917
المشتركون
-124 ساعات
+27 أيام
+930 أيام
أرشيف المشاركات
መስከረም 25/2019 ዓ/ም
የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሱፐርቪዥን መስክ መልስ ግምገማ አካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የጉራጌ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በፓርቲና በመንግሥት ትኩረት መስኮች የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን የሚገመግም የሱፐርቪዥን ቡድን መስክ በማሰማራት ሰፊ የምልከታና የማጠቃለያ ግምገማ መድረክ አካሄደ።
በዚሁ የመስክ መልስ ግምገማ መድረክ ላይ የፓርቲው የፖለቲካ እና የአደረጃጀት ሥራዎች አፈጻጸም፣ የአባላትና የአመራሩ ድርጅታዊ ብቃት፣ እንዲሁም በየደረጃው ያሉ የአደረጃጀት መዋቅሮች እንቅስቃሴ በተገቢው ሁኔታ ተፈትሿል።
በተጨማሪም በፓርቲው መሪነት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ሲከናወኑ የቆዩ ወቅታዊና መደበኛ የህዝብ ንቅናቄ ተግባራት፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች፣ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፣የስራ ዕድል ፈጠራ፣የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት፣ የገቢ አፈፃፀም፣የከተማና የገጠር ኮሪደር ልማት፣የሰላምና የፀጥታ ስራዎች፣የተማሪ ምዝገባና የትምህርት አጀማመር ሁኔታ እና ሌሎች ተግባራት በዝርዝር መገምገማቸው ተገልጿል።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ በመስክ ምልከታው ባረጋገጠው መረጃ መሠረት፤ የሩብ ዓመቱ ሥራዎች ከስልታዊ ዕቅድ ዝግጅትና ከተግባቦት ፈጠራ ምዕራፍ ጀምሮ እስከ ቀጥታ የመስክ ትግበራ ድረስ የነበራቸው ሂደት አበረታች ውጤት ማስመዝገቡ ተረጋግጧል።
በተለይም በየደረጃው ያለው አመራርና አባል ህዝቡን ባስተባበረ መልኩ ያከናወናቸው የልማት እንቅስቃሴዎችና የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያዎች ተስፋ ሰጪ እንደሆኑ ተመላክቷል።
በዞኑ በሁሉም መዋቅር ጠንካራ ስራ በመስራት የሚስተዋሉ የአፈፃፀም ልዩነቶችን በማጥበብ የአመለካከትና የተግባር አንድነት ለመፍጠር የተጀመረው ስራ ይበልጥ አጠናክሮ በማስቀጠል የህዝቡ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ተገምግሟል።
በግምገማው ማጠቃለያ ላይ በመስክ ምልከታው የታዩ ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና በየደረጃው የታዩ ጉድለቶችን ደግሞ የቀጣይ ዕቅድ ውስጥ አካቶ በአስቸኳይ ለማስተካከል የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በቀጣይም የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በላቀ ደረጃ ለመመለስ የሱፐርቪዥንና የክትትል ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
በመድረኩ የጉራጌ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለተካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ፈቀድ፣ የዞኑ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ፈይሰል ሀሰን ጨምሮ በሱፐርቪዥን ምልከታው የተሳተፉ የዞን አመራሮች ተገኝተዋል።
መስከረም 25/2019 ዓ/ም
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሰፍቶ ቀርሳ ቀበሌ በኩራሮ አካባቢ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በስኬች ፕላን ዝግጅት ላይ የሚገኘው የመብራት መስመር ዝርጋታ ሥራ ያለበትን ደረጃ ለማየት የመስክ ምልከታ ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ሲሆን የተመራው የመስክ ምልከታ በወቅቱ የሥራውን ሂደትና አጠቃላይ እንቅስቃሴ በቅርበት ተመልክተዋል።
በመስክ ምልከታው ወቅት እንደተገለጸው ይህ የመብራት መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት የኩራሮ መንደርንና የአካባቢውን ማኅበረሰብ የኃይል አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ታስቦ እየተሠራ የሚገኝ ወሳኝ የልማት ሥራ ነው።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በጉብኝቱ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፣ የሕዝቡን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
አሁን ላይ በስኬች ፕላን ዝግጅትና በሂደት ላይ ያለው ይህ የመብራት ፕሮጀክት ጥራቱን ጠብቆና በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ተጠናቆ ለኅብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ የወረዳው አስተዳደር አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።
በዚህ የመስክ ምልከታ መርሃ ግብር ላይ የገ/ጉ/ወ/ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን፣የወረዳው የከተማ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተማም አደም እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የመደመር መንግሥት ዛሬ ይመሠረታል
****
ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በሰላም አጠናቅቃ፣ የሕዝብን ድምፅ ወደ ተግባር የምትቀይርበት ታሪካዊ ዕለት ላይ ደርሳለች።
ይህ ቀን ዜጎች ድምፃቸውን የሰጡት እና በጉጉት የጠበቁት የመደመር መንግሥት በይፋ ሥራውን የሚጀምርበት ዕለት ነው።
በመላው ሀገራችን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በድምፅ መስጫ ኮረጆ ውስጥ የጣሉት ተስፋ፣ ዛሬ በፓርላማው አዳራሽ ውስጥ ሕያው ይሆናል።
ያለፉት የምርጫ ወራት የውድድር፣ የክርክር እና የሐሳብ ፍጭት ጊዜያት ነበሩ፤ ዛሬ ግን ያ ሁሉ አልፎ፣ የሕዝብን አብላጫ ድምፅ ያገኘው አሸናፊ ፓርቲ ሀገርን በጋራ የማስተዳደር እና ዜጎችን የማስተባበር ታላቅ ኃላፊነትን በይፋ ይረከባል።
መደመር፣ ልዩነቶችን ይዞ በአንድነት መቆምን፣ ያለፈውን ጠባሳ እያከሙ የነገውን ራዕይ በጋራ መገንባትን፣ እና የሁሉንም ዜጋ አቅም ለሀገር ብልጽግና ማዋልን እንደ ዋና መመሪያው አድርጎ አዲሱ መንግሥት ቃለ መሐላውን ሊፈጽም በዝግጅት ላይ ነው።
የምክር ቤቱ መዶሻ ሲመታ፣ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ካቢኔያቸው ቃለ መሐላ ሲፈጽሙ፣ የሀገራችን አዲስ ምዕራፍ ይከፈታል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያመጣው የመደመር መንግሥት ዛሬ ይመሠረታል፤ ከፊቱ ያለው መንገድ የቱንም ያህል ፈታኝ ሊሆን ቢችልም፣ የብዙኃኑን አደራ ተሸክሞ ጉዞውን ይጀምራል።
ታሪክ ዛሬን መዝግቦ ይይዛል፤ የነገዋ ኢትዮጵያም ዛሬ በሚጣለው የመሠረት ድንጋይ ላይ ጉዞዋን ትቀጥላለች።
#ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!
#Ethiopia #EBC #Medemer #የመደመር_መንግሥት
የታሪካዊ ጠላቶችን ሴራ ያከሸፈው የኢትዮጵያ ፅናት
******
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ፕሮጀክቱ በአለም አቀፍና በቀጣናዊ መድረኮች በርካታ ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ጂኦፖለቲካዊ ጫናዎች ሲያጋጥሙት ቆይተዋል።
የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የልማት መብት ለመገደብ የተደረጉ ሴራዎችም ብዙ ርቀት የተጓዙ ቢሆንም ኢትዮጵያ እነዚህን የውስጥና የውጭ ፈተናዎች በፅናት በመቋቋም የግድቡን ግንባታ በተሳካ ሁኔታ አጠናቃ ለውጤት አብቅታለች።
ዛሬ ላይ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የሀገራችን የኢኮኖሚ፣ የዲፕሎማሲና የፖለቲካ ከፍታ ማሳያ ከመሆኑም በላይ ከረጅም ዘመናት የባህር በር ማጣት ጋር ተያይዞ ለተነሳው የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ቁልፍ የታሪክ ምእራፍ ሆኗል።
ግብፅ የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶችን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያን ፍትሃዊ የውሃ አጠቃቀም ለመቀልበስ ከፍተኛ ጥረት ስታደርግ ቆይታለች። ጉዳዩን የአረብ ብሄራዊ ደህንነት ስጋት በማስመሰል የአረብ ሊግ አባላት በኢትዮጵያ ላይ ወጥ አቋም እንዲይዙና ዲፕሎማሲያዊ ማእቀብ እንዲጥሉ ከመጎተቷም ባሻገር የግድቡ መሰራት በታችኞቹ የተፋሰስ ሀገራት ላይ ከባድ የውሃ እጥረት እንደሚፈጥር በማስመሰል መጠነ ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻዎችን አካሂዳለች።
ከአስመራ እስከ ካይሮ ባሉት ሀይሎች የሚመራውና የሚደገፈው ይህ የጥፋት መረብ በኢትዮጵያ ሰላም እንዳይሰፍንና በምጣኔ ሀብት እንዳትለማ ለማደናቀፍ እንዲሁም አልፎ አልፎ የሚነሱ የፖለቲካ አለመግባባቶችን በመጠቀም የሀገራችንን የድርድር አቅም ለማዳከም ጥረት አድርጓል።
ሆኖም ኢትዮጵያ በህዝቧ ሁለንተናዊ ድጋፍና በፅናት ፍትሃዊ እና ተመጣጣኝ የውሃ አጠቃቀም የሚለውን መርህ አፀንታ በመያዝ የናይል ተፋሰስ ሀገራትን የትብብር ማእቀፍ ስምምነት አፅድቃለች።
ይህ በዓባይ ላይ የተመዘገበው ታሪካዊ ድልና እያደገ የመጣው የኢኮኖሚ አቅም ኢትዮጵያ በቀይ ባህር የሚገባትን ስፍራ ለማግኘት የምታደርገውን የመደራደር አቅምን በማሳደግ በከፍተኛ ሁኔታ ይደግፋል።
ኢትዮጵያ ከጥንቱ የአክሱም ስልጣኔ እስከ አዱሊስ ወደብ ድረስ የባህር በር ባለቤት የነበረች ሲሆን ዛሬም ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ያላት ሀገር በመሆኗ የባህር በር ማግኘት የህልውናና የልማት ጥያቄ እንጂ ሌላን ሀገር ለመውረር የሚደረግ ጉዞ አይደለም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደገለፁት ኢትዮጵያ በታሪክም ሆነ በዓለም ህግ መሰረት በሰላማዊ መንገድ የባህር በር የማግኘት መብት ስላላት የጂኦግራፊ እስረኛ ሆና አትኖርም።
ኢትዮጵያ የሕዳሴውን ግድብ በራሷ አንጡራ ሀብትና አቅም ገነብታ የቀጠናው የልማትና የእድገት ማእከል እንዳደረገችው ሁሉ የቀይ ባህር መዳረሻ ፍላጎቷንም ቢሆን ሌሎችን ባገለለ መልኩ ሳይሆን በሰላም፣ በህግ፣ በዲፕሎማሲና በህዝቦቿ የተባበረ ብርታት በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ ተመስርታ እውን ታደርጋለች።
#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
#EthiopianDiplomacy #Sovereignty #EthiopianPanAfricanism #Geopolitics #HornOfAfrica
ከህዝብ ድምፅ ወደ መንግሥት ምሥረታ ውስጥ የማይቀለበሰው የዴሞክራሲ ጉዞ፣ የታሪክ አሻራዎች እና የታላቋ ኢትዮጵያ የቀጣይ ከፍታ ራዕይ
*******
ኢትዮጵያ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዓመታት የሀገረ-መንግሥት ታሪክ ባለቤት የሆነች፣ በፈተናዎች እሳት ውስጥ አልፋ ጽናቷን ያረጋገጠች ግዙፍ አፍሪካዊት ሀገር ናት።
ህዝቧ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ድምፁን ሰጥቶ ያሻውን መሪ ከመረጠበት የታሪክ ምዕራፍ ተነስቶ ወደ አዲስ መንግሥት ምሥረታ የሚደረገው ሽግግር ኢትዮጵያ ያላትን ጥልቅ የፖለቲካ ብስለት፣ የሰከነ ህዝባዊ ወገንተኝነትና የጸና የህግ የበላይነት ባህል በዓለም አቀፍ መድረክ ዳግም ያስመሰከረ ነው።
ይህ ሰላማዊና ሥርዓት ያለው የዴሞክራሲ ሂደት ኢትዮጵያ በየዘመናቱ የሚገጥሟትን የውስጥና የውጭ ውጣ ውረዶች በራሷ ልጆች ብርታት አልፋ፣ ወደ ላቀ የከፍታ ማማ መሸጋገር የምትችል ብርቱ ሀገር መሆኗን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
ያለፈው መንግሥት በኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ መስኮች ላይ ያስቀመጣቸው ቁልፍ አሻራዎች ዛሬ ለደረስንበት ተስፋ ትልቅ መሰረት ሆነዋል።
የውጭ ጫናዎችንና የዲፕሎማሲ ሴራዎችን በጽናት በመመከት፣ በገዛ አቅም ታላቁን የሕዳሴ ግድብ ወደ ፍፃሜ ማድረስ መቻሉ የትውልዱ ትልቁ የድል አርማ ነው።
ከዚህም ባሻገር ሀገራዊ ምክክርን በማካሄድ ልዩነቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ የመፍታት ባህልን ማዳበር፣ እንደ ማዳበሪያና ነዳጅ ያሉ ግዙፍ የኢኮኖሚ አቅሞችን በራስ አቅም ለመገንባት መጀመር፣ በአዲስ ዕይታ የከተማና የትራንስፖርት መሠረተ-ልማቶችን መገንባት እንዲሁም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተከናወኑ አመርቂ ተግባራት የስልጣኔ ጀንበር ብቅ ማለቷን ያበሰሩ ናቸው።
እነዚህ የተመዘገቡ ስኬቶች ኢትዮጵያ አቅሟን አስተባብራ በህብረት ከተነሳች የማትሻገረው ተራራ እንደሌለ ለዓለም ያስመሰከሩ ህያው ማሳያዎች ናቸው።
አሁን በህዝብ ሙሉ ውክልና የሚመሰረተው አዲሱ መንግሥት ደግሞ የተጀመሩትን እነዚህን ታላላቅ ሜጋ ፕሮጀክቶችና የልማት ምዕራፎች በማስቀጠል፣ የጎደለውን ሞልቶና ክፍተቶችን አርሞ ሀገርን ወደ ሙሉ ብልጽግና የማሻገር ታላቅ ታሪካዊ ኃላፊነት ተጥሎበታል።
አዲሱ #የመደመር_መንግሥት የዜጎችን እኩልነት፣ ሰላምና ፍትሕ ይበልጥ በማስፈን፣ የኑሮ ውድነትንና የኢኮኖሚ ጫናዎችን በማቃለል እንዲሁም የህግ የበላይነትን በማጽናት የህዝቡን የልብ ትርታ በተግባር ለመመለስ ጽኑ ቃል ኪዳን ሰንቋል።
ይህ የለውጥና የስራ ምዕራፍ ያለፈውን ጥንካሬ አጠናክሮ ጉድለቶችን የሚሞላ፣ ተቋማዊ አቅምን የሚገነባና የህዝብን የፍትሐዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ በተግባር የሚያረጋግጥ ነው።
ከምንም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነት፣ እውቀትና መስዋዕትነት ታፍራ፣ ተከብራና ሉዓላዊ ክብሯ ተጠብቆ እንድትኖር የማድረግ ራዕይ የቀጣዩ ጉዞ ዋነኛ ማዕከል ነው።
#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ ሰንቀን እንደመነሳታችን መጠን፣ የባሕር በር ተፈጥሯዊ መብትን ከማስከበር ጀምሮ የቀጠናው የሰላምና የልማት ማዕከል የመሆን ጉዟችን በማንኛውም የጠላቶች ሴራና ጊዜያዊ ፈተና አይገታም።
የኢትዮጵያ ህዝብ በዴሞክራሲያዊ መንገዱ የመረጠውን መንግሥት በማጽናት፣ ከዳር እስከ ዳር በአንድነት ቆሞ የሀገሩን ክብርና ብልጽግና እንደሚያረጋግጥ ጥርጥር የለውም።
#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
(EBC)
"የተሰጠን አደራ አለ። የተሰጠንን አደራ ይዘን የጀመርነውን በስኬት እናጠናቅቃለን።"
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የክልሉን አስፈጻሚ የካቢኔ አባላት ሹመት አፀደቀ
ሆሳዕና፣ መስከረም 23፣ 2019 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ7ኛ ዙር መስራች ጉባዔው ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ያቀረቧቸውን የክልሉ አስፈጻሚ የካቢኔ አባላት ሹመት አፅድቋል።
በዚህም መሰረት፡-
1. አቶ ተመስገን ካሳ - የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ
2. ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ - የሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
3. አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ - የዉሃ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ
4 . አቶ ሳሙኤል ዳርጌ - የጤና ቢሮ ኃላፊ
5 . አቶ ሙስጠፋ ኢሳ - የክልሉ የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
6 . አቶ ሰላሙ አማዶ - የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ኃላፊ
7 . አቶ ሳሙኤል መንገሻ - የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ
8 . አቶ ተመስገን ጎዴቦ - የክልሉ የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮ ቢሮ ኃላፊ
9 . አቶ አሰፋ ደቼ - የክልሉ ደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ ኃላፊ
10 . አቶ አብዶ አህመድ - የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ
11 . አቶ አብዱልባሲጥ አባኮ - የክልሉ ፕላን እና ልማት ቢሮ ኃላፊ
12. ወ/ሮ ዘይቱና ኢብራሂም - የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ
13 . አቶ ደምስ ገብሬ - የክልሉ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ
14 ዶ/ር ቶፊቅ አጫሉ - ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
15. አቶ ገብሬ ጋጌ - ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
16. አቶ አክሊሉ መኔዶ - ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ
17 . ዶ/ር ተስፋዬ አጋፋሪ - የክልሉ የህብረተሰብ ተሳትፎ እና የዲያስፖራ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
18 . ወ/ሮ ቀመሪያ ረሻድ - የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
19 . አቶ ታመነ ገብሬ - የክልሉ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
የካቢኔ አባላቱ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ በመፈፀም ስራቸውን በይፋ ጀምረዋል።
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ
መስከረም 13/2019 ዓ.ም
የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የህብረተሰቡን ጤናማነት ማሳደግ እንደሚገባ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨፨//፨፨፨፨፨፨
ይህንን ያስታወቀው በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የማጠቃለያ እና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ የጤና ጉባኤ የንቅናቄ መድረክ ባካሄደበት ወቅት ነው ።
የ2018 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ሪፖርትና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ በፅህፈት ቤቱ ባለሙያ በእናቶችና ህፃናት ስራ ሂደት በአቶ አብዲ በያን ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል ።
መድረኩ የመሩት የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ ሚፍታ ሁሴን አንደተናገሩት የጤና ተቋማት ሀብት አያያዝና አጠቃቀም ጥራቱን የጠበቀ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ወሳኝ በመሆኑ የጤና ማናጅመንት ምሶሶዎች አንዱ እንደሆነ ገልፀው የጤና ተቋማት የፋይናንስ ፣ የመድኃኒትና ሕክምና መሣሪያዎች፣ እንዲሁም መሠረተ ልማትና የመረጃ ሥርዓትን እንደሚያጠቃልል አስታውቀዋል ።
አቶ ሚፍታ አክለው የጤና ተቋማት ንፅህና በመጠበቅ የግልና የጋራ መፀዳጃ ቤቶች በመገንባት የበሽታዎች መተላለፊያ መንገዶች በመግታት፣ የታካሚዎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና የሕክምና ጥራትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ተግባር መሆኑ ገልፀው ፣ጤና ተቋማት የመረጃ ልውውጥ በተደራጀ መልኩ ተደራሽ በማድረግ በተገቢው መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም አብራር በበኩላቸው የጤና ተቋማትን የአገልግሎት ጥራት ማሻሻል፣ የጤና ባለሙያዎችን ሙያዊ አቅም ማጠናከር፣ ለተገልጋዮች ተገቢውን አክብሮትና ተገቢ እንክብካቤ ማድረግ እና የጤና አገልግሎቱን ተደራሽነት ማስፋት የቀጣይ ሥራዎች ትኩረት እንደሚደረግባቸው አስታውቀዋል ።
ህብረተሰቡ የጤና ተቋማትን በተገቢው መጠቀም፣ የእናቶችና ህጻናት ጤናን ለመጠበቅ የሚደረጉ ሥራዎችን መደገፍ፣ የክትባት አገልግሎትን መጠቀምና የተላላፊ በሽታዎችን በመከላከል ረገድ የራሱን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርበው የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች በመለየት የጤና አገልግሎት ጥራትን፣ ተደራሽነትንና የተገልጋይ እርካታን በማሻሻል የህብረተሰቡን ጤና ለማስጠበቅ በትብብር መስራት እንደሚገባ ገልፀው ከመድረኩ የተሰጡ አስተያየቶች እንደ ግበዓት በመውሰድ እንደሚሰራ አቶ ኢብራሂም አክለው
አስታውቀዋል።
ከመድረኩ ከተነሱ ዋና ዋና ሀሳቦች መካከል በቀበሌዎች የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ አለ መኖር ፣በጤና ተቋማት መድሀኒት አለመኖር ፣የጤና ተቋማት ቀበሌዎች በቅርበት መደገፍ እንደሚገባ ፣ለማጤማ የወጡ ደረሰኞች ፅ/ቤቱ መከታተል እንዳለበት የሚሉት ዋና ዋና ዎቹ ናቸው።
በመጨረሻም በ2018 ዓ.ም በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ጤና ኬላዎችና ጤና ጣቢያዎች የሀንዘብና የዋንጫ እንዲሁም የእውቅና ሰርተፍኬት ሲበረከትላቸው መሀል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልና አጋር ድርጅቶች ልዩ ተሸላሚ በመሆን የእውቅና ሰርተፊኬት ተበክቶላቸው፣
የ2019 ዓ.ም መግባቢያ ሰንድ በመፈራረም መድረኩ ተጠናቋል።
