cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

Show more
Advertising posts
536
Subscribers
No data24 hours
-37 days
+1130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✝✞✝ በስመ አብ: ወወልድ: ወመንፈስ ቅዱስ: አሐዱ አምላክ ✝✞✝ "" ግንቦት 27 "" +"+ ቅዱስ አልዓዛር +"+ =>ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያና ማርታ ጋር ይኖር ነበር:: ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት ማርያና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል:: +በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደ ነበር ተገልጧል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደ ነበር ሲነግረን ነው እንጂ:: +ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን ጌታችን በነ አልዓዛር ቤት በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: በመጨረሻዋ ምሴተ ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው:: +ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ አርፏል:: ቅዱሳት እህቶቹ ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል:: (ዮሐ.11:1) ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከ4 ቀናት በሁዋላ ሊያስነሳው ይመጣል:: +ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ:: ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር ተቀበለችው:: "አዳም ወዴት ነህ" ያለ (ዘፍ. 3) የአዳም ፈጣሪ "አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት" አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ:: +ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር አልዓዛር!" ብሎ አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ እንዲህ ታስተምራለች:: (ዮሐ. 11:1-ፍጻሜው) +ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በሁዋላ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ (ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ነውና): ለ40 ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ: በ74 ዓ/ም አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል:: =>የጌታችን ቸርነቱ: የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን:: =>ግንቦት 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አልዓዛር ጻድቅ ሐዋርያ 2.ቅዱሳት ደናግል ማርያ ወማርታ 3.አባ ዮሐንስ ሊቀ ዻዻሳት =>ወርኀዊ በዓላት 1.የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት 2.አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ 3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ) 4.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ 5.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ) 6.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት 7.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት =>+"+ ጌታ ኢየሱስም "ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን?" አላት . . . ይሕንም ብሎ በታላቅ ድምጽ "አልዓዛር ሆይ! ወደ ውጭ ና" ብሎ ጮኸ:: የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ:: ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ:: ጌታ ኢየሱስም "ፍቱትና ይሂድ ተውት" አላቸው:: +"+ (ዮሐ. 11:40-44) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/othodox12
Show all...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

Photo unavailableShow in Telegram
ርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የብፁዓን አባቶች የሀገረ ስብከት ዝውውር መደባ ላይ ውሳኔ አሳለፈ። የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጉባኤው ከግቦት 21 ቀን 2016 ዓም ጀምሮ ባካሄደው ስብሰባ በበርካታ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን፡- በ4ኛ ቀን ውሎው የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትንና የጳጳሳትን ዝውውር ላይ ውሣኔ ማሳለፉን ገልጽዋል፡፡ በዚህም መሠረት፡- 1. ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ከምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ወደ ኤድመንተንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ 2. ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ ከኢትዮ ሶማሌ ሀገረ ስብከት ወደ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ 3. ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ ዳውሮ ኮንታ ሀገረ ስብከትን እንደያዙ የከንባታ አላባ ጠምባሮ ሀገረ ስብከትን ፣ 4. ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ ከምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ወደ የኢትዮ ሶማሌ ጅግጅጋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ፣ 5. ብፁዕ አቡነ ዳንኤል፣ ከምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ወደ የአፋር ሀገረ ስብከት ጳጳስ፣ 6. ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ፣ ከሆሮ ጉድሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ወደ የምሥራቅ ጉራጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ፣ 7. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል፣ ሌሎች አህጉረ ስብከታቸውን እንደያዙ የምሥራቅ ወለጋ ፣ የምዕራብ ወለጋ እና የሆሮ ጉድሩ ወለጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ሆነው እንዲያገለግሉ መመደባቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤትገልጿል። ኢኦቴቤ ቲቪ
Show all...
#ግንቦት_22 #ቅዱስ_እንድራኒቆስ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ሃያ ሁለት በዚች ቀን የከበረና የተመሰገነ ሐዋርያ እንድራኒቆስ አረፈ። ይህንንም ሐዋርያ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መረጠው። እርሱም የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዲሰብኩ ጌታ ከመከራው በፊት ከላካቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የተቆጠረ ነው። በጽርሐ ጽዮንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብሎ በብዙ አገሮች ውስጥ ሰበከ። በኒውብያ አገር ላይም ሐዋርያት በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት በውስጧም ሰበከ በጨለማ በድንቁርና የሚኖሩ ብዙዎች አረማውያንንም የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት አስገባቸው። ከዚህም በኋላ ሐዋርያ ዮልዮስን ወሰደው በአንድነትም በብዙ አገሮች ዙረው አስተማሩ። ብዙ ሰዎችንም አጠመቁ ተአምራትንም በማድረግ ከሰዎች ላይ አጋንንትን አባረሩ። ብዙዎች በሽተኞችንም ፈወሱአቸው የጣዖታትንም ቤቶች አፍርሰው የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናትን አነፁ። አገልገሎታቸውንም በፈጸሙ ጊዜ ጌታችን ከድካም ወደ ዕረፍት ከኀዘንም ወደ ደስታ ሊወስዳቸው ወደደ። ከዚህ በኋላ ሐዋርያ እንድራኒቆስ ታመመና በዚች ቀን አረፈ ቅዱስ ዮልዮስም ገንዞ በመቃብር አኖረው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባቶቻችን ሐዋርያት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት) የእለቱን ስንክሳር ለማግኘት join ያደርጉ share 👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/othodox12
Show all...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

†✝†🌷 እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመገለጥ በዓል (ደብረ ምጥማቅ) በሰላም አደረሳችሁ †✝†🌷 †✝†🌷 ደብረ ምጥማቅ 🌷†✝† =>የአርያም ንግሥት: የሰማይና የምድር እመቤት: የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚሕች ዕለት በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች:: +ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ: +ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ: ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፎ ነበር:: ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር:: +ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ:: እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት 21 ቀን አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች:: +በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም: አሕዛብም ተሰብስበው ለ5 ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ:: እንግዲህ ልብ በሉት:- እንኩዋን የአርያም ንግስት: የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚሕ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን: የመዝናኛው ኢንዳስትሪ ዝነኛ ሰዎችን ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል:: +እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው:: ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው:: +የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው:: ፈልገው የሚያጡት: ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግል: መነኮሳት: መላዕክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና:: እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር:: +እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች: በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል:: 5ቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል:: እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች:: ††† 🌷አባ መርትያኖስ 🌷††† =>አባ መርትያኖስ በበርሃ ከ68 ዓመታት በላይ በቅድስና የኖሩ አባት ናቸው:: ሰይጣን እርሳቸውን ፊት ለፊት ተዋግቶ መጣል ቢያቅተው በዝሙት በተለከፉ ሴቶች ያስቸግራቸው ነበር:: +አንድ ቀን አንዷ ሽቶ አርከፍክፋ በዝሙት ልትጥላቸው ብትል እግራቸውን እሳት ውስጥ ጨምረው እግራቸው እየተቃጠለ በሚወጣው ጠረን አጋንንትን አርቀዋል:: እሷንም በንስሃ መልሰው ለቅድስና አብቅተዋታል:: ጻድቁ ከፈተና ለመራቅ በ108 ሃገራት 108 በዓቶች የነበሯቸው ብቸኛ አባት ናቸው:: ††† ለአባት እናቶቻችን የተገለጠች እመቤታችን ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን:: ጣዕመ ስሟ በአንደበታችን: ጣዕመ ፍቅሯ በልባችን ይደርብን:: ††† =>ግንቦት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅድስት ደብረ ምጥማቅ (የእመቤታችን መገለጥ) 2.አባ መርትያኖስ ጻድቅ (በዝሙት ላለመሰናከል እግራቸውን በእሳት ያቃጠሉ አባት) 3.ቅዱስ አሮን ሶርያዊ 4.ቅዱስ አሞጽ ነቢይ =>ወርኀዊ በዓላት 1.አበው ጎርጎርዮሳት 2.አቡነ ምዕመነ ድንግል 3.አቡነ አምደ ሥላሴ =>+"+ የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ:: ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው:: ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው:: በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . . በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ:: በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ:: ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ:: +"+ (መዝ. 44:12-17) ወስብሐት ለእግዚአብሔር 👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/othodox12
Show all...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

Photo unavailableShow in Telegram
የሮማን_ክፋይ_ኪዳነምህረት♥16 #ሰላም_ነሽ_ለኔ_ፍቅር_በረከት #ስምሽ_ሞገሴ_ክብርሽ_ማዕረጌ #ምን_ብዬ_ልጥራሽ_ድንግል_እናቴ.. #የቃል_ኪዳኗ_እመቤት_ሆይ_አንቺ_እኮ #የመለኮት__ዙፋን_የአለም_እናት #ለታመሙት__ፈውስ #ለተራቡት__ምግብን #ለታመሙት__እርካታን #ለተሰደዱ__ጥንካሬን #ላዘኑ_ዕምነትን #ለሞቱ_የነፍስ_እረፍትን፡ #ለአለማችን ሰላምን የምትሰጪ የጭንቅ አማላጅ እናቴ እመቤቴ ቅድስት #ኪዳነምህረት_ሆይ ልጅሽ በገባልሽ ቃል ኪዳን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ስውሪን ሀገራችንን #ኢትዮጵያን አንቺ በቃል ኪዳንሽ ከውጭም ከሀገር ውስጥ ጠላት ከክፉ ነገር አንቺ ጠብቂልን #የእናታችን_የቅድስት_ኪዳነምህረት እረድኤት በረከት ምልጃ ፀሎት ልመናዋ ጥበቃ እኛን ህዝበ ክርስትያንን አይለየን/አይለያችሁ አሜን፫ 🙏🙏         #መልካም___ቀን🙏 አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች       •➢ 👇  ለማግኘት // 👇
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
🌹🌹🌹እንኳን ለቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ🌹🌹🌹 ኢትዮጵያ ከመላእክት ጋር የሚዘምር ማሕሌታዊ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሚያጥን ካህን የምታፈራ ሀገር ናት። ለሰማይ አገልጋዮችን ገና ሳይሞቱ የምትልክ፣ ከተዋጊዎች መካከል ወደ ድል ነሺዎች መልእክተኛ የምትልክ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ያለች ናት? ቅዱስ ያሬድ በትሕትናው ከትል ተማረ። ትሑታንን ከፍ የሚያደርግ ፈጣሪም ከፍ አደረገውና ከመላእክት ጋር ዘመረ። ትልዋን ከዛፍ አውርዶ ቢጨፈልቃት ኖሮ ለአንድ ሺህ አምስት መቶ ዓመታት ያልነጠፈው የምስጋና ጅረት በሀገራችን ባልፈሰሰ ነበር። ኃይል አለኝ ብለህ የምትጨፈልቃቸው ትሎች ሰማይ የሚያደርሱህ መምህራኖችህ እንዳይሆኑ ተጠንቀቅ ይላል የታሪኩ ተግሣፅ። ቅዱስ ያሬድ እግሩን በጦር እየተወጋ እንኩዋን ዝማሬው ሰማያት ወስዶት አልተሰማውም ነበር። የእኛው ሲላስ የእኛው ጳውሎስ ቅዱስ ያሬድ ሆይ በዘመርክባት ሀገርህ ዛሬ ብዙ ጦር ተሰክቶባታል። ከአንተ ዜማ በቀር ዛሬም መጽናኛ የለንምና በምልጃህ አስበን። ጥዑመ ልሳን ያሬድ: ሊቀ ጠበብት ያሬድ: ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ የቤተ ክርስቲያን ጌጥ!! 👇👇👇👇👇👇👇
Show all...
👍 1
††† እንኳን ለቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ ††† ††† አናንያ : አዛርያና ሚሳኤልን እንዲያው በቀድሞው አጠራር ሠለስቱ ደቂቅ (ሦስቱ ሕጻናት) እንላቸዋለን እንጂ ለእኛስ በእድሜም : በጸጋም : በትሩፋትም አባቶቻችን ናቸው:: ቅዱሳኑ የወቅቱ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጆች ናቸው:: ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ ሕዝቡን ሲማርክ አብረው ተማርከው ባቢሎን ወርደዋል:: ንጉሡ ከምርኮ ወጣቶች ለቤተ መንግስት ሲመርጥ ሦስቱ ቅዱሳንና ዳንኤል ተመርጠው የምቾት ሕይወት ተዘጋጅቶላቸው ነበር:: ነገር ግን በምግብና በአምልኮ ከአሕዛብ ጋር መተባበርን አልፈለጉምና ምርጫቸው ጾምና ጸሎት ከቆሎ ጋር ሆነ:: ምንም እንኳ በቤተ መንግስት ውስጥ ቢኖሩ : ምንም የነገሥታት ልጆች ቢሆኑ ለእነርሱ ከእግዚአብሔር ፍቅር የተሻለ አልነበረምና በጥሬ ቆሎ ተወስነው ኖሩ:: አምላካቸው ከሃሊ ነውና በውበትም ሆነ በጥበብ በባቢሎን ምድር ከነርሱ የሚደርስ አልተገኘም:: ንጉሡም በባቢሎንና በአውራጃዋ ላይ ሾማቸው:: ስማቸውንም በአማልክቱ ስም ሲድራቅ : ሚሳቅና አብደናጐ አላቸው:: ከነገር ሁሉ በኋላ አሕዛብ ቀንተውባቸዋልና የክፋት አዋጅን አሳወጁ:: ናቡከደነጾር 60 ክንድ ቁመት ያለውን የወርቅ ምስል አቁሞ "ስገዱ" ቢላቸው አይሆንም በማለታቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ እሳት ተፈረደባቸው:: ነበልባሉ ከጉድጓዱ ወደ ላይ 49 ክንድ ቢነድም ቅንጣት ያህል ፍርሃት አልጎበኛቸውም:: ወደ እሳቱም ሲጥሏቸው መልዐከ አድኅኖ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ አዳናቸው:: ከሆነው ነገር የተነሳ አሕዛብ አፈሩ:: ናቡከደነጾር ግን ከዙፋኑ ተነስቶ የቅዱሳኑን አምላክ እግዚአብሔርን ባረከ:: ከዚያች ቀን በኋላ አናንያ : አዛርያና ሚሳኤል በአት አጽንተው : በጾምና በጸሎት ተወስነው ኑረዋል:: ነፍሳቸው ከሥጋቸው ስትለይ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆኗል:: ቅዱስ ዳንኤልና ናቡከደነጾር ተሯሩጠው ቢሄዱ ሦስቱም በአንድነት ዐርፈው ተገኝተዋል:: ንጉሡ በእጅጉ ይወዳቸው ነበርና በወርቅ በተለበጠ ሳጥን ቀብሯቸዋል:: ስሞት ከመካከላቸው ቅበሩኝ በማለቱ ዛሬ ድረስ ለበቁ አባቶች የአራቱ መቃብር ባቢሎን ውስጥ ይታያል:: ቅዱሳን አናንያ : አዛርያና ሚሳኤል (ሲድራቅ : ሚሳቅና አብደናጐ) ያረፉት ግንቦት 10 ቀን ሲሆን ዘመኑም ከክርስቶስ 500 ዓመት በፊት ነው:: ††† አምላካቸው ከእሳት ባወጣቸው ቀንም:- "ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ:: ስቡሕኒ ውዕቱ ወልዑልኒ ውዕቱ ለዓለም::" የሚለውን ምስጋና ፈጣሪ ገልጾላቸው ደርሰውታል:: (በእሳቱ ውስጥ ሆነው ተናግረውታል:: ) ድርሰታቸው 2 ወገን ሲሆን ባለ ስድስት አንቀጹ ምስጋናቸው ከ600 ዓመት በኋላ ክርስቶስ እንደሚወለድ የሚያሳይ ነው:: ሌላኛውና 33 አንቀጾች ያሉት ምስጋናቸው ደግሞ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ለ33 ዓመታት እንደሚመላለስ ያጠይቃል:: ቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ ካረፉ ከ900 ዓመታት በኋላ (ማለትም ከክርስቶስ ልደት በ400 ዓመታት) ታላቁ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ቤተ ክርስቲያንን አንጾላቸው ነበርና አጽማቸውን ሊያገኝ ተመኘ:: ወዳጁን ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ጠርቶ "አባ! አጽመ ቅዱሳንን ባቢሎን ወርደህ አምጣልኝ?" አለው:: ቅዱሱ ሐጺር ዮሐንስም በደመና ተጭኖ ባቢሎን ገባ:: በቅዱሳኑ መቃብር ፊትም ሰግዶ አለቀሰ:: ሠለስቱ ደቂቅም "ወዳጃችን! ምን ሆንክ?" አሉት:: ቅዱሱም መልሶ "ወደ ግብጽ እንሒድ:: አባ ቴዎፍሎስ ይፈልጋቹሃል" አላቸው:: እነሱም "ለቅዱሱ ቴዎፍሎስ እንዲህ በለው:: እግዚአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ:: ግን አጽማችን እስከ ዓለም ፍጻሜ ባቢሎንን አይለቅም:: ለክብርህ ግን እንመጣለን::" "ለምልክትም ይሆን ዘንድ መብራት ሳታበራ በሌሊት ጠብቀን በለው" ብለው ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ባርከው ሸኙት:: ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርም መጥቶ መልእክቱን አደረሰ:: በዕለተ ቅዳሴ ቤታቸው ቅዱሳን:- ቴዎፍሎስ : ቄርሎስ : ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና ሌሎችም ከምዕመናን ጋር በጨለማ ሳሉ ቤተ ክርስቲያኑ ቦግ ብሎ በራ:: እጅግ የሚደነቅ ብርሃንም ከበባቸው:: በብርሃኑ መካከል ሠለስቱ ደቂቅ ሲያልፉ በጐ መዓዛ ሸተተ:: ሕዝቡም በደስታና በዝማሬ የቅዱሳኑን ቅዳሴ ቤት አክብሯል:: ††† በረከታቸው ይደርብን:: ††† ግንቦት 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ሠለስቱ ደቂቅ ቅዱሳን (አናንያ : አዛርያና ሚሳኤል) 2.ቅዱስ አብርሃም ጸራቢ (ሰማዕት) 3.አባ ሚካኤል ገዳማዊ 4.አባ ይስሐቅ ግብጻዊ ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ 2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ 3.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ 4.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ 5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ) 6.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት 7.ቅዱስ ዕፀ መስቀል ††† "ናቡከደነፆርም መልሶ:- መልአኩን የላከ : ከአምላካቸውም በቀር ማንንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን : የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን : በእርሱ የታመኑትን ባርያዎቹን ያዳነ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ::" ††† (ዳን. 3:28) ✍ወስብሐት ለእግዚአብሔር 👇👇👇👇👇👇👇👇👇join 🙏https://t.me/othodox12 share
Show all...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

👍 1
          📖ዳግም ትንሣኤ       📖ዳግም ትንሣኤ ለምን ተባለ? በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ሰሙነ ሕማማትና ሰሙነ ትንሣኤን እንድናከብር ቀደም ሲል በዲዲስቅልያ ኋላም በፍትሐ ነገሥት ታዝዟል፡፡ “እስመ ሰሙነ ዐብይ ሰሙነ ሕማማት እንተ ትተልዋሄ ሰሙነ ትንሣኤ ወዘይትፈቀድ ከመ ናእምር እስመ ዘሐመ ናሁ ትንሣአ” ሲል ይገኛል፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 19 ፤ የሰሙነ ትንሣኤ መጨረሻው ስምንተኛው ቀን ዳግም ትንሣኤ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣው አንድ ጊዜ ነው፡፡ ዳግም ትንሣኤ ለምን ተባለ?      📖ዳግም ትንሣኤ የተባለበት ምክንያት፡- በአከባበር፥በሥርዓት የመጀመሪያውን ትንሣኤ ስለሚመስል ነው፡፡የትንሣኤ ዕለት የሚባለው ቃለ እግዚአብሔር ሳይለወጥ፤በሙሉ በዚህ ቀን ይደገማል፡፡ ከዚህም ሌላ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት፡፡ እነዚህም “ፈጸምን አግብዓተ ግብር” ይባላሉ፡፡ “ፈጸምነ” የተባለበትም፤ ሰሙነ ትንሣኤ በዓል አክብረን ፈጸምን ማለት ነው፡፡ “አግብዓተ ግብር” የተባለበትም፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “አባ ወአቡየ ግብር ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ… እኔ ልሠራው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር ላይ አከበርሁህ” ያለውን ከቅዳሴ በኋላ ሊቃውንት በዚህ ቀን ስለሚዘምሩት ነው፡፡ ዮሐንስ 7፥4 በተጨማሪም የሐዋርያው ቶማስ ምስክርነት የሚታሰብበት ነው፡፡ ዳግመኛ ከስምንት ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ በዝግ ቤት ሳሉ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ሳለ ደጁም ተዘግቶ ሳለ፥ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ በመካከላቸው ቁሞ እንዴት ሰነበታችሁ አስታረቅኋችሁ” አላቸው፡፡ ሁለት ሰዓት አሳልፎ ስለመጣ “እምድኅረ ሰሙነ” አለ እንጅ፥ በስምንተኛው ቀን ሲል ነው፡፡ በመጀመሪያው መገለጡ ያልተገኘው ሐዋርያው ቶማስ ትንሣኤውን አላመነም ነበርና፤ “ጣትህን ወደዚህ አምጣ እጆቼንም እይ፤ እመን እንጅ ተጠራጣሪ አትሁን” አለው፡፡ ቶማስም መለሰ “ጌታዬ አምላኬ ሆይ” አለ፡፡ መዳሰሱን ሲያይ “ጌታዬ”፤መቃጠሉን ሲያይ “አምላኬ ሆይ “አለ፡፡ ገቦ መለኮቱን የዳሰሰች እጁ ሕያዊት ሁና፤ (በሕይወት ትኖራለች)በሕንድ አገር ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ያስቀምጧታል፡፡ በዓመት በዓመት በእምቤታችን በዓል በአስተርእዮ ሊያጥኑ ሲገቡ፥ የሚሾመውን ወጥታ ቀኝ እጁን ትይዘዋለች ዓመት አገልግሎ ያርፋል፤ እንዲሁ በዓመቱ የሚሾመውን ተራምዳ ትይዘዋለች፤ እንዲህ እያለች ትኖራለች፡፡ ይህም የሚያስተምረን የጌታን ተአምራት፤ የሐዋርውን ሥልጣንና ብቃት ነው፡፡ጌታም ቶማስ ሆይ! ብታየኝ አመንክን? ሳያዩኝ የሚያምንብኝ ብፁዓን ናቸው አለው፡፡ ዮሐ 21፥24–29 ለብርሀነ ትንሣኤው ያደረሰን አምላካችን፥ፍጻሜ ሕይወታችን በሃይማኖት የቀናን፤ በምግባር የጸናን ያድርገን! አሜን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን ።አሜን 👇👇👇👇👇👇👇👇ሼር https://t.me/othodox12
Show all...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

#በስተመጨረሻ_ይዘነው_የምንሄደው_ምንድን_ነው? 🥀ጠቢቡ ሰለሞን ሁሉን አየ ሁሉን አጣጣመ በስተመጨረሻ “ሁሉም ከንቱ ነው የከንቱ ከንቱ፤ ነፋስንም እንደመከተል ነው” ሲል ኑሮን ደመደመ። እንደኔ ሁሉም ከንቱ ነው ሲል ተስፋ ሊያስቆርጠን አይመስለኝም፤ ተስፋን ሊሰጠን እንጂ። ህይወታችን ከማንኛውም አለማዊ ሃብት፤ ከማንኛውም ዝና ከማንኛውም ክብር የላቀች መሆኗን ሲነግረን ይመስለኛል። ይህንን በቅጡ መረዳት ስለሚሳነን፤ በስተመጨረሻ ይዘናቸው በማንሄዳቸው አላፊ ነገሮችን ኑሮዋችንን እንበጠብጣለን። 🥀ኑሮ ማለት በውልደት እና በሞት መካከል ያለ የመሸጋገሪያ ጊዜ ነው። በድንገት ተጀምሮ በድንገት የሚቆም የመሸጋገሪያ ጊዜ። ጥቂቶች ይህንን የተረዱ ጊዜያቸውን አጣጥመው ይኖራሉ። አብዛኛዎቻችን ግን ዘላለም እንደሚኖር ሰው ተዘናግተን እንኖራለን። መልካም ነገር ሳናደርግባቸው በተራ ነገር የሚያልፉ ቀናቶች ከቆምንበት ህንጻ ስር እየተሸረፉ እንደሚወድቁ ጡቦች ይቆጠራሉ። ቀስ እያሉ ከከፍታው የሚያወርዱን። 🥀ሁሉም ከንቱ ነው የከንቱ ከንቱ ምክንያቱም ምንም ነገር በሞት ፊት ቆሞ ሞትን የሞጋፈጥ ነገር ስለሌለ። ይህን የተረዳ ሰው ትልቁን ቀንበር ከላዩ ላይ አወረደ ማለት ነው። የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ከልቡ ያደርጋል ምክንያቱም እድሉ አንደ ብቻ እንደሆነች ስለሚረዳ። እውነት ከሞት ፊት ቆሞ በቀልን የሚያስብ ማነው? ከመቃብሩ ላይ ቆሞ ገንዘቡ የሚያሳሳው ማነው? በከፈን ውስጥ ሆኖ የሚጠላውን ሰው የሚያስብ የሚቀና ማን ነው? በእርግጠኝነት ማንም። በሞት ፊት ሁሉም ነገር ከንቱ ነው፤ የከንቱ ከንቱ። 🥀በስተመጨረሻ ይዘነው የምንሄድ ምንም ነገር የለም።ይልቅ የመሸጋገሪያ ጊዜያችንን መልካም እናድርገው። ተሰጥዖችንን እናበርክት፤ ማናችንም ያለተሰጥዖ አልተፈጠርንም። ተራ ሆነን መሞትን አንምረጥ። የራሳችንን አሻራ አኑረን፤ ነበሩ ለመባል ያብቃን። ሰለሞን ከንቱ ናቸው ያላቸው ነገሮች ህይወታችንን የሚያጨልሙና የምድር ቆይታችንን መራራ የሚያደርጉትን ነገሮች ነው። ህይወታችን ክቡር ናት፤ ከማንኛውም ነገሮች ሁሉ የከበረች የፈጣሪ ስጦታ። እኛ ግን በኪሳራ እየቸረቸርናት ነው። ፍቅር የሌላት ህይወት፤ እምነት የራቃት ህይወት፤ ሰላም የጎደላት ህይወት፤ ደስታ የሌለባት ህይወት ያለዋጋዋ የተሸጠች ናት። ምክንያቱም በዚህ ምድር የህይወታችንን ዋጋ የሚስተካከል አለማዊ ነገር ስለሌለ። 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/othodox12
Show all...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

. ❤ልደታ ለማርያም❤ግንቦት ፩ እንኳን አደረሰን!!! 💟ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር: 💟እነዚህም በእግዚአብሄር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ:እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሄርም በሰውም ዘንድ የበቁ ባለጸጎች ነበሩ:ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውምና መካን ነበሩ:አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን: 💟አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት:እርሱአም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚ ያለ ነገር እንኩአንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት: 💟እሱአም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም:ትላንትና ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋም ፀሃይን ስትወልድ አየሁ አለችው:: 💟እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው:ያም ህልም ፈቺ እግዚአብሄር በምህረቱ አይቱአቹአል በሳህሉ መግቡአችሁአል 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዱአ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹ የፀሃይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው: 💟እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሱአም እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች: 💟ከዛም ፀንሳ በ9 ወሩአ ሴት ልጅ ወለደች:ስሙአንም ሄሜን ብለው አወጡላት:ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኑአም ደርዲ ብለው ስም አወጡላት:ደርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና ቶና አለቻት:ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት;ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት:ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት:ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደውን ሃናን ወለደች:: 💟ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆተረላቸውምና አልተፃፈም:ይህቺም ሃና በስራት በቅጣት አደገች:ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው(መጽሃፍ ቅዱስ ይገልጸዋል) ከቅዱስ እያቄም ጋር አጋቡአት:: 💟እነዚህ ቅዱሳን እያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ:ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ: 💟ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ:እያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው አትጣለኝ:አትናቀኝ:ፀሎተን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ:ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ:ሃናም በበኩሉአ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው:ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች: 💟እንዲ ብለው ስይዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቹአ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኅኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች: 💟እንዲ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሄርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን:ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስለት ገቡ:: ዘካርያስም እግዚአብሄር ጸሎታችሁን ይስማላቹ ስእለታችሁን ይቀበልላቹ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላቹ ብሎ አሳረገላቸው: 💟ከዚያም በሁአላ ቅድስት ሃና እና ቅዱስ እያቄም እለቱን ራእይ አይተው ነገር አግንተው አደሩ:ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት: 💟ወፍ የተባለው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው:ነጭነቱ ንጽሃ ባህሪው ነው:ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱ:የኢያቄምን ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው እወቅ ሲል ነው:7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባህሪው:ምልአቱ:ስፍሃቱ:ርቀቱ:ልእልናው:ዕበዩ መንግስቱ ናቸው:ሃናም እኔም አየሁ አለችው:ምን አየሽ ቢላት:ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ አለችው:: 💟ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት:ነጭነቱአ ንጽህናዋ:ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው:ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቱአ ብስራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መፀነሱአ ነው:ይህንኑም ራእይ ያዩት ሃምሌ 30 ዕለት ነው:: 💟እነሱም እንዲ ያለ ራዕይ ካየን:ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም:ፈቃደ እግዚአብሄር ቢሆን ብለው አዳምንና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7 ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ: 💟ነሃሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ዓለሙ ሁሉ ተሰብስቦ ቢመዘን አንድ የራሱአን ፀጉር የማያህል ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ስጋ ተገናኙ ብሎአቹሃል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሃና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሄር በብስራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ተፀነሰች(በኦሪት ስርአት እሁድ ዕለት ባል እና ሚስት መገናኘት ልማድ ነበርና): 💟እመቤታችን የተፀነሰች ዕለት አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ:ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት:የሃናም የአጎቱአ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቹአ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ቆዩአት: 💟እርሱአም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነስቶ ስብሃት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሃየ ጽድቅ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስቅዱስ ጽርሃ ቤቱ ተፈስሂ ደስ ይበልሽ ብሎ ሰገደላት:አይሁድ ከዛ ነበሩና ምነው ሳሚናስ ምን አየህ? ምን ትላለህ? ቢሉት ከዚች ከሃና ማህፀን የምትወለደው ህፃን ሰማይ ምድርን:እመቅ አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኑአት ሰማሁአቸው እኔንም ያነሳችኝ የፈወሰችኝ ያዳነችኝ እርሱአ ናት አላቸው በል ተወው ሰማንህ ብለው ቅናት ጀመሩ:: ❤""እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች::"" 💟እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም የተወለደችበት እለት በአባት እናቱአ ቤት ፍስሃ ደስታ ተደረገበት ቤቱንም ብርሃን መላው በስምንተኛውም ቀን ""ማርያም"" ብለው አወጡላት::
Show all...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

1