en
Feedback
WeMind Ethiopia

WeMind Ethiopia

Open in Telegram

Comprehensive Mental Health Resources Across Ethiopia

Show more
1 193
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-1030 days
Posts Archive
Happy Birthday
Happy Birthday

ሪፖርተር ጥቅምት 21 ቀን 2016 ለአእምሮ ህሙማን አስተማማኝ የመድሀኒት አቅርቦት እንዲኖር እንፈልጋለን @gashaw_aweke
ሪፖርተር ጥቅምት 21 ቀን 2016 ለአእምሮ ህሙማን አስተማማኝ የመድሀኒት አቅርቦት እንዲኖር እንፈልጋለን @gashaw_aweke

አይዞሽ

ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ጥቅምት 24 ቀን 2016 ዓም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል:: የዚህ ወር ርዕስም፡- “የአእምሮ
ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ጥቅምት 24 ቀን 2016 ዓም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል:: የዚህ ወር ርዕስም፡- “የአእምሮ ቁስል (Trauma) በህይወታችን ላይ የሚያስከትለው ተፅዕኖ” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳችን የትራውማ ሳይካያትሪስት የሆኑት ዶ/ር ቢንያም ወርቁ ናቸው፡፡ ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡ https://forms.gle/XwpMCVAumak4n7Aj7 የማስታወሻ መልእክት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ https://t.me/mhaddisababa The monthly Mental Health Addis’ event has come and it will be held on Novemeber 4, 2023 at Adore Addis Hotel (near Atlas) in the afternoon at 10:00 local time. This time topic is “Trauma and Its Effects on Our Lives.” Our guest speaker is a Trauma Psychiatrist Dr. Benyam Worku. To attend please register by filling this Google form:- https://forms.gle/XwpMCVAumak4n7Aj7 To get a reminder please join our Telegram Channel: https://t.me/mhaddisababa #mentalhealth #AdoreAddis #mentalhealthawareness #talkmentalhealth #mentalhealthmatters

photo content

Panic attack and Panic disorder - (ድንገተኛ  የመረበሽ ስሜት እና ህመም) 🔹 መንገድ እየተሻገርን ነው ድንገት በፍጥነት መኪና ቢመጣብን፤ የተሳፈርንበት መኪና ከሌላ መኪና ሊጋጭ ሲል የሚገጥመንን ስሜት አስታዉሱ፡፡ ለእንደዚህ አይነት እዉነተኛ አደጋዎች አእምሮአችን ቅጽበታዊ ምላሽ በመሰነድ አድሪናሊን የተባለ ንጥረ-ቅመም እንዲመነጭ ያደርጋል፡፡  ይህም ሩጠን እንድንሸሽ ብሎም ቅጽበታዊ ምላሽ እንድንሰጥ ያደርጋል፡፡ 🔹 አንዳንዴ በተለያየ ምክንያቶች አእምሮአችን ተጨባጭ አደጋዎች በሌሉበት ሁኔታ መደንገጥ ለሌለብን ነገሮች ነገሮች ጭምር የተሳሳተ አተረጉዋጎም በመስጠት አድሪናሊን እንዲመነጭ ያደርጋል፡፡ 🔹ይህም ከፍተኛ  መረበሽ ስሜትስሜት ውስጥ እንድንገባ ያደርገናል፡፡ ይህ ክስተት panic attack ይባላል፡፡ 🔸ፓኒክ አታክ ድንገቴ የሆነ የመረበሽ ስሜት ሲሆን: በይሆናል ለታሰበ ጭንቅ ፈጣሪ ሁነት የሚሰጥ የተጋነነ አእምሯዊ እና አካላዊ ስሜት ነው:: 🔸ይህ የመሸበር ስሜት በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ጣራ የሚነካ እና በደቂቃዎች ውስጥ የሚጠፋ ነው፡፡ 🔸 በዚህ ድንገቴ የመረበሽ ወቅት ሰውነታችን ሊያሳያቸው የሚችሉ 13 ገደማ ምልክቶች አሉ:: 🔸 ከነዚህ ምልክቶች 11ያህሉ አካላዊ ቀሪ ሁለቶቹ ደሞ አእምሯዊ ምልክቶች ናቸው:: ምልክቶቹ:- 1️⃣ልባችን በሃይል መምታት: ልብ በሃይል ስትመታ መታወቅ፣ 2️⃣ ማላብ፣ 3️⃣ ማንቀጥቀጥ፣ 4️⃣ ትንፋሽ ማጠር፣ 5️⃣አንገታችን የመታነቅ ስሜት መሰማት፣ 6️⃣ ደረት አካበቢ ምችት መንሳት፣ 7️⃣ማጥወልወል ወይንም የሆድ ምቾት መንሳት፣ 8️⃣የማዞር: የድንግዝግዝ ስሜት: መንገዳገድ: ወይንም ራስን መሳት፣ 9️⃣ብርድ ብርድ ወይንም ሙቀት ሙቀት ማለት፣ 10. የእጅና እና እግር መደንዘዝ ወይንም መቆጥቆጥ፣ 11.  ለራስ ወይንም ለከባቢ የእንግድነት ስሜት መሰማት፣ 12. ከቁጥጥር ውጭ የሆኑ ያህል ወይንም ወደ እብደት የሄዱ ያህል መሰማት፣ 13. ሊሞቱ ወይንም ነብሳቸው ልትወጣ የደረሰች ያህል መሰማት:: 🔹አንድ ሰው ፓኒክ አታክ አጋጠመው ለማለት ከ 13 ምልክቶች ቢያንስ አራቱን ማሟላት ይኖርበታል:: 🔹 እነዚህ ምልክቶች ካለምንም አባባሽ ሁኔታዎች አልያም በተለያዩ አባባሽ ምክንያቶች ጋር ተያይዘው ሊከሰቱ ይችላሉ:: ✅ አባባሽ ምክንያቶች: *ሰው የተሰባሰበበት ቦታ የሚከሰቱ ( Social Anxiety Disorder with panic attack specifier): ከሚፈሩት ነገር ጋር ሲጋፈጡ(በ specific phobia with panic attack specifier): ድህረ አደጋ አደጋውን ለሚያስታውሱ ሁነቶች ሲጋለጡ( Post traumatic stress disorder with panic attack specifier): * የታወቀ ህመም ካለባቸው ህመሙ በራሱ የሚያመጣቸው የፓኒክ አታክ ምልክቶች( አስም: የእንቅርት ህመም: የልብና የመተንፈሻ አካል ህመሞች) መድሃኒቶች: እጾች(ቡና ጫት እና ሌሎች አነቃቂ ንጥረ ነገሮች) 🟫 Panic Disorder- ✔  ከአንድ በላይ ፓኒክ አታኮች ካለምንም ቅድመ አባባሽ ሁነት ሲከሰቱ: ✔ ይህንም ተከትሎ ድጋሚ ፓኒክ አታክ እንዳይከሰት ወይንም ስለ ፓኒክ አታኩ ጦስ አብዝቶ መጨነቅ ወይንም ፓኒክ አታኩን ሊያመጡ ይችላሉ ተብለው ከታሰቡ ነገሮችን ለመራቅ መሞከር ሲኖራቸው: ✔ ፓኒክ አታኮቹ በመድሃኒት: በእጾች ወይንም በህመሞች ምክንያት እንዳልተከሰቱ ሲረጋገጥ: ✔ ከሌሎች የአእምሮ ህመሞች ጋር ተያይዞ እንዳልተከሰተ መረጋገጥ ሲችል ፓኒክ ዲሶርደርን ማሰብ ይቻላል:: 🛑 ህክምናው:- 🔹መድሃኒቶች:- ጸረ ጭንቀት መድሃኒቶች(Anxiolytics) 🔹 የስነ ልቡና ህክምናዎች    Cognitive behavioral therapy • ይህ ህመም ያጋጠማቸው ሰዎች አካላዊ ምልክቶቻቸውን የማጉላትና የመጥፎ ነገር ማሳያዎች እድረገው መሳላቸው የበለጠ ለጭንቀት እንደሚዳርጋቸው ይታመናል:: • ስለዚህም ነገሮችን ባላስፈላጊ ሁኔታ የማጉላትና የማወሳሰብ እና ሌሎች ጠቃሚ ያልሆኑ አስተሳሰቦችን በመለየት የማሻሻል ሂደት አንዱ የህክምናዉ አላማው ነው:: • ሌላው ባህርይን መሰረት ያደረገ ( ገና ለገና ነገሮች ፓኒክ አታክ ያመጡብናል ብለው ያሰባቸውን ሁነቶች በተጋነነ ሁኔታ ለመራቅ  የሚያደርጉትን ሙከራ እንዲያሻሽሉ: እነዚህ የሚፈሯቸው ነገሮች በርግጥም የታሰበውን ምልክት እንደማያስከስቱ እንዲረዱ ለነገሮች እና ሁኔታዎችን እንዲጋፈጡ በማድረግ : አየር ወደውስጥ እያስገቡና እያስወጡ ሰውነትን ከመረበሽ ስሜት የማስወጣት መንገዶችንና መሰል ራስን የማረጋግያ መንገዶችን እንዲጠቀሙ በማድረግ:: 🔹ራስን የማረጋጊያ ኤክሰርሳይስ- ትንፋሽ በደንብ በመሳብና በማስወጣት: የሰውነትን ጡንቻዎች በማፍታታት: ዮጋ መስራት የመሳሰሉት ተግባሮች ያግዛሉ:: ማጠቃለያ • ፓኒክ አታክ እና ዲሶርደር መታከም የሚችል ህመም ነውና እነዚህ ምልክቶች ሲሰሙን የአእምሮ ባለሞን መማከር ብልህነት ነው፡፡ ቸር ይግጠመን! ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው፡ የስነ-አእምሮ ሬዚደንት ሃኪም 🔹

photo content

🌟 Join the Giving for Living Campaign 🤝 Urgent Call for Help! Meet Tirualem Negash, a courageous 26-year-old woman facing a critical health crisis. Both of Tirualem's kidneys have been plagued by stones, sadly resulting in the failure of her left kidney. Following her recent discharge from Black Lion Specialized Hospital, the remaining right kidney is now severely damaged and suffering from severe hydronephrosis. Despite being under close monitoring at the hospital, Tirualem's treatment has been abruptly halted due to lengthy waiting times and machine breakdowns. As a result, she is enduring excruciating pain caused by the stone and cyst. In desperate need of an alternative, Tirualem has been quoted a daunting amount of 150,000 Birr for treatment at another hospital. Unfortunately, without any family support and working as a courier, she is unable to cover the cost alone. We kindly implore you to reach out and support her before her last kidney shuts down. 💙 Together, let's make a life-saving impact for Tirualem! 💙 We humbly call upon our compassionate community to rally behind Tirualem in her time of need. Your generous contributions, no matter the amount, hold the power to provide her with essential medical care, offering hope and a chance at recovery. Here's how you can make a difference: 💪 Donate: Visit the secure link below to make a donation towards Tirualem's urgent medical needs. Every contribution, big or small, will directly assist in funding his critical treatment. [CBE- 1000005927025] Tirualem Negash 📣 Share: Spread awareness far and wide! By sharing Tirualem's story and urgent plea for assistance, you become a vital catalyst for change, reaching more caring hearts and potential support networks. ✨ Support: Extend a kind hand to Tirualem and her family by offering words of encouragement and empathy. Let them know that they are not alone in this challenging journey, and that we stand united in support. Remember, even a simple act of compassion can create a ripple effect of hope and transform lives. Together, we possess the collective power to be Tirualem's lifeline. Let's unite and ignite positive change! 🌟 #HelpTirualem #GivingForLiving #SupportingHealthcare #CommunityMatters

እንድትደርሱልኝ እማጸናለሁ #Ethiopia | እኔ ጥሩዓለም ነጋሽ እባላለሁ። የ26 ዓመት ወጣት ስሆን በሁለቱም ኩላሊቶቼ በጠጠር ተሞልተው የግራ ኩላሊቴ ሥራ ስላቆመ በቅርቡ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይ
+3
እንድትደርሱልኝ እማጸናለሁ #Ethiopia | እኔ ጥሩዓለም ነጋሽ እባላለሁ። የ26 ዓመት ወጣት ስሆን በሁለቱም ኩላሊቶቼ በጠጠር ተሞልተው የግራ ኩላሊቴ ሥራ ስላቆመ በቅርቡ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀዶ ህክምና ወጥቶ ነበር፡፡ የቀረውም የቀኝ ኩላሊቴ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ በጠጠር በመጎዳቱ፤ ቀኝ ኩላሊቴ ከፍተኛ የሆነ ውሀ የመቋጠር ችግር (severe hydronephrosis) ገጥሞታል፡፡ ለዚህ ክህክምና በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ክትትል እያደረኩኝ ቢሆንም ባለው ረጅም ወረፋ እና ማሽን መበላሸት ምክንያት ህክምናው ተቋርጦብኛል፡፡ አሁን ላይ በጠጠሩ ምክንያት ከፍተኛ ህመም ውስጥ እገኛለሁ፡፡ ይህንን ህክምና በሌላ ሆስፒታል ለማግኘት 150,000 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ) ብር የተጠየቅሁ ሲሆን እኔ ደግሞ የቤተሰብ እርዳታ የሌለኝና ስራዬም መልዕክተኛ በመሆኑ ወጪውን መሸፈን አልቻልኩም፡፡ ያለኝን አንድ ኩላሊት መስራት ከማቆሙ በፊት እንድትደርሱልኝ እማጸናለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቁጠባ ሃሳብ ቁጥር 1000005927025

እንድትደርሱልኝ እማጸናለሁ #Ethiopia | እኔ ጥሩዓለም ነጋሽ እባላለሁ። የ26 ዓመት ወጣት ስሆን በሁለቱም ኩላሊቶቼ በጠጠር ተሞልተው የግራ ኩላሊቴ ሥራ ስላቆመ በቅርቡ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀዶ ህክምና ወጥቶ ነበር፡፡ የቀረውም የቀኝ ኩላሊቴ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ በጠጠር በመጎዳቱ፤ ቀኝ ኩላሊቴ ከፍተኛ የሆነ ውሀ የመቋጠር ችግር (severe hydronephrosis) ገጥሞታል፡፡ ለዚህ ክህክምና በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ክትትል እያደረኩኝ ቢሆንም ባለው ረጅም ወረፋ እና ማሽን መበላሸት ምክንያት ህክምናው ተቋርጦብኛል፡፡ አሁን ላይ በጠጠሩ ምክንያት ከፍተኛ ህመም ውስጥ እገኛለሁ፡፡ ይህንን ህክምና በሌላ ሆስፒታል ለማግኘት 150,000 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ) ብር የተጠየቅሁ ሲሆን እኔ ደግሞ የቤተሰብ እርዳታ የሌለኝና ስራዬም መልዕክተኛ በመሆኑ ወጪውን መሸፈን አልቻልኩም፡፡ ያለኝን አንድ ኩላሊት መስራት ከማቆሙ በፊት እንድትደርሱልኝ እማጸናለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቁጠባ ሃሳብ ቁጥር 1000005927025

ግርሻን መከላከል (Relapse prevention) ```````````` 💎 እንደ ሌሎች ስር የሰደዱ አካላዊ ህመሞች፤ ስር የሰደዱ የአእምሮ ጤና ችግሮችም ክትትል ካልተደረገላቸው ሊያገረሹ ይችላሉ፡፡ ታካሚው ሙሉ ለሙሉ አገግሞ ወይም ሳያገግም የህመሙ ምልክቶች እንደገና መታየት ሲጀምሩ ህመሙ አገረሸ እንላለን፡፡ ▶️ብዙውን ጊዜ ግርሻ የሚፈጠረው በሚከተሉ ምክንያቶች ነው - መድሀኒተን ማቆም - ውጥረት ውስጥ መግባት አልኮል፤ ሲጋራ፤ ጫት እና ሌሎች አደንዣዝ እጾችን መጠቀም ▶️ አንዳንድ ግርሻዎች ቀስ በቀስ (በሳምነታት ውስጥ) ሲከሰቱ፤ በፍጥነት ያለ ማስጠንቀቂያ ምልክት (በቀናት ውስጥ) የሚከሰቱም ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ የአንዳንድ ህመም ታካሚዎች ታካሚዎች ብዙዉን ጊዜ እነዚህን ምልክቶች አይረዷቸውም፡፡ ለምሳሌ የመነጫነጭ ስሜት እንደጀመረዎት ከመረዳት ይልቅ ሰዎቹ ሁሉ አናዳጅ ሁነው ሊታዩዎት ይችላሉ፡፡ ▶️ ሁሌም ከመታከም አስቀድሞ መከላከል የተሻለ ነው፡፡ ህመሙ አገርሽቶ ከመታከም ይልቅ እንዳያገረሽ መጠንቀቁ እጅጉን ይበልጣል፡፡ ህመምዎ ሊያገረሽ ከሆነ ማስጠንቀቂያ ምልክት ይሰጥዎታል፡፡ ለየሰዉ የተለያየ ሊሆን ቢችልም የተለመዱ የግርሻ ማስጠንቀቂያ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡ - መወጠር እና መረጋጋት አለመቻል - የእንቅልፍ ችግር, ድብርት, መነጫነጭ - ከሰው የመነጠል ፍላጎት - ትኩረት ለማድረግ መቸገር - መድሀኒቶችን ወይም ሌሎች ህክምናዎችን ማቆም አልያም መቀነስ- ከመጠን በላይ ወይም በታች መመገብ ▶️ እንደቤተሰብ ግርሻን መኖሩን እና አለመኖሩን ለመረዳት ራሰዎን የሚተሉትን ጥያቄዎች መጠየቅ ይኖርብዎል - በነዚህ ሳምንታ ያልተለመዱ ለውጦች በታካሚው ላይ ተፈጥረዋል? - የባለፈው ግርሻ ከመከሰቱ በፊት የተከሰቱ ምልክቶች አሁን አሉ? ▶️ ማስጠንቀቂያ ምልክቶችን ሲታዘቡ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች - ከቤተሰበዎ ጋር በጉዳዩ ይወያዩ - ታካሚው መድሀኒቱን በሚገባ እየወሰደ መሆኑን ይመርምሩ - ሱሶችን እየተጠቀመ መሆን አለመሆኑን ይመርምሩ - ታካሚው የገባበት ጫና ካለ ይለዩና እንዴት መቀነስ እንደሚችሉ ይመልከቱ - የመድሀኒት መጠን መጨመር ያስፈልገው እንደሆነ ሀኪምዎን ደውለው ያናግሩ t.me/Gashaw_Aweke ጋሻው አወቀ (የስነ አእምሮ ባለሙያ)

ሱስ እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ክፍል 01 ዶ/ር ግርማ ማሞ ዶ/ር ግርማ ማሞ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊንየም ሜዲካል ኮሌጅ የስነ አእምሮ ረዳት ፕሮፌሰር የህክምና መምህር ሲሆኑ ከ16 ዓመታት በላይ በሱስ
ሱስ እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ክፍል 01 ዶ/ር ግርማ ማሞ ዶ/ር ግርማ ማሞ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊንየም ሜዲካል ኮሌጅ የስነ አእምሮ ረዳት ፕሮፌሰር የህክምና መምህር ሲሆኑ ከ16 ዓመታት በላይ በሱስ ህመም ላይ ህክምና እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ▶️ መቅድም ▶️ መግቢያ ▶️ የንጥረ ነገር ሱስ ምን ማለት ነው ▶️ በኢትዮጵያ የተለመዱ ሱስ አምጪ ነገሮች ▶️ ሱስ እንዴት ይጀመራል ▶️ ታዳጊዎች ሱስ አምጪ ነገሮችን መጀመራቸውን ጠቋሚ ምልክቶች ▶️ የንጥረ ነገር ሱስ ምልክቶች ▶️ የሱስ ጉዳት ▶️ የሱስ ህክምና ምን ይመስላል https://youtu.be/ThHtR1Tmg6Q

ደራሲ ሲዲኒ ሸልደን "The other Side of me" የሚል የግለ ታሪክ መፅሐፍ አለው። እንዲህ ገናና ስም ከመገንባቱ በፊት እንዴት ያለ ፈተናን እንደተጋፈጠ እና ተስፋ ለመቁረጥ ተዳርጎ እንደነበ
ደራሲ ሲዲኒ ሸልደን "The other Side of me" የሚል የግለ ታሪክ መፅሐፍ አለው። እንዲህ ገናና ስም ከመገንባቱ በፊት እንዴት ያለ ፈተናን እንደተጋፈጠ እና ተስፋ ለመቁረጥ ተዳርጎ እንደነበር አብራርቷል። በወጣትነት ዘመኑ በድብርት ህመም ይሰቃይ ነበር። ሙከራው ደጋግሞ ይከሽፍበታል፥ አሸነፍኩ ሲል ይሸነፋል፥ አገኘው ባለ ማግስት ያጣል። አንድ ቀን ጨለማ የነገሰበት የሚመስለውን አታካች  ኑሮውን አሰላሰለ። ያኔ መኖር አታክቶት ራሱን ሊያጠፋ ወሰነ። ራሱን ለማጥፋት ከሞከረ በኋላ አባቱ የማይዘነጋ ምክር ለገሰው። "ህይወት መፅሐፍ ናት፥ እያንዳንዱ ቀን የመፅሐፉ አንድ ገፅ ነው። መፅሐፉ ተነቦ ሳያልቅ አትዝጋው" አለው። ከዚህ በኋላ ቆም ብሎ አሰበ። "በገዛ ፈቃዴ ራሴን በመግደል የህይወቴ ገፅ እንዳይነበብ አላደርግም" አለ። ከዚህ በኋላ በመላው አለም ስሙ የናኘ ደራሲ ሆነ። በእርግጥ ህይወታችን መፅሐፍ ብትሆን እያንዳንዱ ቀናት የመፅሐፉ ገፅ ናቸው። በመከራ መካከል ብንሆንም መፅሐፉ ተነቦ ሳያልቅ አንዘጋውም። ነገ ሌላ ቀን ነው፥ በድንግዝግዝ መሐልም ብንሆን እንኳ ሽራፊ ተስፋ አለ። እውነት መስሎ ባይታይም ጨለማው ይገፈፋል። © Alex Abreham

photo content

photo content