ኢትዮ አውቶሞቲቭ - Ethio Automotive
Open in Telegram
1 383
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ስለ አዳዲስ መኪኖች እና አንዳንድ ችግሮች
አዲስ መኪና አለኝ ምን ምን ላድርግ?
አዲስ መኪና ካለዎት በትንሹ እስከ አምስት አመት ምንም አይነት ብልሽት ሊያጋጥመዎ የማይችል መሆን አለበት፡፡ በየጊዜው የሞተር ዘይት ከቀየሩ እንዲሁም የትራንስሚሽን ፍሉድ ከቀየሩ ምንም አይነት ከባድ ችግር አያግጥመዎትም፡፡ በየቀኑ ጠዋት ጠዋት በኩላንት ምትክ ሁ ሚጨምሩ ከሆነ ሞተሩ በቅርቡ ይዝጋል!
አዲስ ሱዙኪ አለኝ የኋላ ማርሽ ሳስገባ ገጭ ሚል ድምጽ እሰማለሁ መካኒክ ሳሳየው ካምቢዎ ይውረድ አለኝ ምን ላድርግ?
ትንሽ ኮሽታ ሲሰሙ ወይም minor noise ሲያጋጥመዎ ሞተር ይውረድ ወይም ካምቢዎ ይወረድ ከሚል መካኒክ ራስዎን ይጠብቁ፡፡ እውነት እውነት እንለዎታለን አንዴ ከተፈታ ሌላ ችግር ውስጥ ነው ሚገቡት፡፡ ማንኛውም ድምጽ ሆነ ችግር ሳይፈታ መለየት አለበት፣ አሁን ባሉት ቴክኖሎጅ በመጠቀም ብዙ ችግሮች መለየት አለባቸው ምክንያቱም የተሽከርካሪውን የመካኒካል ፓርት በኤሌክትሮኒክስ ቁጥጥር ስለሚደረግበት እንደድሮ መኪኖች ለጥቃቅን ችግሮች ሞተር ወይም ካምቢዮ ማውረድ አያስፈልግም፡፡
በተመሳሳይ ቁልፍ ከፍተው እንዳይሰርቁኝ እፈራለሁ፡፡
መጠንቀቅ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን ማወቅ ያለብዎት አንድ ነግር ቢኖር መኪናውን የሸጠለዎ ሰው፣ ከዚህ በፊት የነሩት ባለቤቶች እንድሁም መኪናውን ወደ ሀገር ያስገቡት ሰዎች በርግጠኝነት ቁልፉ ሊኖራቸው እንደሚችል ነው፡፡
መኪና ልገዛ ብዬ ተወደደብኝ
መኪና በውድ ዋጋ መግዛት ያቁሙ፡፡ ከመግዛትዎ በፊት ባለሙያ ያማክሩ፡፡ በተለምዶ በሚዎሩ ወሬዋች መታለል የለብዎትም፡፡
በቀደም ሱዚኪ ዲዛየር ሲንሳፈፍ አይተው ሊሆን ይችላል፡፡ አዳዲስ መኪኖች እጅግ በጣም ቀላል ክብደት እንዲኖራቸው ሁነው ነው የተሰሩት፡፡ አዲስ ከመሆኑ የተንሳም ጎርፍ ላያስገባ ይችላል፡፡
ለምሳሌ ዲዛየር ጠቅላላ ክብደቱ ወደ 1300 ኪግ ሲጠጋ አንድ ቶዮታ ያሪስ ሲዳን ወደ 1600 ኪግ ይጠጋል፡፡
ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የተላለፈ ጥሪ ለሁሉም አመልካቾች
በተለይ ምንም ኢንቪቴሽን አልደረስኝም ላላችሁ አመልካቾች፡፡
ኢሜልዎች ቼክ ያርጉ ከዛም Course Invitation የሚል ርዕስ ያለው search ካደረጉ ከ
Canvas Free for Teachers የተላከ ኢሜል ያገኛሉ እሱን ከፍተው course accept ያድርጉ በቶሎ ይጀምሩ፡፡
ኤሌክትሪክ / ኤሌክትሮኒክስ ለተመዘገባቹ ከታች ባለው ሊንክ ቴሌግራም ይቀላቀሉ::
ማሳሰቢያ የተመዘገባቹ ብቻ ተቀላቀሉ::
If you register for Auto Electric/ Electronics Join the telegram group
https://t.me/autoelectricelectronics
የዚህ ግሩፕ ተከታታዮች ለስልጠና ፍላጎት ያላቹ ባስቀመጥንላቹ መስፈርት እና ዝርዝር መሰረት መርጣቹ ላኩልን ከዚህ በፊትም ያስቀመጥነው ኣድራሻ ከላይ ይፈልጉ:: እናመሰግናለን::
ኢሜል ልካቹ ጥያቄ ያላቹ በላካቹት ኢሜል ጥያቄያችሁንም በኢሜል እንድታቀርቡ እንጥይቃለን፡፡ ኢሜል ተልኮላቹ ያልጀመራቹ በቶሎ እንድትጀምሩ፣ የሎሎች ሰልጣኞች ጊዜ መጉዋተት ስለሌለበት፡፡ ሌሎቻችሁ የምትፈልጉትን ጥያቄ ብቻ ይጠይቁ፣ ሀይ እያላችሁ አትላኩ፣ ይህ የመማሪያ ፔጅ ነው እናመሰግናለን፡፡ ስለስልጠናው እንዳንድ ነገሮች በጥቂቱ
1 ስልጠናው ዘመናዊ ዘዴ የተከተለ ነው፡፡
2 ስልጠናው ክፍያ አለው፡፡ አስተማሪ ቀጥረን ጭምር ነው የምናስተምርዎት፡፡
3 እርስዎ ከ ኮሌጅ ወይም ከዩንቨርሲቲ የተመረቁ እንደመሆነዎ መጠን የንድፍ ሀሳቡን በደንብ ያቁታል ብለን ስለምናስብ ስልጠናው Task ላይ ያተኩራል፡፡
4 ለያንዳዱ ሞጁል አሳይመንት፣ discussion እና quiz እንዲሁም final exam ይኖረዋል፡፡
5 ዝቅተኛውን መስፈርት ካላሟሉ ስልጠናውን ይደግማሉ:: ስለከፈሉ ብቻ ሰርቲፊኬት አይወስዱም፡፡ እንዲሁም የ አስተማሪዎቻችንን ችሎታ ጥያቄ ውስጥ መግባት ስለማይኖርበት፡፡
6 ስልጠናውን የሚወስዱት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ነው፡፡
ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄ
1 ባለ 3 ጥርስ የሆነ አውቶማቲክ ትራንስሚሽን ( 3 speed AT) 1ኛ ላይ እና 2ኛ ላይ ድምጽ አለው ሶስት ሲደርስ ግን ድምጹ ይጠፋል የምን ችግር ነው? ከታች ምስሉን ይመልከቱ፡፡
A. sun gear
B. planetary gear
C. Ring Gear
D. Clutch
E. Torque Converter
2. ሞተሩ በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኝ ተፈትሾ ምንም ችግር የሌለበት አውቶማቲክ ትራንስሚሺን ቶዮታ ኮሮላ መኪና ሁሌ ከቆመበት እየተነሳ ለመሄድ ሲሞክር ፍጥነት ያንሰዋል 55 ለመድረስ ሲቸገር ከ 55 በሃላ ግን ላጥ ብሎ ይሄዳል፡፡ የዚህ ችግር ምንድን ነው?
A. Torque Converter
B. Low ATF fluid
C. Clutch
D. Bad transmission
ማሳሰቢያ!
መልሱን በ ኢንቦክስ ይላኩልን፡፡
መልሱን ኮመንት ላይ መጻፍ አያስፈልግም ሽልማትም አያስገኝም::
ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ውስጥ በ ኦንላይን ስልጠና የትኛውን መውሰድ ይፈልጋሉ?
በዚ ኢሜል autotvetedu@gmail.com ይፃፉልን ሲፅፉልን በ ጀማሪ, መካከለኛ ወይም ኣድቫንስ ደረጃ እንደሚፈልጉ ያስቅምጡ::
Engine Fundamental
Suspension & Steering
Brakes
Electrical/Electronic Systems
Engine Repair
Engine Performance
Light Vehicle Diesel Engines
Heating & Air Conditioning
Automatic Transmission/Transaxle
Manual Drive Train & Axles
የተሽከርካሪዎችን አመታዊ ምርመራ በሚያደረጉበት ጊዜ ማንኛውንም ፍሳሽ ካለ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ የተሽከርካሪዎች ዘይቶች እና ቅባቶች የተለያዩ ቀለማት አላቸው፡፡
የአውቶማቲክ ትራንስሚሽን በሆነ ተሽከርካሪ በሞተር እና በትራንስሚሽን (ካምቢዮ) መካከል ቀይ መሳይ ዘይት ካፈሰሰ ይህ ዘይት የአውቶማቲክ ትራንስሚሽን ዘይት ነው፡፡
የ አውቶማቲክ ትራንስሚሽን ዘይት ፓምፕ ጎሚኒ (seal) ሲበላ ዘይት በሞተር እና በካምቢዮ መካከል አልፎ ይፈሳል፡፡ የሚያፈሰው ዘይት ቀለም ሊለያይ ስለሚችል ከሞተር ዘይት ጋር ሊመሳሰል የሚችልበት አጋጣሚ ስለሚኖር በጥንቃቄ መመርመር ያስፈልጋል፡፡
ደማቅ ቀይ ቀለም ያለው ዘይት= አዲስ እና በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ ዘይት፡፡
ጠቆር ያለ ቀይ ቀለም ያለው ዘይት= በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ መቀየር ያለበት፡፡
ቡናማ ቀለም= የቆሸሸ በቶሎ መቀየር ያለበት፡፡
የጠቆረ ቀለም ያለው ዘይት= በሙቀት ምክንያት መቃጠል የጀመረ በቶሎ መቀየር ያለበት፡፡
ፒንክ ቀለም ወይም አረፋ ነገር ያለው= የ ኩለር መበላሸት እና ኩላንት ከካምቢዮ ዘይት ጋር መቀላቀል ያስከተለው ቀለም፡፡
በምስሉ ላይ የሚታየው ምንድን ነው?
A. Brake Rotor Lateral Runout
B. Brake Rotor Parallelism
c. Brake Rotor Wear
D. Brake Rotor Speed
E. All
የ ፊውል ፓምፕ ቼክ ቫልቨ ችግር ሞተር ቶሎ እንዳይነሳ ያደርጋል፡፡ ቫልቩ ክፍት ከሆነ ሞተር ሲጠፋ መስመር ላይ ያለው ነዳኝ ወደ ነዳጅ ታንክ ስለሚመለስ እንደገና ሞተር በሚነሳበት ሰአት ነዳጅ ከ ታንኩ እስኪደርስ ጊዜ ስለሚፈጅ ቶሎ ያለመነሳት ችግር ይፈጥራል፡፡
ባለ አራት ሲሊንደር በቢንዚን የሚሰራ ተሽከርካሪ electronic control fuel pump ያለው ሲሆን ለመነሳት ብዙ ጊዜ ተደብድቦ ነው፡፡ ነዳጅ ከበቂ በላይ አለው፣ መኪናው እየሰራ የ ነዳጅ ግፊት ሲለካ (fuel pressure) 3.1 bar ያነባል ይህም ትክክል ነው፡፡ ሞተሩ ሲጥፋ በ 2 ደቂቃ ውስጥ ከ 1 bar በታች በ ወረደ ችግሩ ምንድን ነው?
ቴርሞስታት ለምን ያገለግላል? ቴርሞስታት ማስወጣት አግባብ ነው? እርስዎ ቴርሞስታተዎን አስወጥተዋል?
ቴርሞስታት ማለት በማቀዝቀዣ ክፍል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ሞተር መጠነ ሙቀት እስኪደርስ ድረስ ኩላንት ወደ ራድያተር ውስጥ እንዳይገባ ዘግቶ የሚቆይ ነው፡፡
በምናሽከረክርበት ጊዜ የባትሪ መብራት ቢበራብን ምን ማድረግ ኣለብን?
https://youtu.be/nExwrl-qtfA
የመኪና ስርቆት መበራከት
ሰሞኑን የመኪና ስርቆት ከሁልጊዜውም በላይ ተበራክትዋል፡፡ ባብዛኛው ስርቆት የሚፈጸምባቸው ሴኩሪቲ ሲስተም (alarm) የሌላቸው ሲሆን ቁልፍ ተቀርጾ በቀላሉ የሚነሱ ናቸው፡፡
ቁልፍ በመቅረጽ ማን ሊሰርቀን ይችላል?
1. ከመኪና መሸጫ ቤት ጀምሮ ብልሹ ስነምግባር ባላቸው ሰዎች ከመጀምርያውም ሊቀረጽ ይችላል፡፡
2. መኪና የምናሰራበት ቦታ ብልሹ ስነምግባር ባለቸው መካኒኮች ከሌሎች ሌቦች ጋር በመተባበር ሊያስቀርጹ ይችላሉ፡፡ ሁሉም መካኒክ ሌባ ነው ማለት አይደለም፡፡
3. መኪና ስናሳጥብ ቁልፍ ሰጥተን ከሄድን ሊቀረጽ ይችላል፡፡
4. ሬስቶራንት እና ሆቴሎች ለማቆም ቁልፍ ከሰጠን ሊቀረጽ ይችላል፡፡
5. አልፎ አልፎ በራሳችን የቅርብ ሰው ጓደኛ ወይም ለትንሽ ጊዜ ባበደርነው ሰው ሊቀረጽ ይችላል፡፡
ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉ ይሰርቁናል ማለት ሳይሆን የስነምግባር ጉድለት ያለባቸው ሰዎችን ብቻ ይመለከታል፡፡
https://youtu.be/iPyzYGfLC44
ሲቪቲ ትራንስሚሽን ዘይት
ኒሳን እና ሆንዳ መኪና አለዎት? ካምቢዎው (transmission) CVT(Continuously Variable Transmission) ነው? የ ካምቢዮ ዘይት በ የስንት ጊዜ ነው ሚያስቀይሩት?
የ ሲቪቲ ትራንስሚሺን ዘይት ውድ ሲሆን ከ ሌሎች አውቶማቲክ ትራንስሚሺን ዘይትቶች ይለያል፡፡
የትራንስሚሺን ዘይት ሲቀየር ፊልተሩም አብሮ መቀየር አለበት፡፡
ባብዛኛው የኒሳን እና ሆንዳ ሲቪቲ ትራንስሚሽን ዘይት በየ 45,000 ሺህ ኪሜ ወይም 30,000 ማይልስ መቀየር እንዳለበት ካምፓኒዎቹ ያዛሉ፡፡
ተመራጭ የሆነው ዘይትም ባብዛኛው Valvoline Full Synthetic Continuously Variable Transmission (CVT) Fluid ነው፡፡
ዘይቱን በየጊዜው ማስቀየር ካላስፈላጊ ወጪ ይታደጋል፡፡
ይዘይቱን በየጊዜው አለማስቀየር የተሽከርካሪውን ትራንስሚሽን ከጥቅም ውጪ በማድረግ ለጥገና አስቸጋሪ ያረገዋል፡፡
የ ኤሌክትሪክ መኪኖች
በአሁኑ ሰአት የ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በብዛት ወደ ሀገራችን እየገቡ ነው፡፡
ሁሉም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የፍሪን ሲስተማቸው እንደሌሎች በ ነዳጅ ከሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡
12 ቮልት ባትሪ ሲኖራቸው AGM( Absorbent Glass Mat) ተመራጭ ነው፡፡
ባትሪያቸው ቻርጅ የሚደረገው ከትልቁ ባትሪ ከሚመጣ ሀይል ወደ ትንሽ ሀይል በሚቀይር DC/DC converter ነው፡፡
ከነዳጅ መኪኖች አንጻር የኤሌክትሪክ መኪኖች ለጥገና እና አጠቃላይ ወጪ የሚያስወጡት በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡
የኤሌክትሪክ መኪኖች በዋጋ ውድ አይደሉም ነገር ግን በሀገራቸን የሚሸጡት በጣም በተጋነነ ዋጋ ከተገዙበት እጥፍ በላይ ነው፡፡ የ 2023 Volkswagen ID 4 ከ 37 ሺ ዶላር ጀምሮ ነው የሚሸጠው፡፡ Tesla Model 3 ከ 33 ሺ ዶላር ጀምሮ ይሸጣል፡፡
ማንኛውም መኪና ገዢ አዲስ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ከመግዛቱ በፊት አለም ላይ የሚሽጡበትን ዋጋ ማጣራት አለበት፡፡
ማንኛውም መኪና ገዢ ለአጠቃላይ መኪናው እንዲሁም ለባትሪው ከ 5 እስከ 10 አመት የሚደርስ ዋስትና ከሚሰጥ ድርጅት መግዛት አለበት፡፡
