en
Feedback
Yoni Motivation

Yoni Motivation

Open in Telegram

ከማንም አትጠብቅ

Show more
698
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ግድ የለሽ አትሁን የአላማ ሰው መሆን አለብህ፤ ህይወትን በአጋጣም የሚኖሩ በጣም ብዙ ሰወች አሉ፤ የእነዛ ሰወች ደስታ ሁል ጊዜ በሌሎች ሰወች እጅ ውስጥ ነው። ራሳቸው ጀምረው ምንም ነገር ስለማይጨርሱ ከሰሩት ስራ ይልቅ በጎደኞቻቼው ስኬት መደሰት ያምራቿል። ነገ የት እንደምሃዱ ምንም እቅድ የላቸውም ፤በተገኘበት በልተው ሆዳቸው ከጠገበ በመሸበት ተኝተው በሁለተኛው ቀን እበታቸው መጥተው ከሰአት ተመልሰው ወደ ለላኛው ጎደኛቸው ጋር ይሃዳሉ ።እነዝህ ሰወች ናቸው አሁን አንትና እንደዝህ አደረገኝ፤ ውጤተ አነሰ፤ ራሴን አጠፋለሁ፤ ገመድ አገዛለው የምሉ፤ ከእንደዝህ አይነት ተቅበዝባዥ ኑሮ ራሳቹን ጠብቁ !!ነገ አንተ አባት ሆነህ የሚትመራው ቤት አሌ፤ አይ ካልክ ራስህንም ሳትመራ ቁጭ እንዳልክ ትቀራለህ አስብበት ። መልካም ቀን ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ሁል ጊዜ ከአንተ ከምሻሉ ሰወች ጋር ውሎህን አድርግ! ህይወትህ ሳታስብ ተለውጦ ታያለህ። ከአመስጋኞች ጋር መዋልን ተለማመድ፤ ህልም ካላቸው ሰወች ስትሆን ፤ህልም ባይኖርህም ወዴ ማንነት ጥያቀ ውስጥ ትገባለህ። በአስተሳሰብ ከፍ ካሉ ጋር ስትሆን አንተም ከፍታ እንጅ ሰፈር ለሰፈር መመላለስን ታቆማለህ። ከሳጥን ውስጥ ወጥተህ ማስብ ትጀምራለህ፤ የጋረዱ ነገሮች ከፍትህ ገሸሽ ይላሉ ፤ዉሎህን አስተካክል ከንስሮች ጋር ደመና ላይ ለመብረር ከፈለክ ከቆሻሻ ውስጥ ምግብ ከምፈልጉ ከዶሮወች ጋር አትዋል ። መልካም ቀን ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ዛሬ ልመርቃቹ !የለፋቹበት ነገር ሁሉ የእናንተ ይሁን ፤ምሽታቹ የተባረከ ይሁን፤ ሌሊት በህልማቹ አውሬ ስያባርራቹ ሳይሆን ከስኬታቹ ጋር ስትገናኙ ያሳያቹ ። ለቤትሰቦቻቹ ባሉበት የእግዚአብሔር ሰላም ይብዛ ። ጤላታቹ ውድቀታቹን ሳይሆን ክብራቹን ይመልከት፤ እግዚአብሔር ነግያችንን ያሳምር ደስ እንዳላቹ እነንም መርቁ ምሽታቹ የተባረከ ይሁን። Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ትላንት የተበላሸ ነገር ካንተ ቁጥጥር ውጭ ሆኖ ልሆን ይችላል ።ሳታስብ ያመለጠክ ነገር ብሆንስ በሳአቱ ማድረግ የምትችለው ያንን ብቻ ነው። ስለዝህ ትላንት ለተበላሹ ነገሮች አብዝተህ ስትጨነቅ ዛሬን ሳትጠቀም ይነጉዳል ። ነገ እሱም ለላ ቁጭት ነው ይዞብህ የሚመጣው፤ መመለስ ለማትችለው ነገር አብዝተህ አትጨነቅ፤ ይልቅ ዛሬ የፈጣር ስጦታ ናትና ተጠቀማት ነገ በራስህ ትኮራለህ ። መልካም ቀን ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ከአንተ በላይ አራዳ የለም። አው ጫትም መቃም ታውቃለህ ያልጠጣሃው የመጠጥ አይነት ትንሽ ነው !!በጣም ብዙ የሴት ጓደኖች አሉህ፤ አባትህ አናትህ ከአንተ ቃል አይወጡም፤ አንተ የቤቱ ንጉስ ነህ ፤የሰፈር ሰውን ሰላም ማለት ለአንተ በጣም ትንሽነት ነው። የእግዚአብሄርን ቤት መግባት ለአንተ በጣም ፋራነት ነው፤ ሞኝነት ነው ላንተ የተናገረህን ሰው ማሰቀየም በጣም ያስደስታሃል፤ የተከበሩ ሰወችን መናቅና መሳደብ ላንተ ክብር የሚጨምር ይመስለሃል ፤ምክር የሚመክር ሰው አመልህ ነው፤ አታጨስ የሚልህ ጠላትህ ነው ፤አትስከር የሚልህ አሱ ሰው ሳይሆን ጠላትህ ነው፤ ምንም አያውቅም ሞኝ ነው ላንተ። አንተ ግን የዜመናችን ምርጡ አራዳ ነይኝ ብለህ ራስህን ታስብ ይሆናል፤ ልንገርህ ስማኝ!! አንተ የዘመኑ የመጨረሻ ፋራ አንተ ነክ ።ስሙኝ የሀገር ልጆች ካርታ እንደጠፋችባት ፒለን አትቅበዝበዙ። የምትቅምቤት እና የሚትጠጣበት ምንም አይነት ምክንያት የለም ። አባትህ ህይወትህን ካበላሸ አንተስ ህይወትህን ለማስተካከል ምን ሰራ? ንገረኝ ምክንያትህ ወጋ የለውም ንቃ ምናልባት ልመክርህ ካአንተ በላይ አላውቅም ይሆናል ግን ያዘው ይጠቅማሃል ። መልካም ምሽት ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

እስካሁን ልጅ እንደሆንክ ታስባለህ ለተበላሹ ነገሮች ሁሉ ገና ልጅ አይደለሁ እንዴ! ዕድመዬ ገና ነው እያልክ ራስህን ታሳምናለህ ፤በ25 አመትህ ምንም ነገር ካልሰራህ በ50 አመትህ አድስ ነገር እንደምታመጣ ምንም ማስተማመኛ አለው? ዛሬ ሰርተህ አጠራቅመህ ካላስቀመጥክ ነገ በመጦርያ ዕድመ ለልመና ትወጣለህ። ልብህን ሳይሆን ጭንቅላትህን ስማ ፤አድስ ነገር ሞክር፤ ልጅ ነይኝ እያልክ ራስህን አታሳምን፤ አንተ ልጅ አይደለህም። ስንቶች ባንተ ዕድመ ለሀገር ስንት ነገር ሴሩ? ቤትሰቦቻቼውን አኮሩ ።ለተወለዱበት አካባቢ ስም ሆኑ አንተ እንደዛ መሆን አትፈልግም? ቆይ አንድ አይነት ህይወት አንድ አይነት ውሎ አይሰለችም? ቆም ብለህ አስብ ቢሮ። መልካም ህልም ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን ትለወጣለህ Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ሁሉም ነገር የሚቻል ነው ትክክለኛ ሰወች አንተን ከደገፉ እንምትችል ከነገሩ የትኛውንም ነገር ማሳካት ትችላለህ ።አኛ ሀገር ግን የተለመዱ አባባሎች ወይ ''አንትና እኮ ሞክሮ አልሳካ ስል እኮ ነው ያቆመው እሱ ደግሞ ካንተ በእውቀትም በልምድም ጎበዝ ነው ለሱ የለሆነው ላንተ ይሆናል ለማለት አልችልም ግን ማን ያውቃል እስት ዝም ብለህ ዕድልህን ሞክር'' ነው የሚሉ ውስጥህ ያለውን አቅምህን በትችታቸው ከገደሉ በኃላ ነው ሞክር የምሉን፤ መቼም ብሆን ውሎህን Pessimist ከሆኑ ሰወች ጋር አታድርግ ህልምህን ያጨልማሉ ። መልካም ቀን ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

የባከነ ደቂቃ ያለው ኳስ ጨዋታ ላይ ቢቻ መሆኑን ታውቃለህ? በህይወትህ የባከነ ደቂቃ መልሰህ መጠቀም እንደማትችል ታውቃለህ? በቀን ውስጥ የተሰጠህ 24ሰዓት ነው ። 10ሰዓት ተጠቅመህ የቀረውን ባንክ ማስቀመጥ አትችልም! ከለፈ አለፈ ነው። እባክህ ግዘህን ተጠቀም ከተጠቀምክ ለራስህም ለቤተሰቦችህም ሸክም አትሆንም። #እንትራንስ የወደቅከው አባትህ የተሻለ ትምህርት ቤት ስላላስገባህ አይደለም!! ''ነው ካልክ'' ከአንተ ትምህርት ቤት ጥሩ ውጤት ያመጡት እንዳይታዘቡክ!! አመንክም አላመንክም አንተ የወደቅከው ስላላጠናህ ነው ።ማንም ምንም አላጠፍም ራስህ ነህ ቸልተኛ፣ ግድ የለሽነትህ ገና በጣም ብዙ ዋጋ ያስከፍላሃል አቁምና ራስህን መሆን ጀምር ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል ። መልካም ምሽት ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

የሚያስደስታቹን ነገር ነው ወይስ የሚጠቅማቹን ነገር ነው እያደረጋቹ ያላቹት? የሚያስደስታችሁ ነገር በጣም ብዙ ነው ቲክቶክ ቁጭ ብለህ ካየህ ልያስደስትህ ይችላል። ነገር ግን የሚጠቅም ነው ወይ የሚለውን ነገር ማሰብ የግድ ይላል!! የሚጠቅሙን ነገር ስናደርጋቸው ላንደሰት እንችላለን፤ ግን በመጨረሻ በፍርያችን እንደሰታለን፤ የአሁኑኑ ደስታ ካስቀደምክ ግን እድመህን በሙሉ ስታለቅስ ትኖራለህ ። ቆም ብለህ አስብ እያደረግክ ያለሃው የሚጠቅምህን ነው ወይስ የሚያስደስትህን ነው ?መልሱን ለራስህ ንገረው!! መልሱ ደስ የሚያሰኝ ከሆነ ፤ጥሩ ካልሆነ የቆምክበትን ፈትሽ ። መልካም ምሽት ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

በህይወትህ ራስህ ሰጥተህ የሚትኖርልት ጉዳይ ምንድነው? ጧት ማታ የሚያሳስብህ ግዘህን ጉልበትህ የምትገብረው ለ ማን ነው? ከሰው የበታች ለመሆን እየሰራክ ነው ወይስ ከሰው የበላይ ለመሆን እየሰራክ ነው? መልሱን ለራስህ ንገርው ማታፊሪበት ከሆነ ቀጥል!! መልካም እሁድ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ሁሉም ወፎች ዝናብ ስመጣ መሸሸጊያ ጥላ ይፈልጋሉ። ወደ ዛፍም ውስጥ በመግባት ይጠለላሉ #ንስር ግን ዝናብን ሰንጥቆ ወዴ ደመና ይወጣል ።ከፍ ብሎም ይበራል ራሱ ከችግሩ በላይ እንደሆነ ያውቃል። ችግሩ የጋራ ነው ነገር ግን አመለካከት ልዩነትን ያመጣል። መልካም ምሽት ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ህይወት አንዴ ነው በሰዎች ህይወት ውስጥ ገብተህ ብዙ ማስተካከያ መስጠት ይቀናህ ይሆናል ግን ሁሌም በማይመለከትህ ነገር ውስጥ የምታውለው ጊዜ ተመልሶ ላይመጣ እየባከነ መሆኑን አትዘንጋ!! ራስህ ላይ አትኩር ኮማች አትሁን አይንህን ጨፊነ ምትገልጥበት ያክል የተረፋ ጊዜ የለህም ። አንተ ግን ጊዜ ለማሳለፈ ብለህ በየ ቡና ቤቱ በየ ፉል በቱ ስትዞር ትውላለህ!! ከዛን መጨረሻ ላይ መግብያ መውጫ ታጣና እንትና ነው እንደዝህ ያደረገኝ፤ አባቴ እናቴ ማሌት ትጀምራለህ፤ በኋላ ከምታለቅስ አሁኑኑ ጊዘህን ተጠቀም አይ ካልክ ከምነግርህ በላይ ይቆጭሃል ። መልካም ቀን ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f ንቃ

ከፎቅ ላይ ደረጃውን አልጠቀሚም ጊዜ የለኝም ብሎ በመስኮት ዜሎ የሚወርድ ሰው የለም። ከፎቅ ለመውረድ ደረጃውን እንደምትጠቀመው ሁሉ ለመውጣትም ደረጃውን ተጠቀም። የማይመጣ ልፍት አትጠብቅ! በጣም ብዙ ሰው የማይመጣ ልፍት ስጠብቅ ነው ጊዜውን የጨረሰው፤ ጧት እንደምሮጥ ጅብ በኋላ ወደ ቤት ሳትደርስ መንገድ ላይ እንዳትቀር አሁኑኑ ጉዞ ጀምር ፤ ስትሰራ ስተለፋ እግዚአብሔርንም ደስ ይለዋል ምኞትህንም ያሳካዋል። አይ ካልክ ግን ተኝተህ አያበላህም!! አንተ ልጁ ለላው የልጅ ልጁ አይደለም ለእግዚአበሐር አራት ነጥብ መልካም ምሽት ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

የቆምከው በምክንያት ነው ።አቋምህን ልክ እንደ ዛፍ አድርግ ዛፍ ብቆረጥም ራሱን ከመሬት ጋር አዛምዶ ስሮቹን ወደ ጥልቅ ዘርግቶ ስለቆመ መልሶ ይለመልማል ። ዛፍ እንኳን ተስፋ ካልቆረጠ አንተ የሰው ልጅ ሆነህ ተፈጥረህ ማሰብ እየቻልክ እንደት ተስፋ ትቆርጣለህ? አቋምህ የጤነከረ ከሆነ ምንም እንኳን ብያጋጥምህ መልሰህ ትቀጥላለህ እንጅ በጭራሽ አታቆምም!! መለምለም ጀምር ድሮ የነበረክበት ቦታ መድረስ ትችላለህ ፤በትንሽ ነገር ተስፋ ቆርጠህ አትመለስ፤ አንተ ውስጥ የአሸናፍ አምላክ ሀይል አለ። አንተ ግን አይዞ !!ሁሉም ያልፋል አንተ ብቻ ተስፋ አትቁረጥ ። መልካም ምሽት ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

በእጃችን የያዝነው ነገር ብዛት አይደለም ወደ ምንፈልገው ቦታ ልያደርሰን የሚችልው። የምንጠቀምበትን መንድ ማወቅ እንጂ፤በጣም ብዙ ሰው በእጁ ብዙ ነገር ይዟል ፤ግን ያንን ነገር አያውቀውም ያንን ነገር ለምን አትጠቀምም? ብለህ ብትጠይቀው አሱ አሁን ምን ይጠቅማል ብለህ ነው ከሱ የተሻለ ነገር ብኖር በጣም አሪፍ ነበረ ይላል ። ስማኝ Ther is no Elevator to SUCCESS you have to take the STAIRS.አራት ነጥብ ። መልካም ቀን ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ያኔ ዱሮ ልጅ እያለህ ተምረህ ተመራቀህ ራሱ መንግስት የሚቀጥርህ አይመስልህም። ለአንተ ደሞወዝ ሰው የሚከፍልህ አይመስልህም። ይሄን ያህል ራስህን አሳንስህ ለምን ታያለህ? ለምን ለራስህ የሚትሰጠው ቦታ ሁል ጊዜ ዝቅታ ነው? አየህ ስራ ያጣሃው ስራ ጠፍቶ ሳይሆን ያነ ድሮ ተማሪ እያለህ ያሰብከው ህልም አየተፈፀምብህ ነው። አውቀም ሆነ ሳታውቅ ያየሃው ነው በህይወትህ ላይ የሚሆነው፤ዛሬ ጥሩ ነገር ካላየህ የነገው ህይወትህ ከዛሬ ውሎህ ይቀዳል። መቼም ብሆን በራሳቹ ላይ አሉታዊ ነገር አትናገሩ ምክንያቱም ከምታስቡት በላይ በጣም የመስራት ሀይል አለው። መልካም ምሽት ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

በህይወታቸው ደስተኛ የሚባሉ ሰወች የሚቀበሉ ሳይሆን የምሰጡ ናቸው። ሁል ጊዜ መቀበልን ብቻ አትለማመዱ፤ አንዳንደ መስጤትንም ማወቅ አስፈላግ ነው፤ ሁል ጊዜ ለራሳቹ ብቻ አትኑሩ ህይወታቹ ጣዕም እንዲኖረው ከፈለጋቹ የተለመደውን ነገር ከማድረግ #ዩንክ የሆኑ ነገሮች ስታደረጉ በውስጣቹ እንግዳ ስመት ይሰማቿል፤ የተራቡትን አብሉ ፤አቅማቹ በፈቀደ መልኩ ለሰወች ጥሩ ነገር ማድረግን ተለማመዱ ፤ያን ጊዜ በእነሱ ፈገግታ ውስጣቹ ሰላምን ያገኛል ሞክሩት በጣም ደስታ ይሰማቿል ። መልካም ቀን ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ሁሉም ነገር ጥሩ ነገር እንዳለው ሁሉ መጥፎ ጎንም አለው። ሁሉም ነገር ጥሩ በሆነ ቁጥር ለዛ ነገር የሆነ የሚከፈል ዋጋ እንዳሌ ማሰብ የግድ ይላል። በለስ ፍረው በጣም ጣፋጭ ነው፤ ውጭው ግን በእሾህ የተከቤበ ነው መብላት ከፈለክ ተወግተህ ከደማሃ በኋላ ነው፤ ስኬትም እንደዛ ነው ተኝተህ የሚታገኘው ሹመት የለም፤ ተኝተህ የምትበላው እንጀራ አይኖርም፤ ልኖርም አይችልም። #አታስብ የሚታገኘውን ነገር ሁሉ የሚታገኘው በራስህ ጥረትና ልፋት ቢቻ ነው ፤ካልሆነ የእጅህን ታገኛለህ መቼም ማሽላ ዘርተህ ጤፍ እንደማትጠብቅ እርግጠኛ ነይኝ ። መልካም ምሽት ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

photo content

ኢትዮጵያ ከአለማችን ደስተኛ ሀገራት በ130ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።