cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ethio eslamic መረጃ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ውድ ተከታታዮቻችን ይህ ቻናል እውነተኛ ኢስላማዊ መረጃ የምናደርስበት ኢስላማዊ ለኢስላም የቆመ ቻናል ነው። 👉ኢስላሙ ውስጥ ሰለ ተከናወኑ እዉነታዎች🇪🇹 👉ለእውነተኛ ኢስላሚክ መረጃ🇪🇹 👉ለፈጣንና ቀልጣፋ መረጃ🇪🇹 👉አለማችን ላይ ስለ ተከሰቱ እውነታዎች🇪🇹 ⛤Comment : @mewuyaya🌍 ⛤for advert : @alefu_boss

Show more
Advertising posts
574
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-2330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
መስጅድ አልባ ከተማ ስርአት ያለው ሀገር ወዳድ ዜጋ ሊያፈራ አይችልም!!!
Show all...
እንግዲህ የአላህ ቤት በዚህ መልኩ ፈርሶ የአላህ ቃል የሙስሊሞች መመሪያ ቁርዓን በዚህ መልኩ ተቀዳዶ ተጥሎል ሀስቡነሏህ ወኒእመል ወኪል!!
Show all...
Repost from "ኡማ ቲቪ " Tv
እንግዲህ የአላህ ቤት በዚህ መልኩ ፈርሶ የአላህ ቃል የሙስሊሞች መመሪያ ቁርዓን በዚህ መልኩ ተቀዳዶ ተጥሎል ሀስቡነሏህ ወኒእመል ወኪል!!
Show all...
Repost from "ኡማ ቲቪ " Tv
Photo unavailableShow in Telegram
መስጅድ አልባ ከተማ ስርአት ያለው ሀገር ወዳድ ዜጋ ሊያፈራ አይችልም!!!
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
⚡️ ቱርካዊቷ እናት ሀቫ ኩል ለህግ ፈተና እያንዳንዱን የመማሪያ መጽሐፍ አብበዋል፤ በሁሉም ክፍል ተገኝተው ለ4 አመታት ትምህርት ተከታትለዋል፤ ፈተናም ተፈትነዋል። ታዲያ ይህን ሁሉ ያደረጉት ለአይነስውሯ የህግ ተማሪ ልጇ ነበር። ይህ ጥረታቸው በዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አድናቆት አግኝቷዋል። ላደረጉት አስደናቂ እና ያልተቋረጠ ድጋፍ ወይዘሮ ሀቫ ከዩኒቨርስቲው የክብር የህግ ድግሪ ከህግ ምሩቋ ልጃቸው ጋር ተቀብለዋል። «አንድ ሰው ወደ ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) መጥቶ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ከሰዎች መካከል ከማንም በላይ መልካም ልውልለት የሚገባ ሰው ማን ነው? ብሎ ጠየቃቸው ረሱልም እናትህ አሉት፣ ከዚያስ አላችው እናትህ አሉት፣ ከዚያስ እናትህ፣ ከዚያስ አላቸው አራተኛው አባትህ አሉት» ሶሒህ ሙስሊም(2548) አላህ ለእናቶቻችን በዱንያም በአኼራም ይዘንላቸው ሀቃቸውንም የምንወጣ ያድርገን። 🤲❤
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ ዓጃይብ ነው‼️ በጆርዳን በአንዱ መንደር ሓብሓብ ያለ ማንም ሻጭ ሰው ለመሸጥ ገበያ ወጥቷል። ዋጋው ለአንዱ ሓብሓብ ሁለት ዲናር ሲሆን ገዢው ያለማንም ሻጭ ገንዘቡን አስቀምጦ ሓብሓቡን አማርጦ ይዞ ይሄዳል። ከዚህ በላይ መታመንና መተማመን ይኖር ይሆን?!
Show all...
«መዘግየት ከመቅረት ይሻላል!» በሚለው ይህን የአሕመዲን ጀበልን ጽሑፍ ላጋራችሁ። «ሸገር ከተማ መስጂዶችንና ሙስሊሞችን የሚያጸዳ ከሆነ፣ ለሙስሊሞች «ፈተና» እንጂ «የኩራት ምንጭ» ፈጽሞ ሊሆን አይችልም! 🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌 መንግስት ሀገርን የሚያስተዳድረው በዜጎች ስም ዜጎችን በመወከል መሆኑ ለሁሉም ግልጽ ነው። ይህ ባይሆን ኖሮ የመንግስት ባለስልጣናት የሚባሉት በጠቅላላ እንደኛው ተርታ ዜጋና፣ ከእያንዳንዳችን የተለየ ምንም መብትም ስልጣን ሊኖራቸው አይገባም ነበር። ሀገር የጋራ መሆኑ ካልተካደ በቀር የሀገር ሀብትና በሀገር ውስጥ ያሉ እድሎች በጠቅላላ የጋራ ናቸው። ይህ ሆኖ ሳለ በመላ ሀገራችን ከተሞች ማስተር ፕላን ሲዘጋጅ ዘወትር ለፕላን አዘጋጆቹ ብቻ ሳይሆን ለፖለቲካ አመራሮቹ ጭምር መስጂድ ብቻ ተለይቶ ትዝ የማይላቸው እስከመቼ ነው? ሕዝበ ሙስሊሙ እንደዜጋና መስጂዶች በሀገሪቱ በሚዘጋጁ ማስተር ፕላኖች ላይ ሆነ ተብለው እየተረሱ፣ የሙስሊሞች ጥያቄዎች መስጂድና ሂጃብ ብቻ ላይ ታጥረው እንዲቀሩ የማድረግ፣ በውጤቱም ዘወትር የሕዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች እነዚሁ ብቻ እንዲመስሉ በማድረግ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎቹ በአቀበት የተሞላ እንዲሆን የማድረግ ስልት መሆኑ ግልጽ ነው። እነዚህ መሠረታዊ መብቶች የሆኑ ጉዳዮች፣ ጥያቄዎች ሳይጠየቁም በፊት «በማስተር ፕላኑ መሠረት እዚህ ጋር መስጂድ ያሳያል» እየተባለ ሊመለሱ ይገባቸው የነበሩ፣ አልያም ከተጠየቁም በቀላሉ ሊመለሱ የሚገባቸው ጥያቄዎች ነበሩ። ሆኖም በመላ ሀገሪቱ ሙስሊሞች መስጊድን በልመና፣ ወይም መሬት በገንዘባቸው እየገዙ ለመስገጃነት በማዋል፣ ባስ ሲልም በትግልና በደም [የመስጂድ ይዞታን ለማስከበር በሚደረግ ትግል በጸጥታ አካላት ሙስሊሞች የሚገደሉበት አጋጣሚ በርካታ ነው] የመጎናጸፍ ጉዳይ ካልቆመ በቀር፣ በሀገራችን የሙስሊሞች መብት ተከበረ ማለት አይቻልም። አንዳንድ ወገኖች መስጂዶች እየፈረሱ ያሉት «ሕገ-ወጥ ስለሆኑ ነው» ይሉናል። ይገርማል! እነኚህንና መሰሎቻቸውን የምንጠይቀው በሀገራችን «ሕጋዊ» የሚባሉት መስጂዶች የትኛቹ እንደሆኑ እንዲነግሩን ነው። አዲስ አበባን ጨምሮ መስጂዶች ለአስርት ዓመታት ሲሰገድባቸው ቢቆይም፣ ካርታ የሚያገኙት በስንት ጥረትና መንከራተት መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው። ከንጉሠ ዘመን ጀምሮ የኖሩት ታላቁ አንዋር መስጂድና ኑር (በኒን ሰፈር) መስጂድን ጨምሮ ሌሎችም በአዲስ አበባ የሚገኙ ጥንታዊ መስጂዶች ካርታ ያገኙት አቶ አርከበ እቁባይ ከንቲባ በኾኑበት በ1990ዎቹ ነበር። ሆኖም አንዋር መስጂድ የተሠራው በጣሊያን ዘመን ሲሆን፣ ኑር መስጂድ ግን ከጣሊያን ወረራ በፊት ነበር በአባቶቻችን የተገነባው። እነዚህ መስጂዶች በህዝበ ሙስሊሙ ያላሰለሰ ትግል ተሰርተው፣ ለዘመናት እየተሰገደባቸው ቢቆዩም፣ ሕጋዊ ካርታ ያገኙት ግን ከበርካታ አስርት ዓመታት እንግልት በኃላ ነበር። በበርካታ ከተሞች በሕዝብ ስም ስልጣን ላይ ያሉ አስተዳደሮች በሚያስተዳድሩት ከተማና ዜጎች በሚኖሩበት አከባቢ ማስተር ፕላኑ ሆነ ብሎ መስጂዶች እንዳይኖሩት ማድረጋቸው ሳያሳፍራቸውና ሳያሸማቅቃቸው፣ የአከባቢው ሕዝበ ሙስሊም በነጻ ሊሰጠው ይገባ የነበረውን የመስጂድ ይዞታ ከግለሰቦች ሳንቲም አሰባስቦ ለመግዛት ሲገደድ ነው የኖረው። ሆኖም ይህንንም ይዞታውን ጭምር «ለመስጊድነት አልተፈቀም፣ ሕገ-ወጥ ነው!» ብለው ሲያፈርሱ በተደጋጋሚ ጊዜ ታይቷል። የሚያሳዝነው ከብዙ ደጅ መጥናትና ዉትወታ በኋላም በሕጋዊ መንገድ ተብሎ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ከሌሎች እጅግ ያነሰ መሬት፣ ማለትም ለአንዱ በካሬ ለሌላው በሔክታር ተለክቶ፣ አድልዎ የተሞላበት አሰራር አሁንም ድረስ መቀጠሉ አሳዛኝ ነው። ይህንና መሰል እኩይ አድሎ የተሞላበት አካሄድና አሠራር መጅሊስና ሕዝበ ሙስሊሙ በጋራ በሚያደርጉት የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ትግል ውጪ ሊለወጥ አይችልም። «ሕገ-ወጥ» ያሉዋቸው መስጂዶች ዛሬ በአንድ ጀምበር ተሰርተው ያደሩ ሳይሆኑ፣ ይልቁንም ሕዝብም መንግስትም እያወቁ ለዓመታት ለአካባቢያቸው ሕዝበ ሙስሊም ግልጋሎት ሲሰጡ የቆዩ ናቸው። ሌላው ቢቀር በአዲስ መልክና በአዲስ ዕቅድ «ሸገር ከተማ» የሚል አዲስ የከተሞች ግንባታ ስለታቀደ እና በከተማው አዲስ ፕላን መሰረት ስፍራው ለመስጊድ ሳይሆን ለሌላ ጉዳይ ተይዞም ከሆነ፣ ፕላኑን ለመጂድ መገንቢያም ምቹ እንዲሆን ማድረግ እንጂ መስጂዶችን ድንገት ተነስቶ፣ ምንም ምክክር ሳያደርጉ በጅምላ ማፍረስ ፈጽሞ ተገቢ አይደለም። የሸገር ከተማ አስተዳደር «በአዲሱ ፕላን መሰረት ለመስጂድ የተመደበው ስፍራ ይህ ነው» እያለ ተለዋጭ መሬት እያቀረበ፣ በውይይትና በስምምነት በአዲሱ የከተሞች ግንባታ ውስጥ መስጂድ እንዲሰራ በማድረግ ጉዳዮችን መቋጨት እንኳ አልፈለገም። ከዚያ ይልቅ በተግባር ያደረጉት ለሃይማኖቱና ለሙስሊሞች ቅንጣት ታክል ክብር ሳያሳዩ መስጂዶችን በጅምላ ወደ ማፍረስ ነው የገቡት። ይህ ሁኔታ ሲታይና በተግባርም በሸገር ከተማ በርካታ መስጂዶችን በጅምላ ለማፍረስ የሚደረገው አሳዛኝ እንቅስቃሴ ሲታይ፣ ጉዳዩ የሕጋዊነት ጥያቄ ሳይሆን ከሸገር ከተማ መስጂድንና ሙስሊሞችን የማጽዳት [አብዛኛው ቤቱ እየፈረሰበት ያለው ሙስሊሙ መሆኑን ከግምት በማስገባት] የአሻጥር እርምጃ አስመስሏል። ይኼን ማሳካት ፈጽሞውኑ በኢትዮጵያ ምድር ከእንግዲህ የማይታሰብና፣ የሸገር ከተማም መስጂድና ሙስሊሞችን ለማጽዳት ቆርጦ ከቀጠለ፣ ከተማው ለሀገሪቱ ግማሽ ለሆነው ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ «ችግር» እንጂ «የኩራት ምንጭ» ፈጽሞ ሊሆን አይችልም!»
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ህምምም! ክብር ለአባቶች! በተለይ የኔ ይለያል👌
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ህዝብ ሲወድህ እንድህ ነው ስትመራው ብትኖር በስስትና በጉጉት ያይሀል እንጅ ጭራሽ አይሰለችህም ሀቀኛ፣እውነተኛና ለሚመሩት ማህበረሰብ ታማኝና ቅን የሆኑ መሪዎች ሁል ጊዜም ቢሆን ህዝብ ከጎናቸው ይሆናል። ዛሬ ቱርኪዮ ኢስታቡል ላይ ለረሲብጠይብ ኤርዶጋን ድጋፍ የወጣውን የህዝብ ማዕበል ተመልከቱልኝማ አጂብ ኢንሻ አላህ የድሉን ውጤት ከቀናት በኋላ የምናየው ይሆናል👉❤👈
Show all...
01:04
Video unavailableShow in Telegram
ከ2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ቱርካውያን ለኤርዶጋን ድጋፍ በኢስታንቡል ወጥተዋል። ይህ በታሪኩ ትልቁ ነው! ምርጫው አንድ ሳምንት ቀርቶታል! አላህ ያግዘው!! የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇 https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf
Show all...
2.27 MB