WeMind Ethiopia
Open in Telegram
1 193
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-1030 days
Posts Archive
1 193
ሜንታል ሄልዝ አዲስ ቀጣዩን ወርሃዊውን ዝግጅቱን ይዞላችሁ መጣ፡: ቅዳሜ ሀምሌ 29/2015 ከቀኑ 10፡00 ሰዓት በአዶር አዲስ ሆቴል “የስብዕና መዛባት ምንድን ነው? እንዴስ ይታከማል?” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንዲናገሩ ዶ/ር ቢንያም ወርቁን ጋብዟል፡፡ መግቢያ ክፍያ:- ነፃ!!! ለመታደም በዚህ መስፈንጠሪያ ይመዝገቡ=> https://forms.gle/FJA7iLaXYWXVR1DB8
Mental Health Addis is holding its monthly event on Saturday Aug 5/2023 (Hamle 29, 2015) at Adore Addis Hotel near Atlas at 4:00PM (10:00 local time) on the topic of "What is personality disorder and how does it get treated? FREE OF CHARGE. This month’s speaker is Dr Benyam Worku. Please fill out and submit this form using this link https://forms.gle/FJA7iLaXYWXVR1DB8
1 193
Repost from Hakim
በኢቢሲ ቀናሁ
=========
አዲስ ተገነባው የኢቢሲ ጊቢ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ፤ ስራና ፈጠራን የሚነቃቃ ከባቢ ያለው፣ በመንግስት እንዲሁም በንግድ ተቋማት ትኩረትን ያገኘ ቦታ ነው። አደረጃጀት፣ የክህሎት ግንባታ ስራዎች እንዲሁም ሚዛናዊነት ሲጨመርበት ትልቅ ሀገራዊ ተቋም ይሆናል። እጅግ ቀናሁ።
ከ4 ሰዎች 1 ሰው ላይ የሚከሰተው የአእምሮ ጤና ሀገራዊ አጀንዳ (National agenda) የሚሆንበት ጊዜ ይናፍቀኛል። ታካሚዎች የተሟላ ተሀድሶ (Holistic rehabilitation) የሚያገኙበት፤ በባህላችን የተቃኘ የስነ ልቦና ህክምና (Culturally sensitive and culturally adapted psychotherapy) የሚሰጥበት፣ የህክምና ሳይንስ የደረሰባቸው ህክምናዎች (Cutting edge mental illness treatments) የሚገኙበት፣ የጎንዮሽ ጉዳታቸው ዝቅተኛ የሆኑ መድሀኒቶች ያለመቆራረጥ ያለበት ተቋም ተመኘሁ።
አንድ ቀን.....
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
1 193
ከምቀናባቸው ሰዎች -- ዶ/ር በርናንድ አንደርሰን
አሉላችሁ ደግሞ አንዳንድ ሰዎች..... ታድ..ድ..ድ..ለ..ው..ው..ው የሚያስብሏቸሁ…. አለ አይደል በመንገድ እንኳ እየተራመዳችሁ ትዝ ሲሏችሁ ፈገግ የሚያስብሏችሁ... ልባችሁን የሚያሞቁት፡፡ ከተኖረስ አይቀር እንደነሱ የምትሉላቸው፡፡
ከእነርሱ ውስጥ አንዱ ዶ/ር በርናንድ አንደርሰን ነው...ጃማይካዊው ጎንደሬ… ሮል ሞዴሌ፡፡ ስለ እርሱ ስተርክ ደስ ይለኛል፡፡ ለትምህርት ቤት ጓደኞቹ ስለእርሱ ሳወራላቸው ደስ ይለኛል፡፡ እንድቀናበት የሚያደርጉኝ እንደነዚህ ያሉ ታሪኮቹ ናቸው
“የቅርብ ጓደኞቹ በርኒ የሚሉት በርናንድ፤ የሕክምና ትምህርቱን ጨርሶ እንደተመረቀ ወደ ትዉልድ ሀገሩ ጃማይካ ተመልሶ በኪንግስተን የሕዝብ ሆስፒታል ማገልገል ጀመረ፡፡ ወትሮም የሕክምና ሙያ ለአምሳያ ፍጡር የመድረስ መንፈስ አለዉና ከዶ/ር በርናንድ አንደርሰን ዉስጣዊ ተፈጥሮና ተልዕኮ ጋር ገጠመ፡፡
“ሲሠራ ውሎ ቢያድር ደከመኝ የማይል፣ ‹ሕሙማንን ማከም ተልዕኮዬ ነው› ብሎ የሚያምን ሰው ነበር”
“እነ ማርክስ ጋርቬ “ወደ ራሳችን እንመለስ” ወዳሉባት ጥንታዊት ምድር ሄዶ የማገልገል ሕልም ነበረው.... ብዙ ጊዜ ሀገሬ ኢትዮጵያ ገብተን እንድንሠራ እነግረው ነበር፡፡ እርሱም በዚህ ላይ አስቦ እንደሚወስን ይገልጥልኛል፡፡ ከብዙ ጊዜ በኋላ አንድ ማለዳ ‹ላንቺ አስደናቂ ዜና አለኝ› አለኝ፡፡ በጉጉት ጠበቅኩ፡፡ ‹ላንቺ ስል ወደ ኢትዮጵያ ልሄድ ወሰንኩ› አለኝ፡፡›› ትላለቺ ሲሰተር እማዋይሽ ያንን ቀን ስታስታውሰው፡፡ … ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ፣ የድህነቱና የችግሩን መክፋት ተመለከተ፡፡ ነገር ግን አዘነ እንጂ ሸሽቶ አልተመለሰም
“በርካታ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጠዉ መጥተዉ ከየሆስፒታሉ ደጃፍ ተኮልኩለዉ አምላካቸዉን እየተማጠኑ፤ ከዕለታት አንድ ቀን የሐኪም እጅ እንዲነካቸዉ ሳምንታትን የሚጠብቁ ምስኪኖች ልቡን ነኩት፡፡ መንፈሱን ሳቡት፡፡ ጎንደርም በፍቅሯ ነደፈቺዉ፡፡ ቅርልኝ አለቺዉ
“የቀናት ስምና ቁጥር ለዶ/ር በርናንድ ዋጋ አልነበራቸዉም፡፡ ከአጸደ ሥጋ እስከተለየበት ጊዜ ድረስ ለእርሱ ቀናት ማለት የሥራና ሰዉን የማገልገያ ጊዜያት ናቸዉ፡፡ በበርናንድ ዘንድ ሥራ ሲያልቅ እንጂ ሰዓት ሲያልቅ ማቆም አይታሰብም፡፡ አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፡፡ እርሱና ተማሪዎቹ ከጠዋት እስከ ማታ ቀዶ ጥገና ሲያደርጉ ዋሉ፡፡ ምሳ አልነበራቸውም፡፡ ልክ ፀሐይዋ ማቆልቆል ስትጀምር ጨረሱ፡፡ ጨርሰው ልብሳቸውን ሲያወልቁ ግን አንድ የገጠር ሰው አንኳኩ፡፡ ‹ወረፋ እየጠበቅኩ ነበር›› አሉ ረዳት ሐኪሙን፡፡ ‹‹አባቴ አሁንማ መሸ ነገ ይምጡ›› አላቸው፡፡ አማራጭ አልነበራቸውምና ከዘራቸውን አንሥተው ጉዞ ጀመሩ፡፡ በርናርድ ድምጽ ሰምቶ ወጣ፡፡ ረዳቱን ጠየቀው፡፡ ረዳቱም ያደረገውን ነገረው፡፡ በርናርድ አዘነ፡፡ ‹‹እንዲህ ነበር ያስተማርኩህ›› አለው ረዳቱን፡፡ ‹‹በል ቶሎ ተከትለህ ጥራቸው›› ሲል አዘዘ፡፡ ሰውየው ተጠሩና እንደገና ልብስ ተለብሶ ቀዶ ጥገናው ቀጠለ፡፡ ይኼ ረዳት ሐኪም ዛሬ ታዋቂ የቀዶ ጥገና ሐኪም ሆኖ እንዲህ አለ ‹‹ያንን ትምህርት ስላስተማረኝ ተመርቄ ሰው የማይደርስበት ገጠር ገባሁ››
“አንድ ጊዜ እንዲህ ሆነ፡፡ አንዲት ምስኪን እናት መጡ፡፡ እርሱም አከማቸው፡፡ ድህነታቸው ማግኘት ያለባቸውን ሕክምና አልከለከላቸውም፡፡ ከቅኖች ጋር አምላክ ይሠራልና ሴትዮዋ በበርናርድ ታክመው ዳኑ፡፡ ከቀናት በኋላ ሊያመሰግኑት ወደ ሆስፒታሉ ተመለሱ፡፡ መርቀው መርቀው ጨረሱና ከጉንፋቸው እጃቸውን ሰድደው አንድ ነገር አወጡ፡፡ ዐሥር ብር፡፡ ‹‹ሌላ ምንም የለኝም፤ በዚህ ግን ምሳ ብላበት›› ብለው ሰጡት፡፡ ሰው አክባሪው በርናርድ ዐሥር ብሩን አመስግኖ ተቀበለና የዐሥር ብር ምግብ ወደሚሸጥበት ቦታ ሄዶ ምሳ በላላቸው፡፡
ዘርፈ ብዙ ተሰጥዖም ነበረዉ፡፡ በሥነ ሕክምናዉ በጣፊያና በጉበት ሕመም ለሚሰቃዩ በልዩ ጥበብ ብልቶቹ የሚሠሩበትን ዘዴ በምስል ነድፎ የባለቤትነት (ፓተንት) ያለዉ ባለሞያ ነበር፡፡ ዛሬ መዝገብ የያዛቸዉ በዓለም አቀፍ ደረጃ የባለቤትነት ዕዉቅና የያዘባቸዉ ሁለት መሣሪያዎች አሉት፡፡ የግጥም ስብስብ መጽሐፉ ርዕስ Limbic glimpses ይሰኛል፡፡ ዲዛይን በማድረግም ልዩ ችሎታ ነበረዉ፡፡ ዛሬ በአዞዞ የቆመዉ ሆስፒታሉም የ ዶ/ር አንደርሰን ዉጥን ነዉ፡፡
በ2007 ዓ.ም ሲያርፍ ጎንደር እንዲህ ብላ ገጠመችለት አሉ፡፡
“የማን ዘመድ ሞተ አትበለኝ ሀገሬ
ጎንደር ሰው ሞቷታል እናላቅሳት ዛሬ”
ታ….ድ…..ሎ!
ነፍስ ሔር
HAPPY DOCTORS DAY
ጋሻው አወቀ (የስነ አእምሮ ባለሙያ)
1 193
የሁለት ዋልታ ህመም | Bipolar disorder
1. መግቢያ |introduction
https://youtu.be/my8iD0QcpXY
2. ምልክቶቹ፣ አይነቶቹ እና መለያዎች | sign and symptoms, types and specifier
3. መንስኤው እና ቀስቃሽ ነገሮች | Cause and triggering factors
4. ስርጭቱ፤ እድገቱ እና ተጽኖው | Prevalence, Course and Effect
5. ህክምናው |Treatment
1 193
ሱስ ያሲዛሉ?
ቤተሰብ ከሚጠይቃቸው ተደጋጋሚ መድሀኒት ነክ ጥያቄዎች አንዱ ‹‹መድሀኒቶቱ ሱስ ያሲዛል ወይ›› የሚል ነው፡፡
፨ መልስ ፨
በስነ አእምሮ ህክምና ውስጥ የሚያገለግሉ ወደ 150 የሚጠጉ መድሀኒቶች ሲኖሩ ለህክምናው የሚሰጡ ቅድሚያ ተሰላፊ መድሀኒቶች (first lines) ለረጅም ጊዜ ቢወሰዱም ሱስ አያሲዙም፡፡ በአእምሮ ህክምና ትልቅ ክብደት የሚሰጣቸው እና ተኝቶ ወይም በተመላላሽ ህክምና የሚያስፈልጋቸው (ለሁለት ዋልታ [bipolar], ለድብርት፣ ለሱስ፣ ከእውን ለሚነጥሉ ህመሞች [psychosis]..... #የሚሰጡ_መድሀኒቶች_ሱስ_አያሲዙም፨ ስለዚህም ህክምናዎን ያለጭንቀት መከታተል ይችላሉ፡፡
ነገር ግን…. ከዋናው መድሀኒት በተጨማሪ አብረው የሚታዘዙ መድሀኒቶች ሱስ ሊያሲዙ ይችላሉ
1 ቤንዞዲያዜፓም
- በአብዛኛዎቹ ህመሞች ዘንድ የመጀመሪያ አማራጭ አይደሉም
- ቁጥጥር በሚደረግበት የተለየ ማዘዣ ወረቀት የሚታዘዙ
- አስገዳጅ የሆኑ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ለአጭር ቀናት ወይም ሳምንታት የሚሰጡ
- ከአልኮል ጋር ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸው፤ ከ3 ወራት በላይ በተከታይ ወይም ከሀኪም ትዕዛዝ ውጭ ከተወሰዱ ሱስ ያሲዛሉ
- አስቸኳይ ለውጥ ሲፈለግ ወይም አስገዳጅ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ የሚታዘዙ። እነርሱም
* የእንቅልፍ ችግር፡- አብዛኛው የእንቅልፍ ችግሮች በሌሎች የአእምሮ ህመሞች ምክንያት የሚመጣ ሲሆን ዋናው ህመም ሲስተካከል ይስተካከላሉ፡፡ ዋናውን ህመም የሚያክመው መድሀኒት ስራ እሰኪጀምርና መሻሻል እስኪመጣ ቀናት ወይም ሳምንታት ሊፈጅበት ስለሚችል እስከዚያ ድርስ ታካሚው እንቅልፍ እንዲያገኝ ሊታዘዙ ይችላሉ፡፡ ከቀናት ወይም ሳምንታት በኋላ ዋናው መድሀኒት መስራት ስለሚጀምር እና የስነ ልቦና ህክምናዎች ስለሚጨመሩ ይህኛው መድሀኒት ይቆማል፡፡ ስለዚህ ‹‹በመድሀኒት ሀይል የተኛ መድሀኒቱን ሲያቆም አይቸገርም ወይ›› የሚለው ጥያቄ እዚህ ላይ መልስ ያገኛል፡፡
* ከባድ ከሆነ የአልኮል መጠጥ በድንገት ማቆም፡- የብዙ አልኮል ተጠቃሚ የነበረሰ ሰው መጠኑን ሲቀንሰው ወይም ሲያቆመው ምቾት የማይሰጡ ምልክቶችን ያሳያል (አንዳንዶቹ እስከሞት የሚያደርሱ)፡፡ ይህ እንዳይፈጠር ለመከላከል እነዚህ መድሀኒቶች ናቸው፡፡ ይህ ህክምና ከ3 እስከ 5 ቀን ብቻ የሚቆይ ስለሆነ ሱስ አያሳስበንም፡፡
* አስቸኳይ መሻሻል ሲፈለግ፡- ለምሳሌ ድንገተኛ ሽብረት (panic attack) ወይም የማህበር ፍራቻ (social phobia) የመሳሰሉ የጭንቀት ህመሞች እጅግ አስጨናቂ ስለሆኑ እና አስቸይ መፍትሔ ስለሚሹ፤ ሌሎች ህክምናዎች (SSRI or SNRI and psychotherapy) መስራት እስኪጀምሩ ድረስ ሊሰጡ ይችላሉ
* ለህይወት አስጊ የሆኑ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ፡- ታካሚው በሌላ ማረጋጊያ ዘዴዎች አልረጋጋ ያለ ከፍተኛ መታወክ ውስጥ ሲገባና ራሱን ወይም ሌላ ሰው ላይ ጉዳት ሊያደርስ ከሆነ እነዚህ መድሀኒቶች ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ሲያስፈልግ ብቻ በመርፌ ስለሚሰጥ ሱስ አያሳስበንም፡፡
* ጡንቻ ገትር (catatonia)፡- በከፍተኛ ሁኔታ የታመሙ ታካሚዎች ለተከታታይ ቀናት ምግብና ውሀ ላይወስዱ፣ ላይንቀሳቀሱ፣ ሰውነታቸው ድርቅርቅ ሊልና መንቀሳቀስ ሊያቆሙ፣ መናገር ሊያቆሙ…. ይችላሉ፡፡ ይህንን የሚያክሙት እነዚህ መድሀኒቶች ሲሆኑ ለጥቂት ቀናት ብቻ ስለሚሰጥ ሱስ አያሳስበንም
* የማያቋርጥ የሚጥል በሽታ፡- የዚህ ህመም ታካሚ በመሀል ሳይነቃ በተደጋጋሚ ከጣለው ከፍተኛ አደጋ ላይ ይጋለጣል ይህንን የሚያስተካክሉ እነዚህ መድሀኒቶች ናቸው፡፡
* እና ሌሎችም…
- በጠቅላላው፤ በሀኪም ትዕዛዝ መሰረት ከተወሰዱ ሱስ አያሳስበንም፡፡
2. ማርከሻ መድሀኒቶች
- ለአእምሮ መታወክ የሚሰጡ አንዳድ መድሀኒቶች የእንቅስቃሴ ችግር ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ይህንን ለማርከስ የሚሰጠው መድሀኒት ሱስ እንደሚያሲዝ ሪፖርት ተደርጓል፡፡ ስለዚህም ታካሚው በታዘዘው መሰረት ብቻ (የእንቅስቃሴው ችግር ሲፈጠር ብቻ አንድ ጊዜ) መውሰድ ይኖርበታል፡፡
፨ለማጠቃለል፡ በሀኪም ትዕዛዝ መሰረት ከተወሰዱ ሱስ አያሳስበንም፡፡ ስለ ህክምናዎ ጥያቄ ካለዎት በህክምና ቡድኑ ውስጥ ያለውን የጤና ባለሙያ ለመጠየቅ አያንገራግሩ!፨
ጋሻው አወቀ (የስነ አእምሮ ባለሙያ)
t.me/gashaw_aweke
1 193
A Portrait of A Young Ethiopian Lady; A Bipolar Med-student.
.
Hmmmm….i Dont know how to broach this topic …Let’s just begin with this imprudent introduction of mine. My name is Fasika Alemayehu, 5th year Medical student in Addis Ababa University, school of medicine in Ethiopia. And fortunately or say it unfortunately am bipolar (Type I).
.
I have been diagnosed with manic depression about 2 years ago, quite a disaster honestly. It was during my surgery clinical rotation (my favorite – infact i wanted to be a cardiothoracic surgeon). Unfortunately, i was manic and reckless and had done lots of staff to seniors that i end up repeating the year. A very trembling experience; Its when i learnt that physical illness is much better than mental. Why? Because physical you get sympathy but mental illness you get stigma, judgment,pity, to be seen as a wicked or cursed, a sinner and especially in developing countries like Ethiopia mentally ill person is presumed to be possessed by the demons (I have experienced this first hand). To my dismay, the dehumanization is not only seen in the society but also in some psychiatric wards and even by some imbecile psychiatrists.
.
Bipolar or manic depression according to American Psychiatric Association Diagnostic and statistical manual (DSM V) definition; it is a group of brain disorders that causes extreme fluctuation in a person’s mood, energy and ability to function. BD is a category that includes three different conditions; Bipolar I, II and cyclothymic disorder. For further information Google it. In short it is a chronic severe mental illness that requires life time struggle. Yes i know it seems obscene. The good news is its manageable. How? I really don’t know frankly speaking am still struggling.
.
I dont know what kept me going however, am a striving patient with a proper professional Help: I try to read books related to the illness, my proximity to the medical world as a student helped me a lot. I am grateful for my support system, I have 5 altruistic Best friends and supportive family. I am on a mood stabilizer and antidepressants. My Psychiatrist is Dr. Yonas Bahretibebe (who is a humble and intelligent gentleman with a fatherly figure, authour of aynen temelketegn (a book about autism), currently writing a book about Manic-depression and owner of sitota psychiatric center) my psychiatrist who doesn’t like labeling. Labeling here means – your name is your illness.
.
And then i read the book ‘The silver lining play book’ which narrates the romance between a bipolar and unipolar depression couple. It made me to realize the silver lining of my illness! That is, it is a disease of scientists and artists, it is highly associated with higher IQ, creativity and good memory. Which causes which, is still a controversy. And during depression we know pain, and sadness, it makes us understanding and caring. Overall, we have hope!
.
Furthermore, I am a medical student. I have easy access to books, videos, psychiatrists, psychologists and so on. And I would be pleased to share my struggle with others, so that they know it is possible to have a healthy and productive life and to say “you are not alone!”.
.
According to Richard P. Bentall Associate professor of clinical psychology(author of Madness explained), he demonstrates that there is no clear dividing line between sanity and insanity. Some of us need a cocktail of tablets to look sane, some shower, some holywater … You name it. The point is we all have our own issues. I believe this blog will help those who are on the same boat. Mental health is achievable: In other words, look at me am doing this so can you!
.
Stay tuned with the coming stories…
Cheers!
