917
Subscribers
-124 hours
+27 days
+930 days
Posts Archive
ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ማዕከል እና ታዳጊ ከተሞች ላይ "የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ውይይት ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በወረዳው በሚገኙ በተለያዩ አራት ማዘጋጃ ቤቶች "የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ የውይይት መድረኮች ተካሂደዋል።
መድረኮቹ በመሃል አምባ፣ኢንጌ፣ጅማ እና ኮንበል ማዘጋጃ ቤቶች ተካሂዷል።
ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ሰነድ ለተሳታፊዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የውይይት ዋና አላማው ህዝቡ ራሱ የተሳተፈባቸው የመደመር መንግስት ትሩፋት የሆኑ ዋና ዋና ስኬቶችና ቀጣይ ብስራቶች ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር እነዚህን ድሎችና ብስራቶችን ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገሩ ከማድረግ እንጻር ህዝቡ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ማዘጋጀት እንደሆነ ተመላክቷል።
በተጨማሪም በተለያዩ ግዚያት በህዝብ የተነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ መንግስት የሄደበትን ርቀትና የደረሰበትን ደረጃ ህዝቡ እንዲረዳ የሚያደረግ መድረክ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ብልጽግና ፓርቲ እና የመደመር መንግስት የልማቱ ባለቤት የሆነውን ህዝብ በማሳተፍ እና በማዳመጥ የሚያደርጉት ህዝባዊ ውይይት በቀጣይነት የመንግስትን የማስፈፀም አቅም እና የህዝቡን የነቃ ተሳትፎ እያጎለበተ ለመሄድ የሚያስችል ነው።
በመድረኩ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የተሠጠ ሲሆን መንግስት የህዝብ ጥያቄዎች ተቀብሎ በሂደት ለመመለስ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ተጠቁሞ በስኬት የተጀመሩ ስራዎች ከዳር በማድረስ ኢትዮጵያን ለማበልፀግ በሚደረገው በልማት ጉዞ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የበኩሉን መወጣት እንዳለበት በመግባባት መድረኮቹ ተጠናቀዋል።
በመድረኮቹ ላይ የዞንና የወረዳ መካከለኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም
"የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በመሃል አምባ ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በመድረኩ "የጉባ ብስራቶች ፣የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ፅሁፍ እና በየከተሞች የተሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷበታል።
በመድረኩ የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዶ ሀሠን፣የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንዲሁም የወረዳ አመራሮችና የመሃል አምባ ከተማ ነዋሪዎች
ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም
አዲሱ የ“ዜሮ ግቦች” ንቅናቄ ለኢትዮጵያ ብልጽግና
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተዋወቀው እና ሀገራችን ልትደርስበት የሚገባት አምስት ዋና ዋና የ“ዜሮ” ግቦች ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ያለመ ነው። እነዚህ አምስት ወሳኝ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፡-
1. ዜሮ ተረጂነት (Zero Dependency)
የትውልዱ ትልቁ እዳ የሆነውን ድህነት እና የእርዳታ ጠባቂነትን ታሪክ መቀየር በምግብ ራስን በመቻል ማንም ሰው ለምግብ እጁን የማይዘረጋበትን ሀገር መገንባት ዋናው ግብ ነው።
2. ዜሮ መሬት ጦም ማሳደር (Zero Uncultivated Land)
መሬት የሀብት ምንጭ ነው። አንዲትም ስንዝር መሬት ሳትታረስ እና ምርት ሳትሰጥ ጦሟን እንድታድር አይፈቀድም። በጋ እና ክረምት በመስራት ምርታማነትን ማሳደግ ግዴታ ነው።
3. ዜሮ ተፈናቃይነት (Zero Displacement)
ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ከቀያቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ እንዲኖሩ አይገባም። የተፈናቀሉትን መመለስ እና ዳግም መፈናቀል እንዳይኖር ዘላቂ ሰላምን ማስፈን።
4. ዜሮ ኮንትሮባንድ (Zero Contraband)
የሀገርን ኢኮኖሚ የሚቦረቡረውን እና ህጋዊ የንግድ ስርዓትን የሚያዛባውን የኮንትሮባንድ ንግድ ሙሉ በሙሉ ማድረቅ።
5. ዜሮ ሸፍታ እና ሌባ (Zero Crime/Banditry)
ሰላም ለሁሉም መሰረት ነው። በጫካ የታጠቁ ሀይሎችን (ሸፍታ) እና በከተማ የሚንቀሳቀሱ ሌቦችን በማጽዳት የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ሰላማዊ ሀገር መፍጠር።
እነዚህን "የዜሮ ግቦች" ለማሳካት የመንግስት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ ተሳትፎ ያስፈልጋል!!
ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም
የስርዓተ ጾታን ጉዳይ በልማት ሂደት ውስጥ ማካተት የሴቶችን አቅም ማሳደግና የውሳኔ ሰጭነት ብቃት ማሳደግ እንደሚገባ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ገለጸ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለጸው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ፅ/ቤት በስረዓተ ፆታ መካተት እና የልማት ለውጥ መመሪያ ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና በሰጠበት ወቅት ነው።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈቲያ መህዲ በመድረኩ ላይ ፆታዊ ጥቃት እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በሴቶችና ህፃናት ውስብስብ ችግሮች እንደሚያስከትሉ ጠቅሠው የስርዓተ ጾታን ጉዳይ በልማት ሂደት ውስጥ ማካተት የሴቶችን አቅም ማሳደግ፣ የውሳኔ ሰጭነት ብቃት ማሳደግና አሰራርን ማሻሻል ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሮ ፈትያ መህዲ ሌሎች በሁሉም ዘርፎች አካታችና እኩል ተጠቃሚነት ላይ አሳታፊ ለማድረግ ያለመ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል።
የስልጠና ሰነዱን ያቀረቡት የጽ/ቤቱ የሴቶችና ህጻናት ማካተትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ስራ ሂደት አስተባባሪ በአቶ መርሻ አስቻለው አማካኝነት ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይትና ምክክር ተካሄዷል።
ሴቶችና ህፃናት ተቋም የሴቶችን መብት ማስጠበቅ እንደሚገባው፣በሴቶች ላይ የሚደርሱ ፆታዊ ጥቃቶች ሁሉም በጋራ መከላከል እንደሚገባ፣ ወንጀል የፈፀሙ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ ማድረግ፣በየተቋማቱ የህፃናት ማቆያ መዘጋጀት እንዳለበት እንዲሁም ሴቶችን በጎልማሳ ትምህርት ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ያሉት የስልጠና ተሳታፊዎቹ የተሠጠው ግንባዜ ጥሩ ነው ሁሉም የሚመለከተው ባለሙያ ወደ ራሱ ተቋም ወስዶ መስራት ያስፈልጋል፣ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ የተሳካ እንዲሆን ቅንጅታዊ አሠራሮች ማጠናከር እንደሚገባ ከመድረኩ ተመላክቷል።
የወረዳው ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈቲያ መህዲ ከመድረኩ ለተነሱ ሀሳብ አስተያየት ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሰው ጥቃት በየደረጃው የሚገኙ አካላት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልጸው ለሴቶች መብት ጥሰት የተጋለጡ ሴቶችን ተገቢውን ፍትህ እንዲያገኙ እንዲሁም አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም ወ/ሮ ፈትያ ባስተላለፉት መልዕክት
ከፆታዊ ጥቃት የፀዳ እና ለሴቶች ሚመች አከባቢ ለመፍጠር ሁሉም ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
በስልጠና መድረኩ የተቋማት የስርዓተ ፆታ ተጠሪዎች እና ልማት እቅድ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
ታህሳስ 09/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ
"በመደመር መንግስት እይታ፤ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ
"በመደመር መንግስት እይታ፤ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ ከታህሳስ 6 እስከ 09/2018 ዓ.ም በየማህበራዊ መሰረቱ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
የስልጠናውን መጠናቀቅ አስመልክተው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳ እንዳሉት "በመደመር መንግስት ዕይታ ፤ የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሃሳብ በየማህበራዊ መሰረቱ የሚገኘው አመራርና አባላት በግብርና ፣ በአምራች ኢንደስትሪ ፣ በከተማ ልማትና በቱሪዝም ዘርፎች በሁሉም ማህበራዊ መሰረት በሁለት ዙር ከታህሳስ 6 እስከ 09/2018 ዓ.ም ከ19 ሺህ በላይ ለሆኑ አባላት ስልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል።
የመደመር መንግስት እሳቤ አካታች እንዲሁም ለፈጠራና ለአዳዲስ ሃሳቦች ትኩረት የሚሰጥ ነው ያሉት አቶ አ/ረሂም ስልጠናው በተሰጡት አራቱም ዘርፎች ላይ ተጨማሪ አቅም የሚገነባ ሁለተናዊ ብልፅግናን የምናሳካበት ንድፍ ሀሳብ በመያዝ ትጋት በመጨመር በፍጥነት በመተግበር ኃላፊነታችንን መወጣት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በጠንካራ የአመራር ስርዓት የግብርና የገጠር መዋቅራዊ ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ውጤታማ ለማድረግ፣የኢንዱስትሪ ዘርፉን ስኬትማነት ማረጋገጥ፣ከተሜነትን በማስፋፋት የተሻለ የአኗኗር ዘይቤን በመፍጠር የወረዳችንን ፀጋዎች በመለየት የቱሪዝም ዘርፍ እመርታን ለማረጋገጥ ስልጠናው አቅም መሆኑን የፓርቲ ኃላፊው አክለው ገልጸዋል።
በመጨረሻም አቶ አ/ረሂም ባስተላለፉት መልዕክት
ስልጠናው በተቀመጠው አቅጣጫ እንዲሳካ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ጀምሩ በርካታ ስራዎች ሲያከናውኑ ለነበሩ አካላት በወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ስም እና በራሳቸው ስም ላቅ ያላ ምስጋናቸውን አስተላልፈዋል።
ታህሳስ 09/2018 ዓ.ም
የእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፉን በማዘመንና ውጤታማ በማድረግ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት እስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ደነብ ቀበሌ ነዋሪ ለሆኑት ለአቶ ስራጅ ሠማን ከኮንሶ ፍየል ምርምር ማዕከል 70 ፍየሎች ማምጣቱን ጽ/ቤቱ አክሎ አስታውቋል።
የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ እና የእንስሳት ዘርፍ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ፈድሉ ኡስማን በወረዳችን በእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ላይ መስራት አንዱ የመለወጫ መንገድ በመሆኑ ያለንን ፀጋ በመለየትና የመፍትሄ ሀሳብ በማመንጨት የህዝብን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ እንደሆነ ገልጸዋል።
አቶ ፈድሉ አክለውም በዶሮ እርባታ፣በወተት ላም፣በበሬ፣ በበግ ማድለብና በእርባታ፣በዝርያ ማሻሻል፣በንብ እርባታ ላይ በልዩ ትኩረት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሠው በዘንድሮ በጀት አመት
የአነስተኛ አመንዣጊ ስጋ ሀብት ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል 6032 ፍየሎች ለማሞከት ታቅዶ በግማሽ አመቱ 4050 ፍየሎች ማሞከት እንደተቻለ ገልጸው
አርሶ አደሩን የተሻሻለ ዝርያ ተጠቃሚ እንዲሆን
እንደ ሀገር በምርታማነቱ በሚታወቀው ኮንሶ ፍየል ምርምር ማዕከል በተለያዩ ጊዜያት በማምጣት ከአካባቢ ፍየሎች በማዳቀል የስጋ ምርቶች ላይ
ከፍተኛ ለውጥ መታየቱን አስገንዝበዋል።
በተያየዘም በበጀት አመቱ 60 የኮንሶ ፍየል ለማምጣት መታቀዱን የገለጹት አቶ ፈድሉ ኡስማን እስካሁን 70 ፍየሎች በማምጣት መሰራጨቱን ተናግረዋል
አርሶ አደር ስራጅ ሠማን የደነብ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ በእንስሳት ዘርፍ ለመሰማራት በተለይም ፍየል በማሞከት፣በማር ምርት እንዲሆም በሌሎችም ዘርፎች ለመስራት በርካታ እንቅስቃሴ እያደርጉ መሆናቸውን ገልጸው የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ከባለሙያ ድጋፍና ክትትል ባሻገር የትራንስፖርት ወጪ በመሸፈን ከኮንሶ ፍየል ምርምር ማዕከል 70 ፍየሎች እንዲመጣለቸው በማድረጉ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበው ድጋፍና ክትትሉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
“የመደመር እሳቤ በመላው ሕንድ የታወቀ ነው”:- ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ ኢትዮጵያ እና ሕንድ በከፍተኛ የራስ መተማመን ወደ መፃኢ ጊዜ የሚጓዙ ጥንታዊ ሥልጣኔዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለቱ ሀገራት የጋራ የሆኑ እሳቤዎች ላይ በማተኮር አብራርተዋል።
በማብራሪያቸውም የመደመር እሳቤ 'synergy' በመላው ሕንድ የታወቀ ስለመሆኑ አንሥተዋል።
ኢትዮጵያን ሲገልጹም፣ “ዛሬ ኢትዮጵያ ከፍ ብላ ቆማለች፣ ምክንያቱም ሥሯ ጥልቅ ነው፤ የኢትዮጵያ ምድር ላይ መቆም ያለፈው ታሪኳ ክብር ላይ መቆም፣ በአሁኑ ጊዜ ዓላማዋ መሞላት እና መፃኢ ጊዜን በታላቅ ጉጉት መቀበል ነው” በማለት ነው።
የጥንቱን እና አዲሱን አዋህዶ መያዝ፣ በጥንታዊ ጥበብ እና በዘመናዊነት ሕልም መካከል ሚዛን መጠበቅ እውነተኛ የኢትዮጵያ ችሎታ እንደሆነም ጠቁመዋል።
ከአንድ ድንጋይ የተቀረፀው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በኢትዮጵያ እንዳለ ሁሉ በሕንድም ከአንድ ድንጋይ የተቀረፀ ጥንታዊ ቤተ መቅደስ መኖሩን ጠቁመው፣ ሁለታችንም ወደ መፃኢ ጊዜ በራስ መተማመን የምንጓዝ የጥንታዊ ሥልጣኔ ባለቤቶች ነን ሲሉ የሀገራቸውን ከኢትዮጵያ ጋር መመሳሳል ገልጸዋል።
ለእያንዳንዳችን ዕድት እርስበርስ በመተማመን እና በጋራ ጥረት በአብሮነት መጓዝ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።
የሕንድ ብሔራዊ መዝሙር እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ሀገራቸውን ‘እናት' ብለው ነው የሚገልጹት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ እነዚህ መዝሙሮች በቅርሶቻችን፣ በባህሎቻችን፣ በብሔራዊ ውበቶቻችን እንድንኮራ እና እናት ሀገራችን ብለን የምንነጠራትን ሀገር እንድንጠብቅ የሚያደርጉን ናቸው በማለት ገልጸዋቸዋል።
EBC
