cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የዘወትር ምንባብ

ይህ ቻነል በቤተ ክርስትያን የግጻዌ መጽሐፍ መሰረት የየዕለቱን የእግዚአብሔር ቃል ለማካፈል በማሰብተከፈተነል ነው። ሃሳብ አስተያየት ካለችሁ በ@ መስጠት ይቻላል

Show more
Advertising posts
514
Subscribers
-124 hours
No data7 days
+230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

“....... #ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።” — ሉቃስ 24፥5 እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ 😍🙏 1ኛ ቆሮንቶስ 15 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁰ አሁን ግን #ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል። ²¹ ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና። ²² ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ #ሁሉ_በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና። ²³ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ #ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፥ በኋላም በመምጣቱ #ለክርስቶስ የሆኑት ናቸው፤ ትንሳኤን ስናከብር........ ይላሉ አባታችን “ #በእምነት ትንሣኤ፣ #በአምልኮተ_እግዚአብሔር ትንሣኤ፣ #ለእግዚአብሔር_በመታዘዝ ትንሣኤ፣ #በፍቅር ትንሣኤ፣ #በሰላም ትንሣኤ፣ #በይቅርታ ትንሣኤ፣ #በመከባበር ትንሣኤ፣ #በአንድነት ትንሣኤ፣ #በመተሳሰብ ትንሣኤ ወዘተ በመሳሰሉ ሃይማኖታዊና ግብረ ገባዊነት ጸንተን መኖር ከቻልን የፊተኛው ትንሣኤ ማለት እሱ ነው፡፡ “    ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ መልካም በዓል 😍🙏
Show all...
#ያንተም_ዕሁድ_እየመጣ_ነው! #አንድ ጴጥሮስ፣ አንደኛው የክርስቶስ ቅርብ ደቀመዝሙሩ፣ በተከታታይ ሶስት ጊዜ ክዶታል! ከባድ ጊዜዎች እስካልመጡ ድረስ ጓደኞችህ ጥሩ ዘመዶችህ ናቸው። አስቸጋሪ ጊዜዎች ግን እውነተኛዎቹን ለይተህ እንድታውቅ ያደርጉሃል። በመከራህ ጊዜ ከጎንህ ካልሆኑ ጓደኞችህ አይደሉሞ ማለት ነው። #ሁለት በአንደ ወቅት የክርስቶስ ተአምራት ተጠቃሚ የነበሩ ሰዎችም ከክርስቶስ ይልቅ ወንጀለኛውን በርባን መርጠዋል! በሕይወት ሰዎች አጭር የማስታወስ አቅም ነው ያላቸው። ሁሉም ሰው ያደረግክለትን ጥሩ ነገር አያስታውስም። ቢሆንም ግን ጥሩነትህን ማጣት የለብህም። #ሶስት የሰደቡት፣ የተፉበትና የተዘባበቱበት ወታደሮች ማን እንደሆነ አያውቁም ነበር! ሰዎችን ሁሉ አክብር በተለይ ማን እንደሆኑ ካላወቅክ። አንዳንድ ሰዎች ወደ ሕይወታችን የሚመጡት በተቀደሰ ቁልፋቸው የተቀደሱ የሕይወት በሮችን ሊከፍቱልህ ነው። #አራት አርብ ስቀለቱ ነበር፣ እሁድ ደግሞ ትንሳዔው! መልካም ቀኖቻችን ከመጥፎ ቀኖቻችን ብዙ እንደማይርቁ ብናውቅ ኖሮ ትንሽ በርትተን እንቆይ ነበር። ታገስ! ያንተም እሁድ እየመጣ ነው! #አምስት ክርስቶስ የተሰቀለው ከሁለት ሌቦች ጋር ነበር፤ ሲታዩ ሶስት ሌቦች ይመስሉ ነበር! አትፍረድ! ከተጠርጣሪዎች መሐል የሁኔታ ተጠቂዎች አሉ። ሁሏም ሳታገባ ያረገዘች ሴት ዝሙተኛ አይደለችም። የተሰቀለ ሁሉ ወንጀለኛ አይደለም። #የተሰቀለው_ንጉሥ መጽሐፍን ደግሞ አንብበው፤የክርስቶስን ሕማማት፣ ስቅለት፣ ፍቅርና ትንሳኤ በቦታው ያለን ያህል ወስዶ ያሳይሃል።
Show all...
Repost from Nolawi ኖላዊ
ባሕር ተከፈለ ቍጥር የሌለው ኃጢአታችንን ቍጥር በሌለው ፍቅርህ ደምስሰህ ይኸው ባሕር ተከፈለ ። መውለድ መሐን መሆን ሁለቱም ሲያስፈራን ፣ ፍቅር ጥላቻ ሁለቱም ሲያውከን ፣ የምንመርጠውን ለማናውቅ ለእኛ ባሕር ተከፈለ ። ገነትን አጥተን ግዞት ለወረድነው ፣ ንገሡ ብንባል በሌብነት ቅጠል ሥር ለተሸሸግነው ፣ ልጆቻችን ሲጋደሉ ላየነው ፣ ሞትን በልጅ ለጀመርነው ለእኛ ለትኩዛን ደስ ይበለን ባሕር ተከፈለ ። ውኃ ተሸክመን ፣ ውኃ ሆነን ውኃ ለምንፈራ ፣ በውኃ ጅራፍ ልክ የሌለው መከራ ለደረሰብን ፣ ሞገድ የማይቀርበው መርከብ ኢየሱስ ክርስቶስ ፣ ልብሱን ውኃ እንዳይነካው ዕርቃኑን ተሰቅሎ ባሕር ከፈለልን ። በእውነት ደስ ይበለን ። የባለጠጋው አብ ልጅ ፣ ባለጠጋው ኢየሱስ ድሀ መሆን ምን ያስቀናዋል ! ብርዝና ጠጁ ሳለ ሀብታም ሁሉ በድሀ እየቀና ውኃ ፣ ውኃ አለ ። ድሀ የያዘው ሁሉ ሀብታም ያስቀናዋል ። ድሀ መሬት ሲተኛ ፣ መሬት መተኛት ለጤና ጥሩ ነው እያለ ሀብታም በድሀ ቀና ። ባለጠጋው ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ከድሀ ቤት ማደርህ ፣ እንደ ድሀ መኖርህ ፣ በአንዲት ጨርቅ ዕድሜ ልክህን መታየትህ ፣ ምንም እንደሌለው ዕርቃንህን መሰቀልህ ፣ መሬት ላይ ለሦስት ቀን መተኛትህ ፣ ስለ እኛ ብትቀና ነውና ድሀ ሆነህ ባለጠጋ ያደረግኸን የሰማይና የምድር ውበት ፣ የቁንጅና ዳርቻ አማኑኤል ተመስገን ። ባሕር ተከፈለ ሰዎች እልል በሉ ። በባሕር ላይ መሻገር ሳይሆን በተከፈለ ባሕር ውስጥ ማለፍ ለእኛ ሆነ ። በባሕር ላይ መሻገር ብልጠት ፣ በባሕር ውስጥ ማለፍ የእምነት ኃይል ነው ። የትላንት ገዥ ፣ የጣለኝ ድጥ መልሶ ሊይዘኝ ፣ ወጣሁ ስል ሲያስቀረኝ እየገሰገሰ ነው ። ትላንትናዬ ነገ ላይ ተሻግሮ መንገድ ሊዘጋብኝ ነው ። የትላንት ታሪክ ፣ የዛሬ ሕይወት ፣ የነገ ተስፋ የሌለኝ ሊያደርገኝ ነው ። ምስጋና ለአማናዊው ሙሴ ይሁን ባሕር ተከፈለ ። በእምነት የተሻገሩትን ፣ የሚሞክሩ የተዋጡበት የቀይ ባሕር ምሥጢር ድንቅ ነው ። እምነት ያሻግራል ፣ ሙከራ ያሰጥማል። ባሕር ተከፈለ በአማናዊው ሙሴ በክርስቶስ ሞት የጀርባ ታሪክ ሆነ ። ልጆቻችንን የበላ ፣ በውዶቻችን ደም ጡብ የሠራ ፣ ኖረንለት የገደለን ፈርዖን ዲያብሎስ ድል ተነሣ ። ላንገናኝ ከሰይጣን ተለያየን ። በሕልማችን እንዳያውከን የፈርዖን ሬሳ በቀይ ባሕር ታየን ። እባቡ እንዳያስደነግጠን ራሱ ተቀጠቀጠልን ። በደምመላሽ ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ በጠላት ራስ ላይ ቆመን ዘመርን ። የወይራው ቀንበጥ መንፈስ ቅዱስ መዳናችንን አረጋገጠልን ። እውነትን በእውነት ተቀበልን ። መንፈሱ ለመንፈሳችን መሰከረልን ። ስለነገሩን ሳይሆን ስለተሰማን በእውነት በእርሱ ዐረፍን ። ባሕር ተከፈለ ሰዎች ደስ ይበለን !!! ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ሚያዝያ 26 ቀን 2016 ዓ.ም.
Show all...
#ቀዳም ሥዑር የዕለቱን ወንጌል እናንብብ! ሚያዝያ 26 ቀን 2016 ዓ.ም የማቴዎስ ወንጌል ም 27 ቁ 62 - 66 መልካም ዕለተ ቀዳም ሥዑር! #ethiopianorthodoxtewahedochurch #የዕለቱ_ወንጌል #tewahedomediacenter #saturday
Show all...
"ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ። አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ። ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።" (የሉቃስ ወንጌል 23:46) "ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።" (የማቴዎስ ወንጌል 27:50) "ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኸ ነፍሱንም ሰጠ።" (የማርቆስ ወንጌል 15:37) "ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ። ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።" (የዮሐንስ ወንጌል 19:30) 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
ሰቀሉህ !!! አንተስ ሁሉን ስታውቅልን ለራስህ አላውቅ ብለህ በዳይህን እንዴት ትፈጥራለህ ? እኛን የሚያዋድደን አለማወቅ ፣ አለመተዋወቅ ነው ። አንተ ብቻ አውቀህ ትወደናለህ ። ሰቀሉህ መልኬ ያልካቸው ፣ ዝቅ ብለህ ከአፈር ያነሣሃቸው ፣ ሬሳቸውን በአፍህ እስትንፋስ ሕያው ያደረግህላቸው ፣ ሚሊየን ጊዜ አድርገህላቸው አንድ ምስጋና የማያውቁ እነዚያ የአዳም ዘሮች ሰቀሉህ ። አንተ ለሁሉ እንደ ተሰቀልህ ፣ አንተን ሁሉ ሰቀለህ ። ከነጻነት ጋር የፈጠርሃቸው እነርሱ የግርግሪት አሰሩህ ። ካንተ በርባንን መረጡ ፣ አልጋ ስትሰጣቸው አመድ ላይ ተንከባለሉ ። የማይፈርድ ችሎት ፣ እውነትን የማይሻ ሸንጎ አቋቁመው ፣ ፍርድ ቤት አድርሰነዋል ለማለት አደባባይ አቆሙህ ። ስለመግደልህ ሳይሆን ስለመፈወስህ ሞት በየኑብህ ። አንተም አርፈህ አልቀመጥ ፣ ሲጠሉህ አልጠላችሁም ብለህ ይኸው ሰቀሉህ ! የሚደበድባትን ባል ያፈቅረኛል የምትል ሚስት ፣ የሚለመጥጠውን ንጉሥ ቆራጥ መሪ የሚል ሕዝብ ባለበት ዓለም በትዕግሥትህ ምክንያት ሰቀሉህ ። ገራፊ የለመደው ወገን የምትገረፍለትን አንተን መቀበል አቃተው ፣ ዛሬም አስመሳዮች ጌታን ተቀበልን እያሉ ራሳቸውን በመቀበል ፣ የተሰቀልከውን ሳይሆን ምቾታቸውን በማሳደድ ይሰቅሉሃል ። አንተም እንቢ አልክ ሁለት ሺህ ዓመት ልብ አልገዛም ብለህ በየጓዳው ፣ በየምርጫው ይሰቅሉሃል ። አይሁድ ስለሰቀሉህ የሚያለቅሱ ደጋግመው በክፋታቸው የሚሰቅሉህ ግብዞች ባሉበት ዓለም አንተ ተሰቀልህ ። ለሰቀሉህ ተሰቀልህላቸው ። ለገደሉህ ሞታቸውን ወሰድህላቸው ። የታመመ ቢታመሙለት አይድንም ። የሞተ ቢሞቱለት ቀና አይልም ። አንተ ግን በመገረፍህ ቍስል የምታድን ፣ በሞትህ ሕይወት የምትሰጥ ነህ ። ይገርማል ሥጋዬን ብሉ ስላልህ ላይበሉህ ሰቀሉህ ። አንተ ግን ሰቀሉኝ አላልህም ፣ ተሰቀልሁላቸው አልህ አንጂ ። ባንተ ምክንያት ከስንቱ ልጣላ ። ከዙፋን በረትን ፣ ከሰማይ አፈርን መርጠህ በመምጣትህ በር ዘጉብኝ አትበል ። ፍጥረተ ዓለሙን አንዱን በእንጀራ ፣ አንዱን በምስጋና እያጠገብህ የምትኖረው የብላቴናዋን የድንግልን ወተት የለመንከው እኮ ምን ቸግሮህ ነው ! ጠላት የሚፋንንብኝ ባልችል ፣ ድህነት የሚጎስመኝ ቢሳነኝ ነው ። አንተ ግን ወዶ ገብ ድሀ ለምን ሆንህ ! እኮ ከመውደድ አያርፍም ፣ በመጥላት ይራቀን ብለው ሰቀሉህ ። አንተ ግን ሞኝ ሆነህ ሳይሆን አፍቅረህ ፣ መላ አጥተህ ሳይሆን መለኛ ሆነህ ሰቀሉህ ! የባለጠጋው ልጅ ድህነትን ፈቅደህ ተቀበልከው ። ሰውን ለማዳን ሰው ልሁን ብለህ መጣህ ። ሰው ሳይሆኑ ሰውን ለማዳን የሚነሡ ብዙዎች አሉና ልታስተምራቸው ፣ ለሰው ከመሰቀል በፊት ሰው መሆን ይቀድማል ልትላቸው ሰው ሆነህ መጣህ ። የክፋት ብርድ ልብሳቸውን በትምህርት ገፈፍካቸውና ተው ስልህ ይኸው ሰቀሉህ ! የአብ ልጅ ፣ የድንግል ልጅ ያንተ ሞት ግሩም ነው ። በአንድ ዓይን እያስለቀሰ ፣ በአንድ ዓይን የሚያስቅ ነው ። በሚኖርበት ዕድሜ የሚሞቱት ቀዘባዎች ፣ መለሎዎች ፣ ሙናዎች በኀዘን ሰብረውን እንዳይኖሩ አንተ በሠላሳ ሦስት ዓመትህ ሰቀሉህ ። ከሞቱ ያሟሟቱ እያሉ በአደባባይ ለሚወድቁት የሚያለቅሱ አሉና አንተ በአደባባይ በመሰቀል ተጽናኑ አልህ ። ሟች ሁሉ ልብስ አይገፉትም ፣ ለመገነዣም አዲስ ልብስ ይሰፋለታል ። አንተን ግን ልብስህን ገፍፈው ሰቀሉህ ። እነርሱ እኮ ምን ያድርጉ ! ብቻቸውን በር ዘግተው የሚበሉ ናቸው ፤ አንተ አምስት ሺህ ሰው ትመግባለህ ። ሐኪም ቤቱን ልታራቁት በነጻ ትፈውሳለህ ። ባንተ ምክንያት ምግብ ቤቶች ፣ ሸክላ የሚያበሉ ጨካኝ ነጋዴዎች ገቢያቸው ቀነሰ ። አዎ ሰቀሉህ ! እንዲሰቅሉህ ስለፈቀድህላቸው ሰቀሉህ ። መስቀል የቻሉ ትንሣኤህን ማገድ አልቻሉም ። ዛሬም ድሀ እየበደሉ ፣ ፍርድ እያጓደሉ ፣ ለወንድም መርዝ እየበጠበጡ ይሰቅሉሃል ። አንተ ስለሁሉ በሞትህበት ዓለም ሁሉ አንድ ሰውን ተባብረው ይሰቅሉታል ፣ በድንጋይ ይወግሩታል ። የደቦ ፍርድ ይሰጡታል ። ኦ ምንድነው የምትፈልገው ከእኔ ፣ እስቲ ተወኝ ! እኮ ብያለሁ ዛሬም ሰቀሉህ !!! የእናትህ ዘመዶች ሰቀሉህ ። እኮ እርሷስ ላንተ ታልቅስ ወይስ ዘመድ ትቀየም ! ቅያሜው እንዲቀር በመስቀል ላይ ይቅር አልህ ! ልቅሶው እንዲሻር ከሞት ተነሣህ ። አንተ ብሩህ ኮከብ ፣ ላያጠፉህ የመቱህ አማኑኤል ሆይ ብቻህን አትነሣ ፣ እኛንም ይዘህ ተነሣ ! ማር ኢየሱስ ጣፋጭ ነህ ! ማር ኢየሱስ መሐሪ ነህ ! የአፍሪካ ቀንድ ላይ ተቀምጠን ጦርነት አላጣ ያለን ሕዝቦችህን የተሰቀልኸው እባክህ ሰላም ስጠን ! ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ሚያዝያ 25 ቀን 2016 ዓ.ም.
Show all...
ሰቀሉህ – Telegraph https://telegra.ph/ሰቀሉህ-05-03
Show all...
ሰቀሉህ

ሰቀሉህ !!! አንተስ ሁሉን ስታውቅልን ለራስህ አላውቅ ብለህ በዳይህን እንዴት ትፈጥራለህ ? እኛን የሚያዋድደን አለማወቅ ፣ አለመተዋወቅ ነው ። አንተ ብቻ አውቀህ ትወደናለህ ። ሰቀሉህ መልኬ ያልካቸው ፣ ዝቅ ብለህ ከአፈር ያነሣሃቸው ፣ ሬሳቸውን በአፍህ እስትንፋስ ሕያው ያደረግህላቸው ፣ ሚሊየን ጊዜ አድርገህላቸው አንድ ምስጋና የማያውቁ እነዚያ የአዳም ዘሮች ሰቀሉህ ። አንተ ለሁሉ እንደ ተሰቀልህ ፣ አንተን ሁሉ ሰቀለህ ። ከነጻነት ጋር የፈጠርሃቸው እነርሱ የግርግሪት አሰሩህ ። ካንተ በርባንን መረጡ ፣ አልጋ ስትሰጣቸው አመድ ላይ ተንከባለሉ ። የማይፈርድ ችሎት ፣ እውነትን የማይሻ ሸንጎ አቋቁመው ፣ ፍርድ ቤት አድርሰነዋል ለማለት አደባባይ አቆሙህ ። ስለመግደልህ ሳይሆን ስለመፈወስህ ሞት በየኑብህ ። አንተም አርፈህ አልቀመጥ ፣ ሲጠሉህ አልጠላችሁም ብለህ ይኸው ሰቀሉህ ! የሚደበድባትን ባል…

የዕለቱን ወንጌል እናንብብ! ሚያዝያ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ቀን 9:00 የሚነበብ የማቴዎስ ወንጌል ም 27 ፥ 46 - 50 የማርቆስ ወንጌል ም 15 ፥ 34 - 35 የሉቃስ ወንጌል ም 23 ፥ 45 - 46 የዮሐንስ ወንጌል ም 19 ፥ 28 - 30 መልካም ዕለተ አርብ ! #ethiopianorthodoxtewahedochurch #የዕለቱ_ወንጌል #tewahedomediacenter #friday
Show all...
የዕለቱን ወንጌል እናንብብ! ሚያዝያ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ቀን 6:00 የሚነበብ የማቴዎስ ወንጌል ም 27 ፥ 27 - 45 የማርቆስ ወንጌል ም 15 ፥ 16 - 33 የሉቃስ ወንጌል ም 23 ፥ 27 - 44 የዮሐንስ ወንጌል ም 19 ፥ 13 - 27 መልካም ዕለተ አርብ ! #ethiopianorthodoxtewahedochurch #የዕለቱ_ወንጌል #tewahedomediacenter #friday
Show all...
ሉቃስ 23 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁹ ከተሰቀሉት ከክፉ አድራጊዎቹም አንዱ፦ አንተስ ክርስቶስ አይደለህምን? ራስህንም እኛንም አድን ብሎ ሰደበው። ⁴⁰ ሁለተኛው ግን መልሶ፦ አንተ እንደዚህ ባለ ፍርድ ሳለህ እግዚአብሔርን ከቶ አትፈራውምን? ⁴¹ ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው፤ ይህ ግን ምንም ክፋት አላደረገም ብሎ ገሠጸው። ⁴² #ኢየሱስንም፦ ጌታ ሆይ፥ #በመንግሥትህ_በመጣህ_ጊዜ_አስበኝ አለው። ⁴³ #ኢየሱስም፦ እውነት እልሃለሁ፥ #ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው።
Show all...