cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)

♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ) « ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ                  ቁርኣን[ 3:104 ] መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0

Show more
Advertising posts
416
Subscribers
+124 hours
+37 days
+3830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሁሉም ስብራቶች የነገራችን መጨረሻ አይደሉም ...አንዳንድ ስብራቶች ለአድስ ሂወት ብስራቶች ናቸዉ።
Show all...
۞ إِنَّ اللَّهَ لَا يَسْتَحْيِي أَن يَضْرِبَ مَثَلًا مَّا بَعُوضَةً فَمَا فَوْقَهَا ۚ አላህ ማንኛውንም ነገር ትንኝንም ኾነ (በትንሽነት ወይም በትልቅነት) ከበላይዋ የኾነንም ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም፡፡
Show all...
ውበታቸውን በአኽላቃቸው የሚያበለሹ እና ውበታቸው አኽላቃቸው የሆኑ ሰዎች አሉ።ቆንጆ የሚያደርግህ መልክህ ወይም አለባበስህ ሳይሆን...በውስጥህ ያለው አኽላቅክ/ስብዕናህ ነው።
Show all...
አቡ ዑበይዳ (አሚር ኢብኑ አብዱላህ ኢብኑ አል-ጀራህ) በዱንያ ሳሉ በነብያችን ሰ•ዐ•ወ አማካኝነት በጀነት ከተበሸሩ ሰሃባዎች መሃከል አንዱ ነው። "በኑል ሃሪሳ" ተብሎ የሚጠራው የቁረይሽ ጎሳ አባል የሆነው የአል-ሀሪስ ኢብኑ ፊህር ጎሳ አባል ነበር።  ቤተሰቡ በሂጃዝ (በምእራብ አረቢያ) ውስጥ የቁረይሽ መገኛ በሆነችው ዝቅተኛ የመካ ስፍራ ነው። የአቡ ኡበይዳ አባት አብደላህ በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ በሃዋዚን ዘላኖች ላይ በተደረገው የፊጃር ጦርነት ከቁረይሾች አለቆች ውስጥ አንዱ ነበር። እናቱም ቁረይሻዊ ነበረች። አቡ ኡበይዳህ የተወለዱት በዚሁ ስፍራ እ.ኤ.አ በ583 ዓ.ል አካባቢ ሲሆን። እስልምናን ከመቀበላቸው በፊት ከቁረይሽ መኳንንቶች ውስጥ አንዱ እንደሆኑ ይቆጠሩ የነበሩ ሲሆን በጎሳቸዉ ሰዎች ዘንድም በጨዋነታቸው እና በጀግንነታቸው የሚታወቁ ዝነኛ ሰው ነበሩ። እ.ኤ.አ በ611 ዓ.ል ነብያችን ሙሀመድ (ሰ•ዐ•ወ) ለመካ ሰዎች፣ ለቅርብ ባልደረቦቻቸው እና ዘመዶቻቸው በግል እና በመነረገድ ላይ ዳዕዋ የአላህን አንድነት ይሰብኩ በነበረበት ጊዜ አቡበክር ረ•ዐ ከሰለሙ ከአንድ ቀን በኋላ በ28 አመታቸው ኢስላምን ተቀበሉ። አቡ ዑበይዳ ሙስሊሞች በመካ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ባሳለፉት ከባድ እንግልት እና መከራ ውስጥ ኖረዋል። በአንድ ወቅት መኳንንት የነበሩት እኒህ ሰው ለኢስላም ሲሉ ከሌሎች ቀደምት ሙስሊሞች ጋር  ሆነው የቁረይሾችን ስድብና እንግልት ተቋቁመው አልፈዋል። ነብያችን ሙሀመድ (ሰ•ዐ•ወ) ከመካ ወደ መዲና በተሰደዱ ጊዜ አቡ ኡበይዳም እንዲሁ ወደ መዲና ተሰደዱ። ነብያችን ሙሀመድ (ሰ•ዐ•ወ) መዲና በደረሱ ጊዜ ሙሃጅሩን ከአንሷሪዩ ጋር በወንድማማችነት ሲያጣምሩ ከሙሀመድ ኢብኑ መስለማህ ጋር በወንድማማችነት ተጣመሩ። አቡ ዑበይዳህ የሙስሊሞች ጀግና የጦር አዛዥ ሆነው ካለፉ የነብያችን (ሰ•ዐ•ወ) ድንቅ ባልደረባዎች መሃል አንዱ ነበሩ። ከቁረይሽ ሙሽሪኮች ጋር በተደረገው የበድር ዘመቻ ወላጅ አባታቸውን ለኢስላም ሲሉ በሰይፋቸው መቅላታቸው የሚታወስ ነው። በዚህ ቆራጥ ተግባራቸው ሰበብ አላህ ሱ.ወ የቁርአን አንቀፅ ሊያወርድላቸው ችሏል። በሁለተኛው ኸሊፋ በኡመር ረ.ዐ ዘመን የጦር ሰራዊት አዛዥ ሆነው ኢስላምን አገልግለዋል። ኡመር ረ.ዐ እኔን ይተኩኛል ብለው በዝርዝር ከያዟቸው ሹማምንቶች ውስጥ አንዱ የነበሩት አቡ ዑበይዳህ ኢብኑ ጀራህ ረ•ዐ እ.ኤ.አ በ639 ዓ.ል በዑመር የአገዛዝ ዘመን ከነብያችን (ሰ•ዐ•ወ) ዘንድ ቃል ወደ ተገባላቸው አኼራ አለፉ። የAthamina, Khalil, "አቡ ኡበይዳ ኢብን አል-ጀራህ" ከሚለው መፅሀፍ የተወሰደ ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
Show all...
ፍቅር ጥግ …… ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ " ረሱለሏህ !
Show all...
የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያውያን ሑጃጆች ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ በረራ የሚያደርጉበት ቀን ታወቀ #Ethiopia |~ መጅሊስ ለተጓዦች ስለ ሐጅ አፈፃፀም የሚሰጠው ሥልጠና በዛሬው እለት ይጀምራል ። ለ1445 ዓ.ሂ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ከተመዘገቡ ኢትዮጵያውያን ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ተጓዦች በረራ የሚያደርጉበት ቀን ታወቀ። “ሚንበር ቲቪ” ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) የሐጅ እና ዑምራ ዘርፍ እንደሰማው የመጀመሪዎቹ ተጓዦች በረራ የሚከናወነው ግንቦት 13፣ 2016 ነው። ምክር ቤቱ ለዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት ለመላክ በእቅድ የያዘው የምዕመናን ቁጥር መጠን 12 ሺሕ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል። “ሚንበር ቲቪ” ከመጅሊስ ኃላፊዎች ማረጋገጥ እንደቻለው በተያዘው ዓመት ለሐጅ ክንውን ወደ ሳዑዲ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ምዕመናን ቁጥር ከአምናው በ1 ሺሕ 62 ብልጫ ያለው ነው። መጅሊስ ለጉዞው የመዘገባቸውን ምዕመናን ከዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 22/2016 አንስቶ ሥልጠና መስጠት እንደሚጀምር ታውቋል። ይህ ሥልጠና ለስድስት ቀናት የሚቆይ ነው። የዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት ሰኔ 7/2016 ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። በመላው ዓለም የሚገኙ ወደ 2 ሚሊዮን ገደማ የሚቆጠሩ ምዕመናን ሥነ ሥርዐቱን ለመፈፀም ከግንቦት 1/2016 ጀምሮ ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ መግባት እንደሚጀምሩ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ያመለክታል። ምንጭ  = ሚንበር ቲቪን የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ @ https://t.me/Xuqal
Show all...
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)

♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ) « ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ                  ቁርኣን[ 3:104 ] መወያያ ግሩፓችን ☞

https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0

"የነቢዩ (ﷺ) ሰሃባዎች (ስራቸውን አላህ ይውደድላቸው) ገንዘባቸውንና ቤታቸውን ለአላህ ሲሉ በመተዋቸው…አላህ ዱንያን ሙሉ በሙሉ በእጃቸው አደረገላቸው፡፡" #ኡስታዝ_በድሩ_ሁሴን
Show all...
#አላሙዲን_በገባው_ቃል_መሠረት_ስራውን_ጀምረዋል ለ27 አመታት ግንባታው ተቋርጦ የነበረው የሱልጣን አሊሚራህ ኢስላማዊ ኮለጅ ግንባታ ሸህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲን በሰኔ 06/2013 ቃል በገቡት መሠረት የፕሮጀክቱን ግንባታ በይፋ ጀምረዋል። ከወራት በፊት ግንባታ የተፈቀደው ለመስጅድ ብቻ ነው የሚለው ሀሳብ ደስታች ጎዶሎ አድርጎት ነበር። ዛሬ ደግሞ  የመድረሳው ግንባታ አብሮ እንዲቀጥል አላሙዲን መፍቀዳቸውና በቀጣይ ሳምንት ስራ እንደሚጀመር  ስንሰማ ተደስተናል። አላሙዲን በገቡት ቃል መሠረት በቃላቸው በማገኘት ግንባታው ተጀምረዋል ከወራት ቡሗላ ይጠንቀቅ ተብሎ ይጠበቃል።   አሁን የቀረው የክልሉ መንግስታችን የገባልን ቃል ብቻ ነው። እሱም በፕሮጀክቱ ላይ የሚገኘው 25 ሚሊዮን ብር እዳ ጉዳይ ነው። የክልሉ መንግሥት የኮንትራክተሩን ክፍያ በሰኔ 06/2013 ልክ እንደአላሙዲን ለአሳይታ ህዝብ እዳውን እንደሚከፍል በመድረኩ ቃል ገብተዋል። እዳውን ለማክፈል ድርሻውን ወስደዋል። እስካሁን የክልሉ መንግስት በገባው ቃል መሠረት የኮንትራክተሩን ክፊያ አልከፈለም። መንግሥታችን በመስጅዱ ላይ ያለው እዳ በገባው ቃል መሠረት እንደሚከፍል ተስፋ አለን። እዳው ተከፍሎ ከእዳ ነፃ ስንሆን እና  የፕሮጀክቱ ግንባታ ስጠናቀቅ ያኔ ደስታችን ሙሉ ይሆናል። አላህ የዛ ሠው ይበለን! Via @Aloyayyo @ https://t.me/Xuqal
Show all...