✍ዮ_ሚን
Open in Telegram
በሰው የተነበቡ ግጥሞች የአሪፍ መጽሐፍ ጥቁምታ አጫጭር ታሪኮች ፈጠራዎችን እንደመምባቸዋለን ስለሀሳብ እንሰማለን፡፡ እናሰላስላለን፡፡ ሰክረን ሳይሆን ሰክነን፡፡ሀሳብን እናስበዋለን፡፡ ዘላለም የሚቆየው ሀሳብ ነው፡፡ ለማንኛውም አስተያየት 👉 @Ebn_yob
Show more270
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
270
ተረጋጊ ተንፈስ በይ
ሀይል ጩኸት አታውጂ
የቱም ጉልበት አይገዛውም
ወንድ ልጅን ፍቅር እንጂ
የሴትነት ፍቅር ወጉ
ስውር ጥበብ ቢበዛውም
ልማልልሽ ወንድነቴን
ወንድነትሽ አይገዛውም
ከጠላቴ ክንድ ብርታት
እንደ አገዳ ከሚመጠኝ
ሳቅሽ እንጂ ለጉልበቴ
ድብቅ ሀይል የሚሰጠኝ
አልናፍቅም ንትርክን
ጭቅጨቃሽን እጠላለው
በፍቅር ቃል ከሆነ ግን
ባሪያ መሆን እችላለው
ዘውዴ👑 ነሽ
የኔ እመቤት
ካንቺ ውጪ አላጌጥም
አውቃለሁኝ ጨው ከሌለው
አሊጫ ወጥ አይጣፍጥም
ስልጣን አለሽ በራሴ ላይ
ልምራ ስልሽ አትገላምጪኝ
ወንድነትን ለኔ ተዪው
ሴትነትን ብቻ ስጪኝ!
@yomin1_2
