994
Subscribers
No data24 hours
+17 days
+1630 days
Posts Archive
994
Repost from Chercher
Barattoonnii Maqaan keessan armaan gaditti baraa'ee Sa'aa 3:30 irratti koreen BBLG isin barbaada waan ta'eef oraafanaa tokkoo malee bilbila keessan qabachuun akka biiroo Lakk. 1 akka argamtan Cimsinee isin hubachifna
1. Arsemaa Demis
2. Semehal Habtom
3. Idlawit Nesibu
4. Haset Abebe
5. Yostina Belete
6. Meyren Muhammed
7 Kumaa Abbdellaa Kutaa 11ffaa
994
Repost from (E-Library ) St.Raguel General Scondary School
g12 history unit 1 questions.pdf3.64 KB
994
Repost from Chercher
✍✍️ይነበብ✍️✍️
በፈተና ጊዜ ከተማሪዎች የሚጠበቁ ተግባራት
✍️በሰዓቱ መገኘት(አለማርፈድ)፣
✍️መታወቂያና እርሳስ መያዝ፣
✍የደንብ ልብስ አሟልቶ መልበስ
✍ለፈተና የተሰጠውን። ሰዓት በአግባቡ መጠቀም
✍ሞባይል/ስማርት ሰዓትና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን አለመያዝ
✍መጻፍ፣ደብተርና አጤራራዎችን ወደ ፈተና ክፍል ይዞ አለመግባት
✍የፈተና ወረቀቶችን አለመቅደድ
✍የመልስ መስጫ/ማጥቆራያ ወረቀት ላይ ስም፣ክፍልና ሴክሽን መጻፍ
✍አቴንዳንስ መፈረም
✍ፈተናን በራስ አቅም ብቻ ተረጋግቶ መስራት/አለመኮረጅና
✍ለፈታኝ መምህራንና ለት/ቤቱ ሰራተኞች መታዘዝ!!!
🙏መልካም ፈተና🙏
994
Repost from ET QuickBooks
በጣም ወሳኝ ባዮሎጂ የምስል ጥያቄ በኢንትራንስ ፈተና ሊመጣ የሚችል parts of Human eye
1. Cornea: The transparent outermost layer that helps to focus light onto the retina.
2. Iris: The colored part of the eye that controls the amount of light entering the eye.
3. Pupil: The black hole in the center of the iris through which light enters the eye.
4.Lens: A transparent structure behind the iris that helps to further focus.
5. Retina: The innermost layer of the eye that contains photoreceptor cells (rods and cones) w/h detect light.
6. Optic nerve: Transmits the electrical signals from the retina to the brain for visual processing.
7. Sclera: The outer layer and the white part of the eye, helps to maintain the shape of the eyeball.
8. Aqueous humor: A clear fluid that fills the space b/n the cornea and the lens.
9. Vitreous humor: A gel-like substance between the lens and the retina, helping to maintain the shape of the eye.
994
Repost from Chercher
ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናዎች የምትዘጋጁ ውድ ተማሪዎች፤ እንኳን ለዚህ ወሳኝ ምዕራፍ አደረሳችሁ። ይህ ወቅት እስካሁን በትምህርት ገበታችሁ ያሳለፋችሁትን የልፋት፣ የጥረት እና የዕቅድ ውጤት የምታሳዩበት ታላቅ አጋጣሚ ነው።
የፈተና ወቅት የውጤታማነታችሁ ማረጋገጫ እንጂ የጭንቀት ምንጭ አይደለም!
ፈተና መድረሱ መረበሽንና ፍርሃትን ሊፈጥር ይችላል፤ ነገር ግን እውነተኛው ስኬት የሚመጣው ፈተናን ከመፍራት ሳይሆን በራስ መተማመንና ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ነው። ወደ ፈተና ክፍል ስትገቡም ሆነ ከመፈተናችሁ በፊት ልታደርጓቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፡
1. ከፈተናው በፊት፡ የስነ-ልቦና እና የዝግጅት ወቅት
እስካሁን ድረስ ያጠናችሁትን እቅድ አውጥታችሁ ከልሱ (Smart Revision):
አዳዲስ መፃህፍትን ለማጥናትና ለመዳሰስ በመሞከር ከመጨናነቅ ይልቅ እስካሁን የተማራችኋቸውን ዋና ዋና ነጥቦች፣ ማጠቃለያዎችና ያለፉ የፈተና ጥያቄዎችን (Past exam Papers) ደጋግማችሁ ከልሱ።
#አእምሯችሁን_በነፃነት_አዘጋጁ:
"አልችልም" ወይም "ብወድቅስ" የሚሉ አሉታዊ ሀሳቦችን አስወግዱ። ባለፉት አመታት ያሳለፋችኋቸውን ስኬቶች በማሰብ "እችላለሁ፣ አልፋለሁ!" የሚል ጠንካራ ስነ-ልቦና ይኑራችሁ።
#የእንቅልፍና_የጤና_ጉዳይ: በቂ እንቅልፍ አለማግኘት ትኩረትን ይበትናል። በመሆኑም ከፈተና በፊት ባሉት ቀናት ቢያንስ ከ7-8 ሰዓት መተኛት እና ቀላልና ገንቢ ምግቦችን መመገብ ለፈጣንና ንቁ አእምሮ እጅግ አስፈላጊ ነው።
#የቁሳቁስ_ዝግጅት: የተፈታችነት ማረጋገጫ መታወቂያ (Admission ID card)፣ ብዕር፣ እርሳስ፣ ላጲስ እና ሌሎች የሚያስፈልጓችሁን ነገሮች ከፈተናው ዋዜማ ምሽት ጀምሮ አዘጋጅታችሁ አስቀምጡ።
2. በፈተናው ቀን፡ በእርጋታ መጀመር
#በማለዳ_መነሳትና_መድረስ: በፈተናው ቀን በጠዋት በመነሳት፣ አእምሯችሁን አረጋግታችሁ ወደ ፈተና ጣቢያው ቀድማችሁ ተገኙ። መጣደፍ አላስፈላጊ ጭንቀትን ይፈጥራል።
#ትኩረትን_መሰብሰብ (Focus): ወደ ፈተና ክፍል ከመግባታችሁ በፊትም ሆነ ከገባችሁ በኋላ ከጓደኞቻችሁ ጋር የሚያስጨንቁ ወይም ግራ የሚያጋቡ የትምህርት አርዕስቶችን አታንሱ። በምትኩ በጥልቀት ትንፋሽ በመውሰድ ራሳችሁን አረጋጉ።
#ፀሎት_አድርጉ: እንደየእምነታችሁ አእምሯችሁን እንዲያበራላችሁ፣ ትውስታችሁን እንዲያድስላችሁና ሰላም እንዲሰጣችሁ ፈጣሪያችሁን በጸሎት ጠይቁ።
3. በፈተናው ወቅት፡ ብልሃተኛ መሆን
"ፈተናን መስራት እውቀትን ብቻ ሳይሆን ጊዜን የመጠቀም ጥበብንም ይጠይቃል።"
#መመሪያዎችን_በጥንቃቄ_ማንበብ:
የፈተናውን ወረቀት እንደተቀበላችሁ መመሪያዎቹን (Instructions) ሳታነቡ መጀመር ትልቅ ስህተት ነው። ምን ያህል ጥያቄዎች እንዳሉ እና የተሰጠውን ጊዜ በሚገባ አስተውሉ።
#ጊዜን_በአግባቡ_መከፋፈል: ለአንድ ጥያቄ ብዙ ጊዜ አታጥፉ። ቀላል የሆኑትንና የምታውቋቸውን ጥያቄዎች በፍጥነት በመስራት በራስ መተማመናችሁን ጨምሩ። አስቸጋሪ የሆኑትን ጥያቄዎች ምልክት አድርጋችሁባቸው እለፉና በኋላ ተመለሱባቸው።
#መልስ_ማጥቆር (Answer Sheet): በተለይ በመለስ መስጫ ወረቀት ላይ ስታጠቁሩ የጥያቄው ቁጥርና የማጥቆሪያው ቁጥር መገጣጠሙን ደጋግማችሁ አረጋግጡ። አንዱን ጥያቄ ዘላችሁ ከሆነ መልሱ ሌላ ቦታ እንዳይጠቆር ጥንቃቄ አድርጉ።
#ደግሞ_መፈተሽ (Review): ፈተናውን ሰርታችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ ጊዜ ካላችሁ መልሶቻችሁን አንድ በአንድ በጥንቃቄ ከልሱ። የዘለላችሁት ጥያቄ አለመኖሩን አረጋግጡ።
#የማጠቃለያ_መልዕክት
ውድ ተማሪዎች፤ ይህ ፈተና እናንተን ለመጣል ሳይሆን ወደ ቀጣዩ የታሪካችሁ ምዕራፍ እንድትሻገሩ የተዘጋጀ ድልድይ ነው። 6ኛ ክፍሎች ወደ መካከለኛ ደረጃ፣ 8ኛ ክፍሎች ወደ ሁለተኛ ደረጃ፣ እንዲሁም 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ወደ ህይወት ምዕራፍ የምታደርጉትን ጉዞ የሚያፋጥንላችሁ የቁርጠኝነታችሁ መለኪያ ነው።
ወላጆቻችሁ፣ መምህራኖቻችሁና መላው የት/ት ማህበረሰብ እናንተን ለመደገፍና በእናንተ ለመኩራት ዝግጁ ናቸው። በራሳችሁ እውቀት፣ ጥረትና ብቃት ተማመኑ። ከአላስፈላጊ ኩረጃና የፈተና ስርቆት ራሳችሁን ጠብቁ፤ ምክንያቱም በራስ ልፋት የሚገኝ አነስተኛ ውጤት በስርቆት ከሚገኝ የውሸት ውጤት በላይ ዘላቂ ክብርና እውነተኛ እውቀትን ይሰጣል።
እናንተ የኢትዮጵያ ተስፋዎች ናችሁ! መልካም የፈተና ወቅት ይሁንላችሁ፣ ስኬት ከእናንተ ጋር ይሁን!
✍
994
Repost from Yes Smart Education
Online Exams
English and Aptitude
For Grade 12 Students (Ethiopia)
=======
On Telegram Channels:
☞ Chercher (School)
☞ Yes Smart Education (Million)
