en
Feedback
ኢትዮ አውቶሞቲቭ - Ethio Automotive

ኢትዮ አውቶሞቲቭ - Ethio Automotive

Open in Telegram
1 383
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Similar Channels
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
January '24
January '24
+1 422
in 0 channels
Date
Subscriber Growth
Mentions
Channels
30 January+2
29 January0
28 January+1
27 January+4
26 January0
25 January+1
24 January0
23 January+1
22 January+2
21 January+2
20 January+2
19 January0
18 January0
17 January+1
16 January+1
15 January+1
14 January+1
13 January0
12 January0
11 January0
10 January0
09 January0
08 January0
07 January+1
06 January0
Channel Posts
ስለ አዳዲስ መኪኖች እና አንዳንድ ችግሮች አዲስ መኪና አለኝ ምን ምን ላድርግ? አዲስ መኪና ካለዎት በትንሹ እስከ አምስት አመት ምንም አይነት ብልሽት ሊያጋጥመዎ የማይችል መሆን አለበት፡፡ በየጊዜው የሞተር ዘይት ከቀየሩ እንዲሁም የትራንስሚሽን ፍሉድ ከቀየሩ ምንም አይነት ከባድ ችግር አያግጥመዎትም፡፡ በየቀኑ ጠዋት ጠዋት በኩላንት ምትክ ሁ ሚጨምሩ ከሆነ ሞተሩ በቅርቡ ይዝጋል! አዲስ ሱዙኪ አለኝ የኋላ ማርሽ ሳስገባ ገጭ ሚል ድምጽ እሰማለሁ መካኒክ ሳሳየው ካምቢዎ ይውረድ አለኝ ምን ላድርግ? ትንሽ ኮሽታ ሲሰሙ ወይም minor noise ሲያጋጥመዎ ሞተር ይውረድ ወይም ካምቢዎ ይወረድ ከሚል መካኒክ ራስዎን ይጠብቁ፡፡ እውነት እውነት እንለዎታለን አንዴ ከተፈታ ሌላ ችግር ውስጥ ነው ሚገቡት፡፡ ማንኛውም ድምጽ ሆነ ችግር ሳይፈታ መለየት አለበት፣ አሁን ባሉት ቴክኖሎጅ በመጠቀም ብዙ ችግሮች መለየት አለባቸው ምክንያቱም የተሽከርካሪውን የመካኒካል ፓርት በኤሌክትሮኒክስ ቁጥጥር ስለሚደረግበት እንደድሮ መኪኖች ለጥቃቅን ችግሮች ሞተር ወይም ካምቢዮ ማውረድ አያስፈልግም፡፡ በተመሳሳይ ቁልፍ ከፍተው እንዳይሰርቁኝ እፈራለሁ፡፡ መጠንቀቅ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን ማወቅ ያለብዎት አንድ ነግር ቢኖር መኪናውን የሸጠለዎ ሰው፣ ከዚህ በፊት የነሩት ባለቤቶች እንድሁም መኪናውን ወደ ሀገር ያስገቡት ሰዎች በርግጠኝነት ቁልፉ ሊኖራቸው እንደሚችል ነው፡፡ መኪና ልገዛ ብዬ ተወደደብኝ መኪና በውድ ዋጋ መግዛት ያቁሙ፡፡ ከመግዛትዎ በፊት ባለሙያ ያማክሩ፡፡ በተለምዶ በሚዎሩ ወሬዋች መታለል የለብዎትም፡፡ በቀደም ሱዚኪ ዲዛየር ሲንሳፈፍ አይተው ሊሆን ይችላል፡፡ አዳዲስ መኪኖች እጅግ በጣም ቀላል ክብደት እንዲኖራቸው ሁነው ነው የተሰሩት፡፡ አዲስ ከመሆኑ የተንሳም ጎርፍ ላያስገባ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ዲዛየር ጠቅላላ ክብደቱ ወደ 1300 ኪግ ሲጠጋ አንድ ቶዮታ ያሪስ ሲዳን ወደ 1600 ኪግ ይጠጋል፡፡

2
ሁለተኛ ዙር ስልጠና ከ ታህሳስ ወር በኋላ ስለሚጀምር አሁን ምንም አይነት ምዝገባ የለም፡፡
1 352
3
ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የተላለፈ ጥሪ ለሁሉም አመልካቾች በተለይ ምንም ኢንቪቴሽን አልደረስኝም ላላችሁ አመልካቾች፡፡ ኢሜልዎች ቼክ ያርጉ ከዛም Course Invitation የሚል ርዕስ ያለው search ካደረጉ ከ Canvas Free for Teachers የተላከ ኢሜል ያገኛሉ እሱን ከፍተው course accept ያድርጉ በቶሎ ይጀምሩ፡፡
2 167
4
ኤሌክትሪክ / ኤሌክትሮኒክስ ለተመዘገባቹ ከታች ባለው ሊንክ ቴሌግራም ይቀላቀሉ:: ማሳሰቢያ የተመዘገባቹ ብቻ ተቀላቀሉ:: If you register for Auto Electric/ Electronics Join the telegram group https://t.me/autoelectricelectronics
2 727
5
የዚህ ግሩፕ ተከታታዮች ለስልጠና ፍላጎት ያላቹ ባስቀመጥንላቹ መስፈርት እና ዝርዝር መሰረት መርጣቹ ላኩልን ከዚህ በፊትም ያስቀመጥነው ኣድራሻ ከላይ ይፈልጉ:: እናመሰግናለን::
3 004
6
ኢሜል ልካቹ ጥያቄ ያላቹ በላካቹት ኢሜል ጥያቄያችሁንም በኢሜል እንድታቀርቡ እንጥይቃለን፡፡ ኢሜል ተልኮላቹ ያልጀመራቹ በቶሎ እንድትጀምሩ፣ የሎሎች ሰልጣኞች ጊዜ መጉዋተት ስለሌለበት፡፡ ሌሎቻችሁ የምትፈልጉትን ጥያቄ ብቻ ይጠይቁ፣ ሀይ እያላችሁ አትላኩ፣ ይህ የመማሪያ ፔጅ ነው እናመሰግናለን፡፡ ስለስልጠናው እንዳንድ ነገሮች በጥቂቱ 1 ስልጠናው ዘመናዊ ዘዴ የተከተለ ነው፡፡ 2 ስልጠናው ክፍያ አለው፡፡ አስተማሪ ቀጥረን ጭምር ነው የምናስተምርዎት፡፡ 3 እርስዎ ከ ኮሌጅ ወይም ከዩንቨርሲቲ የተመረቁ እንደመሆነዎ መጠን የንድፍ ሀሳቡን በደንብ ያቁታል ብለን ስለምናስብ ስልጠናው Task ላይ ያተኩራል፡፡ 4 ለያንዳዱ ሞጁል አሳይመንት፣ discussion እና quiz እንዲሁም final exam ይኖረዋል፡፡ 5 ዝቅተኛውን መስፈርት ካላሟሉ ስልጠናውን ይደግማሉ:: ስለከፈሉ ብቻ ሰርቲፊኬት አይወስዱም፡፡ እንዲሁም የ አስተማሪዎቻችንን ችሎታ ጥያቄ ውስጥ መግባት ስለማይኖርበት፡፡ 6 ስልጠናውን የሚወስዱት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ነው፡፡
3 041
7
ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄ 1 ባለ 3 ጥርስ የሆነ አውቶማቲክ ትራንስሚሽን ( 3 speed AT) 1ኛ ላይ እና 2ኛ ላይ ድምጽ አለው ሶስት ሲደርስ ግን ድምጹ ይጠፋል የምን ችግር ነው? ከታች ምስሉን ይመልከቱ፡፡ A. sun gear B. planetary gear C. Ring Gear D. Clutch E. Torque Converter 2. ሞተሩ በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኝ ተፈትሾ ምንም ችግር የሌለበት አውቶማቲክ ትራንስሚሺን ቶዮታ ኮሮላ መኪና ሁሌ ከቆመበት እየተነሳ ለመሄድ ሲሞክር ፍጥነት ያንሰዋል 55 ለመድረስ ሲቸገር ከ 55 በሃላ ግን ላጥ ብሎ ይሄዳል፡፡ የዚህ ችግር ምንድን ነው? A. Torque Converter B. Low ATF fluid C. Clutch D. Bad transmission ማሳሰቢያ! መልሱን በ ኢንቦክስ ይላኩልን፡፡ መልሱን ኮመንት ላይ መጻፍ አያስፈልግም ሽልማትም አያስገኝም::
3 006
8
ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ውስጥ በ ኦንላይን ስልጠና የትኛውን መውሰድ ይፈልጋሉ? በዚ ኢሜል autotvetedu@gmail.com ይፃፉልን ሲፅፉልን በ ጀማሪ, መካከለኛ ወይም ኣድቫንስ ደረጃ እንደሚፈልጉ ያስቅምጡ:: Engine Fundamental Suspension & Steering Brakes Electrical/Electronic Systems Engine Repair Engine Performance Light Vehicle Diesel Engines Heating & Air Conditioning Automatic Transmission/Transaxle Manual Drive Train & Axles
2 548
9
የተሽከርካሪዎችን አመታዊ ምርመራ በሚያደረጉበት ጊዜ ማንኛውንም ፍሳሽ ካለ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ የተሽከርካሪዎች ዘይቶች እና ቅባቶች የተለያዩ ቀለማት አላቸው፡፡ የአውቶማቲክ ትራንስሚሽን በሆነ ተሽከርካሪ በሞተር እና በትራንስሚሽን (ካምቢዮ) መካከል ቀይ መሳይ ዘይት ካፈሰሰ ይህ ዘይት የአውቶማቲክ ትራንስሚሽን ዘይት ነው፡፡ የ አውቶማቲክ ትራንስሚሽን ዘይት ፓምፕ ጎሚኒ (seal) ሲበላ ዘይት በሞተር እና በካምቢዮ መካከል አልፎ ይፈሳል፡፡ የሚያፈሰው ዘይት ቀለም ሊለያይ ስለሚችል ከሞተር ዘይት ጋር ሊመሳሰል የሚችልበት አጋጣሚ ስለሚኖር በጥንቃቄ መመርመር ያስፈልጋል፡፡ ደማቅ ቀይ ቀለም ያለው ዘይት= አዲስ እና በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ ዘይት፡፡ ጠቆር ያለ ቀይ ቀለም ያለው ዘይት= በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ መቀየር ያለበት፡፡ ቡናማ ቀለም= የቆሸሸ በቶሎ መቀየር ያለበት፡፡ የጠቆረ ቀለም ያለው ዘይት= በሙቀት ምክንያት መቃጠል የጀመረ በቶሎ መቀየር ያለበት፡፡ ፒንክ ቀለም ወይም አረፋ ነገር ያለው= የ ኩለር መበላሸት እና ኩላንት ከካምቢዮ ዘይት ጋር መቀላቀል ያስከተለው ቀለም፡፡
2 570
10
በምስሉ ላይ የሚታየው ምንድን ነው? A. Brake Rotor Lateral Runout B. Brake Rotor Parallelism c. Brake Rotor Wear D. Brake Rotor Speed E. All
2 641
11
የ ፊውል ፓምፕ ቼክ ቫልቨ ችግር ሞተር ቶሎ እንዳይነሳ ያደርጋል፡፡ ቫልቩ ክፍት ከሆነ ሞተር ሲጠፋ መስመር ላይ ያለው ነዳኝ ወደ ነዳጅ ታንክ ስለሚመለስ እንደገና ሞተር በሚነሳበት ሰአት ነዳጅ ከ ታንኩ እስኪደርስ ጊዜ ስለሚፈጅ ቶሎ ያለመነሳት ችግር ይፈጥራል፡፡
2 614
12
ባለ አራት ሲሊንደር በቢንዚን የሚሰራ ተሽከርካሪ electronic control fuel pump ያለው ሲሆን ለመነሳት ብዙ ጊዜ ተደብድቦ ነው፡፡ ነዳጅ ከበቂ በላይ አለው፣ መኪናው እየሰራ የ ነዳጅ ግፊት ሲለካ (fuel pressure) 3.1 bar ያነባል ይህም ትክክል ነው፡፡ ሞተሩ ሲጥፋ በ 2 ደቂቃ ውስጥ ከ 1 bar በታች በ ወረደ ችግሩ ምንድን ነው?
2 860
13
ቴርሞስታት ለምን ያገለግላል? ቴርሞስታት ማስወጣት አግባብ ነው? እርስዎ ቴርሞስታተዎን አስወጥተዋል? ቴርሞስታት ማለት በማቀዝቀዣ ክፍል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ሞተር መጠነ ሙቀት እስኪደርስ ድረስ ኩላንት ወደ ራድያተር ውስጥ እንዳይገባ ዘግቶ የሚቆይ ነው፡፡
3 095
14
በምናሽከረክርበት ጊዜ የባትሪ መብራት ቢበራብን ምን ማድረግ ኣለብን? https://youtu.be/nExwrl-qtfA
3 280
15
የመኪና ስርቆት መበራከት ሰሞኑን የመኪና ስርቆት ከሁልጊዜውም በላይ ተበራክትዋል፡፡ ባብዛኛው ስርቆት የሚፈጸምባቸው ሴኩሪቲ ሲስተም (alarm) የሌላቸው ሲሆን ቁልፍ ተቀርጾ በቀላሉ የሚነሱ ናቸው፡፡ ቁልፍ በመቅረጽ ማን ሊሰርቀን ይችላል? 1. ከመኪና መሸጫ ቤት ጀምሮ ብልሹ ስነምግባር ባላቸው ሰዎች ከመጀምርያውም ሊቀረጽ ይችላል፡፡ 2. መኪና የምናሰራበት ቦታ ብልሹ ስነምግባር ባለቸው መካኒኮች ከሌሎች ሌቦች ጋር በመተባበር ሊያስቀርጹ ይችላሉ፡፡ ሁሉም መካኒክ ሌባ ነው ማለት አይደለም፡፡ 3. መኪና ስናሳጥብ ቁልፍ ሰጥተን ከሄድን ሊቀረጽ ይችላል፡፡ 4. ሬስቶራንት እና ሆቴሎች ለማቆም ቁልፍ ከሰጠን ሊቀረጽ ይችላል፡፡ 5. አልፎ አልፎ በራሳችን የቅርብ ሰው ጓደኛ ወይም ለትንሽ ጊዜ ባበደርነው ሰው ሊቀረጽ ይችላል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉ ይሰርቁናል ማለት ሳይሆን የስነምግባር ጉድለት ያለባቸው ሰዎችን ብቻ ይመለከታል፡፡ https://youtu.be/iPyzYGfLC44
3 226
16
image_2023-03-14_16-44-46.png
3 190
17
image_2023-03-05_16-55-10.png
3 307
18
image_2023-03-05_16-55-09.png
3 255
19
ሲቪቲ ትራንስሚሽን ዘይት ኒሳን እና ሆንዳ መኪና አለዎት? ካምቢዎው (transmission) CVT(Continuously Variable Transmission) ነው? የ ካምቢዮ ዘይት በ የስንት ጊዜ ነው ሚያስቀይሩት? የ ሲቪቲ ትራንስሚሺን ዘይት ውድ ሲሆን ከ ሌሎች አውቶማቲክ ትራንስሚሺን ዘይትቶች ይለያል፡፡ የትራንስሚሺን ዘይት ሲቀየር ፊልተሩም አብሮ መቀየር አለበት፡፡ ባብዛኛው የኒሳን እና ሆንዳ ሲቪቲ ትራንስሚሽን ዘይት በየ 45,000 ሺህ ኪሜ ወይም 30,000 ማይልስ መቀየር እንዳለበት ካምፓኒዎቹ ያዛሉ፡፡ ተመራጭ የሆነው ዘይትም ባብዛኛው Valvoline Full Synthetic Continuously Variable Transmission (CVT) Fluid ነው፡፡ ዘይቱን በየጊዜው ማስቀየር ካላስፈላጊ ወጪ ይታደጋል፡፡ ይዘይቱን በየጊዜው አለማስቀየር የተሽከርካሪውን ትራንስሚሽን ከጥቅም ውጪ በማድረግ ለጥገና አስቸጋሪ ያረገዋል፡፡
3 244
20
የ ኤሌክትሪክ መኪኖች በአሁኑ ሰአት የ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በብዛት ወደ ሀገራችን እየገቡ ነው፡፡ ሁሉም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የፍሪን ሲስተማቸው እንደሌሎች በ ነዳጅ ከሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ 12 ቮልት ባትሪ ሲኖራቸው AGM( Absorbent Glass Mat) ተመራጭ ነው፡፡ ባትሪያቸው ቻርጅ የሚደረገው ከትልቁ ባትሪ ከሚመጣ ሀይል ወደ ትንሽ ሀይል በሚቀይር DC/DC converter ነው፡፡ ከነዳጅ መኪኖች አንጻር የኤሌክትሪክ መኪኖች ለጥገና እና አጠቃላይ ወጪ የሚያስወጡት በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ የኤሌክትሪክ መኪኖች በዋጋ ውድ አይደሉም ነገር ግን በሀገራቸን የሚሸጡት በጣም በተጋነነ ዋጋ ከተገዙበት እጥፍ በላይ ነው፡፡ የ 2023 Volkswagen ID 4 ከ 37 ሺ ዶላር ጀምሮ ነው የሚሸጠው፡፡ Tesla Model 3 ከ 33 ሺ ዶላር ጀምሮ ይሸጣል፡፡ ማንኛውም መኪና ገዢ አዲስ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ከመግዛቱ በፊት አለም ላይ የሚሽጡበትን ዋጋ ማጣራት አለበት፡፡ ማንኛውም መኪና ገዢ ለአጠቃላይ መኪናው እንዲሁም ለባትሪው ከ 5 እስከ 10 አመት የሚደርስ ዋስትና ከሚሰጥ ድርጅት መግዛት አለበት፡፡
3 209