለትና ወደ ሩቅ ስፍራ መወርወሩ በሚገባ ለሠለጠነና በሰዎች መካከል መኖርን ለለመደው ንጉሤ ከባድ ነበር። በተዛወረበትም ስፍራም ቢሆን የቀበሌ መሪዎች በጠዕርጣሬ ይመለከቱት ጀመር። በዚያ የብቸኝነቱ ወቅት ክሪስ ለተባለችውን የመጀመሪያ መጽሐፍቅዱሱን ለሰጠችው ነርስ ደብዳቤ ጻፈላት። ከደብዳቤው አንዱ መስመር አንዲህ ይል ነበር «ወደ ክብር የሚወስደውን የመስቀል መንገድ መርጫለሁ።» • • • አንድ ቀን ፋንታዬ በህብዕ ስብሰባ ከሌሎች ጋር ሳለች ተያዘችና ታሰረች። ብዙ ሕንጻዎች ነበሩ ለእስር ቤትነት የተመደቡት። እነዚያ እስር ቤቶች ካድሬዎች ለተወሰኑ ሳምንታት ለሚያስሯቸው ሰዎች አሰቃቂና የማይረሳ ትምህርት የሚያስተምሩባቸው ነበሩ። እነዚያ የእስር ወራት በእስረኞችም ሆነ በአሳሪዎች አካል አዕምሮና ነፍስ ላይ ጠባሳ ጥለው አልፈዋል። ፋንታዬ ከእስር ቤት እንደተለቀቀች ባልነበረችባቸው ቀኖች የመጡላትን ደብዳቤዎች ለመውሰድ ወደ ፖስታ ቤት ነበር የሮጠችው ምንም ፖስታ አላገኘችም። ያልጻፈችበትን ምክንያት ለንጉሤ በደብዳቤ አሳወቀችው። ምናልባት ፖስታዋ ተከፍቶ ቢመረመር ችግር እንዳያስከትልባቸው በመሳብ የጻፈችለት በሚስጥራዊ ቋንቋ ነበር። ከንጉሤ ዘንድ ግን ምንም መልስ አልመጣላትም።  ስለርሱ ለመጠየቅ በድፍረት ስልክ ደወለች ያጘኘቸው ጠንካራ መልስ ነበር «ንጉሤ እዚህ የለም» የሚል። በድንጋጤና በጭንቅ ሆና የሚመጣላትን ዜና ትጠብቅ ጀመር። የምታውቃቸው ሌሎች ሰዎች ላለመመለስ ተሰውረዋል «አቤቱ ጌታ ኢየሱስ ሆይ! ንጉሤ የት ደረሰ?» አለች ለራስዋ ጭንቀትዋን መቋቋም ቢያቅታት። . . . . ይቀጥላል... @kabodartfamily @kabodartfamily
960Loading...
22
🤍The name of Jesus is like no other name and is above every name. In Jesus Christ, everyone who believes in His name shall receive salvation, healing (restoration), blessing, and victory. Jesus Christ, who gives this divine power, is the same yesterday, today, and forever.🤍 @kabodartfamily @kabodartfamily
910Loading...
23
"The true Christian is the only happy man, because he has sources of happiness entirely independent of this world." J.C. Ryle @kabodartfamily @kabodartfamily
1281Loading...
24
ሐዋርያት 16 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁵ በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር ²⁶ ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ። @kabodartfamily @kabodartfamily
1050Loading...
25
ለ10 ዓመት ከመዋጋት ለ10ደቂቃ መፀለይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል!! @kabodartfamily @kabodartfamily
1060Loading...
26
ሙት ነበርሁ የማልረባ🥹 ከመንደሬ ስትገባ🥹 ምን ነበርኝና ምኔ ወዶ ልበል🥹 የትኛው እኔነቴ ለዚ ሳበው ልበል🥹 እንዲያው ቸርነትህ ያፍቅር ካልሆነ አይገባኝም መድሀኒቴ የኔ ጌታ ያንተ ውለታ © apostle John❤️❤️ @kabodartfamily @kabodartfamily
1100Loading...
27
አባ ወድሀለሁ 😭😭😭😭 @kabodartfamily
1050Loading...
28
“ጌታም፦ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባልና፥ በከንፈሮቹም ያከብረኛልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛልና” — ኢሳይያስ 29፥13 😭😭😭😭 @kabodartfamily @kabodartfamily
970Loading...
29
ድብቁ ድል በኢትዮጵያ ክፍል አራት ¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤ ጓደኛሞቹ እድሜያቸው በጨመረና በትምህርታቸው በገፉ ቁጥር የመበታተናቸው ነገር እየጨመረ መጣ። በ1970ዎቹ የንጉሤ ጓደኞች መበታተን ጀመሩ። ከእድገታቸው ጋር አዲስ ተግዳሮት መጣባቸው፤ ወደ ተለየዓየ አቅጣጫ የመበታተን ተግዳሮት። ተስፋዬ ከተማው ውስጥ በሚገኘው ትምህርት ቤት የአስራአንደኛ ክፍል ትምህርቱን እንደጨረሰ ሐረር ከሚገኘው ወታደራዊ ኮሌጅ ጥሪ ቀረበለት። ጓደኞቹ ወደ ወታደራዊው ዐዓለም መግባቱን ባይወዱለትም እርሱ ግን አልተወውም። በሠራዊቱ ውስጥ መኮንን መሆን አስደሳች ሆኖ ነበር ለእርሱ የታየው። የኋላ ኋላ የሚገባበት አሰቃቂ ጦርነትና በሰሜን የሚከሰተው ድርቅ ያኔ አልታሰበውም። ይህ በእንዲህ እንዳለ ወ/ዊ ኬዳሞ ወደ አዲስ አበባ በመዛወራቸው እንደ ቀድሞው ወደ ወሊሶ እየተመላለሱ ማስተማራቸውን ቀነሱ። ጆን ለእረፍት ወደ ካናዳ ከወላጆቹ ጋር አመራ። ንጉሴ ብቻወን ቀረ። ንጉሴ በ1972 (እ.ኤ.አ) ለጆን የፃፈው ደብዳቤ እንዲህ በማለት ይጀምር ነበር «ውድ ጆኒ . . .  ባለፈው ጊዜ ተወዳጁ ደብዳቤህ ሲደርሰኝ በጣም ደስ አለኝ፤ አመሰግናለሁ። በዚህ ምድር ላይ ፊት ለፊት የመገናኘት እድል ባይኖረንም እንኳን በየጊዜው በደብዳቤ ስለምንገናኝ ባለፈው ጊዜ አደርግ እንደነበረው አሁን በጣም አልጨነቅም። አንድ ቀን በቅርብ ጊዘ ወደ ኢትዮጵያ ትመለሳለህ የሚል ተስፋ አሁንም አለኝ። ያን እለት በናፍቆት እጠባበቃለሁ። አይመስልህም?» በደብዳቤው ስለ ትምህርቱ ወደ ክርስትና እምነት ስለመጡ ተማሪዎች ስለ ወቅቶች መለዋወጥ ስለአካላዊው ለውጡ እንዲሁም ከርሱ መለየቱ ከባድ እንደሆነበት ጭምር ገልጦለታል። ጊዚያቶች ይነጉዱ ጀመር። አንድ ሁለት እያለ ጥቂት አመታቶች አለፉ። ንጉሴም ጅማ ከሚገኘው መጽሃፍ ቅዱስ ኮሌጅ ተመረቀ። ኤርትራም አቅንቶ መስራት ጀምሯል። እጓላ ማውታን ድርጅት አስተዳዳሪ ሆኗል። በማዕከሉ ውስጥ በተለያየ ጊዜ ስብሰባ ያካሂዳሉ፣ ይማማራሉ፣ ድራማ ይመለከታሉ፣ ልዩ ልዩ ጨዋታዎችን ይመለከታሉ። የማዕከሉን ፕሮግራሞች ከሚካፈሉት ወታደሮች መሀል ንጉሤ ከነበረበት ማዕከላዊ ሸዋ የመጡ ሾስት የበታች ሹማምንቶች ይገኙበታል። ግርማ ፥ ሰለሞን እና ተሾመ ይባላሉ። ሶስቱ ወጣቶች ወደ ማዕከሉ እየመጡ አንድ ካናዳዊ ሚስዮናዊና ኤርትራውያኑ የቤተክርስቲያን መሪዎች ከመጽሃፍ ቅዱስ በሚያስተምሩበትና ስለ ኢየሱስ በሚናገሩበት ጊዜ ያዳምጧቸው ነበር። ክርስቶስን እንደ አዳኙ አድርጎ በመቀበል ረገድ ተⶄመ የመጀመሪያው ሆነ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሰለሞንና ግርማ የእርሱን አርዓያነት ተከተሉ። አንድ ላይ መጽሃፍቅዱስን ማጥናት ጀምረው ክርስቶስን በከፍተኛ ፍቅር የሚከተሉ ሆኑ። ወጣቶች ማዕከል ውስጥ የነበረው ኅብረት ሞቅ ያለ ቢሆንም አየር ኃይሉ ሰፈር ያለው ማርክሳዊው ድባብ፣ የሃይማኖት ዝንባሌ ላላቸው ሰዎች ቀዝቃዛ ሆኖባቸዋል። የአየር ኃይሉ አባል የሆነ አንድ ሰው ክርስቲያን መሆኑ ቢታወቅ ክስ፣ ማስፈራራትና ከማዕረግ እድገት መታለፍ እንዲሁም ሌሎች ጥቅሞችን የመነፈግ ጉዳት ይደርስበታል። ቢሆንም ሰለሞን፣ ግርማና ተሾመ «ጌታችንን ለማገልገል ዋጋ መክፈል አለብን» በማለት ችግሩን ተቀበሉት። በተለይ ተሾመ የደረሰበትን ማስፈራራት ሁሉ በጽናት ይቋቋም ነበር። ንጉሤ የሶስቱን ሰዎች ጽናት እየተመለከተ በረታ። በአጸፋው ደግሞ ሶስቱ ወጣቶችና ሌሎች ሰዎች ንጉሴ በሚያቀርባቸው ብሩህ መጽሃፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይባረኩና ጭንቀታቸውም ገለል ይልላቸው ነበር። አንዳንድ ጊዜ ንጉሴ የሙዚቃ መሳሪያ እየተጫወተ ተወዳጅ የምስጋና መዝሙሮችን ያዘምራል። ተቋሙ ውስጥ የሚሰበሰቡ ሁሉ አብረውት ይዘምራሉ። ከጥቂት ቀናት በኋላ ሌላ የሥቃይ መዝሙር የሚያንጎራጉሩ ስለመሆኑ ግን ብዙ አልተረዱም ነበር። • • • መስከረም 2 1967 ንጉሠ ነገሥት ኃይለስላሤ ታሰሩ፤ የመንግስት ግልበጣ ተደረገና ጥንታዊው የኢትዮጵያ ሥርወ መንግስት ተፈጸመ። ኢትጵያውያን የቤተክርስቲያን መሪዎች በፖለቲካው ብጥብጥ ግራ ተጋብተው ነበር። ወንጌላዊ ኬዳሞ ወዲህና ወዲያ ይላሉ። ኮሚኒስት አገሮች ውስጥ ስለተከናወኑ ነገሮች እንግዳ አይደሉም። ትልቅ መንፈሳዊ ሰው እንደመሆናቸው በጥልቅ የኃላፊነት ስሜት ነበር መንጋቸውን የሚያገለግሉት።   ወንጌላዊ ኬዳሞ አጥብቀው በወቅቱ ስላለው ሁኔታ ቢጸልዩም መልስ አላገኙም ነበር። መስከረም 24 ጸሎታቸውን ጸልየው ወደቤታቸው በሚመለሱበት ጊዜ ጌታ ተናገራቸው ክርስቶስ ሊሰቀል ሲል የተናገራቸውን ንግግር አስታወሳቸው ወንጌላዊ ኬዳሞም እንዲህ አሉ «የእኔ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይፈጸም። የጸሎት ቤቶችና ቤተ ክርስቲያኖች እንዲዘጉ ከፈለግህ ይዘጉ። መጽሃፍ ቅዱስ ከመነበብ የሚታገድ ከሆነ ይታገድ። የምንታሰር ከሆነ እንታሰር። ለእምነቴ እንድሞት ከፈለግህ ልሙት።» ከዚህ ቃል በኋላ እጅግ ታላቅ ሰላምና ደስታ ተሞሉ። በምንም ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑም የሚጠብቃቸው እንዳለ እንዲያምኑ አጽናናቸው። ከዚያ ወዲህ ባለፉባቸው መከራዎች ሁሉ ምንም ያልተሸበሩ መሆኑን ኬዳሞ ገለጡ። ለመሞት የቆረጡ እንደመሆናቸው ለመኖር ነጻ ሆኑ። ታህሳስ 11 ቀን ኢትዮጵያ ኅብረተሰባዊት ወይም ሶሻሊስት መሆኗ ታወጀ። በኤርትራና አከባቢው ውጥረት የደቀ መሐሪን መልካም ስፍራነት እድሜ አሳጠረው። በመሆኑም ንጉሴ ከኤርትራ ወጥቶ ወደ አዲስ አበባ አመራ። በአዲስ አበባም ቢሆን «በጴንጤነቱ» ምክንያት ከሚመጣበት ክስ አላመለጠም። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ መንዝ አመራ። እዚያም ለአጭር ጊዜ በመምህርነት አገለገለ። ንጉሴ የመንዝ ቆይታውን አገባዶ ወደ አዲስ አበባ በተመለሰ ጊዜ የእረፍት ጊዜውን አዲስ አበባ ፤ማሳለፍ ከመጣው ከአብሮ አደጉ ጆን ጋር ተገናኘ። መገናጨታቸው አስፈነደቃቸው። ያለፉ ትዝታዎቻቸውን አነሱ። ከተለያዩ በኋላ የገጠማቸውን የሕይወት ልምድ  ተነጋገሩ። ንገሤ 1969 ወሊሶ በመምህርነት ተመድቦ አመራ። በትምህርት ቤት በነበረው ቆይታ ንቁ የክርስቶስ ምስክር ሆኖ መታየቱ በአከባቢው ባሉት የፖለቲካ መሪዎች ዘንድ «አደገኛ» አሰኝቶታል። ንጉሤ የሚደርስበትን ችግር ቢረዳም በተገቢው መንገድ በእምነቱ ጸና። . . . ይቀጥላል..... @kabodartfamily @kabodartfamily
1110Loading...
30
የእኛ ህይወት 😭😭😭 መምህር በጋሻው stay blessed @kabodartfamily
1201Loading...
31
........አንዱን በግ ለሁሉ አበቃው ይሄ አለም ክፉ ነው ሀጥያት በዝቶበታል ለአንዱ ሰውቼ ሌላው ይከፈታል የበሬ የኮርማ የበግና ጠቦት የዋኖስ የእርግብ አላዳነኝ ከሞት ደግሞም ብገሰግስ ወደ መዳን ስፍራ የመማፀኛ ከተማው ሩቅ ነው ተራራ እባብም ሰቀልኩኝ ለመዳን ከመርዙ ያም አልኩኝ ይህም አልኩኝ በዛብኝ መዘዙ ሀጥያቴ በዝቶ ከመስዋዕቴ አቅም ሰውቼ ስመለስ ይከፈታል ዳግም ግራ ግበቶኝ እኔ ሳለሁ ሳመነታ ለኔ ምትክ አድርጎ ሚሞት በኔ ቦታ በአብ እቅፍ ያለው አንድያ ልጁ ተላከና መጣ ልይዘኝ በእጁ አብ ስራህ ደንቅን ነው መስዋዕትህ ልዩ ሀጥያት የሌለበት ያልታየ በላዩ የኔ ብቻ ሳይሁን የአለምን ሀጥያት የሚያስወግድ መስዋዕት ፣የሚታደግ ከሞት ብዙ ...ብዙ ታርዶበት ብዙ የሞተውን በልጁ ሞት ዋጀ ሲኦል የያዘውን ሳይወጣ ከከተማ ተራራማ ሀገር የመማፀኛ ከተማ አመጣልን እግዚአብሔር አንዱን በግ አርዶ ለሁሉ አበቃው አለማትንና ስልጣናት ለስሙ አስገዛው ቤዛችን ነው ጌታ የታረደው በግ ሁሉን በስልጣን ይዞ ጻዲቃን የሚያደርግ በደሙ ተወራርዶ ዲያብሎስን ቀጣ ስለኛ ሞተልን ሀጥያት በፃዲቅ ተቀጣ አሁን ነፃ ሰው ነን ኩነኔ የሌለብን በአብ ፊት የሚቆም ሊቀ ካህን አለን ✍✍በጌታሁን አናሞ☺️☺️ @Kabodartfamily @kabodartfamily
1060Loading...
32
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” — ዮሐንስ 3፥16 @kabodartfamily @kabodartfamily
970Loading...
33
2ኛ ቆሮ 12 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ትምክህት የሚያስፈልግ ነው፤ አይጠቅምም ነገር ግን ከጌታ ወዳለው ራእይና መገለጥ እመጣለሁ። ² ሰውን በክርስቶስ አውቃለሁ፥ በሥጋ እንደ ሆነ አላውቅም ወይም ከሥጋ ውጭ እንደ ሆነ አላውቅም፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤ እንዲህ ያለው ሰው ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ። ³ እንዲህ ያለውንም ሰው አውቃለሁ፥ በሥጋ እንደ ሆነ ወይም ያለ ሥጋ እንደ ሆነ አላውቅም፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤ ⁴ ወደ ገነት ተነጠቀ፥ ሰውም ሊናገር የማይገባውን የማይነገረውን ቃል ሰማ። ⁵ እንደዚህ ስላለው እመካለሁ፥ ስለ ራሴ ግን ከድካሜ በቀር አልመካም። ⁶ ልመካ ብወድስ ሞኝ አልሆንም፥ እውነትን እላለሁና፤ ነገር ግን ማንም ከሚያይ ከእኔም ከሚሰማ የምበልጥ አድርጎ እንዳይቆጥረኝ ትቼአለሁ። ⁷ ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው። ⁸ ስለዚህ ነገር ከእኔ እንዲለይ ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ። ⁹ እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። ¹⁰ ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና። @kabodartfamily @kabodartfamily
1130Loading...
34
Old is Gold እስከ ሞት ድረስ ጌታ እኔን ወደደ😭😭😭 መሰማት ሳይሆን መደመጥ ያለበት መዝሙር!!! @kabodartfamily @kabodartfamily
1013Loading...
35
ven ven ven ven ven መሲሁ ና ህዝብህ ይጠብቅሀል🙏🙏🙏 @kabodartfamily
991Loading...
36
ሀብተ ሰማይ ሀንቾ❤️❤️❤️ @kabodartfamily
962Loading...
37
ቲቶ 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹¹ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ¹²-¹³ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ ¹⁴ መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል። ¹⁵ ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ። @kabodartfamily @kabodartfamily
1331Loading...
38
👉ከህልውናው መውጣት አንችልም!በወጣን ቅፅበት............ተመልሰን እንገባለን!😂
971Loading...
39
የዘላለም ህይወት ለመስጠት ❤️❤️❤️❤️
1192Loading...
40
"ይሂዱ ተዉአቸው" ዛሬ ወዳጅ መልካሙን ቀን እንጂ ክፉውን ቀን አይጋራም ። መልካም ቀን አጃቢ አያጣም ። ክፉ ቀን ግን አጃቢ የለውም ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን ክፉ ቀን የተካፈል ሳይሆን የቀኑን ክፋትና መከራን ሁሉ የተቀበለ ነበር ። ሕማሙን ለብቻው ተቀበለ ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ እኛ ወዳጆቹን አጋፍጦ ራሱን ነጻ ለማውጣት አልሞከረም ። ገዳይ ፈልጎ ያገኘውን እኔ አይደለሁም ብሎ ማምለጥ እንጂ ለገዳይ "እኔ ነኝ" እንዴት ይባላል ? መድኃኔ ዓለም ግን “እኔ ነኝ አልኋችሁ፤ እንግዲህ እኔን ትፈልጉ እንደ ሆናችሁ እነዚህ ይሂዱ ተዉአቸው” (ዮሐንስ 18፥8) አለ ። "ይሂዱ ተዉአቸው" የመከራውን ፣ የሥቃዩንና የሞቱን ጽዋ እኔ ብቻዬን አጠጣዋለሁ ። በእነርሱ ምትክ እኔ እገረፍለሁ ፣ እናቃለሁ ፣ መከራንም እቀበላለሁ ፣ ሞታቸውንም እሞታለሁ "ይሂዱ ተዉአቸው" ። "ይሂዱ ተዉአቸው" ለእነርሱ መዳን የሚሆነው የመስዋዕቱ በግ "እኔ ነኝ" ። "ይሂዱ ተዉአቸው" ዛሬ መከራን የምቀበልበት ቀን ነው ፤ መከራውን ይካፈሉ ፣ ጽዋውንም ይጠጡ ዘንድ አይችሉም ። "ይሂዱ ተዉአዉ" መዳን ከቶውን የሰው እገዛ አይፈልግም  ። "ይሂዱ ተዉአቸው" በእኔ መያዝ እነርሱ ነጻ ይሁኑ ።  ኃጢአት ፣ ባርነት ፣ ፍርድና የዘላለም ሞት ይሻር ዘንድ "ይሂዱ ተዉአቸው" ። አንድም ጥፊ በፊታቸው ላይ እንዳያርፍ "ይሂዱ ተዉአቸው" ። እፍረት እንዳያገኛቸው ዕርቃኔን እኔ እሰቀላለሁ ፣ አንገታቸውን እንዳይደፉ እኔ በመስቀል ላይ አንገቴን አዘንብዬ ነፍሴን ስለ ነፍሳቸው እሰጣለሁና "ይሂዱ ተዉአቸው" ። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሥዋዕትነቱ እንካፈል ዘንድ አይፈልግም ። እርሱ በሞቱና በትንሣኤው እንድናምን ይፈልጋል ። ታዲያ "ይሂዱ ተዉአቸው" ያለውን ጌታ መከራውን እንቀበል ዘንድ መፍጨርጨር ምን የሚሉት ነው ? በየዱሩ ፣ በየገጠሩና በከተማም "አልሄድም" ብለው የሚሟገቱት ስንቶች ናቸው ? አዎ! ጌታ "ይሂዱ ተዉአቸው" ብሏል ። በነጻነት ፣ በቅድስና ይኖሩ ዘንድ "ይሂዱ ተዉአቸው" ። የኃጢአት ባርነት ተሽሮ ለጽድቅ ባሪያ ይሆኑ ዘንድ "ይሂዱ ተዉአቸው" ። እኔ በእነርሱ በሙላት እኖር  ዘንድ "ይሂዱ ተዉአቸው" ። ሞታቸውን ወስጄ ሕይወቴን ይኖሩ ዘንድ "ይሂዱ ተዉአቸው" አለ ። ከጌታችን ቤዛነት (ቤዝዎት) የቀረ እኛ የምንሞላው የለምና እንሂድ ። እንሂድ በእርሱ እንመን ። እንሂድ በቅድስና እንኑር ። እንሂድ የሞተውንና የተነሳውን እናምልክ ። እንሂድ ይህን ነጻነት ለሰዎች ሁሉ እንገር ። መሄድ ይሁንልን ። አሜን ። ያለም ለገሠ @kabodartfamily @kabodartfamily
1020Loading...
ተደርጎልኝ ነው ምህረት በዝቶልኝ ድንቅ ልብን የሚነካ ቀጥታ ከሰማይ የተቀዳ ድንቅ መዝሙር ነውና አንድትሰሙት ዘንደሰ ግብዣችን ነው @kabodartfamily @kabodartfamily
Show all...
Show all...
ተደርጎልኝ ነው [ዘማሪት ንብረት ዳምጤ ] #protestantmezmure #ethiopianmezmur 2024

ድብቁ ድል በኢትዮጵያ ✍️ by Abate the great presented by #KABOWDARTFAMILY ክፍል 11 "ቆራጡ ታደሰ ~1~" ¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤ በተገደሉ ወይም በተፈቱ እስረኞች ምትክ አዳዲስ እስረኞች መተካት ጀምረዋል። በዚህ ሁኔታ ከተተኩት አንዱ ከጋሞ ጎፋ የመጣው ወጣት ታደሰ ነው። ታደሰ በቁመቱ ከንጉሤ እምብዛም አይልቅም። የታሰረው በአዲስ አበባ ጎዳናዎች እየተዘዋወረ ክርስታነዊ ፅሁፍ በማሰራጨቱ ነው። በነበረበት የአገሪቱ ደቡብ ክፍል ያሉ ክርስቲያኖች ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ይልቅ እስራትና ስደት ደርሶባቸዋል። የሻሸመኔው አሊ ሙሳ ግን ከሌሎች ባለስልጣናት ይልቅ ክርስቲያኖች ላይ ሳይከፋ አይቀርም። ሻሸመኔ ውስጥ ሰዎችን በሕይወት ሳሉ ቀብሯቸዋል። የሻሸመኔው የስጋ ደዌ ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶክተር ሙላቱ ከጅምላ ጭፍጫው ያመለጡት ለጥቂት ነበር። የጋሞ ጎፋው ተወላጅ ታደሰ በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት አምኖ ክርስቲያን የሆነው ገና በለጋ ወጣትነቱ ነው። ብዙም ሳይቆይ በአከባቢው በነበሩ ሰዎች ላይ ክርስቲያናዊ ተጽዕኖ ማሳደር ጀመረ። በየገጠሩና በየገበያው እየተዘዋወረ ስለ ክርስቶስ በመመስከር ብዙ ሰዎችን ክርስቲያኖች አድርጓቸዋል። ወጣቶችን እያደረጀ በማስተማር ኃይል የተሞላውን የክርስቶስ የምስራች ለሌሎች እንዲየዓዳርሱ አበረታታቸው። ይህ የ15 ዓመት ለጋ ወጣት በድርጊቱ ማርክሲስቶችን አበሳጫቸው። ለአብዮታዊ ዓላማቸው ሊመለምሉ ያሰቧቸውን ወጣቶች እንዴት እያደረገ ነው የሚያሳምናቸው? ማለትን ጀመሩ። ታደሰ ለሚሰማው ሁሉ ሕያው ስለሆነው ኢየሱስ መመስከሩን ገፋበት። በዚህ ድርጊት የተበሳጩት ማርክሲስቶች...... ይቀጥላል .... @kabodartfamily @kabodartfamily
Show all...
ድብቁ ድል በኢትዮጵያ ✍️ by Abate the great presented by #KABOWDARTFAMILY ክፍል አስር  ደብዳቤ በደረሳት ጊዜ ፈራች። ሆኖም መርማሪዎችኣ ካቀረቡላት ጥያቄ አንፃር ንጉሴ ላይ ክስ ለመመስረት የሚያስችል ማስረጃ አለማግኘታቸውን ተረዳች። ይህም ስጋትዋን አቀለለው። የንጉሴ ከሳሾችም «በሲ አይ ኤ ወኪልነት መጠርጠር» ብለው ብለው ክሳቸውን አቀለሉት።» ይሄም ክስ ቢሆን መሰረት አልነበረውም። ለማስረጃነት የቀረቡት ደብዳቤዎች ከአብሮ አደጉና ከወዳጁ ጆን ጋር ለረጅም ጊዜያቶች የተለዋወጣቸው ደብዳቤዎች ነበሩ። የንጉሴና የእስር ቤት ጓደኞቹ ዕለታዊ መከራ በቂ አየር በሌለበት ጠባብ ክፍል ውስጥ መታጎራቸውና የመታጠቢያ ውሃ አለማግኘታቸው ነበር። እስረኞቹ ከጠባቧ ክፍል የሚወጡት በተወሰነላቸው ጊዜ ወደ መፀዳጃ ቤት ሲሄዱ ብቻ ነበር። ሌሊት የሚርመሱት አይጦች ደሞ የእስረኞችን እረፍትና ሰላም ይነሳሉ። በመጨረሻም ንጉሴ ስድሳዎቹ የቀድሞ መንግስት ባለስልጣናት ወደ ተረሸኑበት ወደ ዋናው ወኅይኒ ቤት ተላከ።  ጠያቂዎች በተወሰነላቸው በሽቦ አጥር የታጠረ ስፍራ ሆነው እስረኞች ደግሞ በሌላ ወገን ተሰብስበው ጎብኚ ዘመዶቻቸውን በጉጉት ሲጠባበቁ ፋንታዬ ተመለከተች። በዚህ መኃል ነው የንጉሴን እህት አልማዝን ያየቻት። እንዳትታይ ፈጠን አለችና ወደ ኋላ አፈገፈገች። የቆመችበት ሆና አልማዝን በዓይኖቿ ተከታተለቻት። ወሊሶ ከተገናኙ ወዲህ ፋንታዬ ንጉሴን እንደገና አየችው። ልቧም በደስታ ሰከረ። አልማዝ ንጉሴን አነጋግራና የያዘችለትን ሰጥታው ስትመለስ ፋንታዬ እንድትታይ ወደ ፊት ራመድ ብላ የያዘችውን ፍራፈሬ ወደ ላይ ከፍ አድርጋ ያዘች። ንጉሴ ፋንታዬን አያት! ለአንድ አፍታ ትንፋሹ በደስታ ብዛት ቁርጥ አለ። ያን ዕለት የተፈጠረበትን ስሜት ምንጊዜም አይረሳውም። የወሰደችውን ፍራፍሬ በመካከላቸው ባለው የሽቦ አጥር ላይ ተንጠራርታ ሰጠችው። ሰው ከሚያየው ምግብ የበለጠ ነገር ነበር የተከዋወጡት። ከዚያን እለት ጀምሮ ንጉሴ በጉጉት የሚጠብቀው በየሳምንቱ እሁድ ለአጭር ጊዜ የሚኖራቸውን መተያየት ሆነ። ያኔ አይኖቻቸውና ልቦቻቸው ይገናኛሉ፤ ለጥቂት ጊዜ ይነጋገራሉ። አንዳቸው ስለሌላው በሕይወት መኖር እርግጠኖች ይሆናሉ። ንጉሴ እስር ቤት ውስጥ በቆየባቸው ጊዜያት የመፈታት እድል ካልገጠማቸው ሰዎች ጋር በሞት ጥላ ስር  ተጉዟል አንድ እስረኛ ንጉሴ በቅንነትና በተደጋጋሚ የነገረውን የሕይወት ቃል አልቀበልም «እምቢ» በማለት ለረጅም ገዚ ቆየ። ሰላም የለውም፤ የራሱን ተስፋ ቢስ ሁኔታ የንጉሴ ህይወት ከሚገልፅለት እውነት ጋር ያነፃፅር ጀመር። በመጨረሻ ግን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ማመንን በመምረጡ በእስረኛው ሕይወት ታላቅ ለውጥ ይታይ ጀመር። እንዲያ ባለ ሁኔታ ውስጠዕ ሳለ ይገጥመኛል ብሎ ያላሰበውን ሰላም አገኘ። ዘግየት ብሎ ወዳመነበት ጌታ የሚሰበሰብበት ሰዓት ደረሰ። እንዲረሸን ተወሰነ። አዲስ ጓደኞቹ ወደ ሆኑት ክርስቲያኖች ሄደና «ልገደል ነው። ቢሆንም የምሄድበትን ስለማውቅ የሚደንቅ ሰላም አለኝ» አላቸው። ይህን ከነገራቸው በኋላ እንደሚገናኙ ተስፋ በማድረግ አቅ ፎ ሳማቸውና ወደ መገደያው ስፍራ አመራ። . . . . ይቀጥላል.... @kabodartfamily @kabodartfamily
Show all...
መጽሐፍ ቅዱስ በራስ መታመንን ሳይሆን በክርስቶስ ብርታት መታመንን ይናገራል። ሰዎች እንደመሆናችን መጠን የአቅማችንን መገደብ መቀበል አለብን፣ እና የኢየሱስ ኃይል በእኛ እንዲሠራ  መፍቀድ አለብን። ከዚያም ፍርሃትን በጠንካራ እምነት እና ድካማችንን በኃይሉ እንተካለን። በክርስቶስ ከአሸናፊዎች በላይ ነን።  አምላክ እያንዳንዱን እርምጃችንን እንደሚረዳ እርግጠኞች እንሁን። @kabodartfamily @kabodartfamily
Show all...
ብቻ እየሱስ ቤቴ ካለ ሙሉ ነው ይበቃኛል ።
Show all...
👍 2
ድብቁ ድል በኢትዮጵያ ✍️ by Abate the great presented by #KABOWDARTFAMILY ክፍል ዘጠኝ "ከፀጋ ወደ ፀጋ" ¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤ ፋንታዬ «ንጉሤ በተከሰሰበት ነገር ይግባኝ ስለጠየቀ ወደ አዲስአበባ አዛውረውታል» የሚለውን ዜና በሰማች ጊዜ አንዳች ነገር ልቧን አዘለለው። ለእግዚአብሔር እየነገረች ሸክሟን ብቻዋን ነበር የተሸከመችው «እኔ ያለሁት ከተማ ውስጥ ነው፤ ሴቶች ደግሞ ለእስረኛ ዘመዶቻቸው በየቀኑ ምግብ ይወስዱላቸዋል። በድብቅም ቢሆን እኔም እሄዳለሁ።» አለች ለራሷ። ካድሬዎች አዲስ የምርመራ ዘዴ በመጀመራቸውና ሕጋዊ አሰራርም እየጠፋ ስለሄደ ጉዳዩን በይግባኝ ወደ ማዕከላዊ መንግስት መውሰዱ የተሻለ ጥበብ ነው ብሎ ንጉሴ ወሰነ። በዚህም ምክንያት ነበር በጥር 1971 ዓ.ም ንጉሴ ወደ አዲስአበባ ተዛውሮ ፒያሳ አከባቢ በሚገኘው ማዕከላዊ እስርቤት ውስጠዕ እንዲቆይ የተደረገው። ማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ የሚከናወነው ግርፋት ቀለል ያለ ቢሆንም ጥበቃው ግን የሚያፈናፍን አይደለም። ንጉሴን ለመጎብኘት ወደዚያ መሄዱ የሚያስጠርጥር መሆኑን ፋንታዬ ተገነዘበች። በንጉሤ ላየዕ ከቀረቡት ክሶች መሃል «ሚስቱ፣ እህቱ፣ እናቱ ወይም አክስቱ ካልሆነች ሴት ደብዳቤዎች ይላኩለታል» የሚል ነበረ። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፋንታዬን ከአዲስአበባ ውጭ በሸዋ ክፍለሀገር ቡታጅራ ውስጥ መደባት። ፒያሳ በሚተራመሰው ሕዝብ መሀል ሆና አሳቧ ሁሉ ንጉሴ ወደታሰረበት አስርቤት ይሄድ ነበረ። ወደ እስር ቤቱ ለመሄድ በተነሳች ቁጥር ወሊሶ ሳለች ፀጥታ አስከባሪዎች «ይጠይቁሽ ይሆናል ተዘጋጂ » ብሎ ንጉሴ የነገራት ነገር ትዝ ይላታል እናም ወደ እስርቤቱ ሄዳ ነገሮችን ከማወሳሰብ ብላ አስር ቤቱን በሩቁ መመልከት ምርጫዋ አድርጋለች። እንደጠረጠችው ለጥያቄ የምትፈለግ መሆኗን የሚገልጠው የጥሪ ደብዳቤ በደረሳት ጊዜ ፈራች። ይቀጥላል ........ @kabodartfamily @kabodartfamily
Show all...
ጥቂት ቆይታ አገልጋይ በሱፍቃድ ደሳለኝ || Besufekad Desalegn || Bishoftu Emmanuel Unit... https://youtube.com/watch?v=Q-R_29jsbnY&si=hD2OD4oHIcErHhfz
Show all...
ጥቂት ቆይታ አገልጋይ በሱፍቃድ ደሳለኝ || Besufekad Desalegn || Bishoftu Emmanuel United Church

ጥቂት ቆይታ አገልጋይ በሱፍቃድ ደሳለኝ || Besufekad Desalegn || Bishoftu Emmanuel United Church የኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን ቢሾፍቱ አጥቢያ እሁድ ማለዳ 3፡00 – 6፡30 የአምልኮ ጊዜ እሮብ ጠዋት 3፡00 – 7፡00 ሰአት የፈውስና የጸሎት ጊዜ አርብ ምሽት 11፡00 – 1:30 የትምህርት ጊዜ አድራሻ ፦ ቢሾፍቱ ሰርክል ወደ ባቦጋያ በሚወስደው መንገድ መሲ ፎቶ ቤት ፊት ለፊት ባለው መንገድ ገባ ብሎ ። አገልግሎታችንን like share comment በማድረግ ለሌሎች በማካፈል ይደግፉን ። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው #worship #christiansong #halwotemmanuelchurch #worship #christiansong #halwotemmanuelchurch #christiansong #worship #halwotemmanuelchurch