ግጥም
Open in Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Show more4 815
Subscribers
+1324 hours
+617 days
+23730 days
Posts Archive
4 817
ላንቺ ተገዝቼ አፍቅሬሽ የኖርኩኝ
ደስታሽን ስፈልግ ደስታዬን ያጣሁኝ
ሂድ ስትይ የምሄድ ቁም ስትይ የምቆም
ስከተልሽ ብውል ስዞር እማልደክም
እኔ እኮ እንደዚህ ነኝ...
ባልዋልሽበት ቦታ ዓይኔ የሚስልሽ
የእኔ ብትሆኝ እያልኩ ሁሌ የማስብሽ
ሳይሽ የምረካ ሳጣሽ ግን የምነድ
አመድ አፋሽ ሆኜ ባንች ባልወደድ
ምንም ባልልሽም አንድ እርምጃ ባልሄድ
ተውኩት በቃኝ እያልኩ አፍቅሬሽ ይመመኝ
እንዳሻሽ ያረግሽኝ እኔኮ ባሪያሽ ነኝ
ከእንግዲህስ ወዲያ....
ለተገፋው ልቤ ለተንሰፈሰፈው
ለገፋሽው ቀልቤ ባዶ ላስቀረሽው
ካሳም አልጠይቅሽ እሽ የሚል ምላሽ
ቅመሽው አልልም ባንቺ ይድረስብሽ
ግን ግን ቅሬታ አለኝ የምፀልይልሽ
የእኔ ዓይነት አፍቃሪ መቼም እንዳይሰጥሽ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 817
#ለማን_አቤት_ልበል
ስኬት የምትሻው የባከነች ነፍሴ
ታንቀላፋ ጀመር ተጣልታ ከእራሴ
ለስራ ለዝባ እጇን አኮማትራ
ተሰለፈችልኝ ከሰነፎች ተራ
ድንገት በአጋጣሚ ዕድል ስትቸራት
አንድ ሚሊዮን ብር ፊቷ ዘራችላት
አፈስፈስ አድርጋ ድንጋጤ በቀላቀለ ድፍረት
ተሸክማ ለመሰወር ስታፈተልክ በፍጥነት
አልጋው መታትና ባነነች በድንገት
ለካስ እውን ዓይደለም ህልም ነበር ቅዠት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 817
ለእኔ ቦታ የለው መምጣትትሽ መቅረትሽ
ባለሽበት ሆነሽ ቀን በቀን ልውደድሽ
ማጣት አያርቀው ማግኘት አያቀርበው
የፍቅር መነሻው ሚዛኑ ልብ ነው
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 817
#ጌታ_ሆይ
እኔን አድን ብለህ ስንት መከራ አየህ
በህማም በእንግልት በግፍ ተሰቃየህ
ተከፍሎ የማያልቅ ውለታህ አለብኝ
ሀጢያተኛው ልጅህን በምህረት አስበኝ
ደካማ ነኝና ምንም ምግባር የለኝ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 817
ሕማማትህ ካላመመኝ
ግርፋትህ ካልተሰማኝ
እንግልትህ ካልከበደኝ
እኔ ማለት ምንስ ሰው ነኝ?!!!
ከከሰሱህ
ከአንገላቱህ
ከገረፉህ
ከሰቀሉህ
የማልሻል ፈሪሳውያን ሆኜ እንዳልቀር
ሕማማትህ ይመመኝ ይግባኝ ፍቅር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 817
#ከመቃብር_በላይ!!
ሀብትም ሀላፊ ነው ግዜውን ጠብቆ
ሰውም ከሞት አይቀር በተራ ለጥቆ
ውበትም ይጠልቃል አፈር ይሆንና
ሞትን አያሸንፍ ምን ቢቆለል ዝና!!!
መልካም ስራ ብቻ ዘላለማዊ ቅርስ
ከመቃብር በላይ ሁልግዜ የሚወደስ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 817
#ማን_ይሆን
ዓይኑ ተመልክቶ ልቦናው ያልቃኘ
የያዘውን ትቶ ሌላ ያልተመኘ
አካላዊ ወረት ያልረገጠው ደጁን
አለወይ ከሰዎች ያልጎዳ ወዳጁን
ውድ ፍቅረኛውን ልቡ እንዳፈቀረ
በእሷ ተወስኖ ዘላለም የኖረ
እስከ መጨረሻው መንፈሱ ሳይላላ
ከሚወደው በቀር ያልተመኘ ሌላ
ማናት ወይስ ማነው ይኸንን የሰራ
በቃሉ የሚገኝ ባስቀመጡት ስፍራ
ከሴትም ከወንድም ያልተለዋወጠ
ማን ይሆን ወዳጁን በሌላ ያልሸጠ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 817
እናንተ ሳትነግሩት እርሱ ያውቅ የለም ወይ
መች ይፈልግና የሰው ቃል አቀባይ!
ከእርሱ ተሰውሮ ማንስ ቀርቶ ያውቃል
ከንቱ ነው ሰው መሆን ሲካሰስ ይኖራል
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 817
Repost from ZERU_MUSIC 🎶
avacoin
ከጀመረ ረጅም ግዜ አልሆነውም ነገር ግን ብዙ ቁጥር ያለው ሰዎችን ማፍራት ችሏል ይሄ ኮይን ሰኔ ወይንም ከሰኔ በኋላ ሊስት እንደሚደረግ አየተወራ ነው ይሄ ቦት በደንብ ታፕ ማድረግ ይጠይቃል 400ኬ ኮይን እስከ 75$ ወይም 1 ግራም ይቀየርና Withdraw ማድረግ ይቻላል።
🔗https://t.me/avagoldcoin_bot?start=2d504d2b8393591e63f4
⚡️
ቦት ውስጥ እንደገባቹ በ
✅Email
✅yahoo
✅Outlook account Verify አድርጉ Gmail አይቀበልም የቆየሁባቹ ቨርፊኬሽን ስለማይሰራ ነበር አሁን ጀምራቹ መስራት ትችላላቹ።
4 817
#ጎደለብን_ፍቅር
መሬቱ ሳይጠበን አዕምሯችን ጠቦ
በዘር አጥር ሽቦ ዙሪያችን ተከቦ
አንድ ሀገር እያለን አስር ሀገር ናፍቀን
እስከመቼ ድረስ በግፍ ተገፋፍተን?
ልዩነት ውበት ነው ይላል ምላሳችን
በክፋት ተሞልቶ ታጭቆ ልባችን
ሀገሩ ሰፊ ነው ቆላ ወይና ደጋ
ቅንነት ብቻ ነው የሌለው ከእኛ ጋ
ደጋው ቢዘሩበት መሬቱ ገራገር
ሰቃው ቢያመርቱበት ምርቱ የሚናገር
ቆላው ቅባት አብቃይ ጦምን አያሳደር
ምነው እኛ ዜጎች ጎደለብን ፍቅር?!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 817
👫 ይጋብዙ እና ገንዘብ ይስሩ !
🎁 አንድ ሰው ሲጋብዙ 3 ብር ይሰራሉ ።
እስካሁን የጋበዙት ሰው መጠን: 0 ሰው
🔰 መጋበዣ ሊንክ : https://t.me/hulepay_official_bot?start=r09262166944
✅ ዛሬውኑ ጀምሮ ገንዘብ ያካማቹ እና በቴሌብር ይቀበሉ ።
4 817
ሰውነቴም ከዳኝ ልቤም አመለጠ
ሀሳቤ በሙሉ ባቺ ተለወጠ።
እባክሺ አቺ ልጂ አትራቂ ከፊቴ
አቺ ብቻ እኮነሺ የኔ መስታወቴ።
መስታወት ፊት እጂ አያሳይም አገር
አምላኬ ጠብቃት የዛቺን ልጂ ነገር።
እኔ ገና ልጂ ነኝ
ትንሺ እደሆሺ
ሌላውን ተይና እኔ ላፍቅርሺ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 817
#ድንቄም_ባለቅኔ
ለፀሐይ ጨረቃ ቅኔ እየዘረፈ
ምነው ለሰው ሲሆን ቀለሙ ነጠፈ
የእኔ ዘመን ጥበብ ሰውን የዘነጋ
ለጨርቃ ውበት እጁን የዘረጋ
ከዋክብትን ጠቅሶ ፀሐይ አወድሶ
ከጨረቃ ደርሶ ሰማያትን ዳሶ
በምናብ ሲዋትት እንቅልፍ አልባ ሌሊት
እንዴትስ አልታየው? የሰው ልጆች ውበት
ማሽቃበጥ ነው እንጂ ህሊና ባይነቃ
ስዎች አይበልጡም ወይ ከፀሐይ ጨረቃ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 817
የተረገጠ እውነት በጊዜ ውስጥ እግር
ታፍኖ የቆየ በሆታ ግርግር
ትንሽ ጋብ እንዳለ የጭብጨባ ጩኸት
እረጭ ሲል ውሸት ይናገራል እውነት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 817
#ጓደኛ
ታማኝ እውነተኛ ገመና ደባቂ
ችግርን ተካፋይ ሚስጥርን ደባቂ
መስታዎት ካልሆነ ስህተትን የሚያሳይ
ለመወደድ ብሎ ከሆነስ አስመሳይ
ለጥቅም ካደረ ከንቱ ጓደኝነት
ነፃነት ያለበት ጌጥ ነው በቸኝነት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
Available now! Telegram Research 2025 — the year's key insights 
