cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን /አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ። 📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼ ❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

Show more
Advertising posts
22 805
Subscribers
+224 hours
-437 days
-29430 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
"የሰንበትን ቀን ትቀድሰዉ ዘንድ አስብ "!! (ዘፀአት፣20;:8)📚 መልካም እለት ሰንበት ይሁንልን። ከሰንበት ቀን ረድኤት በረከት ይክፈለን አሜን🙏⛪
3625Loading...
02
*©ያከብርዋ ለሰንበት* ጥራዝ 1.ቁ. 41 ያከብርዋ ለሰንበት መላእክት በሰማያት ጻድቃን በውሰተ ገነት/፪/ ወኲሉ ፍጥረት አሣት ወአናብርት እለ ውሰተ ደይን ያዕረፉ ባቲ እስመ ባቲ አዕረፈ እምኲሉ ግብሩ/፪/ ያከብሯታል ሰንበትን መላእክት በሰማያት ጻድቃን በገነት/፪/ ፍጥረታት በሙሉ አሳዎች እና አንበሪዎች በመቃብር ያሉ ያከብሯታል አምላክ በእርሷ እንዳረፈ ከሥራ ኹሉ/፪/
6029Loading...
03
"እግዚአብሔርን "ለምን ትረሳኛለህ?" አትበለው "ጌታ ሆይ የረሳሁህን እኔን ይቅርበለኝ፤ ፍቅርህን ዘንግቻለሁና በመከራዬ ጊዜም አስበኝ" በለው እንጂ።"አቡነ_ሽኖዳ_ሳልሳዊ 🥀መልካም እለተ ሰንበት❤️💒
86011Loading...
04
"ትህትናን ውደዷት ኃጢአታችሁን የምትሸፍን ናትና፡፡ ሁሉም ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ቢሆንም ከኃጢአቶች ሁሉ መጥፎ የሆነው ግን የልብ ትዕቢት ነው:: ራሳችሁን አዋቂ አድርጋችሁ ከፍ ከፍ አታድርጉ፡፡ ይህን ምታድረጉ ከሆነ ጥረታችሁ ሁሉ ፍሬ አልባ ይሆናል፡፡" 🌿አባ_እንጦንስ።🌿 🥀እንደምን አደራችሁ መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን🤲☦💒
9317Loading...
05
🌷መልክአ ጸበለ ማርያም📗 ቅድስት ጸበለ ማርያም ሆይ እረፍት ወዳለበት ገነት ወንድም እህቶችሽ እንገባ ዘንድ እኅት ሆይ አማልጅን አሜን🤲 https://t.me/Orthodoxtewahdoc
8672Loading...
06
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33☦📚          ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ 📗ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት ፲፰/18 https://t.me/Orthodoxtewahdoc 🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊
9413Loading...
07
Media files
8210Loading...
08
ግዜህን በቁጣ ፣በቁጭት ፣ በመጨነቅ እና ቅር በመሰኘት አታሳልፍ ። ህይወት ደስተኛ ላለመሆን በጣም አጭር ናት ❗ 🥀ሰናይ ሌሊት☦🤲
1 0842Loading...
09
⛪️👀 ከሐዘን፡የተነሣ፡ነፍሴ፡አንቀላፋች፤በቃልኽ፡አጠንክረኝ። የዐመፅን፡መንገድ፡ከእኔ፡አርቅ፥በሕግኽም፡ማረኝ፤ የእውነትኽን፡መንገድ፡መረጥኹ፥ፍርድኽንም፡አልረሳኹም። አቤቱ፥ምስክርኽን፡ተጠጋኹ፤አታሳፍረኝ። ልቤን፡ባሰፋኸው፡ጊዜ፥በትእዛዝኽ፡መንገድ፡ሮጥኹ። ሄ አቤቱ፥የሥርዐትኽን፡መንገድ፡አስተምረኝ፥ዅልጊዜም፡እፈልገዋለኹ። እንዳስተውል፡አድርገኝ፥ሕግኽንም፡እፈልጋለኹ፤በፍጹም፡ልቤም፡እጠብቀዋለኹ። ርሷን፡ወድጃለኹና፡የትእዛዝኽን፡መንገድ፡ምራኝ። ልቤን፡ወደ፡ምስክርኽ፡አዘንብል፥ወደ፡ሥሥትም፡አይኹን።ከንቱ፡ነገርን፡እንዳያዩ፡ዐይኖቼን፡መልስ፤በመንገድኽ፡ሕያው፡አድርገኝ። አሜን:አሜን:አሜን
1 2274Loading...
10
ነገ ግንቦት 18 ፃድቁ አባታችን አቡነ ሰላም ከሳቴ ብርሃን ናቸው። ቅዱሱ ለሃገራችን ዻዻስ ሆነው የተሾሙት በዚህች ዕለት ነው: በረከታቸው ይደርብን🤲
1 2809Loading...
11
ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን የወጠነልን እና አያሌ ቤተክርስቲያን ያሰተከለልን ነውና ዘወትር ልናስበው በዓሉን ልናከብርለት ይገባናል፡፡        🌿❤️ ይህ ቅዱስ ኣባት አፅሙ ያረፈበት ገዳሙ የሚገኝው ትግራይ ውስጥ በተንቤን እንዳ ኣባ ሰላማ ሲሆን እንዲሁም ኤርትራ ዛግር እና በኣንዳንድ ቦታዎች ካልሆነ በቀር በአብዛኛው የሃገራችን ክፍል ክብረ በዓሉ እምብዛም ትኩር አይሰጠውም፡፡           🌿❤️ በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው 《ምሳ.10፡6》 ተብሎ እንደተጻፈው ጻድቁ አባታችን ማር ኅሩይ አቡነ ሰላማ ሙታንን አስነስቷል 《የጥርና የሰኔ ገድል》፣ ጸሐይን ከተፈጥሮ ህግ ውጪ አቁሟል 《የነሐሴ ገድል》የአባይን ወንዝ ከፍሎ ተሻግሯል 《የመስከረም ገድል》፣ በዚህ ዓይነት የተጋድሎ ሂደት ለ150 ዓመታት መልካም ገድልን ተጋድሏል፡፡             🌿❤️ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር የገባለት ቃል ኪዳን ስምህን የጠራ ዝክርህን የዘከረ ገድልህን ያነበበ ሲነበብ የሰማ ቤተክርስቲያንህ የሰራ ዘቢብ እጣን ጠዋፍ ሻማ ለቤተክርስቲያንህ የሰጠ ልጁን ብስምህ የሰየመ አምኖ ሳይጠራጠር ጸበልህን የተጠመቀ እርኩሳን መናፍስት አይቀርቡትም አስራ አምስት ትውልድም እምርልሃለሁ የሚል ቃል ኪዳን ተቀብሏል፡፡           🌿❤️ ይህንን ታሳቢ በማድረግና በእግዚአብሔር ቸርነት በተሰጠው ልዩ ቃልኪዳን መሰረት በ21ኛው ክ/ዘመን በስሙ የሚደረጉ ተአምራቶች እንደቀጠሉ ናቸው፡፡            🌿❤️ የዚህ በቸርነቱ ተጠቃሚዎች እንድንሆን አባ ሰላማ በቃል ኪዳኑ እግዚአብሔር በቸርነቱ ይርዳን። ወስብሓት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር
1 1884Loading...
12
እግዚአብሔር ታላቅ ነው። "ስራውም ግሩም ነው": ♥ #አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን♥ ወር በገባ በ18 ፃድቁ #አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ናቸው የጻድቁ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁንና ታላቁ፣ ስመጥሩ አባታችን ጻድቁ አቡነ ሰላማ በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ከአባቱ ከቅዱስ ምናጦስና ከቅድስት እናቱ ማርያም ሰናይት በጢሮስ /ግሪክ/ ተወለደ፡፡         እድሜው ለትምህርት እንደደረሰ በአካባቢው በነበረው ትምህርት ቤት ውስጥ ሃይማኖታዊ ትምህርቱን በሚገባ ተከታትሎ የተማረ በመልካም ሥነ-ምግባርና አስተዳደግ ተኮትኩቶ ያደገ ደግ አባት ነበር፡፡         ሜሮጵዮስ የተባለ ነጋዴ 《ፈላስፋ》ወደ ህንድ አገር ሊያልፍ ወዶ ከጢሮስ አገር በጀልባ ጉዞ ጀመረ፡፡  ከእርሱም ጋር ከዘመዶቹ ወገን የሆኑ ሁለት ብላቴኖች ነበሩ፡፡  የአንደኛው ስሙ ፍሬምናጦስ፣ የሁለተኛው ደግሞ ኤዴስዮስ 《ሲድራኮስ》ይባላል፡፡          🌿❤️ ሜሮጵዮስ እነዚህን ሁለት ወጣቶች አስከትሎ ወደ አፍሪካ ባህር ጠረፍ በመምጣት በቀይ ባህር ወደብ ውሃ ለመጠጣት እግረ መንገዱንም አገር ለማየት ጀልባውን ጠረፍ ላይ አቆመ፡፡          🌿❤️ በዚህ ጊዜ በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች 《የአዱሊስ ነዋሪዎች》 በጀልባዋ ላይ አደጋ በመጣል ሜሮጵያስንና የጀልባዋን ቀዛሪዎች እዚያው ገድለው ሀብታቸውን ዘረፏቸው፡፡  ሁለቱ ወጣቶች ግን ተረፉ፡፡  በማያውቁትም አገር ያለ ዘመድ፣ ያለ ሃብት ብቻቸውን በመቅረታቸው እያዘኑና እያለቀሱ ከዛፍ ሥር ተቀምጠው ሲጸልዩ የአካባቢው ነዋሪዎች ያዟቸውና በጊዜው በአክሱም ነግሶ ለነበረው ለንጉሥ ታዜር በፈረስ አንገት በጦር አንደበት የተማረኩ ሰዎች አመጣንልህ በማለት አስረከቡት፡፡  ንጉሥ ታዜርም በቤተመንግስቱ ውስጥ እንዲያድጉ ፈቀደላቸው፡፡           🌿❤️ ከጊዜ ወደ ጊዜ በቤተመንግስቱ ውስጥ ተወዳጅነትንና ታማኝነትን አገኙ፡፡  የአብርሃ እና አጽብሃ አባት የነበረው ንጉሥ ታዜር ኤዴስዮስን ጋሻ ጃግሬ፣ ፍሬምናጦስን በጅሮንድ አድርጎ ሾማቸው፡፡  ንጉሱ ሊሞት በተቃረበበት ጊዜ ልጆቹ ገና አካለ መጠን አልደረሱም ነበርና መንግስቱን በሞግዚትነት እንድትይዝ ለእቴጌይቱ አደራ ሲል ሁለቱን ሶርያውያን ምርኮኞች ግን ነጻ /ሑር/ ለቀቃቸው፡፡  ነገር ግን በእቴጌይቱ ልመና ወደ አገራቸው መመለሳቸው ቀርቶ ልጆቿ እስኪያድጉ ድረስ በአስተዳደር በኩል ሲረዷትና ሲመክሯት ቆዩ፡፡            🌿❤️ ፍሬምናጦስ በአክሱም በነበረበት ጊዜ የቤተመንግስቱ አማካሪ ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲል የኦሪት እምነት በአንድ እግዚአብሄር ማመን እንደነበረ የሚታወቅ ሆኖ የተዋህዶ እምነት ጥምቀትና ክህነትን በሚገባ  የሚመሰረትበትና የሚሰፋበት መንገድ ይፈልግ ነበር፡፡            🌿❤️ ያን ጊዜ የነበሩት የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ሐይማኖት ብቻ እንጂ ክህነት፣ ቁርባንና የመሳሰሉት የክርስትና ስርዓቶች አልነበራቸውም፡፡  ልዑላኑ 《አብርሃና አጽብሐ》 አካለ መጠን ደርሰው የአባታቸውን መንግስት ሲረከቡ ኤዴስዮስ ወደ አገሩ ተመልሶ ካህን ሆነ፡፡            🌿❤️ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሦስት ጊዜ በላይ ግብጺ እስክንድሪያ ሄዶ ጵጵስና አምጥቶ በኢትዮጵያና በኤርትራ ሃዋርያ ሆኖ እንዲያስተምር እንዲያጠምቅ በእግዚአብሄር መልእክት ተነገረው፡፡ በዚህ መሰረት  ስለአየው ነገር ለነገስታቱ አስረዳቸው ከዚህ በኋላ ጵጵስና እንዲያመጣ መልካም ፍቃዳቸው ስለሆነ ወደ እስክንድርያ ሄደ፡፡             🌿❤️ ፍሬምናጦስ እስክንድርያ የደረሰው እለ እስክንድሮስ አትናቴዎስን አስከትሎ ለጉባኤ ኒቅያ በወጣበት ጊዜ ነበርና እስኪመለሱ ድረስ ትምህርተ ቤተክርስቲያንን እየተማረ በትዕግስት መጠበቅ ግድ ሆነበት፡፡ እለ እስክንድሮስ በጉባኤ ኒቅያ በአትናቴዎስ አፈ ጉባኤነት አርዮስን ረትቶ ከተመለሰ በኋላ ወዲያው ስላረፈ በመንበሩ አትናቴዎስ ተተካ፡፡           🌿❤️ ፍሬምናጦስም የሄደበትን አብይ ጉዳይ ለቅዱስ አትናቴዎስ አቀረበ፡፡  አትናቴዎስም ስለ ኢትዮጵያውያን ሐይማኖት በሚገባ ከተረዳ በኋላ ለፍሬምናጦስ ስርዓተ ቤተክርስቲያንን አስተምሮ ኤጲስ ቆጶስ ዘአክሱም ወዘኩላ ኢትዮጵያ ብሎ በአንብሮተ ዕድ ተሾመ፡፡  በሹመቱም ወቅት ሰላማ የሚል ስም እንዲወጣለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ለኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስ አባ ቄርሎስ በራእይ ተገልጾ ነግሮታል፡፡        🌿❤️ ሰላማ ማለት፡ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ሆኖ የሚያስታርቅ ማለት ነው፡፡  በዘመነ ረሃብ ጥጋብ፣ በዘመነ ጦርነት ሰላም የሚሰጥ ማለት ነው፡፡         🌿❤️ ብርሃነ ወንጌሉን ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን ስላበሰረ፤ በብርሃነ ትምህርቱ የተደሰቱ በጨለማው ውስጥ ኖረው በእርሱ አማካኝነት ወንጌሉ የበራላቸው ምዕመናን ከሳቴ ብርሃን በማለት ሰይመውታል፡፡           🌿❤️ ቅዱስ ያሬድም ዝንቱ ብእሲ መምህርነ ዘተፈነወ ውስተ ምድር ይከስት ብርሃነ ማለትም ብርሃንን ይገልጥልን ዘንድ ወደ አገራችን የተላከ ይህ ሰው መምህራችን ነው ብሎታል፡፡  《መጽ.ድጓ》           🌿❤️ ሰአል ለነ ሰላማ አቡነ ወመምህርነ እለ ፅልመት ነበርነ ከሰትከ ለነ ብርሃነ ዜናሁ ለመድሃኒነ፤ አባታችንና መምህራችን አቡነ ሰላማ በጨለማ የነበርን ለኛ የክርስቶስ ብርሃነ ወንጌል አበራህልን፡፡ 《አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታት》 🌿❤️   አባታችን ከተሾመ በኋላ 🌿❤️                        🌿❤️ ወንጌልን በስፋት ለህዝቡ የሚያደርሱ፣ የሚያጠምቁና የሚያቆርቡ ካህናትና ዲያቆናትን ሾመ፤ በአብርሃ ወአጽብሐ አማካኝነት ብዙ አብያተ-ክርስቲያናትን አሳነጸ፤          🌿❤️ በዘመኑ የኢትዮጵያ ግዛት ወደ ነበሩበት ኑብያ፣ አኑኖ እና መርዌ 5 ቆሞሳትን በመላክ ትምህርተ ወንጌል እንዲሰበክ እና ቤተክርስቲያን እንድትስፋፋ አድርጓል፤          🌿❤️ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሱርስት፣ ከእብራይስጥና ከግሪክ ወደ ግዕዝ ቋንቋ እንዲተረጎሙ አድርጓል፤             🌿❤️ የሳባውያንን የፊደል አቀማመጥ በመለወጥና ከግራ ወደ ቀኝ የመጻፍንና የማንበብን ዘዴ አስተምሯል፤          🌿❤️ በ350 ዓ.ም ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሐይማኖት ሆኖ እንዲታወጅ አድርጓል፤ ↔በአጠቃላይ መሰረቷ ያልተናወጸ ቤተክርስቲያንን በስብከቱ የመሰረተ፤ ↔ቅድስናው በጥንት አብያተ ክርስቲያናት የተመሰከረለት፤ ↔የወንጌልን ብርሃን በመላው ኢትዮጵያና ኤርትራ ዞሮ ያበራ፤ ↔በክርስቶስ መስቀል የተገኘውን ሰላም ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን ያስተዋወቀ፤ ↔ሐዋርያዊ ግዴታውን በሚገባ የተወጣ፤ ↔በኢየሩሳሌም ላለው ርስታችን በነበረበት ዘመን መፍትሔ ያሰጠ፤ ↔የአርዮስን ትምህርት በመጣበት ቦታ የመለሰ፤ ↔መንበሩን በዓለም አቀፍ እውቅና ያካተተ፤ ↔ለአገሪቱ ጭምር የሥነ ፊደል ሥርዓት የዘረጋ፤ ↔አገራችን በራሷ ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስን እንድታገኝ የተረጎመ፤ ↔ፍጹም ሐዋርያዊ ሕይወት የነበረው ታላቅና ቅዱስ የቤተክርስቲያናችን አባት ነበር፡፡🌿❤️ ኣቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን የተባለው ፍሬምናጦስ በኢትዮጵያና በኤርትራ ክርስትና ሓይማኖት እንዲስፋፋ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በመውጣትና በመውረድ የሚገባውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ ሐምሌ 26 ቀን ወደ ዘላለማዊ ክብሩ ተሸጋግሮዋል፡፡           🌿❤️ ይህ ታላቅ አባት የኢትዮጵያውያንና የኤርትራውያን ባለ ውለታ የወንጌልን ፋና ይበልጥ እንዲበራ ያደረገ፡፡ መንበረ ጵጵስና ያስገኘልን ስርዓተ ቤተክርስቲያን
8906Loading...
13
Media files
8155Loading...
14
🌹#ቅድስት_ፀበለ_ማርያም_ማለት⁉🌹 📘♨☞ወር በገባ በ18 ከሚታሰቡት መካከል ክብሯ ቅድስት ፀበለ ማርያም ይቺውም በፀሎቷ ብዛት በወገቧ በታጠቀችው ሰንሰለት በስግደቷም ስጋዋ ከአካሏ ተቆራርጦ እስኪወድቅ ድረስ የጌታዋን መከራ እያሰበች ትሰግድ ነበር ☞ማንም ከቶ እንዳያውቅባት ከአካሏ የወደቀውን ስጋዋን መሬት ቆፍራ ትቀብረው ነበር በዚህም የተነሳ የገዳሟ መሬት ሁለተኛ አካሏ ሆነ ከእንባዋም ብዛት የተነሳ ዝናብ የጣለ መሬት ይመስል መሬቱ በእንባዋ ይረሰርስ ነበር እርሷ ግን ሰው እንዳያውቅባት በደረቅ አፈር ትለውሰው ነበር። ♨የዓለም መዳኒት ኢየሱስ ክርስቶስ በደሀ ሰው ተመስሎ ምግብ ለመናት እርሷም ጌታዋን መገበችው ደክሞኛል እዘይኝ ባላት ጊዜ እርሷ አዛኝ ናትና በጀርባዋ አዝላ የዲንጋይ መወርወሪያ ያህል ተሸክማ ወሰደችው በዚህ ክብርት የምትሆን እናታችን ፀበለ ማርያም ስለንፅህናዋ ፀበል አፈለቀላት እመቤታችንም ከሰማይ ወርዳ ስሜን የተሸከምሽ ፀበለ ማርያም ሆይ ነይ ብላ አቅፋ ሳመቻት። ☞የክርስቲያን ወገኖች ስሙኝ የገዳሟን አፈር የወሰደ የስጋዋን ቁራሽ ለመዳኒትነት እንደወሰደ ይወቅ ይረዳ የእምነት አፈሩ ክርስቶስን ተሸክሟልና የእንባዋን ፀበል የወሰደ ፍፁም ፈውስ ያገኛልና ከቶ እናቴ ፀበለ ማርያም እያላችው ተማፀኗት። ☞ገና ዓለም ሁሉ ገዳሟ እንደሚጎርፉ ዝናዋ የዓለም ጫፍ እንደሚደርስ የማታ የማታ የከተማ ልጆች ቤቴን ይሰሩታል የተባለው ትንቢት መድረሱን የገዳሙ አባቶች ይናገራሉ። የገዳሟ አድራሻ ፦ በደቡብ ወሎ ጃማ ዳጎሎ አህያ ፈጂ የሚባል ቦታ ልዩ ስሙ ንህበት የሚባል ቦታ ነው ። ☞የጻድቋ እናታችን የጸበለ ማርያም የጸሎቷ በረከት አይለየን፡፡ ☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ https://t.me/Orthodoxtewahdoc ጆይን እያላችሁ ግቡ
7312Loading...
15
Media files
6893Loading...
16
🌹#ወር በገባ በ18 #ቅዱሳት ደናግል #አጥራስስና_ዮና ማለት⁉🙏 ♨❖ አጥራስስ ግን ጣዖታትን ለሚያመልክ ንጉሥ እንድርያኖስ ልጁ ናት እርሱም ከሰው ወገን ማንም እንዳያያት አዳራሽ ሠርቶ ለብቻዋ አኖራት እርሷ ግን ስለዚህ ዓለም ኃላፊነት የምታስብ ሆነች አውነተኛውንና የቀናውን መንገድ ይመራት ዘንድ በቀንና በሌሊት እግዚአብሔርን ትለምነው ነበር። ❖ ወደ ፍላጽፍሮን ልጅ ወደ ድንግሊቱ ዮና ላኪ እርሷም የእግዚአብሔርን መንገድ ትመራሻለች የሚላትን ራእይ አየች ከእንቅልፏም ስትነቃ በልቧ ደስ አላት ወደ ዮና ድንግልም ላከች እርሷም ፈጥና መጣች ለዮናም ሰላምታ ሰጠቻትና ከእግርዋ በታች ሰገደችላት የእግዚአብሔርንም ሃይማኖት ታሰተምራትና ትገልጥላት ዘንድ ለመነቻት። ❖:ድንግል ዮናም የእግዚአብሔር ልጅ ሰው የሆነበትን ምክንያት እግዚአብሔር አዳምን ከፈጠረበት ጊዜ በመጀመር ልትነግራት ጀመረች አዳም እንደበደለና ከተድላ ገነት እንደ ወጣ በኖኅም ዘመን የጥፋት ውኃ መጥቶ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንደደመሰሰ የእግዚአብሔርን ሕግ የጠበቁ ስምነት ሰዎች ብቻ እንደ ቀሩ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ ሰዎች በምድር ላይ በበዙ ጊዜ እንደበደሉና ጣዖትን እንዳመለኩ እግዚአብሔርም ለአብርሃም እንደተገለጠለትና መርጦ ወዳጅ እንዳደረገው ከእርሱም ጋር ቃል ኪዳንን እንዳጸና እስራኤልንም ከግብጽ አገር እንዳወጣቸው የሰውንም ወገን ጠላት ሰይጣንን ከማምለክ ለእርሱም ከመገዛት ያድነው ዘንድ የእግዚአብሔር ልጅ መምጣቱንና ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው መሆኑን ነቢያት እንደሰበኩ ነገረቻት። ❖ ሁለተኛም ስለ ከበረ ስሙ መከራ በመቀበል ለሚደክሙ ሰማያዊ ሀብት የዘላለም መንግሥትን እግዚአብሔር ስለ ሚሰጣቸው አስረዳቻት። ❖ አጥራስስም የዮናን ትምህርቷን ሰምታ እጅግ ደስ አላት በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አመነች። ❖ እሊህ ደናግልም ሌሊትና ቀን በተጋድሎ ተጠምደው በአንድነት ተቀመጡ የአጥራስስም አባቷ ይህን አያውቅም ከሌሊቶችም በአንዲቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አዩት እናቱን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንም አዩአት፤ እመቤታችንም ወደ ልጅዋ እግዚአብሔር እንደ ቁርባን አቀረበቻቸውና እርሱም ባረካቸው። ❖ ከዚህም በኋላ ንጉሥ ወደ ጦርነት ሒዶ በተመለሰ ጊዜ ወደ ልጁ አጥራስስ ገብቶ ልጄ ሆይ ወደ መሞሸሪያሽ ከመግባትሽ በፊት ለአምላክ አጵሎን ዕጣን ታሳርጊ ዘንድ ነዪ አላት። ❖ አጥራስስ ድንግልም አባቴ ሆይ ነፍስህና ሥጋህ በእጁ ውስጥ የሆነ የፈጠረህን በሰማይ ያለ አምላክን ትተህ ነፍስ የሌላቸው የረከሱ ጣዖታትን ለምን ታመልካለህ ብላ መለሰችለት። ❖ ንጉሥም እንዲህ ያለ ነገር ከቶ ያልሰማውን ከልጁ አፍ በሰማ ጊዜ አደነቀ በልጁ ላይ ምን እንደደረሰ ልቧንም ማን እንደለወጠው ጠየቀ የፍላጽፍሮን ልጅ ድንግል ዮና የልጁን ልብ እንደ ለወጠች ነገሩት። ❖ ንጉሡም በእሳት ያቃጥሏቸው ዘንድ አዘዘ በወርቅና በብር በተጌጠ የግምጃ ልብሶችን እንደ ተሸለሙ አወጧቸው እነርሱ የነገሥታት ልጆች ስለሆኑ አላራቆቿቸውም ታላላቆችና ታናናሾች ሁሉም ሰዎች ስለ እሳቸው እያዘኑና እያለቀሱ ወጡ ነፍሳቸውንም እንዳያጠፉ ለንገሥ ይታዘዙ ዘንድ ለመኗቸው እነርሱ ግን ከበጎ ምክራቸው አልተመለሱም። ❖ በዚያንም ጊዜ ጉድጓድ ቆፈሩላቸውና በውስጡ እሳትን አነደዱ ነበልባሉም እጅግ ከፍ ከፍ አለ ያን ጊዜ አንዷ ከሁለተኛዋ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው ወደ እሳት ውስጥ ተወረወሩ ፊታቸውንም ወደ ምሥራቅ መልሰው በመቆም ረጅም ጸሎትን ጸለዩ ከዚህም በኋላ ነፍሳቸውን በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ እሳቱም እንደውኃ የቀዘቀዘ ሆነ ምእመናንም ሥጋቸውን አነሡ ተጠጋግተውም ልብሳቸውንም ቢሆን ወይም የራሳቸውን ጠጉር እሳት ምንም ምን ሳይነካቸው አገኟቸው። ❖ የመከራውም ወራት እስቲፈጸም በታላቅ ክብር በአማረ ቦታ አኖርዋቸው ከዚህም በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውላቸው ሥጋቸውን በውስጥዋ አኖሩ ከእርሳቸውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ በቅዱሳት ደናግል ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                   አርኬ ✍️ሰላም ለዮና መጽሐፈ ክርስቶስ መጽሐፋ። ወለአጥራስስ ሱታፋ። በእንተ ሃይማኖት ርትዕት ወበእንተ ጽኑሕ ተስፋ። ሶበ ተወርዋ አሐቲ እደ ካልዕታ ሐቂፋ። ማዕከለ እሳት ኅቡረ አዕረፋ።
7471Loading...
17
Media files
6213Loading...
18
🌹ወር በገባ በ18 የቅዱስ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ነው📌     #ቅዱስ_አቡነ_ኤዎስጣቴዎስ_ማለት⁉🙇 ❖ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ክርስቶስ ሞዓ የእናቱ ስም ስነ ሕይወት ይባላል ሁለቱም ደጋጎች እግዙአብሔርን የሚፈሩና በሕጉ ጸንተው የሚኖሩ ነበሩ። ❖ከዘህም በኋላ በከበረ መልአክ በቅዱስ ገብርኤል አብሣሪነት ይህን ቅዱስ ወለዱት ስሙን የጌታ ጥብቅ ብለው ሰየሙት፤ በአደገም ጊዜ የዳዊትን መዝሙርና የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍትን አስተማሩት። ❖ ከዚህም በኋላ የእናቱ ወንድም አባ ዘካርያስ ወደአለበት የመነኰሳት ገዳም ወሰዱት። አባ ዘካርያስም የእግዚአብሔርን ጸጋ እንዳደረችበት አውቆ የምንኩስናን ሥርዓት አስተምሮ የመላእክትን አስኬማ አለበሰው። ❖ ከገድሉ ጽናት የተነሣ በገዳም ያሉ አረጋውያን እስኪያደንቁ ድረስ በጾም በጸሎት የተጠመደ ሆነ እርሱ በጥበብና በዕውቀት የጸና ነውና፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላም ዲቁና ተሾመ የዲያቆናት አለቃ እንደሆነ እስጢፋኖስም ለቤተ ክርስቲያን አገለገለ። ❖ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሚካኤልና ከገብርኤል ጋር ተገለጠለትና ሰላምታ ሰጠው በንፍሐትም መንፈስ ቅዱስን አሳደበረት እንዲህም አለው ወዳጄ ኤዎስጣቴዎስ ሆይ እኔ ከእናትህ ማሕፀን መረጥኩህ ያለ ፍርሀትና ድንጋፄ ወንጌልን ለብዙዎች ሕዝቦች ትሰብክ ዘንድ ከኢትዮጵያ እስከ አርማንያ ድረስ መምህር አደረግሁህ አንተን የሰማ እኔን ሰማ አንተን ያልሰማ እኔን አልሰማም ጌታችንም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ በክብር ዐረገ። ❖ ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስም ወደ ጳጳስ ሒዶ ቅስና ተሾመ የወንጌልንም ሃይማኖት ይሰብክ ዘንድ ጀመረ ብዙ ሰዎች ወደ ርሱ እስቲሰበሰቡ ድረስ በእርሱም እጅ መንኩሰው ደቀ መዛሙርትን ሆኑት ከእርሳቸውም ታላቁ አባ አብሳዲ ነው። ❖ ብዙዎችንም የከፋች ሥራቸውን አስትቶ ከክህደታቸው መለሳቸው ትምህርቱም በሀገሩ ሁሉ ደረሰ በመላ ዘመኑም የሰንበታትና የበዓላት አከባበር የጸና ሁኖ ተሠራ ከሐዋርያትም ሕግና ሥርዓት ወደቀኝም ሆነ ወደ ግራ ሁሉም ፈቀቅ አላሉም ። ❖ ወደ ኢየሩሳሌምም ሁለት ጊዜ ሔደ እግዚአብሔርም በእጆቹ የዕውራንን ዐይኖች በማብራት አንካሶችንና ጎባጦችን በማቅናት አጋንንትን በማስወጣት ቁጥር የሌላቸው ተአምራትን አደረገ። ❖ ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ፈቃድ ለመሔድ በአሰበ ጊዜ ልጆቹን ሰብስቦ የመነኰሳትን ሥርዓት ይጠብቁ ዘንድ ከመናፍቃንም ጋር እንዳይቀላቀሉ አማፀናቸው። ❖ ልጁ አብሳዲንም በእነርሱ ላይ ሾመውና ወደ ኢየሩሳሌም ሰንበትን እያከበረና የክርስቶስን ሃይማኖት እያስተማረ ሔደ፤ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚንም ደርሶ ከእርሱ ቡራኬ ተቀበለ የሃይማኖትንም ነገር ተነጋገሩ ዳግመኛም ከከበሩ ቦታዎች በመሳለም በረከትን ተቀበለ በዮርዳኖስም ተጠመቀ። ❖"ከዚያም ወደ አርማንያ ሔደ ወደ ኢያሪኮ ባሕርም ሲደርስ በመርከባቸው ያሳፍሩት ዘንድ መርከበኞችን ለመናቸው በከለከሉትም ጊዜ ዓጽፉን በባሕሩ ላይ ዘረጋ በቅድስት ሥላሴ ስም በላዩ ባረከ ራሱንም በመስቀል ምልክት አማተበ እንደ መርከብም ሁኖለት በላዩ ተጫነ ሁለት መላእክትም ቀዛፊዎች ጌታችንም እንደ ሊቀ ሐመር ሆኑለት። ❖ ከባሕሩም ግርማ የተነሣ እንዳይፈሩ ልጆቹን አጽናናቸው፤ ግን እንዲህ አላቸው ልጆቼ በልባችሁ ቂምንና ሽንገላን እንዳታኖሩ ተጠበቁ ለኔ ግን ከእናንተ አንዱ አንደ ሚጠፋ ይመስለኛል ይህን ሲናገር ልቡ የቂም የበቀል ማከማቻ ስለሆነ ወዲያውኑ አንዱ ከእነርሱ መካከል ሠጠመ። ❖ በእግዚአብሔርም ፈቃድ ባሕሩን ተሻግሮ ወደ አርማንያ ከተማ ደርሶ ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋር ተገናኘ ሰገደለትም ከእርሱም ቡራኬን ተቀበለ ሊቀ ጳጳሱም በአየው ጊዜ ታላቅ ደስታን ደስ አለው በፍቅርም ተቀበለው። ❖ አባታችን ኤዎስጣቴዎስም ሁሉም በትመህርቱ አንድ እስከሆኑ ድረስ የአርማንያን ሰዎች ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው የሠሩትን ሥርዓት እያስተማራቸው ኖረ። ❖ ከዚህም በኋላ ዕረፍቱ ሲደርስ ክብር ይግባውና ጌታችን ተገለጠለትና ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ገድሉንም ለሚጽፍ ቃል ኪዳንን ሰጠው፤ በአረፈም ጊዜ ጳጳሳትና ካህናት በታላቅ ክብር ገንዘው በሰማዕቱ በቅዱስ መርምህናም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቀበሩት። ከሥጋውም ብዙ ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                                     አርኬ ✍️ሰላም ዕብል ለዘረከብከ ሞገሰ ምስለ ፈጣሪ ትትናገር ሱባዔያተ ሠላሰ። ኤዎስጣቴዎስ ዘሦጥከ ዲበ በድነ ሕፃን ነፍሰ። ጊዜ ዐደውከ ማዕበላተ ዘአልቦ አርማሰ። በዘባነ ባሕር እንዘ ትሰፍሕ ልብሰ። (https://t.me/Orthodoxtewahdoc ጆይን እያላችሁ ግቡ
5983Loading...
19
Media files
5533Loading...
20
🕊መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስኅ ግቡ🕊 (ማቴ ፫:፫) ✨በአማን ተንሥአ መድኃኒነ!✨ 🌿ብፁዕ አባ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘኤለ ገዳማተ እምኀበ እግዚኡ ይነሣእ እሴተ ቦአ ሀገረ ደብረ ሊባኖስ በፍሥሐ ወበሰላም። ⚜ሰአል ለነ ጊዮርጊስ ኀበ እግዚአብሔር ወጸሊ በእንቲአነ ሐረድዎ ወገመድዎ ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ሐመድ ወወሰድዎ ኀበ ሰብአ ነገሥት ረገጸ ምድረ አንሥአ ሙታነ አባ ጊዮርጊስ በሰላም ዐደወ መንግሥተ ክብር ወረሰ። 🌿ወልደ እግዚአብሔር አምላክነ ወመድኃኒነ ዕቀብ  ሕይወተነ እም ገሀነመ እሳት ወእምኵሉ መንሱት በእንተ ቅዱስ ስምከ ወበእንተ ማርያም እምከ ወበእንተ ቅዱስ መስቀል ወበእንተ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ ወበእንተ ኵሎሙ ቅዱሳን ወሀባ ሰላመ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ወለቅድስት ቤተክርስቲያን። ⚜ሰላም ለክሙ ጻድቃን ወሰማዕት እለ አዕረፍክሙ በዛቲ ዕለት መዋዕያነ ዓለም አንትሙ በብዙኅ ትዕግሥት። ሰአሉ ቅድመ ፈጣሪ በኩሉ ሰዓት እንበለ ንስሐ ኪያነ ኢይንሣእ ሞት። 🌿አንቅሐኒ በጽባሕ ክሥተኒ ዕዝንየ በዘአጸምእ አምላኪየ አምላኪየ እገይሥ ኀቤከ ዘይሰማዕ ግበር ሊተ ምሕረተከ በጽባሕ" ⚜ነቢያት ወሐዋርያት፥ ጻድቃን ወሰማዕት፤ ደናግል ወመነኮሳት፥ አዕሩግ ወሕጻናት፤ ገዳማውያን ወሊቃውንት፤ ሰአሉ ለነ ኲልክሙ፥ ቅድመ መንበሩ ለጸባኦት። 🌿እግዝእትየ ፍትሕኒ እማዕሠሩ ለሰይጣን፤ እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን። ✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር 🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል) 🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር) 🔗https://t.me/zikirekdusn ▶️https://www.youtube.com/@ZikereKedusan 🔰🛑ግእዝ ለመማር  https://t.me/lisanegeez5
5492Loading...
21
Media files
5401Loading...
22
†✝† እንኩዋን ለጥንተ በዓለ ዸራቅሊጦስ (መንፈስ ቅዱስ) እና ለጻድቁ አባ ገዐርጊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †✝† †✝† በዓለ ዸራቅሊጦስ †✝† ✝✞✝ ከዚሕ በፊት እንደተመለከትነው የጌታችን ዓበይት በዓላቱ 2 ጊዜ (ማለትም ጥንተ በዓልና የቀመር በዓል ተብለው) ይከበራሉ:: ዛሬም ከ1,978 ዓመታት በፊት አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ መውረዱን እናስባለን:: ††† ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- +ቸር አምላክ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል *ከልዑል ማዕርጉ ወርዶ: *በማሕጸነ ድንግል ተጸንሶ: *በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: *ከኃጢአት በቀር በግዕዘ ሕጻናት አድጐ: *በ30 ዘመኑ ተጠምቆ: *ቅድስት ሕግ ወንጌልን አስተምሮ: *በፈቃዱ ሙቶ: *በባሕርይ ስልጣኑ ተነስቶ: *በአርባኛው ቀን ያርጋል:: +ታዲያ ደቀ መዛሙርቱን የቅዱስ መንፈሱን ጸጋ ተስፋ እንዲያደርጉ ነግሯቸው ነበርና በተነሳ በ50ኛው ቀን: በዐረገ በ10 ቀን ተስፋውን ፈጸመላቸው:: +እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ እንድትይዝ በአንድ ላይ ሰብስባ ለክብረ መንፈስ ቅዱስ አብቅታቸዋለች:: 120ው ቤተሰብ ከጌታችን እናት ጋር ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ በአውሎ ንፋስ አርአያ ወርዶ በአምሳለ እሳት አደረባቸው:: +ቅዱሳን ሐዋርያት ፈሪዎች የነበሩ ደፋሮች: አሮጌ ሕሊና የነበራቸው ሐዲሶች ሆኑ:: በአዕምሮ ጐለመሱ: ቁዋንቁዋ ተናገሩ: ምሥጢርም ተረጐሙ:: በቅጽበትም ብሉይ ከሐዲስ በልቡናቸው ውስጥ ተሞላ:: +ሐዋርያቱ ቅዱስ መንፈስን ተቀብለው ዓለምን በወንጌል ዕርፈ መስቀል አርሰዋል:: አልጫውን ዓለም ጨው ሆነው አጣፍጠዋል:: ሳይሳሱም አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተዋል:: "ኪያሁ መንፈሰ ነሢኦሙ ለለአሐዱ: ሐዋርያት ለሰቢክ አሕጉራተ ዓለም ዖዱ: ሰማዕትኒ ለሕማም ነገዱ::" እንዳለ ደራሲ:: +በዚህ ቀን 2 ነገሮች በትኩረት ይነገራሉ:- 1."የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክነት:-" *እርሱ ከአብ የሠረጸ: ቅድመ ዓለም የነበረ: በባሕርይ ስልጣኑ ከአብና ከወልድ ጋር እኩል የሆነ: የራሱ ፍጹም አካል ያለው ፍጹም አምላካችን ነውና:: 2."ቅድስት ቤተ ክርስቲያን:-" *አብ ያሰባት: ወልድ በደሙ የቀደሳት: መንፈስ ቅዱስ በጸጋው ያጸናት የክርስቲያኖች አማናዊት አንድነት: አንድም ቤት ናትና:: ዛሬ በጉባዔ ተመስርታለች:: ††† አባ ገዐርጊ ††† =>በዚችም ዕለት የአባ አብርሃም ጓደኛ የከበረ አባ ገዐርጊ አረፈ።ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገን ነው ወላጆቹ ደጎች ጻድቃን ናቸው።በአደገም ጊዜ የወላጆቹን ከብቶች የሚጠብቅ እረኛ ሆነ።ሁል ጊዜም የምንኵስና ልብስ ይለብስ ዘንድ በልቡ ይመኝ ነበር። ዐሥራ አራት ዓመትም በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ አነሣሳችው በጎቹንም ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ።እየተጓዘም ሳለ ከሩቅ የብርሃን ምሰሶ አየ ወደ ወንዝ እስከ ደረሰ ድረስ ወደ ርሱ ሔደ ከዚህም በኃላ ያ የብርሃን ምሰሶ ከእርሱ ተሰወረ። ያንንም ወንዝ በተሻገረ ጊዜ በሽማግሌ አምሳል ሰይጣን ተገለጠለትና ልጄ ሆይ ዕወቅ ስለ አንተ ልብሱን ቀዶ አባትህን አየሁት እርሱም ያዝናል ያለቅሳል ተመልሰህ የአባትህን ልብ ልትአጽናና ይገባሃል።የዱር አውሬ ነጥቆ የበላህ መስሎታልና አለው። አባ ገዐርጊም ደንግጦ አንድ ሰዓት ያህል ቆመ ከዚህም በኃላ የከበረ ወንጌል ከእኔ ሊሆን አይገባውም ደቀ መዝሙሬም ሊሆን አይችልም ብሏል ብሎ አሰበ።ይህንንም በአለ ጊዜ ሰይጣን እንደ ጢስ ሆኖ ተበተነ።አባ ገዐርጊም ሰይጣን እንደ ሆነ አወቀ በዚያን ጊዜም ያ የብርሃን ምሰሶ ደግሞ ተገለጠለት የእግዚአብሔርም መልአክ በመነኵሴ አምሳል አብሮት ተጓዘ ቅዱሱም መልአኩን ተከተለው እርሱም ከአባ አርዮን ገዳም አደረሰው።አባ ገዐርጊም ከአንድ ጻድቅ ሰው መነኵሴ ጋራ በዚያ ዐሥራ አራት ዓመት ወጥሳይቀምስ ወይን ሳይጠጣ የአትክልት ፍሬም ቢሆን በዚህ በዐሥራ አራት ዓመት ያህል ከሚቀመጥ በቀር አልተኛም። ተጋድሎውንም በጨመረ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ሥጋህ እንዳይደክም በመካከለኛ ገድል ተጋደል ብሎሃል ጌታ።ከዚህም በኃላ ሊሠራው የሚገባውን ሥርዓት ሠራለት ።ሁል ጊዜም እስከሚመሽ እንዲጾም ትንሽም እንጀራን እንዲበላ ከአራት ሰዓት እስከ መንፈቀ ሌሊት ስለ ሥጋው ዕረፍት እንዲተኛ በቀረው ሌሊት እስቲነጋ ተግቶ እንዲጸልይ። በዚህም ተጋድሎ ብዙ ዘመናት እየተጋደለ በኖረ ጊዜ በበረሀ ውስጥ ብቻውን ሊኖር ወዶ በጫካ ውስጥ እየተመላለሰ ሁለት ዓመት ኖረ።ከዚህም በኃላ ጌታ ተገለጾለት ወደ ቦታው እንዲመለስ አዘዘው።ያን ጊዜም አምላካዊት ኃይል ከከበሩ መክሲሞስና ደማቴዎስ ገዳም አደረሰችው እርሷም ለደብሩ አቅራቢያ ናት። ወደ ደብሩም በተመለሰ ጊዜ በዚያን ወቅት አብርሃም ከዓለም ወደዚያ ገዳም መጥቶ ሁለቱም ተገናኙና በአንድነት ተስማምተው የአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ወደ ሆነ ወደ አባ ዮሐንስ ደረሱ።እርሱም ቦታ ሰጥቷቸው በውስጡ ኖሩ ያ ቦታም እስከ ዛሬ ታውቆ ይኖራል ። ያቺም ዋሻ በግቢግ ትባላለች የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዐለት የሆነ ጣሪያዋን ሠንጥቆ ወደ እነርሱ የወረዳበት ናት ።እነርሱም ሰገዱለት ሰላምታም ሰጥቷቸው አጽናንቷቸው ከእርሳቸው ዘንድ ዐረገ።በዚያችም ጌታችን በወረደበት መስኮት ብርሃንን አዩ እስከ ዛሬም የተከፈተች ሁና ትኖራለች። እሊህ ቅድሳንም ለመነኰሰኘሳት የሚሆን ብዙ ድርሳናትንና ብዙ ተግሣጻትን ደረሱ።ለአባቶቹ የሚታዘዘውንና የሚገዛውን አመሰገኑት።ከዚህም በኃላ አባ አብርሃም ጥር ሁለት ቀን አረፈ።ከእርሱ በኃላም የከበረ አባ ገዐርጊ በዚች በግንቦት ወር በዐሥራ ስምንት ቀን አረፈ።መላ ዕድሜውም ሰባ ሁለት ዓመት ሆነ።በዓለም ዐሥራ አራት ዓመት በምንኩስና ኃምሳ ስምንት ዓመት ነው።ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትሁን አሜን። =>በዚችም ዕለት የሰማዕት ሲኖዳ መታሰቢያው ነው በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። =>አምላከ ገዐርጊ ከቅዱስ መንፈሱ ጸጋ ለኃጥአን ባሮቹ ያድለን:: =>ግንቦት 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱሳን ሐዋርያት ወአርድእት 2.አባ ገዐርጊ ገዳማዊ 3.ቅዱስ ሲኖዳ ሰማዕት =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ 2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን) 3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ 4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ =>+"+ በዓለ ሃምሳም የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ:: ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው:: እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው:: በእያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው:: በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው:: መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር:: +"+ (ሐዋ. 2:1-4) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdusn
8774Loading...
23
Media files
8751Loading...
24
አጭር ግን ቶሎ እጅ የሚያሰበስብ ቃል ነው። ቅዳሴ ላይ በሰማሁት ቁጥር ሁሌ “እንዴት ሆኜ አይቶኝ ይሆን?” እንድል የሚያደርገኝ ጉልበታም ንግግር ነው። “እግዚአብሔር ያያል!”
1 0587Loading...
25
"አንዳች እንደሌለኝ አውቀዋለሁ ባንተ ቸርነት ግን እመካለሁ የከበደው ሸክሜ ይቀለኛል ይቅርታህ ለባርያ ይደርሰኛል።🙏❤
1 29315Loading...
26
ሊቀ ዲያቆናት ሰማዕት አውጣን ከመቅሰፍት ከመዓት ንፁብ ርግብ ነህ ቀሊለ ክንፍ ና እስጢፋኖስ ከሞት እንትረፍ እልልልልልልልልል👏🌷🌸🌷👏🌷🌸🌷👏🌷🌸🌷👏🌷🌸🌷እልልልልልልልልል
1 3603Loading...
27
«ኦ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሆይ ያለ ንሰሐ በከንቱ እንዳንሞት እድሜን በትጋት እንለምንሃለን ፈጣሪህ እግዚአብሔር የኃጢአተኞችን ሞት አይወድምና። "የቅዱስ እስጢፋኖስ በረከቱ ይደርብን መልካም ቀን ይሁንልን🙏💖
1 75221Loading...
28
የማያረጅ ፣ የማይቀጭ ፣ ወረት አልባ ፍቅር ስጠኝ ፤ ማግኘቴ ውስጥ የምሰጠው ፣ የማግዘው ፣ የሚደሰት ይኖረኝ ዘንድ ቸር ልብ ስጠኝ ፦ የምችለውን ችግር ስጠኝ ፣ መኖሬ በሰው ቸርነት ይቀጥል ዘንድ የምለምን አልሁን ፦ ሳጠፋ ይቅርታ የሚጠይቅ ልቦና ስበደል ይቅርታ አድራጊ ልብ ስጠኝ፦ ገመና የምሸሸግ ፣ ብልግናን የማላጎላ ፣ ዘመዴ የሆነውን የሰው ልጅ የምወድ እና የምረዳ አድርገኝ ፦ እንግዳ እንደሆንኩ ስኖር በዚች አለም ይገባኝ ዘንድ ልቦናዬን አብራልኝ ስለሆነልኝ ፣ ስለምታረግልኝ ነገር እኔ ባሪያህ ወለተ ሥላሴ አመሰግንሃለሁ አሜን 🙏
1 44623Loading...
29
☦መልክአ ቅዱስ እስጢፋኖስ🌷 ቅዱስ እስጢፋኖስ ሆይ ሰላም እልሃለሁ/፫/ በጨነቃችሁ ጊዜ ሁሉ ቅዱስ እስጢፋኖስ አባቴ አለው ይበላችሁ። 🥰🙏🥰
1 3122Loading...
30
Audio from 😥ቃልየ አጽምዕ እግዚኦ ወለቡ ጽራሕየ🙏
1 6286Loading...
31
Media files
1 5642Loading...
32
ነገ ግንቦት 17 ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነውው። ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ይሰውረን።🙏🌷🙏
1 7828Loading...
33
ነገ ሚያዝያ 17 ቅዱስ እስጢፋኖስ ነውው። ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ይሰውረን።🙏🌷🙏
10Loading...
34
#ቅዱስ_እስጢፋኖስ_❤ "እስጢፋኖስ ማለት  የግሪክ ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም «አክሊል»ማለት ነው።ቅዱስ እስጢፋኖስ በግሪክ ሀገር እንደተወለደ የሚነገርለትና ከክርስቶስ እርገት በኋላም አስራ ሁለቱም ሐዋርያት በጋራ ተሰብስበውና ለአገለግሎት ከመረጡዋቸው ሰባት ዲያቆናት አንዱና ዋነኛው ነበር። ሕዝቡን በማዕድ ያገለግሉ ዘንድ ሰባት ዲያቆናት ተመርጠዋል።         🌿❤️ ከእነዚህ መካከል ቅዱስ እስጢፋኖስ አንዱ ሲሆን ለስድስቱ ዲያቆናት ደግሞ አለቃ ሊቀ ዲያቆን ሆኖ ተሹሟል። ቅዱስ እስጢፋኖስ በማዕድ አገልግሎት ሕዝቡን ከማገልገሉ በተጨማሪ ወንጌልን ይሰብክ ነበር ። ተዐምራትን የማድረግ ጸጋም ተሰጥቶት ነበር በዚህም አገልግሎቱ ብዙዎችን ወደ ክርስትና መልሷል።         🌿❤️ በዚህም አይሁድ በቅናት ተነሳስተው በሐሰት ከሰሱት ከከተማውም ወደ ውጭ አውጥተው ቄዳር በተባለ ቦታ በድንጋይ ወገሩት በሚወግሩትም ጊዜ ሰማያት ተከፍተው ምሥጢረ ሥላሴን እግዚአብሔርን በሦስትነቱ ተመለከተ።          🌿❤️ ኢየሱስ ክርስቶስንም በአብ ቀኝ ተቀምጦ አየ ። ለሚወግሩትም ሰዎች ከአምላኩ እንዲህ በማለት ምሕረትን ለመነ «ጌታ ሆይ ይህንን ኃጢአት አትቁጠርባቸው» በመጨረሻም «ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል»ብሎ ነፍሱን ሰጠ።            🌿❤️ ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት። ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ። እስጢፋኖስም። ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር። ተንበርክኮም። ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር። 《የሐ ሥራ 7፥58—60》 🌿❤️ የቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት በረከትና ምልጃው አይለየን ለዘለዓለሙ አሜን ወስብሓት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር አሜን @Orthodoxtewahdoc ቤተሰብ ይሁኑ
1 5019Loading...
35
Media files
1 2345Loading...
36
♥#ወለተ_ጴጥሮስ_ማን_ናት⁉🌹          ➖━⊱✿⊰━➖ 📒☞ወር በገባ በ17 የእናታችን የቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ወርሀዊ መታሰቢያዋ ነው፡፡ይቺ ደገኛ ሴት አባቷ ባሕር ሰገድ እናቷ ክርስቶስ ዕበያ ይባላሉ፡፡ ☞የትውልድ ሀገሯ ጎንደር ደዋሮና ነው፡፡ ይቺ የተቀደሰች እናታችን ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ በሕግ በሥርዓት በሊቀ ጳጳስ ትዕዛዝ የንጉሥ ሱስንዮስን የአማካሪዎች አለቃ የሆነው መላክአ ክርስቶስን አግብታ ሦስት ልጆችን ወልዳለች፡፡ ባሏም ታላቅና እጅግ ባለጸጋ ነበርና ከልጆች ጋር በተድላ በደስታ መኖር እንደጀመረች፡፡ አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ እነዚህ ሦስት ልጆቼ አንተን የሚያስደስቱ ከሆነ በሞት ውሰዳቸው፡፡ ብላ ከጸለየችበኃላ እንደፋላጎቷ ሦስት ልጆቿ በሞት ተወስደውላታል፡፡ ☞ባለቤቷ እጅግ እየወደዳት እርሷ ግን ይህን ዓለም እንደ ጤዛ ያልፋል፡፡ ብላ ከሞላ ሀብቷ ከሞቀ ቤቷ ተለይታ ወጥታ በመመነን ጣና ገባች፡፡ በዚያም በተጋድሎ ስትኖር ባሏ አበምኔቱን ለምን ገዳም አሰገበሀት ብሎ ከሰሳቸውና ከገዳሙ አስወጣት፡፡ እርሷ ግን ተደብቃ አክሱም ሄዳ ደብረ በንኮል ገዳም ገባች፡፡ ተመልሳም መጥታ በጣና ባሕር ላይ ቆማ መጸለይ ጀመረች፡፡ በዘመኗ የነበረው ገዢ ጨካኝ ለጣዎት የሚሰግድ ሰለነበረ በትልቅ ገደል ወረውረው እንዲጥሏት አደረጋት፡፡ ነገር ግን መልአኩ ቅድስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ መጥቶ በክንፋ ተቀብሏት ወስዶ ብሔረ ብፁዓን አሳይቶ መልሶ አምጥቶ ዋልድባ አደረሳት፡፡ ☞ቅድስት እናታችን ወለተ ጴጥሮስ ወደ ጉምዝ ሀገርም ተስዳ ሳለ በነደደ አሳትውስጥ ቢጨምሯት ምንም ሳያቃጥላት ወጥታለች፡፡ ተመልሳም በጣና ባሕርላይ ቆማ ስትጸልይ ልብሷ ለገዳሙ ያበራ ነበር፡፡ ቧላም እምነቱን ቀይሮ ከካቶሊኮች ጋር ሰለተዛመደ ቅድስ እናታችን ካቶሊኮቶችንና ባሏን አጥበቃ ሰለተቃወመች በገመድ አሰረዋት በጎንንደር ከተማ ጎዳና ላይ ጎትተው አሠቃያት፡ ☞ቅድስ ወለተ ጴጥሮስ ሰባት ገዳማትን ያቀናች ሲሆን ከ700በላይ በሚሆኑ ወንዶች መነኮሳትና ሴቶች መነኮሳት ላይ እመ ምኔት ሆና ተሹማ አገልግላለች፡፡ ☞ከመነነችበት ጊዜ ጀምሮ ምግቧም የመረረ ቅጠል፤ኮሶና አመድ ነበር፡፡ ቅድስት እናታችን ታላቁን የራማ መድሀኒአለም ቤተ ክርስቲያን ሠርታ ሙታንን እያነሳች ድውያንን እየፈወሰች በታላቅ ተጋድሎ እያገለገለች ሳለ ኅዳር 17ቀን በታላቅ ከብር ዐርፋለች፡፡ ወርሐዊ የመታሰቢያ ዕለቷ ወር በገባ በ17 ነው፡፡ በዕረፍቷም ጊዜ የብርሃን ምስሶ ከምድር ሰማይ ተተክሎ ታይቷል፡፡ ☞የቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ዐፅሟ በራሷ በመሠረተችው በሬማ መድኃኔአለም አንድነት ገዳም ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል ፡፡በዚህ ገዳም ውስጥ በቅድስ ሥላሴ ምሳሌ የተሠሩ ሦስት የተለያዩ ድምፆችን የሚያወጡ ደወሎች ይገኛሉ፡፡ ሦስቱም ደውሎች የሚያወጡት ድምጽ ፍጽም የተለያየ ነው፡፡ ☞የእናታችን የወለተ ጵጥሮስ አማላጅነት አይለያችሁ፡፡ ☞የጽሁፍ ምንጭ☞መዝገበ ቅዱሳን ☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ ቤተሰብ ይሁኑን ብዙ የቅዱሳንን ታሪክ እናቀርብለወታለን https://t.me/Orthodoxtewahdoc
1 4225Loading...
Photo unavailableShow in Telegram
"የሰንበትን ቀን ትቀድሰዉ ዘንድ አስብ "!! (ዘፀአት፣20;:8)📚 መልካም እለት ሰንበት ይሁንልን። ከሰንበት ቀን ረድኤት በረከት ይክፈለን አሜን🙏⛪
Show all...
🙏 10 4👏 2
*©ያከብርዋ ለሰንበት* ጥራዝ 1.ቁ. 41 ያከብርዋ ለሰንበት መላእክት በሰማያት ጻድቃን በውሰተ ገነት/፪/ ወኲሉ ፍጥረት አሣት ወአናብርት እለ ውሰተ ደይን ያዕረፉ ባቲ እስመ ባቲ አዕረፈ እምኲሉ ግብሩ/፪/ ያከብሯታል ሰንበትን መላእክት በሰማያት ጻድቃን በገነት/፪/ ፍጥረታት በሙሉ አሳዎች እና አንበሪዎች በመቃብር ያሉ ያከብሯታል አምላክ በእርሷ እንዳረፈ ከሥራ ኹሉ/፪/
Show all...
10🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
"እግዚአብሔርን "ለምን ትረሳኛለህ?" አትበለው "ጌታ ሆይ የረሳሁህን እኔን ይቅርበለኝ፤ ፍቅርህን ዘንግቻለሁና በመከራዬ ጊዜም አስበኝ" በለው እንጂ።"አቡነ_ሽኖዳ_ሳልሳዊ 🥀መልካም እለተ ሰንበት❤️💒
Show all...
🙏 27 2
Photo unavailableShow in Telegram
"ትህትናን ውደዷት ኃጢአታችሁን የምትሸፍን ናትና፡፡ ሁሉም ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ቢሆንም ከኃጢአቶች ሁሉ መጥፎ የሆነው ግን የልብ ትዕቢት ነው:: ራሳችሁን አዋቂ አድርጋችሁ ከፍ ከፍ አታድርጉ፡፡ ይህን ምታድረጉ ከሆነ ጥረታችሁ ሁሉ ፍሬ አልባ ይሆናል፡፡" 🌿አባ_እንጦንስ።🌿 🥀እንደምን አደራችሁ መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን🤲☦💒
Show all...
🙏 21 4👍 1
🌷መልክአ ጸበለ ማርያም📗 ቅድስት ጸበለ ማርያም ሆይ እረፍት ወዳለበት ገነት ወንድም እህቶችሽ እንገባ ዘንድ እኅት ሆይ አማልጅን አሜን🤲 https://t.me/Orthodoxtewahdoc
Show all...
🙏 6👍 3 3
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ ✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"📖ምሳ 1፥33☦📚          ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥ 📗ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት ፲፰/18 https://t.me/Orthodoxtewahdoc 🌹የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን🕊
Show all...
5🙏 3
Photo unavailableShow in Telegram
ግዜህን በቁጣ ፣በቁጭት ፣ በመጨነቅ እና ቅር በመሰኘት አታሳልፍ ። ህይወት ደስተኛ ላለመሆን በጣም አጭር ናት ❗ 🥀ሰናይ ሌሊት☦🤲
Show all...
29👍 5🥰 2🫡 2
⛪️👀 ከሐዘን፡የተነሣ፡ነፍሴ፡አንቀላፋች፤በቃልኽ፡አጠንክረኝ። የዐመፅን፡መንገድ፡ከእኔ፡አርቅ፥በሕግኽም፡ማረኝ፤ የእውነትኽን፡መንገድ፡መረጥኹ፥ፍርድኽንም፡አልረሳኹም። አቤቱ፥ምስክርኽን፡ተጠጋኹ፤አታሳፍረኝ። ልቤን፡ባሰፋኸው፡ጊዜ፥በትእዛዝኽ፡መንገድ፡ሮጥኹ። ሄ አቤቱ፥የሥርዐትኽን፡መንገድ፡አስተምረኝ፥ዅልጊዜም፡እፈልገዋለኹ። እንዳስተውል፡አድርገኝ፥ሕግኽንም፡እፈልጋለኹ፤በፍጹም፡ልቤም፡እጠብቀዋለኹ። ርሷን፡ወድጃለኹና፡የትእዛዝኽን፡መንገድ፡ምራኝ። ልቤን፡ወደ፡ምስክርኽ፡አዘንብል፥ወደ፡ሥሥትም፡አይኹን።ከንቱ፡ነገርን፡እንዳያዩ፡ዐይኖቼን፡መልስ፤በመንገድኽ፡ሕያው፡አድርገኝ። አሜን:አሜን:አሜን
Show all...
17🙏 4👍 2👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ነገ ግንቦት 18 ፃድቁ አባታችን አቡነ ሰላም ከሳቴ ብርሃን ናቸው። ቅዱሱ ለሃገራችን ዻዻስ ሆነው የተሾሙት በዚህች ዕለት ነው: በረከታቸው ይደርብን🤲
Show all...
35🙏 9