en
Feedback
ዳዊት ጌታቸው።(እይታ)

ዳዊት ጌታቸው።(እይታ)

Open in Telegram

ፍቅር!ሰላም!ግጥም!እይታ! sad! ለ አስተያየት @addemiinilik

Show more
452
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
❤️‍🩹
❤️‍🩹

ለደከመ
ለደከመ

ህግጋቱን ሳልጠብቅ እንኳን፣አለም አሸንፎኝም፣ከ ሀጥያቴ በፍቅር ወድቄም፣የሰራኝን መኖሩን አየዘነጋውትም፣ከዘረጋልኝ ጎዳና አሻፈረኝ ብዬ ወጥቼም፣በችግሬ ሰአት ድረስልኝ ብዬው ሲደላኝ እየረሳውትም፥አልተወኝም።ይወደኛል።ምን አይነት ሞቶ ማሸነፍ ነው....ምን አይነት መርቀቅ.....

እድሜ ላንቺ....💙
እድሜ ላንቺ....💙

በ ደግነትህ ግደላቸው!ትንሳኤ አይኖራቸውም @dawitview ዳዊት ጌታቸው©

ሲጋራ የሚያጨስ ወንድ እወዳለው አለችኝ....ከ ፓኮ ውስጥ አንድ ኒያላ እያቀበለችኝ...እኔ ኮ አጭሼ አላውቅም አልኳት....ፈራው...ሲጋራውን ተቀበለችኝ እና ከንፈሬ መሀል ቀበረችው ላይተሯን እውጥታ ለኮሰችው እና ቀስ ብለህ ሳብ አትንቀጥቀጥ አለችኝ....ሳብኩት ስስበው በርካታ ጭስ ወደ ሳንባዬ አመለጠ...ከባድ ሳል....አይኔ እንባ...ትስቅብኛለች....አስወጣው ጭሱን አለችኝ...እላዩዋ ለይ ተነፈሰኩት አይኗን ጨፍና ሳበችው። የሲጋራም፤የሷም ሱስ ያኔ ጀመረኝ.... ዳዊት ጌታቸው @dwitview

ከ መፅሀፍ ቅዱስ እጅግ የምወዳትን ቃል ላካፍላችሁ "እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን፤እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው..."። ሮሜ 1:28 ይሔ ማለት እንግዲህ እግዚአብሔርን ወይም ፈጣሪአችንን ለማወቅ በወደድን ቁጥር ደግሞ ለሚረባ አእምሮ አሳልፎ ይሰጠናል የሚል አመክንዮ(logic)አለው ማለት ነው።

እድሜ እና ድንቁርና ለ ራስ አይታዩም @dawitview

ጥቁር ጁምአ

ጥቁር ጁምአ😭

ዠግና ገጣሚ ናት በነገራችን ለይ😎

ድቅድቅ ጨለማ ለይ ረጅም ሰአት አይኗን ተክላ ቆማለች።አንዳንዴ ብቻዋን ፈገግ፣ከዛ ኮስተር ትላለች።ይነፍሳል።የለበሰችው ስስ ልብስ ጀርባው እንደ ጫማ ማሰሪያ ባለ ጥልፍልፍ የተዘጋ ነው(መፍታት ነበር!ይላል ውቃቢዬ) ከ ሗላዋ እንዳለው አላወቀችም!!አይበርዳትም?!! ጋቢ ልደርብላት?፣ከ ሗላ ልቀፋት?፣ሹራቤን አውልቄ ላከናንባት?፣ኩንታል ከሰል ላንድድላት?፣የሞቀ ገንዳ ልሙላላት?፣ሻይ በኩባያዋ ላቅርብላት?፣የአፋርን ኤርታሌ ቆንጥሬ ላምጣላት?!እያልኩ በሀሳብ ስወጠር....ግባ እና ተኛ!!!አለችኝ(እንዴት አወቀች ከ ጀርባዋ እንዳለው😒) @dawitview [ዳዊት ጌታቸው]

​​​​❍●●◦መአዛሽ ፈወሰኝ◦●●❍ ጎራዳ አፍንጫየን ጎራዴ አፍንጫየን ከሰገባው ስቤ ስምግሽ ቀርቤ አንገትሽ ገነት ዛፍ ጡትሽ ደብረ -ከርቤ እፎይ!!!!! እንዲያው ሲፈርድብኝ -ቤቴ አዲስአበባ ሰማዩ ጥንብ ነው-መሬቱም አዛባ አይን ጆሮ ምላስ- ለኑሮ ሳያንሰኝ ምን በደየው ጌታ -አፍንጫ ለገሰኝ እያልሁኝ ሳማርር- አንቺን ልኮ ካሰኝ መዳኒት ሆነና -መአዛሽ ፈወሰኝ!! በእውቀቱ ስዩም©

ለ ፍልሰታ የሰገድኩት እንዳይመስልሽ ለ ሀገር ልማት አልያ አሳስቦኝ መናጋቱ ሰኔ ዝናብ መዘግየቱ መች ጨነቀኝ። ለ አብይ ጦም ያከፈልኩት መስሎሽ ነው ወይ ላለኝ ሀጥያት? መጠበቄ ትእዛዛቱን መፅደቅ አምሮኝ ገነት ስቦኝ አይደለም። መዳከሜ በ ጦም ጅራፍ እንዳይሽ ነው በኔ በራፍ ስታልፊ..... @dawitview ዳዊት ጌታቸው

አሞኝ ብታዪ አትጨነቂ። ጣር ቢያጣድፈኝ ውጋት ቢሰፋኝ... አይደለም ጠበል አይደለም ከርቤ የሚያስታግሰው ገብቶ ከልቤ ደክሜ ብታይ ደርሶ ግዜዬ ጭራሽ አትፍሪ። ይረዳኝ መስሎሽ ሀኪም አትጥሪ። ብቻ... ፈ ገ ግ በይ...... ዳዊት ጌታቸው @dawitview

ብቻ ቀርቦ ጉርሻ ልምዱን ባልኩራራበትም ሰው ራቀኝ ብሎ መቼም እጅ አፉን አይስትም ለምን ስል ልከፋ ደግሞ ልዘን ምን በወጣኝ አንድ አንቺን ነው እንጂ ሀቄን አያሳጣኝ!!!!!