cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

🅿ተር

😍 ውድ ወንድሞቼና እህቶች ሰላማችሁ ይብዛላችሁ🙏🔱 🔆በዚህኛው ቻናሌ 🌟 የስነልቦና ምክሮችን 🌟አስተማሪ ታሪኮችን 🌟 አስደናቂ ገጠመኞችን እንዲሁም አስደማሚ እውነታዎችን እንመለከታለን❣️

Show more
Ethiopia5 718Amharic4 367The category is not specified
Advertising posts
2 618
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

▶️Entrance Hub Ethiopia YouTube Channel ቤተሰብ ሆነዋል?🤫 የYou tube ቻናላችን ቤተሰብ ስሆኑ👑 ✅ከ 9️⃣ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ ትምህርቶች በ Video📼 ✅ 1️⃣2️⃣ኛ ክፍል Entrance ጥያቄዎችን ✅ የREMEDIAL Module ማብራርያ ✅ የFreshman Module ከድንቅ ማብራሪያ ጋር 😍እንዲሁም👑 🔝 የስኬታማ ተማሪዎች ተሞክሮ ለራሳቸው አንደበት 🟩 እነዚህን ሌሎች በርካታ ፕሮግራሞች በነፃ ይዘንላችሁ እንመጣለን✍️ ዛሬውኑ የYou YouTube ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ 👍ENTRANCE HUB ETHIOPIA✔️ 🔵 @ENTRANCEHUBETHIOPIA ▶️ SUBSCRIBE NOW✅ 😐ይህን ይጫኑ📣
Show all...
ለ2016 FRESHMAN ተማሪዎች ከ Entrance HUB University Family Channel ነፃ Link ለ 150 ሰው ክፍት እንድሆን አድርገናል🎖💪💪 ቤተሰብ ያልሆናችሁ ቶሎ Join አድርጉ ስለ ዩንቨርስቲዎች መረጃ በዛ ቻናል ለይ ብቻ Post ምናደርገው 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/+FS6QA5iKYvpjYmZk
Show all...
👍 1❤ 1
አይ አንቺ እናት🥲💔 በግራ በኩል በእናቱ እቅፍ ውስጥ አዲስ የተወለደ ህጻን አለ። ሐኪሙ በቀኝ በኩል ተቀምጦ ሲያለቅስ ይታያል። እናት በጠና ታማለች። ልጁን በህይወት ለመዳን ከባድ መስዋዕትነት እንደሚያስከፍል ዶክተሮች ተረድተዋል። ልጅ እንዲሰጣት ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ደጋግማ ትማፀናለች። የቀዶ ጥገናው ውጤት ልጁን ማዳን ወይም እናቱን ማዳን ሆኗል። ዶክተሩ ለ 7 ሰዓታት ያህል የተቻለውን እያደረገ ሕፃኑን እና እናቱን ለማዳን ጣረ። በመጨረሻም ዶክተሩ በእናትየው የተጠየቀውን ለማድረግ ወሰነ። ልጇን በእሷ የህይወት ዋጋ ማዳን ነበር። አዎ ልጄ በህይወት ይኑር እኔ ግን ይህን አለም ልልቀቅ አለች። ቢሞግቷትም ልትቀበል አልፈቀደችም። ህፃኑ ከእናቱ ሆድ ሲወጣ የለቅሶ ድምፅ አሰማ እናት ፈገግ አለችና ዓይኖቿን ለመጨረሻ ጊዜ ጨፈነች ዳግም ላትመለስ ከጌታዋ ጋር ተገናኘች። ሕይወቷን የሰጠችውን እናቱን ዳግም ላያገኛት ተለያት። አይ አንቺ እናት! እባካችሁ በስህተትም ቢሆን እናታችሁን አታስከፏት🙏 ከወደዳችሁት ሼር አድርጉት ☔️☔️☔️ @Peter_AF
Show all...
❤ 34😢 17👍 2
#ያሳዝናል ይቺ መልከመልካም ወጣት ናዝራዊት ተስፋዬ ትባላለች። ፌስቡክ ገጿ ላይ ብንሔድ ይሻለናል ቀጥላም Dear God Amen የሚል ጽሁፍ ከእንባ ጋር አድርጋ ፌስቡክ ገጿ ላይ ከፖሰተች በሗላ ራሷን አጥፍታለች። ምን ሆና ይሆን? እባካችሁ ሰው ድብርት ውስጥ ከሆነ አይታችሁ ዝም አትበሉ😞 የአንድ ቀን ስሜት ሙሉ ህይወቷን ቀጥፎታል😭 በምንም አይነት ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ብንሆንም ከህይወታችም ስለማይባልጥ የምንወስናቸውን ውሳኔ ተረጋግተን እንወስን🙏
Show all...
በ Moral Education (Civics ) በቂ Concept ያለው እና  በደንብ ማስተማር የሚችል ሰው በፍጥነት ያነግረኝ👇 @EH8131 ትንሽ ሾለ ስራው ገለፃ👇 ስራው የሚሆነው በቤታችሁ በመሆን የFreshman Civics  ማስተማር ነው፣ በድምፅ Record እያደረጉ መላክ። በደንብ የማስረዳት ብቃት ያለው ሰው ይፈለጋል። ክፍያው በምዕራፍ ብዛት ነው። (ስትመረጡ እንወያያለን) ሙሉ Module በአጭር ግዜ ውስጥ መጨረስ ግዴታ ነው። ለመስራት አቅሙ ያላችሁ እና ፍላጎት ያላችሁ ለ10 ደቂቃ ያህል Unit 2 እያስረዳችሁ Voice Record ላኩልኝ👇 @EH8131
Show all...
👍 1
ይህን ለብርሃኑ አድርሱልኝ 🥹 ሰው ግቢ በርሀብ አጥንቶ 3.9 ሰርቶ እንዴት ስያ አጥ ይሆናል ለዛውም የጤና ተማሪ ሆኖ😭 "በምን ሞራል ነው ተማሪዎችን አጥኑ ብለን የምንመክራቸው?" ደብረብርሃን አካባቢ ተወልጄ ከደብረብርሃን ዩንቨርስቲ በሚድዋይፍ የተመረቅሁ ስሜ ታልዬ በጋሻዉ ይባላል:: ለአገራችን በሙያችን ለማበርከት ቀን ከሌት ደፋ ቀና ብለን፣ አራት አመታትን ያለ እንቅልፍ እና እረፍት ስንደክም ቆይተን እጅግ በጣም ከፍተኛ የሚባል ውጤት CGPA 3.9 በላይ ዉጤት ተመርቄ ነበር:: አሁን 4 ኪሎ አካባቢ መንገድ ዳር ያለሙያዬ ጌጣጌጥ በመሸጥ ላይ እገኛለሁ። በምን ሞራል ነው ተማሪዎችን አጥኑ ብለን የምንመክራቸው? በአመት 400 እና ከዚያ በላይ የእናቶች ሞት ባለበት አገር ሆነን ያለስራ 1 አመት ሙሉ መቀመጥና የትገባችሁ የሚል አካል አጥተን ወንበር እያሞቅን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው:: መረጃዎቼ፡- የተመረቅኩበት ፎቶ እና ዶክመንቶቼ ሲሆኑ1ኛ እና 3ኛ ላይ ያለዉ ፎቶ አሁን መንገድ ዳር ጌጣጌጦችን በማዞር
Show all...
ውድ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ውጤት አልመጣልኝ ብላችሁ በፍፁም አትጨነቁ መንግስት ሌላ ድብቅ አጀንዳ ስለያዛ ነው ተማሪዎች ሆን ብሎ እያጠለ ያለው🥹 በለፉት 2 አመታት ብቻ 1.6 Million በላይ ተማሪዎችን ከትምህርት ውጭ እንዲሆኑ ያደረገው በምክንያት ነው እንጅ በርግጥም ተማሪዎች ወድቀው ነው ብዬ አላምንም! ምክንያት የመንግስት እቅድ አሁን ገሃድ እየወጣ ነው። በቅርቡ በቀይባህር ዙሪያ ለኤርትራ ጋር ጦርነት ውስጥ ልገባ እንደሆነ አዝማሚያ እያሳየ ይገኛል። ◈እውነትም መንግስት ሆን ብሎ ተማሪዎች እንዲወድቁ አድርጓል ብዬ እንዲወስን ያደረጉኝ ምክንያቶች👇 1◈ በምን ህሳብ ለተከታታይ 2 አመታት 97.3% ተማሪዎች ከ50% በታች ይሆናሉ?😏 ከ800ሺ ተማሪዎች ውስጥ መስራት አይችሉም ብባል 600ሺዎች ከ50% በታች ናቸው ብል እሽ ይሁን እንዴት ሆኖ ነው ይህ ሁላ ወጣት ምንም አይችሉም! ከ100 ጥያቄ 50 መመለስ አልቻልክም! አንተ ትምህርት አትችልም! ለምንም አትሆንም ልባል ይቻላል? አሁን መንግስት በግልፅ እያለ ያለው ይህን ነው። ከ1ኛ-12ኛ ክፍል የደረጃ ተማሪ የነበረውን 12ኛ ክፍል ስደርስ 50% እንኳን መስራት አትችልም ማለት ምን ማለት ነው?😳 ይህን የሚናገረው ዝም ብዬ ስሜታዊነት ተነሳስቼ ሳይሆን በስሌት ከሁኔታዎች በመነሳት ነው። እኔ በቅርበት የማውቃቸው በትምህርት ቤት እና በቤተሰብ ደረጃ እጅግ ስጠበቁ ነበሩ ጓበዝ ተማሪዎች እንዲወድቁ ተደርጓል። አምና የመጀመሪያ አመት ስለሆነ ምናልባት የቦታ ለውጥ ይሆናል ብለን ነበር ይህን ነገር ዘንድሮም ተደግሟል፣ ተማሪው አመቱ በሙሉ አንብቧል፣ ከበቂ በላይ ዝግጅት አድርጓል ነገር ግን ከ50% በታች የሆነ ውጤት ተሰጥቶታል፣ ታዲያ ችግሩ ለማን ልሆን ይችላል? አምናም ይህን ነገር ተናግሬ ነበር፣ ይህ ፖለቲካ Game ነው! ሌላ አንድ ጉድ ልንገራችሁ 😄 አንድ በጠም የሚወደውን ጓደኛ አለኝ፣ በ2013 ዓ/ም Entrance ከፍተኛ ውጤት አምጥቶ የሚፈልገውን ዩንቨርስቲ ገብቷል። የዩንቨርስቲ የመጀመሪያ አመት ውጤቱንም 4 ነጥም ሰርቷል። ከ2013 ጀምሮ ለተከታታይ 3 አመታት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን አስጠኚ ሆኖ ይሰራል። በየቀኑ ብያንስ ለ4 ሰዓታ የ12ኛ ክፍል መፅሐፍትን ያነባል፣ ምክንያት አስጠኚ ስለሆነ፣ በዩንቨርስቲ የበርካታ ተማሪዎች ህልም የሆነው Medical የ3ኛ አመት ተማሪ ነው፣ የ2014 12ኛ ክፍል ውጤትን እውነት ነው ብለን ማመን አቅቶን ስለነበረ በ2015 ስም ቀይሮ private ለመፈተን ወሰነ፣ እና በሌላ ሰው ስም ከ2015 ተፈታኞች ጋር ተቀላቅሎ ፈተናውን በሰላም ጨርሷል፤ እኔና እሱ ውጤቱን በጉጉት ስንጠብቅ ነበር ምክንያት በሀገር አቀፍ ከፍተኛ ይሆናል ብለን ስለነበረ ፣ የሆነ ግን ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ነው🤠 ጋሽ ብሬ ውጤት ይፋ ስያደርጉ የሱ ውጤት ምን ብሉት ጥሩ ነው አንተ የጤና ተማሪ፣ አንተ በ2013 ከፍተኛ ውጤት የሰራክ ተማሪ፣ አንተ ለ3 አመታት የ12ኛ ክፍል አስጠኚ ተማሪ፣አንተ የ6ሺ ተማሪዎች አስተማሪ የሆንክ ተፈታኝ ብትሆንም በ2015 ግን የ12ኛ ክፍል ፈተና 50% እንኳንም መስራት አልቻልክም ስለዚህ ወድቀሃል ብለው ውጤት ይፋ አደረጉ😁 አቤቤቤቤቤቤት ግን በተማሪዎች ለይ እየተካሄደ ያለው ግፊ😔 እሽ አሁን እሱ 12ኛ ግማሽ ጥያቄ መመለስ አቅቶት ነው? እንደው የስንቱ ጓበዝ ተማሪዎች ህልም አጨልማሁት ይሁን😒 እኔ የነገራችሁ ነገር ብኖር ውጤት አልመጣልኝም እያላችሁ የሚታዝኑ ተማሪዎች አሁኑኑ ተመለሱ መንግስት አደገኛ እቅድ አቅዷ ሆን ብሎ ነው ይህን ያደረገው! በፍጹም እንደታዝኑ! በቀጣይ የመንግስት እቅድ በሙሉ ዝርዝር አድርጌ አቀርባለሁ😊 በቀጣይ እንገናኝ.... ወንድማችሁ 🅿️ተር ነኝ፣በዚህ ቻናሌ ስለትምህርት እና ትምህርት ነክ የሆኑ ትክክለኛ መረጃዎችን ማግኘት ትችላላችሁ ለጓደኞቻችሁ Share አድርጉ👇 @Peter_Af
Show all...
👍 2😱 1
ላም ባልዋለበት...! ሰሞኑን የ12ኛ ክፍል ውጤት መነጋገሪያ ሆኗል፣ ለኔ ግን ምንም አልመሰለኝም ምክንያቱም ፣የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ ተማሪዎች እንደየ አቅማቸው እንዲያገኙ ኩረጃን ለማስቀረት የተወሰደው እርምጃ ጥሩ ጅማሮ ነው ብዬ ባስብም ከዚህ መቅደም የሚገባቸው ነገሮች አሉ። ተማሪ ውጤት መስራት የሚችለው መቼ ነው? 1ኛ፡ የተመቻቸ የመማር ማስተማሪያ አከባቢ ሲኖር 2ኛ፡ ጥሩ መምህራን ሲኖሩ 3ኛ፡ የተማረ ሰው በማህበረሰቡ የተሻለ የኢኮኖሚያዊ ሆነ ማህበራዊ ኑሮ ሲኖረው እነዚህ ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎች ደግሞ ምንም ያልተነኩ ናቸው...አሁን ባለው ተጨባጭ እውነታ መምህራን የመጨረሻ አስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ የሚገኙ ናቸው...ማንም መምህር መሆን አይፈልግም..በዚህም የተነሳ አማራጭ ሲታጣ የሚገባበት ሙያ ሆኗል....የገቡትስ (መምህራን) ምን ያህል አቅም አላቸው? ጥሩ ገበሬ በሌለበት ጥሩ ምርት መጠበቅ ልክ አይደለም... የተማረ ሰው ሰፈር 'ጎበዝ ነው፡ እንደሱ ሁኑ' እየተባለለት ያደገ ተማሪ ለ3 እና ለ 4 ዓመት ስራ አጥቶ ሲንከራተት ማየት የተለመደ ነው...እና ተማሪው በምን ተስፋ ይማር? አሁን ሰርተዋል የተባሉት ት/ት ቤቶች በአብዛኛው አዳሪ ትምህርት ቤቶች ናቸው። ምክንያቱም ግልፅ ነው፣ የተሻለ መምህራን፡ የተሻለ መማሪያ ክፍል፣ የተሻለ የመማሪያ ቁሳቁሶች ስላሏቸው ነው። ሌሎቹ ደ'ሞ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ት/ት ቤቶች ናቸው። ተዓምር አይደለም። ሁሉም ተማሪዎች እኩል ጭንቅላት አላቸው...ግን ያልተዘራባቸውን እንዲያበቅሉ ነው እየተጠበቀ ያለው... ተስፋ ሳናሳይ እንዲነቃቁ እንጠብቃለን፤ ሳናስተምር እንዲያልፉ...አይደለም ተጨማሪ ሪፈራንስ ይቅርና መማሪያ መፅሐፍ በሌለበት እንዲያነብቡ፡ ሙሉ መፅሐፍ በማይሸፈንበት (2-3 ምዕራፍ ቀርቷቸው) ውጤት እንጠብቃለን ...ላም ባልዋለበት ኩበት ፍለጋ እንወጣለን..ያሳዝናል። እኔ ግን እላለሁ...እናስተምራቸው...እናስጠናቸው...ጥሩ መምህራን ይኑሩን...መምህርነት የተከበረ ሙያ ነው ከማለት በዘለለ የመምህራንን ህይወት እንዲሻሻል እናድርግ ...የግል ትምህርት ቤቶች ከገቢ ማስገኛነት የበለጠ ማስተማሪያ መሆናቸውን በደንብ እንስራበት....ትምህርት ቤቶች ይገንቡ...መፅሐፍ 1 ለ 10 ከመጋራት የየግል እንዲኖራቸው እናድርግ...ከዚህ በዘለለ 'ትውልዱ ትውልዱ' መጮህ እና መወቀስ ልክ አይመስለኝም። ፍየል ወዲህ ...ቅዝምዝም ወዲያ። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦ " ከዚህ ፈተና አንድ #ሊያስደነግጠን የሚገባ ነገር ከተፈተኑት ጠቅላላ ተማሪዎች ውስጥ 50 ከመቶ የሚሆኑት እና ከዛ በላይ 26 ከመቶ ነው ያገኙት። ከ845 ሺህ ፤ 422,500 ሺህ ተማሪ ከ26 በታች ነው ያገኘው። እንደው ዝም ብሎ አንድ ተማሪ ፈተናውን በግምት ቢሞላ እንኳን ሊያገኘው የሚችለው ውጤት ነው። ለዚህ ነው ከታች ጀምሮ በደንብ አጥርተን መስራት አለብን የምንለው። " ስለ 2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ቁጥሮች ምን ይላሉ ? - በ2015 የተፈተኑ ተማሪዎች ብዛት 845,099 ፤ 50 በመቶና በላይ ያመጡ 27,267 ተማሪዎች (3.2%) ብቻ ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ፦ • ከተፈጥሮ ሳይንስ ያለፉ 19,017 ተማሪዎች • ከማህበራዊ ሳይንስ ያለፉ 8,250 ተማሪዎች - በማታ የተፈቱ 16,541 ያለፉ 12 ተማሪዎች ብቻ - በግል የተፈተኑ 169,502 ያለፉ 498 ተማሪዎች ብቻ - በመደበኛ የተፈተኑ 659,056 ያለፉ 26,757 ተማሪዎች ብቻ - የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ት/ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች #አንድም_ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም / ምንም ተማሪ አላሳለፉም። - በሀገሪቱ ካሉትና የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑት ትምህርት ቤቶች 42.8 በመቶ የሚሆኑት አንድም እንኳን ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም። - 27 ሺህ 267 ተማሪዎች በቀጥታ ፍሬሽ ማን ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ 160 ሺህ ገደማ ተማሪ በሬሜዲያል ይገባሉ። ሀሳብ ካላችሁ...ሀሳባችሁን ወዲህ በሉ
Show all...
👏 13👍 7❤ 1
#Grade 12 ውጤት ይፋ ስለሆነ የኔትወርክ መጨናነቅ ስለምኖር አብዛኞቹ ውጤታቸውን ማየት አይችሉም ኔትወርክ በምሰራበት ቦታ ያለችሁ በፈቀደኝነት ውጤት ማሳየት የምትችሉት username ላኩልኝ👇 @Zpeterbot
Show all...