የራያ ሰለፍዮች ቻናል
ይህ የራያ ሰለፍዮች ቻናል ነው የተለያዩ የሱና ኡስታዞች ትምህርቶችና ፁሁፎች ይለቀቁበታል። هدفنا الدعوة إلى الله عز وجل بالرجوع إلى الكتاب والسنة بفهم سلف الأمة . قنــاة = تهتــم بنشـر كـل ما هـو مفيـد ونافــع للأمــة . https://chat.whatsapp.com https://t.me/+75U-d0sq3IY4MDk0
Show more- Subscribers
- Post coverage
- ER - engagement ratio
Data loading in progress...
Data loading in progress...
6410
8830
16110
15010
ነብዩ ﷺ መቼ ተወለዱ? ሌላ የመውሊድ ራስ ምታት ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ መውሊድ በኢስላም መሰረት እንደሌለው ከሚያመላክቱ ማስረጃዎች አንዱ ታሪክ ነው። ነብዩ ﷺ በምን ወር ተወለዱ? በስንተኛው ቀን? በስንት አመት? ለነዚህ ጥያቄዎች የሚኖረን መልስ በራሱ የመውሊድን በዓል አላስፈላጊነትና መሰረት-አልባነት ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል። 1. የተወለዱበትን አመት በተመለከተ በዝሆኑ አመት ማለትም የሐበሻው አብረሀ ከዕባን ለማፍረስ በዝሆን የታጀበ ሰራዊት ይዞ የዘመተበት አመት ነው። ይህም እ.ኤ.አ በ 570 ወይም 571 ማለት ነው። በታዋቂዎቹ የሱንና ኪታቦች ውስጥ ይህን የሚያመላክት መረጃ ባይኖርም በኢብኑ ዐባስ ስም በይሀቂ የዘገቡት ግን አለ። ግና ይህም ቢሆን ሰነዱ መጠነኛ ውዝግብ አለበት። “በዝሆኑ አመት በየትኛው ጊዜ?” የሚለው እራሱ የተለያዩ ሀሳቦች ተሰንዝረውበታል። ለምሳሌ ነብዩ ﷺ የተወለዱት፡- 1.1. በዘመቻው እለት ነው የሚል ሰነድ አልባ ዘገባ ከኢብኑ ዐባስ ተዘግቧል። 1.2. ከዝሆኑ ዘመቻ ከወር በኋላ ነው ተብሏል። 1.3. ከዝሆኑ ዘመቻ ከ40 ቀን በኋላ ነው ተብሏል። 1.4. ከዝሆኑ ዘመቻ ከ 50 ቀን በኋላ ነው ተብሏል። [አልኢስቲዓብ፡ 1/30] የዝሆኑ ዘመቻ ሙሐረም 13 እንደተካሄደ አልኸዋሪዝሚና ሌሎችም የጠቀሱ ሲሆን ሌሎች ደግሞ “የለም ረቢዑል አወል ነው” ይላሉ። የነዚህን ሀሳብ ከግምት ካስገባን 8 የተለያዩ ሃሳቦች ኖሩ ማለት ነው። በሙሐረም ከሆነ አራት፣ በረቢዑል አወል ከሆነ ደግሞ ሌላ አራት። በድምሩ ስምንት። 2. “በምን ወር ተወለዱ?” ለሚለውም ብዙ ሀሳቦች ተነስተዋል። 3.1. በሶፈር ወር ነው ያሉ አሉ። 3.2. በረመዷን ወር ነው ያሉ አሉ። ይሄ ሀሳብ ከታዋቂው የታሪክ ምሁር ዙበይር ኢብኑል በካር (256 ሂ.) እና ከሌሎችም ተላልፏል።…
14910