cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

እምየ ተዋሕዶ ሚዲያ - Emye Tewahedo Media

እሔ የቴሌግራም መንፈሳዊ ቻናላችን ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሀይማኖታችን ምንማማርበት መንፈሳዊ መድረክ ነው። ለሌሎች ያጋሩ፣ አዳዲሶችም ተቀላቀሉ(join) አድርጉ።

Show more
Advertising posts
1 780Subscribers
+1724 hours
+487 days
+14230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ብፁዕ አቡነ ሉቃስ በሰላም ገብተዋል
Show all...
12
በድጋሜ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን
Show all...
9
አህዮች ወደ ቤተመቅደስ አይገቡም ነበር። ውርንጭላዋም አህያዋም ግን ገቡ ያልተማሩ ያልተገሩ አሕዛብ ካለማመን ወደ ማመን (ክርስትና) ገቡ።
Show all...
🙏 6
ሆሳዕና በአርያም! እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን። ሰላም አደራችሁ ውድ ኦርቶዶክሳዊያን
Show all...
7
፰ኛዋ ቀን በሳምንቱ ውስጥ ሰባት ቀናት ብቻ አሉ። አንዱ ቀን ሌላውን እየተከተለ ይመላለሳል። እኩል ብርሃን እኩል ጨለማ አላቸው። ክርስቶስ የሚመጣባት ቀን ከነዚኽ ቀናት የተለየች ቀን ናት። ስምንተኛ ቀን ትባላለች። ከኋላዋ የሚከተል ከፊቷም የሚመጣ ቀን የለም። ሰኞ እሑድን ትቀድማለት ቅዳሜ እሑድን ትከተላለች። ስምንተኛዋ ፰ ቀን ግን ከነዚኽ ኹሉ ትለያለች። የዚኽ ዓለም ሥርዓት ሁሉ ያልፍባታል። ዓለም የተፈጠረባት ቀንም ናት። ፍጥረትን ወደ ቀደመ ክብሩ የሚመልስባት ዘለዓለማዊ መንግሥቱ የሚጀምርባት መጀመሪያም መጨረሻም ቀዳማዊትም ደኀራዊትም ናት። ለዘለዓለም ሳትለወጥ የምትኖር ቀን ናት። እንተ ትሰፍን ለዓለም። ውብ ቀን ናት ሙሽራዋ የምትናፍቃት ቀን ናት። መ/ር ንዋይ ካሳሁን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ ይቀላቀሉ (ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ) https://www.youtube.com/channel/UCs7-BeDBlS-PBJpdp0HsHkQ ቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/fionteabewzeorthodox
Show all...
👍 2
ነገ!! የፈራ ይመለስ እኛ እንገኛለን እንቀበላለን!!
Show all...
👏 6
ለአቡነ ሐራ ገዳም የምንችለውን እናድርግ
Show all...
ኦርቶዶክሳዊ መሪ በዘመነ ዐጸባ👇2 (ችጋር፥መከራ፥ጭንቅ፥እጦት፥ድህነት) ...እግዚአብሔርም እንደ መረጠው ተረዱ ከዚህም በኋላ ያለ ውዴታው ይዘው በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት። በተሾመም ጊዜ እንደ ሐዋርያት አጠባበቅ መንጋዎቹን ጠበቀ ወደ እግዚአብሔርም የሚያደርሱ መጻሕፍቶችን ያነቡላቸው ነበር በበጎ ሥራና በቀናች ሃይማኖት የሚያጸናቸው ሆነ ችግር ላለበት ሰው ሁሉ አብዝቶ የሚራራና የሚመጸውት ሆነ። በዘመኑም አንድ መስፈሪያ ሥንዴ ዋጋው ሁለት የወርቅ ዲናር እስኪሆን በግብጽ አገር ታላቅ ረኃብ ሆነ ድኆችና ችግረኞች ከሕዝቡም ውስጥ ብዙዎቹ ወደ ቤቱ ደጃፍ ይሰበሰቡ ነበር። ረዳቱ ማርቆስንም በአብያተ ክርስቲያናት ገንዘብ ላይ ሁሉ ሾመው ጌታችንም ከሰዎች ላይ ቊጣውን እስከ አራቀ ድረስ ለችግረኞች ሁሉ በጥዋትና በማታ የሚሰጣቸው ሆነ ስለዚህም ይህ አባት ዮሐንስ መሐሪ ተብሎ ተጠራ። ከዚህም በኋላ ይህ አባት አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ በጌጥ ሁሉ አስጌጣቸው። ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ ለካህናቱ የሚያርፍባትን ቀን ነገራቸው እንዲህም አላቸው እኔ ጥር ዐሥራ ስድስት ቀን ተወለድኩ በዚችም ቀን ሊቀ ጵጵስና ተሾምኩ ደግሞ በዚች ቀን አርፋለሁ። ይህንንም ሲላቸው ኤጲስቆጶሳቱ አለቀሱና አባታችን ሆይ ከአንተ በኋላ ሊቀ ጵጵስና የሚሾም ማን ነው አሉት። እርሱም ረዳቴ ቀሲስ ማርቆስ ነው የክብር ባለቤት ጌታችን ለዚች ሹመት መርጦታልና አላቸው። በሹመቱ ሃያ ሦስት ዓመት ከኖረ በኋላ ጥር ዐሥራ ስድስት ቀን አረፈ። በዘመኑም በእስክንድርያ ሊቀ ጵጵስና በግፍ የተሾመው ዳዊት ሞተ ዳግመኛም ከእርሱ አስቀድሞ የነበረ በእሥር ቤት ዐሥር ዓመት ከኖረ በኋላ ሌላ ጊዮርጊስ የተባለ ተሾመ። ይህም አባት አባ ዮሐንስ በተሾመ ጊዜ ስለ ቀናች ሃይማኖት መልእክትን ጻፈ ጊዮርጊስም በአረፈ ጊዜ በእርሱ ፈንታ ስሙ ኪራኮስ የሚባል ጻድቅ ሰው ተሾመ መልእክትንም ጽፎ ወደ አባ ዮሐንስ ላከ እርሱም ደስ ተሰኘበት የመልእክቱንም መልስ ጽፎ ላከለት። (ስንክሳር ጥር 16) የእግዚአብሔር  መንፈስ ያለበት  መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ፥ ልብንም ለማቅናት ፥ በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል ።2ኛ ጢሞ 3:17
Show all...
👍 3
ወንድማችን አማኑኤል ዛሬም ፍርድ ቤት ሳይቀርብ እንደታሰረ ነው፣ እግዚአብሔር ያስፈታህ ወንድማችን
Show all...
👍 10🙏 2