925
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
+930 days
Posts Archive
ጥቅምት 08/2019 ዓ.ም
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመሃል አምባ ቁባ ጃሚዓ የቁርአን ሂፍዝ ማዕከል ለ8ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 72 የሂፍዝ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት አሰመረቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የወረዳው እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ሼህ አ/በር ዘይኑ ለተመራቂ ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
መርከዙ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የማህበረሰቡን ኢስላማዊ ህልውና እሴቶች አንድነቱን መጠበቅና ማስጠበቅ፣ ከአካባቢውና አጎራባች ተወላጅ ዳዒዎችንና ኢማሞችን ማፍራት፣ ኢስላማዊ ተቋማት ማቋቋምና መደገፍ የመርከዙ ዋና ዓላማ መሆኑን የገለጹት ሼህ አ/በር ዘይኑ ከዚህ ረገድም አሁን ላይ አበረታች ውጤት እየተመዘገበበት እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አክለውም ቁባ የቁርዓንና ሂፍዝ ማዕከል ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በ8 ዙር ወ= 189 ሴ = 61 በድምሩ 250 ተማሪዎች ያስመረቀ ሲሆን ዛሬው እለት በዚህ ዙር ወንድ= 35 ሴት=37 በድምሩ = 72 ተማሪዎች ማስመረቅ መቻሉን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ሼህ አ/በር ዘይኑ ባስተላለፉት መልዕክት የቁባ የሂፍዝ ማዕከል ለመማር ያለው ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ የመማር ፍላጎት እያደገ የመጣ ቢሆንም እንደ ቁባ የሂፍዝ መዓከል ተማሪዎችን በከፍቸኛ ቁጥር ተቀብሎ ለማስተማር የፋይናስ እጥረት እየገጠመን ስለሆነ ሁሉም በአቅሙ ርብርብና ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈው ፣ተመራቂዎች በመርከዝ ቆይታቸው ያገኙትን የዲን እውቀት ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንደሚጠበቅባቸው ያስገነዘቡ ሲሆን መርከዙ ለዚህ ደረጃ መብቃት የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ ላሉ አካላት ምጋናቸውን አቅርበዋል።
የእለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በበኩላቸው ወረዳችን ቀን ከማታ የሚቀራበት፣ ሰው አክባሪ ኡስታዞች መገኛ፣ በፍላጎት ልክ የሚታፈዝበት፣ ኢልምና ቁርዓን ሞልቶ ወደ ሚታፈስበት የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ እንግዶች እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ተመራቂ ተማሪዎች፣ ወላጆችና መላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ በወረዳው መንግስትና ህዝብ ስም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አቶ ሚፍታ አያይዘውም ቅዱስ ቁርዓን ዘመን የማይሽረው፣ ድንበር የማይገታው የአላህ ቃል ነው፣ ይህን የአላህ ቃል ለማፈዝ፣ ጊዜ ትዕግስት፣ ትህትና፣ ሰው ማክበር፣ ቅንነት፣ ትጋት፣ ጥረት፣ አንድነትና ጽናት ይጠይቃል።
በመሆኑም ተመራቂዎች ይህንን ሁሉ አልፋችሁ ለምረቃት በመብቃታችሁ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ዲናችንን ለመጠበቅ ተቀራርበን እንነጋገር በማለት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በጋራ ጉዳይ መነጋገር እንደሚገባው ገልፀው፣ወረዳችን በኢትዮጵያ እስልምና ታሪክ ታላቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የተለያዩ መሻይኮችና ኡስታዞች መፍለቂያ በመሆኗ ከወረዳችን ቀድሞ የነበረው ታሪክ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል ።
በወረዳው በርካታ ቁጥር ያላቸው መድረሳዎችና የሂፍዝ ማዕከላት የሚገኙ ሲሆን ከነዚህ ማዕከላት በርካቶች ቁርዓን ሀፍዘዋል እያፈዙም ይገኛሉ፣ በመሆኑም ይህንን ቀላል የማይባል አቅም በመረዳት ወረዳችን እና ሃገራችንን ሊለውጥ የሚችል ስራ ልንጠቀምበት እንደሚገባ ገልፀዋል ።
በመድረኩ ላይ የሃይማኖት አባቶች ሃይማኖታዊ ትምህርት የሰጡ ሲሆን ተጋባዥ እንግዶች ደግሞ ልዩ ልዩ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም በመርከዝ ቆይታቸው የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ሃፊዞች እና ለኡስታዞች ልዩ ልዩ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ከአልኑር ኢስላማዊ በጎ አድራጎት ድርጅት የተዘጋጀላቸውን የማበረታቻ ሽልማት ከእለቱ ተጋባዥ እንግዶች እጅ በመቀበል ፣ተመራቂ ተማሪዎችና የተመራቂ የተማሪ ወላጆች ቀጣይ ሁለት አመት አካባቢያቸው እንደሚያገለግሉ ቃለ መሀላ ገብተዋል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ከአ/አበባ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ አሊሞች፣ ኡስታዞች፣ ኡለማዎች፣ የሃግር ሽማግሌዎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና ሌሎችም ተገኝተዋል ።
ጥቅምት 03/2019 ዓ/ም
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶች እና ህፃናት ፅህፈት ቤት ከትምህርት ፅህፈት ቤት ጋር በመተባበር የልጃገረዶች ቀንን በደማቅ ሁኔታ አከበረ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶች እና ህፃናት ፅህፈት ቤት ከወረዳው ትምህርት ፅህፈት ቤት ጋር በጋራ በመሆን የልጃገረዶች ቀንን በገደባኖ ሁለተኛ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት በደማቅ ሁኔታ በዛሬው እለት አክብሯል።
በዓሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ14ኛ ጊዜ “End child marriage and invest in girls' rights” (የሕፃናት ጋብቻን አስወግዱ፣ በሴት ልጆች መብት ላይ ኢንቨስት አድርጉ) በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን፣ በሀገራችን ደግሞ ለ9ኛ ጊዜ “የታዳጊ ሴት ልጆችን ህልም፤ የኢትዮጵያ የነገ ተስፋ” በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ውሏል።
ይህ በዓል በትምህርት ቤቶች መከበሩ ታዳጊ ልጃገረዶች በትምህርታቸው እንዲበረቱ፣ መብቶቻቸውን እና ግዴታዎቻቸውን በአግባቡ እንዲረዱ እንዲሁም በትምህርት ቤት ቆይታቸው የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት በዕለቱ ተገልጿል።
በተለይም ያለ ዕድሜ ጋብቻ ያሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በመከላከል የሴት ልጆችን የወደፊት ህልም ማሳካት እንደሚገባ የፅህፈት ቤቶቹ ኃላፊዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዕለቱ የነበረውን ስነ-ስርዓት ይበልጥ ደማቅ ያደረገው በተማሪዎች የቀረቡት አስተማሪ ድራማዎች እና ማራኪ ግጥሞች ነበሩ።
ተማሪዎቹ በግጥም እና በድራማ ስራዎቻቸው የልጃገረዶችን አቅም፣ ያለዕድሜ ጋብቻ በሴት ልጆች የወደፊት ህይወት ላይ የሚያመጣውን ጉዳት እና ህብረተሰቡ ለሴት ልጆች ትምህርት ሊሰጠው የሚገባውን ትኩረት በግልጽ አሳይተዋል።
በፕሮግራም ላይ የልጃገረዶች የማበረታቻ የሽልማት ስነ-ስርዓት የተካሄደ ሲሆን ከ9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ባሉት የትምህርት ደረጃዎች ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ጎበዝ ሴት ተማሪዎች ልዩ ሽልማትና እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በበዓሉ ማጠቃለያ ላይም በትምህርት ቤቶች ውስጥ የልጃገረዶች ክበባትን ማጠናከር በሚቻልባቸው እና ተማሪዎችን ደጋፊ የሆኑ የትምህርት አካባቢዎችን መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
በዚህ ደማቅ የአከባበር ስነ-ስርዓት ላይ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትምህርት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ኬኔ፣ የሴቶችና ህፃናት ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈትያ መህዲ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ጥቅምት 03/2019 ዓ.ም
ከተረጂነት_ወደ_ምርታማነት
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጉራጌ ዞን፣ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ፣ አንበልታ ቀበሌ በሥራ ዕድል ፈጠራ የተደራጁ ወጣቶች በኩታ ገጠም ከ20 ሄክታር በላይ መሬት ላይ የጤፍ ልማት ሥራ እያከናወኑ ይገኛሉ።
ይህ የጋራ የግብርና ልማት ተግባር ወጣቶች በጋራ በመደራጀት ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ፣ የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩና ከተረጂነት ወደ ራስን መቻል እንዲሸጋገሩ የሚያግዝ ተግባራዊ ምሳሌ ነው።
መስከረም 29/2019 ዓ.ም
በ2018 ዓ.ም ለሕብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ኃላፊነታቸውን ለተወጡ ግንባር ቀደም የመንግስት ተቋማትና ባለሙያዎች እውቅናና ሽልማት መስጠቱን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ፅህፈት ቤት አስታወቀ ።
፨፨፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨
ይህን ያስታወቀው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት የእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር በዛሬው እለት ባካሄደበት ወቅት ነው።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፋሪስ ከማል የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ጽ/ቤቱ የ2018 ዕቅድ አፈፃፀምን በመገምገም በተቋም አፈፃፀማቸው የተሻሉ ተቋማትና ፈጻሚዎችን በእውቅናና ሽልማት አሰጣጥ መመሪያ መሠረት የተዘጋጀ የሴክተር ጉባኤ መሆኑን ተናግረዋል።
የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ የእውቅናና ሽልማት ስርዓት በመዘርጋትና በመተግበር ተቋማዊ የለውጥ መሣሪያዎችን ስራ ላይ በማዋልና ተቋማዊ መሠረት እንዲኖር በማድረግ ውጤታማነትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስና ተልዕኮውንና ስትራቴጂውን ለማሳካትና የበለጠ ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆን ማስቻል መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ፋሪስ አክለውም የአፈፃፀም ውጤትን ከእውቀት፣ ከአመለካከት፣ ከክህሎትና ከግብዓት አጠቃቀም ጋር በማጣጣም ቀጣይነት ያለውን አፈፃፀምን ለማሻሻል፣ ፈጠራንና አምቅ አቅምን በመጠቀም ውጤታማ የመሆን ዕድልን ለማበረታታት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ ሚፍታ ሁሴን በበኩላቸው እውቅናና ሽልማት መስጠት በውጤታማ ባለሙያዎችና ተቋማት መካከል የሥራ ተነሳሽነትን ከማጠናከር ባለፈ፣ ሌሎችም ከተሻሉ ተሞክሮዎች በመማር የሥራ አፈጻጸማቸውን እንዲያሻሽሉ የሚያግዝ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚህም ሁሉም መሥሪያ ቤቶችና ባለሙያዎች የሕዝብን ጥቅም በማስቀደም፣ በግልጽነትና በተጠያቂነት በመሥራት በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ጥረታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
በአጠቃላይ የፐብሊክ እውቅናና ሽልማት መርሐ ግብሩ በወረዳው ውስጥ የውጤታማነት ባህልን ለማሳደግ፣ በባለሙያዎችና በተቋማት መካከል ጤናማ የሥራ ውድድርን ለማበረታታትና ለሕዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ለማሻሻል አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ፋሪስ ከማል የ2018 በጀት ዓመት የተቋም አፈፃፀም ሪፖርት፣ናየ2019 ዓ.ም ዕቅድ እንዲሁም የምዘና ውጤት ሪፖርት አቅርበዋል ።
በ2018 በጀት አመት አጠቃላይ አፈፃፀም የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተቋማት፣ ፈፃሚዎችና ቀበሌዎች የሽልማትና የእውቅና መርሐ ግብር ተካሂዷል።
በዚህም መሰረት በተቋማት ፦
1ኛ ኢንተርፕራይዝ ፅ/ቤት
2ኛ ፋይናስ ፅ/ቤት
3ኛ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፍርድ ቤት ከ1ኛ -3ኛ ደረጃ ሲወጡ ከሴክተር ፈፃሚዎች ፦
1ኛ አ/ከሪም ሁሴን ከፋይናንስ ፅ/ቤት
2ኛ መሀመድሳኒ ሰኢድ ከገቢዎች ፅ/ቤት
3ኛ ሀቢብ ሻንቆ ከፍትህ ፅ/ቤት
በሳይት ደረጃ ተሸላሚዎች
1 አበበ አምሳሉ — ከግብርና ዘርፍ
2 ጌታሁን ዳኜ — ከኢንተርፕራይዝ ዘርፍ
3 መሀመድ ሳኒ — ከሆስታል ዘርፍ
በቀበሌ ደረጃ
1ኛ ረምዚያ በንቲ---የደነብ ቀበሌ ስራስኪያጅ
2ኛ ጀማል በድሩ — የገሬኖ ቀበሌ ስራስኪያጅ
3ኛ አብድልበር ነጋሽ የዘልዋን ሰፋቶ ቀበሌ ስራስኪያጅ እና
አቶ ሰኢድ ነጋሽ የቤደር ቀበሌ ስራስኪያጅ 3ኛ ደረጃ የወጡ ሲሆን የዋንጫ ፣የሜዳልያ ፣የብር እንዲሁም የዕውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።
በፕሮግራሙ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ አስተዳደር አቶ ሚፍታ ሁሴን ጨምሮ የአስተባባሪ አካላት፣ የወረዳ ሴክተር ኃላፊዎች ፣ የቀበሌ ስራ አስከያጆች የየተቋሙ የመንግስት ሰራተኞች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያ ለቀጣዩ ትውልድ በምታሸጋግራቸው አቅሞች ጸንታ እንድትቀጥል ሰፊ ሥራ ይጠበቃል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
***
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ለቀጣዩ ትውልድ በምታሸጋግራቸው አቅሞች ጸንታ እንድትቀጥል ሰፊ ሥራ እንደሚጠበቅ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንደገለጹት፣ በዛሬው ዕለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት የቀረቡትን የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትን አጽድቋል።
ሹመት የምንዝናናበት ሳይሆን የምንፈጋበት፣ የምንሰራበት፣ ኢትዮጵያን ለማጽናት፣ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ፣ ኢትዮጵያን ወደ ስልጣኔ ጉዞ ለማስኬድ ከፍተኛ ጥረት የሚደረግበት መስክና የሀገር ትልቅ አደራ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በሚቀጥሉት ዓመታት ኢትዮጵያ በውሳኔዋ ሉዓላዊ፣ በልዩነት ውስጥ የተሳሰረች፣ እሴት በመፍጠርና ጠብቆ በማቆየት ረገድ ምርታማ፣ ቀጣናዊና አህጉራዊ መልህቅ በመሆን የምትመራ እንዲሁም ለቀጣዩ ትውልድ በምታሸጋግራቸው አቅሞች ጸንታ እንድትቀጥል ሰፊ ስራ ይጠበቃል ብለዋል።
የመደመር መንግሥት ይህንን እውን ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
#የመደመርመንግሥት
#Ethiopia #EBC #Medemer #PMAbiyAhmed #MedemerGovernment
መስከረም 27/2019 ዓ/ም
በወረዳው ''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ'' በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የበጎ ፍቃድ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ወ/ስፖርት ጽ/ቤት በማስተባበር የተጀመረው የበጎ ፍቃድ ተግባር አንዱ የሆነው የአቅመ ደካማ ቤት ግንባታ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጿል።
በወረዳው በዛሬው እለት በኦቼናአንቀዲን ቀበሌ ለአካልጉዳተኛ ለሆነ አቶ አብድል ሰመድ ረዲ 40 ቆርቆሮና 2ፓኬት ሚስማር ድጋፍ ተደርጓል።
የወረዳው ወ/ፖ/ፅ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ ጀማል ናስር በዘንደሮ ክርምት በጎ ፍቃድ ከ61 ቤቶች በላይ በአዲስ ተገንብቶ ለአቅመ ደካማና አረጋዊያን ርክክብ እንደተደረገ ገልጿል።
የወረዳው ፓ/ፅ/ቤት ፖ/አ/ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሚፍታ አረቦ እንደገለፁት የበጎ ስራ ጊዜ የማይገድበው ዞትር የሚከናወን ከመልካም እሳቤ የመነጨ የህሊና እርካታ የሚሰጥ ፅድቅ ተግባር ሲሆን ሁሉም ሰው በበጎ ስራ ላይ የድርሻ እንዲወጣ በመግለፅ እንደ ወረዳ እየተከናወኑ ያሉ የበጎ ተግባራት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስቧል።
መስከረም 27/2019 ዓ/ም
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከ200 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው ጊዜ ያለፈባቸው የእንስሳት መድኃኒቶች ተወገዱ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ*ግብርና ጽሕፈት ቤት የእንስሳት ጤና የሥራ ሂደት ከአምስት ዓመታት በላይ ተከማችተው የቆዩና የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው የተለያዩ የእንስሳት ሕክምናና የክትባት መድኃኒቶች በዛሬው ዕለት መወገዳቸውን ጽ/ቤቱ አስታወቀ።
ለረጅም ዓመታት በወረዳው ውስጥ ተጠራቅመው የነበሩት ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶች ሁለት መቶ ሺህ ብር የሚያወጡ እንደነበሩ ተገልጿል።
የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ እና የእንስሳት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፈድሉ ኡስማን እንደገለጹት መድኃኒቶቹና ክትባቶቹ ከአገልግሎት ውጭ በመሆናቸው ምክንያት ሊያስከትሉ የሚችሉትን የጤናና የአካባቢ ጉዳት ለመከላከል ሲባል ልዩ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ በጥናትና በጥንቃቄ እንዲወገዱ ተደርጓል።
ይህ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የአወጋገዱን ሂደት በበላይነት በመምራት በሕጋዊና ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ኃላፊነቱን መወጣቱንም ኃላፊው አክለው ገልጸዋል።
የእንስሳት ጤና የሥራ ሂደት በቀጣይ መሰል የሀብት ብክነትና የመድኃኒት መከማቸት እንዳይከሰት እንዲሁም አቅርቦትና ፍላጎትን ያመጣጠነ አሠራር ለመዘርጋት የክትትልና የቁጥጥር ሥርዓቱን ይበልጥ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል ።
