cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ካቦድ የኪነ ጥበብ ቤተሰብ🎭🎭

‹‹ ለተጠሩት ግን…የእግዚአብሔር ሀይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነዉ ክርስቶስ ነዉ፡፡ ›› 1ኛ ቆሮ 1፤26 በመንፈስ ቅዱስ እየተመራን ጠቢብ የሆነዉን ክርስቶስን በጥበብ እንገልጣለን፡፡ ከሥነ ፅሁፍ ወደ ኪነ ጥበብ! ማንኛዉንም ጥያቄና አሰተያየት ካላችሁ በዚህኛዉ በ @kabodartfamily_bot ላይ ማቅረብ ትችላላችሁ።

Show more
Advertising posts
237
Subscribers
+224 hours
+87 days
+1630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የዘላለም ህይወት ለመስጠት ❤️❤️❤️❤️
Show all...
"ይሂዱ ተዉአቸው" ዛሬ ወዳጅ መልካሙን ቀን እንጂ ክፉውን ቀን አይጋራም ። መልካም ቀን አጃቢ አያጣም ። ክፉ ቀን ግን አጃቢ የለውም ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን ክፉ ቀን የተካፈል ሳይሆን የቀኑን ክፋትና መከራን ሁሉ የተቀበለ ነበር ። ሕማሙን ለብቻው ተቀበለ ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ እኛ ወዳጆቹን አጋፍጦ ራሱን ነጻ ለማውጣት አልሞከረም ። ገዳይ ፈልጎ ያገኘውን እኔ አይደለሁም ብሎ ማምለጥ እንጂ ለገዳይ "እኔ ነኝ" እንዴት ይባላል ? መድኃኔ ዓለም ግን “እኔ ነኝ አልኋችሁ፤ እንግዲህ እኔን ትፈልጉ እንደ ሆናችሁ እነዚህ ይሂዱ ተዉአቸው” (ዮሐንስ 18፥8) አለ ። "ይሂዱ ተዉአቸው" የመከራውን ፣ የሥቃዩንና የሞቱን ጽዋ እኔ ብቻዬን አጠጣዋለሁ ። በእነርሱ ምትክ እኔ እገረፍለሁ ፣ እናቃለሁ ፣ መከራንም እቀበላለሁ ፣ ሞታቸውንም እሞታለሁ "ይሂዱ ተዉአቸው" ። "ይሂዱ ተዉአቸው" ለእነርሱ መዳን የሚሆነው የመስዋዕቱ በግ "እኔ ነኝ" ። "ይሂዱ ተዉአቸው" ዛሬ መከራን የምቀበልበት ቀን ነው ፤ መከራውን ይካፈሉ ፣ ጽዋውንም ይጠጡ ዘንድ አይችሉም ። "ይሂዱ ተዉአዉ" መዳን ከቶውን የሰው እገዛ አይፈልግም  ። "ይሂዱ ተዉአቸው" በእኔ መያዝ እነርሱ ነጻ ይሁኑ ።  ኃጢአት ፣ ባርነት ፣ ፍርድና የዘላለም ሞት ይሻር ዘንድ "ይሂዱ ተዉአቸው" ። አንድም ጥፊ በፊታቸው ላይ እንዳያርፍ "ይሂዱ ተዉአቸው" ። እፍረት እንዳያገኛቸው ዕርቃኔን እኔ እሰቀላለሁ ፣ አንገታቸውን እንዳይደፉ እኔ በመስቀል ላይ አንገቴን አዘንብዬ ነፍሴን ስለ ነፍሳቸው እሰጣለሁና "ይሂዱ ተዉአቸው" ። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሥዋዕትነቱ እንካፈል ዘንድ አይፈልግም ። እርሱ በሞቱና በትንሣኤው እንድናምን ይፈልጋል ። ታዲያ "ይሂዱ ተዉአቸው" ያለውን ጌታ መከራውን እንቀበል ዘንድ መፍጨርጨር ምን የሚሉት ነው ? በየዱሩ ፣ በየገጠሩና በከተማም "አልሄድም" ብለው የሚሟገቱት ስንቶች ናቸው ? አዎ! ጌታ "ይሂዱ ተዉአቸው" ብሏል ። በነጻነት ፣ በቅድስና ይኖሩ ዘንድ "ይሂዱ ተዉአቸው" ። የኃጢአት ባርነት ተሽሮ ለጽድቅ ባሪያ ይሆኑ ዘንድ "ይሂዱ ተዉአቸው" ። እኔ በእነርሱ በሙላት እኖር  ዘንድ "ይሂዱ ተዉአቸው" ። ሞታቸውን ወስጄ ሕይወቴን ይኖሩ ዘንድ "ይሂዱ ተዉአቸው" አለ ። ከጌታችን ቤዛነት (ቤዝዎት) የቀረ እኛ የምንሞላው የለምና እንሂድ ። እንሂድ በእርሱ እንመን ። እንሂድ በቅድስና እንኑር ። እንሂድ የሞተውንና የተነሳውን እናምልክ ። እንሂድ ይህን ነጻነት ለሰዎች ሁሉ እንገር ። መሄድ ይሁንልን ። አሜን ። ያለም ለገሠ @kabodartfamily @kabodartfamily
Show all...
👍 1
ዕብራውያን 12 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹-² እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። ³ በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ፥ ከኃጢአተኞች በደረሰበት እንዲህ ባለ መቃወም የጸናውን አስቡ። @kabodartfamily @kabodartfamily
Show all...
👍 1
✍ by Abate the great Presented by #KABOWDARTFAMILY ድብቁ ድል በኢትዮጵያ ክፍል ሶስት ¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤ ንጉሤ 15 ዓመት ሲሆነው በሚሲዮናውያኑ ከተዘጋጁት የመጀመሪያ ተጠማቂ ወጣቶች አንዱ ሆነ። ተጠማቂዎቹ ወጣቶች ኮረብታ አከባቢ በሚገኘው «የጨቦ ቤተ ክርስቲያን» በመጡ ሽማግሌዎች ከተፈተኑ በኋላ ተጠምቀው የጌታ እራት ተሰጣቸው። ግርግር ያልበዛበት ስርዓት ነበር፥ የሚሲዮናውያኑ ሠፈር አቅራቢያ ጥቂት አማኝ ጎልማሶች ነበሩ። «አማኞች» የሚለው ቃል «የአዲስቱ ቤተክርስቲያን» አባላት መጠሪያ ነበር። በአከባቢው የነበሩ ኦርቶዶክሳውያን አማኞች የወጣቶቹን መጠመቅ በጥርጣሬ በሚመለከቱበት በዚያ ወቅት የንጉሤ ቤተሰቦች የእርሱን መጠመቅ በዝምታ ማለፋቸው እድለኛ አድርጎታል። አንድ ቀን ግን ንጉሤ በዝምታ የማይታለፍበት ሁኔታ ተፈጠረ። አባቱ አቶ ቁምቢ ሊፈልጉት ሚስዮናውያኑ ቤት ድረስ መጡና «ንጉሤ የታለ ያለበት ንገሩኝ» አሉ በታላቅ ቁጣ ሚስዮናውያኑ ንጉሤን ለሁለት ቀናት ያህል ስላላዩት ወዴት እንደሄደ አላወቁም። አቶ ቁምቢ ንጉሤን ፍለጋ የመጡበት ምክንያት በንጉሤ እናት በእሳቸው ባለቤት መታመም ምክንያት ነበር። በአከባቢው ያሉ ጠንቋዮች ሁሉ አለቃ የሆነ ሰው «ሰድባኛለች» በማለት የንጉሤን እናት ረግሟቸው ነበር። ቀጥሎም አቶ ቁምቢ ገንዘብ አንዲወስዱለትና አንድ ትልቅ በሬ እንዲሰውለትም አዘዛቸው። በተጨማሪም የቅርብ ቤተሰቦች እንዲመጡ ታዘዘ። ከቅርብ ቤተሰቦች አንዱ የሆነው ንጉሤ ግን በአከባቢው አልነበረም። ተፈልጎ ሲታጣ ጊዜ ቤተሰቡ እርሱ ባይኖርም የጠንቋዮቹ አለቃ ያዘዛቸውን ለማድረግ ወሰኑ። ከገና በኋላ አንድ ቀን ንጉሴ በአከባቢው ታየ። ምክር በመፈለግ ኦቢ የሚባል አከባቢ ወዳሉ ሁለት ክርስቲያን መምህራን ዘንድ ሄዶ ነበር። እነርሱም ወደ ጅማ በሚወስደው ሳጃ ወደ ምትባል መኖሪያ መንደራቸው ወሰዱት። ይህን ያደረጉት ለጠንቋዮቹ አለቃ በሚደረገው የመሥዋዕት ስርዓት ላይ እንዳይገኝ በማሰብ ነበር። እርግማኑን ለማስቀረት ጠቋዮ የጠየቀው ሁሉ ቢደረግም የንጉሴ እናት ሞቱ። ሕክምናም አላገኙም ነበረ። ከወላጅ እናቱ ጋር አብሮ ባይኖርም ሲሞቱ ግን ማዘኑ አልቀረም። በመላው ኢትዮጵያ ነበሩ ክርስቲያኖች በወሊሶ ከተማ ዓመታዊ ስብሰባ አድርገው ነበር። ንጉሴን ያስደነቀው ነገር ቢኖር ከተለያየ አከባቢ የመጡት ተሰብሳቢዎች በደስታ የተሞላ የጓኝነት ስሜት ነው። ሰዎቹ የመጡት ከብት ከተሠራረቄ፣ የእርስበርሳቸውን ቤት ካቃጠሉ፣ ለዘመናት ከተገዳደሉ ጎሣዎች ነው። ከሀዲያ፣ ከምባታ፣ ወላይታ፣ ጌዲኦ፣ ከባሌ፣ ከከፋ፣ ከጋሞጎፋ የመጡ ሲሆኑ፤ ከሁሉም ጎሳ የተሰበሰቡና የተለያየ ኅብረ-መልክ ያላቸው ነበሩ። የዘርና ቀለም ልዩነቶች በማንኛው ኅብረተሰብ ውስጥ የግችት ምክንያቶች ቢሆኑም፤ እነዚህ «በክርስቶስ አንድ» መሆናቸውን የተረዱ አማኞች ግን በአንድነት ይመገቡና ከልብ በሆነ ፍቅር ይተቃቀፉ ነበር፤ ብዙዎች ክርስቶስ « ከድቅድቅ ጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ» ያመጣቸው መሆኑ የሚመሰክሩ ሲሆኑ ከአዳኛቸው ጋር በትኩስ ፍቅር የተጣበቁ ናቸው። • • • • • ትምህርት መጀመሩን የሚያበስረው ደወል ከመደወሉ በፊት ንጉሤ የሚሰራቸው ብዙ አሰልቺ ስራዎች ነበሩ። ብርዳማ በሆነው ማለዳ የሚናፍቀው ነገር ቢኖር ትምህርት ቤቱ የሚጠብቀው የጓደኞቹ ሞቅ ያለ ፍቅር ነው። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የሚመሰክሩ ልጆች በተማሪዎች መካከል ነበሩ። ክርስቲያናዊ ጉባዔዎችን ለመምራት በሚመጡ ተዘዋዋሪ የእግዚአብሔር ቃል አስተማሪዎች ሳቢያ ብዙዎች ወደ ክርስቶስ ቀርበዋል። ከአስተማሪዎቹ አንዱ ከከንባታ የመጡት አቶ ኬዳሞ ናቸው። አቶ ኬዳሞ ቁመተ ረጅም ትከሻ ሰፊና እጅግ ታላቅ የንግግር ስጦታ ያላቸው ናቸው። ከጌታ ጋር በፍቅር የተቆራኘ ግንኙነት አላቸው። የእምነታቸው ጠዕንካሬም ወደ ሌሎች የሚተላለፍ ነው። የሚርገበገቡ አይኖቻቸው፣ አልፎ አልፎ ጣል የሚያደርጉት ቀልድና በጥበብ የተሞላ ምሳሌያቸው ስብከቶቻቸውን የማይረሱ አድርገዋቸዋል። አቶ ኬዳሞ አዳዲስ አማኞችን ያማክራሉ፤ የክርስትና ሕይወት መልካም አርዓያነታቸው በወጣቶች ተወርሶ በኋላ ታይቷል። ተማሪዎቹ ከአምስተኛ ክፍል ጀምሮ ያለውን ትምህርት የሚከታተሉት ወሊሶ ከተማ ወዳለው ትምህርት ቤት በመዛወር ነው። ንጉሤና ሌሎቹም ወደዚያ በተዛወሩ ጊዜ ቤት በጋራ ተከራይተው ነበር የሚኖሩት። አንድ ጊዜ ንጉሤ በምሽት በሻማ ብርሃን ማጥናት በጣም አስቸጋሪ መሆኑን ለሚስዮናውያኑ ልጅ ለጆን ነገረው። ይህን የሰሙት የሚሲዮናውያን ልጆች በቤታቸው ውስጥ የነበረውን የሻማ ቁርጥራጭ በማቅለጥ አንድ ትልቅ ሻማ ሠሩና ለንጉሤ ሰጡት። ሻማውም ለረጅም ጊዜ እንዳገለገለው ንጉሴ ሲነግራቸው ደስ አላቸው። እነ ንጉሴ ለመጠመቅ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ጄርሳ ወንዝ አመሩ። ተጠማቂዎቹ ነጭ በነጭ ለብሰው በብሉይ ዘመን እንደነበረው ሻሽ ብጤ ራሳቸው ላይ ጣል አድርገው ነበር። ሀለት የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች ከግራና ከቀኝ ይዘው ውኃ ውስጥ ሲያስምጧቸው «በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም» እያጠመቁዋቸው ክርስቲያንነታቸውን በአደባባይ ያውጁ ነበር። ከዳር የቆሙት ክርስቲያኖች ደግሞ በእልልታ ያጅቡ ነበር። በመጨረሻም ቅዱስ ቁርባን ወስደው የጥምቀት ስርዓቱ ተፈፀመ። ንጉሤ የዚህ ታላቅ የጥምቀት ሥርዓት ተካፋየዕ በመሆኑ እጅግ ተደስትዋል። ተስፋዬና ጆንም አብረው ተተምቀው ነበር በዚህም ምክንያት ደስታው የላቀ ነበር። ሶስቱ ጓደኛሞች እየዓደጉ በሄዱ ቁጥር ሕይወታቸው ከእያንዳንዳቸው ሕይወት ጋር እንደተገናኘ ይቀጥላል። ያ የማይረሳ ዕለት በደስታና በምስጋና የተሞላ ነበር። ለአንዳንድ የማህበረሰብ ክፍሎች ግን ይህ አናዳጅ ድርጊት፣ ያልተለመደና በዝምታ ሊታለፍ የሚገባው አልነበረም። አንዳንድ ወላጆች ተጠማቂ ልጆቻቸውን ከቤታቸው ማስወጣት ጀመሩ። . . . ይቀጥላል.... @kabodartfamily @kabodartfamily
Show all...
ኢሳይያስ 49 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁴ ጽዮን ግን፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ጌታም ረስቶኛል አለች። ¹⁵ በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም። ¹⁶ እነሆ፥ እኔ በእጄ መዳፍ ቀርጬሻለሁ፥ ቅጥሮችሽም ሁልጊዜ በፊቴ አሉ። @kabodartfamily @kabodartfamily
Show all...
ጌታ በጣም ታማኝ ነው።😭😭 @kabodartfamily
Show all...
👍 1
ቲቶ 3 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹-² ለገዦችና ለባለ ሥልጣኖች የሚገዙና የሚታዘዙ፥ ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጁ፥ ማንንም የማይሰድቡ፥ የማይከራከሩ፥ ገሮች፥ ለሰው ሁሉ የዋህነትን ሁሉ የሚያሳዩ እንዲሆኑ ኣሳስባቸው። ³ እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን። ⁴ ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ፥ ⁵ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤ ⁶-⁷ ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው። ⁸ ቃሉ የታመነ ነው። እግዚአብሔርንም የሚያምኑት በመልካም ሥራ በጥንቃቄ እንዲጸኑ፥ እነዚህን አስረግጠህ እንድትናገር እፈቅዳለሁ። ይህ መልካምና ለሰዎች የሚጠቅም ነው፤ @kabodartfamily @kabodartfamily
Show all...
አንድ ነገር አልገባንም የገባቸው ኖረውለት ሄደዋል የገባቸው ሞተውለት ደስ ይላቸዋል የገባቸው ውዱን ሽቶ  ሰብረውለታል የገባቸው በዘይት ተቀቅለዋል በመጋዝ ተቆርጠዋል የገባቸው እርቃናቸውን ዘምረውለታል የገባቸው እስከ ሞት ድረስ ታዘውለታል የገባቸው እነኛ ሀያላን ራሳቸውን ለጌታ ሰተውታልጉዳዩ እኛም የእነርሱን ህይወት መኖር ከብዶን ሳይሆን ያልገባን አንድ ትልቅ ነገር ስላለ ነው፤ ሲገባን ለመስቀሉ ፍቅር እንሞታለን ሲገባን ደስታውን እንጂ ደስታችንን አናይም ሲገባን እየወገሩን ምህረት አድርግላቸው ማለት አይከብደንም ሲገባን ስለ እርሱ አትናገሩ  ብለው ቢወግሩንም እንኳን ስለ ኢየሱስ ማውራት አናቆምም ማነው ይሄን ለክርስቶስ ፍቅር እውር የሚያደርገውን ድንቅ ሚስጢር ከመንፈስ ቅዱስ መማር የሚፈልግ🔥 ኢየሱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ እንዲ አለ " እርሱ ሁሉን ያስተምራቿል ፣ ያሳስባቿል" ከመንፈስ ቅዱስ የተማረ ነው ለክርስቶስ መጨከን የሚችለው... አንዴ ብቻ መንፈስ ቅዱስ እንዲያሰተምረን እድል እንስጠው ከዛም እነ ጳውሎስ ወደው እንዳልተወገሩለት ይገባናል።                        ✍️messager kaleb @kabodartfamily @kabodartfamily
Show all...
መድኅን ዓለም . . . . ♨️አዳም አውራው የትውልድ አባት የመጀመሪያው ሰው፤ በሰይጣን ሽንገላ በራስ ፈቃድ ኃጢአትን በማድረግ ከእግዚአብሔር ኅብረቱን አጎደለ፡፡ ይህም የሰው ልጅ የውድቀት ታሪክ ጅማሮ በመሆን ተመዘገበ፡፡ በኃጢአት የወደቀው አዳም ቀድሞ ከነበረው የእግዚአብሔር ቅድስና ጎድሎ ከኃጢአት እርግማን ሥር ያለ ከርታታ ሆነ፡፡ ከርሱ የተወለዱ በሞላ በዚህ ኃጢአት በሚሉት ወረርሽኝ ይጠቁ ተያያዙ፡፡ ✨የበሽታው አቅም አይሎ የክፋት አስተማሪ መምህር ሳይኖር የሰው ልጅ ልቡ ክፉ ሆነ፡፡ አዳም ባመጣው እዳ ፍርድ ጠባቂ መድኃኒት ፈላጊ በመሆን ባተለ፡፡ ለጆሮ ሰቅጣጭ ለማመን ከባድ የሆኑ ድርጊቶችን በጀብዱ ፈጻሚ ነውር አልባ ሆነ፡፡ ትውልድ በትውልድ ቢተካ ወረርሽኙ ይብስ እንደሆን እንጂ ለአፍታም ከሰው ልጅ ታሪክ ኃጢአት ጎድሎም አያውቅም፡፡ ✨በዚህ ሁሉ መሃል ግን ከውድቀት እንኳን አስቀድሞ በዘለዓለም ውስጥ መፍትሄውን መክሮ የነበረው እግዚአብሔር ለዚህ በዓለም ለገባው የኃጢአት ደዌ ፍቱኑን መድኃኒት አንድያ ልጁን መድኃኒአለም ክርስቶስን ላከ፡፡ እርሱም #ኋለኛውአዳም ነው በፊተኛው አዳም መታመም ሁሉም ደዌን የተቀበለ ቢሆንም በኋለኛው አዳም ግን ታሪክ ሊቀየር ሆነ፡፡ እርሱ #መድህንዓለም ቤዛ ክርስቶስ ነውና የደዌው መድኃኒት ራሱ ነበር፡፡ መድህን ዓለም አመጣጡ ግሩም ነው፡፡ በድንግል ማህፀን በግርግም የተወለደ ጊዜው ሲደርስ ለአባቱ ፈቃድ በመገዛት ነፍሱን ስለኃጢአተኛ ዓለም ቤዛ አድርጎ የሰጠ የዓለም ኃጢአት ያስወገደ የእግዚአብሔር በግ ነው፡፡ ♨️ክብር ይግባውና ኋለኛው አዳም የሰውን ልጅ ከገባበት አዘቅት የደዌ ብዛት አሳረፈ፡፡ ኦ መድህን ዓለም ቤዛ ክርስቶስ ፊተኛው አዳም ያጠፋውን ሊያቀና ሲመጣ ምንም ግድ ብሎት አልነበረም ከ#ፍቅር በስተቀር፡፡ ✨ዓለም ይህንን ይስማ መድህን ዓለም ስለ ሰው ልጅ ኃጢአት በመስቀል ሞቷል፣ የሰውን ልጅ ሊያከብር ከሞት ተነስቷል፡፡ እንኪያስ በሞትና ትንሳኤው ያመነ ከአዳማዊ ደዌ ተፈውሶ በመድህን ዓለም ቤዛን ያገኛል፡፡     #መድኅን_ዓለም_ቤዛ_ክርስቶስ “ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን እንደዚያው አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎቹ ሞተዋልና፥ ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋና በአንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ።”   — ሮሜ 5፥15 ጸጋና ሰላም ይብዛልን❕❕ ✍🏽ተስፋሁን ታረቀኝ @kabodartfamily @kabodartfamily
Show all...
ውዶች ስለ ትላንቱ ፕሮግራም ምትሰጡት ሀሳብ ካላችሁ??!
Show all...