916
Subscribers
-124 hours
+47 days
-330 days
Posts Archive
ግንቦት 05/2018 ዓ/ም
"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ ማኑፌስቶ ፣ የመወዳደርያ ምልክት እና እጩ ትውውቅ እንዲሁም ይፋዊ ቅስቀሳ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በኢንጌ ከተማ ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
“ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል፣ በዛሬው ዕለት በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በኢንጌ ካችመነት የሚገኙ ቀበሌዎች ታላቅ ይፋዊ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በደማቅ ሁኔታ ተካሄዷል።
በዚህ ይፋዊ የይምረጡን ቅስቀሳ ላይ ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ የተውጣጡ ከፍተኛ የፓርቲ አመራሮች፣የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ እጩዎች፣የፓርቲው አባላት እንዲሁም የኢንጌ አገልግሌት ነዋሪዎች፣ ወጣቶችና ሴቶች በነቂስ በመውጣት ለፓርቲው ያላቸውን ጽኑ አጋርነት ገልጸዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች "ብልፅግናን መምረጥ ልማትንና አብሮነትን መምረጥ ነው”የሚሉና ሀገራዊ አንድነት፣ ልማት፣ ሰላምና የዴሞክራሲ ሂደት እንዲጠናከር የሚጠይቁ መልዕክቶችን የያዙ ፅሁፎችና መፈክሮችን አሰምተዋል።
በመድረኩ የተገኙ አመራሮች እና የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ እጩዎች በንግግራቸው፣ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር የሁሉም ዜጎች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ ህዝቡ በመጪው ምርጫ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።
ባለፉት አምስት ዓመታት ሀገሪቱ በበርካታ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ፈተናዎች ውስጥ ብታልፍም፣ በግብርናውና በታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ረገድ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ትኩረታችን የጀመርናቸውን የልማት ስራዎች በማጠናከር የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ማምጣት ነው" ብለዋል።
በሁሉም ዘርፎች የሚታየውን እድገት በማስቀጠል የኢትዮጵያን ብልፅግና እውን ለማድረግ ህዝቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፓርቲው ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
ዛሬ የተካሄደው የቅስቀሳ መርሃ ግብር የብልፅግና ጉዞ የማይገታ መሆኑን ያሳየና ለቀጣዩ ምርጫ ትልቅ መነቃቃትን የፈጠረ እና የአባላቱንና የህዝቡን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ከመሆኑም ባለፈ፣ በቀጣይ ለሚከናወኑ የልማትና የፖለቲካ ስራዎች ትልቅ የሞራል ስንቅ የሚሆን መሆኑ ተመላክቷል።
የሳምንቱ ዓብይት ዜናዎች
ሚያዝያ 25/2018 ዓ.ም
🎤 የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የማኒፈስቶ፣ የምርጫ ምልክት የማስተዋወቅ እና የይምረጡኝ ቅስቀሳ ፕሮግራም ከመሀል አምባ ወጣቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የብልጽግናን ፓርቲ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ማስተዋወቂያና የይምረጡኝ ቅስቀሳ ከየቀበሌው ከተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ጋር የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 በበጀት አፈጻጸም ዙሪያ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤትገለጸ፡፡
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶች ይበልጥ እንዲጎለብቱና በቀጣይ የተቀመጡ ታላላቅ አገራዊ ግቦች ከግብ እንዲደርሱ የሴቶች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 በሰቆጣ ቃል ኪዳን ፕሮግራም በተገኘ ድጋፍ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ደነብ ቀበሌ ነፍሰ-ጡርና አጥቢ እናቶች እንዲሁም የስርዓተ ምግብ ጉድለት ላለባቸው ህፃናት 50 ፍየል ድጋፍ ተደረገላቸው።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 በ3ኛው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻንፒዮና ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ 🆚 ሚቶ ወረዳ ተጨወተ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ግንቦት 01/2018 ዓ/ም
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የማኒፈስቶ፣ የምርጫ ምልክት የማስተዋወቅ እና የይምረጡኝ ቅስቀሳ ፕሮግራም ከመሀል አምባ ወጣቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የወረዳው ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተማም አደም ለመድረኩ የተዘጋጃ መወያያ ሰነድ አቅርበዋል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ እና የወረደው የክልል ምክር ቤት እጩ አቶ ሚፋታ ሁሴን በመድረኩ እንደተናገሩት የስንዴ ነዶ በጥምር የተቀናጀ ህብረትንና አንድነት ማሳያ በመሆኑ ወጣቶችም በህብረትና በአንድነት ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሻገር ተቀናጅታችሁ የብልፅግና ልዕልናን ለመጨበጥ እናንተም የምርጫ ምልክታችን የስንዴ ነዶ መሆኑን አውቃችሁ ብልፅግና መምረጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
አቶ ሚፋታ አክለውም ወጣቶችን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ተጨባጭ ውጤት ማምጣታቸውን ጠቀሰው እነዚህ ተግባራት ቀጣይነት እንዲኖራቸው ብልጽግናን መምረጥ አማራጭ የሌለው መንገድ መሆኑን ተናግረዋል።
የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ኃላፊ እና የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ የፓርላማ እጩ ወይዘሮ ነጅብያ ማህሙድ በበኩላቸው ወጣቶች የዛሬ የሀገር ባለቤትና የነገ ተረካቢ በመሆናቸው ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሻገር በሚደረገው ጉዞ ሚናቸው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸው ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ የጥላቻ ንግግሮች አካባቢን በማጠልሸት ከእውነት የራቁ መረጃዎችን በመታገል እንዲታረሙ በማድረግ በመተባበርና የአንድነት ምልክት የሆነውን
የምርጫ ምልክታችን የስንዴ ነዶ በመሆኑ ብልጽግና ፓርቲን እንዲመርጡ መልእክት አስተላልፈዋል።
የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ረሻድ የፓርቲው ዓላማ ምርጫውን ሙሉ በሙሉ ሠላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ታኣማኒነት ያለው ሆኖ ለማሸነፍ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው ወጣቶች በትጋት እንዲሰሩ አሳስበዋል።
ወጣቶች ለኢትዮጵያ ብልፅግና በጋራ የምንሰራበት ወደ ተምሳሌት ሀገር የሚናሸጋግርበት ወቅት በመሆኑ በአካባቢያችን የሠላም ተምሳሌት በመሆን አባሎቻችን ብልፅግናን እንዲመርጡ ወጣቱ ትልቁን ድርሻ እንድትወስዱ በማለት አቶ ሙራድ ረሻድ ጥሪ አቅርበዋል።
የመድረኩ ተሳታፊ ወጣቶች በበኩላቸው እንደ ሀገር ፣በወረዳ ደረጃ እንዲሁም በመሀል አምባ ከተማ ላይ የተጀመረው ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማስቀጠል ምርጫን ብልጽግና በማድረግ ምርጫው ሠላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ አስገንዝበዋል።
ሚያዚያ 27/2018 ዓ/ም
ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶች ይበልጥ እንዲጎለብቱና በቀጣይ የተቀመጡ ታላላቅ አገራዊ ግቦች ከግብ እንዲደርሱ የሴቶች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለጸው "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የሴቶች ክንፍ የብልጽግናን ፓርቲ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክትና ማኒፌስቶ ማስተዋወቂያ መድረክ በተካሄደበት ወቅት ነው።
በመድረኩ ላይ ላለፉት አምስት ዓመታት በብልጽግና ፓርቲ መሪነት የተከናወኑ ስኬቶችና በቀጣይ የሚሠሩ ታላላቅ ግቦች ላይ ትኩረት ያደረገ የመወያያ ሰነድ የወረዳው ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈትያ መህዲ አማክኝነት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፋታ ሁሴን በመድረኩ ተገኝተው እንደገለጹት ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገርነት ለማሻገር የሴቶች ሚና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
ባለፉት አምስት ዓመታት በብልጽግና ፓርቲ መሪነት በሀገር አቀፍና በወረዳ ደረጃ የተከናወኑ የልማት ተግባራት ተጨባጭ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑንም ገልጸዋል።
ዋና አስተዳዳሪው አክለውም ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶች ይበልጥ እንዲጎለብቱና በቀጣይ የተቀመጡ ታላላቅ አገራዊ ግቦች ከግብ እንዲደርሱ የሴቶች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ኃላፊ እና የወረዳው የፓርላማ እጩ የሆኑት ወ/ሮ ነጅብያ ማህሙድ በበኩላቸው ብልፅግና ፓርቲ ለህዝብ የገባውን ቃል በተግባር በመፈፀም ለቃሉ የታመነ እና በስራው ውጤታማነት በተጨባጭ ያስመሰከረ ፓርቲ መሆኑን ገልፀዋል።
ብልጽግና ፓርቲ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጀመራቸው የልማትና የዴሞክራሲ ግንባታ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆን የአብሮነት፣ የጥንካሬ እና የአንድነት መገለጫ የሆነውን "የስንዴ ነዶ" በሁሉም አካባቢ እንዲመረጥ ሴቶች ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ወ/ሮ ነጅብያ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ፓርቲያችን ያስቀመጣቸውን የብልጽግና ግቦች ለማሳካት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸው የተጀመረው የብልፅግና ጉዞ ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የስንዴ ነዶን መምረጥ እንደሚገባ አስታውቀዋል።
ሚያዚያ 26/2018 ዓ/ም
በሰቆጣ ቃል ኪዳን ፕሮግራም በተገኘ ድጋፍ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ደነብ ቀበሌ ነፍሰ-ጡርና አጥቢ እናቶች እንዲሁም የስርዓተ ምግብ ጉድለት ላለባቸው ህፃናት 50 ፍየል ድጋፍ በዛሬው እለት ተደረገላቸው።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በሰቆጣ ቃል ኪዳን ፕሮግራም አማካኝነት በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ በደነብ ቀበሌ በተመረጡ ሞዴል መንደሮች በአራት መቶ ሺህ ብር በጀት በመመደብ
ለ50 እናቶች ለእያንዳዳቸወ 1 ሴት ፍየል በድምሩ 50 ፍየል ተሰራጭቷል።
ሰቆጣ ቃል ኪዳን ፕሮግራም መቀንጨርንና መቀጨጭን በማስቀረት ጤናማ እና አምራች ዜጋን ለመፍጠር እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
ሴት ፍየሎች የተሰጡበት ዋና አላማ የፍየል ወተት ስርዓተ ምግብን ለማሟላት ከላም ወተት የተሻለ ንጥረ ነገር በመያዙ ሲሆን ፍየሎችን በአግባቡ በመያዝ ወተታቸው ከሁለት አመት በታች ላሉ ህፃናትና አጥቢ እናቶች መጠቀም እንዳለባቸው ስልጠና ተሰጥቷል።
መረጃው የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ነው።
