cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሐሰን ዳውድ

ኢስላማዊ እውቀት የሚተላለፍበት ቻናል 1,አቂዳ 2, ፊቂህ 3, ሀዲስ 4, ሉጋህ( ነህው;ሶርፍ,በላጋ,በያን,አደብ,አሩድ) 5, ሙስጠላህ 6,ኡሱል ሌሎችም አጫጭር መረጃዎች ያገኙበታል።

Show more
Advertising posts
1 126
Subscribers
No data24 hours
+97 days
+14230 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إنّ أولى الناسِ بي يومَ القيامةِ أكثرُهم عليَّ صلاةً﴾ “በትንሳዔ ዕለት ከሰዎች ሁሉ ለኔ በላጭ (ቅርብ) የሚሆነው በኔ ላይ በብዛት ሰለዋት የሚያወርድ ነው።” 📚 ሶሂህ አተርጊብ
881Loading...
02
ቢላል ኢብኑ ረባህ ๏ መጀመሪያ ከሰለሙት አንዱ ነው። ๏ እስልምናውን ለመጀመሪያ ጊዜ ግልፅ ካደረጉት ውስጥ አንዱ ነው። ⇨እስልምናቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ ግልፅ ያወጡት 7 ናቸው እነሱም ረሱል (ﷺ) ፣ አቡበክር ፣ ዐማር ፣ የዐማር እናት ሱመያህ ፣ ቢላል ፣ ሱሀይብ እና ሚቅዳድ ናቸው። ๏ መስለሙን ግልፅ ባወጣ ጊዜ በአለቃው ኡመያህ ኢብኑ ኸለፍ በጣም ከባድ ቅጣት ደርሶበት ነበር ነገር ግን እሱ አሀዱን አሀድ ከማለት አልተወገደም ነበር (ረ.ዐ) እየተቀጣ እያለ አቡበክር አሲዲቅ (ረ.ዐ) መጣና ገዝቶት ነፃ አወጣው። በዚህም ንግግሩ "አሀዱን አሀድ " በጣም ታዋቂ ሆነ አሀዱን አሀድ ሲባል በሁሉም ሰው ፊት የሚመጣው ቢላል እና ታሪኩ ነው። ๏ ለሰላት መጀመሪያ ጊዜ አዛን ያደረገው ነው ๏ በድር ዘመቻ ላይ አለቃው የነበረውን ኡመያን የገደለው እሱ ነው ๏ ረሱል (ﷺ) ዘንድ በጣም ትልቅ ደረጃ ነበረው ስለርሱ ብዙ ብለዋል ከነዛ ውስጥ‥ ⇨ጀነት ውስጥ የቢላልን ኮቴ መስማታቸውን ⇨ቀዳሚዎች 4 ናቸው እኔ የዐረብ ቀዳሚው ነኝ ፣ ስልማን የፋሪስ ቀዳሚ ነው ፣ ቢላል የሐበሻ ቀዳሚ ነው ፣ ሱሀይብ የሮም ቀዳሚ ነው ማለታቸውና ሌሎችም ተናግረዋል። ๏ እድሜው ወደ 60 ምናምን ሲደርስ አጀሉ ቀረበ ሊሞት አከባቢ ሚስቱ ወ ሀዘኔ አለች እሱም " ዋ ደስታዬ ነገ ወዳጆችን እንገናኛለን ሙሐመድን (ﷺ) እና ህዝቦቹን " (الأحبة نلقى غدا وحزبة محمدا) ሻም ውስጥ ሞተ እዛውም ተቀበረ‥ ⇨ትክክለኛ ስሙ ቢላል ኢብኑ ረባህ ይባላል የረሱል (ﷺ) ሙአዚን ተብሎም ይታወቃል ๏ የረሱል (ﷺ) ሙአዚኖች 4 ናቸው አንደኛው ቢላል ሲሆን ሁለተኛው አብደላህ ኢብኑ ኡሚ መክቱም ሶስተኛው አቡ መህዙረህ አራተኛው ሰዐድ አልቁረዚ ናቸው። ⇨የእናቱ ስም ሀማመህ ትባላለች https://t.me/Hassendawd
933Loading...
03
የኒካህ ቀለበት ዛሬ ላይ ብዙ ሰዎች ዘንድ የተሰራጨው ኒካህ ላሰረላት ሴት ቀለበት ማድረግ የሚባለው ተግባር ቀደምት ሙስሊሞች ዘንድ ይተገበር ያልነበረ ከክርስቲያኖች የተወሰደ ተግባር ነው። የዘመናችን ሙሀዲስ የሆኑት ሸይክ ናሲረዲነል አልባኒ እንዲህ ይላሉ "ይህ ተግባር ወደ ቀደመ (የክርስቲያኖች) ተለምዶ ይመለሳል። ሙሽራው በሙሽሪት የግራ እጅ አውራ ጣቷ ጫፍ ላይ ቀለበቱን ያደርግና በስመ አብ ይላል ከዛም አመልካች ጣቷ ጫፍ ላይ ያደርግና በወልድ ይላል ከዛም የመሀከለኛ ጣቷ ላይ ያደርግና በመንፈስ ቅዱስ ይላል በመጨረሻም አሚን በሚል ግዜ ከትንሿ ጣት ቀጥሎ ያለው ጣቷ ላይ ያደርገውና በዛው ይቀራል። ለንደን የሚታተም women የሚል ጋዜጣ (ቁ 19 1960 ገፅ 8) ላይ እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ Why is the wedding ring placed on the third finger of the left hand? ለምንድነው የሰርግ ቀለበት በግራ እጅ ሶስተኛ ጣት ላይሚቀመተው? በርእሱ ላይ መልስ የሚሰጠው Angela Talbot እንዲህ ብሎ “it is said there is a vein runs directly from the the finger to the heart. Also,there is the ancient origin whereby the bridegroom placed the ring on the tip of bride’s left thumb,saying ; “in the name of the father” on the first finger, saying “in the name of the son “ on the second finger, saying ; “And of the holy ghost”,on the word “Amen” , the ring was finally placed on the third finger where it remained” "ከዚህ ጣት ቀጥታ ከቀልብ የሚያገናኝ ደም ስር አለ ይባላል። ከዛም በተጨማሪ የቀደመ መሰረት አለው ካለ በሗላ ከላይ የጠቀስነውን በስምአብ...የሚለውን እስከመጨረሻው ጠቀሰ" በዚህ ንግግር እንደምንረዳው ይህ ተግባር የመጣው ከክርስቲያኖች እንደሆነና ጥንታዊ የሆነ እምነታዊ መሰረትም እንዳለው ነው። ይህንን የሚጠቅሱም ብዙ ኡለሞች አሉ። በመሆኑም ▪️ይህ ተግባር የክርስቲያኖች እምነታዊ መገለጫ ነው። ከነሱ መመሳሰል ደግሞ ከከባባድ ወንጀሎች ነው። ▪️ ይህን ቀለበት ግራ እጅ ከትንሿ ጣት ጎን ሚያደርጉበት ምክንያት ይህ ጣት ከልብ ጋር ግንኙነት አለው የሚል ከንቱ እምነት ይዘው ነው ይህ ደግሞ በእስልምና ቦታ የለውም ▪️ ብዙ ሰዎች ዘንድ ቀለበት ማሰሩ በመሀከላቸው ውዴታን ያመጣል የሚል እምነት አለ ይህም ከእስልምና አቂዳ ጋር ቀጥታ የሚጣረስ የሽርክ አይነት ነው። ▪️ አንዳንዶች ደግሞ ቀለበት ካለበሰ ወይም ካለበሰች ኒካው ትክክል አይመስላቸውም ይህም መሰረት የሌለው አጉል እምነት ነው። ▪️ ይህ ተግባር ቀደምት ሙስሊሞች ዘንድ ያልተለመደ ከክርስቲያኖች የተወረሰ ነው ▪️ አንዳንዶች ገና ሲተጫጩ ኒካም ሳያስሩ ወስዶ ቀለበት ያደርግላታል ይህ ደግሞ የተከለከለችን አጅነብይ ሴት እጅ መንካት ነው ያም ከባድ ወንጀል ነው። እንዳጠቃላይ ለኒካህ ወይም ሰርግ ብሎ ቀለበትን መልበስ የሙስሊሞች ሳይሆን የክርስቲያኖች ሱና ነው። ኢብን ኡሰይሚን ስለዚህ ሲናገሩ "እኔ ማየው አነሰ ቢባል ይህ ተግባር የተጠላ ነው ይላሉ።” ኢብን ባዝም ለሰርግ ብሎ ቀለበት ማሰር የሙስሊሞች ሱና እንዳልሆነ ይገልፃሉ። ሸይኽ አልባኒም እንደማይቻል ይገልፃሉ። ከዛ ውጪ ባለ ሁኔታ ግን ለኒካህ አስበህ ሳይሆን እንዲሁ ቀለበትን በኖርማል ግዜ ብትለብስ ችግር የለውም። ለወንድ ልጅ ግን የወርቅ ቀለበት አይፈቀድም። https://t.me/Hassendawd
54315Loading...
04
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته የተከበራችሁ እህትና ወንድሞች እንኳን ወደ ዛድ ኦንላይን የቂርአት ማዕከል በሰላም መጣችሁ እያልን መመዝገቢያ ፎርም እንደሚከተለው ይቀርባል። 1, ስም ከነ አያት__ 2, አሁን ያለንበት ሀገር____ 3,ዋሳፕና ቴሌግራም ምትጠቀሙበት ስልክ ቁጥር____ 4,ፆታ____ 5,የቂርአት ደረጃ_ 6.መቅራት የሚፈልጉት_ ማሳሰቢያ:- 👉🏿መድረሳችን በአንድ አመት 4 ሴሚስተር የሚኖሩት ሲሆን ክፍያ የሚፈፀመው በየ ሴሜስተሩ ነው። 👉🏿በቁርጠኝነት መማር የምትፈልጉ ብቻ እንድመዘገቡ በትህትና እንጠይቃለን። 👉🏿ትምህርቱ የሚሰጠው በዙም አፕ እና በ ቴሌግራም ስለሆነ ከወዲሁ አፑን በማውረድ ለትምህር እንድትዘጋጁ እናሳስባለን። _ መመዝገቢያ ሊንክ👉🏿 https://forms.gle/Ve6Fcex92Nu5sbRQ8 ይህን ሊንክ በመጫን ከአሁኑ ሰዓት ጀምራችሁ መመዝገብትችላላችሁ።
2202Loading...
05
አቡ ዑበይድ ኢብኑል ጀራህ ๏ መጀመሪያ ከሰለሙት አንዱ ነው። ๏ በጀነት ከተበሰሩት 10 ሳሃቦች አንዱ ነው። ๏ በሁለተኛው ጊዜ ወደ ሐበሻ ከተሰደዱት ሰሃቦች አንዱ ነው። ๏ ቁርአንን ከሀፈዙት (በቃል ከያዙት) ሰሃቦች አንዱ ነው። ๏ ረሱል (ﷺ) የተለያዩ ልኡካንን ሲልኩ አባ ዑበይዳን መሪ አድርጎ ነበር የሚልከው እርሱ ዘንድም በጣም ተወዳጅ ሰሃቢይ ነበር ከዛ የተነሳ ረሱል (ﷺ) ከሞቱ በኋላ አቡበክር ኺላፋው ለአቡ ዑበይዳህ ነው የሚገባው እስከማለት ደርሶ ነበር ከዛ በኋላ ነው ዑመር " አይ አለቃችን ፣ በላጫችን ፣ ረሱልም ዘንድ ይበልጠ ተወዳጅ የሆንከው አንተ ነህ " ብሎ አለ። ኺላፈውም ለአቡ በክር ቃል ተገባ‥ ⇨በአቡ በክር ኺላፋ ዘመን ሻምን ለመክፈት አቡ ዑበይዳን መሪ አድርጎት ነበር የላከው ተሳክቶለት ከፈታት…የተለያዩ ሀገራትንም ከፍቷል። ⇨በዑመር ኺላፋ ዘምንም ዑመር በሰራዊቶችና በሻም ሀገር ላይ መሪ አድርጎት ነበር። ⇨አቅሳ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከፈተችው በዑመር ኺላፋነት ዘመንና በአቡ ዑበይደህ ጦር መሪነት ነበር በዚህም ሰበብ የመሪዎች መሪ ይባላል። ๏ ሻም ሀገር ላይ ወባ ተከስቶ ነበር በዛ ሰበብ ከዚህች አለም ወደ ሌላኛው አለም ተሻገረ‥ ⇨ትክክለኛ ስሙ ዓሚር ኢብኑ አብደላህ ኢብኑል ጀራህ ይባላል ๏ የዚህች ኡማህ (ህዝብ) ታማኝ ተብሎም ይታወቃል ምክኒያቱ ደግሞ … ረሱል (ﷺ) ዘንድ የየመን ሰዎች መጡና " ከኛ ጋር ሱናን እና እስልምናን የሚያሰተምረን አንድን ሰው ላክ " አሉት ከዛም ረሱል (ﷺ) የአባ ዑበይዳህን እጅ ይዘው የዚህች ኡማህ ታማኝ እሱ ነው " አሉ። ⇨በሌላ ዘገባም " ለሁሉም ህዝብ ታማኝ አላቸው የዚህች ህዝብ ታማኝ ደግሞ አቡ ዑበይደህ ኢብኑል ጀራህ ነው " ብለዋል። ⇨የእናቱ ስም ኡመይመህ ቢንት ገነም ኢብኑ ጃቢር ትባላለች ๏ ኢብኑ ሀዝም አል አንደሉሲ ኡመይመህ ቢንት ዑስማን ኢብኑ ጃቢር ኢብኑ አብዱል ዑዛህ ብለውም አስቀምጠዋል ‥ https://t.me/Hassendawd
2051Loading...
06
ለኒካህ ዱፍ መምታት ዱፍ የሚባለው ከአንድ በኩሉ በቆዳ የተሸፈነ በሌላ ጎኑ ክፍት የሆነ ትንሽ ከበሮን የሚመስል በእጅ የሚመታ የሙዚቃ መሳሪያ ነው በዲነል ኢስላም የሙዚቃ መሳሪያዎች በሙሉ የተከለከሉ ናቸው። ማስረጃውም ኢማም ቡኻሪ ሰሒሀቸው ላይ በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል {{ ْلَیَكُونَنَّ من َأُمَّتِي أَقْوَامٌ یَسْتَحِلُّونَ حِرَ وَالْحَرِیرَ وَالْخَمْرَ وَالْمَعَازِف}} {ከኔ ኡማ ሰዎች ይመጣሉ ፦ ዝሙትን ፣ ሀር ልብስን (ለወንድ ልጅ) ፣ አሰካሪ መጠጥን እና የሙዚቃ መሳሪያን የሚፈቅዱ} ይህ ሀዲስ ሁሉም የሙዚቃ መሣሪያ ዱፍንም ጨምሮ መከልከሉን ይጠቁማል በተጨማሪም ኢማም አልበይሀቂ በዘገቡት ሀዲስ አብደላህ ኢብን አባስ ዱፍ ሀራም ነው ማለቱ ተወርቷል።¹⁶² እንደጥቅል ሁሉም የሙዚቃ መሳሪያዎች የተከለከሉ ቢሆንም ዱፍ ግን በተወሰኑ ሁኔታዎች ተፈቅዷል እነሱም በሰርግ፣ በኢድ እና የሩቅ እንግዳን ለመቀበል ነው።በነዚህ ሶስት ቦታዎች ላይ ዱፍ መምታትን የሚፈቅዱ የመጡ የተረጋገጡ ሀዲሶች አሉ።¹⁶³ ከነዚህ ሶስት ሁኔታዎች ውጪ ዱፍን መምታት የተፈቀደበት አናገኝም በመሆኑም የሙዚቃ መሳሪያ እንደመሆኑ እንደሌሎች የሙዚቃ መሳሪያዎች ሁሉ በሌሎች ሁኔታዎች ላይ የተከለከለ ይሆናል። በሸሪአ የተከለከለ ነገር ለሆነ ነገር ተነጥሎ ከተፈቀደ በዛ ላይ ብቻ ነው ፈቃዱ የሚሆነው እንጂ ለሁሉም ሁኔታዎች የተፈቀደ አይሆንም።ስለዚህ ሰርግ ላይ ዱፍን መጠቀም ይቻላል። በሰርግ ላይ እንኳን ቢሆን ከዱፍ ውጪ ያሉ የሙዚቃ መሳሪያዎችን መጠቀም በጭራሽ አይፈቀድም። ለወንድ ልጅስ ይፈቀዳል ወይስ በሴት ልጅ ብቻ የተነጠለ ነው? ለወንድ ልጅ ዱፍ መምታትን በተመለከተ ኡለሞች መሀከል ኺላፍ ያለበት ሲሆን አመዛኝ በሆነው የኡለሞች አቋም መሰረት ዱፋ መመታት የሚፈቀደው ለሴቶች ብቻ ነው።ምክንያቱም በሰሀቦች ዘመን ይህ ሚታወቀው ከሴቶች ዘንድ ነበር ከወንዶች መሀከል ይህን መስራት ደግሞ በሴቶች መመሳሰል ይሆናል።ከሴቶች መመሳሰል ደግሞ ከትልልቅ ወንጀሎች ውስጥ ነው። ሸይኩል ኢስላም ኢብን ተይሚያ እንዲህ ይላል “ከሰሀቦች መሀከል ዱፋ በመምታት የሚታወቅ ወንድ አንድም አልነበረም።እንዲያውም ይህንን የሚያደርግን ሰው ቀደምቶች ሴታሴት ብለው ይጠሩት ነበር” ¹⁶⁴ ኢብን ሀጀር እንዲህ ይላል “ጠንካራ የሆኑ ሀዲሶች ላይ ለሴቶች መፈቀዱን ይጠቁማል። በዚህ ላይ ወንዶች አይገቡበትም ጥቅል የሆነ ከሴቶች ጋር መመሳሰልን የሚከለክሉ ሀዲሶች ስላሉ።” ባጠቃላይ መልኩ ለወንድ ልጅ ጦር ውርወራ ፣ ፈረስ ግልቢያ እና የመሳሰሉት ተግባሮች ላይ መገኘት ነው ተገቢ ሚሆነው እንጂ የሴቶች ተግባር በሆኑት ዱፍ መምታት እና ማጨብጨብ ላይ መገኘት የለበትም። ስንጠቀልል ሴቶች ከወንዶች ጋር ሳይቀላቀሉ በሰርግ ስርአት ላይ ዱፍ እየመቱ እና ግጥምን እየገጠሙ መጫወት ይወደድላቸዋል።
2625Loading...
07
ሰኢድ ኢብኑ ዘይድ ๏ መጀመሪያ ከሰለሙት ውስጥ አንዱ ነው ሲሰልምም ከሚስቱ ጋር ነበር የሰለመው ከዑመር ኢብኑል ኸጣብ በፊትም ነበር የሰለመው። ๏ በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች አንዱ ነው። ๏ የዑመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.ዐ) አጎት ልጅ ነው እህቱ ደግሞ የዑመር ኢብኑል ኸጣብ ሚስት ናት ሚስቱ ደግሞ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ መስለም ሰበብ የሆነችዋ እህቱ ፋጢማህ ቢንቱል ኸጣብ ናት። ๏ ወደ መዲና መጀመሪያ ከተሰደዱት አንዱ ነበር። ๏ በሙዓዊያህ ኢብኑ አቢ ሱፍያን (ረ.ዐ) ኺላፋ ዘመን እድሜው ወደ 73 ከደረሰ በኋላ ጊዜው ደርሶ ይህችን ዱንያ ለቆ ወጣ ጁሙዓህ ቀን ነበር የሞተው ቦታውም ዐቂቅ ነበር ይባላል ከዛ ወደ መዲና ተይዞ ተመጣ ጀናዛውን ሰዐድ ኢብኑ አቢ ወቃስ (ረ.ዐ) አጥቦት ነበር መዲናም ተቀበረ… ⇨ትክክለኛ ስሙ ሰዒድ ኢብኑ ዘይድ ኢብኑ ዐምር ኢብኑ ኑፈይል ይባላል። ๏ የሰዒድ አባት በነቢዩላህ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ሐይማኖት ላይ ነበር ለጣኦቶች አይሰግድም ነበር ቁረይሾች የሚያርዱትን ነገር አይበላምም ነበር ረሱል (ﷺ) ከመላኩ በፊት ተገናኝቶት ነበርና ሱፍራ አቅርቦላቸው ነበር ረሱል (ﷺ) አይ አለው ከዛም ዘይድ እንዲህ አለ " እኔ እናንተ ጣኦቶቻችሁ ላይ የምታርዱትን አልበላም የአላህ ስም ያልተወሳበት ነገርም አልበላም " ๏ ረሱል (ﷺ) ስለ ዘይድ ተጠይቀው ነበር እንዲህም አሉ‥ " ቂያም ቀን ልክ እንደ አንድ ኡማህ (ህዝብ) ሆኖ ይቀሰቀሳል " ๏ በሌላም ቦታ እንዲህ ብለው ነበር " ጀነት ገብቼ ለዘይድ ሁለት ትላልቅ ዛፎችን አይቼ ነበር " ⇨የእናቱ ስም ፈጢማህ ቢንት በዕጀህ ኢብኑ ኡመያህ ትባላለች። https://t.me/Hassendawd
7742Loading...
08
2.3 ለሰርግ ተጠርተህ ግን ፆመኘ ከሆንክ ጾመኛ ስለሆንኩ ብለህ ከጥሪው መቅረት የለብሀም። ይልቁንስ ጥሪውን አክብረህ ትሄድና ከዛሀም ሁለት አማራጮች አሉህ አንደኛው፦ጾምህን ሳታጠፋ ቦታው ላይ ትገኝና ለሱ ዱአ ታደርግለታለህ መልእክተኛው ﷺ እንዲህ ብለዋል {{إذا دعي أحدكم إلى طعام فلیجب فإن كان مفطراً فلیطعم وإن كان صائما فلیصل. يعني :الدعاء }} {{አንዳችሁ ወደ ምግብ ከተጠራ ይሂድ ጾመኛ ካልሆነ ይመገብ ጾመኛ ከሆነ ደግሞ ዱአ ያድርግ}} ሁለተኛው፦ ጾምህ ሱና ጾም ከሆን ወንድምህን ለማስደሰት ስትል ማፍጠርም ትችላለህ።በተለይ ደግሞ ወንድምህ እንድትመገብ የጠነከረ ፍላጎት ካለው።ሱና ጾም መጾሙ ግዴታ እንዳልሆነው ሁላ ጀምሮት ከነበረ መጨረሱም ግዴታ አይሆንም። በዚህ ላይ የመጣ ሀዲስ አለ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል {{ الصائم المتطوع أمیر نفسھ إن شاء صام وإن شاء أفطر }} {{ሱና ጾም የሚጾም ሰው የራሱ አዛዥ ነው።ከፈለገ ይጾማል ከፈለገ ያፈጥራል}} 📖 ጾሙ ሱና እስከሆነ ድረስ ያፈጠረውን ቀን በሌላ ግዜ ቀዳ ማውጣት ግዴታ አይሆንበትም ነገር ግን ቀዳ ቢያወጣውም ይችላል። ይህንን የሚጠቁም ኢማመል በይሀቂ የዘገቡት ሀዲስ አለ። ጾሙ ግን የግዴታ ጾም ከሆነ ለምሳሌ የረመዳን ቀዳ ከሆነ ወይ ደግሞ የመሀላ ከፋራ ከሆነ ማፍጠር አይፈቀድለትም።
3963Loading...
09
‏قال سفيان الثوري رحمه الله : -  لما التقى يعقوب ويوسف عانق كل واحد منهما صاحبه وبكى، فقال يوسف : - يا أبتا ، بكيت علي حتى ذهب بصرك ، ألم تعلم أن القيامة تجمعنا قال : - بلى ، يا بني ولكني خشيت أن تسلب دينك فيحال بيني وبينك• ﴿ شعب الإيمان للبيهقي ( 183/3 ))•
2990Loading...
10
2.2 ሀብታሞችን ብቻ ነጥሎ መጥራት አይቻልም? በድግሱ ላይ ድሀዎች ሳይጠሩ ሀብታሞች ብቻ ተነጥለው ሊጠሩ አይገባም ይህን ዛሬ ላይ በብዙ ሰርጎች ለመታዘብ ችያለሁ ለሰርጉ ፕሮቶኮል ሲባል ደሀዎች ከነጭራሹ አይጠሩም! መልእክተኛው ﷺ እንዲህ ብለዋል {{شر الطعام طعام الولیمة یدعى لها أغنیاء ویمنعها المساكین ومن لم یجب الدعوة فقد عص ﷲ ورسوله }} {{መጥፎ ምግብ የሰርግ ምግብ ነው። ሀብታሙ ይጠራላታል ደሀው ይከለከላል።ተጠርቶ ያልሄደ አላህንና መልእክተኛውን አምጿል}} የሰርግ ጥሪ ማክበር ግዴታ ነው? የሰርግ ጥሪ የተጠራ ሰው የመሄድ ግዴታ አለበት።የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል {{ ومن لم یجب الدعوة فقد عص ﷲ ورسوله }} {{ተጠርቶ ያልሄደ አላህንና መልእክተኛውን አምጿል}} ጥሪው ላይ መገኘት ግዴታ እንዲሆን ግን እነዚህ መስፈርቶች መሟላት አለባቸው 1) ይህ የመጀመሪያ ድግስ ከሆነ ነው፦ አንድትን ልጅ አግብቶ በተደጋጋሚ የሚደግስ ከሆን መገኘቱ ግዴታ ሚሆንብን የመጀመሪያው ድግስ ላይ ብቻ ነው።ሁለተኛና ሶስተኛ ድግስ ላይ መገኘነት ግዴታ አደለም 2) ጠሪው ሙስሊም ከሆነ ፦ ክርስቲያን ወይም የሌላ እምነት ተከታይ ለሰርግ ቢጠራን የመሄድ ግዴታ የለብንም። የጠራን ከእምነቱ ጋር ተያያዥነት በሌለው ድግስ እስከሆነ ደረስ ግን ብንሄድም ችግር የለውም በተለይ በመሄዳችን ለነሱ ዳእዋ ማድረግ ሚያስችለን ከሆነ መሄዱ ተገቢ ይሆናል።መልእክተኛውን የሁድይ ጠርታቸው ሄደዋል። 3) በግለሰብ ደረጃ ተነጥሎ ከተጠራ ነው፦ በግል ተነጥቶ እስካልተጠራ ድረስ በጥቅል ከሰዎች ጋር ከተጠራ መሄድ ግዴታ አይሆንበትም።ለምሳሌ መስጊድ ውስጥ ቁጭ ባለበት አንድ ሰው ተነስቶ እዚህ መስጊድ ያላችሁ በሙሉ ለሰርጌ ተጠርታችኋል ተብሎ ቢጠራ የመሄድ ግዴታ አይኖርበትም። 4) ወንጀሎች ያሉበት ድግስ መሆን የለበትም፦ ሙዚቃ፣ የሴትና ወንድ መቀላቀል፣ኸምር እና የመሳሰሉ ወንጀሎች ያለበት ቦታ ቢጠራ መሄድ አይፈቀድለትም ነገር ግን የተጠራው ሰው እዛ ቦታ ተገኝቶ ያንን ወንጀል ማስወገድ ከቻለ በቦታው መገኘቱ ግዴታ ይሆንበታል። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል {{من رأى منكم منكرا فلیغیره بیده }} {{ከናንተ መሀከል ወንጀልን ያየ ሰው በእጁ ይቀይረው}} ነገር ግን ወንጀሉን ማውገዝ ካልቻለ በቦታው መገኘት አይፈቀድለትም። ለዚህ ማስረጃው አላህ እንዲህ ማለቱ ነው { وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوٰى ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوٰنِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ } {{በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡}} ወንጀል ሲሰራ እያየ እዛው መቀመጥ ከከባባድ ወንጀሎች ነው አላህ እንዲህ ይላል፦ { وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِى الْكِتٰبِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ ءَايٰتِ اللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا مَعَهُمْ حَتّٰى يَخُوضُوا فِى حَدِيثٍ غَيْرِهِۦٓ ۚ إِنَّكُمْ إِذًا مِّثْلُهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ جَامِعُ الْمُنٰفِقِينَ وَالْكٰفِرِينَ فِى جَهَنَّمَ جَمِيعًا } {{በእናንተም ላይ በመጽሐፉ ውስጥ የአላህን አንቀጾች በርሷ ሲካድባትና በርሷም ሲላገጥባት በሰማችሁ ጊዜ በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ ከእነሱ ጋር አትቀመጡ፡፡ ማለትን በእርግጥ አወረደ፡፡ እናንተ ያንጊዜ ብጤያቸው ናችሁና፡፡ አላህ መናፍቃንን እና ከሓዲዎችን በሙሉ በገሀነም ውስጥ ሰብሳቢ ነውና፡፡}} 📖 በመሆኑም ወንጀል የሚፈጸምበት ሰርግ ከተጠራ እንደማይገኝ ለጠሪዎቹ ማሳወቁ ተገቢ ነው።የማይገኝበትም ምክንያት በዛው ቢገልጽላቸው ዳእዋ ይሆንለታል። ምናልባትም ጠሪዎቹ የሱን በቦታው መገኘት በጣም ሚፈልጉት ከሆነ ለሱ ብለው ሊሰሩት አስበውት የነበረውን ወንጀል ይተውት ይሆናል ይህ ደግሞ ትልቅ ዳእዋ ነው ። ስለዚህ ሰርግ ተጠርተን ማንሄድ ከሆነ ምክንያቱን እንንገራቸው ። በተቃራኒው ደግሞ ሳንነግራቸው ከቀረን ንቀናቸው ለኩራት የቀረን ሊመስላቸው ይችላል። ይህ ደግሞ ዳእዋውን ሊያስመታ ይችላል 5) ጥሪውን ተቀብለን በመሄዳችን የተነሳ ችግር ላይገጥመን፦አንድ ሰው ሰርግ ተጠርቶ ነገር ግን ሰርግ መሄዱ ጉዳት ሚያስከስትበት ከሆነ ሰርጉን መሄድ ግዴታ አይሆንበትም 6) ጠሪው አምኖበት የጠራው መሆን አለበት፦የጠራው አካል የጠራበት ምክንያት ወቀሳን ፈርቶ ከሆነ ወይ ደግሞ ስለፈራው ከሆነ አልያ ደግሞ እንዲው እንዲያውቅለት ብቻ ስለፈለገ ከሆነ የጠራው መሔዱ ግዴታ አይሆንም። ለምሳሌ አንድ ሰው ደግሶ ሳይጠራህ ድንገት በቤቱ አጠገብ ስታልፍ ተገጣጥማቹ ስላየህው እፍረት ተሰምቶት ብቻ ና ሰርግ ግባ ቢልህ ይህ ጥሪ በእፍረት እንጂ ከልቡ ያንተን መምጣት ፈልጎ ስላልሆነ በዚህ ሰርግ ላይ መገኘትህ ግዴታ አደለም። እንደውም ጠሪው አካል ያንተን መገኘት ሳይፈልግ ነገር ግን ሳይጠራህ ማለፍ ስለከበደው ብቻ ከሆነ የጠራህ መሄድ የለብህም። የጠራን ሰው ገንዘቡ ከሀራም የሚያገኘው ከሆነ መሄድ ይፈቀዳልን? አንዳንድ ኡለሞች ድግሱን የደገሰው ሰውዬ ገንዘቡን የሚያገኘው ከሀራም ከሆነ እዛ ሄዶ መመገብ አይቻልም የሚል አቋም አላቸው።በነዚህ ኡለሞች አቋም መሰረት ሰውዬው ወለድ ሚበላ ከሆነ እሱ ጋር ሄዶ መመገብ አይቻልም ምክንያታቸው ደግሞ ከሀራም እንዳትመገብ ነው።የሀዲስ ማስረጃዎችን በምንመለከት ግዜ ግን ይህ አቋም ትክክል አለመሆኑን እንረዳለን። መልእክተኛው ﷺ ካፊሮች ስጦታ ሲሰጧቸው ይቀበሉ ነበር አይሁድይ የሆነች ሴት ደግሳ ጠርታቸውም ተገኝተው ተመግበዋል።እንደሚታወቀው አይሁዶች ገንዘባቸው ወለድን ከመሳሰሉ ሀራም ነገራቶች አይጠራም። በሀራም ባገኘው ገቢ መተዳደሩ ለራሱ ከባድ ወንጀል ቢሆንበትም እኛ ግን ይህን ምግብ የደረሰን ሀላል በሆነ መንገድ ስለሆነ ችግር የለውም። https://t.me/Hassendawd
3314Loading...
11
በመስጂድ እንደዚህ ተንጋሎ መተኛት ይቻላል عن عبدِالله بن يزيد أنَّه رأى رسولَ الله ﷺ مُستَلِقياَ في المسَجْدِ وَاضعًا إحْدَى رِجْليْهِ عَلى الأُخْرىَ. متفقٌ عَلَيْهِ
2221Loading...
12
እንዲህም አለ…‼ ============= ✍ አንድ ወንድም ትናንት ይህን መልዕክት በውስጥ ላከልኝ። «Selam, Endet nek  murad  እሁድ እለት ሚሊኒየም አዳራሽ የፋም ውሀ ባለቤት የልጁ ሰርግ ነበር እና 6000 ሰው ነበር የተጠራው።  የሚገርምክ አብዛኛው ሰው ስለሰርጉ ገምቶ የሄደው ጭፈራ፣ ምናምኑን ለማየት ጓግቶ ነበረ። ግን ሰውየው ባልተጠበቀ መልኩ መክፈቻውን በቁርአን አድርጎ ወንድና ሴቱን ለየብቻ አስቀምጦ፣ ብዙ ኡስታዞችን በመጥራት በዳእዋ በሚገርም ሁኔታ ሰርጉ አልፏል። የሚገርምክ የሱ ጓደኞች ሰርግ ላይ ዘፋኞችን ይጋብዛሉ፣ መጠጥ ሁላ ሳይቀር ነበር። ለብዙዎቹ ባለሀብቶች ትልቅ ትምህርት ሰጥቶ ነው ያለፈው።» አለኝ! እኔንም የገረመኝ አሁን ባለንበት ዘመን ሰርጎቻችን ከኢስላማዊ እሴታቸው ወጥተው ፍጹም የሌላን ሰርግ መስለዋል። በዚህ የማን ሰርግ ይድመቅ በሚባልበት አላስፈላጊ ፉክክርና ይይሉኝ እንኳን ባለሃብት የሆነ ሰው፤ ድሃ የሚባል ሰው ራሱ ገንዘብ ከዚህም ከዚያም ተበድሮ በትልቅ አዳራሽ ውስጥ በርካታ ባንድና ካሜራ ማን በተሰባሰበበት በሐራም ጨፍሮና አላህን አምፆ ያሳልፋል። ከዚያ በተጋቡ በአንድ ወሩ ያበደሩት ሰዎች ከስልክ መደወል አልፈው በየተራ በሩን በጠዋት እያንኳንኩ ያሰቃዩታል፤ እርሷንም ያሳቅቃታል። ከዚህም ያለፈ መዘዝ ይከተላል። ይህ በሆነበት ተጨባጭ ይህ ሰው (ስሙን ስለማላውቀው ነው) መሰል ነገሮችን ለማድረግ ለማድረግ አቅሙ ቢኖረውም፤ ግና ነፍስያውን አቅቦ በዚህ መልኩ የልጁን ሰርግ ማሳለፉ ደስ ያሰኛል። ሌሎች ባለሃብቶችም ከዚህ ተማሩ። የልጃችሁ ሰርግ የተባረከና መልካም ልጆች የሚፈሩበት ትዳር ይሆን ዘንድ በዚህ መልክ ሐላል ሰርግ ማሳለፍ ከሰበቦቹ መካከል አንዱ ነው። አላህ ይጨንርለት፤ ደግሞ ውሃውንም እየጠጣችሁስ! || t.me/MuradTadesse
2723Loading...
13
ሰዐድ ኢብኒ አቢ ወቃስ ๏ መጀመሪያ ከሰለሙት ሰምንቶቹ እና በአቡበክር አሲዲቅ (ረ.ዐ) እጅ ከሰለሙት ውስጥ አንዱ ነው። ⇨ሰዐድ እናቱን በጣም ይወዳትም ይታዘዛትም ነበር እናትይው ሰዐድ መሰለሙን ስታውቅ " ሰዐድ ሆይ ይህ ፈጠራ ምንድነው? ይህን ሐይማኖትህን ትተዋለህ ወይም እስክሞት ድረስ አልበላም አልጠጣም ከዛም ታፍርብኛለህ " አለችው። ሰዐድም " እናቴ ሆይ ይህን አታድርጊው እኔ ሐይማኖቴን አልተውም " አላት አንድ ቀንና አንድ ለሊት ስትቆይ በጣም ተዳከመች ከዛ ሰዐድም እንዲህ አላት " በአላህ ይሁንብኝ 1ሺህ ነፍስ ኖሮሽ አንድ በአንድ ብትወጣም ሐይማኖቴን ለአንድም ነገር ብዬ አልተውም " አላት ይህን ስትሰማና ቆራጥነቱን ስታይ መብላትና መጠጣት ጀመረች‥ አላህም ይህችን አንቀፅ አወረደ " ለአንተ በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህም አትታዘዛቸው ፡፡ በቅርቢቱም ዓለም በመልካም ሥራ ተወዳጃቸው ወደእኔም የተመለሰን ሰው መንገድ ተከተል ፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደእኔ ነው ፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ (አልነው) ፡፡" [ሉቅማን 15 ๏ በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ๏ ከረሱል (ﷺ) አጎቶች አንዱ ነው። ๏ በአላህ መንገድ መጀመሪያ ቀስትን የወረወረው ነው። ๏ በአላህ መንገድ መጀመሪያ ደም ያፈሰሰው ነው። ๏ መጀመሪያ ወደ መዲናህ ከተሰደዱት አንዱ ነው። ๏ ብቸኛው ረሱል (ﷺ) እናት እና አባቴ ፊዳእ(መስዋእት) ይሁኑልህ ያሉት ሰሃቢይ ነው። ⇨ኡሁድ ዘመቻ ላይ ሌሎች ሲያፈነግጡ እሱ ከፀኑት ነበር ሰዐድ ቀስት ውርወራ ላይ በጣም ጎበዝ ነበርና የዛን ቀን ቀስት ወርዋሪም ነበር ዙህሪ እንዲህ ይላል " አንድ ሺህ ቀስት ወርውሯል ረሱልም (ﷺ) ወርውር እናት አባቴ ፊዳ ይሁኑልህ ሲሉትም ነበር " ሰዕድም እየነሸደ ይወረውር ነበር። ๏ እድሜው 70 ምናምን ሲደርስ ከዚህች አለም ወደ ቀጣዩ አለም ተሻገረ ከሙሃጂሮች መጨረሻ የሞተውም እርሱ ነበር‥ ⇨ትክክለኛ ስሙ ሰዐድ ኢብኑ አቢ ወቃስ ማሊክ ኢብኑ ዉሀይብ ይባላል። ⇨የእናቱ ስም ሀምነቱ ቢንት ሱፍያን ኢብኑ ኡመያህ ኢብኑ አብዱሸምስ ትባላለች‥
2985Loading...
14
ምእራፍ ሁለት 2.1 የሰርግ ድግስ ሸሪአዊ ብይን አብዛኛዎቹ ኡለሞች ባሉበት አቋም መሰረት ለሰርግ መደገስ የተወደደ ተግባር ነው ለዚህ ደግሞ ማስረጃ የሚሆነው የመልእክተኛው ﷺ ንግግር እና ስራ ነው። ንግግራቸውን በምንመለከት ግዜ ለአብዱረህማን ቢን አውፍ እንዲህ ብለውታል {{أولم ولو بشاة }} {{በፍየል እንኳን ቢሆን ደግስ}} በተግባርም መልእክተኛው ﷺ ሲያገቡ መደገሳቸው ተረጋግጧል።አንዳንድ ኡለሞች “በፍየል እነኳን ቢሆን ደግስ” የሚለውን የመልእክተኛውን ትእዛዝ ይዘው መደገስ ግዴታ ነው ያሉ አሉ። ከድግሱ ጋር የተየያዙ ሱናዎች 1.የሰርግ ድግሱን መደገስ ያለበት ባልየው ነው።ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ ደግስ ያሉት ለአብዱረህማን ቢን አውፍ ለራሱ ነው ለሚስት ቤተሰቦች ደግሱ አላሉዋቸውም በተጨማሪም ደስታው በባል በኩል ያለው የበለጠ ነው በብዛት ልጅቷን ፈልጎ የሄደውና ያገኛት እሱ ነው ሚሆነው። 2. ማባከን ደረጃ እስካልደረሰ ድረስ የድግሱ መጠን ምንም ገደብ የለውም ሀብት ካለው ቢያንስ አንድ ፍየል ማረድ አለበት ምክንያቱም መልእክተኛው ﷺ ለአብዱረህማን “በፍየል እነኳን ቢሆን ደግስ” ብለውታል።በዚህ ሀዲስ መሰረት ከቻለ ሁለት ሶስትም ወይም ከዛ በላይም ቢያርድ ሚከለክለው ነገር የለም። አቅም የሌለው ሰው ግን ከዛ ባነሰም ነገር መደገስ ይችላል። 3. ድግሱን ቤቱ ባስገባት በሶስተኛው ቀን ላይ መሆኑ ይወደዳል።¹⁴⁵ መልእክተኛው ﷺ ሰፍያን ሲያገቡ በሶስተኛው ቀን ነበር የደገሱት። 4. ድግሱ ላይ አላህን ሚፈራ ሰው ነው መጥራት ያለበት ፦ መልእክተኛው ﷺ እንዲህ ብለዋል {{لا تصاحب إلا مؤمنا ولا یأكل طعامك إلا تقي }} {{ሙእሚንን እንጂ ጓደኛ አታድርግ አላህን ሚፈራ እንጂ ምግብህን እንዳይበላ}} ለሰርጉ ክርስቲያኖችን መጥራት ይቻላል? ሙስሊም ላልሆነ እና ሙስሊሞችን ለማያስቸግር ሰላማዊ ሰው ግዲታ ያልሆነን ሰደቃ መስጠት ይቻላል።በመሆኑም ይህን ሰው ለሰርግ ጥሪ ጠርቶት ምግብ ቢመገብ ችግር የለውም። ለዚህ ማስረጃው አላህ እንዲህ ማለቱ ነው { لَّا يَنْهٰىكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ لَمْ يُقٰتِلُوكُمْ فِى الدِّينِ وَلَمْ يُخْرِجُوكُم مِّن دِيٰرِكُمْ أَن تَبَرُّوهُمْ وَتُقْسِطُوٓا إِلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ } {ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ (ከሓዲዎች) መልካም ብትውሉላቸውና ወደእነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም፡፡ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና፡፡} በተለይ ደግሞ በዚህ አጋጣሚ ተጠቅሞ እነዚህን ሰዎች ወደ እስልምና ለመጥራት ይረዳል ተብሎ ከታሰበ ይህን ነገር ማድረጉ እንደውም ያስወድሰዋል። ሙስሊሞችን የሚያስቸግር ሰው ከሆነ ግን ለሱ ሰደቃ ማድረግ አይቻልም።አላህ እንዲህ ይላል { إِنَّمَا يَنْهٰىكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ قٰتَلُوكُمْ فِى الدِّينِ وَأَخْرَجُوكُم مِّن دِيٰرِكُمْ وَظٰهَرُوا عَلٰىٓ إِخْرَاجِكُمْ أَن تَوَلَّوْهُمْ ۚ وَمَن يَتَوَلَّهُمْ فَأُولٰٓئِكَ هُمُ الظّٰلِمُونَ } {አላህ የሚከለክላችሁ ከእነዚያ በሃይማኖት ከተጋደሉዋችሁ፣ ከቤቶቻችሁም ካወጡዋችሁ፣ እናንተም በማውጣት ላይ ከረዱት (ከሓዲዎች) እንዳትወዳጁዋቸው ብቻ ነው፡፡ ወዳጅ የሚያደርጓቸውም ሰዎች እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው፡፡ } 📖 ነገር ግን እነሱን ለሰረግ መጥራቱ ከዳእዋ አንጻር ምንም ጥቅም ከሌለው የተሻለው ባይጠራቸው ነው። የአላህ መልእክተኛ በሀዲሳቸው ላይ “አላህን ሚፈራ ሰው እንጂ ምግብህን እንዳይበላ” ብለዋል። ስጋ የሌለበት ድግስ ከላይ እንዳሳለፍነው የቻለ ሰው ቢያንስ አንድ ፍየልን ወይም በግን አርዶም ቢሆን መደገስ አለበት ነገር ግን ያን አቅም የሌለው ሰው በሌላ በፈለገው ነገር ቢደግስ እና ድግሱ ላይ ስጋ ባይኖርበት እንኳን ችግር የለውም።ለዚህ ማስረጃው ደግሞ መልእክተኛው ﷺ ሰፍያን ሲያገቡ በኸይበርና በመዲና መሀከል ነበር የደገሱት በዛህ ድግስ ላይ ስጋ አልነበረበትም።
7054Loading...
15
የምእራፍ አንድ ማጠቃለያ 1.28 ሶላት ከማይሰግድ ሰው ጋር በትዳር አብሮ ስለመኖር ሰላት ከሁለቱ የምስክርነት ቃሎች ቀጥሎ ትልቁ የእስልምና ማእዘን መሆኑ ይታወቃል።ሚዛን በሚደፋው የኡለሞች አቋም መሰረት ሰላትን ሙሉ ለሙሉ መተው ከእስልምና ያስወጣል። ይህ ሀናቢላዎች አቋም ሲሆን ለዚህ ደግሞ በርካታ ማስረጃዎች አሉ ከነዛ መሀክል 1. መልእክተኛው ﷺ በሀዲስ ላይ እንዲህ ብለዋል፦ {{بین الرجل وبین الكفر ترك الصلاة }} {{በአንድ ሰው እና በኩፍር መሀከል ያለው ሰላትን መተው ነው}} 2. አሁንም መልእክተኛው ﷺ በሌላ በሀዲስ ላይ እንዲህ ብለዋል {{ العهد الذي بیننا وبینهم الصلاة فمن تركها فقد كفر }} {{በእኛ እና በእነሱ መሀከል ያለው ቃል ኪዳን ሰላት ነው የተዋት በርግጥም ከፍሯል}}። 3. በዚህ ላይ የሰሃቦች ጥቅል ስምምነት እንዳለበት ዑለሞች ጠቅሰዋል። 📖 በመሆኑ ሰላትን ሙሉ ለሙሉ መተው ከእስልምና እንደሚያስወጣ ከተረዳን ሰላትን ከተወ ሰው ጋር በትዳር አብሮ መኖር አይቻልም።መጀመሪያውኑም ሰላት ማይሰግድ ከነበረ ከሱ ጋር የታሰረው ኒካህ ትክክል አይሆንም።ኒካው ከታሰረ በኋላ በመሀል ሰላትን ሙሉ ለሙሉ ከተወ ከሱ ጋር አብሮ መኖሩ አይፈቀድላትም። ኢብን ኡሰይሚን እንዲህ ይላሉ “ኒካዊ ሲታሰር ይሰግድ ከነበረና ከዛ በኋል ግን መስገድ ካቆመ (ሰላቱን ያቆመው) ሳይገናኛት በፊት ከሆነ ኒካው ፈርሷል ወዲያውኑ የፈለገችውን ማግባት ትችላለች።ከተገናኛት በኋላ ከሆነ ሰላቱን ያቆመው ኒካው ይፈርሳል ነገር ግን ኢዳዋ እስኪያበቃ ድረስ መጠበቅ አለባት አላህ ወደ እስልምና ከመለሰው ባሏ ነው አልያ ሌላ ማግባት ትችላለች” *የኢብን ኡሰይሚን ምክር “ብዙ ሴቶች የልጆች መኖር ትዳርን ላለማፍረስ ይከለክላቸዋል። ይህ ትልቅ ነጥብ ነው! ትዳሩን አፍርሺ ትባያለሽ (ትዳርሽን ማፍረስ አለብሽ።ከዚህ ሰላቱን ከማይሰግድ ካፊር ጋር ልትቆይ አይፈቀድልሽም, አባታቸው በዚህ ሁኔታ ላይ እስካለ ድረስ ልጆችሽ አይለዩሽም ለሱ በነሱ ላይ ስልጣን የለውም።ካፊር ሙእሚን ላይ ስልጣን የለውም (አላህ ቁርአን ላይ እንዲህ ይላል) { وَلَن يَجْعَلَ اللَّهُ لِلْكٰفِرِينَ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ سَبِيلًا } ( አላህም ለከሓዲዎች በምእምናን ላይ መንገድን በፍጹም አያደርግም፡፡) ባንቺና በልጆችሽ መሀከል አይለይም፡ይህ ባልማ ምንም ኸይር የለበትም ።” https://t.me/Hassendawd
2502Loading...
16
አብዱሮህማ ኢብኑ አውፍ ๏ መጀመሪያ ከሰለሙት ስምንቶቹ እና በአቡበክር አሲዲቅ (ረ.ዐ) እጅ ከሰለሙት 5 ሰሃቦች አንዱ ነው እነሱም … ዙበይር ኢብኑ ዐዋም ፣ ዑስማን ኢብኑ ዐፋን ፣ ጠልሃህ ኢብኑ ዑበይዲላህ ፣ ሰዐድ ኢብኑ አቢ ወቃስ እና አብዱረህማን ኢብኑ ዐውፍ ናቸው (ረ.ዐ) ๏ በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ๏ ወደ ሐበሻ መጀመሪያ ከተሰደዱት ውስጥ ነው። ๏ ረሱል (ﷺ) በተቡክ ዘመቻ ላይ ከኋላው ሆነው ሰግደዋል። ๏ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.ዐ) ለውይይት ብሎ ከመረጣቸው ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ⇨ዑመር ተወግቶ ለሞት በተቃረበበት ጊዜ ለ3ተኛው ኺላፋነት የሚሆንን አካል ተወያይተው እንዲመርጡ ረሱል (ﷺ) ከነሱ ወዶላቸው ነው የሞቱት በማለት 6 ሰሃቦችን መርጦ ወክሎ ነበር። እነኚህ ሰሃቦች 6ቱ የውይይቱ አካላት ይባላሉ እነሱም… ዑስማን ኢብኑ ዐፋን ፣ አብዱረህማን ኢብኑ ዐውፍ ፣ ዐሊይ ኢብኑ አቡ ጣሊብ ፣ ዙበይር ኢብኑ ዐዋም ፣ ሰዐድ ኢብኑ አቢወቃስ እና ጠልሃህ ኢብኑ ዑበይዲላህ ናቸው (ረ.ዐ) ๏ በጣም ሀብታምና ቸር ነበር ንብረቱን ለእስልምና ድጋፍ ያውለው ነበር ለትግል (ለጂሃድ) 500 ፈረሶችንና 500 ግመሎችን ገዝቶ ነበር። ๏ በዑስማን ኺላፋ ዘመን እድሜው ወደ 72 ወይም በሌላ ዘገባ 78 ሲደርስ ጊዜው ደረሰና ከመሞቱ በፊት ንብረቱን በድር ዘመቻ ላይ የተሳተፉ 100 ሰሃቦች ነበሩ ለእያንዳንዳቸው 4መቶ ዲናር ተናዘዘላቸው በአላህ መንገድ ብሎም 1 ሺህ ፈረስን ተናዞ ነበር ከዚህች አለምም ወደዛኛው ዓለም ተሻገረ ‥ . ⇨ትክክለኛ ስሙ አብዱረህማን ኢብኑ ዐውፍ ኢብኑ ዐብዱ ዐውፍ ይባላል ሌላ የተለየ ስያሜ አልነበረውም ነገር ግን በጃሂሊያ ጊዜ አብዱ ዐምር ውይም አብዱል ከዕባህ ይባል ነበር ተብሏል። ከሰለመ በኋላ ረሱል (ﷺ) አብዱረህማን አሉት። ⇨የእናቱ ስም አሺፋእ ቢንት ዐውፍ ኢብኑ ዐብድ ኢብኑ ሃሪስ ትባላለች‥ https://t.me/Hassendawd
1 2463Loading...
17
"ፈገግ በሉ" በሚለው👇 "አቡ ነዋስ" የሚባል የታወቀ ገጣሚ ነበር። በጊዜው የነበረው አሚር ያስጠራውና አሚሩ "የፃፍኳትን ግጥም ገምግምልኝ" ብሎ ግጥሙን አነበበለት። አቡ ነዋስ የአሚሩ ግጥም ከሰማ በኀላ "ምንም ዓይነት የግጥም ሽታም የለውም" አለው። አሚሩ ተናዶ "ውሰዱና በአህያዎች በረት ለ1 ወር እሰሩት" አላቸው። ከወር በኋላ "መልሳችሁ አምጡት" አላቸውና ድጋሚ ሌላ ግጥም አነበበለት። ልክ አንብቦ ሲጨርስ አቡ ነዋስ ሊወጣ ተነሳ። አሚሩ አስቆመውና "የት ልቴድ ነው?" ሲለው 👇👇👇👇 "ወደ አህዮቹ በረት" ❕
4056Loading...
18
"ፈገግ በሉ" በሚለው👇 "አቡ ነዋስ" የሚባል የታወቀ ገጣሚ ነበር። በጊዜው የነበረው አሚር ያስጠራውና አሚሩ "የፃፍኳትን ግጥም ገምግምልኝ" ብሎ ግጥሙን አነበበለት። አቡ ነዋስ የአሚሩ ግጥም ከሰማ በኀላ "ምንም ዓይነት የግጥም ሽታም የለውም" አለው። አሚሩ ተናዶ "ውሰዱና በአህያዎች በረት ለ1 ወር እሰሩት" አላቸው። ከወር በኋላ "መልሳችሁ አምጡት" አላቸውና ድጋሚ ሌላ ግጥም አነበበለት። ልክ አንብቦ ሲጨርስ አቡ ነዋስ ሊወጣ ተነሳ። አሚሩ አስቆመውና "የት ልቴድ ነው?" ሲለው 👇👇👇👇 "ወደ አህዮቹ በረት
10Loading...
19
Media files
3461Loading...
20
የሙሐዲሶች አይተኬ ሚና ! 📚📚📚📚📚📚📚📚📚 እሥልምናን በማንቋሸሽ እና እሥልምና ላይ በማሴር የሚታወቅ አንድ ሰው ተይዞ እርምጃ ሊወሰድበት ኸሊፋው አልረሺድ ዘንድ ይቀርባል። ሰውየውም ኸሊፋውን ተስፋ ለማስቆረጥ በሚመስል አነጋገር "ብትገድለኝም አይቆጨኝም፣ ምክንያቱም አንድ ሺ የሚሆኑ ሐዲስ ያልሆኑ አባባሎችን፣ ሐዲስ በማስመሰል አሰራጭቻለሁ !" አለ። ኸሊፋውም "ለዚህ ብዙ አንጨነቅም እነ አቢ ኢስሐቅ አልፈዛሪን፣ እነ ዐብዱላህ ኢብኑ ሙባረክን...የመሰሉ ሙሐዲሶች አሉልን። እንክርዳዱን አበጥረው የሚለዩ።" በማለት መለሰለት። /አልዘሀቢይ፣ ተዝኪረቱ አልሑፋዝ፣ ቅጽ 1 ፣ ገጽ 273/ 🔘ይህ ክስተት በውስጡ ብዙ ቁምነገሮችን አዝሏል:- 1/ኢስላምን በመጠበቅ ረገድ የሙሐዲሶች አይተኬ ሚና፤ 2/በዘመኑ የነበሩ ኹለፋኦች ለኢስላም ዘብ ይቆሙ እንደነበረ፤ 3/አዕዳኡል ኢስላም ኢስላምን ለመበረዝ የሚችሉትን ከማድረግ ወደኋላ የማይሉ ቢሆንም፣ አላህ ግን በዑለሞች በኩል ዲኑን እንደሚጠብቅ...ዋናዎቹ ናቸው።
3791Loading...
21
1.25 ክርስቲያን እያሉ ተጋብተው ከዛ አስልምናን የተቀበሉ ሰዎች ኒካህ ከእስልምና ውጭ ባለ እምነት ውስጥ ያሉ ሰዎች ባሉበት እምነት መሰረት መስፈርቶቹን አሟልተው ትዳር እስካደረጉ ድረስ ትዳራቸው ትክክል ነው።በመሆኑም እነዚህ ሰዎች ወደ እስልምና በሚገቡ ግዜ ሁለቱም ከሰለሙ ኒክሀቸውን እንደ አዲስ ማደስ አይጠበቅባቸውም መጀመሪያ ባሰሩት ኒካህ በዛው ይቀጥላሉ። ምክንያቱም በመልእክተኛው ﷺ ዘመን ከተለያየ እምነት ያሉ ባልና ሚስቶች እስልምናን ሲቀበሉ መልእክተኛው ﷺ ኒካህቸውን እንዲያድሱ አላዘዟቸውም። በዛው ኒካህ ላይ ነው የቀጠሉት የሰለመው ባል ብቻ ከሆነ እና ሚስት ደግሞ አህለል ኪታብ ከሆነች አሁንም ኒካውን ማደስ አይጠበቅባቸውም በዛው መቀጠል ይችላሉ።ክርስቲያን ሴቶችን ስለማግባት ላይ የተብራራ ጽሁፍ አለ። የሰለመችው ሚስት ብቻ ከሆነችና ባል ግን እስልምናን ካልተቀበለ ከሱ ጋር አብራ ልትኖር አይፈቀድላትም። ነገር ግን ኢዳዋ እስከሚያበቃ ድረስ ሌላ ማግባት አትችልም። ኢዳ በምትቆጥርበት ወቅት ባል ወደ እስልምና ከገባ አብረው ይኖራሉ። እሱ እስልምናን ሳይቀበል ግን ኢዳዋ ካበቃ ሁለት አማራጭ አላት ከፈለገች ሌላ ባል ማግባት ትችላለች ምክንያቱም ኢዳዋ አብቅቷልና። ከፈለገች ደግሞ እስኪሰልም ድረስ በትግስት ትጠብቀውና ከሰለመ ወደሱ ተመልሳ አብረው ይኖራሉ። ለዚህ ማስረጃው የመልእክተኛው ልጅ የሆነችው ዘይነብ ቢንት ሙሀመድ እስልምናን ስትቀበል ባሏ አቡል አስ ቢን ረቢእ ወዲያው አልሰለመም ነበረ እሷ ከሰለመች ከአስራ ስምንት አመታት በኋላ ነው የሰለመው¹³⁶ ። እስልምናን በተቀበለ ግዜ ግን ወደሱ ተመልሳ አብረው ኖሩ ኒካሁን እንደ አዲስ አላደሱትም። መጀመሪያ ሙስሊም የነበረና ወደ ክህደትም የገባ ሰውን በተመለከ ያለው ፍርድ ተመሳሳይ ነው።ነገር ግን በዚህ ግዜ ለየት የሚያደርገው ሚስቱ ሙስሊም ከነበረችና ወደ ክርስትናም ቢሆን ከገባች ከሷ ጋር አብሮ አይፈቀደለትም https://t.me/Hassendawd
9441Loading...
22
Don't put a question mark, where Allah has put a full stop, he knows better.
3581Loading...
23
ዙበይር ኢብኑ ዐዋም ๏ መጀመሪያ ከሰለሙት ውስጥ አራተኛው ወይም አምስተኛው ነው ተብሏል በተለያዩ ዘገባዎች እንደተገለፀው ሲሰልም የ 8 አመት ልጅ ነበር ፣ የ12 አመት ልጅ ነበር እና የ16 አመት ልጅ ነበር ተብሏል። ๏ የረሱል (ﷺ) የአያት ልጅ ነው። ๏ በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ๏ በአላህ መንገድ መጀመሪያ ሰይፉን የሰላው ነው። ይህ የሆነበት ክስተት… ⇨ረሱል (ﷺ) ደዕዋውን በጀመሩበትና ስቃዩ በበረታበት ጊዜ ነበር። ረሱል (ﷺ) ተያዙ የሚል ወሬ ሲሰራጭ ሲሰማ ረሱልን ከተያዙበት ለማስለቀቅ ሰይፉን ሰላና ተነሳ በሰአቱ ገና የ12 አመት ልጅ ስለነበር ያየው ሰው ሁሉ ተገረም ተደንቆበት ነበር። ከዛም ረሱል (ﷺ) አዩትና " ምን ሆነህ ነው?" አሉት።እንደተያዙ ሰምቼ ነው አለ " እና ምን ልታደርግ ነበር?" አሉት ረሱል (ﷺ) የያዞትን ሰው በሰይፉ ልቀላው ነው የመጣሁት አለው ከዛም ረሱል (ﷺ) ለሱም ለሰይፉም ዱዓ አደረጉለት ‥ መጀመሪያ በአላህ መንገድ ሰይፉን የሰላ ሰሃባ ሆነ። ๏ ከሰሃቦች ውስጥ በጣም ጎበዝ ጀግና ፈረሰኛና ማራኪ ተጋዳይ ነበር። ๏ ስለ ሰይፉ ዐሊይ ኢብኑ አቡ ጣሊብ (ረ) እንዲህ ብሎ ነበር " ከረሱል (ﷺ) ፊት ጭንቅን ሲያስወግድ የነበረ ሰይፍ " ๏ መጀመሪያ ወደ ሀበሻ ከተሰደዱት ውስጥ ነበር። ๏ በድር ዘመቻ ላይ ዙበይር ቢጫ ጥምጣም ለብሶ ነበር መላኢኮችም በዙበይር ምልክት ነበር የወረዱት። ๏ እድሜው ወደ 64 ሲሆን ከበስራ ወደ መዲና እየተመለሰ እያለ ኢብኑ ጀርሙዝ በሚባል ሰው ሰላት ላይ ሆኖ ተገደለ ‥ ⇨ትክክለኛ ስሙ ዙበይር ኢብኑ ዐዋም ኢብኑ ኹወይሊድ ይባላል። አባቱ የምእመናን እናት የሆነችው የኸዲጃህ (ረ.ዐ) ወንድም ነው። እናቱ ደግሞ የረሱል (ﷺ) አያት ነች ሰፊያህ ቢንት አብዱልሙጠሊብ ትባላለች። ⇨ዙበይር የረሱል (ﷺ) ሐዋሪያ በመባል ይታወቃል። ምክኒያቱ ደግሞ… ๏ ረሱል (ﷺ) ከአይሁዶች ጋር ያደረጉት ስምምነት በኑ ቁረይዛዎች ስምምነቱን እንዳያፈርሱ ይሰጉ ነበርና ሰሃቦቹ ፊት በመቆም የነዛን ህዝብ ዜና የሚያመጣልኝ ማነው? አለ ዙበይር እኔ አለ አሁንም ጠየቁ ረሱል (ﷺ) ዙበይርም አሁንም እኔ አለ ለ3 ገዜ ሲጠይቁ 3ቱም ጊዜ ዙበይር እኔ አለ ከዛም ረሱል (ﷺ) እንዲህ አሉ " ሁሉም ነቢይ ሐዋሪያት አላቸው የኔ ሀዋሪይ ደግሞ ዙበይር ነው " ከዛ በኋላ የረሱል (ﷺ) ሐዋሪያ ተባለ። https://t.me/Hassendawd
1 1996Loading...
24
“ሶስት ጁምዓዎችን ያለ በቂ ምክንያት የተወ ከሙናፊቆች ተደርጎ ይመዘገባል።” ረሱል ﷺ
3873Loading...
25
ማስተማር ላይ እንበርታ ~ ዐብዱላህ ብኑል ሙባረክ ረሒመሁላህ "ከእድሜህ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረህ ብትባል ምን ነበር የምትሰራው?" ተብለው ቢጠየቁ "ሰዎችን አስተምር ነበር" ብለው መለሱ። [አልመድኸል፣ ሊልበይሀቂይ፡ 2/45]
4161Loading...
26
ቁርዓን ሂፍዝ የምትቀራ ተማሪ ሆይ የምታዳምጠዉ ቃሪእ የተጂወድ አህካሞችን በመጠበቁ የታወቀ ይሁን ትኩረትህ ድምጽ ላይ ብቻ አታድርግ ። አንዳንድ ብዙ ሰዉ የሚያዳምጣቸዉ ወጣት ቃሪዎች ሚድያ ላይ የሚለቋቸዉ ቲላዋዎች የጎላ ክፍተት አለባቸዉ ። ታድያ የእነ ማንን ላዳምጥ ? 1.الحصري 2.المنشاوي 3.عبد الله بصفر 4.علي الحذيفي 5.أيمن سويد ከእነዚህ አንዱን እንድታዳመጥ እኔ እምረጥልሃለዉ ከነዚህ ዉጪ ሙተቂን የሆነም አሉ አንዱም መርጠህ ብታዳምጥም መልካም ነዉ።
4989Loading...
27
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته የተከበራችሁ እህትና ወንድሞች እንኳን ወደ ዛድ ኦንላይን የቂርአት ማዕከል በሰላም መጣችሁ እያልን መመዝገቢያ ፎርም እንደሚከተለው ይቀርባል። 1, ስም ከነ አያት__ 2, አሁን ያለንበት ሀገር____ 3,ዋሳፕና ቴሌግራም ምትጠቀሙበት ስልክ ቁጥር____ 4,ፆታ____ 5,የቂርአት ደረጃ_ 6.መቅራት የሚፈልጉት_ ማሳሰቢያ:- 👉🏿መድረሳችን በአንድ አመት 4 ሴሚስተር የሚኖሩት ሲሆን ክፍያ የሚፈፀመው በየ ሴሜስተሩ ነው። 👉🏿በቁርጠኝነት መማር የምትፈልጉ ብቻ እንድመዘገቡ በትህትና እንጠይቃለን። 👉🏿ትምህርቱ የሚሰጠው በዙም አፕ እና በ ቴሌግራም ስለሆነ ከወዲሁ አፑን በማውረድ ለትምህር እንድትዘጋጁ እናሳስባለን። _ መመዝገቢያ ሊንክ👉🏿 https://forms.gle/Ve6Fcex92Nu5sbRQ8 ይህን ሊንክ በመጫን ከአሁኑ ሰዓት ጀምራችሁ መመዝገብትችላላችሁ።
6311Loading...
28
1.24 ኒካው ሲታሰር መህር ካልተሰጣት ከዛም ሳይስማሙ ቀርተው ከፈታት መህሯ ምን ያክል ነው የሚሆነው? በሰአቱ የመህሩ መጠን ተወስኖ ከነበረ በሰአቱ መህሩን ወስኖላት ነገር ግን ሳይገናኛት ወይም ደግሞ ከሷ ጋር ለብቻቸው ሳያገሉ በፊት ከፈታት የመህሯን ግማሽ የመስጥት ግዴታ አለበት። አላህ እንዲህ ይላል { وَإِن طَلَّقْتُمُوهُنَّ مِن قَبْلِ أَن تَمَسُّوهُنَّ وَقَدْ فَرَضْتُمْ لَهُنَّ فَرِيضَةً فَنِصْفُ مَا فَرَضْتُمْ إِلَّآ أَن يَعْفُونَ أَوْ يَعْفُوَا الَّذِى بِيَدِهِۦ عُقْدَةُ النِّكَاحِ ۚ} {{ለእነርሱም መወሰንን በእርግጥ የወሰናችሁላቸው ስትኾኑ ሳትነኳቸው በፊት ብተፈቷቸው ካልማሩዋችሁ ወይም ያ የጋብቻው ውል በእጁ የኾነው (ባልየው) ካልማረ በስተቀር የወሰናችሁት ግማሹ አላቸው፡፡}}¹³¹ የፈታት ከታገናኛት በኋላ ወይም ደግሞ ለብቻቸው ካገለሉ በኋላ ከሆነ ሙሉ መህሯን የመስጠት ግዴታ አለበት።በዚህ ላይ የሰሀቦች ጥቅል ስምምነት እንዳለበትም ተወርቷል። በሰአቱ የመህሩ መጠል ያልተወሰነ ከነበረ ) በሰአቱ የመህሩን መጠኑን ያልወሰነላት ከነበረና ከዛህ በኋላ ግን ሳይገናኛት ወይም ደግሞ ከሷ ጋር ለብቻቸው ሳያገሉ በፊት ከፈታት እሷን በሚችለው ልክ ያጠቃቅማታል። ያ ማለት አቅሙ በሚፈቅድለት መጠን የሆነ ነገር ያደርግላታል መህር ግን አይኖርበትም። አላህ ﷻ እንዲህ ይላል፦ { لَّا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ إِن طَلَّقْتُمُ النِّسَآءَ مَا لَمْ تَمَسُّوهُنَّ أَوْ تَفْرِضُوا لَهُنَّ فَرِيضَةً ۚ وَمَتِّعُوهُنَّ عَلَى الْمُوسِعِ قَدَرُهُۥ وَعَلَى الْمُقْتِرِ قَدَرُهُۥ مَتٰعًۢا بِالْمَعْرُوفِ ۖ حَقًّا عَلَى الْمُحْسِنِينَ } {{ሴቶችን ሳትነኳቸው (ሳትገናኙ)፤ ወይም ለነሱ መህርን ሳትወስኑላቸው ብትፈቷቸው በናንተ ላይ ኃጢኣት የለባችሁም፡፡ (ዳረጎት በመስጠት መፍታት ትችላላችሁ፡፡) ጥቀሟቸውም፡፡ በሀብታም ላይ ችሎታው በድኀም ላይ ችሎታው(አቅሙ የሚፈቅደውን መስጠት) አለበት፡፡ መልካም የኾነን መጥቀም በበጎ ሠሪዎች ላይ የተረጋገጠን፤ (ጥቀሟቸው)፡፡}} 2) በሰአቱ የመህሩን መጠኑን ያልወሰነላት ከነበረና ከዛህም ከተገናኛት በኋላ ወይም ለብቻቸው ካገለሉ በኋላ ከፈታት እሷን የመሰሉ ሌሎች ሴቶች ሚሰጣቸውን መህር ያክል ለሷ መስጠት አለበት። ይህንንም ራሳቸው ተስማምተው መጠኑን ከወሰኑ ቃዲ (ዳኛ) ጋር መሄድ አይጠበቅባቸውም። ካልተስማሙ ግን ቃዲ (ዳኛ) ጋር ሄደው እሱ ይፈርድላቸዋል። ኒካህ አስሮላት ሳይገናኛት በፊት ባል ከሞተ መህር አላት? ከተጋቡ በኋላ ሳይገኛት በፊት ባል ከሞተ ለሚስት ውርስ እንዳላት ሁላ ሙሉ መህርም አላት። ስለዚህ ውርሱ ከመከፍፈሉ በፊት መህሯን ትወስዳለች ከዛህም ከውርሱ የሚደርሳትን ትወስዳለች።ውርስ ያላት በመሆኑ ላይ ምንም ኺላፍ የሌለበት ሲሆን መህሩን በተመለከተ ድግሞ እንደሚሰጣት ከመልእክተኛውﷺ ተላለፏል¹³³ ኢማሙ ሻፍእይም ሀዲሱ ትክክለኝነቱ ከተረጋገጠ እኔም በዚሁ አቋም ነው ምለው ብለዋል። ሀዲሱ ደግሞ ትክክለኝነቱ ተረጋግጧል ስለዚህ ይህ የኢማሙ ሻፍእይም መዝሀብ ነው ማለት እንችላለን። https://t.me/Hassendawd)
9956Loading...
29
1.23 መህር መህር የሚባለው ኒካህ በማሰሩ የተነሳ ባል ለሚስቱ የሚሰጣት ግዴታ የሆነ ገንዘብ ነው።በመሆኑም ይህ የሚስት ሀቅ ነው ባል አልሰጥም ማለት አይችልም።ያለ መህር ነው ምንጋባው ማለትም አይችሉም። መህርን ለትንሹም ለትልቁም ገደብ የለውም፦አላህ እንዲህ ይላል { وَأُحِلَّ لَكُم مَّا وَرَآءَ ذٰلِكُمْ أَن تَبْتَغُوا بِأَمْوٰلِكُم مُّحْصِنِينَ غَيْرَ مُسٰفِحِينَ } {{ከዚሃችሁም (ከተከለከሉት) ወዲያ ጥብቆች ኾናችሁ ዝሙተኞች ሳትኾኑ በገንዘቦቻችሁ ልትፈልጉ ለእናንተ ተፈቀደ፡፡ }} በዚህ የቁርአን አንቀጽ ላይ እንደምንመለከተው የገንዘቡ መጠን ገደብ አልተደረገለትም።በመሆኑም ኒካህ ሲያስሩ ሚስት መህሬ ይህን ያክል ነው ብላ መስፈርት ካስቀመጠችና ባልም በዛ ላይ ከተስማማ ያን የተስማማበትን የመስጣት ግዴታ አለበት በራሷ ፍቃድ ይቅር እስካላለችው ድረስ። በራሷ ፍቃድ ይቅር ካለችው ግን ትችላለች።አላህ እንዲህ ይላል { وَءَاتُوا النِّسَآءَ صَدُقٰتِهِنَّ نِحْلَةً ۚ فَإِن طِبْنَ لَكُمْ عَن ሲኾን ብሉት}} መህር ሊሆን የሚችለው ምንድ ነው? ወደ ገንዘብነት መቀየር የሚችል ነገር በሙሉ መህር ሆኖ ያገለግላል።ለምሳሌ ብር፣ወርቅ፣ልብስ፣ጫማ፣ሽቶ፣ኪታብ እና ጅልባብ የመሳሰሉት ባጠቃላይ ወደ ገንዘብነት ሊቀየሩ የሚችሉ (ሊሸጥ ሊለወጥ የሚችል) ነገራቶች በሙሉ መህር ሊሆኑ ይችላሉ።ከዚህም በተጨማሪ ለሷ አገልግሎት መስጠትን እንደመህር ሊያደርግላት ይችላል ለምሳሌ ለሷ ከብቶች ቢኖሯት የሷን ከብቶች ለሁለት አመት ያክል ለመጠበቅ መህር አድርገው ቢስማሙ ይችላሉ።ልክ ነብዩላሂ ሙሳ መድየን በሄደ ግዜ ልጅቷን ለማግባት ስምንት አመትን በመኻደም እንደተስማማው ማለት ነው። በርግጥ የኻደመው አባቱን ቢሆንም እሷ ትሰራው የነበረ ስራን በመስራት ስለኻደመው ልክ ለሷ እንዳገለገላት እንቆረዋለን ምክንያቱም እሱሳይኖር በፊት ያን ስራ ትሰራ የነበረው እሷ ናትና። በዚህ መሰረት መህሬ ቁርአን ወይም ኪታብ እንዲያስቀራኝ ነው ብትል ይቻላል።ምክንያቱም ቁርአን ለሚያስቀራ ሰው ገንዘብ ሊከፈለው ይችላልና ነው።ከዚህም በተጨማሪ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል {{فعلمها ما معك من القر آن }} {{አንተ ዘንድ ባለው ቁርአን ድሬልሀለው}}¹²⁷ وفي رواية {{زوجتكھا بما معك من القرآن }} በሌላ ዘገባ ደግሞ {{አንተ ዘንድ ያለውን ቁርአን አስተምራት}} 📖 መህሩን ቁርአን እንዲያስቀራት በሚል ተስማምተው ነገር ግን በጣም ደጋግሞ ደጋግሞ ቢያስቀራትም ሊገባት ካልቻለ መህሯ ውድቅ አይሆንም ነገር ወደ ገንዘብ ይቀየራል ያም ወደ ገንዘብ ሲቀየር አንድ ሰው ቁርአን እንዲያስቀራ ቢቀጠር ሊከፈለው የሚችለው ገንዘብ ተሰልቶ በመህር መልኩ ለሷ ይሰጣታል ። አስካሪ መጠጥና እሱን የመሳሰሉ መሸጣቸው የማይፈቀዱ ነገራቶችን መህር ማድረግ አይቻልም። መህር ላይ የሚወደዱ ነገራት አንደኛ፦ መህርን ቀለል ማድረግ፦ ማስረጃው 1) መልእክተኛው ﷺ ይሰጡት የነበረው መህር ቀለል ያለ ነበረ። ልጆቻቸውንም ሲድሩ እንዲሁ መህራቸው ቀለል ያለ ነበር 2) መህር በቀለለ ቁጥር ሰዎች ኒካህ ለማድረግ ይቀላቸዋል ይህ ደግሞ የነብዩ ኡመት እንዲበዛ አስተዋጽኦ ያደርጋል 3) መህር በከበደ ቁጥር ሰዎች ከኒካህ ይርቃሉ ዚና ላይ እንዲወድቁም መንስኤ ይሆንባቸዋል 4) እሷን ለማግባት ብዙ መህር የከፈለባት ከሆነ ባሰባት ቁጥር ያወጣባት ወጪ ትዝ እያለው ውዴታውን ሊቀንስበት ይችላል 5) መህሩ ትንሽ ከሆነ አለመግባባቶች ከተከሰቱና ሊቀረፉ ካልቻሉ በቀላሉ ይፈታታል አያሰቃያትም መህሩ ብዙ ከሆነ ግን ያወጣው ወጪ ስለሚያሳዝነው በቀላሉ ላይፈታትና ከራሷ በኩል ፍቺ ጥያቄ እንዲመጣ ብሎ ሊያሰቃያት ይችላል። 6) ሚስት ፍቺን ብትፈልግ መህሩ ቀላል ከሆነ በቀላሉ መህሩን መልሳለት ልትፈታ ትችላለች። ብዙ ከሆነ ግን ለመመለስ ልትቸገር ትችላለች 📖 መህሯ ትንሽ የሆነች ሴት ትልቅ በረካ አላት የሚል ሀዲስ ቢኖርም ከሰነድ አንጻር ግን ደካማ ነው። ሁለተኛ ፦ የመህሩ መጠን ስንት እንደሆነ ኒካው በሚታሰር ሰአት መነጋገሩ የተወደደ ነው፦ ለዚህ ማስረጃው ደግሞ 1) መልእክተኛው ﷺለሰሀቦች ኒካህ ሲያስሩ እዛው በቦታው የመህሩን መጠን መሰየማቸው ተገኝቷል። 2) ኒካው በሚታሰር ሰአት መህሩ መጠቀሱ በኋላ ላይ ከሚፈጠር ጭቅጭቅ ይጠብቃቸዋል 📖 ኒካህ በሚታሰር ግዜ የመህሩ መጠን ባይጠቀስም ግን ኒካሁን አያበላሸውም ሶስተኛው፧ መህሩን ወዲያው እዛው መከፈል ይወደድለታል፦ለዚህ ማስረጃው 1) ከላይ ባሳለፍነው ሀዲስ ላይ እንዳየነው በቁርአን የዳሩት ሰሀባ የብረት ቀለበትም ቢሆን ፈልግ ብለውት ሲያጣ በቃ ሌላ ቀን ስታገኝ ትሰጣታለህ አላሉትም ይልቁንስ ወደ ሌላ ወደ ሚችለው ተሸጋገሩ። እናም መህርን ማዘግየት የተጠላ ነው ወደ ሚለው አቋም ሸይኹል ኢስላምም ይዘነበላል 2) እዛው ማይሰጣት ከሆነ እዳ ይሆንበታል እዳ ውስጥ መግባት ደግሞ ቀላል ነገር አደለም 📖 ነገር ግን መህሩን ቢያቆየው ወይም ግማሹን አሁን ሰጥቷት ሌላውን ሌላ ግዜ ቢሰጣት ችግር የለውም። https://t.me/Hassendawd
1 90822Loading...
30
1.22 ሚስት ወይም ባል ላይ ሚገኙ አይቦች (ጉድለቶች) በተመለከተ ኒካህ ከሚታሰርበት አላማዎች ውስጥ አንዱን የሚያሳጣ ጉድልት (አይብ) ከተገኘበት ወይም ከተገኘባት ኒካሁን ማፋረስ ትችላለች እሱም እሷ ላይ ካገኘ ማፍረስ ይችላል። ከነዚህ ጉድለቶች እንደምሳሌ ወንድ ልጅ ላይ ሊገኙ የሚችሉ ጉድለቶች 1) አፈረተገላው (ብልቱ) ከተቆረጥ ወይም ግንኙነት ሊያደርግበት ማይችልበት ያክል ብቻ ከሆነ የቀረው፦ የትዳር አንዱ አላማው ስሜቷን ሀላል በሆነ መልኩ ማርካት ስለሆን በንደዚህ ግዜ ኒካውን ማፋረስ ትችላለች። 2) የዘር ፍሬ ማመንጫው (ከብልቱ ጎን ያሉ ፍሬዎች) መቆረጥ ፦ ይህም ስሜቱን ያዳከምበታል ወይ ደግሞ ከነጭራሹ ስሜት እንዳይኖረው ያደርጋል 3) ከነጭራሹ ግንኙነት ማድረግ የማይችል ከሆነ ፦ ይህ አንዳንዴ በተፈጥሮ የሚኖር ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ ሲህር ተሰርቶበት መገናኘት ሊያቅተው ይችላል በዚህን ግዜ ለሷ ኒካውን የማፍረስ መብት አላት። ከሌላ ሴት መገናኘት እየቻለ ራሱ ከሷ ጋር መገናኘት ካልቻለ ኒካውን ማፍረስ ትችላለች ሴት ልጅ ላይ ሊገኙ የሚችሉ ጉድለቶች 1) የብልቷ መጣበቅ ወይም ደግሞ የወንዱን ብልት የማያስገባ መሆኑና በቀላል ህክምና ሊወገድ ሚችል አለመሆኑ ሴትም ትሁን ወንድ ላይ ሊገኙ ሚችሉ ጉድለቶች 1) የአእምሮ በሽታ ካለበት ወይም ካለባት 2) ሽንት ወይም ሰገራ ማይቋረጥለት ወይም ማይቋረጥላት ከሆነና በአጭር ግዜ ህክምና ሊድን ሚችል ካልሆነ 3) የለምጥ በሽታ 4) የቁምጥና በሽታ እነዚህ እንደምሳሌ እንጂ ጉድለቶች ብዙ ናቸው120 ። እንደአጠቃላይ እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ በኒካህ ከሚገኘው ጥቅም ውስጥ የተወሰነውን ሊያስቀርበት የሚችሉ ጉድለቶችን ያገኘ ሰው ኒካውን የማፍረስ መብት አለው።ይህ ኢብኑል ቀይም የመረጠው አቋም ነው። በመሆኑም ወንዱ ላይ ከሆነ ይህ ጉድለት የተገኘውና ሳይገናኛት¹²² በፊት ከሆነ ኒካውን ያፈረሰችው የመህሩን ግማሽ ትወስዳለች።ምክንያቱም ለኒካው መፍረስ ሰበብ የሆነው እሱ ነው ጉድለት ባታገኝበት ኖሮ አታፈርሰውም ነበርና ነው። ለኒካው መፍረስ ሰበቡ ባል ከሆነ ደግሞ ለሷ ግማሽ መህር ይገባታል። አላህ እንዲህ ብሏል { وَإِن طَلَّقْتُمُوهُنَّ مِن قَبْلِ أَن تَمَسُّوهُنَّ وَقَدْ فَرَضْتُمْ لَهُنَّ فَرِيضَةً فَنِصْفُ مَا فَرَضْتُمْ إِلَّآ أَن يَعْفُونَ أَوْ يَعْفُوَا الَّذِى بِيَدِهِۦ عُقْدَةُ النِّكَاحِ } {{ለእነርሱም መወሰንን በእርግጥ የወሰናችሁላቸው ስትኾኑ ሳትነኳቸው በፊት ብተፈቷቸው ካልማሩዋችሁ ወይም ያ የጋብቻው ውል በእጁ የኾነው (ባልየው) ካልማረ በስተቀር የወሰናችሁት ግማሹ }}¹²³ ከተገናኛት በኋላ ከሆነ ግን ኒካውን ያፈረሰችው ሙሉ መህሩን ትወስዳለች።ከላይ ናሳለፍነው አንቀጽ ላይ ሳትነኩዋቸው በፊት ብትፈቷቸው ብሎ ግማሽ መህር ማስቀመጡ ከተነኩ (ከተገናኙዋቸው) በኋላ ከሆነ ሙሉ መህር መሆኑን ያስይዛል። ከፈለገች ደግሞ ከነ ጉድለቱም አብራው መኖር ትችላለች የሷ ምርጫ ነው። ሴቷ ላይ ከሆነ ጉድለቱ የተገኘው ሳይገናኛት በፊት ኒካውን ካፈረሰው ምንም መህር አይኖራትም።ከተገናኛት በኋላ ከሆነ ግን ያፋረሰው ሙሉ መህሯን ይሰጣታል ።ከፈለገም እስከነ ጉድለቷ አብሯት መኖር ይችላል።ነገር ግን ጉድለቷን ሳያቅ እስከሆነ ድረስ ያገባት ያታለለው አካል ካለ ይህን ኪሳራ ይከፍልለታል ያ ማለት፦ ◦ የሷ ወልይ በሷ ላይ ይህ ጉድለት እንዳለባት እያወቀ ከሆነ ለሱ የዳረለት ባልን ያታለለው እሱ ነውና ባል ለመህር ያወጣውን ኪሳራ ወልዩዋ ይከፍላል። ◦ ወልዩዋ ያለባትን ጉድለት የማያቅ ከነበረና እሷ ግን ታቅ ከነበረ ኪሳራውን ምትከፍለው እሷ ናት መህሩን ትመልስለታለች ማለት ነው ምክንያቱም ያታለለችው እሷ ናትና ◦ ወልዩዋም ይሁን እሷ ይህ ጉድለት በሷ ላይ እንዳለ የማያቁ ከነበረ ¹²⁴ ማንም ያታለለው ስለሌለ ኪሳራውን የሚከፍለው አይኖርም ይህ ጉድለት የተከሰተው ከተጋቡ በኋላም ቢሆን እንኳን ኒካውን ማፋረስ ይችላሉ።ለምሳሌ ከባሏ ጋር አብራ እየኖረች በመሀል አእምሮውን ቢታመምና ሊድን ማይችል ከሆነ እሷ ኒካውን የማፋረስ መብት አላት መቼም ከእብድ ጋር ኑሪ ተብላ ያለ ምርጫዋ አትገደድም። ሸይኩል ኢስላም ኢብን ተይሚያ እንደሚገልጸው ኒካውን በማፍረስ ላይ ሁለቱ ከተስማሙ ቃዲ(ዳኛ) ጋር መሄድ አይጠበቅባቸውም ካልተስማሙና ከተጨቃጨቁ ግን ቃዲ ጋር ሄደው እሱ ያፈርስላቸዋል።ጉድለቱ እንዳለበት አውቃ ከነጉድለቱ አብሬው እኖራለሁ ብላ አንዴ ከተስማማች ከዛህ በኋላ ኒካውን ማፍረስ አትችልም። https://t.me/Hassendawd
1 1058Loading...
31
ጠልሃህ ኢብኑ ዑበይዲላህ ๏ መጀመሪያ ከሰለሙት ውስጥ ነው 3ተኛ ነበር የሚሉ ዘገባዎች አሉ። ๏ በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ๏ በጣም ለጋሽና ቸር የሆነ ሰሃቢይ ነበር ๏ እድሜው ከ60 በላይ ከሆነ በኋላ መርዋን ኢብኑል ሀከም የሚባል ሰው በቀስት ገደለው። . ⇨ ትክክለኛ ስሙ ጠልሃህ ኢብኑ ዑበይዲላህ ኢብኑ ዑስማን ይባላል። ብዙ ስያሜዎች አሉት ከነዛ ውስጥ  ๏ በህይወት ያለው ሸሂድ ይባላል ምክኒያቱ ደግሞ እንደሚከተለው ይሆናል ⇨ኡሁድ ዘመቻ ላይ ሙስሊሞች ሲሸነፉ ከረሱል (ﷺ) ጋር 11 ሰው እንጂ አልቀሩም ነበር ከነዚህም መካከል አንዱ ጠልሃህ (ረ) ነበር የዛን ረሱል (ﷺ) እነዚህን 11ዱን ወደ ተራራ ይዟቸው እየወጡ ነበር የተወሰኑ ሙሽሪኮችም ለመግደል እየተከተሏቸው ነበር። ከዛም ረሱል (ﷺ) " ማነው እነዚህን የሚመልስልን ከኔም ጋር በጀነት ውስጥ ጓደኛዬ የሚሆን " ብለው ጠየቁ ጠልሁ ከሁሉም በፊት እኔ አለ የዚህን ጊዜ ረሱል (ﷺ) አይ ቆይ አንተ ቦታህን አሉት ከአንሳሮች አንዱ እኔ ያ ረሱለላህ አለ እሺ ብለው ፈቀዱለት ያሰው እስኪገደል ድረስ ተፋለማቸው አሁን ወደ ተራራው እየወጡ ሙሽሪኮች መከተላቸውን አላቆሙም " አንድ ሰው ለነዚህ " አሉም ረሱል (ﷺ) አሁንም ጠልሃህ (ረ) ከሁሉም በፊት እኔ አለ አይ ቆይ አንተ ቦታህን አሉት ከአንሳሮች አንዱ እኔ ያ ረሱለላህ አለ ተፈቀደለት ከዛ እስኪገደል ድረስ ተፋለማቸው እያሉ እያሉ ከረሱል (ﷺ) ጋር ጠልሃህ ብቻ ቀረ። ከዛም እንዲጋደል ፈቀደለት ለጠልሃህ እየተፋለማቸው ከረሱል (ﷺ) እየተከላከለ ወደ ተራራውም ይዟቸው እየወጣ ሙሽሪኮችን እስኪመልሳቸው ድረስ ተፋለማቸው‥ ⇨አቡበክር አሲዲቅ (ረ) እንዲህ ይላሉ እኔና ዑበይደህ የዛን ቀን ከረሱል (ﷺ) ርቀን ነበርና መጥተን ልንወስዳቸው ስንል እኔን ተውኝና ሂዱ ለጠልሃህ አሉን። ጠልሃህ ጋር ስንሄድ ደሙ እየፈሰሰ ነው ከ70 በላይ የሰይፍ ወይም የጦር ወይ ደግሞ የቀስት ምት ነበረበት። ነዳፉም ተቆርጦ እራሱን ስቶ ጉድጓድ ውስጥወድቆ ነበር ‥ ከዛ አንዲት አንቀፅ ወረደች ረሱልም ሰሃቦቹ ፊት ቀሯት " ከአማኞቹ በእርሱ ላይ ለአላህ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አልሉ ከነርሱም ስለቱን የፈጸመ (ለሃይማኖቱ የተገደለ) አልለ ከነርሱም ገና የሚጠባበቅ አልለ (የገቡበትን ቃል) መለወጥንም አልለወጡም ፡፡" [አህዛብ 23] ከቀሯትም በኋላም ረሱል (ﷺ) ጣታቸውን ወደ ጠልሃህ በማመላከት እንዲህም አሉ " ሸሂድ ሆኖ ምድር ላይ የሚሄድን ሰው ማየት የፈለገ ጠልሃህን ይመልከት " ๏ ጠልሀተል ኸይርና ጠልሀተል ጁድም ይባል ነበር። ምክኒያቱ ደግሞ በጣም ሀብታም ነጋዴ ነበር።አንድ ጊዜ በጣም ብዙ ብር አገኘ 700 ሺህ ዲርሃም ነበር የዛን ቀን ለሊት በጣም አዝኖ ነበር ባለቤቱ ኡሙ ኩልሱም አቡበክር ገባችበትና አባ ሙሀምድ ሆይ ምን ሆነህ ነው? አለችው። አንድ ሰው በጌታው ምን አስቦ ነው ይህ ብር ቤቱ እያለ የሚተኛው? አላት ከሱ ምን ይጨንቅሃል ስታነጋ አከፋፍለው አለችው። አላህ ይዘንልሽ የተወፈቅሽና የተወፈቀ ልጅ ነሽ አላት። ከዛ ሲነጋ ለአንሳሮች እና ለሙሃጂሮች አከፋፈለው። ጠልሀተል ኸይር እና ጁድም ተባለ። ⇨የእናቱ ስም ሰዕበህ ቢንት ሀድረሚይ ኢብኑ ዐብደህ ትባላለች https://t.me/Hassendawd
1 0348Loading...
32
⭐️قـال أبو حاتم البستي رحمه الله : ‏  " من اشتغل بعيوب الناس عن عيوب نفسه : عمي قلبه ، وتعب بدنه ؛ وتعذر عليه ترك عيوب نفسه " . 📚 روضة العقلاء ١٢٥】
4032Loading...
33
መጥፎ ተግባር ወዳጅ ያሳጣል! ረሱል (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إنّ شرَّ الناسِ منزلةً عند اللهِ يومَ القيامةِ من تركه الناسُ اتِّقاءَ فُحشِه﴾ “ከሰዎች መጥፎ ሆኖ በትንሳዔ ዕለት አላህ ዘንድ የሚመጣው፤ ከመጥፎ ስራው ለመጠንቀቅ ሲሉ ሰዎች የተዉት ሰው ነው።” 📚 ቡኻሪ (6032) ሙስሊም (2591) ዘግበውታል
4674Loading...
34
4,አሊይ ኢብኑ አቡ ጧሊብ ๏ ከልጆች መጀመሪያ በረሱል (ﷺ) ያመነና የተቀበለው ነው 10 አመት ነበር እድሜው ሲሰልም። ๏ የረሱል (ﷺ) አጎት ልጅና አማችም ነው። ๏ ከዑስማን (ረ.ዐ) በኋላ 4ተኛው ኸሊፋ ነው። ๏ በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ๏ በኢስላም የመጀመሪያው ፊዳእ (መስዋእት) ነው። ๏ ወህይን ወይም ቁርአንን ከሚፅፉ ሰሃቦች አንዱ ነበር። ๏ የረሱል (ﷺ) አምባሳደርም ነበር። ๏ ልክ ዑስማን (ረ.ዐ) እንደተገደለ ኺላፋውን ተረክቦ። 6 አመት ከ3 ወራት ከመራ በኋላ ፈጅር ሰላት እያሰገደ አብዱረህማን ኢብኑ ሙልጂም በሚባል የኸዋሪጆች ራስ የሆነው ከኋላው መጣና በተመረዘ ሰይፍ ራሱ ላይ መታው ከዛ ፉዝቱ ወረቡል ከዕባህ (በከዕባው ጌታ ይሁንብኝ አሸነፍኩ) እያለ ከዚህ አለም ተለየ። ๏ በሌላ ዘገባም ወደ መስጂድ እየሄደ ነበር ይባላል ልክ ከተመታ በኋላ ወደ ቤቱ ተወሰደ የመታኝን ከምግቤ አብሉት አጠጡትም ከሞትኩም እንደገደለኝ ግደሉት ከተርፍኩ ደግሞ ውሳኔዬ እወስድበታለሁ አለ ከዛ ብዙ ሀኪሞች መጡ ሊያተርፉት አልቻሉም ከ3 ቀን በኋላ ሞተ .. ⇨ትክክለኛ ስሙ ዐሊይ ኢብኑ አቡጣሊብ ኢብኑ አብዱልሙጠሊብ ነው ብዙ ስያሜዎች አሉት ከነዛ ውስጥ ๏ አቡ ቱራብ ይባላል የተባለበት ምክኒያት ከእለታት አንድ ቀን መሬት ካይ ተኝቶ ረሱል (ﷺ) መጡበትና እንዲህም አሉት “ከስሞችህ የሚገቡህ አቡ ቱራብ ነው አንተ አቡ ቱራብ ነህ” አሉት። ๏ ሀይደረህም ይባላል ምክኒያቱ ደግሞ ሲወለድ እናትየው ሀይደረህ ብላ መሰየም ፈልጋ ነበር ነገር ግን አባትየው እንቢ ብሎ ዐሊይ አለው ሀይደረህ ማለት ከአንበሳ ስሞች አንዱ ነው። ኸይበር ዘመቻ ላይ ከየሁዶች መሪ ጋር ሲፋለም እንዲህ ብሎ ነበር። ๏ አልከራር ተብሎም ይታወቅ ነበር።ስያሜውን ረሱል (ﷺ) ነበር የሰየሙት እዛው ኸይበር ዘመቻ ላይ ሙስሊሞች በተደጋጋሚ መክፈት ያቃታቸውን ምሽግ ረሱል (ﷺ) ዐሊይ (ረ.ዐ) እንዲከፍተው ባንዲራውን ሰጠው ሲሰጠውም እንዲህ ብሎ ነበር የሰጠው “ባንዲራውን አላህንና መልእክተኛውን ለሚወድ አላህና መልእክተኛውም ለሚወዱት ሰው እሰጣለሁ ወደፊት የሚሄድ እንጂ የሚሸሽ አይደለም " ከራር ማለት ወደ ኋላ የማይል የማይሸሽ ማለት ነው ... ⇨የእናቱ ስም ፋጢማህ ቢንቱ አሰድ አልሃሺሚየህ ትባላለች.... ☞ እስካሁን ያየናቸው 4ቱ ሰሃቦችና ከዋክብቶች አቡበክር አሲዲቅ ፣ ዑመር አልፋሩቅ ፣ ዑስማን ኢብኑ ዐፋን እና ዐሊይ ኢብኑ አቡ ጣሊብ (ረ.ዐ) 4ቱ ኹላፋኡ ራሺዲን በመባል ይታወቃሉ። https://t.me/Hassendawd
9236Loading...
35
"If Allah can take away something you never imagined losing, then surely Allah can grant you something you never imagined gaining."
4180Loading...
36
1.21 ኒካህ ሲታሰር መስፈርቶችን ማስቀመጥ ሴት ልጅ በምትዳር ግዜ የተለያዩ መስፈርቶችን ማስቀመጥ ትችላለች ከነዚህ መስፈርቶች መሀከል እንደምሳሌ ▪️ ሌላ ሚስት እንዳያገባ መስፈርት ማድረግ ትችላለች። ▪️ ከቤቷ ወይም ከሀገሯ እንዳያወጣትና እዛው በቤቷ ወይም በሀገሯ እንዲያኖራት መስፈርት ማድረግ ትችላለች ▪️ መንገድ ይዟት እንዳይሄድም መስፈርት ማድረግ ትችላለች እነዚህን የመሳሰሉ መስፈርቶችን ማስቀመጥ ትችላለች 📖 ባል ሲጋቡ የተስማሙባቸውን መስፈርቶች የሟሟላት ግዴታ አለበት።እነዚህን መስፈርቶች ካጓደለ (ካላሟላ) ሚስት ትዳሩን የማፋረስ ስልጣን አላት።ከፈለገችም ደግሞ በዛው ልትቀጥልበት ትችላለች ኒካውን ለማፍረስ ዳኛ ጋር መሄድም አይጠበቅባትም ወንድ ልጅም ቢሆን ኒካህ ሲያስር የተለያዩ መስፈርቶችን ማስቀመጥ ይችላል እንደ ምሳሌ ▪️ በአዳር ከሌላኛዋ ሚስቱ ያነሰ ቀንን እንደሚሰጣት ከተስማሙ ይህን መስፈርት ማስቀመጥ ይችላል።ለምሳሌ አንደኛዋ ሚስቴ ጋር ሁለት ቀን እያደርኩ አንቺ ጋር አንድ ቀን አድራለው በሚለው ከተስማሙ ይችላሉ።ልክ ሰውዳ የሷን ቀን ለአኢሻ እንደሰጠችው ▪️ ወይም ልጃገረድ መሆኗን መስፈርት ካደረገ ይችላል።ሆና ካልተገኘች ማፋረስ ይችላል በሷ ላይ ሌላን እንዳያገባ መስፈርት ማድረግ ኒካህ በሚታሰር ግዜ ሚስት ባሏ ከሷ ውጪ ሌላ እንዳያገባ መስፈርትን ማስቀምጥ ትችላለች።ባል ፍቃደኛ ሆኖ እስከገባበት ድረስ ይህንን ማክበር ይጠበቅበታል ካላከበረና ሌላ ሚስት ከደረበባት ለሚስት ኒካኋን የማፍርስ ስልጣን አላት ሀቆቿንም አትከለከልም። ኢብን ቁዳማ¹¹³ ሙግኒ ላይ እንደጠቀሰው ይህ አቋም ከኡመር፡ ከሰአድ ቢን አቢ ወቃስና አምር ቢን አስ ተወርቷል ከፊል ኡለሞች ይህ አላህ የፈቀደለትን የባልን ሀቅ መከልከል ነው ብለው ስለዚህ አይቻልም ያሉ ቢሆንም ነገር ግን ይህ ባል ራሱ ተስማምቶ ያወደቀዉ ሀቁ ስለሆን ሚከለክል ነገር አይኖረውም። ኢማም ኢብን ቁዳማ (رحمه ﷲ ) እንዲህ ይላል “ከቤቷ ወይም ከሀገሯ ላያወጣት ወይም መንገድ ይዟት ላይሔድ አልያ ደግሞ ሌላ ላያገባባት መስፈር ካደረገላይ መስገርቱን መሙላት ይገባዋል።” ሸይኽ ሳሊህል ፈውዛን (حفظه ﷲ) እንዲህ ይላሉ “ኒካህ ላይ ካሉ ትክክለኛ መስፈርቶች መሀከል ሌላ እንዳያገባ መስፈረት ካደረገችና ይህንን ካልፈጸመ ለሷ ኒካውን ማፋረስ ትችላለች” አላመት ኢብን ባዝም ባሏ ሌላ እንዳያገባ መስፈርት ስለማድረግ ተጠይቀው “ምንም ችግር የለውም......” ብለው መልሰዋል የማይቻሉ መስፈርቶች ▪️መህር እንዳይኖራት ብሎ መስፈርት ማድረግ አይቻልም።ምክንያቱም ሴትን በገንዘባችን እንድናገባቸው ነው የታዘዝነው { وَأُحِلَّ لَكُم مَّا وَرَآءَ ذٰلِكُمْ أَن تَبْتَغُوا بِأَمْوٰلِكُم مُّحْصِنِينَ غَيْرَ مُسٰفِحِينَ } {{ ከዚሃችሁም (ከተከለከሉት) ወዲያ ጥብቆች ኾናችሁ ዝሙተኞች ሳትኾኑ በገንዘቦቻችሁ ልትፈልጉ ለእናንተ ተፈቀደ}} ▪️ ነፈቃ ላይሰጣት መስፈርት ማድረግም አይችልም ምክንያቱ ይህ ሂካህ በመታሰሩ ምክንያት የሚመጣ እና ግዴታ የሚሆንበትን ነገርን ስለሚጻረር ነው። መልእክተኛው እንዲህ ብለዋል {ولهن علیكم رزقھن وكسوتھن بالمعروف} {{እነሱን ተገቢ በሆነው መልኩ ማብላትና ማልበስ በናንተ ላይ አለባችሁ}}¹¹⁸ ነፈቃን ውድቅ ካደረገ ሀዲሱን ተጻሯል ስለዚህ ተቀባይነት አይኖረውም። https://t.me/Hassendawd
1 21215Loading...
37
ዋዛ እና ቁምነገር ~ አልሙጊራህ ብኑ ዐብዲረሕማን ብኒ ሂሻም በቁስጠንጢኒያ ዘመቻ ላይ አንድ አይኑን ያጣል። ሙጊራህ በየደረሰበት ምግብ የሚያበላ ሰው ነበር። አንዴ እንደተለመደው ምግብ ደግሶ በቀረበበት አንድ አዕራቢይ መጣ። ሰውየው ምግቡን መብላቱን ጥሎ ሙጊራን በረጅሙ ትክ ብሎ ያየው ያዘ። ሙጊራህ፡ "ምን ሆነሃል አዕራቢው?" አለው። አዕራቢዩ፡ "የምግብህ ብዛት ይገርመኛል። አይንህ ግን አጠራጥሮኛል።" ሙጊራህ፡ "ምንድነው ያጠራጠረህ?" አዕራቢዩ፡ "ምግብ የምታበላ አንድ አይና ሆነህ እያየሁህ ነው። ይሄ የደጃል ምልክት ነው።" ሙጊራህ፡ "ብላ ይልቅ አዕራቢው! ደጃል በአላህ መንገድ በመዝመት አይኑን አያጣም።" 📗 [ጀምዑል ጀዋሂር ፊልሙለሒ ወነዋዲር ] እኛ ብንሆን አክብረን የጋበዝነው ሰው እንዲህ አይነት ነገር ቢያነሳብን በምን መልኩ እናስተናግደዋለን? = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
3293Loading...
38
3,ዑስማን ኢብኑ አፍን ๏ መጀመሪያ ከሰለሙት ውስጥ ነው። ๏ ከአቡበክርና ከዑመር (ረ.ዐ) ቀጥሎ 3ተኛው ኸሊፋ ነው። ๏ መላኢኮች የሚያፍሩት ነው። ๏ በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ๏ መጀመሪያ ወደ ሀበሻ የተሰደደው እሱ ነበር ๏ በኺላፋው ዘመን ቁርአንን በሙስሀፍ ሰበሰበ ๏ አርማኒያ ፣ ኹራሳን ፣ ኩርማን ፣ አፍሪካንና የተለያዩ ሀገራትን ከፈቶ ኢስላማዊ መንግስትን አስፋፍቷል ๏ መስጂደል ሀረምንና መስጂደ ነበዊን አስፋፍቷል። ๏ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢስላመዊ የባህር ሀይልን አቋቋመ። ๏ በሁለተኛው አጋማሽ ኺላፋው ወደ 12 አመት ከቆየ በኋላ ፊትና ብቅ አለች በዛ ምክኒያት በሙናፊቆች ቁርአን እየቀራ ሸሂድ ሆነ ተወግቶ ደሙ በአንዲት አንቀፅ ላይ ፈሰሰ «እነሱንም አላህ ይበቃሃል ፣ እርሱም ሰሚው አዋቂው ነው።» [በቀራህ 137] . ⇨ ትክክለኛ ስሙ ዑስማን ኢብኑ ዐፋን አል ኡመዊ ይባላል ዚ ኑረይን ተብሎም ይታወቃል። ዚ ኑረይን የተባለበት ምክኒያት ደግሞ ๏ የረሱል (ﷺ) 2 ሴት ልጆችን ስላገባ ነው።ሩቀያህን አግብቶ ከሞተች በኋላ ዳግም ረሱል (ﷺ) ኡሙ ኩልሱምን ዳሩት እሷም ስትሞት ረሱል (ﷺ) 3ተኛ ልጅ ቢኖረኝ ዑስማንን እድረው ነበር ብለው ነበር። ๏ ይህን በማስመልከት ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንዲህ ይላሉ አጎቴ እንዲህ አሉኝ “ ዑስማን ለምን ዚ ኑረይን እንደተባለ ታውቃለህን? አላውቅም አልኩኝ  ከአደም ፍጥረት ጀምሮ እስከ እለተ ቂያም ድረስ ዑስማን እንጂ የአንድ ነቢይ 2 ሴት ልጅ አግብቶ ማንም አያውቅም ለዛም ነው ዚ ኑረይን የተባለው ” አለኝ። ๏ እናቱ አርዋ ቢንት ኩረይዝ ኢብኑ ረቢዐህ ትባላለች።
3913Loading...
39
1.20 ኒካህ እንዴት ነው የሚታሰረው? ኒካህ ለማሰር ከላይ የጠቀስናቸው መስፈርቶች ከተሟሉ በኋላ የሷ ወልይ ወይም ደግሞ እሱ የወከለው አካል ሊያገባት ለፈለገው ወይም ለሱ ተወካይ የልጅቷን ስም ጠርቶ ወይም ወደሷ አመላክቶ ላንተ(ላንተ የሚለው የሚያገባትን ሰው እያናገረ ከሆነ ነው ካልሆነ ግን ስሙን ነው ሚጠራው) ድሬልሀለው ወይም አጋብቼሀለው ይለዋል።እሱም(የሚያገባት ሰውዬ) ተቀብያለሁ ይለዋል። ይህ ንግግር ሰዎቹ በሚግባቡበት በየትኛውም ቋንቋ ሊሆን ይችላል። የሚድረው አካል ተወካይ ከሆነ የተወከለ መሆኑን መግለጽ አለበት።ስለዚህም ሲድር የወከለኝ እከሌ ልጅ የሆነችውን ለእከሌ ድሬለታለሁ ነው የሚለው።ተቀባዩም ተወካይ ከሆነ ተቀብያለሁ ሳይሆን ለወከለኝ እከሌ ተቀብዬለታለሁ ነው የሚለው።ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች አሟልቶ ይህ ከተፈጸመ በኋላ ኒካው ታስሯል ማለት ነው። https://t.me/Hassendawd
4159Loading...
40
1.19 ወልዮቿ በሙሉ አልድርም ቢሉስ በዲኑም ይሁን በስነ-ምግባሩ ለሷ የሚመጥናትና ለማስተዳደር አቅም ያለው ልጅ መጥቶ እሷም ወዳውና ፈልጋው ነገር ግን ወልዩዋ ምንም ሸሪአዊ ምክንያት ሳይኖረው አልድርም ብሎ መከልከል አይችልም።ምክንያቱም ወልዩዋ ለሷ የሚጠቅማትን የማድገር ግዴት አለበት። እንቢ ብሎ ከከለከላት ግን ወልይነቱ ከሱ ተነስቶ ወደ ሚቀጥለው አካል ይተላለፋል። ወልዮቿ በሙሉ ተጠይቀው አንድርሽም ብለው ከከለከሏት ሙስሊም መሪ ወይም ቃዲ ካፊር ሀገር ላይ ከሆነች ደግሞ ሙስሊሞችን ሊወክል የሚችል ድርጅት ሙዲር ወይም ኢማም ይድራታል።ልጁ ከሸሪአ አንጻር የሚመጥናት ከመሆኑ ጋር እነዚህ ሁሉም እሷን ከመዳር እንቢ ካሉ ራሷን ትድራለች የሀነፍዮችን መዝሀብ ይዘን። ይህን አቋም ኢብን ኡሰይሚን አሸርሁል ሙምቲእ ኪታብ ላይ ጠቅሰውታል።¹⁰⁶ 📖 ሸሪአዊ ምክንያት ካለው ግን ለምሳሌ ሊያገባት ያሰበው ሰው ስነ ምግባሩ ብልሹ ከሆነ ወይ በዲኑ ጠንካራ ካልሆነ ወይ ደግሞ ማስተዳደር አቅም ከሌለው ወልዩዋ እሱን ከማግባት ሊከለክሏት ይችላሉ።ምክንያቱም ወልይ የተቀመጠው የማይሆናት ሰው ሲመጣ አይሆንም ብሎ እንዲመልስ ነው። https://t.me/Hassendawd
3575Loading...
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إنّ أولى الناسِ بي يومَ القيامةِ أكثرُهم عليَّ صلاةً﴾ “በትንሳዔ ዕለት ከሰዎች ሁሉ ለኔ በላጭ (ቅርብ) የሚሆነው በኔ ላይ በብዛት ሰለዋት የሚያወርድ ነው።” 📚 ሶሂህ አተርጊብ
Show all...
ቢላል ኢብኑ ረባህ ๏ መጀመሪያ ከሰለሙት አንዱ ነው። ๏ እስልምናውን ለመጀመሪያ ጊዜ ግልፅ ካደረጉት ውስጥ አንዱ ነው። ⇨እስልምናቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ ግልፅ ያወጡት 7 ናቸው እነሱም ረሱል (ﷺ) ፣ አቡበክር ፣ ዐማር ፣ የዐማር እናት ሱመያህ ፣ ቢላል ፣ ሱሀይብ እና ሚቅዳድ ናቸው። ๏ መስለሙን ግልፅ ባወጣ ጊዜ በአለቃው ኡመያህ ኢብኑ ኸለፍ በጣም ከባድ ቅጣት ደርሶበት ነበር ነገር ግን እሱ አሀዱን አሀድ ከማለት አልተወገደም ነበር (ረ.ዐ) እየተቀጣ እያለ አቡበክር አሲዲቅ (ረ.ዐ) መጣና ገዝቶት ነፃ አወጣው። በዚህም ንግግሩ "አሀዱን አሀድ " በጣም ታዋቂ ሆነ አሀዱን አሀድ ሲባል በሁሉም ሰው ፊት የሚመጣው ቢላል እና ታሪኩ ነው። ๏ ለሰላት መጀመሪያ ጊዜ አዛን ያደረገው ነው ๏ በድር ዘመቻ ላይ አለቃው የነበረውን ኡመያን የገደለው እሱ ነው ๏ ረሱል (ﷺ) ዘንድ በጣም ትልቅ ደረጃ ነበረው ስለርሱ ብዙ ብለዋል ከነዛ ውስጥ‥ ⇨ጀነት ውስጥ የቢላልን ኮቴ መስማታቸውን ⇨ቀዳሚዎች 4 ናቸው እኔ የዐረብ ቀዳሚው ነኝ ፣ ስልማን የፋሪስ ቀዳሚ ነው ፣ ቢላል የሐበሻ ቀዳሚ ነው ፣ ሱሀይብ የሮም ቀዳሚ ነው ማለታቸውና ሌሎችም ተናግረዋል። ๏ እድሜው ወደ 60 ምናምን ሲደርስ አጀሉ ቀረበ ሊሞት አከባቢ ሚስቱ ወ ሀዘኔ አለች እሱም " ዋ ደስታዬ ነገ ወዳጆችን እንገናኛለን ሙሐመድን (ﷺ) እና ህዝቦቹን " (الأحبة نلقى غدا وحزبة محمدا) ሻም ውስጥ ሞተ እዛውም ተቀበረ‥ ⇨ትክክለኛ ስሙ ቢላል ኢብኑ ረባህ ይባላል የረሱል (ﷺ) ሙአዚን ተብሎም ይታወቃል ๏ የረሱል (ﷺ) ሙአዚኖች 4 ናቸው አንደኛው ቢላል ሲሆን ሁለተኛው አብደላህ ኢብኑ ኡሚ መክቱም ሶስተኛው አቡ መህዙረህ አራተኛው ሰዐድ አልቁረዚ ናቸው። ⇨የእናቱ ስም ሀማመህ ትባላለች https://t.me/Hassendawd
Show all...
ሐሰን ዳውድ

ኢስላማዊ እውቀት የሚተላለፍበት ቻናል 1,አቂዳ 2, ፊቂህ 3, ሀዲስ 4, ሉጋህ( ነህው;ሶርፍ,በላጋ,በያን,አደብ,አሩድ) 5, ሙስጠላህ 6,ኡሱል ሌሎችም አጫጭር መረጃዎች ያገኙበታል።

የኒካህ ቀለበት ዛሬ ላይ ብዙ ሰዎች ዘንድ የተሰራጨው ኒካህ ላሰረላት ሴት ቀለበት ማድረግ የሚባለው ተግባር ቀደምት ሙስሊሞች ዘንድ ይተገበር ያልነበረ ከክርስቲያኖች የተወሰደ ተግባር ነው። የዘመናችን ሙሀዲስ የሆኑት ሸይክ ናሲረዲነል አልባኒ እንዲህ ይላሉ "ይህ ተግባር ወደ ቀደመ (የክርስቲያኖች) ተለምዶ ይመለሳል። ሙሽራው በሙሽሪት የግራ እጅ አውራ ጣቷ ጫፍ ላይ ቀለበቱን ያደርግና በስመ አብ ይላል ከዛም አመልካች ጣቷ ጫፍ ላይ ያደርግና በወልድ ይላል ከዛም የመሀከለኛ ጣቷ ላይ ያደርግና በመንፈስ ቅዱስ ይላል በመጨረሻም አሚን በሚል ግዜ ከትንሿ ጣት ቀጥሎ ያለው ጣቷ ላይ ያደርገውና በዛው ይቀራል። ለንደን የሚታተም women የሚል ጋዜጣ (ቁ 19 1960 ገፅ 8) ላይ እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ Why is the wedding ring placed on the third finger of the left hand? ለምንድነው የሰርግ ቀለበት በግራ እጅ ሶስተኛ ጣት ላይሚቀመተው? በርእሱ ላይ መልስ የሚሰጠው Angela Talbot እንዲህ ብሎ “it is said there is a vein runs directly from the the finger to the heart. Also,there is the ancient origin whereby the bridegroom placed the ring on the tip of bride’s left thumb,saying ; “in the name of the father” on the first finger, saying “in the name of the son “ on the second finger, saying ; “And of the holy ghost”,on the word “Amen” , the ring was finally placed on the third finger where it remained” "ከዚህ ጣት ቀጥታ ከቀልብ የሚያገናኝ ደም ስር አለ ይባላል። ከዛም በተጨማሪ የቀደመ መሰረት አለው ካለ በሗላ ከላይ የጠቀስነውን በስምአብ...የሚለውን እስከመጨረሻው ጠቀሰ" በዚህ ንግግር እንደምንረዳው ይህ ተግባር የመጣው ከክርስቲያኖች እንደሆነና ጥንታዊ የሆነ እምነታዊ መሰረትም እንዳለው ነው። ይህንን የሚጠቅሱም ብዙ ኡለሞች አሉ። በመሆኑም ▪️ይህ ተግባር የክርስቲያኖች እምነታዊ መገለጫ ነው። ከነሱ መመሳሰል ደግሞ ከከባባድ ወንጀሎች ነው። ▪️ ይህን ቀለበት ግራ እጅ ከትንሿ ጣት ጎን ሚያደርጉበት ምክንያት ይህ ጣት ከልብ ጋር ግንኙነት አለው የሚል ከንቱ እምነት ይዘው ነው ይህ ደግሞ በእስልምና ቦታ የለውም ▪️ ብዙ ሰዎች ዘንድ ቀለበት ማሰሩ በመሀከላቸው ውዴታን ያመጣል የሚል እምነት አለ ይህም ከእስልምና አቂዳ ጋር ቀጥታ የሚጣረስ የሽርክ አይነት ነው። ▪️ አንዳንዶች ደግሞ ቀለበት ካለበሰ ወይም ካለበሰች ኒካው ትክክል አይመስላቸውም ይህም መሰረት የሌለው አጉል እምነት ነው። ▪️ ይህ ተግባር ቀደምት ሙስሊሞች ዘንድ ያልተለመደ ከክርስቲያኖች የተወረሰ ነው ▪️ አንዳንዶች ገና ሲተጫጩ ኒካም ሳያስሩ ወስዶ ቀለበት ያደርግላታል ይህ ደግሞ የተከለከለችን አጅነብይ ሴት እጅ መንካት ነው ያም ከባድ ወንጀል ነው። እንዳጠቃላይ ለኒካህ ወይም ሰርግ ብሎ ቀለበትን መልበስ የሙስሊሞች ሳይሆን የክርስቲያኖች ሱና ነው። ኢብን ኡሰይሚን ስለዚህ ሲናገሩ "እኔ ማየው አነሰ ቢባል ይህ ተግባር የተጠላ ነው ይላሉ።” ኢብን ባዝም ለሰርግ ብሎ ቀለበት ማሰር የሙስሊሞች ሱና እንዳልሆነ ይገልፃሉ። ሸይኽ አልባኒም እንደማይቻል ይገልፃሉ። ከዛ ውጪ ባለ ሁኔታ ግን ለኒካህ አስበህ ሳይሆን እንዲሁ ቀለበትን በኖርማል ግዜ ብትለብስ ችግር የለውም። ለወንድ ልጅ ግን የወርቅ ቀለበት አይፈቀድም። https://t.me/Hassendawd
Show all...
ሐሰን ዳውድ

ኢስላማዊ እውቀት የሚተላለፍበት ቻናል 1,አቂዳ 2, ፊቂህ 3, ሀዲስ 4, ሉጋህ( ነህው;ሶርፍ,በላጋ,በያን,አደብ,አሩድ) 5, ሙስጠላህ 6,ኡሱል ሌሎችም አጫጭር መረጃዎች ያገኙበታል።

👍 3
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته የተከበራችሁ እህትና ወንድሞች እንኳን ወደ ዛድ ኦንላይን የቂርአት ማዕከል በሰላም መጣችሁ እያልን መመዝገቢያ ፎርም እንደሚከተለው ይቀርባል። 1, ስም ከነ አያት__ 2, አሁን ያለንበት ሀገር____ 3,ዋሳፕና ቴሌግራም ምትጠቀሙበት ስልክ ቁጥር____ 4,ፆታ____ 5,የቂርአት ደረጃ_ 6.መቅራት የሚፈልጉት_ ማሳሰቢያ:- 👉🏿መድረሳችን በአንድ አመት 4 ሴሚስተር የሚኖሩት ሲሆን ክፍያ የሚፈፀመው በየ ሴሜስተሩ ነው። 👉🏿በቁርጠኝነት መማር የምትፈልጉ ብቻ እንድመዘገቡ በትህትና እንጠይቃለን። 👉🏿ትምህርቱ የሚሰጠው በዙም አፕ እና በ ቴሌግራም ስለሆነ ከወዲሁ አፑን በማውረድ ለትምህር እንድትዘጋጁ እናሳስባለን። _ መመዝገቢያ ሊንክ👉🏿 https://forms.gle/Ve6Fcex92Nu5sbRQ8 ይህን ሊንክ በመጫን ከአሁኑ ሰዓት ጀምራችሁ መመዝገብትችላላችሁ።
Show all...
1
አቡ ዑበይድ ኢብኑል ጀራህ ๏ መጀመሪያ ከሰለሙት አንዱ ነው። ๏ በጀነት ከተበሰሩት 10 ሳሃቦች አንዱ ነው። ๏ በሁለተኛው ጊዜ ወደ ሐበሻ ከተሰደዱት ሰሃቦች አንዱ ነው። ๏ ቁርአንን ከሀፈዙት (በቃል ከያዙት) ሰሃቦች አንዱ ነው። ๏ ረሱል (ﷺ) የተለያዩ ልኡካንን ሲልኩ አባ ዑበይዳን መሪ አድርጎ ነበር የሚልከው እርሱ ዘንድም በጣም ተወዳጅ ሰሃቢይ ነበር ከዛ የተነሳ ረሱል (ﷺ) ከሞቱ በኋላ አቡበክር ኺላፋው ለአቡ ዑበይዳህ ነው የሚገባው እስከማለት ደርሶ ነበር ከዛ በኋላ ነው ዑመር " አይ አለቃችን ፣ በላጫችን ፣ ረሱልም ዘንድ ይበልጠ ተወዳጅ የሆንከው አንተ ነህ " ብሎ አለ። ኺላፈውም ለአቡ በክር ቃል ተገባ‥ ⇨በአቡ በክር ኺላፋ ዘመን ሻምን ለመክፈት አቡ ዑበይዳን መሪ አድርጎት ነበር የላከው ተሳክቶለት ከፈታት…የተለያዩ ሀገራትንም ከፍቷል። ⇨በዑመር ኺላፋ ዘምንም ዑመር በሰራዊቶችና በሻም ሀገር ላይ መሪ አድርጎት ነበር። ⇨አቅሳ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከፈተችው በዑመር ኺላፋነት ዘመንና በአቡ ዑበይደህ ጦር መሪነት ነበር በዚህም ሰበብ የመሪዎች መሪ ይባላል። ๏ ሻም ሀገር ላይ ወባ ተከስቶ ነበር በዛ ሰበብ ከዚህች አለም ወደ ሌላኛው አለም ተሻገረ‥ ⇨ትክክለኛ ስሙ ዓሚር ኢብኑ አብደላህ ኢብኑል ጀራህ ይባላል ๏ የዚህች ኡማህ (ህዝብ) ታማኝ ተብሎም ይታወቃል ምክኒያቱ ደግሞ … ረሱል (ﷺ) ዘንድ የየመን ሰዎች መጡና " ከኛ ጋር ሱናን እና እስልምናን የሚያሰተምረን አንድን ሰው ላክ " አሉት ከዛም ረሱል (ﷺ) የአባ ዑበይዳህን እጅ ይዘው የዚህች ኡማህ ታማኝ እሱ ነው " አሉ። ⇨በሌላ ዘገባም " ለሁሉም ህዝብ ታማኝ አላቸው የዚህች ህዝብ ታማኝ ደግሞ አቡ ዑበይደህ ኢብኑል ጀራህ ነው " ብለዋል። ⇨የእናቱ ስም ኡመይመህ ቢንት ገነም ኢብኑ ጃቢር ትባላለች ๏ ኢብኑ ሀዝም አል አንደሉሲ ኡመይመህ ቢንት ዑስማን ኢብኑ ጃቢር ኢብኑ አብዱል ዑዛህ ብለውም አስቀምጠዋል ‥ https://t.me/Hassendawd
Show all...
ሐሰን ዳውድ

ኢስላማዊ እውቀት የሚተላለፍበት ቻናል 1,አቂዳ 2, ፊቂህ 3, ሀዲስ 4, ሉጋህ( ነህው;ሶርፍ,በላጋ,በያን,አደብ,አሩድ) 5, ሙስጠላህ 6,ኡሱል ሌሎችም አጫጭር መረጃዎች ያገኙበታል።

ለኒካህ ዱፍ መምታት ዱፍ የሚባለው ከአንድ በኩሉ በቆዳ የተሸፈነ በሌላ ጎኑ ክፍት የሆነ ትንሽ ከበሮን የሚመስል በእጅ የሚመታ የሙዚቃ መሳሪያ ነው በዲነል ኢስላም የሙዚቃ መሳሪያዎች በሙሉ የተከለከሉ ናቸው። ማስረጃውም ኢማም ቡኻሪ ሰሒሀቸው ላይ በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል {{ ْلَیَكُونَنَّ من َأُمَّتِي أَقْوَامٌ یَسْتَحِلُّونَ حِرَ وَالْحَرِیرَ وَالْخَمْرَ وَالْمَعَازِف}} {ከኔ ኡማ ሰዎች ይመጣሉ ፦ ዝሙትን ፣ ሀር ልብስን (ለወንድ ልጅ) ፣ አሰካሪ መጠጥን እና የሙዚቃ መሳሪያን የሚፈቅዱ} ይህ ሀዲስ ሁሉም የሙዚቃ መሣሪያ ዱፍንም ጨምሮ መከልከሉን ይጠቁማል በተጨማሪም ኢማም አልበይሀቂ በዘገቡት ሀዲስ አብደላህ ኢብን አባስ ዱፍ ሀራም ነው ማለቱ ተወርቷል።¹⁶² እንደጥቅል ሁሉም የሙዚቃ መሳሪያዎች የተከለከሉ ቢሆንም ዱፍ ግን በተወሰኑ ሁኔታዎች ተፈቅዷል እነሱም በሰርግ፣ በኢድ እና የሩቅ እንግዳን ለመቀበል ነው።በነዚህ ሶስት ቦታዎች ላይ ዱፍ መምታትን የሚፈቅዱ የመጡ የተረጋገጡ ሀዲሶች አሉ።¹⁶³ ከነዚህ ሶስት ሁኔታዎች ውጪ ዱፍን መምታት የተፈቀደበት አናገኝም በመሆኑም የሙዚቃ መሳሪያ እንደመሆኑ እንደሌሎች የሙዚቃ መሳሪያዎች ሁሉ በሌሎች ሁኔታዎች ላይ የተከለከለ ይሆናል። በሸሪአ የተከለከለ ነገር ለሆነ ነገር ተነጥሎ ከተፈቀደ በዛ ላይ ብቻ ነው ፈቃዱ የሚሆነው እንጂ ለሁሉም ሁኔታዎች የተፈቀደ አይሆንም።ስለዚህ ሰርግ ላይ ዱፍን መጠቀም ይቻላል። በሰርግ ላይ እንኳን ቢሆን ከዱፍ ውጪ ያሉ የሙዚቃ መሳሪያዎችን መጠቀም በጭራሽ አይፈቀድም። ለወንድ ልጅስ ይፈቀዳል ወይስ በሴት ልጅ ብቻ የተነጠለ ነው? ለወንድ ልጅ ዱፍ መምታትን በተመለከተ ኡለሞች መሀከል ኺላፍ ያለበት ሲሆን አመዛኝ በሆነው የኡለሞች አቋም መሰረት ዱፋ መመታት የሚፈቀደው ለሴቶች ብቻ ነው።ምክንያቱም በሰሀቦች ዘመን ይህ ሚታወቀው ከሴቶች ዘንድ ነበር ከወንዶች መሀከል ይህን መስራት ደግሞ በሴቶች መመሳሰል ይሆናል።ከሴቶች መመሳሰል ደግሞ ከትልልቅ ወንጀሎች ውስጥ ነው። ሸይኩል ኢስላም ኢብን ተይሚያ እንዲህ ይላል “ከሰሀቦች መሀከል ዱፋ በመምታት የሚታወቅ ወንድ አንድም አልነበረም።እንዲያውም ይህንን የሚያደርግን ሰው ቀደምቶች ሴታሴት ብለው ይጠሩት ነበር” ¹⁶⁴ ኢብን ሀጀር እንዲህ ይላል “ጠንካራ የሆኑ ሀዲሶች ላይ ለሴቶች መፈቀዱን ይጠቁማል። በዚህ ላይ ወንዶች አይገቡበትም ጥቅል የሆነ ከሴቶች ጋር መመሳሰልን የሚከለክሉ ሀዲሶች ስላሉ።” ባጠቃላይ መልኩ ለወንድ ልጅ ጦር ውርወራ ፣ ፈረስ ግልቢያ እና የመሳሰሉት ተግባሮች ላይ መገኘት ነው ተገቢ ሚሆነው እንጂ የሴቶች ተግባር በሆኑት ዱፍ መምታት እና ማጨብጨብ ላይ መገኘት የለበትም። ስንጠቀልል ሴቶች ከወንዶች ጋር ሳይቀላቀሉ በሰርግ ስርአት ላይ ዱፍ እየመቱ እና ግጥምን እየገጠሙ መጫወት ይወደድላቸዋል።
Show all...
👍 6 1
ሰኢድ ኢብኑ ዘይድ ๏ መጀመሪያ ከሰለሙት ውስጥ አንዱ ነው ሲሰልምም ከሚስቱ ጋር ነበር የሰለመው ከዑመር ኢብኑል ኸጣብ በፊትም ነበር የሰለመው። ๏ በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች አንዱ ነው። ๏ የዑመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.ዐ) አጎት ልጅ ነው እህቱ ደግሞ የዑመር ኢብኑል ኸጣብ ሚስት ናት ሚስቱ ደግሞ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ መስለም ሰበብ የሆነችዋ እህቱ ፋጢማህ ቢንቱል ኸጣብ ናት። ๏ ወደ መዲና መጀመሪያ ከተሰደዱት አንዱ ነበር። ๏ በሙዓዊያህ ኢብኑ አቢ ሱፍያን (ረ.ዐ) ኺላፋ ዘመን እድሜው ወደ 73 ከደረሰ በኋላ ጊዜው ደርሶ ይህችን ዱንያ ለቆ ወጣ ጁሙዓህ ቀን ነበር የሞተው ቦታውም ዐቂቅ ነበር ይባላል ከዛ ወደ መዲና ተይዞ ተመጣ ጀናዛውን ሰዐድ ኢብኑ አቢ ወቃስ (ረ.ዐ) አጥቦት ነበር መዲናም ተቀበረ… ⇨ትክክለኛ ስሙ ሰዒድ ኢብኑ ዘይድ ኢብኑ ዐምር ኢብኑ ኑፈይል ይባላል። ๏ የሰዒድ አባት በነቢዩላህ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ሐይማኖት ላይ ነበር ለጣኦቶች አይሰግድም ነበር ቁረይሾች የሚያርዱትን ነገር አይበላምም ነበር ረሱል (ﷺ) ከመላኩ በፊት ተገናኝቶት ነበርና ሱፍራ አቅርቦላቸው ነበር ረሱል (ﷺ) አይ አለው ከዛም ዘይድ እንዲህ አለ " እኔ እናንተ ጣኦቶቻችሁ ላይ የምታርዱትን አልበላም የአላህ ስም ያልተወሳበት ነገርም አልበላም " ๏ ረሱል (ﷺ) ስለ ዘይድ ተጠይቀው ነበር እንዲህም አሉ‥ " ቂያም ቀን ልክ እንደ አንድ ኡማህ (ህዝብ) ሆኖ ይቀሰቀሳል " ๏ በሌላም ቦታ እንዲህ ብለው ነበር " ጀነት ገብቼ ለዘይድ ሁለት ትላልቅ ዛፎችን አይቼ ነበር " ⇨የእናቱ ስም ፈጢማህ ቢንት በዕጀህ ኢብኑ ኡመያህ ትባላለች። https://t.me/Hassendawd
Show all...
ሐሰን ዳውድ

ኢስላማዊ እውቀት የሚተላለፍበት ቻናል 1,አቂዳ 2, ፊቂህ 3, ሀዲስ 4, ሉጋህ( ነህው;ሶርፍ,በላጋ,በያን,አደብ,አሩድ) 5, ሙስጠላህ 6,ኡሱል ሌሎችም አጫጭር መረጃዎች ያገኙበታል።

2👍 1
2.3 ለሰርግ ተጠርተህ ግን ፆመኘ ከሆንክ ጾመኛ ስለሆንኩ ብለህ ከጥሪው መቅረት የለብሀም። ይልቁንስ ጥሪውን አክብረህ ትሄድና ከዛሀም ሁለት አማራጮች አሉህ አንደኛው፦ጾምህን ሳታጠፋ ቦታው ላይ ትገኝና ለሱ ዱአ ታደርግለታለህ መልእክተኛው ﷺ እንዲህ ብለዋል {{إذا دعي أحدكم إلى طعام فلیجب فإن كان مفطراً فلیطعم وإن كان صائما فلیصل. يعني :الدعاء }} {{አንዳችሁ ወደ ምግብ ከተጠራ ይሂድ ጾመኛ ካልሆነ ይመገብ ጾመኛ ከሆነ ደግሞ ዱአ ያድርግ}} ሁለተኛው፦ ጾምህ ሱና ጾም ከሆን ወንድምህን ለማስደሰት ስትል ማፍጠርም ትችላለህ።በተለይ ደግሞ ወንድምህ እንድትመገብ የጠነከረ ፍላጎት ካለው።ሱና ጾም መጾሙ ግዴታ እንዳልሆነው ሁላ ጀምሮት ከነበረ መጨረሱም ግዴታ አይሆንም። በዚህ ላይ የመጣ ሀዲስ አለ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል {{ الصائم المتطوع أمیر نفسھ إن شاء صام وإن شاء أفطر }} {{ሱና ጾም የሚጾም ሰው የራሱ አዛዥ ነው።ከፈለገ ይጾማል ከፈለገ ያፈጥራል}} 📖 ጾሙ ሱና እስከሆነ ድረስ ያፈጠረውን ቀን በሌላ ግዜ ቀዳ ማውጣት ግዴታ አይሆንበትም ነገር ግን ቀዳ ቢያወጣውም ይችላል። ይህንን የሚጠቁም ኢማመል በይሀቂ የዘገቡት ሀዲስ አለ። ጾሙ ግን የግዴታ ጾም ከሆነ ለምሳሌ የረመዳን ቀዳ ከሆነ ወይ ደግሞ የመሀላ ከፋራ ከሆነ ማፍጠር አይፈቀድለትም።
Show all...
👍 2

👍 1