ኢትዮጲክ -Ethiopique
Open in Telegram
2 550
Subscribers
-124 hours
-247 days
-12230 days
Posts Archive
2 550
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል አባል እና ለካውንቲ ኤክስኪዩቲቭ እጩ የሆኑት ዊል ጃዋንዶ የቅርጫት ኳስ በመጫወት ላይ ሳሉ የልብ ድካም (Heart Attack) አጋጥሟቸው ወደ ሆስፒታል ከተወሰዱ በኋላ በማገገም ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ። ስለ ጤና ሁኔታቸው እና ስለሚቀጥለው ሂደት የተሰጠውን ሙሉ መግለጫ ሊንኩን ተጭነው ያንብቡ።
ዝርዝሩ 👇🏾
https://ethiopique.com/will-jawando-recovering-after-heart-attack/
2 550
የ2026 የኢትዮጵያ ቀን በዓል በሲልቨር ስፕሪንግ ቬተራንስ ፕላዛ በድምቀት በመካሄድ ላይ ይገኛል! ድንኳኖች እየተተከሉ፣ የሙዚቃ፣ የፋሽን ትርኢት እና የህፃናት መርሃ ግብሮች ደምቀው ቀጥለዋል። ከቤተሰብዎ ጋር በመገኘት የዚህን ልዩ ቀን አካል ይሁኑ! ሙሉውን ጽሑፍ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ።
https://ethiopique.com/ethiopian-day-festival-2026-silver-spring-veterans-plaza/
2 550
+2
በወርሃዊ የመንገድ ጽዳት መርሃ ግብራችን በመገኘት ላካፈላችሁት ሃይል እና ጉልበት እንዲሁም ለተሰባሰባችሁ የማህበረሰባችን አባላት እና ጎረቤቶች ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን። በተጨማሪም ከእኛ ጋር በመሆን በመሳተፍ መልካም ውይይት ስላደረጉ የሞንጎምሪ ካውንቲ ምክር ቤት አባል ኬት ስዋርት Councilmember Kate Stewart ልዩ ምስጋና እናቀርባለን።
የማህበረሰብን ድምፅ ማዳመጥ ያለውን ትልቅ ዋጋ በጥልቅ እናምናለን፤ ከሕዝብ ተወካዮቻችን እና የቢሮ ኃላፊዎቻችን ጋር በአካልና በቅርርብ ለመገናኘት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር በመቻላችንም ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል። የህብረተሰብ አባላትን በአካል ተገናኝቶ ማነጋገር፣ አብሮ መስራት እና አካባቢያችንን መንከባከብ ሁልጊዜም እንደ ባህል መልመድና ለልጆቻችንም አርአያ መሆን ያስፈልጋል::
2 550
የሞንጎምሪ ካውንቲ የአደጋ ጊዜ ማናጅመንት እና የሀገር ውስጥ ደህንነት ቢሮ (Office of Emergency Management and Homeland Security) ለአንዳንድ የ'Alert Montgomery' የድንገተኛ አደጋ መረጃዎች በድረ-ገጽ ላይ የተመሰረተ የትርጉም አገልግሎት መጀመሩን ዛሬ ሴፕቴምበር 4 አስታውቋል። በአዲሱ አገልግሎት ከተካተቱት ቋንቋዎች መካከል አማርኛ አንዱ ነው።
ዝርዝሩ 👇🏾
https://ethiopique.com/2026-09-04-montgomery-county-emergency-alert-translation-amharic/
2 550
የሜሪላንድ ትራንዚት አስተዳደር (Maryland Transit Administration - MTA) ከሰኞ፣ ሴፕቴምበር 28፣ 2026 ጀምሮ በሳምንቱ የስራ ቀናት በብሩንስዊክ መስመር (Brunswick Line) ጣቢያዎች እና በባልቲሞር ካምደን ጣቢያ (Baltimore Camden Station) መካከል በቀጥታ የሚጓዙ የ MARC ባቡሮችን ማስተናገድ ይጀምራል።
ዝርዝሩ 👇🏾
https://ethiopique.com/2026-09-03-new-marc-trains-brunswick-baltimore/
2 550
በቨርጂንያ የአርሊንግተን ካውንቲ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች እና የሕዝብ ዩኒቨርሲቲዎች፦ ብቁ ለሆኑ ፕሮጀክቶች እስከ $25,000 የሚደርስ የምግብ ዋስትና ድጋፍ (Food Security Grant) የገንዘብ ድጋፍ አዘጋጅቼያለሁ ብሏል።
የአርሊንግተን ካውንቲ የምግብ ዋስትና ስትራቴጂክ ዕቅድን (Food Security Strategic Plan) ለሚደግፉ ሥራዎች በድምሩ $150,000 የሚሰጥ ይሆናል።
🗓️ የማመልከቻው ማብቂያ ጊዜ፦ ኦክቶበር 5, 2026 በ 10 pm ላይ።
ድርጅትዎ በምግብ አቅርቦት ተደራሽነት፣ ርሃብን በማስታገስ ወይም በማህበረሰብ የምግብ ዋስትና ላይ የሚሰራ ከሆነ፣ ወይንም ያን መሰል ፕሮጀክቶች ይዘው መቅረብ ከፈለጉ የዚህን ዜና ዝርዝር ሊንኩን ተከትለው በመሄድ ያንብቡ። ድርጅቶች ከአርሊንግተን ውጪ የተቋቋሙ ቢሆኑም ማመልከት ይችላሉ። https://ethiopique.com/2026-09-02-arlington-opens-food-security-grant-applications/
2 550
በማህበረሰባችን ውስጥ የአእምሮ ጤና ተግዳሮቶች እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በደረሱበት በዚህ ወቅት፣ በውሳኔ ሰጪነት ጠረጴዛ ዙሪያ የእኛ ድምጽና ውክልና መኖር ከምንጊዜውም በላይ ወሳኝ ነው። የሞንጎምሪ ካውንቲ የአእምሮ ጤና አማካሪ ኮሚቴ 14 ክፍት ቦታዎችን ለማሟላት አመልካቾችን እየፈለገ ይገኛል። ፖሊሲዎች፣ በጀቶች እና አገልግሎቶች ማህበረሰባችንን በሚጠቅም መልኩ እንዲቀረጹ ቀጥተኛ ተፅዕኖ ለመፍጠር እባካችሁ አመልክቱ፤ በቦታው ለማገልገል ካልቻሉ ደግሞ ለዚህ ሚና ብቁ ናቸው ለሚሏቸውን ሰዎች በማጋራትና ሼር በማድረግ አጋርነታችሁን አሳዩ። ማመልከቻው እስከ ሴፕቴምበር 21, 2026 ድረስ ክፍት ነው። ሙሉ መረጃውን እና የማመልከቻውን ሊንክ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ። https://ethiopique.com/montgomery-county-mental-health-advisory-committee-applicants/
2 550
ማስታወቂያ
ጆንስ ሆፕኪንስ የነርሲንግ ትምህርት ቤት (Johns Hopkins School of Nursing) በውጭ አገር የተወለዱ ስደተኛ ሴቶች ስለ ቢሼፕ (BSHAPE) የምርምር ጥናት የበለጠ እንዲማሩ እየጋበዘ ይገኛል።
ዕድሜዎ 18 ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ፣ የማንኛውም ዘር ወይም ዜግነት ያላቸው በውጭ አገር የተወለዱ ስደተኛ ሴት ከሆኑ፣ ደጋግመው ለሚከሰቱ አስጨናቂ የሕይወት ተሞክሮዎች ተጋልጠው የሚያውቁ ከሆነ፣ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ኮምፒውተር ወይም ስማርት ስልክ ከኢንተርኔት ጋር መጠቀም የሚችሉ ከሆኑ ለዚህ ጥናት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እና ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ፦ https://nursing.jhu.edu/bshape/bshape-about-the-research-study/
ለጥያቄዎች በ 443 203 8628 ይደውሉ ወይም በ bshape@jhu.edu ኢሜይል ያድርጉ።
2 550
ሴፕቴምበር 11 ከ25 ዓመታት በኋላ፦ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ደስታ፣ ዓለም አቀፍ ሀዘን እና የማይረሱ የሦስት ኢትዮጵያውያን ህይወት። በዚያ አስከፊ ጥቃት ህይወታቸውን ያጡትን እስከዳር መላኩን፣ ጀማል ለገሰ ዴሳንቲስን እና ዶ/ር የኔነህ በትሩን እንዲሁም የተከፈለውን መስዋዕትነት እና የተቋማትን ለውጥ የሚዘክረውን የ9/11 መታሰቢያ ልዩ ሙሉ ዘገባ ሊንኩን ተጭነው ያንብቡ።
https://ethiopique.com/september-11-25-years-ethiopian-new-year-remembrance/
2 550
የአርሊንግተን ካውንቲ ቅዳሜ፣ ሴፕቴምበር 5፣ 2026 ለሚካሄደው 24ኛው ዓመታዊ የአርሊንግተን ፖሊስ፣ እሳት አደጋ፣ ሸሪፍ እና የድንገተኛ አደጋ መገናኛ ማዕከል (ECC) በፔንታገን እና በክሪስታል ሲቲ ዙሪያ የታቀዱ የ9/11 መታሰቢያ የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድርን በማስመልከት የመንገድ፣ የመውጫና መግቢያ መንገዶች (ramps) እና የፓርኪንግ ገደቦች መኖራቸውን አስታውቋል።
ዝርዝሩ 👇🏾
https://ethiopique.com/2026-08-28-arlington-road-closures-memorial-run/
2 550
በቤተስዳ I-270 አውራ ጎዳና ላይ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የሁለት ቨርጂንያ ሴቶች ህይወት አለፈ
ዝርዝሩ 👇🏾
https://ethiopique.com/2026-08-30-bethesda-wrong-way-crash-two-virginia-women-killed/
2 550
የኢትዮጲክ አዲሱ የዜና መጽሔት (Newsletter) ነገ ጠዋት ለተመዝጋቢዎቻችን በቀጥታ በኢሜይል ይላካል! እርስዎም ይህ እትም እንዳያመልጥዎ ዛሬውኑ ይመዝገቡ (ሰብስክራይብ ያድርጉ)።
በነገው እትማችን ውስጥ ከሚካተቱት ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች መካከል፦
*የማህበረሰብ ድጋፍ፦ የሞንጎምሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤት ተማሪዎቹ ሚካኤልና ኒኮላስ ለስደተኞች እያደረጉት ስላለው አርዓያነት ያለው ድጋፍ፤
*አዲስ የግብር ሕግ፦ ከጃንዋሪ 2027 ጀምሮ በሜሪላንድ ተቀጣሪዎች ደሞዝ ላይ ተፈጻሚ ስለሚሆነው አዲስ ታክስ ዝርዝር መረጃ፤
*የትራንስፖርት ወሬዎች፦ የሞንጎምሪ ካውንቲ የሬድ ላይን (Red Line) ባቡር ጥገና መጠናቀቅን ተከትሎ የቀረቡ አማራጭ አውቶቡሶች እንዲሁም የራይድ ኦን አዳዲስ መስመሮች ማሻሻያ፤
*የስደተኞችና የፌደራል ጉዳዮች፦ የቨርጂኒያ ሜዲኬይድ አዳዲስ አሰራሮች
ነገ ጠዋት ወደ ኢሜይል ሳጥንዎ በቀጥታ እንዲደርስዎ አሁኑኑ ይመዝገቡ!
ሰብስክራይብ ለማድረግ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦
https://mailchi.mp/eef309e2301b/ixe7m6uotn
2 550
የፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲ ዲስትሪክት 8 የዩቲሊቲ ክፍያ ዕገዛ ማመልከቻ ማለቂያ ቀን ኦገስት 31 መሆኑ ተገለጸ
https://ethiopique.com/2026-08-29-prince-georges-county-district-8-utility-assistance/
2 550
በአሜሪካ በመንግስት ጥበቃ የሚደረግላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የዱር ፈረሶች በአዲሱ የትራምፕ አስተዳደር መመሪያ መሰረት በዝቅተኛ ዋጋ ለግል ገዢዎች ከተሸጡ በኋላ ወደ ቄራ መወሰዳቸውን ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ይፋ አደረገ። ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ። https://ethiopique.com/federally-protected-wild-horses-sold-slaughter-investigation/
2 550
ሞንጎመሪ ኮሌጅ ቅዳሜ ኦገስት 29 የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት አቀባበል በዓልን ለማክበር ፕሮግራም ያዘጋጀ ሲሆን፤ ይህም ቤተሰቦችንና የማህበረሰብ አባላትን ለአንድ ከሰዓት የኢትዮጵያ ባህል፣ ሙዚቃ፣ የምግብ ወጎች እና የማህበረሰብ ሀብቶች አንድ ላይ በማሰባሰብ ነዋሪዎች የሚዝናኑበትና የሚማሩብት ፕሮግራም ይሆናል ተብሏል።
ይህ ነፃ የማህበረሰብ አቀፍ በዓል ከ11 am እስከ 3 pm በሞንትጎመሪ ኮሌጅ ታኮማ ፓርክ/ሲልቨር ስፕሪንግ ካምፓስ፣ 7625 Fenton Street, Takoma Park, Maryland ውስጥ ይካሄዳል።
ዝግጅቱ በኮሜድያን ክበበው ገዳ የታጀበ ፕሮግራም ሲሆን በተጨማሪም የኢትዮጵያ ባህላዊ ሙዚቃና መዝናኛዎች፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ ቁሶች ነጋዴዎችና የንግድ ተቋማት፣ ለማህበረሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ ሌሎች ተቋማት የሚሳተፉበት ሲሆን ባህላዊ የቡና ስነ-ስርዓት፣ ባህላዊ ኤግዚቢሽኖች እና ለቤተሰብ ተስማሚ የሆኑ ፕሮግራሞችን ያካትታል።
ሞንጎመሪ ኮሌጅ ለWorkforce Development and Continuing Education (WDCE) ፕሮግራሞቹ እና ለEducational Opportunity Center (EOC) የተለዩ የመረጃ መስጫ ጠረጴዛዎችን ያዘጋጃል። ኢትዮጲክን ጨምሮ ሌሎች የማህበረሰብ ድርጅቶችም ተጨማሪ መገልገያዎችንና መረጃዎችን ይዘው በቦታው ይገኛሉ።
አዘጋጆች እንዳሉት ከሆነ ይህ በዓል የማህበረሰቦች መቀራረብን የሚያበረታታ ከመሆን ባለፈ ፤ ለአካባቢው ነዋሪዎች የኢትዮጵያን ባህል እያከበሩ በአካባቢው ስለሚገኙ የትምህርት፣ የሥራ እድልና የማህበረሰብ ሀብቶች መረጃ የሚያገኙበትን ዕድል ይሰጣል።
ዝግጅቱ የኢትዮጵያን ባህል ለማክበርና በመላው የዲኤምቪ (DMV) አካባቢ ከሚገኙ ሌሎች ሰዎች ጋር ለመገናኘት ፍላጎት ላላቸው ቤተሰቦች፣ ተማሪዎች እና የማህበረሰብ አባላት በሙሉ ክፍት ነው።
2 550
ሜታ ከህፃናት ደህንነት እና ሱስ አስያዥ ናቸው ከተባሉት ከፌስቡክና ኢንስታግራም ጋር በተያያዘ የቀረቡበትን ክሶች በድርድር ለማስቆም እስከ $17.1 ቢሊዮን ለመክፈል ታሪካዊ ስምምነት አደረገ። በዚህ ስምምነትም መሰረት በኢንስታግራም እና በፌስቡክ ላይ ለታዳጊዎች አዳዲስ ጥብቅ ገደቦች የሚጣሉ ሲሆን ዲሲ፣ ሜሪላንድ እና ቨርጂኒያም በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር የካሳ ክፍያ ያገኛሉ። ዝርዝሩን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ። https://ethiopique.com/meta-agrees-to-17-billion-settlement-over-child-safety/
2 550
ማስታወቂያ.. ቤት ለመግዛት ያስባሉ? ከ20% ባነሰ ዳውን ፔይመንት እንዴት መግዛት እንደሚችሉ ለማወቅ መአዛን በስልክ ቁጥር 571-250-9612 ደውለው ያናግሩ
2 550
ኦገስት 31 የተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት መመለስ በማስመልከት በትምህርት ቤት ዞኖች የተማሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ በአርሊንግተን 10 ተጨማሪ የፍጥነት መቆጣጠሪያ ካሜራዎች ተተከሉ! የ$100 ቅጣት የሚጣልባቸው አሰራሮች፣ የ30 ቀናት የማስጠንቀቂያ ጊዜ እና ካሜራዎቹ የሚገኙባቸውን 35 ጎዳናዎች ሙሉ ዝርዝር ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ። 👇🏾
https://ethiopique.com/arlington-school-zone-speed-cameras-2026-27/
2 550
ለዶ/ር ብርኃኔ የህግና መሰል ድጋፎች ለማድረግ የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ ቀረበ. . .- የዶ/ር ብርኃኔን የህግ ክትትልና መሰል ወጪዎች ለመሸፈን ይረዳ ዘንድም የጎ ፈንድ ሚ መዋጮ ጥሪ ለማህበረሰባችን የቀረበ ሲሆን አቅም ያላቸው በዚህ መዋጮ በመሳተፍ ዶ/ር ብርኃኔን እንዲደግፉ ጥሪ ቀርቧል። ዝርዝሩ 👇🏾
https://ethiopique.com/ethiopian-university-maryland-instructor-denied-bond-ice-detention/
