en
Feedback
WeMind Ethiopia

WeMind Ethiopia

Open in Telegram

Comprehensive Mental Health Resources Across Ethiopia

Show more
1 193
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-1030 days
Posts Archive
• ከእርግዝና አንስቶ ልጁ እስከተወለደ ባለው ጥቂት ጊዜ ውስጥ እናቶች ላይ የስሜት እና የባህሪ ለውጦች ሊከሰቱ ይችላሉ • የእርግዝና ጋር የተያያዘ የሀዘን ስሜቶች (Postpartum Blues) በብዙ እናቶች ላይ ይከሰታል፡፡ ይህ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ሲሆን የስሜት መለዋወጦች፣ መነጫነጭ፣ “አልቅሽ አልቅሽ” የሚል ስሜት፣ ጭንቀት፣ የእንቅልፍ ማጣት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ድካም ድካም የሚል ስሜት እና የመሳሰሉትን ምልክቶች ይይዛል፡፡ • ይህ የስሜት ለውጥ ያጋጠማቸው 20 በመቶ በሚሆኑ እናቶች ወደ ህመምነት (Postpartum Depression) ሊለወጥ ይችላል፡፡ ሀዘን፣ ንጭንጭ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ድካም፣ የጥፋተኝነት ወይም የአልረባም ስሜት፣ ራስን ወይም ልጁን ለመጉዳት ማሰብ፣ ፍላጎት ማጣት የመሳሰሉት ስሜቶች ሊከሰቱባት ይችላሉ፡፡ • ብዙ ያልተለመደ ቢሆንም (ከ1000 እናቶች አንድ ወይም ሁለቱ) የሌሉ ድምጾችን መስማት፣ የተዛቡ አስተሳሰቦችን መያዝ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ራስን ስለማጥፋት ማሰብ፣ ልጁን ለመጉዳት መፈለግ…. እና የመሳሰሉት (Postpartum psychosis) ሊያጋጥም ይችላል፡፡ @gashaw_aweke

ከእያንዳንዷ ጠባሳ ጀርባ፥ ያልተነገረ የአሸናፊነት ታሪክ አለ:: #Share @gashaw_aweke

https://youtu.be/ayrjuV8bhEM በቦሌ ደ/ም/ቅ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የአእምሮ ጤና እና ህመምን በተለመለከተ የተደረገ የጋራ ምክክር ክፍል 03

ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ጥር 4 ቀን 2016 ዓም በብይነ መረብ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል:: በዕለቱ በአእምሮ ጤና ዙሪያ የሚያጠነጥነው “የሁሉ” የልብወለድ መፅሃ
ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ ጥር 4 ቀን 2016 ዓም በብይነ መረብ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል:: በዕለቱ በአእምሮ ጤና ዙሪያ የሚያጠነጥነው “የሁሉ” የልብወለድ መፅሃፍ ላይ ከዶ/ር አዜብ አሳምነው ከዶ/ር ዮናስ ላቀው እንዲሁም ከደራሲው ከዶ/ር ዳዊት አሰፋ ጋር የኦንላይን ውይይት ይደረጋል፡፡ በዕለቱ ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡፡ https://meet.google.com/gsd-iztg-rop The monthly Mental Health Addis’ event will take place on Saturday January 13, 2024 at 4:00 PM. On the day, there will be an online discussion on the book written in Amharic by Dr Dawit Assefa by the title “Yehulu”. We will have time with Dr Azeb Asamenew, Dr Yonas Lakew and Dr Dawit Assefa. Please use this link to be part of the discussion, on the day. https://meet.google.com/gsd-iztg-rop #mentalhealthmatters #mentalhealth #health #yehulu

Š Tewedros Regassa
Š Tewedros Regassa

ውጥረትን መቀነስ/መቋቋም ክፍል 01 ለህመም እንድንጋለጥ ወይም ህመሙ ተመልሶ እንዲያገረሽ ከሚያደርጉት ዋና ዋና ምክንያቶ ውስጥ ውጥረት አንዱ ነው፡፡ ውጥረት (stress) ማንኛውም ጫና የሚፈጥርብን ነገር ሲሆን ምልክቶች መልሰው እንዲያገረሹና ወደ ሆስፒል እንድንገባ ሊያስገድዱን ይችላሉ፡፡ የሚከተሉትን ልብ ይበሉ ▶️ ውጥረት ውስጥ የሚከትዎትን ነገር መለየት አንድ ሰው ላይ ጫና የፈጠረው ሌላ ሰው ላይ ጫና ላይፈጥር ይችላል፡፡ ሆኖም በዋናንት ውጥረት ከሁለት ነገር ይመነጫል 1. የሕይወት ኩነቶች (Life events) ▪️ጫና ውስጥ የሚከቱ ነገሮች ከሰው ሰው የሚለያዩ ቢሆኑም ልጅ መውለድ፤ አዲስ ስራ መጀመር፤ ቦታ መቀየር፤ መታመም፤ የቤተሰብ አባል በሞት መነጠል፤ ፍቺ… እንምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ 2. ተደጋጋሚ ጫናዎች (Ongoing Stressors) ▪️ ለምሳሌ በገንዝብ አቅም መዳከም፤ የሚረብሽ ድምጽ ያለባቸው ቦታዎች፤ ተደጋጋሚ ግጭቶች፥ የቤት ዕጦት... ▶️ ለገቡበት ውጥረት የሚያሳዩትን ምላሽ ያስተውሉ - ለምሳሌ፤ ራስ ምታት፤ የምግብ አለመፈጨት፤ የልብ ምት መጨመር፤ ድብርት፤ ጭንቀት፤ መረጋጋት አለመቻል፤ ጥፍር መብላት፤ ቱግ ማለት፤ መጠጣት….. ✅ አንድ ነገር ከማድረገዎ በፊት ምን አይነት ምላሽ መስጠት እንዳለበዎ ያስቡ፡፡ ምክንያቱም ውጥረት ውስጥ ስንሆን ወዲያውን የምንሰጣቸው ምላሾች ችግሩን የባሰ ከማወሳሰብ የዘለለ ፋይዳ የላቸውም፡፡ ከእነዚህም መጮህ፤ ራስን ጥፋተኛ አድርጎ መኮነን፤ ውጥረቱን እንዳላዩ ሆኖ ማለፍ… ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ✅ የሚከተሉት የተሻሉ አማራጮች ናቸው 1። የውጥረትን ምንጭ መቀነስ - ካሁን በፊት ውጥረት ውስጥ የከተቱዎተን ነገሮች ያስወግዱ ወይም ያስተካክሉ - ከመጠን በላይ አይጠብቁ፤ ምክንያታዊ ግብ ይኑርዎት (avoid too much expectations) - ትርጉም የሚሰጡዎት ተግባራት ላይ ያሳልፉ (ስራ፤ በጎ አድራጎ፤ ሙዚቃ፤ ስፖረት…) - መደበኛ የእረፍትና የመዝናኛ ጊዜ ይኑርዎት - ራሰዎን ያለልክ አይተቹት፤ ለራስዎ ደግ መሆንን ይለማመዱ፡፡ ጋሻው አወቀ (የስነ አእምሮ ባለሙያ) t.me/gashaw_aweke ይቀጥላል

ደራሲ ሲዲኒ ሸልደን "The other Side of me" የሚል የግለ ታሪክ መፅሐፍ አለው። እንዲህ ገናና ስም ከመገንባቱ በፊት እንዴት ያለ ፈተናን እንደተጋፈጠ እና ተስፋ ለመቁረጥ ተዳርጎ እንደነበ
ደራሲ ሲዲኒ ሸልደን "The other Side of me" የሚል የግለ ታሪክ መፅሐፍ አለው። እንዲህ ገናና ስም ከመገንባቱ በፊት እንዴት ያለ ፈተናን እንደተጋፈጠ እና ተስፋ ለመቁረጥ ተዳርጎ እንደነበር አብራርቷል። በወጣትነት ዘመኑ በድብርት ህመም ይሰቃይ ነበር። ሙከራው ደጋግሞ ይከሽፍበታል፥ አሸነፍኩ ሲል ይሸነፋል፥ አገኘው ባለ ማግስት ያጣል። አንድ ቀን ጨለማ የነገሰበት የሚመስለውን አታካች ኑሮውን አሰላሰለ። ያኔ መኖር አታክቶት ራሱን ሊያጠፋ ወሰነ። ራሱን ለማጥፋት ከሞከረ በኋላ አባቱ የማይዘነጋ ምክር ለገሰው። "ህይወት መፅሐፍ ናት፥ እያንዳንዱ ቀን የመፅሐፉ አንድ ገፅ ነው። መፅሐፉ ተነቦ ሳያልቅ አትዝጋው" አለው። ከዚህ በኋላ ቆም ብሎ አሰበ። "በገዛ ፈቃዴ ራሴን በመግደል የህይወቴ ገፅ እንዳይነበብ አላደርግም" አለ። ከዚህ በኋላ በመላው አለም ስሙ የናኘ ደራሲ ሆነ። በእርግጥ ህይወታችን መፅሐፍ ብትሆን እያንዳንዱ ቀናት የመፅሐፉ ገፅ ናቸው። በመከራ መካከል ብንሆንም መፅሐፉ ተነቦ ሳያልቅ አንዘጋውም። ነገ ሌላ ቀን ነው፥ በድንግዝግዝ መሐልም ብንሆን እንኳ ሽራፊ ተስፋ አለ። እውነት መስሎ ባይታይም ጨለማው ይገፈፋል። መልካም ቀን!!! Via Alex Abraham

ሀይማኖት/መንፈሳዊነትና የአእምሮ ጤና በስነ አእምሮ ከዚህ በፊት ችላ የተባለው አሁን ግን ትርጉም እያገኘ ከመጣው ነገር አንዱ የሀይማኖት/መንፈሳዊነት ለአይምሮ ጤና ደህንነት ያለው ጠቀሜታ ነው፡፡ ጥናቶች በአንድ መልኩ ይህንኑ ይደግፋሉ፡፡ በሀገራችን የሀይማኖት/መንፈሳዊነት ያለው እተዋጽኦ ጥልቅ ነው፡፡ የሀይማኖት/መንፈሳዊነት ለአእምሮ ጤና ያላቸው ጥቅም፡-   - ከራስና ከፈጣሪ ጋር ግንኙነት ከመፍጠር ለሕይወት ትርጉምም እንዲኖር ያደርጋሉ   - ተስፋ እና ለልሾ ከብር መስጠትን ያዳብሉ (ሀይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ ፊል 4፡13)   - ሰዎች በጸሎት የሚያስጨንቀንቃቸውን ሁሉን ለሚችል አካል አሳልፈው ይሰጣሉ   - ቅዱስ ቁርዓን ወይም መጽሐፍ ቅዱስ በማንበብ ሰዎችን ያረጋጋሉ፤ ተሰፋ ተስፋ ያሲዛሉ   - ቤተሰባዊና ማህበረሰባዊ ፍቅርን በማጎልበት (በተለይ በበዓላት ይህ የጎላ ነው) ብቸኝነትን ይቀንሳሉ    -  ራስን ከሰው ከመነጠል ይጠብቃሉ፤ የቤተሰብነት፤ የእኛነት፤ የእኔነት ስሜት ይፈጥራሉ   - ጭንቀትን ማካፈል፤ ማዋያት እና ምክርን የሚቻልበት ስርዓት አላቸው - ቤተሰባዊነት፤ ፍቅርን፤ መደጋገፍን… በመስበክ ሰዎች እርዳታ እንዲያገኙ ያደርጋሉ   - መቆጣጠር የማንችላቸው ችግሮች በሚገጥሙን እርሱን የሚያተካክል ነገሮች ሁሉ ለበጎ ለሚያደርግ አምላካዊ ሀይል በመስጠት ጭንቀት፤ ድብርትና ውጥረትን ማለፍ ያስችላል (በእርግጥም ከችግር በኋላ ምቾት አለ፤ ሱራህ አሽ-ሻርህ 94፡6)   - ሹሾ በአአመሮ ጤና ላይ ከፍተኛ ተጽኖ አለው፡፡ ሀይማኖቶች ሱስን አይደግፉም   - አስከፊ የህይወት አጋጣሚዎችን በሚሰጣቸው ትርጉም አወንታዊ አስተሳሰብ እንድናዳብር ይጠቅሙናል፡፡ ለምሳሌ የምንወደውን ሰው በሞት ማጣት ከባድ ነው፡፡ የሀይማኖት አማኝ ለሆነ ሰው ሞት ከዚህኛው ዓለም ወደዛናው ዓለም መሻገሪያ ድልድይ ነው፡፡   - በእነዚህ ጊዜያት የሚደረገው መተጋገዝ እና ማጽናናት አጋጣሚውን ማለፍ እንድንችል ያደርገናል፡፡   - በአስጨናቂ የሕውት ዉጣ ውረዶች ውስጥ በምናልፍበት ጊዜ፤ አስተሳሰባችንን በመቀየር፤ ውጥረት ከታች የሆነውን ከባቢ በአወንታዊ መልኩ እንድንቀይራቸው ይረዳናል፡፡          @gashaw_aweke

የተወሳሰበ ሀዘን (complicated grief) ~ በዓለም ላይ አንድ ሰው ብቻ ተወዶ ያም አንድ ሰው ሲሞት ምን ይደረጋል… [ያ ሐመልማል (አለንጋና ምስር፡ አዳም ረታ)] በሕይወትሽ ውስጥ “የህይወቴ ትርጉም” የምትይው… “የምኖርለትም፤ የምሞትለትም” የምትይው… “ያለ እርሱ ራሴን ማሰብ አልችልም” የምትይለት…  ያ የአንቺ ትንፋሽ የሚመስል ነገር.. ድንገት ከጎንሽ  ተኖ ሲጠፋ የሚሰማሸ “የተዘበራረቁ ስሜቶች ፓኬጅ” ሀዘን ይባላል፡፡ ቴሌ ፓኬጅ መግዛት ስትፈልጊ ገንዘብ ትከፊ የለ? እዚህኛው ላይም የምትሳሽለትን ነገር ትከፍያለሽ… ልዩነቱ ገንዘቡን የምተከፍይው በፍላጎት ሲሆን የምትወጅውን ግን የምትከፍይው ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ሀይል ነው፡፡ ምንም ማድረግ የማትችው ሀይል፡፡ ቴሌ ካለሽ ገንዘብ ቀንሰሽ ነው የምትከፍይው፤ እዚህኛው ላይ ግን “ሁሉ ነገርሽን” ነው የምትከፍይው፡፡ ፓኬጅሽ እነዚህን ይይዛል፡- ባዶነት… ንዴት… ጸጸት… ናፍቆት…ግራ መጋባት… መሰበር… ድብርት… እና የፍርሀት የፓኬጁ ርዝመት እንደየሰው ሊለያይ ይችላል፡፡ የሁለት ሳምንት ሊሆን ይችላል… የወር… የዓመት… ወይ የ2ዓመት…፡፡ ረዘም ያለ ፓኬጅ ለመግዛት ከፍ ያለ ገንዘብ ያስፈልግሽ የለ? ከፍ ያለ ትርጉም የምትሰጪውን ነገርም ስታጪም የሀዘንሽ ጥልቀትና ርዝመት ይተልቃል፡፡ የቴሌን ጥቅል አንዴ ተጠቅመሽ ትጨርሽዋለሽ አይደል? ይህኛው ግን ይለያል፡፡ ወይ ያልቃል ወይም የጠፋ እየመሰለ የሚፈነዳ የተዳፈነ እሳት ይሆናል፡፡ የተቀበረ ቦምብ፡፡ ነገርዬው ደረጃዎች አሉት:- ክህደት -->ንዴት --> ድርድር --> ድብርት --> መቀበል፡፡ ለቅሶ የምንዳረሰው እነዚህ ደረጃዎች አልፈን ሕይወት እንድትቀጥል ነው፡፡ ያዘነን ሰው እንዴት እንርዳው? 💡አጠገቡ መሆን፡- አጠገቡ ሰው ሲኖር ቶሎ የመጽናናት እድሉ ይጨምራል 💡በስሜት ማገዝ     ▫️ ስሜቱን እንዲገልጥ መርዳት     ▫️ የየሰው የሀዘን አገላለጽ የተለያየ ነው፡፡ ሀዘኑን በፈለገው መንግድ እንዲወጣ እንርዳው እንጅ “እንደዚህ ሊሰማህ አይገባም… እንዲህ ሊሰማህ ይገባል…” እያልን ማዋከብ የለብንም፡፡    ▫️ ሀዘንተኛው ለልሹ ደግ እንዲሆን መርዳት    ▫️ ፈገግ ሊያደርጉት የሚችሉ ነገሮች ውስጥ መክተት    ▫️ እንዲታገሱ ያበርቱት-- ነገ ደህና ይሆናልና፡፡    ▫️ የማጣቱን መጥፎ ጎን እና ከማጣቱ በኋላ እንዴት መቀጠል እንዳለበት እንዲለይ ይርዱት 💡አካላዊ እርዳታ እንዲያገኝ ማገዝ    ▫️ በቂ እንቅልፍ እንዲያገኝ    ▫️ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲያደርግ    ▫️ ራሱን ወደሚጎዱ ነገሮች ውስጥ እንዳይገባ (ለምሳሌ ሹሾ አምጪ ነገሮች)    ▫️ አመጋገብ፤ እንቅልፍ፣ ስሜት እና ሀይል ላይ ቋሚ ለውጦች ካሉ ቶሎ በመለየት 💡 ስነ ልቦናዊ እርዳታ እንዲያገኝ ማገዝ    ▫️ ስሜቱን እንዲጽፈው (ሲጻፍ ሊቀል ይችላል)    ▫️ ቢያንስ በሳምንት አንዴ ሀዘንተኛው ሀዘኑን የሚያስረሳ ነገሮች ውስጥ እንዲገቡ መርዳት      ▫️ ሀዘን ሊያነሳሱ የሚችሉ ነገሮችን መለየትና እቅድ ማውጣት የሚከተሉትን አያድርጉ      ▫️ “እንዴት እንደተሰማህ አውቀዋለሁ” ከማለት ስሜታቸውን ጠይቀው ለመረዳትም ስሜታቸውንም ማውጣት ይረደል        ▫️ እንደዚህ ማድረግ ነበረብህ… እዚህኛው ሀኪም ቤት መውሰድ ነበርብ… እንዲህ ማድግ አለብህ 🎯 ሀዘን ተወሳስቦ ወደ ህመምነት ደረጃ ሊያድግ ይችላል የተራዘመ ሀዘን ህመም (Prolonged Grief Disorder) ` 💡 ወዳጅ ካረፈ ቢያንስ ከ1 ዓመት በኋላ የሚከተሉት ምልክቶች ሲከሰቱ         ▫️ ያረፈውን ሰው በጽኑ መናፈቅ         ▫️ ባረፈው ሰው ትዝታዎች ወይም ሀሰቦች መወሰድ         ▫️ ያረፈውን ሰው አሁንም በሕይወት እንዳለ ማመን         ▫️ ያረፈውን ሰው ከሚያስታውሱ ነገሮች መሸሽ         ▫️  የባዶነት ስሜት ወይም ሕይወት ትርጉም የማጣት ስሜት         ▫️  ጽኑ የመንፈስ ህመም (ንዴት፣ ምሬት፣ ሀዘን)         ▫️  ስሜት አልባ መሆን         ▫️  በሀዘኑ ምክንያት የሚሰማ ጽኑ የብቸኝነት መንፈስ 💡እነዚህ ምልክቶች በህይትና በስራ ላይ ጣልቃ ሲገቡ እና ከማህበረሰቡ ባህል እና ከሁኔታው አንጻር የተጋነነ ሲሆን ህመም ይሆናል ስለዚህም የህክምና እርዳታ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ጋሻው አወቀ (የስነ አእምሮ ባለሙያ) @Gashaw_aweke

የመድሀኒት ሰው መባል አልፈልግም! ~~~~~ ስር ለሰደደ (chronic) ሕመም እየታከምክ ወይም ህክምናውን ልትጀምር ነው? “እስከመቼ እንዲህ ይኖራል ያን ሁላ ዓመት ክኒን ልውጥ ነው?” ብለህ ይሆን? 🎯 ሁሉም የመድሀኒት ሰው ነው! ሰውነታችን የተገነባው ከኬሚካሎች ነው፡፡ ስራውንም የሚሰራው በኬሚካልና በኤልክትሪክ ንዝረት አመካኝነት ነው፡፡ ሰውነት የሚፈልገውን ኬሚካል ለማግኘት በየቀኑ ለሰውነታችን ማቅረብ ይኖርብናል፡፡ ቀላል ምሳሌ፡ ምግብና ውሀ ሳትወስድ ከሁለት ቀን በላይ የቆየህበት ቀን የለም አይደል? በየቀኑ ቢያንስ ለሶስት ጊዜ በመደበኛ ሰዓት ትመገባለህ? ማብላያ ወይ ማነቃቂ ትልና ሌላም ትጨምርበት ይሆናል፡፡ ወሀ ይጠማህና ትጠጣለህ፤ ባይጠማህም ትጠጣለህ፡፡ ምን እያደረክ መሰለህ… ሰውነትህ የሚፈልጋቸውን ኬሚካሎች በጥቅል እያቀረብክለት ነው፡፡ እንዴት አልከኝ… የምትመገበው ምግብ ይፈጭና ሀይል ይሆንሀል ወይ ሰውነትህ ያረጁ ህዋሶቹን ይተካበታል ወይ ለስራው የሚፈልገውን ኬሚካል ይወስዳል፡፡ ስለዚህ ምግብ ማለት ሰውነትህ ውስጥ ያሉ ኬሚካሎች ሲያልቁ እነርሱን ለመተካት የምትወስደው መድሀኒት ነው ማለት ነው። ወደ ሰውነትህ የትኛው ይግባ ትኛው ይቅር የሚለውን የሚቆጣጠሩት ኬሚካሎች ሳይቀር ከምትበላው ምግብ የተወሰዱ አልያም ከዛ ወስዶ ሰውነትህ ራሱ ያመረታቸው ናቸው፡፡ ዛሬ ስራ የሄድከው፥ ስራህን ሰርተህ የዋልከው፣ ስትተነፍስ የዋልከው፣ ማታ እንቅልፈህ መጥቶ የተኛኸው፣ አሁን ይህንን ጽሑፍ የምታነበው… ከምግብ ተወስደው በተሰሩ ንጥረ ነገሮች አማካኝነት ነው፡፡ መድሀኒት ማለት እነዚህ ንጥረ ነገሮች መጠናቸው ሲዛባ የሚያስተካከል ወይም ሰውነታችንን በሚጎዱ ነግሮች ሲጠቃ የሚዋጋቸው ነገር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ “ምግብ ማለት በየቀኑ የሚወሰድ የመድሀኒቶች ጥቅል ነው” የሚለው አያስማማንም? በዚህ ከተስማማን ሁሉም ሰው በየቀኑ መድሀኒት ሳይወስድ መኖር አይችልም በሚለው እንስማማለን፡፡ ምግብና ውሀ በየቀኑ መውሰድህ ነጻነትህን ወሰደው? መድሀኒት በቀን ወይም በሳምንት ወይም በወር መውሰድህስ ነጻነትህን ወሰደው? 🎯 ወተት ለዶሮ ምኗ ነው? ጥሬ ለድመት ምኗ ነው? እኔ መስሪያ ቤት ለመድረስ የሚፈጅብኝ 40 ደቂቃ አከባቢ ነው፡፡ 5 ደቂቃ ብቻ የሚፈጅበትም አለ፡፡ ወደ 2 ሰዓት የሚፈጅበትም አለ፡፡ ነገር ግን ሁላችንም ሰርተን እንገባለን፡፡ ጧት መነሳት ያለብን ሰዓት እና መሔድ የሚጠበቅብን መንገድ ርዝመት ግን የተለያየ ነው፡፡ ስለዚህ 5 ደቂቃ የሚፈጅበት ሰው 2 ሰዓት የሚፈጅበት ሰው በሚነሳበት ሰዓት መነሳት ላያስፈልገው ይችላል፡፡ ዶሮም ድመትም ለመኖር መመገብ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ግን ወተት ለዶሮ ምኗ ነው? ጥሬስ ለድመት ምኗ ነው? አየህ! አንዳችን ከሌላች ልዩዎች ነን፡፡ አንተም ከሌላው የምትለየው ከምግብህ ከያዘው በተጨማሪ ሚጥጥዬ ቅመም [መድሀኒት] ጣል ማድረግ ይጠበቅብሀል! ይኸው ነው። ይመስለኛል፤ ያን ያህል ልዩ አለመሆንህን ተቀበልህ፥ መድሀኒትህን በአግባቡ መውሰድ እንዳለብህ የመቀበያው ጊዜ አሁን ነው፡፡ 🎯 ከሰይጣን እና ከውሻህ ማንን ትመርጣለህ? የውሻህን ጥቅም አልነግርህም። ካናደድከው ግን ሊነክስህም ይችላል። ውሻህ ጸባይ ከሌለው ሌላ ጸባየኛ ውሻ ታሳድጋለህ። ያለ ሀኪም ትዕዛዝ ከምትገዛው የራስ ምታት ወይም የጉዞ መደሀኒት ጀምሮ ማንኛውም መድሀኒት የራሱ የጎንዮሽ ጉዳት አለው፡፡ እንደየሰው ይለያያል። በትክክል ካልተጠቀምከው ሊጎደህም ይችላል። መድሀኒቱ ካልተስማማህ ከሀኪምህ ጋር ተነጋግረህ ታስቀይረዋለህ። ሰይጣን ያው ሰይጣን ነው። ህመም ያው ህመም ነው። ባንድም በሌላ መልኩ ይገልሀል ወይም አካል ጉዳተኛ ያደርገሀል፡፡ ስር የሰደዱ ህመሞች (ስር የሰደዱ የአእምሮ ህመሞችን ጨምሮ) ለአጭር ወይም ለረጅም ጊዜ በመድሀኒቶች ሊታከሙ ይችላሉ። ያ ማለትን ግን ዱብዳ ነው ማለትም አይደለም። t.me/gashaw_aweke

Repost from WeMind Ethiopia
The_self_love_workbook_a_life_changing_guide_to_boost_self_esteem.pdf3.00 MB

Repost from WeMind Ethiopia
👉 ለራስ ስለመራራት (Self compassion) የተሳሳቱ ግንዛቤዎች ⏺ ራስን መውደድ ለሰው አለማሰብ ሊሆን ይችላል፤ ወደ Selfishness ያመራል፡፡ ➡️ “Being selfish ማለት only me ማለት ነው፡፡ ራስን መውደድ (self love) ግን for me too፤ ለኔም ጭምር፤ ለኔም ይገባኛል ማለት ነው…[#ሜሪ_ፈለቀ] ሜሪ ፈለቀ ራስን መውደድን ውብኛ አብራርታዋለች t.me/Gashaw_Aweke/209 ⏺ ሀለፊነት ላለመውሰድ፣ የግዴለሽነት፤ ለስህተትህ ይቅርታ መፈለጊያ በር ነው፡፡ ➡️ ራስን መውደድ ማለት የት ነህ ብትባል የምታፍርበትን ቦታ ለእኔ አይገባኝም ብለህ ዘወር ማለት ነው፡፡ መርዛማ የፍቅር ዝምድና ለእኔ አይገባኝም! ጥቃት ለእኔ አይገባኝም! ስንፍና ለእኔ አይገባኝም! ብለህ መቁረጥ ነው፡፡ ⏺ ከማህበራዊ ዕሴት ሊያስወጣ ይችላል ➡️ ራስን መውደድ ከሞራልና ከመርህ ውጭ መሆን ማለት አይደለም፡፡ ለሰው የምትሰጠውን ደግነት ለራስም መስጠት ማለት እንጅ፡፡ ይልቁንም እሴትና መርሆችን ለመከተል ፍላጎህን፤ ደካማ ጎንህን፣ አቅምህን፣ ዋጋህን፣ ዉጫዊና ውስጣዊ ድንበርህን መለየት ነው እንጅ፡፡ የምታልመው አንተነትህን ለመሆን ስትጥር ብትሰበር፤ ራስህ ከምትቆጣው አበርታው ማለት ነው እንጅ፡፡ ➡️ ራስን መውደድ ተፈሯዊ ነው፡፡ በምናደርገው ማንኛውም የመልካምነት ስራ ውስጥ ራስን መውደድ አለበት፡፡ ድሆችን ስትዘክር ‹‹ስጡ ይሰጣችል›› የሚል ዜማ በውስጥህ አልተንቆረቆረም? ያም ቢቀር ውጣዊ ሰላምና እርካታ አልፈለክም? ሰደቃ ስታደርግ ጀነት ውስጥ ቦታ እንዲኖህ በመመኘት ጭምርም አይደል? እናትህን አንዱ ቢሰድብብህ ውስጥህ ያለው ነብር ተወርዉሮ የልጁን ጉሮሮ ያንቀው የለ? - የተሰደበችው እናት-ህ ናታ፡፡ ራስን መውደድ መለማመድ እንችላለን፡፡ ግን በአንድ ውሎና አዳር አይመጣም፡፡ በሂደት እንጅ፡፡ [ራስን መውደድ መለማመጃ መጽሀፍ ከዚህ ያውርዱ t.me/Gashaw_Aweke/216 ] የሚከተሉት ሊጠቀምዎት ይችላሉ፡፡ ✔️ ራሰዎን እና ስለራስዎ የሚናገሩትን ያስተውሉ 🗒ለራስዎ የሚነግሩት ምንድነው፣ እንዴት አድርገው? 🗒 ይህንን ለሌላ ሰው ይናገሩታል? 🗒 ውጥረትን መቋቋም ይልመዱ… ይህም ያልፋልና 🗒 ራስዎን ይቀበሉ (መቀየር ስለማይቻለዎት ነገሮችን መቀበል ይልመዱ… ለምሳሌ የሚወዱትን ሰው ቢያርፍ ሊመልሱት አይችሉም) ✔️ ሚዛናዊ የሆኑ አመክንዮዎች 🗒 ሌሎችም ይህ ስሜት ይሰማቸዋል 🗒 ለራሴ የምሰጠው መመዘኛ (standard) ለሌሎችም የምመዝንበት ነው ✔️ ሌሎችን እና ራስዎን በማይጎዳ መልኩ ስሜትዎት እንዲወጣ ይፍቀዱለት፡፡ ለምሳሌ ማልቀስ ካለበዎት ያልቅሱ… crying does not indicate that you are weak. Since birth, it has always been a sign that you are alive. [Charlotte Bronte] ✔️ ሌላ ወዳጅዎ እንደሚጽፍልወት አድርገው ለራስዎ ደብዳቤ ይጻፉ…ለሜሳሌ የምትወድሽ እናትሽ እዚህ ስብራት ውስጥ ሆነሽ ብታይሽ አጽናኝ ደብዳቤ እንደምትጽፍልሽ አይነት፡፡ ✔️ የሚያነሳሱ ነገሮችን [triggers] ይለዩ፡፡ ለራስዎ ደግ እንዳይሆኑ ከሚያደረጉዎት አነሳሽችዎች ይራቁ፡፡ ለራስዎ ብርታት የሚሆኑበትን አነሳሽዎች ያብዙ፡፡ ስለ ስነ-አእምሮ ያንበቡ t.me/Gashaw_Aweke ጋሻው አወቀ (የስነ አእምሮ ባለሙያ) #ጤናማ_አእምሮ፤ ረፍት_የሞላው_ሕይወት☺️

Repost from WeMind Ethiopia
🗒 ራሴን በላሁት 🗒 💡በቀን 80,000 ሀሳቦችን አእመሯችን ያስተናግዳል፡፡ ከነዚህ ውስጥ 80% አሉታዊ (negative) ናቸው (ጥናቶች እንደሚያሳዩት) ገብቼ ሱባኤ፤ ከብቻ ጉባኤ፤ ለአያሌ ዓመታት፤ በ‹እኔ›ነት ማሳ ተመላልሼበት፤ ወጥቼ ወርጄበት፤ አዝመራ ባጣበት፤ ራሴን በላሁት … [ደበበ ሰይፉ 1965] {የግጥም መጽሐፉን ያግኙ t.me/Gashaw_Aweke/215 } ፍጥረት ሁሉ ፍጹም አይደለም፤ ስለዚህ በውድቀቱና በዝቅታው ጊዜ ፍቅር እና እርዳታ ያስፈልገዋል ብሎ ማመን compassion ይባላል፡፡ compassion ግለሰቡን ከባህሪው መለየት ማለት ነው፡፡ መጠጥ ለማቆም ሞክሮ ያልተሳካለት ልጅ አለሽ እንበል፡፡ ስካሩን አትወጅለትም፡፡ እንዲህ ሆኖ መቅረቱ ያሳስብሻል፤ ለልጅሽ ያለሽ መውደድ ግን ቅንጣት አልቀነሰም፡፡ ያን መውደደ ለራስሽም ጭምር ትሰጭዋለሽ? የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለበት ልጅህን ታዝንበታለህ ወይስ ታዝንለታለህ? የ2 ዓመት ልጅህ ድክ ድክ ሲል ቢወድቅ ሮጠህ አንስተህ፤ ‹እኔን› ብለህ አቅፈህ ታባብለዋለህ ወይስ ‹እንዴት ትወድቃለህ!› ብለህ ትጮህበታለህ? በህይወት ድክ ድክ ስትል አንተ ስትወድቅስ? ስሜትህ ተሰብሮ ጎብጠሀል፤ ያለምከው እና የሆነው አውራምባና እና ቆቦ ሁኖብሀል… ያኔ ለራስህ የምትነግረው ቃለ ምን አይነት ነው-የሚያረጋጋ ወይስ የሚዋጋ? የሚጠግን ወይስ የሚሰብር? ራስህ ላይ ወረድክበት ወይስ ለራስሽ ደግ ሆንክለት? እያንዳንዱ ሰው “ነኝ” ብሎ ራሱን የሳለበት የራሱ ስዕል (Self image) አለው፡፡ ከራሱና ከሰዎች ጋር በሚኖረው ዝምድና መሰረት ለራሱ የሚሰጠው ግምት (self esteem) ያዳብራል፡፡ ይህንን ለራሱ የሰጠውን ግምት ሲመነዝረው ደግነት ወይ ክፋት፤ ራስ ወዳድነት ወይ ርህራሄ፤ ተንኮል ወይ የዋህነት፤ የበታችነት ስሜት ወይ ሚዛናዊ ስሜት፣ ትዕቢት ወይት ትህትና… ይሆናሉ፡፡ ክፋቱ፤ ብዙዉን ጊዜ ስለራሳችን የምናስበው ክፉ (negative) ሀሳቦች ናቸው፡፡ ስለዚህ ለራሳችን የምንሰጠው መውደድና ግምት በትክክል የተመዘነ አይሆንም-- የተዛባ ነው:: ትክክለኛውን ‹እኛነት› አይወክልም፡፡አውቀነውም ይሁን ሳናውቀው፤ ብዙዎቻችን ለራሳችን ክፉዎች ነን፡፡ ልክ ወሃና አየር ለመኖር አስፈላጊ እንደሆኑ መወደድ እና መውደድም እንደዛው ናቸው፡፡ “How you love yourself is how you teach others to love you.” [#Rupi_Kaur]፡፡ እሱም ብቻ አይደለም፡፡ ራስህን መውደድ ካልቻልክ በትክክል ሌላውንም መውደድ አትችልም፡፡ እያንዳንዱ ስሜታችን የሚመነዘረው ለራሳችን ከሰጠነው ግምት ነው ብለን የለ? ራስህ ልክ እንደ ብርጭቆ ሳለው፡፡ ወተት ብትጨምር ነጭ ትሆናህ፤ ቡና ብታደርገው ጥቁር፣ ወሀ ከሆነ ቀለም አልባ፡፡ አየኸ! ለራስህ ከሌለህ ለሌላው የምትሰጠው ብርሀን የለህም፡፡ የለለህን ፍቅር ለሌላው ለመስጠት ከወደየት ታመጣዋለህ? ራስህን ምን ያህል ትወደዋለህ? ከምትወዳቸው ሰዎች ውስጥ ዘርዝር ብትባል የአንተ ስምን ስንተኛውን መስመር ላይ ይሰፍራል? ማንዴላ ፕሬዝደንት ሆነው የእግር ኳስ ጨዋታ ይከፍቱ ነበር፡፡ ተጨዋቾችን ከጨበጡ በኋላ ኳሷን ሲመቱ ጫማቸው ወለቀ፡፡ ጋዜጠኞች አንድ ነገር አዩ፤ የእግር ሹራባቸው ቀዳዳ ኑሯል… በካልሲው ቀዳዳ የወጣውን ጣታቸውን ጋዜጠኞች እያነሱ የጋዜጣቸው የመጀመሪያ ገጽ ሽፋን አደጓቸው፡፡ በአያሌ ተሳቀ፡፡ ማንዴላ ለምን ሳቃችሁብኝ ብለው የሚቆጡ መሪ አይደሉም፡፡ ሁሉንም በደግ ስሜትና በመልካም አይን ማየት ይወዳሉ፡፡ እናም፤ አብረው ሳይስቁ አይቀሩም… [Sheger FM] ራህን ስትወደው በጥቃቅን ይሁኑ በግዙፍ ውደቀት መስለው በታዩህ ነገሮች ሁሉ ራስህን አታሸማቅቅም፡፡ ራስህን ከወደድክ መውደቅን አትፈራም፡፡ እመኒ ወደቁ እትነሳእ.. (ብወድቅ እነሳለሁ…በጨለማ ብሄድ ያበራልኛል.. [ሰዓታት]) እኒሁ ፕሬዝደንት በእስር ቤት ሳሉ ብርታት ይሰጣቸው የነበረውን ግጥም መጥቀስ ተገቢ ይሆናል፡፡ It matters not how strait the gate How charged with punishment the scroll I am the master of my fate I am the captain of my soul. [William Ernest Henley] ለራሰህ ስትራራ ከራስህ ጋር በሰላም ትኖራለህ፡፡ ያ ደግሞ ምን ያተርፍልሀል መሰለህ? - ️ በሰላም ትተኛለህ - ️በሽታ የመቋቋም አቅምህን ትጨምራለህ (boost your immunity) - የህመም ስሜትህን ትቀንሳለህ ((reduce pain threshold) - ️ የስኳር መጠንህ አያሻቅብም (blood sugar control) - ከዝለት (Burnout) ይከላከልልሀል ️- ለራስህ ህብር ይኖርሀል (Self esteem) ️ - መልካም ተግባቦት ይኖርሀል (Interpersonal relationships) 👉 ራስህን ላለመውደድ መሰናክሎች 1. “ራስን መውደድ ወደ ስግብግብነት፣ ሀለፊነትን አለመውሰድ፣ ዝርክርክነት፤ ስግብግብነት… ያመራል” የሚል እምነት 2. “የእኔ ፍቅርና እንክብካቤ ለ‹ታጥቦ ጭቃዎች› አይገባቸውም” ▫️ ደህና፤ ሰውን እና ባህሪን ነጥለን ማየት የምንችልበት ሁኔታ መፍጠር አንችልም?

Repost from WeMind Ethiopia
ሜሪ ፈለቀ ራስን ስለመውደድ Part 2 ይህ የተወዳጇ ደራሲ ሜሪ ፈለቀ የሰጠቸው ማብራሪያ ነው የእኔን ቀጥዬ አቀርባለሁ

Repost from WeMind Ethiopia
ሜሪ ፈለቀ ራስን ስለመውደድ Part 1

https://youtu.be/LylmMVCFko8 በእዚህ የምክክር መድረክ ላይ አራት ታሪኮች ቀርበው ተሳታፊዎቹ የየራሳቸውን እይታ አቅርውበታል፡፡ ከአራቱ ታሪኮች የመጀመሪያውን እነሆ! ከከባድ የአእምሮ ህመሞች አንዱ የሆነው ስኪዞፍሬኒያ የተለያዩ ምልክቶችን የሚያሳይ ህመም ነው፡፡ የህመሙ ምልክቶች የሀይማኖት ይዘት ሊይዙ የሚችሉ ቢሆንም ከሀይማኖቱ አስትምህሮ ጋር አብሮ የማይሄዱ ናቸው፡፡ ይህ የምክክር መድረክ ከሙስሊም የሀይማኖት አባቶች እና መድሀኒት አዋቂዎች ጋር የተደረገ ሁለተኛው የምክክር መድረክ ነው፡፡ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሀይማኖት አባቶች እና የጥምቀት አገልግሎት ሰጪዎች ጋር የተደረገውን የምክክር መድረክ ለማግኘት በእዚህ ይከተሉን https://www.youtube.com/@sitotapsy FOLLOW US ON: https://www.facebook.com/sitotapsy

ከሙስሊም መንፈሳዊ እና የባህል ህክምና አዋቂዎች ጋር የተደረገ የምክክር መድረክ: Part 01 https://youtu.be/tPoQ0gdZcaw
ከሙስሊም መንፈሳዊ እና የባህል ህክምና አዋቂዎች ጋር የተደረገ የምክክር መድረክ: Part 01 https://youtu.be/tPoQ0gdZcaw

ከሙስሊም መንፈሳዊ እና የባህል ህክምና አዋቂዎች ጋር የተደረገ የምክክር መድረክ: Part 01 https://youtu.be/tPoQ0gdZcaw