Ethio Space (ኢትዮ ጠፈር)
Closed channel
ሰለ ሌሎች ዓለማላቶች እና አስትሮኖሚ ሳይንስ ስታስብ በሰዎች መካከል ያሉት የጎሳ ,የብሔር ,የሐይማኖት ልዩነቶች እንዲውም የአገር ልዩነቶች ለአንት ተራ ነገሮች ይሆናሉ ምክንያቱም እራስክን የምታነፃፅረው በሌሎች አለማት ላይ ይኖራሉ ተብለው ከሚታሰቡ ልዩ ፍጥሮች ጋር ይሆናል ሰለዚህ አንት ሰው ከሆነክ በቂ ነው ምክንያቱም ሰው መሆንክ በራሱ በቂ ማንነት.. @unverseand 👈ለcross
Show more1 981
Subscribers
No data24 hours
-127 days
-4330 days
Posts Archive
ይህ የምታዩት ቅዠት የሚመስል ነገር ቻይና እና የአለም መንግስታት ተባብረው ሊሰሩት ያሰቡት በUniverse ውስጥ ከአንዱ ፕላኔት ወደ አንዱ ለመሄድ የሚያስችል ከአማችን ወደ ማርስ በረቀቀ ባቡር ለመሄድ የሚያስችል ነው ! ስራውም በቅርቡ ይጀመራል !
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ታይተዋል ስለተባሉ ዩፎዎች ምንነት ሪፖርት አቀረበ
******
የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር ፔንታገን ለበርካታ ዓመታት በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ውስጥ ምንነታቸው ያልታወቁ በራሪ አካላትን (ዩፎ) መታየታቸውን በተመለከተ የማጠቃለያ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።
በተለይ በአውሮፓውያኑ 1950ዎቹ እና 60ዎቹ በከፍተኛ ቁጥር የታዩት እና ዩፎዎች ናቸው ተብለው የተደመደሙት በራሪ ነገሮች የአሜሪካ መንግሥት የሠራቸው የተራቀቁ የስለላ አውሮፕላኖች እና የህዋ ቴክኖሎጂ ሙከራ ውጤቶች ናቸው ብሏል።
የመከላከያ ባለሥልጣናት አክለውም ከሌላ ዓለም የመጡ እንግዳ ፍጡራን ማጋጠማቸውን በሚመለከት “ምንም ዓይነት” ማስረጃ የለም ብለዋል።
አርብ ዕለት ለአሜሪካ ምክር ቤት የቀረበው ሪፖርት እንዳመለከተው፥ ዩፎ ተብለው መታየታቸው ከተገለጹት መካከል አብዛኞቹ ክስተቶች ከምድር ላይ የተነሱ የተለመዱ ነገሮች ናቸው ብሏል።
ነገር ግን የተደረገው ምርመራ ውጤት በሕዝቡ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ዩፎዎችን በተመለከተ ያለውን እምነት በቀላሉ የሚለውጠው እንዳልሆነ የፔንታገን ባለሥልጣናት መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ሪፖርቱ ባለሥልጣናት “ምንነታቸው ያልታወቁ ያልተለመዱ ክስተቶች” የሚሏቸውን በራሪ አካላትን በተመለከተ ምርመራ በማድረግ ለመገንዘብ በአሜሪካ መንግሥት የተደረገ ሙከራ ነው።
በስዊድን የታየው የሰማይ ላይ ትንግርት
****
በሰሜናዊው የስዊድን ክፍለ ግዛት ውስጥ በምትገኘው የኪሩና ከተማ ሰማይ ላይ ከሰሞኑ የታየው የብርሃን ህብረ ቀለማት የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ነው፡፡
ክስተቱ በጠፈር ተመራማሪዎች አገላለፅ "አውሮራ" እየተባለ የሚጠራ ሲሆን፤ ከፀሀይ ወለል ላይ የሚነሱ በአይን የማይታዩ ቅንጣቶች ከምድር የመግነጢሳዊ መስክ ጋር በሚፈጥሩበት ሰበቃ ወይም ፍሪክሽን የሚፈጠር ክስተት ነው፡፡
ተመራማሪዎች እንደሚገልፁት በተለያዩ ግዜያት ከፀሀይ ወለል ላይ የሚነሱ በአይን የማይታዩ "ፕላስማ" የተባሉ ቅንጣቶች ያሉ ሲሆን፤ እነዚህ ቅንጣቶች በሰአት 1,609,344 ኪ.ሜ የመጓዝ ፍጥነት አላቸው።
ቅንጣቶቹ ወደ ምድራችን የሚመጡት በነፋስ መልክ ሲሆን ይህ ነፋስ (Solar wind) ወይንም ሞቃት የፀሀይ ነፋስ ተብሎ ይጠራል።
እነዚህ ነፋሳት ከምድራችን ውጫዊ ከባቢ አየር እና የመግነጢሳዊ መስክ (Magnetic field) ጋር ሰበቃ (friction) በሚፈጥሩበት ጊዜ ሰማዩ ላይ የተለያየ ህብረቀለማት ያላቸው ነፋሳት ሲነፍሱ ሰማዩ ላይ አውሮራ (Aurora) ተከሰተ ይባላል።
አውሮራ በሰሜናዊው እና ደቡባዊው ዋልታ ላይ ብቻ አልፎ አልፎ የሚከሰት የሰማይ ላይ ትንግርት ሲሆን ከምድር የከባቢ አየር ጋዞችም ጋር ጥብቅ ቁርኝት አለው።
እነዚህ ጋዞች በዋነኝነት ናይትሮጅን እና ኦክስጅን ሲሆኑ አንዳንድ ጊዜ ሌሎች የጋዝ አይነቶችም ይካተታሉ።
የአውሮራን ቀለም የሚወስነው ፕላስማ ሰበቃ የፈጠረበት የከባቢ አየር ጋዝ እና ሰበቃው የተፈጠረበት ቦታ ከምድር ወለል ያለው ከፍታ ትልቅ ነው።
ፕላስማው ሰበቃ የፈጠረው ከምድር ወለል እስከ 96 ኪ.ሜ ርቆ ከሚገኝ የናይትሮጅን ጋዝ ጋር ከሆነ አውሮራው ሰማያዊ ቀለም ይኖረዋል።
ፕላስማው ከ96ኪ.ሜ በላይ ርቆ ከሚገኝ የናይትሮጅን ጋዝ ጋር ሰበቃ ከፈጠረ አውሮራው ወይነጠጅ ቀለም በውስጡ ይይዛል።
ፕላስማው ከምድራችን ወለል ከ 96ኪ.ሜ እስከ 241ኪ.ሜ ርቆ ከሚገኝ የኦክስጅን ጋዝ ጋር መስተጋብር ከፈጠረ አውሮራው አረንጓዴ ቀለም ይይዛል።
ፕላስማው መስተጋብር የፈጠረው ከምድር ወለል ከ241ኪ.ሜ በላይ ከሚገኝ የኦክስጅን ጋዝ ጋር ከሆነ አውሮራው ቀይ ቀለም በውስጡ ይይዛል።
ከላይ እንደተጠቀሰው አውሮራዎች በሁለት አይነት መልኩ ሊከሰቱ ይችላሉ። አንደኛው በሰሜናዊው ዋልታ ብቻ የሚታየው አውሮራ ቦሪያሊስ (Aurora Borealis) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በደቡባዊው ዋልታ ላይ ብቻ የሚታየው አውሮራ አውስትራሊስ (Aurora Australis) የሚባለው ነው።
አውሮራዎች ጠንካራ በሚሆኑበት ጊዜ የራዲዮ፣ ቴሌቪዥን እና የስልክ ሞገዶችን በማወክ ሊያስተጓጉሉ እንደሚችሉ የዋይልስዊድን ዘገባ ያመለክታል።
ልቷዮቸው የሚገቡ የዩቱውብ ቪድዮዎች👇
1. ለኤልያኖች የተላከው መልክት እና የሳይንቲስቱ ማስጠንቂያ👇👇
https://www.youtube.com/playlist?list=PLL84IYkPmzk1ZA0sySTE6_bK_JnQau5WJ
2. በጊዜ መጓዝ እና ጊዜ👇👇
https://www.youtube.com/playlist?list=PLL84IYkPmzk0kcS_JlWRVD9i9H2xeNTh4
3. ከመሬት እስከ ጨረቃ እና ከመሬት እስከ ፀሐይ ያለው እርቀት እንዴት ተለካ: 👇👇👇
https://www.youtube.com/playlist?list=PLL84IYkPmzk0cDMejIwjk-nwdue2UxEi1
4. ቶፕ 10 አስገራሚ እና አስፈሪ ፕላኔቶች ,የውሃው ዓለም👇👇
https://www.youtube.com/playlist?list=PLL84IYkPmzk3IbHh009W2c6BJIuVT9y8m
5. ቤርሙዳ ትሪያንግል እና ዳይኖሶሮች የጠፉበት አሳዛኙ ክስተት:👇👇👇
https://www.youtube.com/playlist?list=PLL84IYkPmzk0BPwYX_RNAfmsqdgCUQTcA
6. ግርዶሽ:👇👇👇
https://www.youtube.com/playlist?list=PLL84IYkPmzk0OttyKrfTPcRw9BD8LCuPS
7. የ ሳይንቲስቶች ታሪክ:👇👇
https://www.youtube.com/playlist?list=PLL84IYkPmzk2cm1JUfTCR9mleOEuav-_v
የገሀነብዋ 🔥 #planet
ከናሳ በ 2009 የወጣው አስደንጋጭ እና ለማመን የሚከብደው ዜና እንዲህ ይል ነበር
"ሙሉ በሙሉ #በእሳት የተሞላች #እሳት የሚፈላባት ,#የእሳት ባህር እና ውቅያኖሶች የሞሉባት,#እሳት እየተነነ #ድንጋይ የሚዘንብባት ,እንኩዋን ለመኖርያ ለማሰብ እንኩዋ በእጅጉ #ምታስፈራ ,#ገሀነብን በእጅጉን የምታመለክት ምናልባትም #የገሀነብ አንዱ አካል የሆነችውን አለም(planet ) አግኝተናል "
ይህች planet #COROT 7B በመባል ትጠራለች
ሁለት #ገሀነብ በ አንድ ላይ የሚገኙባት ይህች planet ግማሹ አካልዋ በ ሚፍለቀለቅ የ #እሳት ባህር እና ውቅያኖስ ሲሆን የቀረው ግማሽ አካልዋ ደሞ ከ እሳቱ የሚተነው የ #እሳት ትነት በ አየር ላይ ከቆየ በሁዋላ ወደ ትንንሽ ድንጋይነት በመቀየር #ድንጋይ የሚዘንብበት የ (lava) ምድር ነው፡፡
ከሚገርማቹ ነገር የዚች planet የ #ሙቀት መጠን 2500 c° ወይም 4500f° ነው፡፡ ይህ ሙቀት ምድር ላይ ቢሆን ኖሮ ምድር ላይ ውሀ የተባለ ነገር አይታሰብም ነበር ፣ ድንጋዮችም ሙሉ በሙሉ ቀልጠው ምድራችን ሙሉ በሙሉ ወደ ኤርታሌ እሳተ ጎመራነት በተቀየረ ነበር፡፡
ምድር ላይ የምናውቀው ዝናብ የ ውሀ ጠብታ ግፋ ካለ በረዶ ነው በ #corot 7b ግን የሚዘንበው የ ድንጋይ ዝናብ ነው።
• UFO👽 || Part - 4
የዚህ መላ ምት ዋነኛ ደጋፊዎች ከሆኑት አንዱ " ሊምቦ ኦፍ ዘ ሎስት " የተባለው መጽሐፍ ደራሲ ጆን ስፔንሰር ነው ! ስፔንሰር በአየር ሃይል ውስጥ ለአስር አመታት ያህል ያገለገለ በመሆኑ ስለአውሮፕላኖች በሚገባ ያውቅ ነበር በተጨማሪም ስለ UFO ክስተቶች የቅርብ ተከታታይ ነበር ! ስፔንሰር ባሁን ዘመንም ሆነ ታሪክ በጽሁፍ መስፈር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ስለ UFO የቀረቡትን መረጃዎች ከመረመረ በኋላ እነኚህ ያልታውቁ በራሪ አካላት 2 አይነት ናቸው ይላል ! አንደኛው ዓይነት " በራሪ ሳህን " ሲሆን የስፋቱ 80 ጫማ ይሆናል ! ሌላው ደግሞ በውስጡ በርካታ 'በራሪ ሳህኖችን' ወይም ምድራችን ላይ ያሉ ትላልቅ መርከቦችን የሚይዝና ግዙፍ የሆነ " እናት መርከብ(mother ship) " አይነት ነው ! ይህ ትልቅ በራሪ አካል አልፎ አልፎ ታየ ከሚባለው ክብ ግዙፍ ሳህን መሳይ ቅርጽ ካለው አካል ጋር ይመሳሰላል ! ሆኖም እንደ ትናንሾቹ በራሪ ሳህኖቹ ብዙ ጊዜ አይታይም ! ከኛ አለም ውጪ በሌላ አለማት ሌሎች በጣም የተራቀቁ ስልጣኔዎች ሊኖሩ ይችላሉ ይላል ስፔንሰር
ክፍል 5 ይቀጥላል ........
ከተመቻችሁ ሼር በማረግ በተጨማሪም ለሌሎችም ትምህርት እንደሆን ቤተሰቦቼ ! ❤️
@Yihen_Yawkalu 📲
Repost from የአለም ጋለሪ
መሬት ጠፍጣፍ ሳትሆን ክብ ናት በሚታይ ማስረጃ
ሰለ አስትሮኖሚ ብቻ የሚወራበተን ቻናል ለመቀላቀል👇👇👇👇
@ethio_tefer0 @ethio_tefer0
🚀Join us share🙏🙏🙏🙏🙏🙏🗽
https://t.me/ethio_tefer
• 𝙪𝙛𝙤 👽 || Part - 3
በ1968 በዩንቨርስቲ ኦፍ ኮሎራዶ የተቋቋመ የጥናት ቡድን ስለ UFO በቀረቡ ሁኔታዎች ላይ ጥናት አካሂዶ ነበር ። ከፊሉ ዘገባዎች ማስረጃ ሊቀርብላቸው ቢችልም ጥቂቶቹ ደግሞ ምንም አይነት ማብራሪያ ሊቀርብላቸው አልቻለም ! የ UFO ጥናትና ምርምር ብዙ አወዛጋቢ ሁኔታዎች እየገጠሙት ቢሄድም UFO ግን መታየትቸውን ቀጠሉ !
በተለይ በፍሎሪዳና በባሃማስ መካከል ባለው ክልል የሚታዩት UFO ቁጥር ከሌሎች አካባቢዎች ሁሉ የበዛ ነው ! በውሀ ውስጥና በ አየር ላይ ከመታየታቸውም በላይ ከአየር ወደ ባህር ከባህር ወደ አየር ሲመላለሱ ብዙ ጊዜ ተስተውለዋል ! አየን ካሉት ሰዎች አብዛኞቹ እምነት የሚጣልባቸው ነበሩ ! በእነኚሁ አካባቢ የUFO በብዛት መታየት ቤርሙዳ ትራያንግል ክልል ውስጥ ከሚከሰቱ የመሰወር ሁኔታዎች ጋር የተያያዙ ናቸው የሚል አስተሳሰብ አሳድሯል ! እንዲያውም UFO ለዘመናት አውሮፕላኖችንና መርከቦችን ሲጠልፉ ኖረዋል የሚል አስተሳሰብም በብዙዎች ዘንድ አለ ......
ክፍል 4 ይቀጥላል ......
UFO part 2
ዶክተር ጄ አለን ሀይኒክ የተባሉ የ UFO ተመራማሪ እንደሚሉት " UFO አየን የሚሉ የብዙ ሰዎች የአእምሮ ብስለት መሃከለኛ የጥቂቶች ደግሞ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው ! እነዚህ አካላት በተለያየ የጥራት መጠን ፈቶ ተነስተዋል ! ከአውሮፕላኖች ጎን ሲበሩ መታየታቸውም ተወስቷል ! በርካታ የምርምር ዘገባዎች እነዚህን ነገሮች ከብዙ ሁነታዎች ጋር አያይዘዋቸዋል ! ለምሳሌ ከጨረቃ ፣ ተወርዋሪ ኮከብ ፣ ፊኛዎች ፣ ብሩህ መብራቶች ፣ የሰሜን ብርሃኖች ፣ የእሳት ኳሶችና የመሳሰሉት ሊሆኑ ይችላሉ እሚል ግምት አለ ! ሌሎች በርካታ መላምቶች ቢኖሩም ሁሉንም የሚያስማማ መላ ምት አለ ማለት ግን አዳጋች ነው ! በምድር ላይ ያሉ ሃያላን መንግስታት የሰሯቸው የሚስጥር መሳሪያዎች ሊሆኑ ይችላሉ የሚለው መላ ምት ግን በሁሉም ዘንድ ተቀባይነትን አጥቷል
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት እነዚህ ከተዋጊ አውሮፕላኖች አካባቢ ያንዣብቡ የነበሩ ብርሃናማ አካላት ተፋላሚ ወገኖች አንዱ የሌላውን ሚስጥር መሳሪያዎች ናቸው የሚል ጥርጣሬ ነበራቸው ! ግን እነኚህ UFO የሚስጥር መሳሪያዎች ቢሆኑ ኖሮ ሁኔታው በመገናኛ መሳሪያዎችና በመሳሰሉት መጋለጡ አይቀርም ነበር ! የአሜሪካ አየር ሃይል "UFO ማብራሪያ ሊገኝላቸው አይችልም ! ስለዚህም የሉም" እሚል አቋም አለው ! የሚገርመው ግን የአየር ሀይሉ የውስጥ ህግ አንዱ ክፍል አውሮፕላን አብራሪዎች UFO ቢገጥማቸው መውሰድ የሚገባቸውን እርምጃዎች ይጠቅሳል !
መሬት ጠፍጣፋ ናት❓🤔
መሬት ጠፍጣፋ ናት የሚደንቅ ተፈጥሮ መሬት ገና ከለጋ እድሜያችን ክብ ናት ተብለን ተምረን አድገናል ነገር ግን ይህን እሳቤ በመቃወም በተለያዩ ዘመናት የተነሱ ፈላስፎች ቀልዳቸውን ነው በማይባል ደረጃ ምድር ክብ ሳትሆን ጠፍጣፋ ነት የሚለውን አስተሳሰባቸውን የተለያየ እሳቤን ያንፀባርቅልኛል ያሉትን ነገር በመጠቀም ሲሞግቱ ታይተዋል በዚህም 19ሰባቶዎቹ ውስጥ ቀላል የማይባሉ ሰዎች መፀሀፍ እስከ መፃፍ ደርሰዋል አሁን ባለንበት በ21ኛው ክፍለ ዘመንም ፍላት ኧርዝ ቲዎሪ የሚል ካንፓኒ እስከ መክፈት ደርሰዋል፡ መሬት ጠፍጣፋ ናት የሚሉ ሰዎች የመሬትን ቅርፅ ሲያስረዱ መሬት ጠፍጣፋ ሆና የአንታርቲካ የበረዶ ግግር ዙሪያዋን ከቧታል ይላሉ የሚገርመው ነገር መሬት ጠፍጣፋ ከሆነች እንዴት ወቅቶች ይፈራረቃሉ ሲባሉም መሬት ጠፍጣፋ ሆና ፀሀይ እንደ እስፖት ላይት ጋደድ ብላ ዙሪያዋን ታበራለች ይላሉ ነገርግን እንደዛ ቢሆን ኖሮ ቢያንስ ትንሽ ጨረፍታ ብርሀን ማየት ነበረብን በማለት ይህንን ሀሳባቸውን መልሰው ውድቅ ያደርጉባቸዋል፡፡የሚገርመው ነገር እነዚህ ሰዎች ጭራሽ የመሬት ስበት አለ ብለው እንኩዋን አያምኑም ታዲያ ለምን ምድር ላይ ተጣብቀን ቀረን ለምን አንሳፈፍም ተብለው ሲጠየቁም መሬት ወደ ላይ በ9.8ሜ ፐር ሰከንድ ስኩዌር ወደ ላይ ስለምቴድ ነው ይላሉ፡፡
•|| UFO Part - 1
- ከስሙ እንደምንመለከተው UFO (Unidentified flying object) በሰማይ ላይ ከተለምዶ የበረራ ህግ ውጪ ወይንም ከaerodynamic ህግ ውጪ የሚንቀሳቀሱ በራሪ አካላት ማለት ነው።
~ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰላም በሰፈነበት ወቅት እ.ኤ.አ በ1947 ዓ.ም ታዩ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ UFO በ አሜሪካ ውስጥ ለብዙ ሺህ ዘገባዎችና ምርምሮች ምክንያት ሆነዋል።
* በተቀረው ዓለምም ስለ UFO መታየት ብዙ ሺህ ዘገባዎች ከርበዋል። በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በ አሜሪካና በሌሎች አገሮች UFO ማየታቸውን ተናግረዋል እነዚህ በራሪ አካላት የጠለቀ የሳይንስ እውቀት ባላቸው ሰዎችም በስዕላዊ መግለጫ መልክ ቀርበዋል።
ዶክተር ጄ አለን ሀይኒክ የተባሉ የUFO ተመራማሪ እንደሚሉት "
Part - 2 ይቀጥላል
🥓🛰 የሆነ ጊዜ ''NASA'' ጠፈርተኞችን ባቄላ እንዳይበሉ ከልክሏቸዉ ነበር ፣ ምክንያቱም የጠፈርተኞቹ ፈስ መንኩራኩሩ ላይ ቅፅበታዊ ቃጠሎ ሊያስከትል ስለሚችል ነዉ።
በአለማችን በከፍተኛ ሁኔታ የዝናብ እጥረት ያለበት ቦታ አንታርቲካ ሲሆን ለ2 ሚልዮን አመታት ዝናብ አግኝቶ አያቅም !
መሬት ጠፍጣፍ ናት ብለው የሚያምኑ አካላቶች ማስረጃቸው ይሄንን ይመስላል
ከንግግሮቹ መካከል ፀሐይ በቀን ጨረቃ በማታ ብቻ እንደሚበሩ ያነሳል ይሁን እንጂ ጨረቃ በቀን የምትታይበት ሁኔታ አለ ለዚስ መን መልስ አላቸው ?
ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13
ሳይንስን አምነክ በፕሌን ትሄዳለክ ሳይንስ የሰራውን ስልክ ተጠቅመክ ስልክ መደዋወል እንደምትችል ታምናለክ በቲቪ ኳስ ማየት እንደምትችል ታምናለክ በካሜራ የራስክን ምስል ማንሳት እንደምትችል ታምናለክ ወይም እርግጠኛ ነክ ሰለዚህ እኔ በሳይንስ አላምንም እንዴት ልትችል ትችላለክ ምክንያቱም ከላይ የተጠቀሱት ቴክኖሎጂዎችን የፈጠረው ሳይንስ ነው✍
Repost from የአለም ጋለሪ
ልቷዮቸው የሚገቡ የዩቱውብ ቪድዮዎች👇
1. ለኤልያኖች የተላከው መልክት እና የሳይንቲስቱ ማስጠንቂያ👇👇
https://www.youtube.com/playlist?list=PLL84IYkPmzk1ZA0sySTE6_bK_JnQau5WJ
2. በጊዜ መጓዝ እና ጊዜ👇👇
https://www.youtube.com/playlist?list=PLL84IYkPmzk0kcS_JlWRVD9i9H2xeNTh4
3. ከመሬት እስከ ጨረቃ እና ከመሬት እስከ ፀሐይ ያለው እርቀት እንዴት ተለካ: 👇👇👇
https://www.youtube.com/playlist?list=PLL84IYkPmzk0cDMejIwjk-nwdue2UxEi1
4. ቶፕ 10 አስገራሚ እና አስፈሪ ፕላኔቶች ,የውሃው ዓለም👇👇
https://www.youtube.com/playlist?list=PLL84IYkPmzk3IbHh009W2c6BJIuVT9y8m
5. ቤርሙዳ ትሪያንግል እና ዳይኖሶሮች የጠፉበት አሳዛኙ ክስተት:👇👇👇
https://www.youtube.com/playlist?list=PLL84IYkPmzk0BPwYX_RNAfmsqdgCUQTcA
6. ግርዶሽ:👇👇👇
https://www.youtube.com/playlist?list=PLL84IYkPmzk0OttyKrfTPcRw9BD8LCuPS
7. የ ሳይንቲስቶች ታሪክ:👇👇
https://www.youtube.com/playlist?list=PLL84IYkPmzk2cm1JUfTCR9mleOEuav-_v
አለም ክብ ናት ከተባለ አሁን ካላቹበት ቦታ ላይ ሁናቹ ዝንብላቹ በስተምስራቅ አቅጣጫ ብቻ ቀጥ ብላቹ ብትሄዱ የት ልትደርሱ ትችላላቹ ?
በምዕራብ አቅጣጫ መታቹ የመጀመሪያ ቦታቹ ላይ ትድርሳላቹ ምክንያቱም መሬት ክብ ናት መሬት ጠፍጣፍ ብትሆን ደግሞ የመሬት ጫፍ ላይ ደርሳቹ ቁልቁል ትወድቃላቹ ።
የቱ ነው ትክክለኛ የሚመስላቹ
