cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አሌክስ ነኝ ባለን ነገር በተሰጠን እንማማር

በዚህ page የኔ የሆኑ በማህበራዊ ህይወቴ ዉስጥ ትስስር ያላቸው ወዳጆቼን ይብለጥ እዴዘልቅ የሚፈጥር የመማማሪያ ብሎም የመተዋወቂያመንገድ ስለሆነ የሚተላለፎትን በማበብ በመረዳት ለወዳጅኦ ያካፍሉበት።በተጨማሪም ያገባኛል ያገባናል የሚል ሀቅ እውነትን ይዘን እድንማማር ጭምር ነው ።።

Show more
Advertising posts
195
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ቢያንስ ሰው ልለካህና ልመዝንህ ካለኝ ከእኔ የተሻለ ማንነቱን በተግባር ኖሮ አሳይቶኝ ከሆን ብቻ ነው የምሰማው አልያ ግን እደመጣለት አፍ ለከፈተ እና ቦታውን እና ቦታዬን ላላወቀ ማርያምን እምዬን አልሰማውም
Show all...
አንድ የመኖር ሚስጥር አለን ለወደደን እና ላከበረን መኖር ቦታ ለሰጠን እና ለፈለገን መገኜት ለሰላም እና ለይቅርታ በትህትና እና በእሺ ባይነት አንድ የመኖር ሚስጥር አለን ለወደደን እናላከበረን መኖር ቦታ ለሰጠን እናለፈለገን መገኜት ለሰላም እናለይቅርታ በትህትና እናበእሺባይነት የሰው ልጂ ብቻ ጋ ሳይሆን ተፈጥሮጋ ተስማምቶ የመኖር ሚስጥር ሲኖረን ደስታ የበላይ እኛ ደግሞ እዲህ የውስጣችንን ሰላም እናካፍላለን፡፡ጎበዝ የሰው ልጂ ብቻ ጋ ሳይሆን ተፈጥሮ ጋ ተስማምቶ የመኖር ሚስጥር ሲኖረን ደስታ የበላይ እኛ ደግሞ እዲህ የውስጣችንን ሰላም እናካፍላለን፡፡ጎበዝ አድም ቀን የበላይነት ለፍቅር እጂ ለሰው ልጂ መለያ መስፈርቶች የበታችነት ተሰምቶኝ አያውቅም ዛሬም ነገም ከሰው በላይ እጂ ከሰው በታች አስቢም አላቅም መልካም በአል
Show all...
💊 ሕሊና እንጂ መልክ አያስብም፡፡ 💊 አንደበት እንጂ መልክ አይናገርም፡፡ 💊 መልካምነት እንጂ መልክ ከሰው አያኖርም፡፡ 💊 ስነ ምግባር እንጂ መልክ አያስከብርም፡፡  💊 እምነትና ፍቅር እንጂ መልክ ሞትን አያሻግርም፡፡ 💊 መልክ የላይ ማንነትን እንጂ የውስጥ ሰብእናን አይገልጥም። 💊 ፊት ቀልቶ ውስጥ ሊጠቁር ፣ ውጪ አጊጦ ልብ ሊቆሽሽ ይችላል፡፡ 💊 እውነተኛ ፍቅር በአይን ሳይሆን በልብ ነው መልካም የገና ባአል ሳምታት ዋዜማ አደረሳችሁ
Show all...
በሚስቴና በጉንዳን መሀል ምንም ልዩነት የለም ብሎኝ አንዱ ወዳጅ እንዴት ስለው... #ሁለቱም_ልብሴን_ያሶልቁኛል😜 አላለኝም፦፦፦ ችግር ሁሌም ፈተና ነው ።ፈተና ደግሞ ሁሌም ፈታኝ ነው ።ስትፈተን ደግሞ አይጣል ነው አንዱን ችግር ፈታሁ ስትል ሌላ ችግር 😢😢😢😢 ፈታኝ ህይወት ለእዉነተኞች ነው ።ላስመሳይ እና ለሆድ አደር ሌቦች አይመለከትም ጋይስ መልካም ጁመአ
Show all...
የሰው እንጂ የስራ ትልቅ የለውም ከጀበር ድራማ የሰዉ ልጂ የትኛውም ሥራ የከበደ ቢመስልም በፅናት እና በትግስት የትኛዉንም ስራ መሰራት ይቻላል ።ነገር ግን የሰዉ ክፋት እና ተንኮል ደግሞ በፈጣሪ እንጂ በዚህ ዘመን በግልፍት እና በበላይነት መወጣት አይቻልም ።ሁኑም ግን የትኛውም ሰዉ ከሰዉ በላይ አይደለም ባይ ነኝ በዘመናችን በየትኛውም ጭቅጭቅ እና አፍ ከፈታ ለዉጥ አምጥተዉ አያዉቁም ባይሆን በዝምታ እና በትግስት የመጡ ለዉጦች ግን ሀያሌ ዘመናት መኖር ችለዋል መልካም እሁድ
Show all...
መናደፍ የጊንጡ ባህርይ ነው! አንድ ጥበበኛ ወጣት እጅግ በሚያምርና ዕይታን በሚስብ ወንዝ ዳርቻ ተቀምጦ ሳለ በንፋስ ተገፍቶ ወደ ውሃው የወደቀ እጅግ በጣም አስፈሪ ጊንጥ ይመለከታል። የጊንጡ ህይወት እንዳያልፍ ብሎ በማሰብም ይታደገው ዘንድ ወስኖ ሊያወጣው እጁን ወደ ወንዙ ሰደደ። ጊንጡ ግን ህይወቱን ሊታደግ ለሚጥረው ሰው ምላሹ መንደፍ ሆነ። በጊንጡ አፀፋ የተደናገጠው ወጣት በቅፅበት የሚነዝረው እጁን አነሳ። ነገር ግን አንዲትም ደቂቃ ሳይዘገይ ስቃዩን እንደተሸከመ ለሁለተኛ ጊዜ የዚያን ጊንጥ ህይወት ለማዳን እጁን ዳግም ሰደደ። አጅሬ ጊንጥም ለሁለተኛ ጊዜ ተናደፈ። ወጣቱ በሲቃ ውስጥ ሆኖ እየተዝለፈለፈ የተነደፈ ጣቱን በጨርቅ ጠቅልሎ ለሶስተኛ ጊዜ እጁን ወደ ጊንጡ ከመሰንዘር አልቦዘነም። ይሄን ጊዜ ድራማዊ የሚመስለውን ትዕይንት በቅርብ ርቀት ሆኖ ሲከታተል የነበረ አንድ ሰው በመገረም እንዲህ ሲል ጮኸ « አንተ ሰው! ምን እስኪያደርግህ ነው የምትጠብቀው ? እየነደፈህ ለምን ልታድነው ትጥራለህ ? ለምን አትገድለውም ?» ይለዋል። ወጣቱ ግን ለዚያ ግለሰብ የሚሆን ጆሮ ያለው አይመስልም። ላመል እንኳን አንገቱን ወደ ሰውየው ሳይመልስ ጊንጡን ለማዳን ጥረቱን ቀጠለ። በመጨረሻም ተሳክቶለት ጊንጡን ከሞት ታደገው። ከዚያም ፣ ቀድሞ ጊንጡን ስለመግደል ምክር ለግሶት ወደ ነበረው ግለሰብ እያማተረ እንዲህ ሲል በጩኸት ተናገረ፤ « ስማኝ ወዳጄ ... መናደፍ የጊንጡ ባህርይ ነው ፤ የኔ ባህርይ ደግሞ ማዘንና ማሰብ ሆነ ። ታዲያ ስለምንድን ነው የኔ ባህርይ ከርሱ ባህርይ የከፋ እንዲሆን የምትመክረኝ ?» አለው። ምንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ እንዲህ እንደ ጊንጡ በመናደፍ እያቆሰሉህና እያደሙህ ፤ እየገዘገዙህና እየሸረከቱህ የሚመሳሰሉ ሰዎች ቢኖሩም እምነትህ ባጎናፀፈህ መልካም ሥነ ምግባር ልትገራቸውና ልታቀርባቸው ግድ ይልሃል። በዙሪያህ ያሉ አካላት ወደ እልህና አላስፈላጊ ስሜት ውስጥ እንድትገባ ቢያደርጉህና ያልሆነ ሥነ ምግባር ውስጥ እንድትዘፈቅ ቢወተውቱህም ጆሮ ልትቸራቸው አይገባም
Show all...
"ለጠላቶችክ ደስታ ብለክ ሳይሆን መሸነፍክ ለሚያስከፋቸው ሰዎች ብለክ ጠንካራ ሁን" ዛሬ ውስጥህ ሰላም አጥቶ መኖር አስጠልቶካል? ተስፋ እንዳትቆርጥ ነገ ሌላ ቀን ነው። ዛሬ ሰዎች ከሰው ክብር ዝቅ አርገውክ በሚጠሉክ ሰዎች ተከበሀል? የሚወዱክ ይመጣሉ፤ ነገ ሌላ ቀን ነው። ዛሬ ስንት የደከምክበት ቢዝነስ ብልሽትሽቱ ወጥቷል? ቀና በልና አማራጮችን ተመልከት፤ ነገ ሌላ ቀን ነው። ዛሬ በትዕምርትህ የተዘጋጀከውንና የደከምክበትን ያህል ውጤት አላመጣህም? ትምርት በቃኝ እንዳትል፤ ነገ ሌላ ቀን ነው። የተሸነፍከው የወደክ ፣ የተሰበርክ ቀን አይደለም። የተሸነፍከው በወደክበት ለመቅረት አምነክ የተቀመጥክና ዳግም መሞከር ያቆምክ ዕለት ነው። በል ተነስ የእኔ አንበሳ፤ ይቺ ምድር ለተሸናፊ ቦታ የላትምና "ለችግሮችህ በሙሉ ትልቅ ችግር ሁንባቸው።"
Show all...
እዲህ ናት ሀገሬ ክብር ለሚገባት ክብር ትሰጣለቺ ማሪቱ ለከተማችን የጥበብ እድገት የልጂነቷን፣የህትነቷን፣የእናትነቷን በሚገባ ያሳዬች ዉበትን፣ጀግንነትን በግጥሞቿቯ ብቻ ሳይሆን እኛም ትውልዶች ወደናት እድንኖር ያረገች አርቲስታችን ናት፡፡ Alex Prizu
Show all...
#መልካም_ሰው_የት_አለ?! በአንድ ወቅት አንድ አረጋዊ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦ “አንድ ሰው መልካም ሰው መሆኑን እንዴት ማወቅ ይችላሉ?” አረጋዊው እንዲህ መለሱ:- “መልካም ሰውን በሚናገረው ወይም በመልኩ አትለየውም። ነገር ግን #በእርሱ_መገኘት_በሚፈጠረው_ድባብ_ነው። ማስረጃው ይህ ነው ፡፡       ምክንያቱም ማንም ከመንፈሱ ያልሆነ አከባቢ መፍጠር አይችልም ” ብዙ ሰዎች የመንፈሳቸው ያልሆነውን አካባቢ ለመፍጠር ሲሞክሩ ይታያል ነገር ግን የማይሆን ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ሰው ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በመገዛት የመንፈስ ፍሬዎችን ያፈራል አካባቢውንም በፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የዋህነት፥ ራስን መግዛት ይመላዋል። (ገላ 5: 22)። አካባቢያችን እንዲለወጥ ለመንፈስ ቅዱስ እንገዛ ያኔ መልካምነታችን ለሌሎች ይታያል።
Show all...
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏 የወደቀ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን የወደቀ ሰውንም ማንሳት እንልመድ፡፡ እናብላቸው፣ እናጠጣቸው፡፡ ከእኛ የሚፈልጉት አንድ ነገር ቢኖር የዕለት ጉርሳቸውን ብቻ ነው፡፡ እስቲ ዛሬ ሻይ ፣ ማኪያቶ ፣ ማስቲካ ከፍ ሲልም የምንጋተው አንድ ቢራ ይቅርብንና የእለት ጉርሱን የሚለምን አንድ ነዳያንን አለው እንበለው፡፡ ይሄ ፎቶ እንደ አጋጣሚ እነዚህ 2ሴቶችና 2ወንዶች ተነሱት እንጂ ሁላችንም ያው ነን፡፡
Show all...