1 283
Subscribers
No data24 hours
-17 days
+1530 days
Posts Archive
1 283
አላሁማ አጊስና፣ አላሁማ አጊስና፣ አላሁማ አጊስና።
አላሁማ እስቂና ገይተን ሙጊሳን፣ መሪአን፣ መሪአን፣ ናፊአን፣ ገይረ ዳርሪን፣ አጂላን ገይረ አጂል🙏🙏🙏
ነቢዩ ﷺ በድርቅ ጊዜ የኢስቲስቃ ሰላት እየሰገዱ አላህን በትህትና ይለምኑ ነበር።
1 283
#ኸሚስ_ሙባረክ
እሱ ሙሀመድ ...
ኑሩ የቀደመ ያ'ደምን ጭቃ፣
ለሱው ጀምሮ በሱው ያበቃ ።
የስሙ ሲልሲል ዓርሽ የደመቀው ፣
ጀሊል የሻለት ብቻ የሚያውቀው ።
የኩኑ ኩን ቃል የምስጢር ሳንዱቅ ፣
በኑን ውዳሴ የሚሸበረቅ ::
(በሁስነል ኹሉቅ)
ሙሐመድ በለኝ ..
የሀርፉ ሚስጥር ያዋልለኛል፣
ሀዘን መከራ በሚሙ ሺፋእ ይነሳልኛል ።
በ'ሐ' ክንብንብ ዱንያ ይዋጣል ፣
የ'ሚም' መደገም ...
ላሺቅ በልግ ነው ዙላል ያጠጣል ።
'ሙሐመድ' በለው
የቀን ጨለማን ፊቱ ይገ፤ፋል ፣
ወዳጅ ነው የሀቅ
እንደኔ እንዳንተ መቼ ይ-ገፋል ።
ያቅፋል ከደረት ሀድራውን ይዞ ደጁን ላንኳኳ፣
መቼም አዛኝ ነው ረኡፉ ያለው በስሙ መልካ ።
የሲሩን ሸራብ ...
ከሰሊው ቅንጥብ መቅመስ ብትሻ ፣
ከርር ልበሰው
መንገድ ተነሳ ለመዳረሻ ።
እሱ ሙሐመድ ...
ቃል አይወስፈው ሚስጥሩን ገልጦ፣
እንባ ይቀድማል ቀለሙን በልጦ ።
💚 اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا ومولانا محمد 💚!
📝አይዳ
1 283
#ኸሚስ_ሙባረክ
ቀዬውን ካማተርኩበት
ሀበሻ ኖሬ ወዳጁ ፣
ሰርክ ለት ባንኳኳሁ ቁጥር
መዘጋት አያውቅም ደጁ ።
ወትሮም ባዘል ነውና
ረኡፉ ሲል ያሞካሸው ፣
ዝምታው ለኔው መሆኑን
ነጋሪም ሰሚም አይዋሸው ።
አህመዴ በሚል ስርቅታ
ሙት አካል ነፍሱን ይዘራል ፣
በስሙ ነሁልሎ ቢታይ
አፍቃሪ ጅስሙ ይከራል ።
ቢደግም በአሚን ተራ
ስያሜ መጥሪያ አብጅቶ ፣
ለበይኩን በሐያት ማዱ
አይነፍግም ለአፍታ ከቶ ።
በሻሻነቱ ቢጠና
ከሆድም ሰፍቷል መቻሉ፣
ሰው መሳይ ከሰው የራቀ
በረበል ዒዛ መሰሉ ።
እሱማ ...
እሱማ የረቢዕ ረቢዕ
ለምለሙ የዘመን ዕጣን ፣
የኑህን ኪዳን የሞላው
በነጃህ መርከብ ያወጣን ፤
ኢብራሒም አለበት ግድም
ሚሙን ለሺፋእ ያዋሰ ፣
አደምን በዳሉ ደዋእ
ወደ ጀነቱ የመለሰ ።
በዒሳ የቃል ትንቢት ስር
ከመምጣት የተለፈፈ ፣
እሱ እንጂ በኢንጂሉ ላይ
ማን ደምቆ ጎልቶ ተፃፈ ።!
ወንድሙን ከሊም ያን ሙሳ
በባህር ድልድይ ሲታደግ ፣
የስሙ ጥላ ብቻውን
እስካፅናፍ ሲያረገርግ ።
ሙሐመድ ውቡ አይነታ
ከማል ጀማሉ የደመቀው ፣
አላህን ማየት የሻለት
ባንድ ቃል ቀድሩን የሚያውቀው ።
አጃኢብ ይሉት በሙላ ለነእቱ የተሰረገ ፣
ለሱ ሲል ሁሉ ጀምሮ ለሱ ሲል ሁሉ ያደገ ።
ከአደድ የማይስማማ
ያንድ ቀን ናፍቆቱን ማተት ፣
ለነፍሱ ቅንጣት ያላለ
ዘላለሙን ግን ለኡመት ።
ይህ ድንቁ የጌታ ካዝና
ባምሳሉ የተበጃጀው ፣
ጀነት ከወጅሑ ቁንፅል
ተነጥቶ የተደራጀው ።
እንደኛም ባይሆን በሱ አይነት
ኡመት መሆንን ባደለው ፣
ከዝነቱ ደጃፍ በስተቀር
በዳይ ሰው የት ነው ሚውለው ?።
የመውደድ ልኩን ለማተት
ቢደክም አያሌ ድርሳን ፣
ከታምር የሚያዘልቀው
ቃል ሁሉ ለመግለፅ ሲሳን።
💚اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا ومولانا محمد 💚!
📝አይዳ
1 283
መወለዱን ሰምተው ቃጥባሬ ወስጥ ያለው
እጅግ ተደስተው በያሉበት ዋለው
ጣራ በእጅ አንስተው በላይ ተንጠል ጥለው
ሊያዩት ጨንቋቸው ሄዱ ዘለውዘለው
ሸዋል ሊቃ ብለው እየተባረኩ
አብል ጀበል ግርማ አለወ ለመልኩ
ጌታዬ ሺሊላ በእጅ ያረገው ሙልኩ
አቡል ጀበል ግርማ አለው ለመልኩ🌙💚
1 283
በዒድ ቀን ሴቶች ነቢ ቤት ውስጥ በአጠገባቸው ዱፍ (ድቤ እየመቱ) በመንዙማ ፈታ ይሉ ነበር። ዓኢሻም ትመለከት ነበር። ሸሪዐውን ሳትለቁ ፈታ በሉ።
1 283
ጁሙዐና ዒድ ገጥመዋል። ዒድ የሰገደ ጁሙዐ አለመስገድ ይችላል የሚባለው እኛ ጋር አይሰራም። ዒድ የሰገደ ጁሙዐ አይቀርለትም።
(ፊ ሻፊዒያ)
1 283
🚨 ሰበር መረጃ
👉 የዒድ አል-ፊጥር በዓል #አርብ ይከበራል ።
ዛሬ ጨረቃ ባለመታየቷ ነገ ረመዷን 30 ሆኖ ዒድ አል ፊጥር በዓል ደግሞ #አርብ መጋቢት 11 እንደሚከበር ይፋ ተደርጓል ።
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ ከወዲሁ እንኳን ለ1447 ተኛው የዒድ አል ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳቹ ለማለት እንወዳለን ።
ኢድ ሙባረክ 🫶❤
1 283
ዛሬ 21ኛው የረመዷን ሌሊት ነው
በዱአ እንበርታ
🤍قال البغوي فى تفسيره
《《 قال المفسرون : " ليلة القدر خير من ألف شهر " معناه : عمل صالح في ليلة القدر خير من عمل ألف شهر ليس فيها ليلة القدر 》》
ትርጉም
"ለይለተል ቀድር ከአንድ ሺህ ወራት ትበልጣለች" የሚለውን ሙፈሲሮች እንዲህ ተርጉመውታል ፦
"በለይለተል ቀድር (በመወሰኛይቱ ሌሊት ) የሚሠራ ኸይር ሥራ ለይለተል ቀድር ከሌለችበት የአንድ ሺህ ወሮች ኸይር ሥራ ሁሉ ይበልጣል"🤍🪴
💡ተፍሲረል በገዊ
https://t.me/anwarulyeqin38
