cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን /አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ። 📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼ ❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

Show more
Advertising posts
22 878
Subscribers
-1224 hours
-597 days
+34730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🌷መልክአ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ📗 🥰ቸሩ መድኃኔዓለም በቅዱሳን ፀሎት ይማረን በቀኝ ያዉለን መልካም ቀን🤲
Show all...
2👍 1🙏 1
Audio from 😥ቃልየ አጽምዕ እግዚኦ ወለቡ ጽራሕየ🙏
Show all...
5👍 1
🌷እንደምን አመሻችሁ ቤተሰብ🤲 ገብረ መንፈስ ቅዱስ አባታችን በረከትህ ይግባ ቤታችን🤲♥️🙏
Show all...
30🙏 16👏 2
"ነገ ጥር 5 ፃድቁ አብን ገብረ መንፈስ ቅዱስ አባታችን ናቸው። ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ይሰውሩን🙏
Show all...
30🙏 21👍 3
️🌹📘#የአባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታሪክ ባጭሩ 🌹 📌 አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐገራቸው ንሂሳ ግብጽ ነው፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች፡፡ ♨ በዚህ መሠረት ቅዱስ አባታችን ጻድቁ አቡዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለዱ፡፡ ♨አባታችን ዓይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ተነስተው «ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘዓውፃእከኒ እምጽልመት ውስተ ብረሃን» ብለው አመስግነዋል። ♨በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን ይመስላሉ፡፡ አባታችን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማጸነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል፡፡ ♨መላእክት በአክናፈ እሳት ኢየሩሳሌም ወስደው በየማነ ምስዋዕ ቀብረዋቸዋል፡፡ ♨ለፅንሰትከ ፤ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በብሥራተ መልአክ ለተፀነስነከው መፀነስና በወርኃ ታኀሣሥ ለተወለድከው ልደትህ ሰላም እላለሁ። 🙏ክቡሩ አባት ሆይ ስለ ዓለሙ መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ጌትነቱ ልደት ተርሴስ ግብር እንደገበረ፤እኔም ፍጹም ልባዊ የእጅ መንሻ ወርቅ አቀርብልሃለሁ። 💙ለተኃፅኖትከ፥ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የቤተ ክርስቲያን መብራት የምትሆን የተመረጠች የክብርት እናትህን ጡት ባለመጥባት በመንፈስ ቅዱስ እንክብካቤ ስለ አደግኸው አስተዳደግህ ሰላም እላለሁ። የአባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከትታቸው አይለየን አሜን ወስብሓት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር አሜን https://t.me/Orthodoxtewahdoc
Show all...
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን /አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥

https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ። 📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼ ❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

🙏 3👍 2 2
✳ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ📍 "ወር በገባ በ5 የሐዋርያው ቅድስ ጴጥሮስ☞ለሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወርሐዊ መታሰቢያቸው ነው፡፡☞ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ የአባቱ ስም ዮና ይባላል፡፡ ☞ጌታን ከመከተሉ በፊት ከአምስት ዓመት ጀምሮ ያደገው በቅፍርናሆም ከተማ ሲሆን በጎልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሣ አጥማጅ ነበረ፡፡ ማር16-18 ☞ለደቀ መዝሙርነት ሲመረጥ ዕድሜው55 ዓመት እንደነበረ ይነገራል፡፡ ☞የመጀመሪያ ስሙ ሰምዖን ሲሆን ጌታችን ጴጥሮስ ብሎታል፡፡ በላቲን ቋንቋ ዐለት ማለት ነው፡፡ ☞የመንግሥተ ሰማያት ቁልፍ ተሰጥቶታል፡፡ ☞ቅዱስ ጴጥሮስ በማንኛውም ነገር ፈጣንና ቀልጣፋ እንደነበር ይነገራል፡፡ ☞ቅዱስ ጴጥሮስ በፍልስጤም፤ በልዳ፤ በኢዮጴ፤ በቂሳሪያ፤ በገላትያ፤ በሮሜና በተለያዩ ሀገሮች እየተዘዋወረ አሰተምሮ አሳምኗል፡፡ ☞ከአሕዛብ ወገን የነበረ ቆርሌዎስን ከነቤተሰቡ አጥምቋል፡፡(የሐዋ' ሥራ 10፥38) ☞በጥብርያዶስ የጥርጥር ባሕር ጌታ እንዳዳነው(ማቴ14፤22) ☞ማልኮስ ጆሮውን እንደቆረጠው(ዮሐ18፤10 ጌታ በአይሁድ እጅ ተይዞ ሳለ የገባው ቃል አጥፎ ሦስት ጊዜ ጌታን አላውቀውም ብሎ እንደካደ የማቴዎስ 26-፡ ተጠቅሶል ☞በኀላም ግን በንስሐ በመመለሱ ጌታ ግልገሎቼን አሰማረ፤ ጠቦቶቼን ጠብቅ፣ በጎቼን አሰማረ በማለት አደራ እንደሰጠው በወንጌል ተገልጿል (ዮሐ 21፥15) ☞ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ንጉሥ ነገሥት ኔሮን ቄሣር ዘመነ መንግሥት በክርስቲያኖች ላይ ስደትና መከራ በመስቀል ተስቅሎ ግን እን እንደክርስቶስ ተስቅሎ ሞት የማይገባኝ ስለሆነ ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ ብሎ በሐምሌ 5 በሰማዕትነት አርፏል፡፡ ☞1'2☞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ☞ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የተወለደው ጠርሴስ ከተማ ሲሆን ትውልዱ ከዕብራውያን ከብንያም ነገድ ነው፡፡ ☞ጠርሴስ በንግድ ዓለም የታወቀች የኪልቅያ ዋና ከተማ ነበረች፡፡ ☞ሮማውያንም በሥራቸው ለሚተዳደሩ ሕዝቦች የሮማ ዜግነት ይሰጡ ሰለነበረ የቅዱስ ጳውሎስ አባት በዜግነት ሮማዊ ነበር፡፡ ☞ቅዱስ ጳውሎስ በ15 ዓመቱ ወደ ኢየሩሳሌም በመመለስ ከገማልያ የአይሁድን ሕግና ሥርዓት ጠንቅቆ ተምሯል፡፡ ☞በ30 ዓመቱም የአይሁድ ሸንጎ አካል ሆኖ ተቆጥሯል፡፡ ☞በአይሁድ ሸንጎ አባልነት ለሁለት ዓመታት በሠራበት ወቅት ለኦሪት እምነቱ ቀናተኛ ፈሪሳዊ በመሆኑ ክርስቲያኖችን በማንኛውም አጋጣሚ ይቃወምና ያሳድድ ነበር፡፡ ☞ቅዱስ እስጢፋኖስ ክርስትናን በማስተማሩ በአይሁድ ሸንጎ ተከሶ ሲቀርብ የተከራከረውን ቅዱስ ጳውሎስ ነበረ፡፡ ☞ኀላም በድንጋይ እስጢፋኖስ ሲወገር የወጋሪዎችን ልብስ ይጠብቅ የነበረው እርሱ ነው፡፡ ☞ቅዱስ ጳውሎስ ክርስቲያኖችን ሊሳድድ ሲሔድ ድንገት ታላቅ ብርሃን መጥቶ ሳወል ሳወል ለምን ታሳድደኛለህ የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ፡፡ ☞ሐዋርያውም ጳውሎስም ጌታ ሆይ አንተ ማነህ ብሎ በጠየቀ ጌዜ የምታሳድደኝ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ አለው፡፡ ☞ቅዱስ ጳውሎስ ከዛ በኃላ በሐናንያ ከተጠመቀና ከተማረ በኃላ አይሁድ ለኦሪት ሕግ ሲቆረቆር የነበረው አሁን ደግሞ ስለ ወንጌል ሲሰብክ በማየታቸው አይሁድ ሊገሉት ፈለጉ እሱ ግን ገላትያ፤ ጢሮአዳ፤ ኤፌሶን፤ ቆሮንቶስ፤ልስጥራ እና ሌሎች ከተማ ወንጌልን በማስተማር ቆየ፡፡ ☞በመጨረሻም በክርስቲያኖች ላይ ሞት ታወጆ ስለነበረ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከተማ ተይዞ 2 አመትከ7 ወር በጨለማ ቤት በእስር ከቆየ በኀላ በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ አንገቱ ተሰይፎ በሐምሌ 5ቀን በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ☞የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እና የቅዱስ ጴጥሮስ የጸሎታቸው በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ ☞(ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ መጽሐፍ የተወሰደ) ☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
Show all...
5
📘#አቡነ_አሮን_ማለት_ማን_ናቸው⁉🌹 ☞••📕ወር በገባ በ5 ጣራ ክፍት ሆኖ ዝናብ የማያስገባው የአባታችን የአቡነ አሮን (ዘመቄት) ወርሐዊ መታሰቢያቸው ነው፡፡የመቄቱ አቡነ አሮን ወላጅ አባታቸው የላስታው ጻድቁ ንጉሥ ዐፄ ገብረ መስቀል ነው፡፡ ☞የላስታ ነገሥታት የዘር ሐረጋቸው ከንጉሥ ሰለሞን ዘር ሲያያዝ የመጣ ነው፡፡ ☞ከ 10ኛው እሰከ 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (920-1253) ዓ/ም ገደማ በላስታ ቡግና ምድር የነገሡ የላስታ ቡግና ተወላጅ የሆኑ የኢትያጵያ ቅዱሳን ነገሥታት የንግሥናቸው መጠሪ የዛጉዌ ሥርወ መን በመባል ይታወቃል፡፡ ☞የንጉሥ ሰለሞን ዘር የሆነው መራ ክርስቶስ 3 ልጆችን ወለደ፡፡ እነሱም ጠንጠወድም፤ ግርማ ስዩምና ዣን ስዩም ናቸው፡፡ ]☞ጠንደውድም ገብረ መስቀልን ወለደ፤ ገቡረ መስቀልም አቡነ አሮን ወለደ፤ ግርማ ስዩም ይምርሐነ ክርስቶስን ወለደ፤ ዣን ስዩም ደግሞ ገብረ ማርያምንና ላሊበላን ወለደ፡፡ ገብረ ማርያም ነዓኩቶ ለአብን ወለደ፡፡ አነዚህ ቅዱሳን ነገሥታት እንደ መልከጸዴቅ ክህነትነን ከንግሥና ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ እግዚአብሔርንም ሕዝብንም በቅድስናና በንጽሕና አገልግለው አልፈዋል፡፡ ☞ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ አቡነ አሮን በ5 ዓመታቸው ሙት አስነስተዋል፡፡ ☞በ16 ዓመታቸው መንነው ዋልድባ ገዳም ገብተዋል፡፡ ☞በሀገራችን እየተዘዋወሩ ወንጌልን ሲሰብኩ የሸዋው ንጉሥ አንኮበር ድረስ ጠርተዋቸው ሄደው ሲመለሱ አዋሽ ወንዝ ሞልቶባቸው አገኙት፡፡ ሲሻገሩ ዳዊታቸውን ወሰደባቸው፡፡ አሁንም በድጋሚ ሌላ ጊዜ በሸዋው ንጉሥ አንኮበር ድረስ ተጠርተው ከ7 ዓመት በኃላ ተመልሰው በአዋሽ ወንዝ ሲሄዱ መልአክ መጣና"መቋሚያህን ወደ ወንዙ ላክ አላቸው፡፡ መቋሚያቸውንም ቢልኩ ዳዊታቸውን ይዘው አወጡ፡፡ ☞ዳዊቱም በውኃው አልራሰም ነበር፡፡ ይልቁንም አቧራውን አራግፈው ፈጣሪያቸውን አመሥግነው ዳዊታቸውን ይዘው ሄደዋል፡፡ ያ ዳዊታቸው ዛሬም ድረስ በጋይንት አብርጎት ቅዱስ ሚካኤል ይገኛል፡ ☞ሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ የሚገኘው እጅግ አስደናቂ ገዳማቸው ፍልፍል ዋሻ ሲሆን ጣራው ክፍት ነው፡፡ ክፍት በሆነው ጣራ በኩል ፀሐይ ሲገባ ሰለሚያቃጥል ጥላ ይይዛሉ ነገር ግን የጻድቁ ግዝት ስላለበት ዝናብ ወደ መቅደሱ ፈጽሞ አይገባም፡፡ ☞አቡነ አሮን በአንቺም ሜዳ በሚባል ቦታ ፀሐይንም ገዝተው አቁመዋታል፡፡ ☞ከታች ጋይንት ተነሥተው መንገድ ሲሄዱ በሰንበት ቀን በሬ ጠምዶ ሲያርስ የነበረን ገበሬ ለምን በሰንበት ታርሳለህ ቢሉት ምቀኛ መነኩሴ ብሎ በጅራፉ ቢገርፋቸው በሬዎቹ ግን ፈጽሞ አልንቀሳቀስ ብለው ቆመዋል፡፡ ☞በዚህ የተናደደው ገበሬም አቡነ አሮንን መሬት ላይ ጥሎ ገረፋቸው፡፡ እሳቸው ተነሥተው ሲሄዱ ዛፎች ተነቅለው እየተከተሏቸው ቃል አውጥተው በሰው አንደበት አመስግነዋቸዋል፡፡ ☞የህንጻው አይነት☞ ስቁረት ሁለት አምዶች አስራ አራት መስኮት ሰባት አንደኛው ስቁርት ዝናብ የማይገባበት ፀሐይና ጨረቃ እንዲሁም ከዋክብት ብርሃናቸውን የሚሰጡበት ለማየት የሚያስደንቁ ሁለተኛው ብርሃናትም ዝናባትንም ይፈራራቁበታል፡፡ የወረደው ወይም ዝናብም ወዴት እንደሚሄድ ወይም የት እንደሚጠራቀም አይታወቅም፡፡ ይህንን እነደዚህ አድርገው አንፀው ወደ ፈጣሪያቸው አመለከቱ፡፡ ☞ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መላእክት አስከትሎ ወርዶ ቤተ መቅደሱን ባርኮ ቃል ኪዳኑን አፅንቶ አስከ ምፃት ድረስ እንዲሁ እያበራች ትኑር ብሎ አርጓል፡፡ ☞አባ አሮን መንክራዊም ቃል ኪዳናቸውን ተቀብለው ትንሽ ጊዜ ከቆዩ በኃላ ወደ በኬ ምድር ለቡራኬ ወጡ መላአክ ጊዜ እረፍታቸው እንደቀረቀበ ነገራቸው ያን ጊዜ ደስ ብሏቸው ወደ ገዳማቸው ሲመለሱ የመጀመሪያይቱ የእሳት ጥላሻት ተሰማያቸው ጎዳና በር እናላቲ የሚባሉ አቀበትና ቁልቁለት አሉ በነዚህ መንገዶች ለመጓዝ በጣም ደከሙና አየተደገፋ ዘለቁ፡፡ ☞ከበሩ ሲደርሱ አሳረፏቸው ከዚያ በኃላ አንደበታቸው በረታ ልሳናቸው ፈታ ማኅበረ መነኮሳቱን አዕናኑ ቃል ኪዳናቸው አበረከቱ፡፡ ☞በገዳሙ ውስጥ የምንኩስና ክብር የተቀበለ ከቤተክርስቲያኑ ስጋ ወደሙ የተቀበለ እጣን ጧፍ ማንኛውም በጎ አድራጎት ለቤተ መቅደሱ የተራዳ በተለይም ይህችን ቦታ የረገጠ ገድልህን የሰማ ያሰማ የጻፈ ያፃፈ እሰከ አስራ አምስት ተውልድ እምርልሃለሁ ብሎ የሰጣቸውን ተስፋ ተናግረው ወደ ገዳሙ ሴት እንዳያልፍ በለው ካሰናበቱ በኃላ ጌታችን መላእክት አስከትሎ የብፁአ አባታችን ነፍስ ለማሳረግ ሲወርድ ታላቅ ግርማ ሆነ፡፡ ☞ከበሩ አንዲት ወይራ ነበረች ወይራይቱም ለፈጣሪዋ ሰገደች፡፡ እሰከአሁን ደርቃ ተጋድማ የወንድና የሴት መለያ ሁና ትታያለች በዚያ ግርማ መላእክት በማህሌት መስከረም 5ቀን ነፍሳቸውን ከስጋቸው ለይተው አሳረጓት ፡፡ ☞ስለዚህ መስከረም አምስት የእረፍታቸው ቀናቸው ነው በረከታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ ☞የጻድቁ ታላላቅ ገድላት ☞እንደነ ሙሴና አሮን በአምደ ደመና ከመሬት መሰወር፡፡ ☞እንደ ዳንኤል አናብስት ማሰገድ ☞እንደ ሙሴ ከድንጋይ ላይ ውሃ ማፍለቅ ☞እንደ ኤልሳ ባህርን ሁለት ጊዜ መሻገር፡፡ ☞እንደ እያሱ ፀሐይ ማቆም ☞እንደ ሐዋርያት ድውይ መፈወስ፡፡ ከቡዙ በጥቂቱ ነው፡፡ ☞ባህሩን የከፈሉበት ውሃ ያፈለቁበት ፀሐይ ያቆሙበት ዳዊታቸውን ያወጡበት በትረ መስቀላቸው ልዩና በቁመቱ በአራት ማዕዘን የተቀረፀ ሲሆን እስካሁን በገዳሙ ያለና ብዙ በሽተኞችን በመፈወስ ላይ ይገኛል፡፡ ☞ህንፃውን ያነፁበትና ጉድብ የተባለው መጥረቢያ ቅዱስ ኡራኤል የሰጣቸው ሶስት መልክ ያለው ይህም እየታጠበ ብዙ ድውያንን በመፈወስ ላይ ይገኛል፡፡ ☞የጻድቁ አባታችን የአቡነ አሮን ምልጃቸው ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ ☞(መዝገበ ቅዱሳንእና ገድለ አቡነ አሮን) ☞ሲራክ ተክላጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ በዚህ ጆይን እያላችሁ አንብቡ እናንብብ ከቅዱሳን በረከት ይክፈለንhttps://t.me/Orthodoxtewahdoc
Show all...
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን /አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥

https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ። 📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼ ❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

🙏 2