cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የመካሽ አስራት እይታወች ፩

Advertising posts
194
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ጎንደር ለለቅሶ ሔጄ ምን ሆኖ ነው የሞተው ስል ምግብ እየበላ አንቆት ውሀ እንካ ጠጣ ስንለው አሁን ጠጣው እያለ ሲግደረደር.....🙆‍♂🙆‍♂ 😁😂🤣 Mak man
Show all...
እንደ ቦታቸው ተረዳቸው! ፨፨፨፨፨///////////፨፨፨፨፨ ከጀርባህ ሆነው በሚያወሩ፣ በስኬትህ በሚቀኑ፣ በከፍታህ በሚበሳጩ፣ ተግባርህን በሚያቃልሉ ሰዎች በፍፁም አትናደድ። ምክንያቱም ስሜታቸው እንጂ ውስጣቸው መድረስ በሚፈልገው ስፍራ ሊናደድ አይችልምና። ምክንያቱም የንግግራቸው ይዘት በእራሱ ካንተ እንዳነሱ፣ ከኋላህ እንደቀሩ፣ ከአቅማቸውን እንደጎዱ አመልካች ነውና። ማንም ሰው ያለምክንያት ከጀርባ ሆኖ የሌላውን ሰው ስም ለማጥፋት አይሞክርም፤ በሌላው ውድቀት ለመደሰት አያኮበኩብም፤ በሌላው ችግርና ፈተና የእራሱን ህይወት ለማሻሻል አይሯሯጥም። በእራሱ የሚተማመን፣ በሳልና ብልህ ሰው የወንድሙ ደስታ ደስታው ነው፤ የጓደኛው ስኬት ስኬቱ ነው፤ የወገኑ ሰላም፣ የህዝቡ እረፍት ሰላሙ፣ እረፍቱ ነው። ማንም ክፉ የሚያስብ፣ ከኋላ ቢዶልት፣ ደባ ቢያደባ ከጀርባ ሆኖ የሚያሸንፈው ትግል አይኖርም። ስም በማጥፋት፣ ገፅታን በማጠልሸት፣ ጫናዎችን በማብዛት የእርሱ ስም የሚገነባ፣ ገፅታው የሚስተካከል ቢመስለውም ቅሉ ግን የተዛባው እይታው ለከፋ ውድቀት ይዳርገዋል። አዎ! ጀግናዬ..! እንደ ቦታቸው ተረዳቸው! ወዳጅህ መስለው የጠላት ስራ የሚሰሩብህ፣ በልብ ጓደኝነት ሰበብ ከጀርባ የሚያደቡብህ፣ አጀንዳቸው ሁሉ ያንተ እድገትና ለውጥ በሆነባቸው ሰዎች አትበሳጭ፣ አትዘን፣ አትናደድ። ክፉዎች ሁሌም ስፍራቸው ከኋላ ነው፤ ተንኮለኞች ዘወትር ምልልሳቸው በዝቅታ ነውና እንደ ቦታቸው ተረዳቸው። የምቀኝነት እሳቤ የውድቀት መንገድ ነው፤ የንፉግነት ማንነት የትንሽነት ልክ ነው። መልካምነት ልብን ይጠይቃል፤ ሰው መሆን ይፈልጋል። ለእራስ እንዲሆን የሚመኙትን በሰው ሲመለከቱ ከኋላ ከመንሾካሾክና በድብቅ ክፋትን ከመዶለት ይልቅ በግልፅ የደስታው ተካፋይ መሆን የመልካምነት መለኪያ ነው። ልበ ቀና ደግ ሰው ሃሳቡ በእራሱ በጎነትን ያድለዋል። አዎ! በወዳጅህ ደስታ ተደሰት፣ ከስኬቱ የምስራች ተቋደሰው፣ የከፍታውን ብስራት አካፍልለት። ትልቅነት በቅንነት፣ ብስለትም በአጋዦነት የሚገለፅ ነው። አርቆ የሚያስብ፣ ህልመኛና ባለራዕይ ሰው ትልቅ ስፍራ በደረሱ፣ ስኬትን በተቆናጠጡ፣ ከከፍታው በደረሱ ሰዎች አይቀናም፤ አይናደድም፤ አይበሳጭም። መንገዳቸውን መማሪያ፣ ስኬታቸውንም እንደ መነቃቂያ ይወስደዋል። ሁሉም ታስቦ የሚደረግ ነገር የእራሱ በቂ ምክንያት አለው። ሰዎች ያለምክንያት በለውጥህ አይበሳጩም፣ በእድገትህ አይናደዱም፣ በደስታህ አይቃጠሉም። አስከፊው ከፋት የስሜት ጭካኔ፣ የስሜት ደባ፣ የስሜት ጥላቻ ነው። ተንኮልን ከውስጡ የሚያወጣ፣ ጥሎ ለማለፍ ሁሌም የሚሯሯጥ፣ ሰው ሲያልፍለት አይኑ የሚቀላ ሰው አደገኛ ነውና ተጠንቀቀው። ግብህ ላይ ካተኮርክ፣ ልዩነት መፍጠር ከጀመርክ፣ ብዙዎች የሚመኙትን ነገር እጅህ ወደማስገባት ከተጠጋህ የኋላ ጫናና ክፋቶች ይበዛሉና ለእራሰህ ታመን፣ በጅማሬህ ቀጥል፣ ጫናዎችን ተጋፈጥ፣ ጥላቻውንም ጥልህ እለፍ። ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨ Mak man
Show all...
Photo unavailable
ተስፋ እንዳትቆርጥ: ተስፋ እንዳትቆርጪ! በ17 ዓመቷ ከኮሌጅ ተባረረች። በ25 ዓመቷ እናቷ በሞት አጣች። በ27 ዓመቷ አገባች። ባሏ ክፉኛ ያሰቃያት ነበር ይህ ቢሆንም ሴት ልጅ ወለደችለት በ28 ዓመቷ ከባሏ ተፋታ እንዲሁም ከባድ የመንፈስ ጭንቀት አጋጠማት። በ29 ዓመቷ በድህነት ልጇን ለብቻዋ ታሳድግ ጀመረ። በ30 ዓመቷ በዚህ አለም መኖር እስኪያንገሸግሻት እራሷን ለማጥፋት እስክታስብ ድረስ ተፈተነች። ነገር ግን በስተመጨረሻ መክሊቷን አገኘች፣ ከማንም በተሻለ ልታደርገው የምትችለውን አንድ ነገር ተረዳች ያም ነገር መጻፍ ፃሀፋ ደራሲ መሆን ነበር። በ 31 ዓመቷ በመጨረሻ የመጀመሪያውን መጽሃፏን አሳትማለች። በ 35 ዓመቷ, 4 መጽሃፎችን አውጥታለች, እናም የዓመቱ ደራሲ ተብላ ተጠራች. በ42 ዓመቷ፣ በተለቀቀችበት የመጀመሪያ ቀን 11 ሚሊዮን ኮፒ የተሸጠ መጽሐፏን አሳተመች። ይህች ጀግና ሴት ጄ.ኬ. ሮውሊንግ ነች፡፡ ዛሬ ሃሪ ፖተር ከ15 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው ዓለም አቀፍ የንግድ ምልክት ነው። ተስፋ እንዳትቆርጥ፡ ተስፋ እንዳትቆርጪ. መክሊትህን ፈልግ፡በራስህ እምነት ይኑርህ፡ ጠንክሮ መስራት ዘግይቶ አያውቅም ዛሬ እርምጃ ይውሰዱ፡፡ ከፌስቡክ መንደር
Show all...
በሰው ተስፋ አትቁረጥ _____________ “You must not lose faith in humanity. Humanity is an ocean; if a few drops of the ocean are dirty, the ocean does not become dirty”—Mahtama Gandih _____________ ምናልባት ሰዎች በድለውህ፤ አልያም አስከፍተውህ ሊሆን ይችላል። ማን ያውቃል ያመንከው ከድቶህ፤ የጠበቅከው እረስቶህ፤ ተስፋ የጣልክበት ጥሎህ ሊሆንም ይችላል። _____________ ወይም ደግሞ የእለቱን ዜና ስትሰማ፤ ሰው በሰው ሲጨክን ስታይ እውነት መልካም ሰዎች ይኖሩ ይሆን ብለኽ አስበህ ሊሆንም ይችላል። _____________ ማን ያውቃል ከልብህ ወደህ ልብህን የሰጠኸው ሰው፤ ልብህን የጣለበት ጠፍቶት ሌላ መውደጃ ልብ አጥተኽ ይሆናል። _____________ በእለት ተእለት ኑሮዋችን የመገናኛ ብዙሃን የሚያሰሙን ዜናዎች፤ እውነትም በሰው ልጅ ተስፋ እንድንቆረጥ ያደርገናል። _____________ መልካም ሰዎች እና ምግባሮቻቸው እየመነመኑ የመጡ ይመስለንና እራሳችንን ከማህበረሰቡ እየነጠልን እንመጣለን። _____________ ሰው ለመውደድ ሁለቴ እናስባለን፤ ልባችንን እንዳይሰበር በመስጋት። ደግ ለመስራት ግራ ቀኙን እናያለን፤ በበጎነታችን እንዳንጎዳ በማሰብ። _____________ ሰው ማመን ፈተና ሆነብን። በዚህ መሃከል ግን መልካም ሰዎች እያሉ እንደሌሉ ተቆጠሩ። የክፋት ወሬ አለምን ሲያዳርስ፤ መልካም ዜና ግን ከቤት አልፎ ጎረቤት መሰማት አቃታት። _____________ በሰው ልጅ ተስፋ መቁረጥ ያለብን አይመስለኝም። አንዴ ስለተከዳን ሁሉም ሰዎች ከሃዲዎች ናቸው ብለን መደምደም የለብንም። _____________ መጥፎ ዜናዎች ከፍ ብለው ስለተሰሙ፤ መልካም ስራ የለም እያልን በሰብዓዊነት ላይ ተስፋ ባንቆርጥ መልካም ነው። _____________ አለም ልክ እንደ ውቂያኖስ ናት፤ ጥቂት የክፉ ሰዎች ጠብታ ስላለባት ብቻ ውቂያኖሱ ተበክሏል ብለህ ተስፋ አትቁረጥ። _____________ ደግመህ ለመውደድ አትፍራ፤ ደግመህ ይቅር ለማለት አትስጋ፤ የዋህ መሆንህን አትጥላው።አለምን በርቀስ አርገን ብናያት፤ ማመን ከሚከብደን በላይ መልካም ሰዎች አሏትና። _____________ “አለም ልክ እንደ ውቂያኖስ ናት፤ ጥቂት የክፉ ሰዎች ጠብታ ስላለባት ብቻ ውቂያኖሱ ተበክሏል ብለህ፤ ተስፋ አትቆረጥ።” _____________ #ሼር
Show all...
00:13
Video unavailable
🤣🤣😅 Mak man
Show all...
2.40 MB
Photo unavailable
ችግርህን በማሰብ ጊዜ አታጥፋ! አሁን ባለህ ሕይወት ግራ ግብት ብሎህ ስትጨነቅ የምትታየው የመፍትሔ ሃሳብ ማመንጨቱን ትተህ ችግሩን በማሰብ እዛ ላይ ጊዜህን ስለምታጠፋ ነው። ነገር ግን በችግርህ ማለቃቀስህን ትተህ ችግርህን በማወቅ መፍትሔው ላይ ብታተኩር ስኬታማና ድንቅ ሕልሙን ያሳካ ሰው ትሆናለህ። ስለዚህ በፍፁም በችግርህ አታልቅስ፤ ከእዛ ችግር ተማርበት እንጂ!                                          Mak man
Show all...
እያደረሰህ ነው! ፨፨፨//////፨፨፨ ህይወት ከ "ሀ" ጀምራ እስከ "ፐ" ስትጓዝ በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ የእራሷ መልክና አሻራ አላት። የፈተናን ፅንፍ፣ የደስታን ጥግ፣ የችግርን መዓት፣ የሃሴትን መዓቀፍ በአንድላይ እያፈራረቀች ማሳየት የሚትችል መልከ ብዙ፣ ገፀ ብዙ ትልቅ ዠንጉርጉር መሃደር ነች። በእያንዳንዳችን ምርጫ ውስጥ ህይወት የምትመራን አቅጣጫ ይኖራል፤ አቅጣጫዎቹም ምቾትን ወይም ስቃይን፣ ደስታን ወይም ሃዘንን፣ እረፍትን ወይም ድካምን ሊያስከትሉብን የሚችሉ ናቸው። አብዛኛው ሰው የሚኖረው ህይወት የግዳጅ ሳይሆን የምርጫ ህይወት ነው። ከሆነው ሰው፣ ከማንነታችን ጀምሮ እስከ ከበቡን ሰዎች፣ አስከምናውቃቸው ጉዳዮች፣ እስከምንከተላቸው ሰዎች ድረስ መርጠንና ፈልገን የምናደርጋቸው ናቸው። የትኛውም ምርጫ ደግሞ ውጤትን ያመጣል፤ ለውጤቱም ሃላፊነት መውሰድ ይጠይቃል። ለእያንዳንዶቹ ምርጫና ውሳኔዎችህ ደግሞ ሃላፊት ካልወሰድክ አንድ እርምጃ ልትራመድ ትችላለህ፣ ሁለተኛውን ግን አትደግመውም። አዎ! ጀግናዬ..! እያደረሱህ ነው! ምርጫዎችህ ወደ ግብህ እያቀረቡህ ነው፤ ውሳኔዎችህ ወደ ህልምህ እያቀረቡህ ነው፤ እርምጃዎችህ ወደ መዳረሻህ እያቀረቡህ ነው። ከምቾትህ ስትወጣ፣ የህይወት ክብደት ሲሰማህ፣ ግራ መጋባት ሲወርህ፣ ጨለማው ሲመጣ፣ ፈተናዎች ሲደጋገሙ፣ ፍረሃት ሲቆጣጠርህ፣ ስጋት ውስጥ ስትወድቅ፣ ድፍረት ስታጣ ህይወት እየፈተነችህ ነው፤ ልኬትህን እየፈለገች ነው፤ አቅምህን እየለካች ነው፤ ፅናትህን፣ ትግስትህን፣ ብርታትህን እየመዘነች ነው። የዚህ ሁሉ ክስተት ዋናው መንስዔ መርጠህ የተጓዝክባቸው የህይወት መንገዶችህ፣ ውሳኔህና እርምጃዎችህ ናቸው። ነገር ግን በፅናትህ ልክ፣ በብርታትህ መጠን ስታሸንፍ ህይወት የምትሰጥህ ህልም አለ፤ ስትሻገራቸው የምትሸልምህ ዋንጫ አለ፤ ስታልፋቸው የምታበስርህ የድል ዜና አለ። አዎ! ፊትህ የቆመው መሰናክል ከግብህ የሚያደርስህን መንገድ የሚከፍት ነው፤ ብርታት የሚያድልህ፣ ጥንካሬን የሚያጎናፅፍህ፣ የሚሰራህ ነው። እንቅልፍ የነሳህ ችግር በረከት የሚያመጣ፣ ትሩፋትን የሚያድል፣ ጥበብን የሚያጎናፅፍ፣ ደስታን የሚያስከትል ነው። ተስፋ ለመቁረጥ አትቸኩል፤ አቅምህን ለማጣት፣ ከጥንካሬህ ለመለየት አትጣደፍ። የደበዘዙ የህይወት ገፆች እንዳሉ ሁሉ የፍካትና የደስታ ጊዜያትም ይኖራሉ፤ የሽንፈትና የስንፍና ወቅቶች እንደመኖራቸው የአሸናፊነት፣ የጥንካሬና የብርታት ጊዜያትም አሉ። ህይወት ገና ስንቱን ታሳይሃለች? መዓቱን፣ እልፉን ታስጎበኝሃለች፤ በብዙ ውጣወረዶች ትፈትንሃለች፤ መዓቱን ታወርድብሃለች፤ ያለህን ታሳጣሃለች። ከፈተናህ ጀርባ ግን ሃሴትን ታድልሃለች፤ ከመዓቱ ቦሃላም በበረከት ትሞላሃለች፤ ያለህን ወስዳም አትቀርም በምትኩ የተሻለውን ትለግስሃለች። በተስፋህ አትደራደር፣ ሃላፊነትን ውሰድ፣ ኮራ ጀነን ብለህ በፍጥነት ከመዳረሻህ ለመድረስ ወደፊት ተራመድ። ከሰው ምንም አጠብቅ ጉዋደኞችህ ያንተን ህይወት አይኖሩልህም የቀረበህን ቅረብ የራቀህን አርቀህ እራቅ ምክንያቱም ሲመለስ ካንተ የሆነ ነገር ፈልጎ መሆኑን አትርሳ!!! ግሩም ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒✨💫 Mak man
Show all...
      💔 "ሂጂ ፈቅጃለሁ"❤️‍🔥 የውስጤን ላይ ሸማ #አንቺው ጀምረሽው በሰፊው ልቤ ላይ ባጭር #ከቀጨሽው😔 ……………………ደርቢው አልልም! ድሮም #አጭር ነገር ከሰው ላይ #አያምርም!! እውነቴን ነው ውዴ ለሰው ልጆች ሁሉ ያልተመለሰልን ብዙ ጥያቄ አለ አንቺም #ካልተመቸሽ የልቤ ላይ ሸማ ላንቺ #ካልተባለ መሄድ ትችያለሽ!🤷‍♂ #አልከለክልሽም ! ለኔ የሞተብሽ ስሜትሽ ካየለ ግን #ማወቅ ያለብሽ? ገፍቶ #በመሄድ ላይ ብዙ #መውደቅ አለ😒 እውነቴን ነው ውዴ❤️ በዚች ዓለም ስኖር መገፋት #ቢኖርም በፍቅር #መረገጥ ሽንፈት #አይወክልም🙏 ደሞ ይሄን #ስልሽ #እንዲገባሽ እንጂ #እንድትመጪ አደለም!🙌 ሂጂ #ፈቅጃለሁ☹️ በኳታኙ እግርሽ #እንዳሻሽ ሁኝበት💁‍♂ ድሮም መሄድ እንጂ መምጣት #አታውቂበት😏 ስለዚህ ፍቅሬ❤️ ጥለሽኝ ብትሄጅም😟 #መነሳቴ አይቀርም መቃብር ፈልፍየ በፍቅር ዓለም ውስጥ #ከሞት በኃላ ነው 'ሚኖረው #ትንሳኤ 🙌           Mak man
Show all...
በተቃራኒውም አትርፍበት! ፨፨፨፨፨///////////፨፨፨፨፨ በጊዜ መነሳትህ ብቻ ሳይሆን በቂ እንቅልፍም ያስፈልግሃል፤ ጠንክረህ መስራትህ ብቻ ሳይሆን እረፍት መውሰድህም ይጠቅምሃል፤ ምቾት ብቻ ሳይሆን የሚያሳድግህ ችግርና ፈተናም ያስፈልግሃል፤ ዘወትር ለብቻ ማሳለፍ ብቻ ሳይሆን ሰውም ያስፈልግሃል። እራስህን ለመረዳት በምታደርገው ጥረት ጥንካሬህ ላይ እንደምታተኩረው ሁሉ ድክመትህንም መዘንጋት የለብህም፤ ብትቀርፈው ውጤታማነትህ ያድጋል፤ ብታሻሽለው ምርታማነትህ ይጨምራል፤ ብትሰራበት ጥንካሬህን ያጎለብታል፤ አቅምህንም ያሳድጋል። በትንሹም ቢሆን የተወሰኑ ተግባራት ተቃራኒያቸውም በጣም ጠቃሚና አስፈለጊ ነው። ሁሌም ደስተኛ ህይወት ላትኖር ትችላለህ፣ ተስፋ የምታጣበት፣ ጉልበትህም የሚዝልበት፣ በነገሮች የምትሰላችበት ጊዜ ይኖራል በዚህ ሰዓት ነገሮችን በተግባር መወጣት ካልቻልክ ሁሌም ጫናቸው ከባድና ለመታለፍ አስቸጋሪ ይሆናሉ። አዎ! ጀግናዬ..! በተቃራኒውም አትርፍበት፤ ከአሉታዊ ጎኑም ተጠቀም፤ በጉዳትህም ጥንካሬን ተማር፤ በብቸኝነትህ እራስህን ፈልገህ አግኘው፤ ግራ ከመጋባት በመውጣት ለሌሎች ምሳሌ ሁን፤ ተስፋ በመቁረጥ መሃል ተስፋን ፈልጋት፤ ከድካምህ በማረፍ እራስህን ጠግነህ ተመለስ፤ ሊዓላዋቂነትህም የተሻለ እውቀትን ሸምት፣ ለጭንቀትህም ለሁሉም የሚሆን መፍትሔ ፈልግ፤ ለችግሮችህም መውጫ ቀዳዳ አብጅ። አያንዳንዱ ጉዳዮች ላይ ሙጭጭ ስላልንባቸው ብቻ የሚሳኩ፣ እውን የሚሆኑ አይደሉም፤ ፋታ መውሰድ፣ አቅጣጫ መቀየርና በተሻለ ወኔ፣ በተለየ ብርታት ልናደርጋቸው የሚገቡ ይሆራሉ። በተደጋጋሚ ሞክረህ አላዋጣ ያለህን መንገድ ከመቀየርና ከመተው የተሻለ አማራጭ የለህም። በእርግጥም የታከተህ፣ ያሳመመህ፣ አቅምህን የጨረስ፣ የጠበከውን ውጤት ያላመጣለህን፣ ለረጅም ዘመናት በልፋት ብቻ ያታከተህ ጉዳይ ካለ ተስፋ ቆርጦ ሌሎች አማራጮችን መመርመሩ የተሻለ የሚሆንበት ጊዜ እንደሚኖር አስተውል። አዎ! ከግብህ የምትደርስበት መንገድ አሰለቺ፣ አድካሚ፣ እጅጉን ፈታኝና ተስፋ አስቆራጭ ከሆነ የምትቀይረው መንገድህን እንጂ ግብህን አይደለም፤ የማይሳካ የመሰለህን ህልምህን ሳይሆን ህልምህን ለማሳካት የተጠቀምካቸውን ሁኔታዎች ነው። ባሰብከው መጠን ማሳካት የተሳነህ ግብህ ስለገዘፈ፣ ሃሳብህ የማይቻል ስለሆነ፣ የከፈልከው ዋጋ ያነሰ ስለሆነና ህልምህ የማይቻል ስለሆነ አይደለም። የእቅዶችህን ውጤታማነት፣ የድርጊቶችህን ጥራት፣ የልማዶችህን አዋጪነት፣ ምቹነትና ሳቢነት ካለመመርመር ሊሆን እንደሚችልም አስታውስ። ለዚህ ጉዳይ ትኩረትና ጊዜ ካልሰጠህ ህልምህ ቢቻልም አንተ ሳትችለው ትቀራለህ፤ በአቅምህ በማመን ፈንታ ተስፋ ወደ መቁረጥ ትቃረባለህ፤ በአምላክህ በመተማመን ፈንታ ለማማረር ትሽቀዳደማለህ። ያልደረስከው መዳረሻው በጣም የራቀና የማይደረስ ስለሆነ ሳይሆን የመረጥከው መንገድ ጉራንጉር የበዛበት፣ በእሾህ አሜኬላ የተሞላ፣ ዘወትር ለመደጋገም የማይመች ስለሆነ ብቻ ይሆናል። መንገድህን መርምር፣ በተቃራኒው አቅጣጫም ነተሻሉ አማራጮችን ፈልግ። ውብ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅 Mak man
Show all...
መጠጋትህን ቀጥል! ፨፨፨፨/////////፨፨፨፨ አዎ! የቻልከውን እያደረክ፣ ከቻልከው በላይም እየጣርክ፣ እየለፋህ፣ እየተጋህ፣ በአዳዲስ መንገዶች እየሞከርክ ህይወት ላላትሞና የታሰበችውን ያክል ላትሆን ትችላለች። ያዝኩት ስትላቸው የሚበተኑ፣ ደረስኩ ስትል የሚርቁህ፣ አገኘዋቸው ስትል የሚበኑ አያሌ ጉዳዮች ይኖራሉ። ጭራዉን አጥብቀህ መያዝህ እንኳን ላሰብክበት መዳረሻ ዋስትና ላይሆንህ ይችላል። ብዙ ዋጋ ከፍለህ የገነባሀው የፍቅር ህይወት የከፈልክለትን ዋጋ ያክል ሳይሆንልህ ሲቀር፤ ለዘመናት የለፋህበት ትምህርት ምንም ሳይጠቅምህ ሲቀር፣ የተማመንከው ስራ ውጤቱ አልባ ሲሆን፣ ተስፋ ያደረከው ሰው እየሸሸህ ሲመጣ፣ ነገሮች በተገላቢጦሽ መጓዝ ሲጀምሩ የተለየ ግንዛቤ፣ የተለየ አረዳድና ከወትሮው የላቀ ጥረት እንደሚጠበቅብህ አስተውል። በአንዳንድ የህይወት አጋጣሚ አንዳንድ ጉዳዮች ከሚጠቅባቸው ላነሰ እርካታ ይዳርጋሉ፣ ደስታ መስጠት ላይ ችግር ይኖርባቸዋል፣ የተሻለ ነገር ለመፍጠር አቅም ሲያንሳቸው ይስተዋላል። አዎ! ጀግናዬ..! ውጤትህ ከጠበከው በታች በመሆኑ፣ የጓጓህለትን ያክል እርካታ ስላልሰጠህ፣ ስሜትህን ስላልቀየረ ብቻ ካመንክበት ተግባር እንዳትገታ። መጠጋትህን ቀጥል! የህይወትህ ትልቁ ሚስጥር ልታቆምበት ከነበረው አንድ እርምጃ ቦሃላ ሊሆን እንደሚችል አስብ፤ አንተነትህን የሚለካው፣ አቅምህን የሚያሳየው፣ ጥረትህን የሚያስመለክተው ውጤት በቅርብ ሊሆን እንደሚችል አስተውል። ምንም እንኳን የተጓዝከው አጭር መንገድ፣ በፅናት የታገልከውም ለተወሰነ ጊዜ ቢሆንም የሚቀርህና የሚጠበቅብህ ግን ካለፈው ጥረትህ በእጅጉ ያነሰ ነው። ስትነሳ በነበረህ ተነሳሽነት፣ ስትጀምር በነበረህ እውቀት፣ በጠዋቱ በነበረህ ሰሜትና ብቃት ላይ አይደለህም። አንድ በሞከርክ ቁጥር ምንም ካለመሞከር ተሽለህ ትገኛለህ፤ ወደጓጓህለት ግኚት በአንድ እርምጃ ትቀርባለህ፤ የሚቀርህን መንገድ ታሳጥራለህ። አዎ! ያለዋጋ የሚገኝ ጠቃሚና ዋጋ ያለው ነገር የለም። መሃበራዊ ግንኙነትህ ያድግ ተዘንድ ተግባቢነት ላይ፣ ሰዎችን መረዳት ላይ፣ የእርስ በእርስ ግንኙነት ላይ መስራት ይኖርብሃል። የፍቅር ህይወትህ እንዲያድግ፣ ትርጉም እንዲሰጥህ፣ እንዲረጋጋና ሰላማዊ የደስታ ምንጭ እንዲሆንህ እለት እለት በመታደስ፣ በአዳዲስ ማራኪ ክስተቶችና ትርጉም ሰጪ ክንውኖች መሞላት ይኖርበታል። ሙያዊ አቅምህ እንዲዳብር፣ በብቃትህ የመተማመን ደረጃ ላይ እንድትደርስ፣ ተፈላጊነትህ እንዲጨምር፣ ያንተም ዋጋ ጎልቶ እንዲወጣ የበዛ ጥረት ከማያቋርጥ መስተጋብር ጋር ይጠበቅብሃል። የዛፉ ፍሬ ላይ ሳይሆን መወጣጫው ላይ አተኩር፣ በእርሱ ተማረክ። በስተመጨረሻ ከምትጎናፀፈው ድል በበለጠ ከትግሉ ጋር በፍቅር ውደቅ፣ በስሜት ተገናኘው፤ ከሂደቱ ጋር ተሳሰር፣ ከልብህ ውደደው። እንደ መዓድን አውጪው መዓድኑን ለማግኘት የመጨረሻው አንድ ቁፋሮ ሲቀርህ ጥረትህን እንዳታቆም። Mak man
Show all...