cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Tᴏʟᴇʜᴀ Aʜᴍᴇᴅ (ጦለሃ አህመድ)☪️

Ethɪo Short Dᴀ'wa ለአስተያየትዎ እና ለጥያቄያቹ ጦለሃን ለማግኘት 👉🏿 @tolehaahmedbot👈🏿 ቢንት አብደላህን ለማግኘት 👉🏿 @bintabdellahbot👈🏿

Show more
Advertising posts
4 438
Subscribers
+424 hours
+327 days
+15230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

☁️ .. ‏إن صوت القرآن في الليل الساكن .. يُحرّك في قلوبنا حجارة الغفلة فتنكشف لنا أسرار مواعظه لنحيا من جديد 🤍! • تراتيل الشيخ #منصور_السالمي • من سورة التوبة https://t.me/tolehaahmed
Show all...
ልብን ማፅዳት
ከአማርኛ የፅሁፍ ትርጉም ጋር
ሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል -ዑሠይሚን አላህ ይዘንላቸው https://t.me/tolehaahmed
Show all...
"ልጆቻችሁን መስጂድ በመሄድ ላይና ቁርዓንን  በመሀፈዝ አነሳሱ ። የእነሱን አምሳያ አጅር ታገኛላችሁ።" 📕 الإمام الألباني أحكام الجنائز 126 https://t.me/tolehaahmed
Show all...
ከላይ የተጠቀሱትን ጥያቄዎች ከመለስክ በኃላ አጠቃላይ ነጥቦችህ ስንት ናቸው?Anonymous voting
  • 6/5 ነጥብ
  • 7/8 ነጥብ
  • 9/10/11 ነጥብ
  • 12/13 ነጥብ
  • 14/15 ነጥብ
0 votes
🌕 ከሰዎች ጋር ያለህን ግንኙነት የበለጠ ለመረዳት የሚያስችሉህ ጥያቄዎች ናቸው ። ስለራስህ ትክክለኛ የሆነውን መረጃ በመመለስ ውጤትህን ነጥቦችን በመያዝ ማወቅ ትችላልህ ። 1. የብዙ ሰዎች እይታ ወዳንተ ያተኮረ መሆኑን ስትረዳ ምን ይሰማሀል ? - እፍረት ( አንድ ነጥብ) - ምንም የተለየ ነገር አይሰማህም ( ሁለት ነጥብ) - በራስ መተማመንና ደስ የሚል ስሜት ( ሶስት ነጥብ) 2 .ብዙ ጊዜ እይታን የሚስብ አለባበስ ትለብሳለህ? - አው ሁሌም ( ሶስት ነጥብ) - በተወሰኑ አጋጣሚዎች ብቻ ( አንድ ነጥብ) - በጭራሽ ( ሁለት ነጥብ) 3. ስብስሶች የበዙበት ቦታ ላይ ስትሆን ድምፅህን ዝቅ አድርገህ ነው የምታወራው? - አው… አንዳንዴም ንግግሬ እንዲሰማ ልደግመው እችላለሁ ( አንድ ነጥብ) - አይ… ድምፄን ዝቅ አድርጌ የማወራበት ምክንያት የለም ( ሶስት ነጥብ) - አንዳንዴ ( ሁለት ነጥብ ) 4.ብቻህን ስትሆን ምን አይነት ስሜት ይሰማሃል? - ከባድ የሆነ ብቸኛነት ( አንድ ነጥብ) - በእርፍትና መረጋጋት ( ሶስት ነጥብ) - ነፃነት (ሁለት ነጥብ) 5. ሰዎች ሲተቹህ ምን ይሰማሀል ? - ቅሬታ ( ሁለት ነጥብ) - ምንም አይመስልህም ( አንድ ነጥብ) - ደስታና ራስህን ለማሻሻል ጥሩ አድል እንደሆነ ታምናለህ ( ሶስት ነጥብ) ---------------------- ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 ┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓        @tolehaahmed ┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛
Show all...
"ما عُولِجَ جُرحٌ بشيءٍ أنفَعَ من القُرآن"
Show all...
ልጆች ጋር ለሚያጋጥሙን ችግሮች መፍትሔዎ  (2)  🔹ልጅሽ ሲያወራ ይኮላተፋልመፍትሔው ፦  እያሞገሽ በብዛት አበረታቸው። በሚያወራ ጊዜ መሳቅ የለብሽም። በተወሰነ ጊዜ መቀረፍ ካልተቻለ የንግግር ባለሙያ ጋር መቅረብ ያስፈልጋል ። 🔸ልጅሽ አይታዘዝሽም❔ መፍትሔው ፦ ወላጆችሽ በህይወት ካሉ እነሱን በመንከባከብ አሳዪው።  እንዲሁም " ንግግሬን ከሰማህ እንዲህ እንዲህ አደርግልሀለሁ " አትበዪው። ይህ በጥቅም ብቻ መስራት እንዳለበት ( ሙስናን)  ያስተምረዋል። 🔹ልጅሽ ይሰርቃል ❔ መፍትሔው ፦ በጭራሽ " ሌባ " ብለሽ እንዳትጠሪው። ለብቻው ቀስ ብለሽ ምከሪው። የወሰደውንም እንዲመልስ አድርጊው ።እንዲሰርቅ የሚያደርጉትን ምክንያቶች ፈልጊና አክሚያቸው ።በምትችዪው መጠን ፍላጎቱን ለማሟላት ሞክሪ ። ሌብነትም አላህ ዘንድ ምን ያህል ከባድ ወንጀል እንደሆነ አስረጂው ። 🔸ልጅሽ የጉርምስና ምልክቶች እየታዩበት ነው❔ መፍትሔው ፦ የጠሃራን አደቦች አስተምሪው ። በራስ መተማመኑንም አዳብሪለት ። በድምፁም ሆነ በሁኔታው አታሹፊበት። ለሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ ሃላፊነት ሊሰማው እንደሚገባው አሳወቂው ። 🔹ልጅሽ ወደ ሴቶች ባህሪ ያዘነብላልመፍትሔው ፦  ከሴቶች ጋር ያለውን ግንኙነትና ውሎን ቀንሺ ። በብዛት የወንዶች ስብስቦች ጋር  እንዲውል አድርጊው። መስጂድ እየሄደ እንዲሰግድም አበረታችው ። 🔸ልጅሽ ማንነቱ ደካማ ነው ❔ መፍትሔው ፦ በራስ መተማመን እንዲኖረው አድርጊ ።  የተለያዩ ሃላፊነቶችን ስጪው። ደህንነት እንዲሰማው አድርጊ ። ስፓርት የሚሰራባቸው ቦታዎች ይሂድና ይሳተፍ ። የስፓርት ድባቡ በራሱ ጥንካሬን ይሰጠዋል። 🔹ልጅሽ የኩራት ስሜት ይስተዋልበታል ❔ መፍትሔው ፦ ኩራት አላህ ዘንድ እጅግ የተጠላ ተግባር እንደሆና ሰው ሁኖ ማንም ሊኮራ እንደማይገባው አስረጂው። ረሱልንም የመተናነስ ተምሳሌት እንደሆኑና ያለበት ኒዕማ በአጠቃላይ ለእሱ የተገባ ሁኖ ሳይሆን ከአላህ የተዋለለት እንደሆነ አሳውቂው። ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 ┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓        @tolehaahmed ┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛
Show all...
ያስቸገረኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር! ተወልዶ ካደገበት ሃገሩ በተፈጠሩ ማሕበራዊ ቀውሶች ምክንያት ወደሌላ ሃገር በስደት ለመሄድ የቆረጠ አንድ ሰው ረጅም፣ አድካሚና አስፈሪ የሆነን በረሃ ለቀናት በእግሩ በመሄድ ካቋረጠ በኋላ እጅግ ደክሞና ዝሎ ነበር፡፡ በመጨረሻም በደረሰበት አንዲት ከተማ ውስጥ በተሰጠው እርዳታ ትንሽ አገገመ፡፡ የዚህን ሰው ጉዞ የሰማና ለሕብረተሰቡ ለማቅረብ የፈለገ አንድ ጋዜጠኛ አገኘውና አንድን ጥያቄ ጠየቀው፡፡ “ተጉዘህ የመጣኸው በረሃ ብዙ ሰው የማይደፍረው በረሃ ነው፡፡ ለመሆኑ በመንገድህ ላይ በጣም የጎዳህና ያስቸገረህ ውኃ ጥም ነበር? ምግብ ማጣት ነበር? አውሬ ነበር? ሽፍቶች ነበሩ? ወይስ . . . ? የዚህ ስደተኛ መልስ ለጋዜጤኛው ያልተጠበቀ ነበር፡፡ በዚህ አደገኛ በረሃ አቋርጬ ስመጣ በጣም ያስቸገሩኝ የጠቀስካቸው ትልልቅ ነገሮች አልነበሩም፡፡ ጉዞየን በጣም አድካሚና አስቸጋሪ ያደረገብኝ በእርምጃዬ ወቅት ጫማዬ ውስጥ እየገባ የሚቆረቁረኝና አላራምድ ያለኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር፡፡ የሕይወት ጉዞም እንዲሁ ነው! አብዛኛውን ጊዜ የሚያስቸግረን፣ የሚቆረቁረን፣ አላራምድ የሚለንና ከዓላማችን የሚጎትተን ችግር ትልልቁ አይደለም፡፡ በየቀኑ የሚያጋጥሙን ጥቃቅን “አሸዋዎች” ናቸው፡፡ ትንንሽ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ባህሪይ፣ ትንንሽና አናሳ ወሬን የሚያወሩ ሰዎች ሁኔታ፣ ትንንሽና ስሜትን የሚነካኩ የየቀን ገጠመኞች . . . ጉዟችንን አዳጋችና አድካሚ ያደርጉታል፡፡ “በትንንሽ” ሰዎችና ሁኔታዎች ሳትበገሩ ትልቁ የሕይወት ስእልና ዓላማችሁ ላይ በማተኮር ወደፊት መገስገስን ያወቃችሁበት ጊዜ ዋናውን የሕይወት ድል የተጎናጸፋችሁበት ጊዜ ነው፡፡ በርቱ! #copy https://t.me/tolehaahmed
Show all...
Tᴏʟᴇʜᴀ Aʜᴍᴇᴅ (ጦለሃ አህመድ)☪️

Ethɪo Short Dᴀ'wa ለአስተያየትዎ እና ለጥያቄያቹ ጦለሃን ለማግኘት 👉🏿 @tolehaahmedbot👈🏿 ቢንት አብደላህን ለማግኘት 👉🏿 @bintabdellahbot👈🏿

የአላህ ዲን በክርክር ላሸነፈ ሰው አይደለም!!
ከአማርኛ የፅሁፍ ትርጉም ጋር
ሸይኽ ዶ/ር ዐብዱ-ር'ረዛቅ ኢብኑ ዐብዱ-ል-ሙሕሲን አል-ዐባድ አል-በድር አላህ ይጠብቃቸው
Show all...