en
Feedback
Yoni Motivation

Yoni Motivation

Open in Telegram

ከማንም አትጠብቅ

Show more
698
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው የዒድ-አልፊጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ። በአሉ የሰላም፣ የጤና፣ የመተሳሰብና የፍቅር እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!! ዒድ-ሙባረክ Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ጧት ልክ 11:00 ሰአት ላይ ከእንቅልፍህ ተነስና ስፖርትን ስራ፤ ከዛም በቀዝቃዛ ውሃ ሻውር ግባ፤ እመነኝ ቀንህ ከምታስበው በላይ ያማረ እና የተሳካ ይሆናል ።ተማር ከሆንክ ክፍል ውስጥ በጣም ደስ
ጧት ልክ 11:00 ሰአት ላይ ከእንቅልፍህ ተነስና ስፖርትን ስራ፤ ከዛም በቀዝቃዛ ውሃ ሻውር ግባ፤ እመነኝ ቀንህ ከምታስበው በላይ ያማረ እና የተሳካ ይሆናል ።ተማር ከሆንክ ክፍል ውስጥ በጣም ደስ እያለክ ተምሬ ትጨርሳለህ፤ ሰራተኛም ከሆንክ የምታስተናግደው ደንበኛ ጭምር ባንተ ፈገግታ ቀኑ አምሮበት ይውላል ።ሞክሬው ትደስትበታለህ፤ ውስጥህ ሰላም ይሰማል፤ ሌሎችን ሰወች ሰላም ስትል እንኳን በነቃ መንፈስ ነው ፤የነቃው መንፈስህ ብዙወችን ደግሞ ያነቃል፤ በራስ መተማመንህ ከመቼውም ግዜ በላይ ይጨምራል። ደስተኛ ህይወት ይኖረሃል ሞክረው ታመሰግነኛለህ ። እንቅልፉ አታብዛ!! መልካም ምሽት ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

አንድን ስህተት ለመሸፈን ስትል ለላ እጥፍ ስህተት ውስጥ አንዳትገባ ጥንቃቄ አድርግ። እኛ ብዙ ግዜ የለመድነው ስህተትን ተናግረን ይቅርታን ከመጠየቅ ይልቅ ስህተትን በስህተት ማጣፋት ይቀለናል ።ያ ግን መጨረሻ ላይ የማይፋቅ ጠባሳ በህይወታችን ጥሎብን ያልፋል፤ መቼም ብሆን ምንም ያክል እንኳን ከባድ ነገር በስህተት ፈፅመን ከሆን፤ከመደበቅ ይልቅ ተናግሮ ይቅርታን እንደመጠየቅ ጥሩ ነገር የለም ። አዕምሯችን እና መንፈሳችን ሰላምን ያገኛል ። መልካም ምሽት ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ህልምህን ለመኖር እዝህ ያለሃው አንተ ቢቻ ነህ። ለሎች ሰወች አዝህ ያሉት የራሳቸውን ጉዳይ ለማስፈፀም እንጅ ያንተ ነገር አስጨንቋቸው እንዳልሆነ ታውቃለህ? አብዛኛው ሰው የራሱን ህልም አባቱ እንዲያሳካለት ይፈልጋል! አብዛኛው ሰው ወጭ ያለው አጎቱ አክስቱ የራሱን ህልም እንድያሳኩለት ይመኛል፤ አክስትሽ አጎትሽ አዛ ያሉት የራሳቸውን ህልም እውን ለማድርግ እንጅ ላንች ህላም ብለው አይደለም። ህልምሽ የታየው ላንች ከሆነ ለምን ለሎችን ትጠብቅያለሽ?የሚከፈለውን ያህል ከፍለሽ ህልምሽን ሚታሳክ ከሆነ ህይወትሽን በሙሉ ደስተኛ ሆነሽ ትኖርያለሽ እመኘኝ ።የሚትኖሩለት ህልም ካላቹ አውነትም በህይወት አላቹ ህልም ይኑራቹ ። መልካም ምሽት ተከተለኝ አንድ ቀን ትለወጣለህ Yoni Motivation https://t.me/yon3f

የዱር እንስሳትን የማመግብ አምላክ አንተን በአምሳሉ ፈጥሮ አንደት ይረሳሃል? የከፈተውን ጉሮሮ ከየትም አምጥቶ ሳይዘጋ አያሳድርም። የሰማይ ዎፎችን የምድር ነፍሳትን እንኳን ሳይቀር ይመግባል ።ነገር ግን በተኙበት ምግብ በ Delivery እያስመጣ አይደለም ፤እንደት ''ይመግባል ካልከኝ ''?ስንቀሳቀሱ ነው። ጥሬታቸው ተጨምሮ ነው፤ ወፊቷ ከጎጆዋ ውስጥ ሳትወጣ እዛው ተኝታ #delivery አየጠበቀች ብትሞት እግዜአብሄር ምን አደረጋት? ወጥታ ግን ብትንቀሳቀስ የሚትበላውን ነገር ታገኛለች፤ ህይወቷንም ታቆየዋለች፤ Delivery አትጠብቅ ወጥተህ ተንቀሳቀስ፤ ስትንቀሳቀስ ሁሉም ነገር ቦታ ይይዛል፤ ቆሜ በሃሳብ ብቻ ራስህን አታስጨንቅ ። አይዞን እግዚአብሔር አሌ!! መልካም ቀን ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

የአንድን አመት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግክ 👉የአንድን አመት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግክ ክፍሉን የደገመን ተማሪ ጠይቀዉ ! 👉የአንድን ወር ዋጋ ለማወቅ ከፈለግክ ካለወሩ የተወለደ ህፃን የወለደችን ሴት ጠይቃት ! 👉የአንድን ሳምንት ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ በየሳምንቱ የሚወጣን ጋዜጣ አሳታሚ ጠይቀዉ ! 👉የአንድን ቀን ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ የወሳኝ ፈተናን ዉጤት ነገ ለመስማት የሚጠብቅን ተማሪ ጠይቀዉ ! 👉የአንድን ሰአት ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ ለመገናኘት የተቀጣጠሩ አዲስ ፍቅረኞችን ጠይቃቸዉ ! 👉የአንድን ደቂቃ ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ አዉቶቢስ ለትንሽ ያመለጠዉን ሰዉ ጠይቀዉ ! 👉የአንድን ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ ከአደጋ ለጥቂት ያመለጠን ሰዉ ጠይቀዉ ! 👉የአንድን ሚሊ ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ በኦሎምፒክ ሩጫ ለጥቂት የተቀደመን ሯጭ ጠይቀዉ! ጊዜ=ህይወት! ስለዚህ ጊዜህን ስታባክን ህይወትህን ታባክናለህ! ጊዜህን በትክክል ስትመራ ደግሞ ሕይወትህን በትክክል ትመራለህ!! ✍ዶ/ር ኢዮብ ማሞ ዕለታዊ አስታዋሽ ከ Abrish Dream የተወሰደ @dailyremindere 🅐.🅕

የአንድን አመት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግክ 👉የአንድን አመት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግክ ክፍሉን የደገመን ተማሪ ጠይቀዉ ! 👉የአንድን ወር ዋጋ ለማወቅ ከፈለግክ ካለወሩ የተወለደ ህፃን የወለደችን ሴት ጠይቃት ! 👉የአንድን ሳምንት ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ በየሳምንቱ የሚወጣን ጋዜጣ አሳታሚ ጠይቀዉ ! 👉የአንድን ቀን ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ የወሳኝ ፈተናን ዉጤት ነገ ለመስማት የሚጠብቅን ተማሪ ጠይቀዉ ! 👉የአንድን ሰአት ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ ለመገናኘት የተቀጣጠሩ አዲስ ፍቅረኞችን ጠይቃቸዉ ! 👉የአንድን ደቂቃ ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ አዉቶቢስ ለትንሽ ያመለጠዉን ሰዉ ጠይቀዉ ! 👉የአንድን ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ ከአደጋ ለጥቂት ያመለጠን ሰዉ ጠይቀዉ ! 👉የአንድን ሚሊ ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ በኦሎምፒክ ሩጫ ለጥቂት የተቀደመን ሯጭ ጠይቀዉ! ጊዜ=ህይወት! ስለዚህ ጊዜህን ስታባክን ህይወትህን ታባክናለህ! ጊዜህን በትክክል ስትመራ ደግሞ ሕይወትህን በትክክል ትመራለህ!! ✍ዶ/ር ኢዮብ ማሞ ዕለታዊ አስታዋሽ @dailyremindere 🅐.🅕

(የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 24) ---------- 1፤ ነገር ግን ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ያዘጋጁትን ሽቱ ይዘው ከእነርሱም ጋር አንዳንዶቹ ወደ መቃብሩ እጅግ ማልደው መጡ። 2፤ ድንጋዩንም ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት፥ 3፤ ገብተውም የጌታን የኢየሱስን ሥጋ አላገኙም። 4፤ እነርሱም በዚህ ሲያመነቱ፥ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ፤ 5፤ ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው። ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም። 6-7፤ የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደ ተናገረ አስቡ። መልካም የትንሳኤ በአል ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ዛፍን ከቆረጥነው በጣም ቢዙ ሆነው ነው የሚያለመልመው። አንዳንድ ጊዜ ብዙ ሆነህ አና በኃይል ለማደግ ካለህበት ቦታ መቆረጥ መቃጠል ልኖርብህ ይችላል። ስትቆረጥ ያማል! ምንም ተስፋ የምባል ነገር አይታይም! ስትቃጠልም እንደዛው፤ ነገር ግን ከትንሽ ጊዚያት በኃላ ልክ እንደ ዛፉ አለምልመህ እና አቆጥቁጠህ ራስህን ታገኛዋለህ። እስከዛው ግን አደራህን፤ ተስፋ እንዳትቆርጥ ፤ጠንከር በል፤ ቆፍጠን በል፤ ሁሉም ነገር በራሱ ጊዜ እና ሳአት ይሆናል። አንቴም ስለፈለግክ ሳይሆን መሆን ስላለበት ይሆናል አንተ ግን በጭራሽ እጂህን እንዳትሰጥ ። መልካም የትንሳኤ በአል ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ስዕሉ በሮማን ቻርቲ ውስጥ ይገኛል። ምንም እንኳን ስዕሉን ለመጀመሪያ ጊዜ ስናየው የማይመች ስሜት የሚያሳድር ቢሆንም የተሳለበትን አላማ እና ከስዕሉ ጀርባ ያለውን ታሪክ ስንሰማ በርግጥ ድንቅ ስሜት
ስዕሉ በሮማን ቻርቲ ውስጥ ይገኛል። ምንም እንኳን ስዕሉን ለመጀመሪያ ጊዜ ስናየው የማይመች ስሜት የሚያሳድር ቢሆንም የተሳለበትን አላማ እና ከስዕሉ ጀርባ ያለውን ታሪክ ስንሰማ በርግጥ ድንቅ ስሜት ያጭራል። °°° በአውሮፓ ምድር በፈረንሳይ ሀገር lious XIV በነገሰበት ዘመን ሲሞን የተባለ አንድ ሰው በፈፀመው ወንጀል የሞት ፍርድ ይበየንበታል። የሞት ፍርዱም በርሃብ እንዲፈፀም ወይም እንዲተገበር ፤ ርሃቡ እስኪገድለው ድረስም ወይኒ ቤት እንዲቆይ ወደ ማቆያው ይወረወራል። ይኸን የሰማችው ፖሮ የምትባል ሴት ልጁ የሚሞትበት ቀን እስኪደርስ ድረስ ለመጎብኘት መንግስቱን ትማፀናለች። መንግስቱም ምንም አይነት የሚበላ ነገር ሳትይዝ እንድትጎበኘው ፈቃዱን ይሰጧታል። °°° ልጁም ለወራት በየቀኑ ምግብ ሳትይዝ ገብታ ጎብኝታው ትወጣለች። በወራት ውስጥ በርሃብ የተነሳ የሲሞን መጠውለግ መክሳት እንዲሁም ሞት ቢጠበቅም ሰውዬው ወዙ የተሻለ እየወጣ እያማረበት ለ6 ወራት ይቀጥላል። ይኸን ያስተዋሉ ፓሊሶችም ምን እየበላ እንደሆነ ሲሰልለሉ የገዛ ልጁ ጡቷን ከጨቅላ ልጇ አትርፋ የአባቷን ህይወት ለማሰንበት ስትል እያጠባችው እንደሆነ አዩ። °°° ይኸን ነገር ሪፓርት ሲያደርጉ ስለፍቅሯ ሲባል ሰውዬውን በነፃ እንዲለቀቅ ተወስኗል። °°° ይኸ ስዕል በ30 ሚሊዮን ዩሮ የተሸጠ ሲሆን የምንጊዜ ውድ ስዕሎች ውስጥ ይመደባል። °°° ሀውልቱም David klndt በተባለ ዲዛይነር 1741 ማቆያ ቤቱ ወደዚህ ከአንድ ዓመት በፊት የቀረፀው ነው። °°° ስዕሉ እና ሀውልቱ ሴት ልጅ ለአባቷ ያላትን ከፍተኛ ፍቅር ያሳያል ተብሎም ይታመናል።

የዛሬው ቀን ከሌሎች ቀናት በጣም ይለያል። ምክንያቱም አየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ኃጥያት ስል ራሱን አዋርዶ አንደ ወንጀለኛ በእንጨት የተሰቀለበት ቀን ስለሆነ፤ይህ በአለም ታርክ የመጀመሪያ ነው። እዝች አልም ማንም ስለ ማንም ሀጥያት ስሞት አይተንም ሰምተንም አናውቅም የእኛ እየሱስ ይለያል ። ክብር ለእየሱስ ይሁን መልካም ቀን ይሁንላቹ Yoni Motivation https://t.me/yon3f

አምላክ ጠላትህን ውደድ ሲልህ ጠላትህን ለመጥቀምን አንተን ለመጉዳት አይደለም ። በተጨማሪ አንተ እንዳትጎዳበት ነው እንጂ። እባብ ከነደፈህ በኃላ መርዙ ሰውነትህ ውስጥ ሳይሰራጭ መከላከል ትችላለህ ። መርዙ ሰውነትህ ውስጥ በመሰራጨት ላይ እያለ አንተ እባቡን ለመግደል ብትሮጥ ቀድመህ ልትሞት ትችላልህ። ጠላቾችህን ለማጥፋት ያለህ ብቸኛ አማራጭ እነርሱን መውደድ ነው ። ቂም ማለት አንተ መርዙን ጠጥተህ ሌላው እንዲሞት መጠበቀ ማለት ነው። 👉👉በየዕለቱ ራስህን መባረክ አታቁም አትርሳ! መልካም ምሽት ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ገንዝብ ፍቅርና ጤናን አይገዛም ይላሉ፤ እሽ ይሁን እነም እስማማለሁ ፤አይገዛም። ነገር ግን ድህነተን በጣም ወደዋለው የምትሉ ሰወች ደሃ በመሆነ እኮራለሁ የምትሉ ድህነት ምን ይገዛል? እስክ ንገሩኝ? ያለህበት ድህነትህ ተመችቾክ እንደምትኖር አታስመስል! እርግጠኛ ነይኝ አልተመቸህም! ራስህን ለማፀናናት ስትል ገንዘብ ምንም መስራት አንደማይችል አብዝተህ ትናገራለህ። ያ ማለት ደግሞ ገንዘብ ምንም መስራት አይችልም ማለት አይደለም። አትሞኝ! በአሁኑ ጊዜ ከፈጣር ቀጥሎ ከማንም በላይ ቀና የሚያረግህ ያለህ ገንዘብህ ነው። የገንዘቡ ጤናን መግዛትና አለመግዛት የሚያውቀው፤ የኩላልት ንቅለ ተከላ ለማደረግ በየ መንገድ ዳር፤ በምንባስ መክና ውስጥ ተኝተው አላፊውን አግዳምይውን የሚያስለምነውን ምስክን ሰው ጠይ፤ ይነግራሃል ።ፍቅርን አይገዛም የሚትለኝ በጣም ተፈላልገው፤ ተፋቅረው ከተጋቡ በኃላ የሚቀመስ ነገር አጥተው፤ በተጋቡ በወራቸው የተለያዩ ጥንዶችን ጠይቅ። የገንዘብን ጥቅም ይነግሩሃል ሳጠቃልሊ ገንዘብ ያሰፈልጋል! ያለህን በአግባብ ተጠቀም ከእጅህ ከወጣ ዋጋ ያስከፈላሃል ። መልካም ምሽት ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ከተሰበረ ተመልሶ የማይጠገነው ሸክላ ብቻ ነው ።የሰው ልጅ ከተወለደበት ቀን ጀምሮ በህይወቱ በጣም ብዙ ነገሮችን ያሳልፋል። ባመነው ሰው ይከዳል፤ ያዝኩት ያለው ከእጁ ያመልጣል፤ ቁኑ ይመሽበታል፤ መግብያ መውጫ ያጣል፤ ያለቅሳል፤ ራሱን ለማጥፋት ይሞክራል፤ ከዛም ይመለሳል፤ ይረጋጋል! ታድያ አንተ የሰው ልጅ አይደለህም? ራስህን እንደ ሸክላ ለምን ታያለህ? የተበላሹ ነገሮችን ለማስተካከል እኮ ትችላለህ! እጅህ ብሰበር ተሰብሯል በቃ! ከአሁን በኃላ አይጠቅመኝም ብለህ አትቀመጥም፤ ወገሻ ቤት ትመላለሳለህ፤ መልሰህ ለመጠቀም። በህይወታችን የሚገጥሙን የትኛውም ችግሮች ከእንዝህ ጋር አንድ አይነት ናቸው። መልሰህ ራስህን ስራ፤ እህቴ መልሰሽ ለራስሽ ቦታ ስጭ፤ ከቁስሉ ለማገገም ሁለተኛ ዕድልሽን ተጠቀም ። መልካም ምሽት በያላቹበት ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ዛሬ በጣም ውስጥ ተነሳስቶ ፍላጎትህ ጨምሮ ያቀድከውን ስራ ከመጀመርህ በፊት ቆም ብለህ አስብ። ፍላጎት ያደረብህ እውነትም ያንን ነገር ለመስራት ከዛ በፊት አስበህ ታውቃለህ? ወይስ የዛሬው ውሎህ ነው ያነሳሳክ? ዛሬ አይተህ ለመስራት ከተነሳ በስሜትህ ልሆን ስለምችል አስብበት! ዛሬ በስሜት ተነስተህ ነገ ለማስቀጠል አንዳይከብድህ ተጠንቀቅ። ውስጥህ ለመስራት የሚትመኘውን ስራ ሞክር፤ እንጅ እንትና ሰርቶ ስለተሳካለት ለአንተም ይሳካል ማለት አይደለም! የሱ ፋሽን ለአንተ ላይሰራ ይችላልና ጥንቃቄ ያስፈልጋል። መልካም ምሽት ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ለምታገባት ምስትህ ጥሩ ባል መሆን ትችላለህ?ለልጆችህስ ጥሩ አባት መሆን ትችላለህ ? ለቤትሰቦችህስ ጥሩ ልጅ መሆን ትችላለህ? ራስህን ጠይቅ! አንተ ጥሩ ባል ሳትሆን ምስትህ ጥሩ ሴት እንድትሆን ለምን ትፈልጋለህ? አንተ ጥሩ አባት ሳትሆን ጥሩ ልጆችህ እንዲኖሩ ለምን ትመኛለህ? መጀመርያ አንተ ተቀየር! ሁሉም ነገር እንዲቀየር ከፈለክ። አንተ ጥሩ ስትሆን ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል! ውሎህን ቀይር ፤አጠገብህ ያሉ ሰወች እንዲቀየሩ ከፈለክ ቁጭ ብለህ አታማርር ተቀይረህ ቀይራቸው። መልካም ምሽት ይሁንላቹ ። ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ጧት 11:30ላይ ከእንቅልፍህ ተነስ፤ በመጀመርያ ፀሎት አድርግ ፤ከዛ ስፖርት ስራ፤ በቀዝቃዛ ውሃ ሻውር ውሰድ፤ ቁርስህን በአግባቡ ተመገብ ፤ከቤትህ ስትወጣ እነዝህን ዛሬ አሳካቿለሁ ብለህ ዉጣ!! እመነኝ ቀኑ ያአንተ ነው። በጣም ደስ እያለክ ትውላለህ!! ማታ ስትመለስ ከመተኛትህ በፍት አመስግን ፤ጧት ከአቀድካቸው ምን ያህሉን እንዳሳከህ ስራህን ገምግም፤ ነገ ምን እንደምትሰራ የት እንደምትውል ዕቅድ አውጣ !!ከትንሽ ጊዜ በኃላ ስኬታማ ከምባሉ ሰወች ውስጥ አንዱ አንተ ነህ ። መልካም እሁድ ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

የት ልግባ? ምን ልሁን?ብለህ አትጨነቅ!! አንገትህን ዝቅ አድርገህ እግዚአብሔርን ጠይቅ፤ ላንተ የማይቻለው ለእግዚአበሐር ይቻላል ።በአንተ አቅም የማይሆነው ነገር ለአላክህ በጣም ቀላል ነው ።ሁል ጊዜ በራስህ ዕውቀት በራስህ ጥበብ ቢቻ ነገሮችን ለማድረግ ስትሞክር ብዙ ትለፋለህ ።ነገር ግን በእሱ ላይ ከጣልክ አምላክ ነውና አይጥልህም፤ ልብ በል ያ ማለት ደግሞ አግዚአብሔር ያደርጋል ብለህ አንተ ተኛ ማለት አይደለም ። መልካም ምሽት ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ልብህ የተደፋ ውሃ እንኳን አያቃናም፤ ለነገሮች ምንም አይነት ደንታ የለህም!! እያየህ ለምበላሹ ነገሮች ለምን ትንሽ ስሜት አይኖርህም?ለምን ይሃን ያህል ክፉ ትሆናለህ? ሁል ጊዜ ለምን ሌሎች ሰወች በከፈሉበት ወጋ መኖር ያምራሃል? ትንሽ እንኳን ቆም ብለህ ለራስህ አስብ እንጂ!! መልካም ቀን ይሁንላቹ ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን Yoni Motivation https://t.me/yon3f

ቀኑ በጣም የሚያስጨንቁ ነገሮችን ይዞልን ነው የሚመጣው። ጧት ከአልጋችን ስንነሳ በሰላም አውለኝ ብሎ መውጣት አስፈላጊ ነው!! በዛውም ልክ ደግሞ በጣም ብዙ መልካም ነገሮችን ይዟልን ነው የሚመጣው፤ ነገር ግን የእኛን አጠቃቀም በጣም ይፈልጋል፤ አዎንታዊ አመለካከት ልኖረን ያስፈልጋል፤ ጧት ስንነሳ፤ ዋውው ዛሬ ቀኑ ደስ ይላል፤ ስትል ደስ የሚያሰኝ ነገር ባይኖር እንኳን ጧት የተናገርካት ቃላትህ ቀኑን አሳምራ ታውለዋለች። ስለዝህ ቀናችንን በመልካም አመለካከት እንጀምር፤በህይወታችን ደስተኛ መሆን እንጀምራለን ሞክሩት ትወዱታላቹ ። መልካም ቀን ይሁንላቹ !! ተከተለኝ አንድ ቀን እንለወጣለን