cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

Show more
Advertising posts
559
Subscribers
No data24 hours
+87 days
+2130 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከመቃብር ከተነሳሣ በኋላ አርባ ቀን በሆነው ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ተገልጾ በደብረ ዘይት ተራራ ሁላችሁም ተሰብሰቡ አላቸው ። በዚያም እንደተሰበሰቡ ከእነርሱ እንደ አንዱ ሆኖ ተገለጸላቸውና መቼም መች ከዚያ ሳልለይ በነበርኩበት ወደ ጌትነቴና ክብሬ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ አርጋለሁ ወደ ክብሬና ወደ ጌትነቴ ተመልሼ ካልኬድኩ መንፈስ ቅዱስ ከእናንተ ጋር ሊኖር አይችልም ። ወደ ሰማይ ባረግሁ ጊዜ እኔ እርሱን ወደ እናንተ እልከዋለሁ እርሱም በእኔ ያለውን ኮብር ይገልጽላችኋል እሱ ከእኔና ከአብ ጋር በሕልውና ያለ ነውና። ይህም የሕይወት መንፈስ የጸሐይ ብርሃን በምድር ላይ ወርዶ ወለል አድርጎ እንሚያበራ በእናንተ ላይ ወርዶ ያበራል። እርሱም ባደረባችሁ ጊዜየምትፈልጉትን ሁሉ ይሰጣችኋል በእናንተም ላይ በማደሩ ታላላቅ ተአምራት ለማድረግ ትችላላችሁ። ከእኔና ከአብ ሳይለይ እርሱን ወደ እናንተ እልከዋለሁና። ከዚህም ወደ እርሱ አቀረባቸውና እንኩ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ ብሎ እፍ አለባቸው በዚህ ንፍሐተ እስትንፋስ አዳም ሕያው ነፍስ ያለው ሆኗልና። እንግዲህ እስከ አለም ዳርቻ ድረስ ከሙታን ተለይቼ መነሣቴን እያስተማራችሁ ሰዎችን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አጥምቋቸው የአመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ያልተጠመቀ ግን ነፍሱን አጠፋ። እናንተስ በስሜ አጋንንትን ታወጣላችሁ፣ በሐገሩ ቋንቋ ሁሉ ትናገራላችሁ እባቡንና እፉኝቱንም በእጃችሁ ብትጨብጡ ወይም የሚገድል መርዝ ብትውጡ አንድችም የሚጎዳችሁ ነገር አይኖርም ይልቁንም እጆቻችሁን በሕሙማን ላይ ብታኖሩ ከደዌያቸው ይፈወሳሉ አላቸው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ። ጌታም ይህን በዚያ እንደተሰበሰቡ እየነገራቸው ሳለ ተራራውንም እነሱንም ብርህት ደመና ከበበቻቸው ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የእሳት መሰላል ሠረገላ ተመለከቱ ብዙ የሰማይ ሠራዊት መላእክትም በዙሪያው ተሰልፈው ነበር ። በእጃቸውም መለከት ጸናጽልና ከበሮም ይዘው ነበር መለከቱን በአፋቸው ይነፉታል በዚያም ተራራ ላይ በምድር ላይ ከቶ እንደሱ ያለ ተወዳዳሪ የሌለው ሽታ ሸተተ።አበሞና ቀናንሞ ከሚባለው መልካም ሽቶ ይልቅ የእሱ ሽታ ልዩ ጣፋችነት አለውና ዳግመኛም የእሳት ሠረገላ አዩ በዙሪያውም ልብሳቸው እሳት የሆነ ተሰልፈው ነበር ሁሉም በዚያች መሰላል ወደ ሰማይ ይወጣሉ ወደ ምድርም ይወርዱ ነበር። ከሽቶ ሁሉ ሽታው የሚበልጥንጹሕ እጣን በውስጡ ያለበት የወርቅ ጽና የያዙ መላእክትም አዩ ክንፋቸውም እርስ በእርሱ እየተሳበቀ እንደነጎድጓድ ድምጽን ያሰማ ነበር። ከዚያም የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ፊት ከጸሐይ ብርሃን ከሚሊዮን በላይ የሚልቅ ጊዜ ብልጫ ባለው ብርሃን አሸብርቆ አዩ ። የክርስቶስ ደቀመዛሙርትም ይህን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው እየወደቁ ሰገዱ ታላቅ ፍርሃትና ድንጋጤም አደረባቸው ልቅሶንም አበዙ። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም አይዟችሁ ተነሡ አትፍሩ ድሃ አደግ ትሆኑ ዘንድ አልተዋችሁምና።ነገርግን ከላይ ከሰማይ ኃይልን እስክትቀዳጁ ድረስ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ አላቸው ። ከዚያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሂዶ የጴጥሮስን እጅ ያዘ ያዕቆብንና ዮሐንስንም በእግራቸው አቆማቸውና ለስምዖን ጴጥሮስ የሰማይና የምድር መክፈቻ ሰጠው ለፍርድ ዳግመኛ እስክመጣ ድረስ የሲዖል ኃይሎች  የማያነዋውጧት ቤተክርስቲያኔን በእሷ ላይ የምሠራበት አለት ድንጋይ አንተ ነህ አለው። ከዚያም ዳግመኛ በዓለም እስክታዩኝ ድረስ ከእናንተ መካከል ሞትን የማይቀምሷት አሉ አላቸው ። ቀጥሎም እወቁ በምድር ያሰራችሁትን እኔም እኔ ደግሞ በሰማይ አስረዋለሁ። የፈታችሁትንም ሁሉ እኔ በሰማይ እፈታዋለሁ አላቸው። ከዚያም ንጹሕ የሚሆን ቀኝ እጁን በጴጥሮስ ራስ ላይና በሁሉም ደቀመዛሙርቱ ዘርግቶ እንሆ ሥልጣን ሰጠኋችሁ እናንተ ለሰዎች ኃጢአቱ ይቅር ያላችሁላቸው እኔም ይቅር እልላችዋለሁ ይቅር ያላላችሁላቸውም ይቅር አልላቸውም ። እንሆ የክቡሩን አረጋዊ መልከጼዴቅንና የአሮንን ሥልጣነ ክሕነት ሰጠኋችሁበፍጥረቱ ሁሉ ሰውነት ላይ አሰለጠንኋችሁ ያምኑብኝም ዘንድ መንግሥተ ሰማይን ስበኩላቸው። ንገሯቸው አስተምሯቸው ከምእመናን ወገን የሆነ ሁሉ ከካህናቶቼ አንዱን ወደ ቤቱ ጠርቶ በፍጹም ሃይማኖት ተቀብሎ ቢጋብዘው እኔም ከእርሱ ጋር ወደዚያ እገባለሁ የቤተሰቡን ሁሉ ኃጢአት ይቅር እላለሁ። ማንኛውም ክርስቲያናዊ ሰው በዚህ በአርባኛው ቀን ውስጥ ካህን ጠርቶ በቤቱ በረከት ያልተቀበለ በዚያን በአርባው እለት ወራት የሚጸልየውን ጸሎት አልቀበለውም ኃጢአቱም በመናፍቃን መዝገብ ይመዘገባል። ማንኛውም የስጦታ ሥራ ሁሉ የሚፈጸመው በአርባው ቀናት ውስጥ ነውና ስለዚህ ከመቃብር ከተነሣሁ በኋላ ወደሰማይ የማርግበትን ጊዜ በአረባ ቀን አደረግሁ ። ማንኛውም ሰው ካህንን ለመማታት እጁን ቢዘረጋ በሚቃጠል እሳት ይነዳል ። ከትእዛዜ ማንኛውንም አታፍርሱ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ በማንኛውም ጊዜ ከማንም ሁሉ ጋር ቢሆን በስምምነት ኑሩ ። እወቁ እኔ ወደሰማይ ካረግሁ ከአስር ቀን በኋላ መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ ይወርዳልና ። ዳግመኛም በአስራ አንዱ ደቀ መዛሙርትና በሰብዓው አርድእት ላይ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ባረካቸውና የአሮንን ክህነትና ልዩ ታላቅ ኃይል አሳደረባቸው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ለደቀ መዛሙርቱ ይህን ካደረገ በኋላ በብርሃን ሠረገላ ወደ ሰማይ አረገ። በዚያን ጊዜም ምድር ተናወጠች ተራሮች ተንቀጠቀጡ ዓለም በመላዋ ተነዋወጠች ደመናት ደነገጡ መባርቅትም ድምጻቸውን አሰሙ። መላእክት የተሸከሙት ሠረገላ ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለ ኪሩቤል ከእርሱ ጋር ወጡ በረሩ ሱራፌል ስሙን ቀደሱ ኃይላትና ሥልጣናትም ዕልል አሉ ገብርኤል በሚያምር ጣዕመ ዜማ ዘመረ ሚካኤልም መለከትን ይነፋ ነበር ማኅበረ መላእክት ሁሉሙ በሙሉ ክንፋቸውን ዘረጉ ። የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቶችም በሙሉ ጌታ በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በክነፈ ነፋስ ወደሰማይ ሲያርግ አዩት ከዚያም በላይ በሰማይ እግዚአብሔር ለዘለዓለሙ በእውነት የተመሰገነ ነው የሚል የምስጋና ቃል ሰሙ ።   ይቅርታው ቸርነቱ ለዘለዓለሙ በእውነት ለሁላችን                                ይደረግልን       🙏 🙏 🙏 🙏  🙏  🙏  🙏  🙏 🙏                 ተአምረ ኢየሱስ ዘዕርገት https://t.me/othodox12                   ✨✨✨✨✨✨✨   ✍️
1 3923Loading...
02
#ዕርገት #በአባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ "አሁንም በዓልን ከእኛ ጋር በዓልን እንዲያደርጉ አባቶችን እንጥራቸው። ከሁሉ በፊት አዳምን እንጥራው፡ እነሆ እግዚአብሔር ከገነት በወጣህ ጊዜ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ያለው ተፈጸመ፡ እግዚአብሔር ሥጋን ከሴት ልጅህ ለበሰ በአባቱም ቀኝ በሰማያት ተቀመጠ ይህን የወደድኸውን አምላክነት ከሴት ልጅህ በተወለደ በመለኮት ሰው መሆን አገኘኸው እንበለው። የሕያዋን እናታቸው ስለሆንሽ ሕይወት የተባልሽ ሔዋን ሆይ በሴት ልጅሽ ደስ ትሰኚ ዘንድ ነዪ፡ ሕይወትን አምጥታልሻለችና፡ በታተመ አፈ ማኅፀኗ የወለደችው እርሱ በረከትን ካገኙ ደቀመዛሙርቱ ጋር ቆማ እያየችው ወደ ሰማያዊው አባቱ ዐረገ። ዘፍ. ፫፥፳፪ ሄኖክ ሆይ ከእኛ ጋር በዓል ታደርግ ዘንድ ና ከሞት ፊት የሠወረህ በተሠወረች ሥፍራም ያኖረህ እርሱ ራሱን ከሥጋዊያን ሠወረ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ። የእግዚአብሔርም ወዳጅ አብርሃም ሆይ ከእኛ ጋር በዓል ታደርግ ዘንድ ና። በድንኳን ደጃፍ አጠገብ ባለ የወይራ ዛፍ አጠገብ ከአንተ ጋር የተቀመጠ የሦስት መሥፈሪያ ስንዴ ዱቄት የተጋገረ እንጎቻ የበላ አንተም ርጎና ማር የሰባ ወይፈንም ያቀረብህለት እርሱ ዛሬም ከደቀመዛሙርቱ ጋር በደብረ ዘይት ምሳ አደረገ ከምሳም በኋላ ባርኳቸው ከሴት ልጅህ በነሣው ሥጋ ወደ ሰማይ ዐረገ። ይስሐቅ ሆይ ከእኛ ጋር በዓል ታደርግ ዘንድ ና ከአባትህ ከአብርሃም ሾተል ቀንዶች በሐረግሬሳ በተያዘ በግ ደም የተቤዠህ እርሱ እንደበግ ሊታረድ መጣ ለመታረድም እጆቹን በመስቀል ግንድ ላይ ዘረጋ። በደሙም ሰይጣን የተናጠቃቸውን ተቤዣቸው ቁስላቸውም በሞቱ ቁስል ደረቀ ተነሥቶም የሰውና የመላእክት አእምሮ ወደማይደርስበት ወደ ሰማይ ዐረገ። ዘፍ. ፭፥፳፩ ፣፲፰፥፩-፲፭ ፣ ፳፪፥፱-፲፱ የእግዚአብሔር ሰው ያዕቆብ ሆይ ከእኛ ጋር በዓል ታደርግ ዘንድ ና እነሆ በሎዛ ከምድር እስከ ሰማይ ተተክሎ ያየኸው የወርቅ መሰላል እርሱ በደብረ ዘይት ተተከለ ቁመቱም እስከ አርያም ከፍታ ደረሰ የወልድ ሥጋ ከደብረ ዘይት ወደ ጽርሐ አርያም ከማረጉ በቀር የወርቅ መሰላል ምንድር ነው። ዘካርያስ የእግዚአብሔር እግሮች በደብረ ዘይት ይቆማሉ እንዳለ ለመባረክም እጁን በሐዋርያቱ ላይ ያኖር ዘንድ ቆመ ሰውነቱን ከመለኮቱ ክብር ያሳትፋት ዘንድ ቆመ ሰውነቱን ከመለኮቱ ክብር ያሳትፋት ዘንድ ወደላይ ከፍ ከፍ በማለት ራቃቸው ስለ ሰው ልጆች ፍቅር በምድር ላይ ያገኛት ያለፈው መከራ በቃት አሁን ግን በመለኮት ክብር ዐረገች በአብም ቀኝ ተቀመጠች። ዘፍ. ፳፰፥፩-፳ ፣ ዘካ. ፲፬፥፬ ፣ ሐዋ. ፯፥፶፩ የእግዚአብሔር ልጅ ግን ያለመሰላል በሚንቦገቦግ ደመና ተን ዐረገ መለኮቱ ይተጋለታልና ወደ አየራትም ነጥቆታልና ኪሩቤል ሊያሳርጉት አልመጡም እርሱ ራሱ በመለኮት ኃይል አብን ተካክሎ በቀኝ በኩል ተቀመጠባቸው የማረጉም ምስጋና ለእኛ መሰላል ሆነን። ከገሊላ ሴት እንደተወለደ ባሰብን ጊዜ ወደ አባቱ እንዳረገ እናስታውሳለን። በጭኖቿ እንደታቀፈ ስናስታውሰው በአባቱ እቅፍ እንዳለ እናስባለን። በደብረ ዘይት ከደቀመዛሙርቱ ጋር እንደተቀመጠ ባሰብነው ጊዜ በመላእክቱ እልልታ እንዳረገ በወላጁም ቀኝ እንደተቀመጠ እናስታውሳለን።.... ዳግመኛም የእግዚአብሔርን ሕግ ያስተማረ ሙሴን ከእኛ ጋር በዓል ታደርግ ዘንድ ና ብለን እንጥራው በደብረ ሲና ሕግን የሰጠው እርሱ ለደቀመዛሙርቱ ሸክምን የምታቀል በዳግም ሕግ ያለውንም የርግማን ማሠሪያ የምትሽር ሕግን ሰጣቸው። ወገኖችህን ቀን በደመና ሌሊትም በእሳት ዓምድ የመራቸው በእሳት ዓምድ ወደላከው ወደ አብ ዐረገ። ዘጸ. ፴፩፥፲፰ ፣ መዝ. ፻፬፥፵፰ ነቢዩ ዳዊት ሆይ ከእኛ ጋር በዓል ታደርግ ዘንድ ና! መሰንቆ ከሚመታ ከአሳፍ ከሚዘምር ከኤማን በትንቢት መሰንቆዎች ከሚዘምሩ ከቆሬ ልጆችም ሁሉ ጋር ና 👆እግዚአብሔር በእልልታ ዐረገ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ብለህ አመስግን፤ 👆ዳግመኛም ለአምላካችን መዘመርን ዘምሩ ለንጉሣችንም መዘመርን ዘምሩ ብለህ ዘምር። 👆እንደገናም ዓለምን የሚገዛት ከፍ ከፍ አለ ብለህ አመስግን፤ 👆ዳግመኛም አቤቱ በኃይል ከፍ ከፍ አልህ ኃይልህን እናመሰግናለን እንዘምራለን በል፡ 👆ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ ብለህ አመስግን 🙏 በመጨረሻም #ጌታ_ጌታዬን:- "#ጠላቶችህን_ከእግርህ_መረገጫ_በታች_እስካስገዛልህ_ድረስ_በቀኜ_ተቀመጥ_አለው ብለህ ዘምር። ፩ዜና ፮፥፳፪ መዝ፲፯፥፲ ፣፵፮፥፭ ፣ ፻፱፥፩" (#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ - #መጽሐፈ_ምስጢር )❤❤❤ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/othodox12
1 3287Loading...
03
🔴👉#የ2016 #ጾመ_ሐዋርያት(#ሰኔ_ፆም) 🔷#መቼ_ይገባል ? ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, 🔵👉 ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገር ሁሉ መከልከል ማለት ነው፡፡ ወይም ለሥጋ የሚመቸውን የሥጋ ፍላጎት ሁሉ ስለ እግዚአብሔር ብሎ መተው ማለት ነው። 🔴👉 ጾም እንኳን የጠበቅነውንና ያሰብነውን ቀርቶ ያላሰብነውንና ያልጠበቅነውን ፈጽሞም የማይገባንን ጸጋና ክብር የሚየሰጥ ነው፡፡ 🔴👉 ከሐዋርያት ቤተክርስቲያን በዓልና ትውፊት መሠረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከመጀመሪያዎቹ አብያተ ክርስቲያናት አንዷ ስለሆነች የጾም ሕግና ሥርዓት አላት እነዚህም የፈቃድና የአዋጅ አጽዋማት ይባላሉ፡፡ 🔷👉 ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ የሐዋርያት (የሰኔ) ፆም ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ በየትኛውም አመት ላይ ቢውሉ ሰኞ ቀን ከሚጀምሩት አፅዋማትም አንዱ ነው። 🔴👉 ይህም ጾም የሚፈሰክበት ከሐምሌ 5 የማይለቅ ቢሆንም የሚጀመርበት ግን የተወሰነ ቀን የለውም በዚህም ምክንያት የጾሙ ዕለት ቁጥር ከፍና ዝቅ ይላል አንዳንድ ጊዜ ከአርባ ይበልጣል አንዳንድ ጊዜ ከ30 ያንሣል ያሁኑም ጾም ሰኔ 17 ይገባል፡፡ ❗#ሐዋርያት_መቼ_ጾሙ?❗ 🔷👉 ቅዱሳን ሐዋርያት የአምላካቸውን የመምህራቸውን አርአያ ተከትለው እርሱ ወደ ማዳን ሥራው ማለትም ህሙማነ ሥጋን በተዓምራት ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት ከማዳን አስቀድሞ የስራውን መጀመሪያ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ 40 ቀን 40 ሌሊት እንደ ጾመና እንደጸለየ ሁሉ ቅዱሳን ሐዋርያትም አብነቱን ተከትለው ጾመዋል፡፡ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ዓለምን ዕጣ ተጣጥለው (ተከፈፍለው) ዞረው ከማስተማራቸው አስቀድመው የሥራቸው መጀመሪያን ጾምን አድርገዋል፡፡ 🔴👉 ሐዋርያትም ይህንን ጾም እንደሚጾሙ በጌታችን አስቀድሞ ትንቢት የተነገረለት ቀን የተቆጠረለት ምላሴ የተመሰለለት ታላቅ ፆም ነው። 🔷👉 ይህስ እንደምን ሆነ ቢሉ :- የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው በጠየቁት ጊዜ ተናግሮ ነበር፡፡ ‹‹ እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለምንድን ነው? አሉት ኢየሱስም እንዲህ አላቸው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል በዚያን ጊዜም ይጦማሉ›› ማቴ 9፥15-16 ❗#የሰኔ_ጾም_የቄስ_ብቻ_ነውን?❗ 🔵👉 ይህ ጥያቄ ከብዙ ሰዎች ዘንድ የሚነሣ ጥያቄ ነው ብዙ ምዕመናን የሰኔን ጾም አይፆሙም ለመጾም የሚፈልጉትንም ሰዎች የቄስ ነው እያሉ ሲነቅፉ ይታያሉ ነገር ግን ይህ ጾም ከሰባቱ የአዋጅ ጾም አንዱ ነው ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታቸንን ምሣሌ አድርገው የጾሙት እኛም እነርሱን አርአያ አድርገነው ልንጾመው የሚገባ ታላቅ የበረከት ጾም ነው፡፡ 🔴👉 ዛሬ ዛሬ ግን ብዙ ሰዎች ትተውት ቀሳውስት ብቻ የሚጾሙት ነው ይላሉ ለራስ የከበደን ነገር በሌላው ላይ መጫን ተገቢ አይደለም ካላወቁ ለማወቅ መማር ዐውቆ ከማጥፍት መቆጠብ ተገቢ መሆኑን መዘንጋት አይገባም 🔴👉 እኛ ይህንን ጾም የምንጾመው የሐዋርያትን በረከት ለመላበስ፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን በመሆኑ ይህንን ‹‹መሣሪያ›› አንጣለው ጾሙም ለመላው ክርስቲያን የተሰጠ እንጂ የቀሳውስት ብቻ አይደለም ለቄስና ለምዕመናን ተብሎ በክህነት ደረጃ የተለየ ጾምም የለም፡፡ ❗#እንዴትና_ከምን_እንጹም?❗ 🔵👉 የጾም ሃይማኖታዊ ትርጉም ፈጣሪን መለመኛ ከኃጢአት ቁራኛ መላቀቂያ መሣሪያ ስለሆነ በጾም ወራት ለአምሮት ለቅንጦት የሚበሉ ወይም ለመንፈሳዊ ኋይል ተቃራኒ የሆኑ የአልኮል መጠጦች ሥጋና ቅቤ ወተትና እንቁላል ማራቅ ታዟል። 🔷👉 ሥጋዊ ጉልበትን በጾም የማድከም ቅብአት ካላቸው ምግቦች መከልከልም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አለው ለምሳሌ ዳዊት በመዝሙር 109፥24 ጉልበቶቼ በጾም ደከሙ ሥጋዮም ቅቤ በማጣት ከሳ ብላል ። ዋናው ነገር ጾም እንጂ መብል ወደ እግዚአብሔር አያቀረበንም ብንበላም የምናተርፈው ባንበላም የሚጎዳን ነገር የለም። 🔴👉 ከአዳም ጀምሮ መብል ሲጥል እንጂ ሲያነሣ አላየንምና ጾሙን ከኃጢአት በመራቅ ለራስ ያስብነውን ለነዳያን በመስጠት፣ ጾም ከፀሎት ጋር ሲሆን ጸጋን እንደ ሐዋርያቱ ያሠጣልና በጸሎት በመትጋት በስግድት ወደ እግዚአብሔር በፍፁም ልብ በመመለስ ልንጾመው ይገባል፡፡ 🔷እግዚአብሔር አምላክ ይህን ጾም ባርኮልን የቅድስና ሥራን የምናበዛበት ያድርግልን አሜን፡፡🔵 ❗#ረድኤተ_እግዚአብሔር_አይለየን❗ ፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨ ።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።። ።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።። 🙏⏩ሼር አድርጉ አይከፈልበትም 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/othodox12
1 82620Loading...
04
በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየትና ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ግንቦት ፳፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. ኢትዮጵያ አዲስ አበባ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇share join https://t.me/othodox12
2871Loading...
05
የ ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ ተጠናቀቀ። በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከግንቦት ፳፩ - ፳፰ ቀናት ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም ድረስ በተለያዩ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ እና አገራዊ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመወያየት ውሳኔዎችን አስተላልፏል። በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መግለጫ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅዱሳን አበው ሐዋርያት ትውፊት በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በርካታ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ውይይት ሲያካሄድ ሰንብቷል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት፣ ለመንፈሳዊ ዕድገትና ለምእመናን ደኅንነት ትኩረት በመስጠት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በዚሁ መሠረት፡- 1.በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን መንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፤ 2.በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንኦት ጥሪውን ያቀርባል፤ 3.በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ምክንያት ለፈረሱ የቤተ ክርስቲያናችን ይዞታዎች የከተማ አስተዳደሩ ምትክ ቦታ በመስጠትና ቤተ ክርስቲያናችን ወደ መልሶ ማልማት እንድትገባ ድጋፍ በማድረግ፤ በተለይም ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በፈረሰው የጽርሐ ምኒልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃ ምትክ በከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ወጭ ተጨማሪ ምድር ቤትና የቦታ ስፋት ያለው B+G+4 ሕንፃ ገንብቶ ለማስረከብ ቃል በመግባትና የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ ኃላፊ አባቶች በተገኙበት የመሠረት ድንጋይ እንዲጣል ማድርጋቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ከምስጋና ጋር የተቀበለው ሲሆን በተሰጠን ምትክ ቦታ ላይም የከተማው ፕላን በሚፈቅደው መሠረት የመልሶ ማልማት ሥራው እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 4.የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጅ ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን ቅር አሰኝቷል፡፡ በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡ 5.የብፁዓን አባቶች የዝውውርና የአህጉረ ስብከት ሥያሜን አስምልክቶ የቀረቡ ጥያቄዎችን ምልዐተ ጉበኤው ተመልክቶ ተገቢውን ውሳኔ አሳልፏል፤ 6.የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በረቂቅ አዋጁ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡ 7.በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ አባታዊ ምክርና ተግሣጽ ማስተላለፍ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑ ቢታወቅም በሀገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገለጸ ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ይቻል ዘንድ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉበኤ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ 8.ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ እያወገዘ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና የግብረ ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ 9.በደቡብ የሀገራችን ክፍል የቤተ ክርስቲያኒቱን አብነት ትምህርት ከማስፋፋትና ከፍ ያለ መዐርግ ከመስጠት አንፃር የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የዝጊቲ ደብረ ሰላም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያት ማስመስከሪያ ትምህርት ቤት እንዲሆን በቀረበው ጥናት መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ለምሥክር ጉባኤ ቤቱ ዕውቅና በመስጠት ወደ ትግበራ እንዲገባ ወስኗል፡፡ 10.ከሀገራችን ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀጳጳስ ሲጠየቅ በሙያ ብቃታቸው፣ በምግባራቸውና በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 11.የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲገባ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሠረት ለአፈጻጸሙ ያመች ዘንድ በባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበውን መዋቅራዊ አደረጃጀት በማጽደቅ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዓዋዲው ተካቶ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 12.በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበውን የ2017 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀት በማጽደቅ በሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
2611Loading...
06
✝✞✝ በስመ አብ: ወወልድ: ወመንፈስ ቅዱስ: አሐዱ አምላክ ✝✞✝ "" ግንቦት 27 "" +"+ ቅዱስ አልዓዛር +"+ =>ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያና ማርታ ጋር ይኖር ነበር:: ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት ማርያና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል:: +በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደ ነበር ተገልጧል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደ ነበር ሲነግረን ነው እንጂ:: +ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን ጌታችን በነ አልዓዛር ቤት በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: በመጨረሻዋ ምሴተ ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው:: +ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ አርፏል:: ቅዱሳት እህቶቹ ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል:: (ዮሐ.11:1) ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከ4 ቀናት በሁዋላ ሊያስነሳው ይመጣል:: +ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ:: ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር ተቀበለችው:: "አዳም ወዴት ነህ" ያለ (ዘፍ. 3) የአዳም ፈጣሪ "አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት" አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ:: +ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር አልዓዛር!" ብሎ አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ እንዲህ ታስተምራለች:: (ዮሐ. 11:1-ፍጻሜው) +ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በሁዋላ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ (ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ነውና): ለ40 ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ: በ74 ዓ/ም አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል:: =>የጌታችን ቸርነቱ: የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን:: =>ግንቦት 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አልዓዛር ጻድቅ ሐዋርያ 2.ቅዱሳት ደናግል ማርያ ወማርታ 3.አባ ዮሐንስ ሊቀ ዻዻሳት =>ወርኀዊ በዓላት 1.የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት 2.አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ 3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ) 4.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ 5.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ) 6.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት 7.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት =>+"+ ጌታ ኢየሱስም "ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን?" አላት . . . ይሕንም ብሎ በታላቅ ድምጽ "አልዓዛር ሆይ! ወደ ውጭ ና" ብሎ ጮኸ:: የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ:: ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ:: ጌታ ኢየሱስም "ፍቱትና ይሂድ ተውት" አላቸው:: +"+ (ዮሐ. 11:40-44) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/othodox12
3002Loading...
07
ርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የብፁዓን አባቶች የሀገረ ስብከት ዝውውር መደባ ላይ ውሳኔ አሳለፈ። የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጉባኤው ከግቦት 21 ቀን 2016 ዓም ጀምሮ ባካሄደው ስብሰባ በበርካታ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን፡- በ4ኛ ቀን ውሎው የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትንና የጳጳሳትን ዝውውር ላይ ውሣኔ ማሳለፉን ገልጽዋል፡፡ በዚህም መሠረት፡- 1. ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ከምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ወደ ኤድመንተንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ 2. ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ ከኢትዮ ሶማሌ ሀገረ ስብከት ወደ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ 3. ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ ዳውሮ ኮንታ ሀገረ ስብከትን እንደያዙ የከንባታ አላባ ጠምባሮ ሀገረ ስብከትን ፣ 4. ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ ከምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ወደ የኢትዮ ሶማሌ ጅግጅጋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ፣ 5. ብፁዕ አቡነ ዳንኤል፣ ከምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ወደ የአፋር ሀገረ ስብከት ጳጳስ፣ 6. ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ፣ ከሆሮ ጉድሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ወደ የምሥራቅ ጉራጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ፣ 7. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል፣ ሌሎች አህጉረ ስብከታቸውን እንደያዙ የምሥራቅ ወለጋ ፣ የምዕራብ ወለጋ እና የሆሮ ጉድሩ ወለጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ሆነው እንዲያገለግሉ መመደባቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤትገልጿል። ኢኦቴቤ ቲቪ
1 0543Loading...
08
#ግንቦት_22 #ቅዱስ_እንድራኒቆስ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ሃያ ሁለት በዚች ቀን የከበረና የተመሰገነ ሐዋርያ እንድራኒቆስ አረፈ። ይህንንም ሐዋርያ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መረጠው። እርሱም የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዲሰብኩ ጌታ ከመከራው በፊት ከላካቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የተቆጠረ ነው። በጽርሐ ጽዮንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብሎ በብዙ አገሮች ውስጥ ሰበከ። በኒውብያ አገር ላይም ሐዋርያት በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት በውስጧም ሰበከ በጨለማ በድንቁርና የሚኖሩ ብዙዎች አረማውያንንም የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት አስገባቸው። ከዚህም በኋላ ሐዋርያ ዮልዮስን ወሰደው በአንድነትም በብዙ አገሮች ዙረው አስተማሩ። ብዙ ሰዎችንም አጠመቁ ተአምራትንም በማድረግ ከሰዎች ላይ አጋንንትን አባረሩ። ብዙዎች በሽተኞችንም ፈወሱአቸው የጣዖታትንም ቤቶች አፍርሰው የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናትን አነፁ። አገልገሎታቸውንም በፈጸሙ ጊዜ ጌታችን ከድካም ወደ ዕረፍት ከኀዘንም ወደ ደስታ ሊወስዳቸው ወደደ። ከዚህ በኋላ ሐዋርያ እንድራኒቆስ ታመመና በዚች ቀን አረፈ ቅዱስ ዮልዮስም ገንዞ በመቃብር አኖረው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባቶቻችን ሐዋርያት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት) የእለቱን ስንክሳር ለማግኘት join ያደርጉ share 👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/othodox12
6863Loading...
09
†✝†🌷 እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመገለጥ በዓል (ደብረ ምጥማቅ) በሰላም አደረሳችሁ †✝†🌷 †✝†🌷 ደብረ ምጥማቅ 🌷†✝† =>የአርያም ንግሥት: የሰማይና የምድር እመቤት: የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚሕች ዕለት በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች:: +ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ: +ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ: ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፎ ነበር:: ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር:: +ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ:: እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት 21 ቀን አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች:: +በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም: አሕዛብም ተሰብስበው ለ5 ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ:: እንግዲህ ልብ በሉት:- እንኩዋን የአርያም ንግስት: የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚሕ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን: የመዝናኛው ኢንዳስትሪ ዝነኛ ሰዎችን ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል:: +እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው:: ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው:: +የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው:: ፈልገው የሚያጡት: ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግል: መነኮሳት: መላዕክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና:: እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር:: +እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች: በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል:: 5ቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል:: እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች:: ††† 🌷አባ መርትያኖስ 🌷††† =>አባ መርትያኖስ በበርሃ ከ68 ዓመታት በላይ በቅድስና የኖሩ አባት ናቸው:: ሰይጣን እርሳቸውን ፊት ለፊት ተዋግቶ መጣል ቢያቅተው በዝሙት በተለከፉ ሴቶች ያስቸግራቸው ነበር:: +አንድ ቀን አንዷ ሽቶ አርከፍክፋ በዝሙት ልትጥላቸው ብትል እግራቸውን እሳት ውስጥ ጨምረው እግራቸው እየተቃጠለ በሚወጣው ጠረን አጋንንትን አርቀዋል:: እሷንም በንስሃ መልሰው ለቅድስና አብቅተዋታል:: ጻድቁ ከፈተና ለመራቅ በ108 ሃገራት 108 በዓቶች የነበሯቸው ብቸኛ አባት ናቸው:: ††† ለአባት እናቶቻችን የተገለጠች እመቤታችን ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን:: ጣዕመ ስሟ በአንደበታችን: ጣዕመ ፍቅሯ በልባችን ይደርብን:: ††† =>ግንቦት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት ደብረ ምጥማቅ (የእመቤታችን መገለጥ) 2.አባ መርትያኖስ ጻድቅ (በዝሙት ላለመሰናከል እግራቸውን በእሳት ያቃጠሉ አባት) 3.ቅዱስ አሮን ሶርያዊ 4.ቅዱስ አሞጽ ነቢይ =>ወርኀዊ በዓላት 1.አበው ጎርጎርዮሳት 2.አቡነ ምዕመነ ድንግል 3.አቡነ አምደ ሥላሴ =>+"+ የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ:: ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው:: ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው:: በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . . በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ:: በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ:: ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ:: +"+ (መዝ. 44:12-17) ወስብሐት ለእግዚአብሔር 👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/othodox12
2491Loading...
10
የሮማን_ክፋይ_ኪዳነምህረት♥16 #ሰላም_ነሽ_ለኔ_ፍቅር_በረከት #ስምሽ_ሞገሴ_ክብርሽ_ማዕረጌ #ምን_ብዬ_ልጥራሽ_ድንግል_እናቴ.. #የቃል_ኪዳኗ_እመቤት_ሆይ_አንቺ_እኮ #የመለኮት__ዙፋን_የአለም_እናት #ለታመሙት__ፈውስ #ለተራቡት__ምግብን #ለታመሙት__እርካታን #ለተሰደዱ__ጥንካሬን #ላዘኑ_ዕምነትን #ለሞቱ_የነፍስ_እረፍትን፡ #ለአለማችን ሰላምን የምትሰጪ የጭንቅ አማላጅ እናቴ እመቤቴ ቅድስት #ኪዳነምህረት_ሆይ ልጅሽ በገባልሽ ቃል ኪዳን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ስውሪን ሀገራችንን #ኢትዮጵያን አንቺ በቃል ኪዳንሽ ከውጭም ከሀገር ውስጥ ጠላት ከክፉ ነገር አንቺ ጠብቂልን #የእናታችን_የቅድስት_ኪዳነምህረት እረድኤት በረከት ምልጃ ፀሎት ልመናዋ ጥበቃ እኛን ህዝበ ክርስትያንን አይለየን/አይለያችሁ አሜን፫ 🙏🙏         #መልካም___ቀን🙏 አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች       •➢ 👇  ለማግኘት // 👇
1 3604Loading...

Show all...

👍 1 1

👍 1

Photo unavailableShow in Telegram

Go to the archive of posts
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!