cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አንድነት በጎ አድ. ማኀበር

❤አቅመ ደካሞችን መርዳት፦ ሥነ ልቦናዊ እኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ውስጥ ያሉትን ሰዎች እንደርስላቸዋለን እንረዳቸዋለን።❤ አንድነት በጎ አድራጎት ማኅበር (አበአማ)❤

Show more
Advertising posts
198Subscribers
No data24 hours
-27 days
-330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Repost from N/a
እንደምን ከረማችሁ ወዳጆች ከነገ ጀምሮ ስለ ሕማማት ሳምንት በጣም ምገራርሙ ትምህርቶችን እንከፋፈላለን በደምብ ለመከታተል ሞክሩ ! ደግሞ ወዳጆቻችንን በመጋበዝ እንድንተባበር በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ የሕማማት ሳምንት ትምህርት በተላይ ጌታችን ኢየሱስ በሕይወቱ ማብቂያ ላይ የተናገራቸው የኑዛዜ ንግግሮችም ስለሆኑ ትኩረት ልሰጥበት ይገባል ። እንግዲህ በትዕግሥትና በትህትና እንትጠብቁኝ በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ ። I love so much in the chirst name Join us https://t.me/ZOEEternallife Join us https://t.me/ZOEEternallife
Show all...
ZOE (ዞዊ) Eternal life

የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና። ቆላ 3:24 ማደግህ በነገር ሁሉ እንድገለጥ ይህን አስብ ፥ ይህንም አዛወትር... ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና። 1ጢሞ 4:15-16 @ዞዊ ማለት የእግዚአብሔር ሕይወት ወይም ዘላለማዊ ሕይወት ማለት ነው ። መገኛ ምንጩም የኢየሱስን ሞትና ትንሣኤውን በማመን ነው ።

#ሊሞቱ_የደረሱ_ሰዎች_የሚቆጫቸው_10_ነገሮች በተለያየ ህመም ምክኒያት በህይወት ጥቂት ጊዜ የቀራቸው ሰዎች ቀሪ ጊዜያቸውን ያለ ስቃይ እንዲያሳልፉ ህክምና የሚያገኙበት ቦታ Hospice ይባላል። ሆስፒስ ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች እነዚህን ከጥቂት ሳምንታት እስከ ጥቂት ወራት የቀራቸው ሰዎች በህይወታቸው ምን እንደሚቆጫቸው ጠይቀዋቸው የሚከተሉትን 10 ነጥቦች አግኝተዋል። 1) ደስተኛ አልነበርኩም- ህይወቴን በሚገባ enjoy አላደረግሁም። 2) በእውቀት ራሴን አላሳደግሁም። ለመማር ብዙ እድል ነበረኝ ግን አልተማርኩም። 3) እራሴን አልተንከባከብኩም-ጥሩ እንቅልፍ አልተኛሁም፤ ስፖርት አልሰራሁም፤ አመጋገቤ ላይ አልተጠነቀቅኩም፤ የጤና ምርመራ በሰአቱ አላደረግሁም። 4) የኖርኩት በቂምና በጥላቻ ነው-ሁሉም ነገር እንደዚህ ማለፉ ለማይቀር ለምን በቂምና በጥላቻ ራሴንም ሰዎችንም ጎዳሁ? 5) ለቤተሰቤ ጊዜ አልሰጠሁም-ላይ ታች ስል ከልጆቼ ጋር አልተጫወትኩም፤ ወላጆቼን እንደምወዳቸው አልነገርኳቸውም። አብሬያቸው ጊዜ አላሳለፍኩም። 6) ሰዎችን አልረዳሁም- ብዙ የእኔን እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ነበሩ። አቅሙ እያለኝ እኔ ግን 'ቢዚ' ስለነበርኩ አልደረስኩላቸውም። 7) ህልሜን አልኖርኩም- ለብዙ አመታት ለአንድ መስሪያቤት ተቀጥሬ ነው የሰራሁት እንጂ የራሴን ህልም አልኖርኩም። 8) ያለምክኒያት ነው የለፋሁት- በማይጠቅሙኝ ነገሮች ተጠምጄ በጣም ስለፋ ነበር። 9) ለሰዎች ፍቅሬን አልገለፅኩም- ለምወዳቸው ሰዎች 'እወድሀለሁ' ወይም 'እወድሻለሁ' አላልኩም።ፍቅሬን ከመግለፅ ይልቅ እኮሳተራለሁ። 10) ሀይማኖትን እንቅ ነበረ- መንፈሳዊነትን እጠላ ነበር። አሁን መጨረሻዬ ላይ እስከምደርስ ወደ አምላኬ ዞር አላልኩም ነበር። ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ Dawit Dreams ላይ ከተናገረው የተወሰደ። ሞት መቼ እንደሚመጣ አይታወቅም። በየሰአቱ በአለማችን 7500 ሰዎች ይሞታሉ። በየቀኑ በአለም አቀፍ ደረጃ 180ሺ ሰዎች ይሞታሉ። ሞት ማን ጋር መቼ እንደሚመጣ አይታወቅም።  ደስተኛ ሆነን፣ ህልማችንን እየኖርን፣ ራሳችንን እየተንከባከብን፣ብዙም ኮስታራ ሳንሆን፣ ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ጊዜ እያሳለፍን በይቅርታ ልብ እንዲሁም በመንፈሳዊነት መኖር ሞት ሲመጣ እዳንፀፀት የሚያግዙ ነጥቦች ይመስሉኛል። @UoG_Psych
Show all...
Repost from N/a
ክፍል 10 👍.....እንደቀጠለ ነው ሐይሚ የተስፍሽን ተጣረች፡ ወዬ ! ወዬ...አቤታ አበዛ። ሐይሚን አሁንም ብስጭት እያከነፋት ነው ፡ ንዴትና ቁጣም ግንፍልፍል ይልባታል። ፊቱዋ ተጨማዶ ፡ ጸጉሩዋ መንጨባረር ጀምሯል። ምክንያቱም የምረዳት ሰው አላገኘችምና ። የክርስቲ ቢሽቂያ ፣ ከቡና ቤቱ የወጣው የወጣቱ ጉዳይና የብሬ መመጻደቅ ተደራርቦባት ትንሽ በልቡዋ ተናጠች ። ነገር ግን አሁንም ዝምታን መረጠች ። ለምን ? ግን ለምን ...ዝም ! ዝምታ ግን አመራጭ ይሆናል ? በአንድ ዓይኑዋ ክፋት እያየች ! በአንደኛዋ ደግሞ ሽንገላን እየተመለከተች ! በሁለቱም ዓይኖቹዋ ደግሞ ያልበሰለ ክርስቲያን ! ግን ለምን ዝም ትላለች ? እውነትን አፍኖ፡ደብቆ፡ አምቆ ከመያዝ አውጥቶ ተናግረው ከእውነት ጋር መሞት አይሻልም ። ለነገሩማ ውሸት ደምቆ ሸብርቆ ቢኖር ብብለጨለጭ ለጊዜው ነው ይሞታል ። እውነት ግን ብጓሳቆልም ቀና ይላል ፣ ብታፈንም ይወጣል ፣ ብሞትም ሕያው ሆኖ ይነሳል ። ለውሸት ከሞት በኃላ ዋስትና የለውም ! እውነት ግን ትንሣኤ አለው ! እኛስ ከእውነት ጋር ሞተን ብንነሳ አይሻልም ? የውሸት አባት ሳይጣን ነው ፤ የእውነት አባትም ባለቤትም ራሱም እውነት የሆነ ኢየሱስ ብቻ ነው ። ።።።።።።። ይቀጥላል ።።።።።።..... https://t.me/FishTemesgen share comment like subscribe
Show all...
ሕብረት ምንድነው?? ሕብረት ማለት የአሳብ አንድነት ወይም የአካል አንድነት ያለበት የተለያዩ ነገሮች ተዋሕዶ ወይም ቅንጅት ነው ። ምን አልባት ሕብረቱ የሰው ከሆነ ደግሞ ብዙ ትርጉሞችን መስጠት ይቻላል። በተረቱ ድር ቢያብር አምበሳ ያስራል እንደምባለው ሰዎችም ሲያብሩ የማያደርጉት ነገር የማይንዱት ተራራ የማይፈነቅሉት ድንጋይ አይኖርም ዋናው አንድነቱ ከአካል ባለፈ የልብም ይሁን እንጂ። አንድነት አንድ አይነትነት አይደለም ግን የተለያዩ አመለካከትና ሀሳብ ያላቸው አካላት ለአንድ ዓላማ የሚቆሙበት የስምምነት መንገድ ነው። ሕብረት ደግሞ የአንድነት ውጤት ነው። በሕብረት ውስጥ አንድነት ከሌላ መለያየት ይፈጠራል። በእርግጥ በሕብረት ውስጥ መለያየት አይገባም ተብሎ ባይታሰብም የሕብረት ትርጉም ያልገባቸው ሰዎች ሁሌም የሕብረት መፍረስ መዋጮ ይሆናሉ። ጠንካራ ሕብረቶችን ምገነቡና ምመሠርቱ ጀግኖች እንዳሉት ሁሉ ያንን የሚያወድሙ ሰዎችም እንዳሉ ነው ። በሕብረት ውሰጥ መለያየት እንዳይኖር ከተፈለገ ከራስ ይልቅ ሌሎችን መውደድ ፣ ከራስ ደስታ በላይ የሌለውን ደስታ ማስቀደም፣ከግል ፈላጎትና ስሜት አብልጦ ለሌሎች መቆርቆር ሕብረትን ለማጽናት ወሳኝ ንጥረ ነገሮች ናቸው። በሕብረት ውስጥ ትልቅ እንቅፋት የምሆን ጉዳይ የግል ነጻነት የሚባል ነገር ነው። ነጻነታችን የሌሎችን ነጻነት ምጋፋ ከሆነ ከመጀመሪያውም ነጻነት አይደለም ወይም አጠቃቀሙን አላወቅንበትም ይሆናል።(ነጻነት የሚለውን ሀሳብ በዚህ ቻናል ወደ ላይ ሄዳችሁ ፈልጋችሁ ማንበብ ትችላላችሁ) በአጠቃላይ ሕብረት ለሁሉም ነገር መሠረታዊ ነገር የሚሆንበት ሁኔታ ይኖራል ግን ከራሱ ጋር ያልሆነ ሰው ከሰው ጋር መሆን አይችልም Thanks Fish T
Show all...
👍 1
እርዕስ ያዘነልኝ ማን ነዉ(ሉቃስ 10-30_36 ከለታት አንድቀን መንደር ለመቀየር ከሰፈሬ ወጣሁ ሰፈሬንም ትቼ ጉዞኤንም ጀመርኩ ሠፈሬንም ትቼ ትንሽ እንደሔድኩኝ ያዉም ባጋጣሚ ወንበዴ አገኙኝ እንደዉ ሣላስበዉ እኔን በጣም ጎዱኝ በሞትና በህወት መካከልም ተዉኝ ያዉም በዚያ መንገድ አንድ ካህን መጣ እንደዉ  ባዘነልኝ  ህይወቴ    እንዳላጣ ብኤ አስቤ ነበር ወደኔ በመጣ ካህኑም መጣና እንዳላየ ሆኖ እሡም አለፈና አንድ ሌዋዊ መጣ ያዉም በመንገዱ እንደዉ ቢያዝንልኝ ቢበላዉ አንጀቱ ብኤ አስቤ ነበር በመጣ ወደኔ ህይወቴ እዳላጣ ቢሆነኝ ደጀኔ                            ያዘነልኝ ማን ነዉ ? የሚገርመዉ ነገር ሌዋዊዉ መጣና እንዳላየ ሆኖ እሡም አለፈና ያዉም በመንገዱ አንድ ሣምራዊ መጣ ከገጠመኝ ሁሉ ሊያወጣኝ ከጣጣ እሡም አዘነልኝ ህይወቴ እዳላጣ                  ያዘነልኝ ማን ነዉ ?? ቀረበኝ ተጠጋኝ ቁስሌንም አከመዉ በቁስሎቼም ላይ ወይኑን አፈሠሠዉ እንደዉ ያዘነልኝ ማን ቢሆን ጥሩ ነዉ? እሡ ባይደርሥልኝ ባይመጣ ወደኔ መች ይቀጥል ነበር ህይወቴማ የኔ አዘነልኝ እንጂ እሡ በመሆኑ ሌላዉ ትቶኝ ሲሔድ እያንጎራጎሩ ባይደርስልኝ ኖሮ ባይመጣ ወደኔ መች ይቀጥል ነቀር ህይወቴማ የኔ። ዮናስ React ❤️ Subscribe Our YouTube channel https://youtu.be/Zm-qdcs5jhQ
Show all...
ገጣሚ፡-በእምነት ጥላሁን ርዕስ፡- ባልረዳው

ባልረዳው.... የአለም መድሀኒት ብርሀነ ፍጥረት፤ ሞልቶህ ክብር ተትረፍርፎህ ግብር፤ አዕላፍ መላዕክት ሲሰግዱልህ፤ ገርሟቸው ሞገስህ ማርኳቸው ውበትህ፤ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉህ በዜማቸው፤ ማምለክ ተስኗቸው በሚታይ ፊታቸው፤ ተሸፍነው በክንፋቸው፤ ባይገባኝ እንጂ ባይገባኝ እንጂ ባልረዳው፤ እንዲህ ካለ ክብር ይዤህ እንደወጣው፤ ስምህን አርክሼ ፀጋህን ሳጣጥል፤ ፍቅርህን ስገፋ፤ ሳቃልል የሰጠኸኝን ተስፋ፤ ጠፋሁ ወጣሁ ከመስመሩ፤ አጣሁት ተሰወረ በሩ፤ ልሰፍር ብፈልግ በእጄ፤ የሰራውን የቀራኒዮው ወዳጄ፤ ልለካ የኖርከውን ህይወት፤ ስናገር በረከሰ አንደበት፤ ተሸወድኩ...

በጎ የሚያደርገው በጎ የሚያደርግ ማንነት ይዤ ስለተፈጠርኩ እንጂ በጎነት መልካም ነው ተብሎ ስለተነገረኝ አይደለም ። ሰበብ ፈልጌ ከበጎነት ገሸሽ አልልም ፤ ሰበብ ፈልጌ ወደ በጎነት ፍልስ ከማለት ውጪ፤ ስለዚህ በጎ አለማድረግ አልችልም።ባገኘሁት አገጣሚ ሁሉ ቸርነት ማድረግ እንጂ በጎ ማድረግ ያለመቻል ንፉግነት እንድኖርብኝ አልፈልግም ። ያለውን ያልሰጠ እንጂ ንፉግ በሌላው እያማረረ ሲኖር እሰጣለሁ የሚል ሰው አይደለም። ስለዚህ አንድነቶች እንደዚህ ከምሉት ወገን አይደለችሁምና ኩራት ይሰማችሁ ደግሞም መፈለግንና ማድረግ በእናንተ ውስጥ ለሚሠራው አምላክ ምስጋና ስጡለት🙏👍❤ share share comment 👇👇 https://t.me/tobecharitable https://t.me/tobecharitable
Show all...
አንድነት በጎ አድ. ማኀበር ❤❤

❤አቅመ ደካሞችን መርዳት፦ ሥነ ልቦናዊ እኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ውስጥ ያሉትን ሰዎች እንደርስላቸዋለን እንረዳቸዋለን።❤ አንድነት በጎ አድራጎት ማኅበር (አበአማ)❤

Repost from N/a
Share share share join join ለጌታ ሥራ ቀኝ እጃችሁን ዘርጉ ❤❤👇❤❤👇❤❤👇❤❤ https://t.me/FishTemesgen https://t.me/FishTemesgen 🙏☝🙏☝🙏🙏☝🙏🙏☝🙏
Show all...
ዞዊ (ZOE)❤❤Eternal life

የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና። ቆላ 3:24 ማደግህ በነገር ሁሉ እንድገለጥ ይህን አስብ ፥ ይህንም አዛወትር... ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና። 1ጢሞ 4:15-16 @ዞዊ ማለት የእግዚአብሔር ሕይወት ወይም ዘላለማዊ ሕይወት ማለት ነው ። መገኛ ምንጩም የኢየሱስን ሞትና ትንሣኤውን በማመን ነው ።