cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

Advertising posts
5 358
Subscribers
-824 hours
-407 days
-22230 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
ለሥራ ወደ ውጭ አገሮች ለሚሄዱ ከ500 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የመድን ዋስትና መስጠት ተጀመረ ወደ ውጭ አገሮች በሥራ ስምሪት ለሚጓዙ ከ500 ሺሕ በላይ ለሚደርሱ ኢትዮጵያውያን የሕይወት የመድን ሽፋን አገልግሎት ለመስጠት፣ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር ለሁለት ዓመታት ውል የተፈራረመው ኒያላ ኢንሹራንስ አገልግሎቱን በይፋ መጀመሩን ገለፀ። በዚህም ኒያላ ኢንሹራንስ ኩባንያ ወደ ተለያዩ አገሮች ተጉዘው የሥራ ቅጥር ውል ለሚፈጽሙ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ለሚደርስባቸው የሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የአዕምሮ መታወክና ሌሎች ተጓዳኝ ጉዳቶችን የሚሸፍን መሆኑን ሪፖርተር አስነብቧል። ለእነዚህ የመድን ሽፋኖችም ተጠቃሚዎች በዓመት እንዲከፍሉ የሚጠበቅባቸው 500 ብር ብቻ መሆኑ ሲጠቆም ይህ የመድን ሽፋን በአንድ ክፍያ ሰው እስከ 1.35 ሚሊዮን ብር ድረስ የሕይወት መድን ሽፋን አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑንም ተነግሯል። TikvahethMagazine
1520Loading...
02
በመላው ሃገሪቱ የነዳጅ ማደያ ፍቃድ ላልተወሰነ ጊዜ መታገዱ ተገለጸ አሁን ላይ የነዳጅ ማደያ ማስፋፊያ ፍቃድ መታገዱን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡ መንግስት የነዳጅ ማደያ ማስፋፊያን የትኩረት አቅጣጫ አድርጎ ሲሰራ መቆየቱን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ናቸው የተናገሩት፡፡ መንግስት የነዳጅ ማደያዎችን በሀገር ውስጥ ለማስፋፋት በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሯ አሁን ላይ ግን ባልተፈለገ አቅጣጫ እየሄደ መሆኑን ባለስልጣኑ በማረጋገጡ ፍቃዱ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲታገድ ተደርጓል ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ባለስልጣኑ ጥናት እያደረገ እንደሚገኝ የገለፁት ወ/ሮ ሳህረላህ የማደያዎች ፍቃድ አሰጣጥ እና ተደራሽነት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች መፍትሄ ካገኙ በኋላ ፍቃድ የመስጠቱ ስራ ዳግም እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡ ችግሩ ከተፈታ በኋላ በተለይም የነዳጅ ማደያ ተደራሽ ባልሆኑባቸው አካባቢዎች በስፋት የሚሰራ ይሆናል ነው ያሉት፡፡                 የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳህረላህ አብዱላሂ የነዳጅ ማደያ ፍቃድ አሰጣጥ ብዙ ጥናት ማድረግን የሚፈልግ ስራ በመሆኑ መቼ ይጀምራል የሚለውን አሁን መግለጽ አይቻልም ብለዋል፡፡ መናኸሪያ ሬዲዮ
1601Loading...
03
ዓለም አቀፉ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ ተሰማ በዋናነት ነዳጅ አምራችና ላኪ ሃገራት ላይ በታየው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ምክንያት ዛሬ ማለዳ ላይ ጭማሪ ማሳየቱን ሬውተርስ በቢዝነስ ዘገባው አስነብቧል። አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ በትንሹ የ0 ነጥብ 5 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱንም ዘገባው አመላክቷል። የኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲን ጨምሮ የሃገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት ባላስልጣናት በሄሊኮፕተር አደጋ ለህልፈት ከተዳረጉ በኋላ ጭማሪው መመዝገቡንም ዘገባው ጠቅሷል። በተጨማሪ የሳዑዲ አረቢያው ንጉስ ሳልማን የጤና መታወክ ያጋጠማቸው ሲሆን፥ ዜናው ከተሰማ በኋላም የዋጋ ጭማሪው ታይቷል ነው የተባለው። Arada_Fm
1842Loading...
04
ግብርና ሚኒስቴር ፀረ ተባይ እና የግብርና ኬሚካሎችን የሚረጩ አውሮፕላኖችን በኪራይ ሊያቀርብ ነው ተባለ የግብርና ሚኒስቴር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለማግኘት በማሰብ እርሻዎች ላይ ፀረ ተባይ እና ሌሎች የግብርና ኬሚካሎችን ለመርጨት የሚያስችሉ አውሮፕላኖችን በኪራይ ሊያቀርብ መሆኑን ሪፖርተር አስነብቧል። ሚኒስቴሩ በሀገሪቱ በምስራቅ እና ሰሜን የአንበጣ ወረራ መከሰቱን ተከትሎ 5 አውሮፕላኖች መግዛቱን ሲገልፅ የኢንሹራንስ እና የጥገና ወጪዎችን እንዲሁም ተባዮችን ለመቆጣጠር የሚያስችል አቅም ለማዳበር አውሮፕላኑን ለግሉ ዘርፍ ሊያከራይ እንደሆነ ገልጿል። የግብርና ሚኒስቴር ግርማ አመንቴ እነዚህን አውሮፕላኖች ለግሉ ሴክተር እና ለትልልቅ እርሻዎች አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችለውን አሰራር ለመዘርጋት መመሪያ መዘጋጀቱን የገለፁ ሲሆን አገልግሎቱ በቅርቡ ይጀምራል ብለው እንደሚጠብቁ ገልፀዋል። @TikvahethMagazine
1950Loading...
05
በአዲስ አበባ በዓመት ከ80 ሺ ቶን በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ ይመነጫል ተባለ በአዲስ አበባ ከተማ በዓመት ከ80 ሺ ቶን በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ ይመነጫል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አሰታወቀ። ይህም በከተማዋ ከሚመነጨው ቆሻሻ 13 በመቶ የሚሆነዉ የፕላስቲክ መሆኑ ሲነገር የሀገሪቷ የፕላስቲክ ፍጆታ ከ 2007 ከነበረበት 43000 በ 2022 ወደ 224000 አድጓል። ይህም በሰዎች ጤና፣ የአካባቢ ውበትና የውኃ ኃብት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ስለመሆኑም ተጠቁሟል። በዚህም አካባቢን የሚበክሉ የፕላስቲክ ምርቶች ውፍረታቸው ከ0.03 ማይክሮ ሜትር በታች ሆነው እንዳይመረቱና አገልግሎት እንዳይሰጡ ማድረግ፣ በፕላስቲክ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ ታክስ መጣል ተግባራዊ መደረግ ያለበት መሆኑን የዘገበው ካፒታል ነው። @TikvahethMagazine
1800Loading...
06
ሀገሪቷ ከወጪ ንግድ ከ2.5 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሏ ተገለፀ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር እንደገለፀዉ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ ከ 2.5 ቢሊየን በላይ የአሜሪከን ዶላር ገቢ መገኘት ችሏል ብሏል። ሚንስትሩ እንደገለፀዉ በዘጠኝ ወሩ 3.56 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 2.511 ቢሊዮን ዶላር ወይም 70.49 በመቶ ገቢ ማግኘት ተችሏል፡፡ ከተገኘው ገቢ የግብርና ምርቶች 73.6%፣ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ 51.54%፣ ማዕድን ዘርፍ 66.53% እዲሁም ኤሌክትሪክና ሌሎች ምርቶች 71.25% ዕቅድ አፈፃፀም ማሳየት ችለዋል በማለት በሪፖርቱ ገልጿል ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ክትትል የሚደረግባቸው የቅባት እህሎች፣ የጥራጥሬ ምርቶች፣ የብርዕና አገዳ ሰብሎች፣ የጫት ምርት፣ የቁም እንስሳት እና የደንና ደን ውጤቶች እንዲሁም የቁም እንሰሳት መኖ 811.13 ሚሊዮን ገቢ ለማግኝት ታቅዶ 699.11 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘት ችሏል ማለቱን ካፒታል ዘግቧል።
2580Loading...
07
አየር መንገዱ ከሰኔ 1 ጀምሮ ወደ አክሱም ዳግም በረራ ይጀምራል ተባለ ከመጪው ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ዳግም በረራ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ገለጸ። የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ፤ አየር መንገዱ ወደ አክሱም ዳግም በረራ ለመጀመር የሚያስችሉትን ቅድመ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል። በመሆኑም ከመጪው ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ታሪካዊ የቱሪዝም መዳረሻ ወደሆነችው አክሱም ከተማ ዳግም በረራ እንደሚጀመር ገልጸዋል። በረራው መጀመሩ ዓለም አቀፍ ቱሪስቶችና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ወደ ሥፍራው የሚያደርጉትን ጉዞ ለማሳለጥ እንደሚያስችልም ተናግረዋል። በረራው በሣምንት ሰባት ጊዜ የሚደረግ መሆኑንም መጠቆማቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው። አየር መንገዱ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በረራውን በቀን ወደ 3 እንደሚያሳድግም ገልጸዋል። የበረራው መጀመር የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን ለማሳለጥና ማኅበራዊ መስተጋብርን ለማጠናከር ያስችላል ብለዋል።
2812Loading...
08
50 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበት የሀገር ዉስጥ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ማስመረቁን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ አየር መንገዱ 5ዐ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መዋዕል ንዋይ ፈሰስ ያደረገበትን የአገር ዉስጥ መንገደኞች ተርሚናል በዛሬው ዕለት አስመርቋል ። በተርሚናሉ ላይ የተሰራዉ እድገት እና ማስፋፊያ የመሰረተ ልማቱን ይዞታ ከሁለት እጥፍ በላይ በማድረግ ወደ 25,750 ስኩዌር ኪሎሜትር ማሳደጉን ገልጿል ። ሲሲሲሲ በተሰኘዉ የቻይና ኩባንያ የተገነባው ተርሚናሉ 4 ከግዙፉ አዉሮፕላኖች ጋር ተገጣጣሚ የሆኑ መሳፈሪያ በሮችን ጨምሮ ከአለም አቀፍ የመንገደኞች ማስተናገጃ ህንፃ ጋር እንዲገናኝ ሆኖ ተገንብቷል ተብሏል። ካፒታል
2440Loading...
09
በተለያዩ ምክንያቶች አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የነዳጅ ማደያዎች በአዲስ መልክ ስራ ሲጀምሩ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኃይል የመሙላት አገልግሎት እንደሚሰጡ ተገለጸ በመዲናይቱ 132 የነዳጅ ማደያዎች ቢኖሩም በኮሪደር ልማቱ እና በሌሎች ችግሮች ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያቆሙት ከኮሪደር ልማት ግንባታው መጠናቀቅ በኋላ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኃይል የመሙላት አገልግሎት እንደሚሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡ አዲስ አበባን ስማርት ሲቲ ለማድረግ እየተሰራ ባለው የኮሪደር ልማት ስራ ሙሉ ለሙሉ የፈረሱ 5 የነዳጅ ማደያዎችና በሌላ ብልሽት ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ 7 ማደያዎች በሙሉ አቅማቸው ስራ ሲጀምሩ አሁን ላይ ሃገር ውስጥ እየገቡ ያሉትን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ታሳቢ እንደሚያደርጉ የቢሮው ምክትል ኃላፊ ቅድስት ስጦታው ተናግረዋል፡፡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በብዛት ሃገር ውስጥ እየገቡ መሆኑን ተከትሎ ለተሽከርካሪዎቹ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የሰለጠኑ ባለሙያዎች እንደሚመደቡ ነው ሃላፊዋ የገለጹት፡፡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በኢትዮጵያ ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ ያለውን የአየር ብክለት ለመቀነስ እንደሚረዱ የተናገሩት ሃላፊዋ ለነዳጅ ግዢ የሚወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ መጠን እንደሚቀንሰው አስታውቀዋል፡፡ በመዲናይቱ መግቢያ ካሉት ማደያዎች ያላግባብ ነዳጅ ሲወጣ እየተስተዋለ ነው ያሉት ምክትል የቢሮ ኃላፊዋ፤ ችግሩን ለመቅረፍ ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ እየተሰራ ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡ መናኸሪያ ሬዲዮ
2670Loading...
10
ዳሸን ባንክ የዓለም ባንክ አካል ከሆነው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) ሽልማት ተቀበለ። ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) የላቀ ዓለም አቀፍ የንግድ ፋይናንስ አገልግሎት በሚሰጡ ባንኮች ዘርፍ ለዳሸን ባንክ "Outstanding Global Trade Finance Program Issuing Bank" ሽልማት መስጠቱን ስናበስር በደስታ ነው ብሏል ባንኩ፡፡  ሽልማቱ የተሰጠው ኮርፖሬሽኑ  8ኛ ዓለም አቀፍ ጉባኤውን በስፔን ሀገር ባርሴሎና  ከተማ ባደረገው ጉባኤ ላይ ነው፡፡  በተያያዘ ዜና ዳሸን ባንክ በሀገሪቱ ለሚገኙ ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ተቋማት የፋይናንስ አገልግሎት የመስጠት አቅሙን ይበልጥ ለማሳደግና የፋይናንስ ተደራሽነትን በተሻለ ሁኔታ ለማቅረብ የሚያስችለውን ስምምነት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን  ጋር ተፈራርሟል፡፡  ስምምነቱን ሩዋንዳ ኪጋሊ ተገኝተው የፈረሙት የባንካችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው አለሙ ናቸው፡፡ ስምምነቱ ዳሸን ባንክ የፋይናንስ ተደራሽነትን እና አካታችነትን ይበልጥ እውን ለማድረግ አቅም የሚጨምርለት ሲሆን በጥቃቅን፣አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም በግብርና ላይ ለተሰማሩ ባለሀብቶች በተለይ በሴት ባለቤትነት የሚመሩትን ይበልጥ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል ።
2350Loading...
11
ከወጪ ንግድ ከ2.5 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ ከ 2.5 ቢሊየን በላይ የአሜሪከን ዶላር ገቢ ተገኝቷል። በዘጠኝ ወሩ 3.56 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ በተሰራው ስራ 2.511 ቢሊዮን ዶላር ወይም 70.49 በመቶ ገቢ ማግኘት ተችሏል፡፡ ከተገኘው ገቢ የግብርና ምርቶች 73.6%፣ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ 51.54%፣ ማዕድን ዘርፍ 66.53% እዲሁም ኤሌክትሪክና ሌሎች ምርቶች 71.25% ዕቅድ አፈፃፀም አሳክተዋል፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ክትትል የሚደረግባቸው የቅባት እህሎች፣ የጥራጥሬ ምርቶች፣ የብርዕና አገዳ ሰብሎች፣ የጫት ምርት፣ የቁም እንስሳት እና የደንና ደን ውጤቶች እንዲሁም የቁም እንሰሳት መኖ 811.13 ሚሊዮን ገቢ ለማግኝት ታቅዶ 699.11 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡ ይህም የዕቅዱን 86.19 በመቶ ያሳካ ሲሆን ከ2015 በጀት አመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 629.23 ሚሊዮን ጋር ሲነፃፀር 69.88 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ (የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር)
2320Loading...
12
ቴክኖ ሞባይል ካሞን 30 ፕሮ 5G የተሰኘ የስልክ ቀፎ ለኢትዮጵያ ገበያ ይፋ አደረገ ቴክኖ ሞባይል በቅርቡ በባርሴሎናው ዓመታዊ የቴከኖሎጂ አውደ ርዕይ ላይ ይፋ ያደረገውን ካሞን 30 ፕሮ 5G የተሰኘ ሞዴል ለኢትዮጵያ ገበያ ይፋ አደረገ። አዲሱ ስልክ ከጃፓኑ ሶኒ የካሜራ ሴንሰር ቴከኖሎጂን እንዲሁም የኩባንያው ምርምር ውጤት የሆኑ የረቀቁ የቴከኖሎጂ ግብዓቶችን በመጠቀም የተመረተ መሆኑን ኩባንያው ለአዲስ ዋልታ በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል። የቴክኖ ሞዴል ተገጠመለት የሶኒ (SONY) ምርት የሆነውን ዘመናዊ ሴንሰር (Sony IMX890) በመጠቀም በማንኛውም አይነት ሁኔታ እና የብርሃን መጠን ጥራት ያላቸው ፎቶዎችን ማንሳት እንደሚያስችልም ተጠቁሟል። አዲሱ ካሞን 30 ፕሮ 5G ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እየሰጠ መቆየት የሚችል ባትሪ፣ ማራኪ ቅርጽ እና ውበት ያለው የመጨረሻው የቴከኖሎጂ ውጤት የሆኑ የሞባይል ስልክ ግብዓቶችን አካቶ መመረቱም ነው የተገለጸው፡፡ ቴክኖና ሶኒ ኩባንያዎች በጋራ በስማርት ስልክ ኢንዱስትሪው የመጀመሪያ ነው የተባለለትን ፖላርኤስ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የቪድዮ ኢሜጂንግ ስርዓቱን በማዘመን እና እንከን የለሽ በማድረግ የካሜራ ቴከኖሎጂውን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ምድረጋቸውም ተመላክቷል። በተለያዩ ዘርፎች የሚፈለጉትን አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር በማቀናጀት ለተለያዩ ግልጋሎቶች የሚውሉ የፈጠራ ውጤቶችን በትኩረትና በዘርፉ ፋና ወጊ ኩባንያዎች ጋር እየሰራ ይገኛልም ተብሏል። ኩባንያው በአዲስ አበባ ከተማ ጎሮ አይሲቲ ፓርክ ባስገነባው ዘመናዊ ፋብሪካ የሚገጥማቸውን ዘመናዊ የሞባይል ስልኮች ወደተለያዩ ሀገራት በመላከ የውጭ ምንዛሬ እያስገኘ እንደሆነም ተነግሯል፡፡
2990Loading...
13
#BrewingGrowth In the face of growing competition, BGI Ethiopia is doubling down to reclaim its market leadership in the brewing industry. CEO Herve Milhade revealed that the company plans to expand production capacity to an impressive 10 million hectolitres by 2028. This ambitious growth is supported by investments ranging between 60 million and 100 million euros annually to upgrade infrastructure and enhance employee skill sets. Read More Source: Addisfrtune @Ethiopianbusinessdaily
3010Loading...
14
የኢትዮጵያ ሽሮ ወጥ ደረጃ እየተዘጋጀለት መሆኑ ተገለጸ የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት FOOD PRODUCTS IN GENERAL የቴክኒክ ኮሚቴ (TC 91) የኢትዮጵያ ሽሮ ወጥ ደረጃን በማዘጋጀት ላይ ይገኛል ። ደረጃውን አሳታፊ በሆነ መንገድ እያዘጋጀ እንደሆነ የገለጸው ኮሚቴው የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ አዲስ አበባና ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚ/ር ፣ የተስማሚነት ምዘና ተቋማት፣ የተለያዩ ማህበራትና አምራቾች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በደረጃ ዝግጅቱ ተሳታፊ መሆናቸውን ገልጿል ። የደረጃው መዘጋጀት በንግድ ስርአት ውስጥ ለአምራቾችና ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ጥራትን ከማረጋገጥ አንጻር ከሚኖረው ጠቀሜታ ባሻገር ሀገር በቀል የሆነው የሽሮ ወጥ አለም አቀፍ እውቅና እንዲኖረው የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል። ደረጃው ሲጠናቀቅ በኢንደስትሪ የታገዘ ምርትን በስፋት ለማምረትና ሰፉፊ ተጠቃሚዎችን የሚያስተናግዱ ተቋማት ጥራቱን የጠበቀ ምርት እንዲያቀርቡ የሚያግዝ እንደሚሆን ይጠበቃል ። የደረጃ ዝግጅት ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝና በቅርብ ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለውሳኔ እንደሚቀርብ ኮሚቴው ገልጿል ። ምንጭ: የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት
2850Loading...
15
አዲሱን የኤርፖርት ሲቲ ግንባታ ዲዛይን የሚያከናውን የአማካሪ ድርጅት መረጣ እስከ መጪው መስከረም ይጠናቀቃል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱን የኤርፖርት ሲቲ ግንባታ ለማስጀመር ዝርዝር ዲዛይኑን የሚያከናውን አማካሪ ድርጅት መረጣ እስከ መጪው መስከረም እንደሚጠናቀቅ አስታወቀ። አየር መንገዱ በፍጥነት እያደገ የመጣውን የደንበኞቹን ቁጥር ታሳቢ በማድረግ ዘመናዊና ግዙፍ የኤርፖርት ከተማ ግንባታ እንደሚያከናውን ከ4 ዓመት በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ከቢሾፍቱ ከተማ ወጣ ባለ ሥፍራ ላይ የሚገነባው ይህ ፕሮጀክት፥ የካርጎ ሎጂስቲክ ማዕከል፣ ዘመናዊ ሆቴሎችና ከቀረጥ ነጻ የተለያዩ የግብይት ስፍራዎች እንደሚኖረውም ተገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምክንያቶች በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ሳይጀመር ቆይቷል። የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት እስከ 25 ሚሊዮን ያህል ብቻ መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ያነሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ ሆኖም የደንበኞች ቁጥር በመጪዎቹ ጥቂት ዓመታት በእጥፍ እንደሚያድግ ይጠበቃል ብለዋል። በመሆኑም የአየር መንገዱን እድገት እና የመንገደኞችን ቁጥር መጨመር ታሳቢ ያደረገ ግዙፍ አውሮፕላን ማረፊያ (ኤርፖርት ሲቲ) መገንባት የግድ መሆኑን በማመን ወደ ስራ መገባቱን ጠቅሰዋል። ከቢሾፍቱ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ ስፍራ የሚገነባውን አዲሱን ፕሮጀክት ግንባታ ለመጀመርም የተለያዩ የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል። ለአብነትም የኤርፖርት ሲቲ ግንባታውን ዲዛይን የሚሰሩ ሁለት አማካሪ ድርጅቶችን ለመቅጠር ይፋዊ ጨረታ መውጣቱን ጠቅሰው፥ የአማካሪዎች መረጣ እስከ መጪው መስከረም እንደሚጠናቀቅ አመላክተዋል። ፕሮጀክቱ ከዘገየባቸው ምክንያቶች አንዱ ኤርፖርት ሲቲው በሚገነባበት ቦታ የሚኖሩ አርሶ አደሮችን ሁኔታ ለማስተካከል ረጀም ጊዜ በመውሰዱ ነው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት አርሶ አደሮቹ ኑሯቸውን የሚመሩበትን ስራ ለመፍጠር የሚያስችል ጥናት መከናወኑን ገልጸዋል። የአርሶ አደሮቹን ፕሮጀክት ወደ ተግባር ለማስገባትም የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን የታወቀ ሲሆን፥ የፕሮጀክት ዲዛይን የሚሰራ አማካሪ እየመረጥን ነው ብለዋል። አዲስ የሚገነባው ኤርፖርት ሲቲ ለአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክና ለሞጆ ደረቅ ወደብ ቅርብ በመሆኑ ትልቅ የኢንዱስትሪያል ሎጂስቲክ ማዕከል እንደሚሆንም ተገልጿል። የኤርፖርት ሲቲ ግንባታ ሲጠናቀቅ በዓመት 100 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም እንዳለውም ነው የገለጹት፡፡(ENA)
3251Loading...
16
Media files
2860Loading...
17
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በአቃቂ ግዙፉን ዋና መስሪያ ቤት ግንባታ በ 1.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ሊገነባ ነዉ መንግስታዊዉ ነዳጅ አቅራቢ የሆነዉ ድርጅቱ 1.6 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚያደርግበትን ግዙፉን ህንፃ ለመገንባት የኮንትራት ዉል ስምምነት ማድረጉ ታዉቋል። በአቃቂ የሚገነባው 2B+G+14 ስማርት የችርቻሮ ጣቢያ ዋና መስሪያቤት በ 24 ወራት ዉስጥ ለማጠናቀቅ ዕቅድ መያዙን ካፒታል ሰምቷል። ኢኢአይጂ ከተባለው ተቋራጭ ጋር የዉል ስምምነት ያደረገው የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ አማካሪ ነዉ። (capital)
2970Loading...
18
አዋሽ ባንክ ለ3ኛ ጊዜ ከኢትዮጵያ ምርጥ ባንክ በመባል መመረጡ ተገለፀ። ግሎባል ፋይናንስ ማጋዚን ለ31ኛ ጊዜ የምርጥ ባንኮችን ዝርዝር ይፋ ባደረገው መሠረት ከ36 የአፍሪካ አገራት ውስጥ ከተመረጡ ባንኮች መካከል አዋሽ ባንክ አንዱ ሆኗል። የምርጥ ባንኮች ልየታ የተደረገው በተለያዩ መስፈርቶች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ የባንኮቹ ትርፋማነት፣ የሀብት ዕድገት፣ተደራሽነት እና የመሳሰሉት ከመስፈርቶቹ መካከል የተካተቱ ናቸው። በዚህ መሠረት አዋሽ ባንክ ከ36 አገራት ከተመረጡ የአፍሪካ ባንኮች መካከል አንዱ ሆኖ መመረጡን እና ከኢትዮጵያ ደግሞ ብቸኛው ባንክ መሆኑን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው ገልጸዋል። በዚህኛው አመት በተካሄደው ምርጫ ከ1መቶ50 በላይ አገራት የሚሰሩ ባንኮች የተካተቱበት መሆኑም ነው የተገለጸው። አዋሽ ባንክ በአሁኑ ጊዜ ከ9መቶ38 በላይ ቅርንጫፎች በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች እንዳለው የተገለፀ ሲሆን ከ12.1 ሚሊየን በላይ ደንበኞችንም ማፍራቱ ተነግሯል። የባንኩ ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ2መቶ15 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱም ተገልጿል። ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የተሰጠው የብድር መጠንም ከብር 1መቶ78 ቢሊየን ብር በላይ መሆኑንም ነው ያስታወቁት። የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንደገለፁት ለባንኩ የሚሰጠው ዕውቅናና የሽልማት ስነ-ስርዓት የአለም ገንዘብ ድርጅት እና የአለም ባንክ በዋሽንግተን ዲሲ በኦክቶበር 2024 በሚያደርጉት ጉባኤ ወቅት እንደሚከናወን አስታውቀዋል።(ethiofm)
2700Loading...
19
የፌደራል መንግሥት በኤሌክትሪክ እና በውሃ አገልግሎት ላይ ቫት የሚጥል ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ አቀረበ የኤሌክትሪክ እና የውሃ አገልግሎት በገደብ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እንዲከፈልባቸው የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ። ከታክሱ ነጻ የሚሆኑት የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ ከሚወሰን በታች የኤሌክትሪክ እና ውሃ ፍጆታ ያላቸው እንደሆኑ ተገልጿል። አዋጁ ሲጸድቅ ለሁለት አስርት ዓመታት በስራ ላይ ቆየውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ እና ከዛ በኋላ እሱን ለማሻሻል ሁለት ጊዜ የወጡትን የማሻሻያ አዋጆች ሙሉ በሙሉ የሚሽር ነው ተብሏል። “አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ያለበትን ወጪ ለማርገብ ሲባል” የኤሌክትሪክ እና የውሃ አገልግሎት ከታክሱ ነጻ ተደርገው እንደነበር ሲገለፅ ረቂቁ “የተጨማሪ እሴት ታክስ ከሚታይበት ጉድለት አንዱ እና ዋነኛው በርካታ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ከታክሱ ነጻ መደረጋቸው ነው” ይላል። በረቂቅ አዋጁ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ በማድረግ የተሰጠውን “ልዩ መብት” እንደገና በመፈተሽ ማስተካከያዎች መደረጋቸውን ማብራሪያው ይገልጻል። ከታክስ ነጻ ተደርገው አሁን ታክስ እንዲከፈልባቸው ከተደረጉ አግልግሎቶች መካከል የውሃ እና ኤሌክትሪክ እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎቶች ይገኙበታልም ተብሏል። በስራ ላይ ያለው አዋጅ የኤሌክትሪክ፣ የኬሮሲን [ናፍጣ] እና የውሃ እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎትን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እንዲሆኑ እድርጎ ነበር። ይህን አዋጅ የሚሽረው አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ግን የውሃ የኤሌክትሪክ፣ የውሃ እና የትራንስፖርት አገልግሎቶች በገደብ ታክስ እንዲከፈልባቸው አድርጓልም ነው የተባለው። ምንጭ፦ BBC Amharic
2510Loading...
20
Ethiopia Vies to Host Prestigious Logistics Congress Read More 👉🏾 https://onestop.et/ethiopia-vies-to-host-prestigious-logistics-congress/
2630Loading...
21
Ethio-Djibouti Railway Marks New Era with Handover Ceremony Read More 👉🏾https://onestop.et/ethio-djibouti-railway-marks-new-era-with-handover-ceremony/
3330Loading...
22
#LocalNews | EIH, Toppan Gravity to transform security printing industry Ethiopian Investment Holdings (EIH), a recently established sovereign wealth fund (SWF) that has teamed up with a dominant global security printing firm, is making its first greenfield investment. By 2026, the initiative aims to transform the security printing industry. The facility called Toppan Gravity Ethiopia (TGE), established by Toppan Gravity, EIH, Berhanena Selam Printing Enterprise, and Education Materials Production and Distribution Enterprise, both of which are under EIH, will be equipped with cutting-edge technology and stringent security measures to produce high-quality passports, ID cards, and banking cards, setting new standards for security and integrity. Read More Source: Capitalethiopia @Ethiopianbusinessdaily
3330Loading...
23
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የሚያዚያ ወር ሀገር አቀፍ የዋጋ ግሽበቱ 23.3 በመቶ ሆኖ መመዝገብን አስታውቋል የዋጋ ግሽበቱ በመጋቢት ወር ከነበረበት 26.2 በመቶ ወደ 23.3 በመቶ በመሆን ቅናሽ አሳይቷል ብሏል። በወሩ ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ምግብ ነክ ዕቃዎች 27 በመቶ እንዲሁም ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ደግሞ 18 በመቶ ድርሻ መያዛቸዉ ታዉቋል ። Source: Capitalethiopia @@Ethiopianbusinessdaily
3110Loading...
24
ኩዌት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን በሀገሯ ለማሰራት የሰራተኛ ምልመላ ልትጀምር ነው ተባለ ኢትዮጵያ እና ኩዌት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በኩዌት ሀገር የስራ አድል አንዲያገኙ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነቱን ለማጠናቀቅ የመጨረሻው ሂደት ላይ መሆኑን የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱ በዚህ ወር መጨረሻ ይፈረማል የተባለ ሲሆን ስምምነቱ የሰራተኞችን መብት፤ አሰሪዎች የስራ ውል በሚያቋርጡበት ጊዜ ሰራተኞች ስለሚያገኙት ክፍያ፤ የሰራተኞች የሳምንት፣ የአመት እረፍት እና ተያያዥ ስምምነቶችን የያዘ መሆኑ ተነግሯል፡፡ የሰራተኛ ምልመላው ስምምነቱ እንደተፈረመ ይጀመራል የተባለ ሲሆን ስምምነቱ ኩዌት ያጋጠማትን የሰራተኞች እጥረት ይቀርፋልም ነው የተባለው፡፡ @TikvahethMagazine
3983Loading...
25
The Ethiopian Commodity Exchange (ECX) is considering adding salt to its list as the 24th tradable commodity. Executives are currently conducting feasibility studies and preparing sales contracts. Read More Source: Addis Fortune @Ethiopianbusinessdaily
3530Loading...
26
Media files
10Loading...
27
#FeatureNews | Chamber calls for government attention over Addis Ababa Exhibition Center The Addis Ababa Chamber of Commerce and Sectoral Associations (AACCSA) conducted a design study seven years ago to reconstruct the Addis Ababa Exhibition Center, a facility with a history of over 40 years. However, due to a lack of attention from the government, the project has not yet commenced. The AACCSA has recently announced that none of the proposed projects for the exhibition center have been included by the government, despite its many years of service. The Chamber of Commerce attributes the delay and bureaucratic issues to government fluctuations and problems. They have called for attention to be given to this matter and have expressed frustration with the system. In the past few months, the Supreme Court has consistently ruled in favor of the plaintiffs’ motion to dismiss the case. Read More Source: Capitalethiopia @Ethiopianbusinessdaily
3430Loading...
28
በአፍሪካ ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ለሚደረገው ፈጣን ሽግግር ኢትዮጵያ ማሳያ ናት ተባለ ** ኢትዮጵያ በነዳጅ ከሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ይልቅ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን የመጠቀም ልምድ እንዲያድግ የወሰደችው እርምጃ በአፍሪካ ጥሩ ምሳሌ መሆኑን ግሪን ቴክኒካ የተሰኘ የዜና አውታር አስታውቋል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚሰሩ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ዘገባዎችን የሚሰራው ግሪን ቴክኒካ፤ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎችን ቁጥር 148 ሺህ ለማድረስ ማቀዷን ዘግቧል። አገሪቱ ባለፉት 2 ዓመታት ብቻ በሀገሪቱ ያሉ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎች 100 ሺህ እንዲደርሱ ማድረጓ ለአረንጓዴ ልማት ምን ያህል ቁርጠኛ መሆኗን ያሳያል። በኢትዮጵያ ጎዳናዎች ከሚነዱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መካከል 10 በመቶ ያህሉ በሀገር ውስጥ የተገጣጠሙ መሆናቸው "አስደሳች ዜና ነው" ሲል ገልጾታል ተቋሙ፡፡ ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለሚያመርቱ ኩባንያዎች ልዩ ድጋፍ እንደምታደረግ ይፋ ማድረጓን ተከትሎ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች ቁጥር እያደገ መምጣቱን በዘገባው ተመላክቷል።
3080Loading...
29
#FeatureNews |Excise stamps expected to curb illegal activities in the beverage sector According to reports, the upcoming implementation of excise stamps is anticipated to help eliminate illegal players in the beverage industry. In alignment with the Excise Tax Proclamation 1186/2020, the Ministry of Finance (MoF) has recently drafted a directive for the management system of excise stamps, which will be applied to beverage products like bottled water and alcohol. The preamble of the directive states that its objectives are to safeguard public health and safety, combat illicit trade, and ensure the integrity of excise tax collection systems. Read More Source: Capitalethiopia @Ethiopianbusinessdaily
3030Loading...
30
ባንኩ ለአምራች ኢንዱስትሪው 30 ቢሊየን ብር ብድር መስጠቱን ገለጸ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 30 ቢሊየን ብር ለአምራች ኢንዱስትሪው ብድር መስጠቱን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አስታውቋል። ከኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ጎን ለጎን "የግል ኢንቨስትመንት እና አስቻይ ሁኔታዎች" በሚል የፓናል ውይይት ተካሂዷል። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ባንኩ መንግሥት ቅድሚያ በሚሰጣቸው የትኩረት መስኮች ላይ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም ለአምራች ኢንዱስትሪው ከፍተኛ ትኩረት በማድረግ በዝቅተኛ ወለድ ብድር በመስጠት የዘርፉን ተዋንያን እየደገፈ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ባንኩ ከዚህ ቀደም በከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ እንደነበር ገልጸው÷ መንግሥት በወሰደው እርምጃ ከነበረበት ችግር ማውጣት መቻሉን ጠቁመዋል። አሁን ላይ ባንኩ በዓመት እስከ 6 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ትርፍ እያገኘ መሆኑን፣ ካፒታሉ 38 ቢሊየን ብር መድረሱንና ለአንድ ፕሮጀክት እስከ 9 ቢሊየን ብር ማበደር የሚችልበት አቅም መፍጠሩን ተናግረዋል። በዘጠኝ ወራት ውስጥ 44 ቢሊየን ብር ብድር ማጽደቁን ገልጸው÷ ከዚህም 30 ቢሊየን የሚሆነው ለአምራች ዘርፉ የተሰጠ መሆኑን አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ በበኩላቸው÷ንግድ ባንክ በከፍተኛ ሁኔታ አምራች ዘርፉን እየደገፈ የሚገኝ ተቋም ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
3320Loading...
31
ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፉ ሀብት ቢኖራትም አውጥታ መጠቀም አለመቻሏ ብዙ እያሳጣት ነው ተባለ፡፡ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አዘጋጅቶ እያተደረገ ባለው ኢትዮጵያ ታምርት ኤግዚቢሽን ላይ ዘርፉን ለማሳደግ ምክክሮች ጎን ለጎን እየተደረገ ሲሆን በተለይም ከኃይል አቅርቦትና ተደራሽነት እንዲሁም ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፉ ያላት ሀብት አውጥቶ ለገብያ ከማቅረብ አኳያ ያለባት ክፍተት ተነስቷል፡፡ የማዕድን ሚኒስትር አቶ ሃብታሙ ተገኝ እንዳሉት ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፉ ሀብት ቢኖራትም አውጥታ ግን እየተጠቀመችበት አይደለም፡፡ እያወጣች የምትጠቀምባቸው ውስን የማዕድን ሀብቶችም ቢሆኑ እሴት እየጨመረች ከመላክ ይልቅ በጥሬ እቃ ነው የምትልከው ያሉት ሚንስትሩ ይህ ነገር ከፍተኛ ገቢ እያሳጣ ነው ብለዋል፡፡ (ሸገር)
3400Loading...
32
ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከአሳ ሀብት ሽያጭ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ብቻ ገቢ ማግኘቷ ተነገረ ኢትዮጵያ በዘንድሮው የ2016 በጀት አመትና ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለሱዳን ገበያ ካቀረበችው የአሳ ምርት 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ብቻ ገቢ ማግኘቷን የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዮት አስታውቋል።በኢንስቲትዮቱ የማህበራዊ ኢኮኖሚክስ እና እሴት ሰንሰለት አስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ሳህሉ ሙሉ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ባለፋት ዘጠኝ ወራት ኢትዮጵያ የተወሰነ መጠን የአሳ ስጋን ለሱዳን ገበያ ማቅረብ ችላለች። በሱዳን ድንበር አካባቢ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት በዘጠኝ ወራት ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ከአሳ ሽያጭ ጥሩ የሚባል ገቢን ማግኘት እንዳልቻለች አስረድተዋል።በመዳረሻ ገበያ ላይ የተስተዋለውን የፀጥታ ችግር ተከትሎ በታቀደው ልክ ምርቱን ለውጪ ገበያ ማቅረብ አልተቻለም ያሉት ዶክተር ሳህሉ በበጀት አመቱ ዘጠኝ ወራት 31 ቶን የአሳ ምርት ብቻ ወደ ጎረቤት ሀገር ሱዳን ተልኳል ብለዋል። ኢትዮጵያ ከዘርፋ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ ለማድረግ በቀጣይ የአሳ ምርት በብዛት ወደማይገኝባቸው ሀገራት ምርቱን ለመላክና አዳዲስ የገበያ መዳረሻ ሀገራትን የማፈላለግ ስራ እንደሚሰራ ተገልጿል።በቀጣይ ይህ ችግር ሲቀረፍ ምርቱን ወደ ውጪ ሃገራት በመላክ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንድትሆን ለማድረግ ጥረት ይደረጋል። በዘርፉ የምርት መጠን ማነስ የሚስተዋል በመሆኑም በዚሁ ስራ ላይ አሉታዊ ጫና ማሳደሩን አያይዘው ጠቁመዋል፡፡ ዳጉ_ጆርናል
3020Loading...
33
መርከቧ ላሙ ወደብ ደርሳለች! "ዓባይ" የተሰኘችው የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ቅዳሜ'ለት 60 ሺህ ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ በመጫን ከአዲሷ የኬንያ ወደብ ላሙ ደርሳለች። ከኢትዮጵያ ንግድ መርከቦች ላሙ ወደብ በመድረስ፣ "ዓባይ" የመጀመሪያዋ ናት። ላሙ ወደብ ላይ የተራገፈው ማዳበሪያ በጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ሞያሌ ይጓጓዛል። መርከቧ ከወደቡ ስትደርስ፣ ግብርና ሚንስትር ግርማ አመንቴ የመሩት ልዑካን ቡድን ተቀብሏታል። ኢትዮጵያ ላሙ ወደብን ለመጠቀም ዝግጁ መሆኗን ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ ስትገልጽ መቆየቷ አይዘነጋም። ኢትዮ ኤፍ ኤም
3171Loading...
34
Last week, officials teamed up to lay out a 55 million-dollar industrial security printing plant at Bole Lemi Industrial Park. Partnering with Japanese multinational Toppan Gravity, the plant is expected to embark on passport printing, with over five million passports printed annually at full throttle. Read More Source: Addis fortune @Ethiopianbusinessdaily
2880Loading...
35
በቻይና የተገነባው ግዙፉ የኢትዮጵያ-ጁቡቲ የባብር መስመር ከግማሽ ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን እና 9.5 ሚሊዮን ቶን ጭነት ማጓጓዝ መቻሉ ተነገረ የኢትዮጵያ -ጁቡቲ የባቡር መስመር የመንገደኞች እና የጭነት አገልግሎት የንግድ ስራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ 9.5 ሚሊዮን ቶን ጭነት ያላቸው 7,700 የእቃ ማጓጓዣ ባቡሮች አገልግሎት መስጠት መቻላቸው ታዉቋል። በቻይና የተገነባዉና ሁለቱ ሀገራትን የሚያገናኘዉ የባቡር መንገዱ 752 ኪሎሜትር ርዝመት ያለዉ ሲሆን ስራ ከጀመረበት ዓመታት ወዲህ 2,500 የመንገደኞች ባቡሮችን እና  7,700 የጭነት ባቡሮች ማስተናገድ መቻሉንና 680 ሺህ መንገደኞች መጓጓዛቸዉን ካፒታል ያገኘው መረጃ ያመለክታል ። የአዲስ አበባ ጅቡቲ የባቡር መስመር ሥራ ከጀመረ ወዲህ የጅቡቲ ወደቦች የትራንስፖርት መጠን 20 በመቶ ገደማ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን የንግድ ትራንስፖርት ገቢም 11.3 ቢሊዮን ብር  በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ መገኘቱን የባቡሩ ማኔጅመንት ቡድን አስታውቋል ። መረጃዎች እንደሚያመላክቱት የባቡር መስመሩ የተገነባው ከቻይና ኤክስፖርትና ኢምፖርት ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በ4 ቢሊዮን ዶላር ብድር ነዉ። እ.ኤ.አ. በ2011 ከአዲስ አበባ ወደ ጁቡቲ የሚደረገው የባቡር ኮንትራት ግንባታ በሁለት የቻይና መንግሥታዊ ኩባንያዎች ማለትም በቻይና ምድር ባቡር ግሩፕ (CREC) እና በቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የተጀመረ ሲሆን እኤአ በጃንዋሪ 2018 የመጓጓዣ አገልግሎት መጀመሩ ይታወቃል ። ካፒታል
3200Loading...
36
Meet the Businesses Turning Waste into Opportunity in Addis Ababa Research indicates that the waste Addis Ababa produces is projected to double by 2030. However, a growing number of enterprises are seeing this challenge as an opportunity, viewing waste as a valuable resource rather than a burden. Read More Source: shegahq @Ethiopianbusinessdaily
3530Loading...
37
በአማዞን ቤት ፡ እያንዳንዱ መፅሀፍ ሲሸጥ ደወል ይደወል ነበር ። 🔔 እ.ኤ.አ. በ 1995 ላይ  በትንሽ ጋራጅ ውስጥ አማዞንን  የመሰረተ ጊዜ ፡  የሚጠቀሙበት ሰርቨር ብዙ የኤሌትሪክ ሀይል ስለሚፈልግ ፡ በስራ ሰአት ሚስቱ የፀጉር ማድረቂያ መጠቀም ፡ ወይም በቫኪዩም ክሊነር ቤት ማፅዳት አትችልም ነበር ። .... ይህን ድርጅት ከመሰረቱ ከቀናት በኋላ ቢዝነሱን  ሰፋ አድርገው ሀያ የሚሆኑ ሰራተኖችን ቀጥረው ፡ በዌብሳይታቸው ገብቶ መፅሀፍ የሚገዛ ሰው መጠበቅ ጀመሩ ። እና በዛን ወቅት ወደ አማዞን ዌብሳይት  የሆነ ሰው ገብቶ አንድ መፅሀፍ ሲታዘዝ ፡ በአማዞን ቤት ደስታ ይሆናል ። አስገራሚው ነገር አማዞን ሽያጭ በጀመረባቸው በነዚህ ሳምንታት ፡ አንድ መፅሀፍ ሲታዘዝ ፡ ደወል ይደወላል 🔔 ይሄኔ የአማዞን ሰራተኞች የሆነ ሰው በኦንላይን መፅሀፍ እንደገዛቸው ያውቃሉ ፡ እና ኮምፒውተሩን ከበው ፡ ይህን ከአማዞን መፅሀፍ ያዘዘውን ሰው ስም ለማየት ኮምፒውተሩን ይከባሉ ። ...... ማለትም  በቀን ውስጥ አስር ጊዜ ሽያጭ ከፈፀሙ ፡ አስር ጊዜ ደወል  ይደወላል ። ሆኖም አማዞን ከሚጠበቀው በላይ ብዙ ትእዛዞች መቀበል በመጀመሩ  አንድ መፅሀፍ ሲሸጥ ደወል መደወል ያቆመው በሳምንታት ውስጥ ነው ። .... ዛሬ ላይ ያ ፡ አንድ መፅሀፍ ሲሸጥ ደወል ይደውል የነበረው አማዞን በአንድ ቀን ከስድስት ሚሊዮን በላይ የተለያዩ እቃዎችን ይሸጣል ። እንደድሮው ቢሆን በቀን ውስጥ ስድስት ሚሊየን ጊዜ ደወል ይደወል ነበር ማለት ነው  ። .... እያንዳንዱን ስኬቱን ደወል በመደወል ያበስር የነበረው አማዞን ፡ አንድ መፅሀፍ ሲሸጥ በደስታ ያጨበጭብ የነበረው አማዞን ፡ ዛሬ ላይ ከ1,525,000 በላይ ጊዜያዊና ቋሚ ሰራተኞችን ቀጥሮ ያሰራል ። እንደምንም በቆጠባት አስር ሺህ ዶላር ቢዝነስ የጀመረው ጄፍ ቤዞፍ አሁን 197 ቢሊየን ዶላር ሀብት በስሙ አስመዝግቧል ። ...... በያንዳንዱ ትናንሽ ስኬትህ ተደሰት ፡ በያንዳንዱ እርምጃህ እንደጄፍ ቤዞስ በደስታ  ደወልህን አንሳ 🔔 Via - Wasihune
4111Loading...
38
ይህንን ያውቃሉ 🤔 በእስያዊቷ ሀገር ታይላንድ መገበያያ ገንዘቧን መሬት ላይ በመጣል የረገጡት እንደሆነ ከፍተኛ ወንጀል ነው ምክንያቱም የረገጡት ንጉሣቸውን እንጂ ወረቀት ገንዘቡን ብቻ አይደለም ይሄ የሆነው በሀገሪቱ ገንዘብ ላይ የተቀመጠው የሀገራቸው ንጉስ ምስል ስለሆነ ነው ገንዘብ መርገጥ ማለት በታይላንድ የሀገሪቱን ንጉስ ክብር ዝቅ እንደ ማድረግ እንደ መቃወም ይቆጠራል በዚህም ቅጣት ያስከትላል ።😇
3761Loading...
39
Ethiopia: Financial Sector’s Loan Portfolio Reaches Birr 2.3 Trillion Governor Mamo Mehretu of the National Bank of Ethiopia (NBE) addressed the ongoing financial sector reforms at the 7th Annual East African Finance Conference in Addis Ababa. He revealed a significant rise in the loan portfolio of Ethiopian financial institutions, now standing at Birr 2.3 trillion. Read More Source: 2Merkato @Ethiopianbusinessdaily
4030Loading...
40
ሪል ስቴቶች ከፍተኛ ብክለት እያደረሱ ነው ሲል የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ገለፀ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ሪል ስቴቶች ከፍተኛ ብክለት እያደረሱ መሆኑን የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ገለጸ። በባለስልጣኑ የአካባቢ ጥበቃ ህግ ተከባሪነት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ጉደታ ብክለትን በመከላከል ረገድ የተቋማት ቅንጂታዊ አሰራር ውስን መሆኑን ለአራዳ ተናግረዋል። ይህም በመከላከል ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን ጠቅሰው በዚህ ሳቢያ ሪል ስቴቶች ከፍተኛ ብክለት እያመነጩ ነው ብለዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ በመዲናዋ ሪል ስቴቶችና ህንጻዎች ሲገነቡ የቆሻሻ ውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች እንኳን የላቸውም ነው ያሉት። ሪል ስቴቶቹ ቆሻሻ ፍሳሽን የሚያክሙበት ቀርቶ አስመጥጦ ለመውሰድ የሚያከማቹበት መንገድ አልያም፥ የውሃና ፍሳሽ መገናኛ መንገዶች እንደሌላቸውም አስረድተዋል። ሪል ስቴቶች የሚፈልጉት ህንጻውን ገንብቶ ቤቱን መሸጥ በመሆኑ፥ ሪል ስቴቶችን ጨምሮ ሆስፒታሎችና የተለያዩ የመንግስትና የግልም ተቋማት የተበከለ ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዞች እንደሚለቁ ጠቅሰዋል። የመንግስት ተቋማት ፈቃድ ሲሰጡ ከስራ እድል ፈጠራ እና ከምጣኔ ሃብታዊ ፋይዳው አንጻር እንጅ የሚያደርሰውን ብክለት ታሳቢ ያደረገ አለመሆኑንም ነው የገለጹት። Arada_Fm
4312Loading...
Photo unavailableShow in Telegram
ለሥራ ወደ ውጭ አገሮች ለሚሄዱ ከ500 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የመድን ዋስትና መስጠት ተጀመረ ወደ ውጭ አገሮች በሥራ ስምሪት ለሚጓዙ ከ500 ሺሕ በላይ ለሚደርሱ ኢትዮጵያውያን የሕይወት የመድን ሽፋን አገልግሎት ለመስጠት፣ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር ለሁለት ዓመታት ውል የተፈራረመው ኒያላ ኢንሹራንስ አገልግሎቱን በይፋ መጀመሩን ገለፀ። በዚህም ኒያላ ኢንሹራንስ ኩባንያ ወደ ተለያዩ አገሮች ተጉዘው የሥራ ቅጥር ውል ለሚፈጽሙ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ለሚደርስባቸው የሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የአዕምሮ መታወክና ሌሎች ተጓዳኝ ጉዳቶችን የሚሸፍን መሆኑን ሪፖርተር አስነብቧል። ለእነዚህ የመድን ሽፋኖችም ተጠቃሚዎች በዓመት እንዲከፍሉ የሚጠበቅባቸው 500 ብር ብቻ መሆኑ ሲጠቆም ይህ የመድን ሽፋን በአንድ ክፍያ ሰው እስከ 1.35 ሚሊዮን ብር ድረስ የሕይወት መድን ሽፋን አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑንም ተነግሯል። TikvahethMagazine
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በመላው ሃገሪቱ የነዳጅ ማደያ ፍቃድ ላልተወሰነ ጊዜ መታገዱ ተገለጸ አሁን ላይ የነዳጅ ማደያ ማስፋፊያ ፍቃድ መታገዱን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡ መንግስት የነዳጅ ማደያ ማስፋፊያን የትኩረት አቅጣጫ አድርጎ ሲሰራ መቆየቱን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ናቸው የተናገሩት፡፡ መንግስት የነዳጅ ማደያዎችን በሀገር ውስጥ ለማስፋፋት በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሯ አሁን ላይ ግን ባልተፈለገ አቅጣጫ እየሄደ መሆኑን ባለስልጣኑ በማረጋገጡ ፍቃዱ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲታገድ ተደርጓል ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ባለስልጣኑ ጥናት እያደረገ እንደሚገኝ የገለፁት ወ/ሮ ሳህረላህ የማደያዎች ፍቃድ አሰጣጥ እና ተደራሽነት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች መፍትሄ ካገኙ በኋላ ፍቃድ የመስጠቱ ስራ ዳግም እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡ ችግሩ ከተፈታ በኋላ በተለይም የነዳጅ ማደያ ተደራሽ ባልሆኑባቸው አካባቢዎች በስፋት የሚሰራ ይሆናል ነው ያሉት፡፡                 የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳህረላህ አብዱላሂ የነዳጅ ማደያ ፍቃድ አሰጣጥ ብዙ ጥናት ማድረግን የሚፈልግ ስራ በመሆኑ መቼ ይጀምራል የሚለውን አሁን መግለጽ አይቻልም ብለዋል፡፡ መናኸሪያ ሬዲዮ
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዓለም አቀፉ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ ተሰማ በዋናነት ነዳጅ አምራችና ላኪ ሃገራት ላይ በታየው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ምክንያት ዛሬ ማለዳ ላይ ጭማሪ ማሳየቱን ሬውተርስ በቢዝነስ ዘገባው አስነብቧል። አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ በትንሹ የ0 ነጥብ 5 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱንም ዘገባው አመላክቷል። የኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲን ጨምሮ የሃገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት ባላስልጣናት በሄሊኮፕተር አደጋ ለህልፈት ከተዳረጉ በኋላ ጭማሪው መመዝገቡንም ዘገባው ጠቅሷል። በተጨማሪ የሳዑዲ አረቢያው ንጉስ ሳልማን የጤና መታወክ ያጋጠማቸው ሲሆን፥ ዜናው ከተሰማ በኋላም የዋጋ ጭማሪው ታይቷል ነው የተባለው። Arada_Fm
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ግብርና ሚኒስቴር ፀረ ተባይ እና የግብርና ኬሚካሎችን የሚረጩ አውሮፕላኖችን በኪራይ ሊያቀርብ ነው ተባለ የግብርና ሚኒስቴር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለማግኘት በማሰብ እርሻዎች ላይ ፀረ ተባይ እና ሌሎች የግብርና ኬሚካሎችን ለመርጨት የሚያስችሉ አውሮፕላኖችን በኪራይ ሊያቀርብ መሆኑን ሪፖርተር አስነብቧል። ሚኒስቴሩ በሀገሪቱ በምስራቅ እና ሰሜን የአንበጣ ወረራ መከሰቱን ተከትሎ 5 አውሮፕላኖች መግዛቱን ሲገልፅ የኢንሹራንስ እና የጥገና ወጪዎችን እንዲሁም ተባዮችን ለመቆጣጠር የሚያስችል አቅም ለማዳበር አውሮፕላኑን ለግሉ ዘርፍ ሊያከራይ እንደሆነ ገልጿል። የግብርና ሚኒስቴር ግርማ አመንቴ እነዚህን አውሮፕላኖች ለግሉ ሴክተር እና ለትልልቅ እርሻዎች አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችለውን አሰራር ለመዘርጋት መመሪያ መዘጋጀቱን የገለፁ ሲሆን አገልግሎቱ በቅርቡ ይጀምራል ብለው እንደሚጠብቁ ገልፀዋል። @TikvahethMagazine
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአዲስ አበባ በዓመት ከ80 ሺ ቶን በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ ይመነጫል ተባለ በአዲስ አበባ ከተማ በዓመት ከ80 ሺ ቶን በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ ይመነጫል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አሰታወቀ። ይህም በከተማዋ ከሚመነጨው ቆሻሻ 13 በመቶ የሚሆነዉ የፕላስቲክ መሆኑ ሲነገር የሀገሪቷ የፕላስቲክ ፍጆታ ከ 2007 ከነበረበት 43000 በ 2022 ወደ 224000 አድጓል። ይህም በሰዎች ጤና፣ የአካባቢ ውበትና የውኃ ኃብት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ስለመሆኑም ተጠቁሟል። በዚህም አካባቢን የሚበክሉ የፕላስቲክ ምርቶች ውፍረታቸው ከ0.03 ማይክሮ ሜትር በታች ሆነው እንዳይመረቱና አገልግሎት እንዳይሰጡ ማድረግ፣ በፕላስቲክ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ ታክስ መጣል ተግባራዊ መደረግ ያለበት መሆኑን የዘገበው ካፒታል ነው። @TikvahethMagazine
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሀገሪቷ ከወጪ ንግድ ከ2.5 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሏ ተገለፀ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር እንደገለፀዉ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ ከ 2.5 ቢሊየን በላይ የአሜሪከን ዶላር ገቢ መገኘት ችሏል ብሏል። ሚንስትሩ እንደገለፀዉ በዘጠኝ ወሩ 3.56 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 2.511 ቢሊዮን ዶላር ወይም 70.49 በመቶ ገቢ ማግኘት ተችሏል፡፡ ከተገኘው ገቢ የግብርና ምርቶች 73.6%፣ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ 51.54%፣ ማዕድን ዘርፍ 66.53% እዲሁም ኤሌክትሪክና ሌሎች ምርቶች 71.25% ዕቅድ አፈፃፀም ማሳየት ችለዋል በማለት በሪፖርቱ ገልጿል ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ክትትል የሚደረግባቸው የቅባት እህሎች፣ የጥራጥሬ ምርቶች፣ የብርዕና አገዳ ሰብሎች፣ የጫት ምርት፣ የቁም እንስሳት እና የደንና ደን ውጤቶች እንዲሁም የቁም እንሰሳት መኖ 811.13 ሚሊዮን ገቢ ለማግኝት ታቅዶ 699.11 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘት ችሏል ማለቱን ካፒታል ዘግቧል።
Show all...
👍 2