ሰዋስው ☘☘☘☘
Open in Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
Show more1 161
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
1 161
ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል የአቡነ አሮን የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፭ (5) ቀን።
❤ እንኳን ለከበረች ለቅድስት ሐጊያ ሶፍያ ለሁለት ልጆቿ ለቅዱሳት አክሶስናና ከበርናባ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ለታላቁ ሰማዕት ለበሉት የሚጡትን አንበሳ በላቸው ላይ ለተቀመጠ ለቅዱስ ማማስ ለዕረፍት በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሚባሉት ከቅዱስ ማማስ ከአባቱ ቅዱስ ቴዎዶስዮስና ከእናቱ ቅድስት ታውፍና እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ ሰመዕቷ ቅድስት ሐጊያ ሶፊያ ከሁለት ልጆቿ ቅዱሳት አክሶስናና በርናባ፦ ይችም ቅድስት አስቀድማ አማናዊት ነበረች ወላጆቿም ጣዖታትን የሚያመልኩ ናቸው። እርሷም በልቧ አስተዋለች መረመረችም የወላጆቿ ሃይማኖት ከንቱ እንደሆነ ተረዳች ከዚህም በኋላ ወደ መኖፌ ኤጲስቆጶስ ሔዳ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ታመነች እንዲህም "በሕያው አምላክህ አምኜአለሁና አጥምቀኝ" እርሱም ሃይማኖት የቤተ ክርስቲያንም ሕግ አስተማራት። ከዚህም በኋላ ከወላጆቿ ጋራ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃት።
❤ ከዚህም በኋላ የአገረ ሰዎች ለአማልክት መስገድ ትታ ክርስቲያን እንደሆነች በገዢው በከላድያኖስ ዘንድ ወነጀሏት ገዢውም ወደ እርሱ አስቀርቦ መረመራት እርሷም ክብር ይግባውና በክርስቶስ አመነች እንጂ አልካደችም ከልጆቿም ጋር ብዙ ሥቃይ አሰቃያት። በሥቃይ ውስጥ ሳሉ ልጆቿን ታስታግሳቸውና ታጽናናቸው ነበር እንዲህም ትላቸው ነበር "ልጆቼ ጠንክሩ ጨክኑ እኔ የአንጌቤዋን እመቤት ሶፍያን እመስላታለሁ እናንተም ጲስጢስ፣ አላጲስ፣ አጋጲስ የተባሉ ልጆቿን ምሰሉ" እነርሱም እንዲህ ብለው መለሱላት "እናት ሆይ እኛ ፍለጋሽን እንከተላለንና ስለእኛ አትፍሪ ይህንንም በሚባባሉ ጊዜ ከእናታቸው ጋር ተሳሳሙ።
❤ ገዢውም ሲሳሳሙ አይቶ ደናግል ልጆቿን እንዲፈሩ እናታቸው በጅራፍ ይገርፏት ዘንድ አዘዘ ያን ጊዜም የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ወርዶ እናታቸውን ከግርፍት ሲሰውራት አዩ። ዝንጎዎች ሊገርፏት በአራቆቷት ጊዜ በዚያ ሰዓት እንዲህ በማለት ትጮህ ነበር "ዓለሙን ሁሉ በፈጠረ በእውነተኛ አምላክ በእግዚአብሔር የማምን ክርስቲያናዊት ነኝ" ያን ጊዜም ገዢው ምላሷን ከሥሩ እንዲቆርጡ አዘዘ እርሷ ግን መጮህንና በመናገርን አላቋረጠችም።
❤ ከዚህም በኋላ ገዢው ወደ እስር ቤት እንዲወስዷት አዘዘ ትሸነግላትም ዘንድ ሚስቱን ወደ እርሷ ላከ እርሷን ግን ምንም አልመለሰችላት። ራሷንም በሠይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ የድል አክሊልንም ተቀበለች። አንዲት ሴት መጥታ ሥጋዋን በጭልታ ወሰደች ወደ ቤቷም አስገብታ በፊቷ መብራትን አኖረች።
❤ ከዚህም በኋላ ልጆቿን ጠርቶ እሺ ይሉት ዘንድ አስፈራራቸው እምቢ ባሉትም ጊዜ እያከታተለ ራሳቸውን አስቆረጠ ምስክነታቸውንና ተጋድሏቸውንም ፈጸሙ። ከመቃብራቸውም በሽታውንና ደዌውን ሁሉ የሚፈውሱ ብዙ የሆኑ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ።
❤ ደግ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ዜናቸውን በሰማ ጊዜ የቅዱሳት ሰማዕታትን ሥጋቸውን ወደ ቊስጥንጥንያ አፍልሶ ወሰደ። የሶፍያንና የልጆቿን ዜና ከመስማቱ በፊት ታላቅና ሰፊ የሆነ ቤት እንዲሠሩ በላይዋም "ይቺ ቤት የንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ናት" ብለው ጽሑፍ እንዲቀርጹባት አዘዘ እነርሱም ንጉሡ እንዳዘዘ ወደማታ ሲሆን ይጽፍሉ የእግዚአብሔር መልአክም ወርዶ ያንን ደምስሶ "ይቺ ቤት የሶፍያ ናት" ብሎ ይጽፍል። የሕንፃውም ባለ ሙያዎች የሚያደርጉት አጡ መጻፍቸውን ተዉ።
❤ በአንዲት ቀንም የንጉሥ ልጅ ብቻውን ሲጫወት መልአክ ተገለጸለትና "የዚች ቤት ስሟ ማነው" አለው ሕጻኑም "አላውቀም" አለው መልአኩም ሁለተኛ እንዲህ አለው "አባትህን የሶፍያን ቤት ብለህ ሰይማት ብለህ ንገረው" ሕጻኑም "ተመልሼ እክመጣ ትጠብቀኛለህን" አለው መልአኩ "አዎ እጠብቅሃለሁ" አለው። አባቱም ይህን ሰምቶ መልአክ እንደሆነ አወቀ ሕጻኑንም በመጠበቅ ምክንያት ያ መልአክ ከዚያች ቦታ እንዳይሔድ ብሎ ንጉሡ ልጁን ገደለው። መልአኩም ሕጻኑን እየጠበቀ እስከ ዛሬ ድረስ አለ
❤ የዚያች ቤተ ክርስቲያንም ርዝመቷ 709 ክንድ ሆነ አግድመቷም 307 ክንድ ምሶሶዎቿም 400 ጠረጴዛዎቿም 8 የሚያበሩ ዕንቊዎቿ 4 ናቸው ከአጎበሩ በላይ የተቀረጹ ኪሩቤልም በየሁለት ክንፎቻቸ የእግዚአብሔር ሕግ የተጻፈበትን ታቦት ይጋርዳሉ።
❤ ሥጋቸው በውስጡ ያለበትን የቅድስት ሶፍያንና የልጆቿን ሣጥን በታላቅ ምስጋናና ክብር ወደዚያ አስገብተው አኖሩ። በድኖቻቸውንም የሰበሰበች ያቺንም ሴት ከእርሷቸው ጋር ቀበሩዋት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ሰማዕታት በቅዱስ ሶፍያና በልጆቿ ቅዱሳት አክሶስናና በርናባ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ "ሰላም ለማማስ ሰማዕተ ወልድ ዘአቊረራ ለነድ ዘሎቱ አንበሳ ይሰግድ"። ትርጉም፦ አንበሳ ለሚሰግድለትና ነበልባልን ላቀዘቀዛት የወልድ ምስክር ለኾነ ለማማስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ ሰማዕቱ ቅዱስ ማማስ፦ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ቴዎዶስዮስ የእናቱም ታውፍና ናቸው። በንጉሥ ዑልያኖስ ዘመንም ስለ ሃይማኖታቸው ይዘው አሠሩአቸው በእሥር ቤትም ሳሉ ዐረፉ። አንዲት ክርስቲያናዊት ሴት መጥታ ይህን ሕፃን ወስዳ እንደ ልጅዋ አድርጋ አሳደገችው። ስሙንም ማማስ ብላ ሰየመችው ትርጓሜውም። የሙት ልጅ ማለት ነው አባትና እናት የለውምና።
❤ ዐሥራ ስምንት ዓመትም በሆነው ጊዜ ወደ ከሀዲው ገዢ ሒደው ክርስቲያን ነው ብለው ወነጀሉት ይዘውም በበትሮች ደበደቡት በአንገቱም የሚከብድ ሸክም ታላቅ የዓረር ደንጊያ አንጠልጥለው ከባሕር ውስጥ ጣሉት። ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር ኃይል ከባሕር ስጥመት ዳነ ወጥቶም በዋሻ ውስጥ ተሠውሮ ከጎሽ ወተትን እየተመገበ ተቀመጠ።
❤ ከዚህም በኃኋላ ሁለተኛ ያዙት ወስደውም ከሚነድ እሳት ውስጥ ጨመሩት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አዳነው። ዳግመኛም ተነጣጥቀው እንዲበሉት አንበሶችን በላዩ ሰደዱ በእግዚአብሔርም ኃይል በአንበሳ ላይ ተቀመጠ።
❤ ከዚህም በኋላ ብዙ አሠቃዩት ሕዋሳቶቹ እስቲለያዩና የሆድ ዕቃው እስቲፈስ ጎተቱት ተጋድሎውንና ምስክርነቱን በዚህ ፈጽሞ የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ማማስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ "ሰላም እብል ለማማስ ምቱር። በአስይፍተ መንገን በሊሐት ወበመንኰራኵር፡፡ ዝንቱ መዋዒ ሶበ ጸለየ በደብር። ተውህበ ሎቱ እምሰማይ በትር። ወበዘቢቢጦቱ ማየ አውጽአ እምድር"። ትርጉም፦ ስሎች በኾነ የመዘውር ሰይፎች እና በመንኰራኵር የተቆረጠ ለኾነ ለማማስ ሰላም እላለኊ፤ ይኽ አሸናፊ በተራራ ላይ በጸለየ ጊዜ ከሰማይ ለርሱ በትር ተሰጠለት፤ በምቱም ውሃን ከምድር አወጣ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 5።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "አዋልደ ንግሥት ለክብርከ። ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት"። መዝ 44፥9። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 5፥1-7፣ 1ኛ 3፥5-10 እና የሐዋ ሥራ 16፥8-16። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 13፥31-44። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፭ (5) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያውያኑ ጻድቃን ታላቁን አስገራሚውን ጣራዊ ክፍት ሆኖ ዝናብ የማይገባው ቤተ መቅደስ ለአነጹ ለታላቁ አባት ለአቡነ አሮን ዘመቄት (መንክራዊ) ለዕረፍት በዓል፣ ጥርሳቸው እያበራ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ይሰጥ ለነበሩት ለአቡነ ገብረ ኢየሱስ ዘጎንደር ለልደት በዓልና እግዚአብሔር ለሚወድ ሃይማኖቱ ለቀና ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ለአፄ ልብነ ድንግል ለዕረፍት በዓልና በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አቡነ አሮን ዘመቄት (መንክራዊ)፡- የመቄቱ አቡነ አሮን ወላጅ አባታቸው የላስታው ጻድቁ ንጉሥ ዐፄ ገብረ መስቀል ናቸው፡፡ እናታቸው አመተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የላስታ ነገሥታት የዘር ሐረጋቸው ከንጉሥ ሰሎሞን ዘር ሲያያዝ የመጣ ነው፡፡ ከ10ኛው እስከ 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (920-1253 ዓ.ም ገደማ) በላስታ ቡግና ምድር የነገሡ የላስታ ቡግና ተወላጅ የሆኑ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ነገሥታት የንግሥናቸው መጠሪያ "የዛጉዌ ሥርወ መንግሥት" ወይም "የላስታ መንግሥት" በመባል ይታወቃል፡፡ የንጉሥ ሰሎሞን ዘር የሆነው መራ ክርስቶስ 3 ልጆችን ወለደ፡፡ እነርሱም ጠንጠውድም፣ ግርማ ስዩምና ዣን ስዩም ናቸው፡፡
❤ ጠንጠውድም ገብረ መስቀልን ወለደ፣ ገብረ መስቀልም አቡነ አሮንን ወለደ፣ ግርማ ስዩም ይምርሐነ ክርስቶስን ወለደ፣ ዣን ስዩም ደግሞ ገብረ ማርያምንና ላሊበላን ወለደ፡፡ ገብረ ማርያምም ነዓኲቶ ለአብን ወለደ፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ነገሥታት እንደ መልከጼዴቅ (ዘፍ14፡18) ክህነትን ከንግሥና፣ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ እግዚአብሔርንም ሕዝብንም በቅድስናና በንጽሕና አገልግለው አልፈዋል፡፡
❤ አቡነ አሮን ግን ገና በ7 ዓመታቸው ነው ዓለምን ፍጹም ንቀው በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል እጅ የመነኰሱት፡፡ በ16 ዓመታቸውም ዋልድባ ገዳም ገብተዋል፡፡ ነሐሴ 5 ቀን ገና ሲወለዱ ሙት አስነሥተዋል፡፡ በሀገራችን እየተዘዋወሩ ወንጌልን ሲሰብኩ የሸዋው ንጉሥ አንኮበር ድረስ ጠርቷቸው ሲሔዱ አዋሽ ወንዝ ሞልቶባቸው አገኙት፡፡ ሲሻገሩም ዳዊታቸውን ወስደባቸው፡፡ "ልጆቼን አመነኰስክብኝ" በሚል ሰበብ ንጉሡ 7 ዓመት በግዞት አስሮ አስቀመጣቸው፡፡ ነገር ግን ከ7 ዓመት በኋላ አቡነ አሮን ተመልሰው በአዋሽ ወንዝ ሲመጡ መልአክ መጣና "መቋሚያህን ወደ ወንዙ ላክ" አላቸው። መቋሚያቸውንም ቢልኩ ከ7 ዓመት በፊት ወደ ወንዙ ገብቶባቸው የነበረውን ዳዊታቸውን ይዘው አወጡ፡፡ ዳዊቱም በውኃው አልራሰም ነበር፣ ይልቁንም አቧራውን አራግፈው ፈጣሪያቸውን አመስግነው ዳዊታቸውን ይዘው ሄደዋል፡፡ ያ ዳዊታቸው ዛሬም ድረስ በጋይንት አበርጉት ቅዱስ ሚካኤል ይገኛል፡፡
❤ ሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ ውስጥ የሚገኘው እጅግ አስደናቂ ገዳማቸው ፍልፍል ዋሻ ሲሆን ጣራው ክፍት ነው፣ ክፍት በሆነው ጣራ በኩል ፀሐይ ሲገባ ስለሚያቃጥል ጥላ ይይዛሉ ነገር ግን የጻድቁ ግዝት ስላለበት ዝናብ ወደ መቅደሱ ፈጽሞ አይገባም፡፡ እጅግ አስደናቂ ነው፡፡ አቡነ አሮን በዋድላ ሜዳ አልፈው ሲሄዱ አንችም ሜዳ ላይ እንደ ኢያሱ ፀሐይን በቃላቸው ገዝተው አቁመዋታል፡፡ ከታች ጋይንት ተነሥተው መንገድ ሲሄዱ በሰንበት ቀን በሬ ጠምዶ ሲያርስ የነበረን ገበሬ "ለምን በሰንበት ታርሳለህ?" ቢሉት "ምቀኛ መነኵሴ" ብሎ በጅራፉ ቢገርፋቸው በሬዎቹ ግን ፈጽሞ አልንቀሳቀስ ብለው ቆመዋል፡፡ በዚህ የተናደደው ገበሬም አቡነ አሮንን መሬት ላይ ጥሎ ገረፋቸው፡፡ እሳቸውም ተነሥተው ሲሄዱ ዛፎች ተነቅለው እየተከተሏቸው፣ ቃልም አውጥተው በሰው አንደበት አመስግነዋቸዋል፡፡ ከአቡነ አሮን መንክራዊ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!።
+ + +
❤ አቡነ ገብረ ኢየሱስ ዘጎንደር፦ የትውልድ አገራቸው ጎንደር ፎገራ ሲሆን መስከረም 5 ቀን ተወለዱ። ጻድቁ የሚታወቁት አንድ ትልቅ ግብር አላቸው። እርሱም ጥርሳቸው እያበራ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ይሰጥ ነበር። መነኰሳቱ በጥርሳቸው ብርሃን ብቻ አገልግሎት ያካሄዱ ነበር። ጻድቁ ሲያርፉም ጥርሳቸው የ6 ሰዓት መንገድ ተሂዶ ሲያበራ ታይቷል። በጻድቁ ስም የተጠሩ ገዳማት በትግራይና ሽሬና በጎንደር ይገኛል። ዕረፍታቸው መጋቢት5 ነው። ከአባታችን ገብረ ኢየሱስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።
+ + +
❤ በዚችም ቀን እግዚአብሔርን የሚወድ ሃይማኖቱ የቀና ደግ ጻድቅ የኢትዮጵያ ንጉሥ ልብነ ድንግል ዐረፈ። የንጉሥ የአፄ ልብነ ድንግል በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 5 ስንክሳር።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
ዛሬ የፍቁረ እግዚእ በዓለ ልደቱ ነው፡፡ በዓለ ልደቱን በሕላዌ ሁኖ የሚያከብረው የሐዋርያው ረድኤት አይለየን ለእዚህ ቅዱስ የጥንቷ ታዋቂዋ የሴት መምህር እሜቴ ገላነሽ ይህችን ድንቅ ዘመን ተሻጋሪ ጉባኤ ቃና አድርገዋል ወደ ጉባኤ ቃናዋ
ዘማ መቅበርት ለወልደ ነጎድጓድ ትቤሎ
እመትጸልአኒ አንተ ዘያፈቅረኒ ሀሎ
ወደ አማርኛ ስንመልሳት
ዘማዊት መቃብር ለዮሐንስ (ለወልደ ነጎድጓድ) አንተ ብትጠላኝ የሚያፈቅረኝ ሞልቷል አለችው
ለሰሙ:-
አንዲት ሴት ወዳው የጠላትን ወንድ አንተ ብትጠላኝ ሌላው ይወደኛል መች የሚወደኝ አጣው እንደምትለው ያቺ ዘማዊት ሁሉን ወዳጅ ተብላ የተጠራችው መቃብር ስትሆን የጠላት የመነናት ደሞ ዮሐንስ ነው፡፡
ይህም ወደ ወርቅ ስንወስደው ዮሐንስ አልሞተም , ሞትን አልቀመሰም ነው ፡፡
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ዮሐ. 10:1-22፡ "አማን አማን እብለክሙ" - "እውነት፡እውነት፡እላችኋለሁ፥ወደበጎች፡በረት፡በበሩ፡የማይገባ፡በሌላ፡መንገድ፡ግን፡የሚወጣ፡እርሱ፡ሌባ፡ወንበዴም፡ነው፤ በበሩ፡የሚገባ፡ግን፡የበጎች፡እረኛ፡ነው። ለእርሱ፡በረኛው፡ይከፍትለታል፤በጎቹም፡ድምፁን፡ይሰሙታል፥የራሱንም፡በጎች፡በየስማቸው፡ጠርቶ፡ይወስዳቸዋል። የራሱንም፡ሁሉ፡ካወጣቸው፡በኋላ፡በፊታቸው፡ይሄዳል፥በጎቹም፡ድምፁን፡ያውቃሉና፡ይከተሉታል፤ ከሌላው፡ግን፡ይሸሻሉ፡እንጂ፡አይከተሉትም፥የሌላዎችን፡ድምፅ፡አያውቁምና። ኢየሱስ፡ይህን፡ምሳሌ፡ነገራቸው፤እነርሱ፡ግን፡የነገራቸው፡ምን፡እንደ፡ሆነ፡አላስተዋሉም። ኢየሱስም፡ደግሞ፡አላቸው፦እውነት፡እውነት፡እላችኋለሁ፥እኔ፡የበጎች፡በር፡ነኝ። ከእኔ፡በፊት፡የመጡ፡ሁሉ፡ሌባዎችና፡ወንበዴዎች፡ናቸው፤ዳሩ፡ግን፡በጎቹ፡አልሰሟቸውም። በሩ፡እኔ፡ነኝ፤በእኔ፡የሚገባ፡ቢኖር፡ይድናል፥ይገባልም፡ይወጣልም፡መሰማሪያም፡ያገኛል። ሌባው፡ሊሰርቅና፡ሊያርድ፡ሊያጠፋም፡እንጂ፡ስለ፡ሌላ፡አይመጣም፤እኔ፡ሕይወት፡እንዲሆንላቸው፡ እንዲበዛላቸውም፡መጣሁ። መልካም፡እረኛ፡እኔ፡ነኝ።መልካም፡እረኛ፡ነፍሱን፡ስለ፡በጎቹ፡ያኖራል። እረኛ፡ያልሆነው፡በጎቹም፡የርሱ፡ያልሆኑ፡ሞያተኛ፡ግን፥ተኵላ፡ሲመጣ፡ባየ፡ጊዜ፥በጎቹን፡ትቶ፡ይሸሻል፤ተኵላም፡ይነጥቃቸዋል፡በጎቹንም፡ይበትናቸዋል። ሞያተኛ፡ስለ፡ሆነ፡ለበጎቹም፡ስለማይገደው፡ሞያተኛው፡ይሸሻል። መልካም፡እረኛ፡እኔ፡ነኝ፥አብም፡እንደሚያውቀኝ፡እኔም፡አብን፡እንደማውቀው፡የራሴን፡በጎች፡ዐውቃለሁ፡የራሴም፡በጎች፡ያውቁኛል፤ነፍሴንም፡ስለ፡በጎች፡አኖራለሁ። ከዚህም፡በረት፡ያልሆኑ፡ሌላዎች፡በጎች፡አሉኝ፤እነርሱን፡ደግሞ፡ላመጣ፡ይገ፟ባ፟ኛል፥ድምፄንም፡ይሰማሉ፥አንድም፡መንጋ፡ይሆናሉ፥እረኛውም፡አንድ። ነፍሴን፡ደግሞ፡አነሣት፡ዘንድ፡አኖራለሁና፡ስለዚህ፡አብ፡ይወደኛል። እኔ፡በፈቃዴ፡አኖራታለሁ፡እንጂ፡ከእኔ፡ማንም፡አይወስዳትም።ላኖራት፡ሥልጣን፡አለኝ፡ደግሞም፡ላነሣት፡ሥልጣን፡አለኝ፡ይህችን፡ትእዛዝ፡ከአባቴ፡ተቀበልሁ። እንግዲህ፡ከዚህ፡ቃል፡የተነሣ፡በአይሁድ፡መካከል፡እንደ፡ገና፡መለያየት፡ሆነ። ከእነርሱም፡ብዙዎች፦ጋኔን፡አለበት፡አብዷልም፤ስለ፡ምንስ፡ትሰሙታላችሁ፧አሉ። ሌላዎችም፦ይህ፡ጋኔን፡ያለበት፡ሰው፡ቃል፡አይደለም፤ጋኔን፡የዕውሮችን፡ዐይኖች፡ሊከፍት፡ይችላልን፧አሉ። በኢየሩሳሌምም፡የመቅደስ፡መታደስ፡በዓል፡ሆነ።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
በቅዳሴ ጊዜ
#ምስባክ
መዝሙር ፶፱÷፬
ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሑከ
ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅስት
ወይድኀኑ ፍቁራኒከ
#ትርጉም፦
ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ፥
ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው።
ወዳጆችህ እንዲድኑ በቀኝህ አድን፥
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማቴ. 11:7-20 "ወእምድኅረ ኀለፉ ላእካነ እግዚእ" - "እነዚያም፡ሲሄዱ፡ኢየሱስ፡ለሕዝቡ፡ስለ፡ዮሐንስ፡ሊናገር፡ጀመረ፥እንዲህም፡አለ፦ምን፡ልታዩ፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ወጣችሁ? ነፋስ፡የሚወዘውዘውን፡ሸምበቆን፧ወይስ፡ምን፡ልታዩ፡ወጣችሁ? ቀጭን፡ልብስ፡የለበሰ፡ሰውን? እንሆ፥ቀጭን፡ልብስ፡የለበሱ፡በነገሥታት፡ቤት፡አሉ። ወይስ፡ምን፡ልታዩ፡ወጣችሁ? ነቢይን፧አዎን፡እላችኋለሁ፥ከነቢይም፡የሚበልጠውን። እንሆ፥መንገድህን፡በፊትህ፡የሚጠርግ፡መልክተኛዬን፡በፊትህ፡እልካለሁ፡ተብሎ፡የተጻፈለት፡ይህ፡ነውና። እውነት፡እላችኋለሁ፥ከሴቶች፡ከተወለዱት፡መካከል፡ከመጥምቁ፡ዮሐንስ፡የሚበልጥ፡
አልተነሣም፤በመንግሥተ፡ሰማያት፡ግን፡ከሁሉ፡የሚያንሰው፡ይበልጠዋል። ከመጥምቁም፡ከዮሐንስ፡ዘመን፡ጀምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡መንግሥተ፡ሰማያት፡ትገፋለች፥ግፈኛዎችም፡ይናጠቋታል። ነቢያት፡ሁሉና፡ሕጉ፡እስከ፡ዮሐንስ፡ድረስ፡ትንቢት፡ተናገሩ፤ ልትቀበሉትስ፡ብትወዱ፥ይመጣ፡ዘንድ፡ያለው፡ኤልያስ፡ይህ፡ነው። የሚሰማ፡ጆሮ፡ያለው፡ይስማ። ነገር፡ግን፥ይህን፡ትውልድ፡በምን፡እመስለዋለሁ? በገበያ፡የሚቀመጡትን፡ልጆች፡ይመስላሉ፥እነርሱም፡ባልንጀራዎቻቸውን፡እየጠሩ። እንቢልታ፡ነፋንላችሁ፥ዘፈንም፡አልዘፈናችሁም፤ሙሾ፡አወጣንላችሁ፥ዋይ፡ዋይም፡አላላችሁም፡ይሏቸዋል። ዮሐንስ፡ሳይበላና፡ሳይጠጣ፡መጣ፥እነርሱም፦ጋኔን፡አለበት፡አሉት። የሰው፡ልጅ፡እየበላና፡እየጠጣ፡መጣ፥እነርሱም፦እንሆ፥በላተኛና፡የወይን፡ጠጅ፡ጠጪ፥የቀራጮችና፡የኀጢአተኛዎች፡ወዳጅ፡ይሉታል።ጥበብም፡በልጆቿ፡ጸደቀች። በዚያን፡ጊዜ፡የሚበዙ፡ተኣምራት፡የተደረገባቸውን፡ከተማዎች፡ንስሓ፡ስላልገቡ፡ሊነቅፋቸው፡ጀመረ፡እንዲህም፡አለ።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
4/1/2015 ዓ.ም (፬/፩/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
አጽምኡ ሕዝብየ ሕግየ።
ወጽልው ልብከሙ ኀበ ቃለ አፉየ።
እከሥት በምሳሌ አፉየ፡፡ መዝ. 77፥1
🕯 ትርጉም
ሕዝቤ ሆይ ሕጌን አድምጡ።
ጆሯችሁንም ወደ አፌ ቃል አዘንብሉ።
አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፬ (4) ቀን።
❤ እንኳን ለወንጌላዊው ለወልደ ነጎድጓድ ለቅዱስ ዮሐንስ ለልደት በዓል፣ ለነዌ ልጅ ለቅዱስ ኢያሱ ለመታሰቢያ በዓሉና ለእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ መቃርስ ዕረፍት በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ በአንጾኪያ በሰማዕትነት ከዐረፉ ከ 2መቶ ሰዎች ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ "ሃሌ ሉያ ፣ሃሌ ሉያ፣ ሃሌ ሉያ "ኮከበ ሰመይናከ ፀሓየ ጽድቅ ዘሐፀነከ ውስተ ሕፅኑ ዘአርፈቀከ ኮከበ ሰመይናከ፡፡ በአፉሁ ዘሰዐመከ ወበቅናቱ ዘአቅነተከ ኮከበ ሰመይናከ፡፡ ኅቡአቲሁ ዘአርአየከ ወንጌለ ጸጋሁ ዘአወፈየከ ኮከበ ሰመይናከ። ዮሐንስ መኑ ከማከ አስተምህር ለነ ሰአልናከ"። ትርጉም፦ ሃሌ ሉያ፣ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ። ኮከብን ብለን ጠራንኽ፤ የጽድቅ ፀሓይ ያሳደገኽ ባጠገቡ (በጉያውም) ያስቀመጠኽ ኮከብን? ብለን ጠራንኽ፡፡ በአፉ የሳመኽ በመታጠቂውም ያስታጠቀኽ ኮከብን ብለን ጠራንኽ፡፡ የተሰወረውን ምስጢር ያሳየኽ የጸጋውን ወንጌል የሰጠኽ ኮከብን ብለን ጠራንኽ፡፡ ዮሐንስ እንዳንተ ያለ ማን ነው ታማልደን ዘንድ ማለድንኽ። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።
+ + +
❤ "ሰላም ለኢያሱ መስፍን እስራኤልሀ ተከዜ በእግር ዘአዕደወ፤ ምድረ ርስት ሎሙ ዘአርኀወ፤ ወፀሓየ በገባዖን ዘዓቀመ ወወርኀ መንገለ ኤላም"። ትርጉም፦ እስራኤልን ባሕረ ተከዜን (ዮርዳኖስን) በእግር ያሻገረ፤ ምድረ ርስትን ያወረሰ ለእነርሱ የከፈተ (ድል አድርጎ የገለጠ) ፀሓይን በገባዖን፤ ጨረቃን ወደ ኤላም ያቆመው ለኾነ ለመስፍኑ ለኢያሱ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ መቃርስ፦ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ከቍጥራቸው ውስጥ ነው።
ይህም አባት ከታናሽነቱ ጀምሮ በገድል የተጠመደ ሆነ የምንኲስናንም ልብስ ሊለብስ ወዶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወጣ። በዚያም በመጀመሪያው አባት በአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መነኰሰ በምንኲስና ያለውንም ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ።
❤ ይህምእርሱም ሁልጊዜ መጻሕፍትን የሚያነብና ትርጓሜያቸውንም የሚያስረዳ ሁኗልና በትሩፋት ስራ ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ ቅስና ተሾመ። ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤልም በዐረፈ ጊዜ ኤጲስቆጶሳቱ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔዱ። ከእርሳቸውም ጋር ሃይማኖታቸው የቀና ብዙዎች አዋቂዎች ካህናት ነበሩ በአስቄጥስ ገዳም ከሚኖሩ ከታላላቅ መነኰሳትም ጋራ ስብሰባ አድርገው ለዚች ለከበረች ሹመት ስለሚገባው ሰው እየመረመሩ ብዙ ቀኖች ተቀመጡ።
❤ ከዚህም በኋላ የተሻለና ለዚች ለከበረች ሹመት የሚገባ ይህን አባ መቃርስን አግኝተው ሊቀ ጵጵስና ሊሾሙት ሁሉም በአንድ ምክር ተስማው። ስለ ትሩፋቱና ስለ ተጋድሎው በአስቄጥስ ገዳም የሚኖሩ ብዙ መነኰሳት ምስክሮች ሁነዋልና ይዘውትም ሊሔዱ ያለ ፍቃዱ ይዘው አሰሩት እርሱ ግን እንዲህ እያለ ይጮህ ነበር። "እኔ ለዚች ለከበረች ሹመት የማልገባ ነኝ እናቴ ሁለት ባሎችን አግብታ ስለነበር" ይህንንም ያለው እንዲተዉት እንጂ እናቱ ግን በአንድ ባል ብቻ የኖረች ሌላ የማታውቅ ንጽሕት እንደሆነች ስለርሷ ብዙዎች ምስክሮች ሁነዋልና። ስለዚህ እርሱ የተናገረውን ምክንያት አልተቀበሉትም።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ወስደው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት ከዚያም ወደ ምስር አውጥተው በመዓልቃ በሚገኘው አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሹመቱ ደብዳቤ በዮናኒ በቅብጥ በአረብ ቋንቋ ተነበበች።
❤ ከዚህም በኋላ በሹመቱ ወራት በጎ ስራ ትሩፋትን ተጋድሎውን አብዝቶ የሚሰራ ሆነ ። ሁል ጊዜም ለህዝቡ እግዚአብሔርን እንዲፈሩ ያስተምራቸዋል ስለ ነፍሳቸውም ድኀነት ይገሥጻቸው ነበር።
❤ በሹመቱ ወራትም ከራሱ ከሚገባው ከግብሩ ለቤተ ክርስቲያን ይሰጣል ለድኆችና ለችግረኞችም ይመጸውታል እንጂ ከቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ምንም ምን አልወሰደም። በሹመቱም ሃያ ሰባት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርንም አገልግሎ ደስ አሰኝቶ በሰላም በፍቅር ሳለ ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ መቃርስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 4 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለመቃርስ በእስክንድርያ ዘተአምነ። መርዔተ ክርስቶስ ይርዓይ መሲሐውያነ። ለእለ ኀረይዎ ሕዝብ ዘይሰመዩ ኄራነ። ጸሊዖ ሢመተ እንዘ ውእቱ ኢኮነ። ወልደ ዳግሚት ብእሲት ይቤሎሙ አነ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 4።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ። ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅስት። ወይድኀኑ ፍቁራኒከ"። መዝ 59፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት 1 ጢሞ 3፥1-8፣ 1 ጴጥ 5፥9-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 7፥44-51። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 6፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ የልደት በዓል እና የብፁዕ አባ ሙሴ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንል።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
