cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የጋዜጠኛው ማጮለቂያ

አያለሁ፣እሰማለሁ፣እናገራለሁ ሰለኢትዮጵያ

Show more
Advertising posts
413
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ይህ የላኩልህ መኪና ራይድ ሲሆን ትናንት በስቅለቱ ከስግደት ስንመለስ ቱሉዲምቱ ኮንዶምንየም ፕሮጀክት 12 ከቀኑ 11:30ላይ ሶስት የመኪና ሌቦች ውስጥ ሆነው ሹፌሩን በ ጊሌ እና በፌሮ እየቀጠቀጡት ልጁ መኪናውን ሳያቆም ለመውሰድ እየታገለ ግማሽ ጉኑ ከመኪናው ውጭ እየተጎተተ አይተን እየሮጥን ስነ ከተል በዚመልኩ ከመኪና ጋር ተጋጭቶ ሲቆም ወርደው ሲሮጡ ሌቦችን የግድያ ሙከራ አድራጊዎችን ተረባርበን 2ቱን ይዘናቸው ልጁን ወደ ህክምና ሌቦችን ለፖሊስ አስረክበናል። ሲሉ መልህክት አድርሰውናል :: እንዲህ ተባብረው ተረባርበው ሌቦችን የያዙ አካላት ክብር ምስጋና ይገባቸዋዋ ። #የሾፌሮች_አንድበት
Show all...
👍 1
ታማኙ ይሁዳ ከሙት ባህር እየተነሳ የሚነፍሰው ንፋስ ፤ ሙቀት ያዘለ ነው። አንድ ጊዜ ኃይሉን አሰባስቦ ሲመጣ ጨርቅ ያስጥላል። ልጃገረዶች ቀሚሳቸውን ወደታች እየጎተቱ ከነፋሱ ጋር እየታገሉ ወደ አንዱ ጥግ እፍረት በወለደው ሳቅ እያሽካኩ ይፈተለካሉ። ገርበብ ተደርጎ በተከፈተው መስኮት በኩል የሚገባው ንፋስ መጋረጃውን እንደ ሰንደቅ እያነሳ ሲያርገበግበው ነበር የቆየው። ኃይል ጨምሮ ሲመጣ ግን መስኮቱን እንደ ልጃገረዶቹ ቀሚስ ጎትቶ የሚያስጥለው አላገኘም። ወስዶ ከግርጊዳው ጋር አላተመው። ጓ !! ተመስጠው በነበሩ ሰዎች መሃል ይሄ ድምፁ ከፍተኛ ነው። ዘኪዮስ ለንግግሩ ጆሮውን ጣል እንዳደረገ ተነስቶ መስኮቱን ሸጎረው። "መንገድም ፤ ህይወትም እኔ ነኝ" ይላል ድምፁ የቤቱ ማዕዘናት ላይ ፋኖሶች ተንጠልጥለዋል። ቤቱ የኖራ ድንጋይ ከሚባለው ነው የተሰራው። መሬቱ ሰሌን ለብሶ ጥግጥጉ ላይ የሀር አልጋ ልብስ የለበሱ ፍራሾች ተዘርግተዋል። በዚህ ፍራሽ ላይ ዛሬ ብዙ እንግዶች ተቀምጠዋል። ከገሊላ ወገን የሆኑ ፤ የሳምራዊያን ዘሮች ፤ አይሁዶች ፤ የተለያየን ነን የሚሉ በአንድ ላይ ተቀምጠዋል። አንድ ላይ ስለመሆናቸው ምክንያት የሆነው ደግሞ ዛሬ በመካከላቸው ቁጭ ያለው። ኢየሱስ ነው። ኢየሱስ የማሪያም ልጅ!! ማነው የውቅያኖስን ውሃ ጭልጥ አድርጎ ጠጥቶ 'እፎይ' ብሎ ጥሙን የቆረጠ ? ማነው ሀሳብን ሁሉ ጥሎ ራሱን ባዶ አድርጎ ከደመና በላይ ወቶ የተደላደለ ? ማነው ? ማንም !! ኢየሱስን ለቅስፈት መመልከት ግን ከዚህ ሁሉ በላይ ፍፁም እርካታ ፤ ፍፁም ሰላም ነው። ለዚህም ነው ሀገር ምድሩ ሁሉ "ጌታ ሆይ " እያለ የሚከተለው። ከሚከተሉት ውስጥ የተመረጡት ዛሬ በዘኪዮስ ቤት አብረውት አሉ። ከእነሱ ውስጥ የአስቆረጦሱ ይሁዳ አንዱ ነው። ይሁዳ ወደዚህች ከተማ ከሶስት አመት በኃላ መመለሱ ነው። አሁን በቤቴ እረፉ ብሎ ካስተናገዳቸው ሰውዬ በቅርብ ርቀት ባለች መንደር ነበር የሚኖረው። በዛ መንደር ውስጥ ሰንበት ሲሆን 'የጥቅምት አበባ' መስላ መታ ወደ ከተማው ዳርቻ ወዳለ ኮረብታማ ቦታ ይዛው ሄዳ 'በሚፍነከነክ ሳቋ ፤ በሚደንሰው ሰውነቷ ፤ በሚንዛለፈው ፀጉሯ ፤ 'ዘራፍ' በሚለው ደረቷ " አለሙን አሳይታ ፤ ፍሳውን አስዳስሳ የምትመልሰው 'ሴፔራ' አለች። ይሁዳ ወደዚህ ቤት ከገባ ጀምሮ የሚያስበው ስለ እርሷ ነው። "በህይውት ትኖር ይሁን ? አግብታስ ቢሆን ? ያን ፀጉሯን ተቆርጣው እንዳይሆን ብቻ " ይሁዳ ከዚህ ውጪ ሌላ ነገር ሊያስብ አልቻለም። ይሁዳ በሀሳብ እንደተዋጠ ኢየሱስ "እንካቹሁ ተቃመሱ" ብሎ ለደቀመዛሙርቱ የሳጣቸው ቂጣ እርሱ ጋር ደረሰ ከላዩ ላይ ቆንጠር አርጎ አሳልፎ ለጴጥሮስ ሰጠው። ተከትሎ በዋንጫ የሆነ ነገር መጣ። ተቀብሎ አየው። ወይን ነው። ከሶስት አመት በፊት የተውው ነገር። ወይን ስትቀምስ ሙዚቃ የሚመስል ሳቅ የምትስቀው ሴፔራ መጣችበትና አፉ በሳቅ ተሞላ። ወንጫውን ከፍ አድርጎ ከንፈሩን አስነክቶ ሽራፊ ሳቁን ዋጫው ውስጥ ሳቀ። በቤቱ ፀሎት ሆነ። ሁሉም በአንድ ላይ ተጉ። ይሁዳ ግን ሆዴን አመመኝ ብሎ ጥጉን ይዞ ቁጭ አለ። ትንሽ ቆይቶ በሩን ከፍቶ ወጣ። ከቤቱ ልክ እንደወጣ ጉልበቱ አገጩን እስኪነካ ድረስ እያነሳ ሮጦ ወደነ ሴፔራ መንደር ገባ ! የተቀየረ ነገር የለም። መንደሩ ያው በፊት እንደሚያውቀው ነው። በቀጥታ ወደ ሴፔራ ቤት ሄዶ በቀስታ ቆረቆረ። ሴፔራ ነበር የከፈተችው። "ማን ልበል" አለችው ፤ ሳይነግራት በድንገት የጠፋባት ይሁዳ መሆኑን አለየችውም። ይሁዳ ግን አዘነ ! ሴፔራ ተጎሳቁላለች። ግንባሯ ላይ ያለችው ፀሀይ ጠልቃለች። እንደፈራው ፀጉሯንም ተቆርጠዋለች። የጎደጎደው አይኗ ከህይወት አርቋታል። ሴፔራ በጎረምሳ እጅ ላይ እንዳለች ሎሚ ሟምታለች። በይሁዳ ጉንጭ ላይ የሚፋጅ እንባ ወረደ ! ፈጥኖ አቅፉ ወደ ጉያው ሸጎጣትና ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ። ጥሎት በመሄዱ ራሱን እየወቀሰ ይሁዳ አለቀሰ !! ይሁዳ ከሴፔራ ተለይቶ ሲመለስ መንገድ ላይ የተባባሉትን መልሶ እያሰበ ነበር። ከንፈሩን ስማ " ድጋሚ ጥለህኝ አትሂድ" ስትለው 'እሺ' ብሏታል። "ትንሽ ሳንቲም ብናገኝ ፤ የመኮመሪያ ቤት ከፍተን ኑሯችን ይደላደላል" ስትለውም አምኗት "ልክ ነሽ" ብሏታል። ነገር ግን ሳንቲሙን ከየት እንደሚያመጣው ሊገባው አልቻለም፤ ብቻ "መላ አላጣም" እያለ ነው ወደ ዘኪዮስ ቤት የተመለሰው። በአንድ ማለዳ በጌቴሰማኔ እያሉ ሴፔራ በስትክክል ያለበሰችውን ሻርፕ ወደ ግራ ወደ ቀኝ እያማታች መጣች። የተጣደፈች ትመስላለች። እንደ ደረሰች ከህዝብ ማሃል እጇን ከፍ አድርጋ ለይሁዳ አውለብልባ ምልክት ሰጠችው። ይሁዳ እንዳያት ሰዎችን ይቅርታ እየጠየቀ አቆራርጦ መጣ። ሴፔራ የይሁዳን ክንድ ለቀም አድርጋ ወደ ጥግ ወሰደችውና "እንኳን ደስ አለህ " አለችው "ለምኑ" አላት " ብዙ ብር ሊኖርህ ነው " "እንዴት ሆኖ " "ቄሳሮች ሲፈልጉህ ነበር " "እኔን? ለምን? " "ኢየሱስ ወንጀለኛ ነው' ነው የሚሉት ፤ ሊቀጡት ፈልገዋል መሰለኝ" "እና" "ሊይዙት ብለው የትኛው እንደሆነ አለዩትም" "ልክ ነው " አለ ይሁዳ " አይለዩትም ፤ ኢየሱስና ዮሀንስ አንድ ነው መልካቸው። ከአፉ ላይ ቀበል አርጋ "እኮ" አለች ሴፔራ "እነሱም የፈለጉኹ ለዚህ ነው። አንዳቸውን በምልክት አሳልፈህ እንድትሰጣቸው ይፈልጋሉ። ለዚህም '30 የወርቅ ዲናር አለህ" አለችው። ድምፆ ውስጥ የኔ ጌታ ፤ የሚል ማባበል ነበረው። በመሸም ጊዜ ትምህርቱ አብቅቶ ስለነበር ደቀመዛሙርቱ ሰውን ሁሉ በአቅራቢያው ወዳለ መንደር ሸኝተው እነርሱ ኢየሱስን ይዘው ወደ ተራራው ወጡ። ይሁዳ ቀን ላይ ወደ ቄሳሮቹ ጋር ሄዶ ተስማምቶ 30 ዲናሩን ተቀብሎ ነው የመጣው። "ስንመጣ ኢየሱስ የሆነውን ስመህ ምልክት ስትሰጠን እንይዘዋለን" ሲሉት እሺ ብሏል። አሁን ከተራራው ላይ ፈንጠር ብሎ ለብቻው ተቀምጦ በሀሳብ ተጠምዶል።ዕቅዱ ዮሀንስን "ኢየሱስ ነው " ብሎ ስሞ አሳልፎ መስጠት ነው። 'ያበላኝ ፤ያጠጣኝ' ኢየሱስ ላይ ከምጨክን ምንም የማልግባባው ዝምተኛው ዩሀንስ ቢሆን ይሻላል ብሎ ደምድሟል። ሚጠብቀው መምጣታቸውን ነው። ብዙም ሳይቆዩ ቄሳሮች መጡ ! ይሁዳ ፈንጠር ብሎ ተነሳ። ከፊት ላለው ቄሳር ሰላምታ ሰቶ እየመራ ወደ ተሰበሰቡበት ቦታ ይዟቸው ሄደ። አጋጣሚ ሆኖ ኢየሱስና ዩሃንስ ጎን ለጎን ቆመው ነበር። ይሁዳ ፈንጠር ብሎ ተራምዶ ኢየሱስና ዩሀንስ ፊት ቆመ። ዩሀንስን ተመለከተው ፤ ደሞም በተራ ኢየሱስን አየው። አሁን በሁለት ምርጫዎች መሀል ነው የቆመው ። የመምረጥ ግዴታ ደግሞ አለበት። ቄሳሮች ከኃላ ተላልፎ የሚሰጣቸውን ሰው ለመሸለት ሻሞላቸውን ስለው እየጠበቁት ነው። እንደ ቃሉ ኢየሱስን አሳልፎ መስጠት ፣ ወይም ዋሽቶ ገራገሩን ዮሀንስን ስሞ ወደ እርድ መላክ - - - ይሁዳ ይሄን ሀሳብ በፍጥነት እያመነዥገ ወደ ዩሃንስ ተጠጋና እጁን ትከሻው ላይ አድርጎ መታ መታ አድርጎ ተወውና ኢየሱስን አቅፎ ስሞት ፊቱን አዙሮ ሄደ- - - ✍️ Henok Mengistu
Show all...
አቃቂ ገበያ እሳት ተነስቷል።(ምሽት 3:20) የእሳት  አደጋው በተለምዶ ቡቲክ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተከሰተ ሲሆን እጅግ በርካታ ሱቆች የሚገኙበት ነው። አደጋው እንደደረሰ በአካባቢው መብራት የጠፋ ሲሆን ባለንብረቶች ንብረት ካላወጣን እያሉ ሲሆን ፖሊስ ደግሞ ለማረጋጋት እየሞከረ ነው። አደጋው የተከሰተው 3:20 ሲሆን አሁን የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታው ደርሰዋል። አቃቂ ገበያ  ከመርካቶ ቀጥሎ ትልቅ የንግድ እንቅስቃሴ ያለበት ነው። (ቢኒያም ፍርዳወቅ)
Show all...
Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

እንኳን ደህና መጡ‼ ✔ማስታወቂያ ለማሰራት እና ጥቆማ ለመስጠት በዚህ ይጠቀሙ ☞

https://t.me/WasuMohammed

✔ ቻናሉን ለመቀላቀል Join ☞http://t.me/Wasulife ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏

👍 1
#ጉልባን ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በፀሎተ ሀሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትዉፍቱም የስቅለቱ ሀዘን መገለጫ ነዉ ። የአመት ሰዉ ይበለን ❤🙏
Show all...
ከመቀሌ ወደ ከሚሴ‼ በሰሌዳ ቁጥር አማ 17744 ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ መነሻውን መቀሌ በማድረግ ከሲሚንቶ ጋር በድብቅ ተጭኖ መዳረሻውን ከሚሴ ያደረገው ህገ ወጥ የቡድን እና የነፍሰ ወከፍ የጦር መሳሪያ ከነ አሽከርካሪውና ረዳቱ በህብረተሠቡ ጥቆማ ደጋን ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡2 ዲሽቃ እና 1 ስናይፐርን ጨምሮ በአጠቃላይ 8 የነፍስ ወከፍ እና የቡድን መሳሪያ መያዙ ነው የተሰማው።   23/08/2016 ዓም
Show all...
አዋጅ‼️ #የፌዴራል_ ፀጥታ_ኃይሎች በራያ አላማጣ_ከተማ ከትናንት ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸውን የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገለፁ‼️ 👉 ማንኛውም #ተሽከርካሪ ከጠዋቱ 12: 00 እስከ ምሽቱ 12 : 00 መንቀሳቀስ የሚቻለው‼️ 👉  #እግረኞች ከጠዋቱ 12:00 እስከ ምሽቱ 4:00 መንቀሳቀስ የሚቻለው‼️ 👉 ማንኛውም #ጦር_መሳሪያ ( ስለት ያለባቸው ጭምር )  መያዝ ፍፁም የተከለከለ ነው‼️ 👉 #መብራት ኃይል ፣ #ውሃና_ፍሳሽ_አገልግሎት ፣ #ጤና_አገልግሎት ፣ #ቴሌ_አገልግሎት ፣#ባንኮች ስራቸው በአግባቡ እንዲሰሩ። 👉 የህዝብ ትራንስፖርት #በመነሃሪያ ብቻ አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ" ተገልጿል
Show all...
👍 1
#TikTok‼️ " የቲክቶክን አደጋ በትክክል እናውቃለን " - ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን‼️ ' ቲክቶክ ' አውሮፓ ውስጥ የመታገድ ዕጣፋንታ ሊገጥመው እንደሚችል ተሰማ። ባለፈው ሳምንት አሜሪካ ' ቶክቶክ ' በመላ ሀገሪቱ እንዲታገድ አልያም ለአሜሪካ ኩባንያ እንዲሸጥ ሕግ ማውጣቷ ይታወቃል። ለዚህም የሰጠችው ጊዜ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ብቻ ነው። አሁን ደግሞ መተግበሪያው የአውሮፓ ሀገራት ውስጥ የመታገድ ዕጣፋንታ ሊገጥመው እንደሚችል ተነግሯል። የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን ለኮሚሽኑ የ2024 ምርጫ በተደረገ አንድ ክርክር ላይ ' ቲክቶክ ' በአውሮፓ ሀገራት የመታገድ ዕጣፋንታው ዝግ እንዳልሆነ ጠቁመዋል። ይህን ያሉት የአሜሪካ ' ቲክቶክ ' ን የማገድ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሷን በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ ነው። ቮን ደር ሌየን ኮሚሽኑ ከመላው ዓለም በተቋሙ ስልኮች ላይ መተግበሪያው እንዳይሰራ ያደረገ የመጀመሪያ ተቋም መሆኑን አስታውሰዋል። " የቲክቶክን አደጋ በትክክል ምንእንደሆነ እናውቃለን " ሲሉ አክለዋል። ምንም እንኳን የአውሮፓ ኮሚሽን አውሮፓ ሀገራት ውስጥ ' ቲክቶክ ' ሊታገድ እንደሚችል ፍንጭ ቢሰጥም ልክ እንደ አሜሪካ በፍጥነት ተመሳሳይ መንገድ ይከተል እንደሆነ ለመደምደም ገና ነው ተብሏል። የአውሮፓ ኮሚሽን በቅርቡ ከዋናው ቲክቶክ አነስ ብሎ የተዘጋጀው ' ቲክቶክ ላይት (ተጠቃሚዎች ተከፍሏቸው ቪድዮ የሚያዩበት) ' በህጻናት እና ተጠቃሚዎች የአዕምሮ ጤንነት ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው አደጋ ጥያቄ ማንሳቱ ይታወሳል።
Show all...
በልጆች መካከል የተፈጠረን ግጭት ለመገላገል የገባችው እናት በተፈጸመባት ጥቃት ህይወቷ አለፈ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን መልካ ቦሎ ወረዳ ጨፌ ደበላ በተባለ አካባቢ  ልጆችን ለመገላገል  ገብታ  ከልጆቿ ጋር በተጣሉ ሌሎች ልጆች የቤተሰብ አባል በተሰነዘረ ጥቃት ህይወቷ ማለፉ ተገልጿል፡፡ ሟች አልፊያ አብሮሽ የተባለች ግለሰብ  ልጆቿ ሊጫወቱ  ወተው  ይቀሩበታል፡፡በመሆኑም ልጇቿን  ለመፈለግ ስትወጣ  ከሌሎች ልጆች ጋር ሲጋጩ  በማግኘቷ ለማገላገል ስትሞክር  በቦታው ላይ የነበረ የሌሎቹ ልጆች ቤተሰብ የሆነው  ለምን አገላገልሻቸው  ይዋጣላቸው ይከባበራሉ  የሚል ምላሽ በመስጠቱ ምክንያት በመካከላቸው  ግጭት  እንደተፈጠረ  የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ የኮሙኒኬሽን  ጉዳዮች  ሃላፊ ሳሚን ቱጅሃን በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ በልጆች መካከል የተፈጠረው ጸብ  ተመልክቶ ለምን ገላገልሽ በሚል ተከሳሽ ነስረዲን የተባውን ግለሰብ   አልሰማም በማለት ልጆቹን ማገላገሏን በመቀጠሏ ድንጋይ በመወርወር ሆዷ ላይ ጉዳት ያደረሰባት መሆኑ ተነግሯል፡፡ ይሁን እና ግለሰቧ ወዲያውኑ  የህክምና  ተቋም ብትወሰድም የደረሰበት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ከአንድ ቀን በኋላ ህይወቷ  አልፏል፡፡ ፖሊስም በደረሰው ጥቆማ ተከሳሽ ነስረዲንን በቁጥጥር ስር በማዋል በሰው እና በህክምና ማስረጃ መዝገቡን አጠናክሮ ለዓቃቢህግ ልኳል፡፡ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዓቃቢ ህግ የመሰረተውን ክስ በመመልከት ተከሳሽ ጥፋተኛ አይደለሁም ብሎ ቢከራከርም  ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ10 ዓመት እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን  የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ የኮሙኒኬሽን  ጉዳዮች  ሃላፊ ሳሚን ቱጅሃን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
በህማማት ለምን መስቀል አንሳለምም ወይስ ለምን አናማትብም ? የመስቀል ክብር እና ሐይል የታወቀው ጌታ በመስቀል ከተሰቀለ በሗላ ነው፡፡ በሰሞነ ህማማት ከሰኞ እስከ አርብ ያሉት ቀናት የአመተ ፍዳ መታሰቢያ ናቸው፡፡በነዚህ ዘመናት ሰዎች የመስቀልን አገልግሎት እንዳልጀመሩ ለማሳየት በሰሞነ ህማማት በቤተክርስቲያን ስርዓት መሰረት መስቀል መሳለምም ሆነ ማማተብ ስርዓት አይደለም፡፡   በሰሞነ ህማማት ለምን አንሳሳምም? ይሁዳ ጌታውን በመሳም አሳልፎ ሰጥቷል እኛ ግን እንደ ይሁዳ ክፋት ካለው መሳሳም መለየታችንን ለማስረዳት ከዚህም በተጨማሪ ሰላም በዘመነ ፍዳ እንዳልነበረ ለማሳየት በሰምነ ህማማት እስከ መሳሳም የደረሰ ጥብቅ ሰላምታ የለም፡፡ በሰሞነ ህማማት የማይደረጉ ሌሎች ነገሮች ምን ምን ናቸው? ማንኛውንም ለስጋ የሚያደሉ ተግባራትን መቀነስ እና ቢቻለን አብዛኛውን ጊዜያችንን የጌታን ህማም መከራ በማሰብ በፆም በፀሎት በስግደት ማሳለፍ ፤ቢቻል አመጋገባችንን ከወትሮው መቀነስ አለብን
Show all...