cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

السنة(ሱናህ)

ኢስላማዊ እውቀት የሚተላለፍበት ቻናል 1,አቂዳ 2, ፊቂህ 3, ሀዲስ 4, ሉጋህ( ነህው;ሶርፍ,በላጋ,በያን,አደብ,አሩድ) 5, ሙስጠላህ 6,ኡሱል ሌሎችም አጫጭር መረጃዎች ያገኙበታል።

Show more
Advertising posts
1 066
Subscribers
+424 hours
+837 days
+15130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

1.18 ያለ ወልይ የታሰረ ኒካህ (የሹብሀ ኒካህ) ኒካህ ለማሰር ወልይ መስፈርት መሆኑን ከላይ አሳልፈናል።በመሆኑም ያለ ወልይ ኒካህ ማሰር አይቻልም።ነገር ግን ያለ ወልይ ማሰር የሚቻል መስሎት ካለ ወልይ ኒካህ አስረው ሚኖሩ ከሆነ ይህ ኒካ የሹብሀ ኒካ ይባላል።በመሆኑም ያለ ወልይ ማሰር እንደማይቻል ካወቁ ሰአት ጀምሮ ኒካሁን ማደስ ይጠበቅባቸዋል።ነገር ግን እስካሁን ያሳለፉት እንደ ዝሙት አይቆጠርም ልጅ ወልደውም ከሆነ በራሳቸው ነው ሚጠራው።ኒካሁን ለማደስ ፈትቼሻለሁ ማለት አይጠበቅበትም። https://t.me/Hassendawd
Show all...
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህቱሏሂ ወበረካቱሁ የተከበራቹ ሙስሊም ወንድሞችና እህቶች ከላይ ባለው ቪዲዮ ላይ የምትመለከቱት ቦታ በሰሜን ወሎ ዞን የሚገኘው የወልዲያ ዪኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ ሲሆን ከምትመለከቱት የውዱዕ ማድረጊያ በታች ያለው መሬት መንገድ በመሆኑ ለመስጂዱ የሚቀረው ቦታ በቂ አይደለም።በተጨማሪም መስጂዱም እንደምትመለከቱት በአግባቡ የተሰራ ባለመሆኑ ተጨማሪ የመስጂድ ቦታ ለመግዛትና መስጂዱንም በአግባቡ ለመገንባት የተማሪው አቅም ስላልቻለ የእናንተን እገዛ እንሻለን ።በመሆኑም አቅማቹ በቻለው ሁሉ እንድታገዙንና ለሌሎችም ሼር በማድረግ እንድትተባበሩን በአሏህ ስም እንጠይቃለን። የጀመዐው የባንክ አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:1000520261943 woldia universities Muslim student union http://t.me/wdumuslimstu
Show all...
1.17 መወከልስ ይቻላል? ወልይ የሆነ ሰው ኒካህ ለማሰር ቦታው ላይ መገኘት ካልቻለ በቦታው ሌላ የፈለገውን ሰው መተካት ይችላል።የተተካው ሰው ልክ እንደወልይ ሆኖ ኒካውን ያስራል። ሙስሊም ያልሆነን ሰው መወከልን በተመለከተ ኡለሞች መሀከል ጭቅጭቅ ያለበት ሲሆን ሻፍእዮችና ሀናቢላዎች አይቻልም ይላሉ።ማሊኪዮችና ሀነፍዮች ግን ይቻላል ይላሉ።አይቻልም ያሉ ኡለሞች ለራሱ ወልይ መሆን ስለማይችል መወከልም አይችልም ይላሉ።የተሻለው ከኺላፉ ለመውጣት ካፊርን አለመወከን ነው። https://t.me/Hassendawd
Show all...
1.16 በዝሙት የተወለደች ሴት ልጅ ማን ወልይ ይሆናታል? ሚዛን በሚደፋው የኡለሞች አቋም መሰረት በዝሙት የተወለደች ልጅ የምትጠራው በእናቷ እንጂ በአባቷ አደለም። በዚህ ላይ ደግሞ የመጣ ሀዲስ አለ።በመሆኑም አባቷ ለሷ ወልይ አይሆናትም ቢሞትም አትወርሰውም ብትሞትም አይወረሳትም።እናት ደግሞ ወልይ ሆና ኒካህ ማሰር አትችልም የናት ቤተሰቦችም እንዲሁ ወልይ መሆን አይችሉም። ስለዚህ ይህች ሴት ወልይ የላትም።ወልይ የሌላት ደግሞ ወልዩዋ የሙስሊም ባለስልጣን ነው። መልእክተኛው ﷺ እንዲህ ብለዋል {ባለስልጣን ወልይ ነው ወልይ ለሌለው} በመሆኑም በአካባቢዋ ሸሪአ ፍ/ቤት ካለ የዛ ፍርድ ቤት ቃዲ ወልይ ሆኖ ያስርላታል።ያ ከሌለ በአካባቢዋ ያለ ሙስሊሞችን የሚወክል ተቋም ካለ የዛ ተቋም ሙዲር (ተጠሪ) ወልይ ሆኖ ይድራታል።ያም ከሌለ የመስጂድ ኢማም ወልይ ይሆናታል። https://t.me/Hassendawd
Show all...
1
1.15 ቤተሰቦቿ በሙሉ ክርስቲያን የሆኑባት ሴት ማን ይድራታል? ክርስቲያን አባት ሙስሊም ልጁን ወልይ ሆኖ መዳር ዕንደማይችል ከላይ አሳልፈናል።በመሆኑም ቤተሰቦቿ በሙሉ ክርስቲያን የሆኑባት ሴት የሷ ወልይ የሚሆነው ሙስሊም መሪው ወይም ደግሞ የሸሪአ ፍ/ት ቃዲ ነው ያለችው ካፊር ሀገር ሆኖ ሙስሊም መሪም ቃዲም ከሌለ በአካባቢ ያለ የሙስሊሞች መርከዝ ወይም ተቋም ጋር ሄዳ የዛ እስላማዊ ተቋም ሙዲር ወልይ ሆኖ ሊድራት ይችላል። ምንም አይነት ሙስሊሞችን ሊወክል የሚችል ተቋም በሌለበት አካባቢ ብትሆንና ሊያገባት ከፈለገው ሰው ውጪ ከጎኗ ማንም ከሌለ ከሱ ጋር ደግሞ ኒካህ ካላሰርን ዝሙት ላይ እንወድቃለን ብለው ከፈሩ ደሩራ ነውና ምንም አማራጭ ስለሌለ ራሷን ትድርለታለች።በዚህ አማራጭ በጠፋበት ግዜ ራሱ ሚያገባት ወልይ ይሆናታል ያሉም አሉ። https://t.me/Hassendawd
Show all...
السنة(ሱናህ)

ኢስላማዊ እውቀት የሚተላለፍበት ቻናል 1,አቂዳ 2, ፊቂህ 3, ሀዲስ 4, ሉጋህ( ነህው;ሶርፍ,በላጋ,በያን,አደብ,አሩድ) 5, ሙስጠላህ 6,ኡሱል ሌሎችም አጫጭር መረጃዎች ያገኙበታል።

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏህ ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ለዘቱል  ኢባዳ በሚል አርእስት ዛሬ ጁምአ ከመግሪብ እስከ ኢሻእ በሀሰን ዳውድ ጕሮ አንቢያ መስጂድ ሙሀደራ አለ ይጠብቁን።
Show all...
1.14 የሴት ልጅ ወልዮች እነማን ናቸው ሴት ልጅን ወልይ ሆነው ሊድሯት የሚችሉት በቅደም ተከተል ስንመለከት 1.ኛ አባቷ እሱ ከሌለ የአባቷ አባት እያለ .......ወደላይ ይቀጥላል እነዚ ከሌሉ ወደ ሁለተኛው እንሄዳለን 2.ኛ ልጇ እሱ ከሌለ የወንድ ልጇ ልጅ እያለ .....ወደታች ይቀጥላል ከሌሉ ወደ ሶስተኛው እንሄዳለን 3.ኛ በአባትም በእናትም የሚገጥም ወንድሟ እሱ ከሌለ በአባት ብቻ ሚገጥም ወንድሟ 4.ኛ የወንድሟ ልጅ (አባትም በእናትም የሚገጥም ወንድሟ ልጅ) እሱ ከሌለ በአባት ብቻ ሚገጥም ወንድሟ ልጅ 5.ኛ የአባቷ ወንድም (አጎቷ) 6.ኛ የአጎቷ ልጅ (የአባቷ የወንድም ልጅ መታወቅ ያለባቸው ነጥቦች ▪️ ቅርብ የሆነው ወልይ እያለ ያለ ምንም ምክንያት የሩቁ ካሰረ ኒካው አይሆንም። ለምሳሌ አባት እያለ እሱ ሳይጠየቅ ወንድም ሊያስር አይችልም። ወንድም እያለም እሱ ተዘሎ አጎት አያስርም።ሌላውም እንዲሁ ቅደም ተከተሉን ጠብቆ ነው መሄድ ያለበት። ▪️ ነገር ግን ቅርብ የሆነው ወልይ በህይወት ቢኖርም ከሀገር ጠፍቶ አሁን ላይ ሊገኝ ካልተቻለና እሱን ማግኘት ካዳገተ ቀጣዩ ወልይ ያስራል ▪️በእናት በኩል ያለ ቤተሰብ ወልይ ሆኖ ኒካህ አያስርም ▪️ የእንጀራ አባትም ያሳደጋት እሱ ቢሆንም እክኋል ወልይ ሊሆናት አይችልም። *ወልይ ሆኗት ራሱ ሚያገባት* የአጎት ልጅ ያጎቱን ልጅ ራሱ ወልዩዋ ሆኖ ለራሱ ሊድራት ይችላል። https://t.me/Hassendawd
Show all...
السنة(ሱናህ)

ኢስላማዊ እውቀት የሚተላለፍበት ቻናል 1,አቂዳ 2, ፊቂህ 3, ሀዲስ 4, ሉጋህ( ነህው;ሶርፍ,በላጋ,በያን,አደብ,አሩድ) 5, ሙስጠላህ 6,ኡሱል ሌሎችም አጫጭር መረጃዎች ያገኙበታል።

👍 4