cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሚራስ - ميراث - Miras

🌟 አስገራሚ ቁርአናዊ ምክሮች 🌟 ጣፋጭ የነቢዩ ﷺ ሐዲሶች 🌟 የሰለፎች ጥበባዊ ንግግሮች 🌟 ጠቃሚ ምክረ ሐሳቦች 🌟 ጥዑም ቲላዋዎች 🌟ወሳኝ ዱሩሶች : ፈታዋዎች : በሱና መሻይኾች በድመጽ: በጹሁፍ.. በሚራስ የቴሌግራም ቻናል በየእለቱ እንደ ጅረት ይፈሳሉ። ኢንሻ አላህ !! ከዚህ ማዕድ ለመቋደስ 👉 @mirasss55 ይህንን የመሰለ ቻናል ከወዳጅዎ አይሰስቱ! ሼር በማድረግ አጅሮትን ያብዙ!

Show more
Advertising posts
709
Subscribers
No data24 hours
+27 days
+230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

«አንዱ አረብ ሒሳብ አዋቂ ተጠየቀ .... . ... ስለ ሴት ምን ታስባለህ? . ፈከረ . 'ሴት' አለ ... ...   እምነት ካላት 1 ነጥብ አላት ...   ውበት ካላት  0 ከጎኑ ጨምር ...ዘሯ ካማረ ሌላ 0 አሁንም ጨምር ... ሀብትም ካላት 0 ጨምር ከኋላ . ሁሉም ካላት 1000 ነጥብ አላት ... የመጀመሪያው ከጎደለ ግን ምንም ናት! منقول
Show all...
👍 1
ቤተሰብ በእጅጉ ተጨንቀዋል #ሼር በማድረግ ተባበሩን ይህቺ ከላይ በፎቶ ያያቿት ልጅ ዛሬ ሚክሲኮ አደባባይ አከባቢ ከቀኑ 7:30 ገደማ ከእናቱዋ እያለች በእናቷ አምልጣት ጠፍታለች ስሟ ሂዳያ በድሩ ትባላለች በሰኣቱ የለበሰችው ልብስ ከስር ቀላ ያለ ከላይ ነጭ ቀሚስና ሂጃብ አድርጋለች። የሚያሳዝነው ሌላኛው ደግሞ እናቷም ከጠፋችባት ቦኃላ ደንግጣ ስልኳን ዘግታ ወደ ቤት አልተመለሰችም ቤተሰብ በጣም በጭንቀት ውስጥ ነው። #ሼር በማድረግም በመፖሰትም በዱኣም ተባበሩኝ ቤተሰብ ናት 💔 የአባቷ ስልክ በድሩ መሐመድ 0912409463 አ/ወሃብ መሐመድ 0928021661
Show all...
ፈገግ እያላችሁ ~~~ አንዱ አዛን በል ሲሉት " አግኝቼ ነው እንዴ እንኳንስ ታዝዤ ድሮም ጩህ ጩህ ይለኛል" አለ አሉ። ©
Show all...
😁 4👍 1
"እኔ" ገደል እንዳይከተን ~ "እኔ እኔ" ሲበዛ ለሰሚው ያቅለሸልሻል። ድንበርም ያስታል። ለራስ የተጋነነ ግምት ማሳደር ጎንበስ ብሎ ለመማር እንቅፋት ይሆናል። በ "እኔ" የተለከፈ ማንነት ከኢኽላስ ጋር የመጣላቱ እድል ሰፊ ነው። እዚህ ላይ አንድ የሚደንቅ የሶሐቦች ስብእና አለ። ከሚያስተላልፏቸው ገድሎች ውስጥ የራሳቸው ሲሆን ጊዜ "አንድ ሰው እንዲህ አድርጎ" በማለት እንደዋዛ የአንድ ማንነቱ የማይታወቅ ሰው ጉዳይ በሚመስል መልኩ የሚያቀርቡበት ሁኔታ አለ። ታሪኩ በሌላ አቅጣጫ ሲፈተሽ ግን የራሳቸው ገድል ሆኖ ይገኛል። ሱብሓነላህ! ኢኽላስን ለማረጋገጥ፣ ስግብግብ ነፍስያን ለማሸነፍ፣ በራስ ፍቅር ክንፍ ከማለት ለመዳን "እኔ፣ እኔ" በሚል ክፉ ስሜት ላይ ጦርነት ማወጅ ያስፈልጋል። ነፍሲያን ጉሮሮዋን አንቆ መያዝ። የኢኽላስ ነገር ለነፍሲያ ፈተና ነው። የአንድ ሸይኽ ደርስ ላይ የሚገርም ገጠመኝ ሰማሁኝ። የሆነ ሰው ሌሊት እየተነሳ ሶላት መስገዱ ማንም ዘንድ አለመታወቁ ይከነክነዋል። እና በብልሃት ሰጋጅነቱን ማሳወቅ ፈለገ። ፋርማሲ ገባና * "በሌሊት ሶላት ምክንያት ለሚሰማ ድካም የሚሆን መድሃኒት አለህ ወይ?" ብሎ ይጠይቃል። - "የለኝም" አለው። * "እሺ ሷሊሖችን ትውዳለህ'ንዴ?" ብሎ ይጠይቀዋል። - ፋርማሲስቱ ነገሩ ቢገርመው አሳለፈው። * "ለማንኛውም ሷሊሖችን ውድድ አላህ ይወድሃል" ብሎት ወጣ። ✅ "እኔ" ይሉኝታ ያሳጣል። ✅ "የኔ" ስግብግብ ያደርጋል። ✅ "እኔ ዘንድ" ትእቢት ያወርሳል። እነዚህ ስሜቶች ልባችንን እንዳይቆጣጠሩ መጠንቀቅ ይገባል። ጠቢቡ ኢብኑል ቀዪም - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦ " 'እኔ'፣ 'የኔ' እና 'እኔ ዘንድ' ማለት ድንበር እንዳያልፍብህ መጠንቀቅ ይገባል። እነኚህ ሶስት ቃላት ኢብሊስ፣ ፊርዐውን እና ቃሩን ተፈትነውባቸዋል። 👉🏾 'እኔ ከሱ በላጭ ነኝ' የሚለው የኢብሊስ ነው። 👉🏾 'የግብፅ ግዛት የኔ ነው' የሚለው የፊርዐውን ነው። 👉🏾 '(ሀብቱን) የተሰጠሁት እኔ ዘንድ ባለው እውቀት ብቻ ነው' የሚለው የቃሩን ነው። ➡️ 'እኔ' የምትለዋ ቃል ያረፈችበት ያማረ ቦታ 'እኔ ባሪያ ነኝ'፣ 'እኔ አጥፊ ነኝ'፣ 'እኔ ምህረትን ለማኝ ነኝ'፣ 'እኔ ወንጀለኛነቴን የማምን ነኝ'፣ ... በሚለው የባሪያ ንግግር ውስጥ ነው። ➡️ 'የኔ' የምትለዋ ቃል ያረፈችበት ያማረ ቦታ 'የኔ ወንጀል'፣ 'የኔ ውርደት'፣ 'የኔ ድህነት' በሚለው ውስጥ ነው። ➡️ 'እኔ ዘንድ' የምትለዋ ቃል ያረፈችበት ያማረ ቦታ ደግሞ 'ምሬንም ሆነ ቀልዴን፣ ስህተቴንም ሆነ አውቄ የፈፀምኩኑን ምህረት አድርግልኝ። ይሄ ሁሉ እኔ ዘንድ አለና' በሚለው ውስጥ ነው።" 📖 [ዛዱል መዓድ] = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
አንዱ "ለፈጅር የምትቀሰቅሰኝን ሚስት ስጠኝ" ብሎ ዱዓ አድርጎ ነበር አሉ ከዛም አሏህ አላሰፈረውም'ና ጊዜውን ጠብቃ የምትሰቅስ ሚስት ሰጠው አሉ ግን ምን ያደርጋል እሱን ቀስቅሳ ለራሷ የምትተኛ ሆነች አሉ! ዱዓ ሲደርግ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል ማለቴ ነውስ! https://t.me/mirasss55
Show all...
ይህን ሳያስፈቀድ ልብን ሰርስሮ የሚገባ ቲላዋ አዳምጡልኝማ! ጆሯችሁን ረጠብ እያረጋችሁ ያ ኪራም! 🎙ሸይኽ ሙሀመድ አዩብ -ረሂመሁሏህ-
Show all...
ያ ጀማዓ ያልጾማችሁ ወይም ጀምራችሁ ያልጨረሳችሁ ከነገ ጀምራችሁ ለመጨረስ ሞክሩ። ቀሪ 7 የሸዋል ቀናት ከፊታችን ይቀራሉ። عَنْ أَبي أَيوبِ، أَنَّ رسولَ اللَّهِ ﷺ قَالَ: " مَنْ صَامَ رَمَضانَ ثُمَّ أَتَبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ كانَ كصِيَامِ الدَّهْرِ " رواهُ مُسْلِمٌ. https://t.me/mirasss55
Show all...
👍 6
እሱ፦ «ባለቤቴ ለሱብሂ ሰላት ስቀሰቅሳት አትሰማም፤ መተኛት ሆነ ነገሯ!» እሳቸው፦ «በሌላ ሴት ስም ጠርተህ ቀስቅሳት፤ የማን ስም ነው? ብላ ብድግ ትላለች!» ©
Show all...
😁 8👌 3
"والمرأ لا ترفعه الألقاب وإنما يرفعه الملك الوهاب" "ሰውን ቅጽል ስሞች ከፍ አያደርጉትም ይልቅ ንጉሱ እና ለጋሹ አሏህ ነው ከፍ የሚያደርገው" የቅጽል ስም ጉዳይ በጣም አሳሳቢ እየሆነ ነው። https://t.me/mirasss55
Show all...
👍 1
"ጨረቃ ዳቦ ጣይልኝ፣ ኮከቢት ተቀበይልኝ" ~ የልጅ አእምሮ ነጭ ወረቀት ማለት ነው። እኛ ዋዛ የሚመስሉንን ብዙ ነገሮች እንደ ቁምነገር ይይዛል። በልጅነቱ የሰው ጅብ ወይም ጭራቅ የሚባል አለ ብለው ስለነገሩት ካደገ በኋላም እንዲህ የሚባል ነገር አለ ብሎ የሚያምን ብዙ ሰው አለ። በርግጥ ከእድገት ጋር የሚቀየሩ ነገሮች አሉ። ቢሆንም ኋላ ተቀየረም አልተቀየረም ለህፃናት ያልሆነ ነገር እየነገርን አእምሯቸው ውስጥ የተዛባ ነገር እንዳንተክል መጠንቀቅ ይገባል። ከዚህ ጋር የተያያዙ እንደየሃገሩ እንደየባህሉ ብዙ ልማዶች አሉ። ለምሳሌ፦ * ህፃናት ሲጫወቱ "ጨረቃ ዳቦ ጣይልኝ፣ ኮከቢት ተቀበይልኝ" እያሉ መዘመር። ይሄ ሺርክ ነው። * ጥርሳቸውን ሲጥቅሉ "አይጢቷ! የኔን ወስደሽ ያንቺን ስጪኝ" ብሎ ጣራ ላይ መጣል። ይህም ሺርክ ነው። * ጆሮ ደግፍ ሲያዛቸው የሰው ቤት በድንጋይ እንዲመቱ መላክ። በዚህም ውስጥ ትንሹ ሺርክ አለ። * የቀብር አፈር ቤት ላይ መበተን። ልጆች ውጭ ላይ አጥፍተው ሲመጡ ቤተሰብ እንዳይቀጣቸው ሲፈሩ የቀብር አፈር ይዘው በመምጣት ቤት ላይ ይበትናሉ። በቃ ይህን ሲያደርጉ ቤተሰብ ስለዚያ ጉዳይ አይጠይቅም ብለው ያምናሉ። በዚህም ውስጥ ሺርክ አለ። መስጠት የፈለግኩት ጥቆማ ነው። እነዚህና መሰል ባህሎች ዛሬ ከተማ ውስጥ በብዛት አይኖሩም። ግን አንዳንዴ የማንጠብቀው ነገር ይዘው እናገኛቸዋለን። ስለዚህ ልጆቻችንን በጨዋታም ይሁን በቁም ነገር፣ በእምነትም ይሁን በልማድ መልክ የተዛባ ነገር እንዳይዙ መጠንቀቅ መልካም ነው። አንዳንዱ በጨዋታ መልክ የሚቀርብ ቢሆንም በሺርክ መቀለድ በእሳት መጫወት ነው። © IbnuMunewor
Show all...
👍 1