ru
Feedback
የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

Открыть в Telegram
917
Подписчики
-124 часа
+27 дней
+930 дней
Архив постов
ታህሳስ 09/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "በመደመር መንግስት እይታ፤ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "በመደመር መንግስት እይታ፤ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ ከታህሳስ 6 እስከ 09/2018 ዓ.ም በየማህበራዊ መሰረቱ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ የስልጠናውን መጠናቀቅ አስመልክተው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳ እንዳሉት "በመደመር መንግስት ዕይታ ፤ የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሃሳብ በየማህበራዊ መሰረቱ የሚገኘው አመራርና አባላት በግብርና ፣ በአምራች ኢንደስትሪ ፣ በከተማ ልማትና በቱሪዝም ዘርፎች በሁሉም ማህበራዊ መሰረት በሁለት ዙር ከታህሳስ 6 እስከ 09/2018 ዓ.ም ከ19 ሺህ በላይ ለሆኑ አባላት ስልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል። የመደመር መንግስት እሳቤ አካታች እንዲሁም ለፈጠራና ለአዳዲስ ሃሳቦች ትኩረት የሚሰጥ ነው ያሉት አቶ አ/ረሂም ስልጠናው በተሰጡት አራቱም ዘርፎች ላይ ተጨማሪ አቅም የሚገነባ ሁለተናዊ ብልፅግናን የምናሳካበት ንድፍ ሀሳብ በመያዝ ትጋት በመጨመር በፍጥነት በመተግበር ኃላፊነታችንን መወጣት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በጠንካራ የአመራር ስርዓት የግብርና የገጠር መዋቅራዊ ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ውጤታማ ለማድረግ፣የኢንዱስትሪ ዘርፉን ስኬትማነት ማረጋገጥ፣ከተሜነትን በማስፋፋት የተሻለ የአኗኗር ዘይቤን በመፍጠር የወረዳችንን ፀጋዎች በመለየት የቱሪዝም ዘርፍ እመርታን ለማረጋገጥ ስልጠናው አቅም መሆኑን የፓርቲ ኃላፊው አክለው ገልጸዋል። በመጨረሻም አቶ አ/ረሂም ባስተላለፉት መልዕክት ስልጠናው በተቀመጠው አቅጣጫ እንዲሳካ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ጀምሩ በርካታ ስራዎች ሲያከናውኑ ለነበሩ አካላት በወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ስም እና በራሳቸው ስም ላቅ ያላ ምስጋናቸውን አስተላልፈዋል።

ታህሳስ 09/2018 ዓ.ም የእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፉን በማዘመንና ውጤታማ በማድረግ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት እስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ደነብ ቀበሌ ነዋሪ ለሆኑት ለአቶ ስራጅ ሠማን ከኮንሶ ፍየል ምርምር ማዕከል 70 ፍየሎች ማምጣቱን ጽ/ቤቱ አክሎ አስታውቋል። የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ እና የእንስሳት ዘርፍ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ፈድሉ ኡስማን በወረዳችን በእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ላይ መስራት አንዱ የመለወጫ መንገድ በመሆኑ ያለንን ፀጋ በመለየትና የመፍትሄ ሀሳብ በማመንጨት የህዝብን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ እንደሆነ ገልጸዋል። አቶ ፈድሉ አክለውም በዶሮ እርባታ፣በወተት ላም፣በበሬ፣ በበግ ማድለብና በእርባታ፣በዝርያ ማሻሻል፣በንብ እርባታ ላይ በልዩ ትኩረት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሠው በዘንድሮ በጀት አመት የአነስተኛ አመንዣጊ ስጋ ሀብት ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል 6032 ፍየሎች ለማሞከት ታቅዶ በግማሽ አመቱ 4050 ፍየሎች ማሞከት እንደተቻለ ገልጸው አርሶ አደሩን የተሻሻለ ዝርያ ተጠቃሚ እንዲሆን እንደ ሀገር በምርታማነቱ በሚታወቀው ኮንሶ ፍየል ምርምር ማዕከል በተለያዩ ጊዜያት በማምጣት ከአካባቢ ፍየሎች በማዳቀል የስጋ ምርቶች ላይ ከፍተኛ ለውጥ መታየቱን አስገንዝበዋል። በተያየዘም በበጀት አመቱ 60 የኮንሶ ፍየል ለማምጣት መታቀዱን የገለጹት አቶ ፈድሉ ኡስማን እስካሁን 70 ፍየሎች በማምጣት መሰራጨቱን ተናግረዋል አርሶ አደር ስራጅ ሠማን የደነብ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ በእንስሳት ዘርፍ ለመሰማራት በተለይም ፍየል በማሞከት፣በማር ምርት እንዲሆም በሌሎችም ዘርፎች ለመስራት በርካታ እንቅስቃሴ እያደርጉ መሆናቸውን ገልጸው የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ከባለሙያ ድጋፍና ክትትል ባሻገር የትራንስፖርት ወጪ በመሸፈን ከኮንሶ ፍየል ምርምር ማዕከል 70 ፍየሎች እንዲመጣለቸው በማድረጉ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበው ድጋፍና ክትትሉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

“የመደመር እሳቤ በመላው ሕንድ የታወቀ ነው”:- ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ ኢትዮጵያ እና ሕንድ በከፍተኛ የራስ መተማመን ወደ መፃኢ ጊዜ የሚጓዙ ጥንታዊ ሥልጣኔዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለቱ ሀገራት የጋራ የሆኑ እሳቤዎች ላይ በማተኮር አብራርተዋል። በማብራሪያቸውም የመደመር እሳቤ 'synergy' በመላው ሕንድ የታወቀ ስለመሆኑ አንሥተዋል። ኢትዮጵያን ሲገልጹም፣ “ዛሬ ኢትዮጵያ ከፍ ብላ ቆማለች፣ ምክንያቱም ሥሯ ጥልቅ ነው፤ የኢትዮጵያ ምድር ላይ መቆም ያለፈው ታሪኳ ክብር ላይ መቆም፣ በአሁኑ ጊዜ ዓላማዋ መሞላት እና መፃኢ ጊዜን በታላቅ ጉጉት መቀበል ነው” በማለት ነው። የጥንቱን እና አዲሱን አዋህዶ መያዝ፣ በጥንታዊ ጥበብ እና በዘመናዊነት ሕልም መካከል ሚዛን መጠበቅ እውነተኛ የኢትዮጵያ ችሎታ እንደሆነም ጠቁመዋል። ከአንድ ድንጋይ የተቀረፀው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በኢትዮጵያ እንዳለ ሁሉ በሕንድም ከአንድ ድንጋይ የተቀረፀ ጥንታዊ ቤተ መቅደስ መኖሩን ጠቁመው፣ ሁለታችንም ወደ መፃኢ ጊዜ በራስ መተማመን የምንጓዝ የጥንታዊ ሥልጣኔ ባለቤቶች ነን ሲሉ የሀገራቸውን ከኢትዮጵያ ጋር መመሳሳል ገልጸዋል። ለእያንዳንዳችን ዕድት እርስበርስ በመተማመን እና በጋራ ጥረት በአብሮነት መጓዝ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። የሕንድ ብሔራዊ መዝሙር እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ሀገራቸውን ‘እናት' ብለው ነው የሚገልጹት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ እነዚህ መዝሙሮች በቅርሶቻችን፣ በባህሎቻችን፣ በብሔራዊ ውበቶቻችን እንድንኮራ እና እናት ሀገራችን ብለን የምንነጠራትን ሀገር እንድንጠብቅ የሚያደርጉን ናቸው በማለት ገልጸዋቸዋል። EBC

ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሀሳብ የብልፅግና ፓርቲ የመምህራንና የፐብሊክ ሰርቫንት አባላት ስልጠና መድረክ ተጀምሯል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ስልጠናው "በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬን ጨምሮ ተከታታይ ሁለት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።

ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም "በመደመር መንግስት እይታ፣የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሃሳብ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለፓርቲ አባላት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ‎ "በመደመር መንግስት እይታ፣የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሃሳብ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ለኢንተር ፕራይዞች፣ለከተማ ነዋሪዎች እና ለአርሶ አደር የፓርቲ አባላት ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረወ ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል። የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ እና የወረዳው ደጋፊ አመራር የሆኑት አቶ አብዶ ሀሰን ስልጠናው ማጠቃለያ አስመልክተው እንዳሉት "በመደመር መንግስት ዕይታ ፤ የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሃሳብ በየደረጃው የሚገኘው አመራርና አባላት በግብርና ፣ በአምራች ኢንደስትሪ ፣ በከተማ ልማትና በቱሪዝም ዘርፎች የተዘጋጁ ሰነዶች በዝርዝር የቀረቡበት ስልጠና መሆኑን በመግለፅ ለነዚህ ዘርፎች መንግስት የሰጠውን ትኩረት በመረዳት የመደመር መንግስት የአመራርና የአባላት ባህሪን በመላበስ የተጀመረውን ሀገራዊ የከፍታ ጉዞ በውጤታማነት መምራት የሚያስችል አቅም እንዲፈጥር ያለመ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በበኩላቸው ስልጠናው በመደመር መንግሥት እይታ የግብርና እና የገጠር ትራንስፎርሜሽን ፣የቱሪዝም እና የከተማ ልማት እምርታ በሚሉ በተመረጡ ርእሰ -ጉዳዮች ዙርያ ለአባላቱ የግንዛቤ መስጠቱን ገልጸው የተቀመጡ አቅጣጫዎች በተገቢው ተገንዝቦ በመተግበር ሁለንተናዊ ብልፅግና የተረጋገጠባትን ታላቅ ሀገር በመፍጠር ሂደት የፓርቲው አባላት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በሚገገባ እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል። ስልጠናው በአመራርና አባላት መካከል የአመለካከትና የተግባር አንድነትን በመፍጠር አመራሩና አባላቱ የብልፅግና እሳቤን በተጨባጭ እንዲተገብር ስለሚያስችል ሰልጣኝ አባላት በወሰዱት ስልጠና መሰረት ወደ ተግባር መቀየር እንዳለባቸው አቶ ሚፍታ ሁሴን አስገንዝበዋል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳ በሁለት ቀናት የስልጠና ቆይታ አስመልክተው እንደገለጹት "የመደመር መንግስት እይታ ፣ የግብርና ፣ የኢንዱስትሪ፣ የከተማ ልማት እና የቱሪዝም ዘርፎች እምርታ" በሚሉ ርዕሶች ስልጠና የተሰጠ መሆኑን ጠቅሠው በስልጠናውም የመደመር መንግስት የሀገርን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በተለዩ ዋና ዋና ዘርፎች ያስቀመጣቸውን የልማት ትልሞችንና የትግበራ አቅጣጫዎችን በተመለከተ የብልፅግና ፓርቲ አባል በቂ የሆነ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና ያለንን ፀጋ በመጠቀም እንዴት ማደግና መበልፀግ እንደሚቻል የእይታ ለውጥ የሚያመጣ እና የአባሎቻችን ትጋት የሚጨምር እና ለለውጥ የሚያነሳሳ ስልጠና እንደነበር ተናግረዋል። አቶ አ/ረሂም በመጨረሻም ባስተላለፉት መልዕክት የመጀመሪያው ዙር ለኢንተር ፕራይዞች፣ለከተማ ነዋሪዎች እና ለአርሶ አደር የፓርቲ አባላት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እንዲሳካ ከቅድመ ዝግጀት ጀምሮ በርካታ ስራዎች መፈጸማቸውና ስልጠናውም ስኬታማ መሆኑን ጠቅሠው ሁለተኛ ዙር ስልጠና ማለትም የመንግስት ሠራተኞች እንዲሁም የመምህራ አባላት ስልጠና ነገ እሮብ ታህሳስ 08 ከጥዋቱ 2፡30 ጀምሮ በተዘጋጁ ማስልጠኛ ማዕከላት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ‎"በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሃሳብ የአርሶ አደር፣የከተማ ነዋሪዎች እና ኢንተርፕራይዞች ስልጠና ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በዛሬው እለትም በመደመር መንግስት እይታ የከተማ ልማትና የቱሪዝም ዘርፍ እምርታ በሚል ርዕስ ስልጠናው እየተካሄደ ይገኛል። የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳ የስልጠናውን ሂደት በመከታተልና መልዕክት በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ።