en
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Open in Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Show more
1 161
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለማርያም ቅድስት እሙ ለፀሓየ ጽድቅ፤ ማኅደረ መለኮት፤ ዘኤዶም ገነት እንተ ዕፀዊሃ ስርግዋን በሥነ ሕይወት፤ እለ ይፈርዩ አፈዋተ፤ ወእለ ይጸግዩ በረከት፤ ዘአበው በአተ መዛግብት እንተ ውስቴታ ዕንቊ ወያክንት"። ትርጉም፦ የአባቶች የሀብታቸው ማከማቻ በር (መግብያ)፤ በውስጦቿ ዕንቊና ያክንት ያሉባት፤ ሽቶን የማያፈሩ በረከትንም የሚያብቡ ዕንጨቶቿም የሕይወት ውበት ያጌጡ የተሸለሙ የኤዶም ገነት የተባለች፤ የመለኮት ማደርያ የፀሓይ ጽድቅ እናቱ ቅድስት (ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣ ልዩ) ለኾነች ማርያም ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። @Eotcw @Eotcw @Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ የተባረከ የግንቦት ወር መዓልቱ ዐሥራ አራት ሰዓት ነው ከዚህም ይጨምራል። ❤ ግንቦት ፩ (1) ቀን። ❤ እንኳን አምላክን ለወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ለጸናች ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ለልደቷ መታሰቢያ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። + + + ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ፦ "ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም እም ሐና ወኢያቄም ከመ ትቤዙ ነቢያት ወጻድቃነ አማን ተወልደት እመ ብርሃን"። ትርጉም፦ በእመቤታችን ልደት ዛሬ ደስታ ሆነ ይኸውም ከሐና ከኢያቄም መወለዷ ነው ነቢያትና ጻድቃንን በልጇ ታድናቸው ዘንድ በእውነት የብርሃን እናት ተወለደች። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ አምላክን የወለደች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት፦ እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ናት። ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ቅዱስ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ቅድስት ሐና ይባላሉ። ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ በዚያ ወራት የመካኖችን መብዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበርና። እርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኀዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር። ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ኀሳባቸውን ተመለከተ። ❤ ክብር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገልጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እደሚሰጠው አበሠረው። በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱ ለቅድስት ሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ኢያቄምም ለሚስቱ ሐናን እንዲህ አላት "ሰማያት ሲከፈቱ አየሁ፤ ነጭ ወፍ መጣ በራሴ ላይም አረፈ" እንደዚህም ሁሉ ሐናም "ርግብ በራሴ ላይ ስትቀመጥብኝ በማሕፀኔም ስታድር አየሁ ገባች" አለችው። ነገራት ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርም አመሰገኑት። ❤ የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ በቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች። ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ነሐሴ ሰባት ቀን ተፀነሰች ከስድስት ወር በኋላም የብፅዕት ሐና መፅነስ ታወቀ። ዘመዶችም ሰሙ ወደ እርሷ መጥተውም "የምንሰማው ይህ ነገር አውነት ነውን? ዘመንሽ ካለፈ በኋላ በአንቺ ላይ የተደረገው ነገር ምንድን ነው?" አሏት። ከሐና ዘመዶች ወገን የአርሳባን ልጅ የምትሆን አንዲት ዐይኗ ማየት የተሳናት አንዲት ሴት ነበረች። "የሰማሁት እውነት ነውን?" ብላ የሐናን ማኅፀን ዳሰሰች። "እህቴ ሆይ ሽማግሌ ስትሆኚ እንዴት ፀነስሽ" አለቻት። ዳግመኛም ማየት የተሳነው ዐይኗን ዳሰሰችው ያን ጊዜም ዐይኗ ተከፈተላት ብርሃንንም አየች። "ብፅዕት ሐና ሆይ ለአንቺ ብፅዓን ይገባሻል ፅንስሽ በማኅፀንሽ እያለ ገና ሳይወለድ በሽተኞችን የፈሰ በግልጽ ከታየ ከማሕፀንሽ ከወጣማ ምን ያህል ይፈውስ ይሆን?" እንደዚሁም ሁሉ ብዙ በሽተኞች መጥተው እየዳሰሱ ከበሽታቸው ይፈወሱ ይድኑም ነበር። ይህ ነገርም በእስራኤል ሽማግሎዎች ሁሉ ዘንድ ዕፁብ ድንቅ ሆነ። ❤ ቅድስት ሐናም የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ በግንቦት አንድ ቀን ከፀሓይ ይልቅ ፈጽማ የምታበራ ሴት ልጅ በሊባኖስ ተራራ ላይ ወለደች፤ የመልኳም ደም ግባት ከመዓር ከሦከር ይልቅ ደስ ያሰኛል፤ የመዓዛዋም ሽታ ከሽቱ ሁሉ ይበልጣል። ዘመዶቿና ጐረቤቶቿም በሰሙ ጊዜ ፈጽሞ ደስ አላቸውና ተሰብስበው ወደስዋ መጡ ወደሷም መጥተው ልጅዋን ባዩ ጊዜ ፈጽመው አደነቁ እርስ በርሳቸውም "እንደዚች ያለች ብላቴና ከቶ አይተን አናውቅም" ተባባሉ ጸጋ እግዚአብሔር በርሷ ላይ አድሯልና የእግዚአብሔርም ብርሃን በሰውነቷ ሁሉ መልቷልና። ከኢያቄምና ከሚስቱ ከሐና ጋራ ደስ እያላቸው የእግዚአብሔርን ቸርነት እየተናገሩ ሰባት ቀን ተቀመጡ ያችንም ብላቴና ስሟንም ማርያም ብላ ሰየመቻት ትርጓሜውም እመቤት ነው ደግሞም ሀብትና ስጦታ ማለት ነው። በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ናት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። ምንጭ፦ ተአምረ ማርያም፣ ድርሳነ ቅድስት ሐና ወኢያቄምና የግንቦት 1 ስንክሳር ። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወለገጽኪ ይትመሀለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር። ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን። በዘአዝፋረ ወርቅ ዑፅፍት ወኊብርት"። መዝ 44፥12-13። የሚነበቡት ወንጌል ማቴ 1፥1-18። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን። ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን። እምኵሉ ተዐይኒሁ ለያዕቆብ"። መዝ 86፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 4፥1-13፣ 1ኛ ጴጥ 8፥13፣ የሐዋ ሥራ 7፥44-51 ወይም 1፥12-15 የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥39-57። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን ማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የልደታ ለማርያም በዓል፡፡ ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @Eotcw @Eotcw @Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፩ (1) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቃን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ለአክስት ልጅ እንደ ነቢዩ ኤልያስ እሳት ከሰማይ አውርደው በሸዋ ክፍለ አገር ፈንታሌ ተራራ ላይ ሰሪቲ ለምትባ ጠንቋይ እየተላላኩ ሕዝቡን የሚያስቱና የሚያሰቃዩ አራት መቶ ሰባ ሽህ ሦስት መቶ አጋንንት በአንድ ጊዜ ላጠፋ ለታላቁ አባት ለአቡነ ቀውስጦስ ለልደታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ ቀውስጦስ፦ ጻድቁ የተወለዱት ሸዋ ክፍለ አገር በወግዳና ቡልጋ ውስጥ ሲሆን አባታቸው ቅዱስ ገላውዴዎስ እናቸው ቅድስት እምነ ጽዮን ይባላሉ። የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እናት እግዚእ ኃርያ እና እምነጽዮን ታናሽና ታላቅ እህትማማቾች ናቸው። ❤ ቅዱስ ገላውዴዎስና ቅድስት እምነ ጽዮን እግዚአብሔር የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ለዓመታት በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስዕል ፊት ሲጸልዩና ሲለምኑ እመቤታችን በስዕሏ ላይ አድራ አናገረቻቸው፤ እንዲህም አለቻቸው፦ " አንድ ልጅ አስቀድማችሁ ትወልዳላችሁ፤ የሚወለደውም እኔ በተወለድኩበት ግንቦት1 ቀን ዕረፍቱም በእኔ ዕረፍት ቀን ጥር21 ነው እሱም የሰማያዊ ንጉሥ ጭፍራ ይሆናል" አለቻቸው። በቃሏ መሰረትም ግንቦት1 ቀን ጻድቁ አቡነ ቀውስጦስ ተወለዱ። ❤ ጻድቁ አባታችን አቡነ ቀውስጦስ የዚህን ዓለም ተድላ፣ ደስታና ጠዐም ንቀው ፈለገ ሐዋርያትን ተከትለው በሸዋ፣ በከፋና በጅማ ዞረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በማስተማር አረማውያን፣ ነገሥታትና ባላባቶች የሚደርስባቸውን መከራና እንግልት በመታገስ በተጋድሎ ፀንተው ብዙውን ሕዝብ ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር ከኃጢያት ወደ ጽድቅ መልሰዋል። በተለይም በሸዋ ክፍለ አገር ፈንታሌ ተራራ ላይ ሰሪቲ ለምትባ ጠንቋይ እየተላላኩ ሕዝቡን የሚያስቱና የሚያሰቃዩ ፬፻፸ሺ፫፻ (አራት መቶ ሰባ ሽህ ሦስት መቶ) አጋንንትን እንደ ነቢዩ ኤልያስ በጸሎታቸው ከሰማይ እሳት አውርደው ተራራውን ደምስሰው አጋንንቱን አቃጥለዋል። ሕዝቡንም ለጣዖትና ለጠንቋይ ከመገዛት አድነውታል። ❤ ጻድቁ አባታችን አቡነ ቀውስጦስ በብዙ ተጋድሎ ሲኖሩ በሰማዕትነት ያርፉ ዘንድ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚተጉ እንጂ የዚህን ዓለም መንግሥት ሀብትና ስልጣን የማይሹ እውነተኛ መናኝ ነበሩና የታናሽ ወንድማቸው የአፄ ይኩኖ አምላክ ልጅ አፄ አምደ ጽዮን የአባቱን እቁባት በማግባቲ "ይህንን ልታደርግ አይገባህም"። ብለው እንደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቢገስጹት ዐሥራ አንድ አሽከሮቹን በሌሊት ልኮ ከበዩ ወደ እንሳሮ አገር ካስወሰዳቸው በኋላ ኮሶ አረህ ከሚባለው አፋፍ ላይ በእኩለ ሌሊት በጦር ጎናቸውን አስወግቶ ደማቸውን አስፈሰሰ። ደማቸውም እስከ ታላቁ ወንዝ ጀማ ድረስ ሆነ። የፈሰሰው ደማቸውም ቀይ ብርሃን ሲሆን የሌሊቱ ጨለማ ከፀሐይ ሰባት እጅ የሚበልጥ ብርሃን በአውራጃዎቹ ሁሉ ታየ። በዚህ የተነሳ እስከ ዛሬ ድረስ አገሩ ቀን ተብሎ ይጠራል። ❤ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ሳትለይ በስቃይ ላይ ሳሉም በዘመናቸው ሁሉ ስለነበራቸው ተጋድሎ፣ ንፅህናና ምናኔ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምንና ቅዱሳን መላእክትን አሰከትሎ በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት መጣና ቃል ኪዳን ሰጣቸው። እንዲህም አላቸው፦ "እኔ ለአንተ አይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን መንግሥተ ሰማያትን አዘጋጀውልህ። በዘመንህ ስላሳለፍከው ክርስቲያናዊ ፍፁም ተጋድሎህ ሰባት የብርሃን አክሊል (ዘውዶችን) ያዘጋጀውልህ ሲሆን ሁለቱ እንደ እነ ነቢዩ ኤልያስና ነቢዩ ሳሙኤል ለሆነ ንጽህናህ፣ ሁለቱ እንደ እነ ቅዱስ ጴጥሮስና ጳውሎስ ለሆነ የወንጌል ስብከትህ፣ ሁለቱ እንደ እነ ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ፊቅጦር በትዕግሥት ስለተጋደልክ፣ አንዷ ስለ ልብህ ርህራኄ ናት ብሎ አጎናፅፏችኋል። እንዲሁም ስለ እኔ ምስክርነት የሞትክባት ምድር እንደ ዳዊት አገር እንደ ኢየሩሳሌም ትሁንል ወደእርሷ የሄደውንም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ መቃብሬ ጎልጎታ እንደሄደ እቆጥርለታለሁ። ብዙ ኃጢያት የሥራ ሰው ንስሐ ገብቶ በዚያች አገር በስምህ ጥቂት ምጽዋት ቢሰጥ እኔ ኃጢያቱን እደመስስለታለሁ፤ በጠበልህም ቢጠመቅ በደሉን አጠፋለታለሁ ደምህ በምድሪቱ ፈሷልና፤ በዕረፍትህ ዕለት ለቤተ ክርስቲያንህ ለቅዱስ ቁርባን ስንዴ፣ ወይንና ዕጣን ያቀረበ ኃጢያት የሰራ ተነሳሂ (ንስሃ የገባ) ሰው ቅዱስ ሥጋውንና ክብር ደሙን እንደተቀበለ ንፁህ ሰው አደርገዋለሁ፣ ለስምህ መታሰቢያ በታነጸው ቤተ መቅደስ በንጽህና ቅዱስ ሥጋውንና ክብር ደሙን የሚቀበል (የሚቆርብ) ሰው ራሱን፤ ቤተሰቡንና ባልንጀሮቹን ያድናል"። ❤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለጻድቁ አባታችን አቡነ ቀውስጦስ ይህንን ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው ዐረገ። ቅዱሳን መላእክትም ነፍሳቸውን ከስጋቸው በክብር ለዩ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በሰማይ መካከል ነፍሳቸውን በፈገግታ ተቀበለች። የዕረፍታቸውም ዕለት እመቤታችን ባለፈችበት ጥር 21ቀን በመሆኑ እመቤታችንም "መታሰቢያህን ለሚያደርጉ ሁሉ በልጄ በረከት እበርካቸዋለሁ" ብላ ቃል ኪዳን ገባችላቸው። ጻድቁ አባታችን አቡነ ቀውስጦስ ባረፉበት ዕለትም ብዙዎች ከዴዌአቸው ተፈውሰዋል። የጻድቁ አባታችን በረከትና ፈውስ አሁንም ድረስ ደማቸው በፈሰበትና አፅማቸው ባረፈበት ቦታ ሁሉ እየታየ ብዙ ምዕመናን ፈውስ ነፍስና ፈውሰ ሥጋ እያገኙበት ነው። ❤ ገዳመ ቀውስጦስ የሚገኘው ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 120ኪ.ሜ ርቀት ላይ ሲሆን ወደ ደብረ ሊባኖስ በሚወስደው መንገድ ሙከጥሪ ከተማ ሲደርሱ ወደቀኝ በመታጠፍ ሜጤና ባዩ በሚባለው አካባቢ ልዩ ስሙ ተግባሬ (መገንጠያ) ከሚባል ቦታ ነው። ከጻድቁ አቡነ ቀውስጦስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ቀውስጦስ (በአጭሩ) ከሚለው መጽሐፍ። @Eotcw @Eotcw @Eotcw

ዛሬ የእናቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ሳነብ ያገኘዋትን ላካፍላችሁ ❤❤❤ + የእናት ነገር + ከጥቂት ወራት በፊት በዚሁ የኢንተርኔት አደባባይ ይህንን ፎቶ ስንመለከት ብዙዎቻችን ‹#አይ_የእናት_ነገር!› ብለን አዝነናል ፣ ተደንቀናል፡፡ ይህች ወጣት የልጅዋን መርፌ መወጋት ማየት አቅቷት ዓይኗን ጨፍና ስትሸማቀቅ ያየ ሁሉ መቼም ምንም እንደ ድንጋይ የጠጠረ ልብ ቢኖረው እንኳን ለአፍታ ማዘኑ ና ከንፈር መምጠጡ የማይቀር ነው፡፡ የሚያሳሳው ሕጻን ልጅ ያለ አንዳች ፍርሃት ክትባቱን እየሠጠችው ያለችውን ሐኪም አተኩሮ እያየ ነው ፤ እናት ግን ለልጁ ያልተሰማው ሕመም ከመጀመሪያው ተሰምቷት ጥርሷን ነክሳለች፡፡ እናት የሆኑ የእስዋ ስሜት ይሰማቸዋል ፤ #እናት ያለን ሁላችን ደግሞ እናቶቻችንን እናስባለን፡፡ የስነ ልቡና እውቀት ቢኖረኝና ስለ እናትና ልጅ ትስስር ጽንሰ ሃሳብ (mother child attachment theory) መተንተን ቢቻለኝ ኖሮ ይህች እናት ይህ ፎቶ በተነሣበት ቅጽበት ምን ዓይነት ስሜት ተሰምቷት እንደነበር ብዙ ነገር በተናገርኩ ነበር፡፡ ያለሙያዬ ገብቼ እንዳልዘባርቅ ይህን ለባለሙያዎቹ ልተወውና በዚህ ፎቶ ምክንያት ላነሣት ስለወደድሁት ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ስለነበረች እናት ላስታውሳችሁ፡፡ #ልጅዋ_በጅራፍ_ሲገረፍ_ቆማ_ያየች_የእሾህ_አክሊል_ሲደፉበት_የተመለከተች ፣ #ከመርፌ_በሚበረታ_ጦር_ጎኑን_ሲወጉት_የተመለከተችዋን_ኀዘንተኛ_የድንግል_ማርያምን_ነገር_እስቲ_ለአንድ_አፍታ_እናስታውሰው፡፡ በእርግጥ በዕለተ አርብ #ድንግል_ማርያም ምን ተሰምቷት ነበር? ኢትዮጵያዊው #አባ_ጽጌ_ድንግል ‹‹ከቀለም ጋር ዕንባዬን እያንጠባጠብሁ የድንግልን ሰቆቃዋን እጽፋለሁ... በማንኛውም ጊዜ የእርስዋ ዓይነት ኀዘንና ስደት የደረሰበት ሰው ካለ የልብ ዓይን ያለው ሰው አይቶ ያልቅስ›› (ሰቆቃወ ድንግል እጽሕፍ በቀለመ አንብዕ ወአንጠብጥቦ ... ከማሃ ኀዘን ወተሰዶ ሶበ በኩለሄ ረከቦ ... ርእዮ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ) እንዳለው እስቲ ለደቂቃ #የድንግል_ማርያምን ኀዘን መለስ ብለን እናስታውሰው፡፡ በእርግጥ ግን በዚህ ፎቶ ላይ ያለችውን እናት ስናይ የተሰማን የሃዘን ስሜት #ድንግል_ማርያም_ከመስቀሉ_ስር ቆማ_ተስሎ ስናይ ተሰምቶን የማያውቀው የልብ ዓይን ስለሌለን ይሆንን? #ያለ_አባት_የወለደችውን_አንድያ_ልጇን_አጥንቱ_እስኪታይ_ሲገርፉት_በእርግጥ_ድንግል_ማርያም_ምን_ተሰምቷት_ይሆን? #ከሔሮድስ_ሰይፍ_ይዛው_የሸሸችውን_ልጇን_በወታደሮች_ተከብቦ_ስታየው_ምንኛ_ቆስላ_ይሆን? አቅፋ ያሳደገችውን በጉያዋ ይዛው የተሰደደችውን #ልጅዋን_መስቀል_አሸክመው_ሲያዳፉት_በወደቀበት_ቦታ_በጭካኔ_ሲረግጡት_ባየች_ጊዜ_የድንግል_ልብ_ምንኛ_ታመመ_ይሆን? እስቲ በንጹሕ ሕሊና ተመልከቱት ፣ ይህ የየትኛውም እምነት ተከታይ መሆን አይጠይቅም፡፡ እናት የሆነና እናት ኖራው የሚያውቅ ሁሉ ሊመልሰው የሚችል ጥያቄ ነው፡፡ በምድር ላይ እጅግ አሰቃቂ የተባለውን ሞት ልጅዋ ሲቀበል ያየችውን #ድንግል እስቲ በዓይነ ሕሊናችን እንመልከታት፡፡ #ጌታችን የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ እያለ ወደ ኢየሩሳሌም ይዘውት በሔዱ ጊዜ ጠፍቶባቸው ነበር፡፡ #ዮሴፍና_ድንግል_ማርያምም የአንድ ቀን መንገድ ከሔዱ በኋላ መጥፋቱን አወቁ ፣ ከዘመዶቻቸው ጋርም ፈልገው አጡት፡፡ በመጨረሻም ከሦስት ቀን በኋላ #በቤተ_መቅደስ ቁጭ ብሎ ከመምህራን ጋር ሲጠይቅና ሲሰማ አገኙት፡፡ #ድንግል_ማርያም ይህን ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን አለችው።›› (ሉቃ. 2፡48) ለሦስት ቀን ያህል በመጥፋቱ ምክንያት መጨነቅዋን ተናገረች ፣ ‹ለምን እንዲህ አደረግብን?› ብላም ጠየቀችው፡፡ ለሦስት ቀን መጥፋቱ ያስጨነቃት #ድንግል ደሙ ሲፈስስ ባየች ጊዜ ምንኛ ተጨንቃ ይሆን? #ከመስቀል ጋር በሚስማር ተቸንክሮ በስቃይ ላይ ሆኖ ስታየው ምን ያህል ተሰቃይታስ ይሆን? በእርግጥም #አረጋዊው_ስምዖን እንዳለው #በጌታችን ሰውነት ውስጥ ሚስማርና ጦር ሲገባ #በእናቱ ደግሞ ‹‹በነፍስዋ ሰይፍ ያልፍ ነበር›› (ሉቃ. 2፡35) #ያዕቆብ አሥራ አንድ ልጆች እያሉት ‹ልጅህ ዮሴፍ ሞተ› ብለው ብለው በነገሩት ጊዜ ልብሱን ቀደደ፥ በወገቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ። (ዘፍ. 37፡34) #ኢትዮጵያዊው_ሊቅ_ርቱዐ_ሃይማኖት ታዲያ ስለ #ድንግል_ማርያም ኀዘን ሲናገር ‹‹#የያዕቆብ_ልቅሶ_ዛሬ _ታደሰች_አለ›› በእርግጥም #ያዕቆብ አሥራ አንድ ልጆች እያሉት እንዲህ ካለቀሰ #ድንግል_ማርያም_በድንግልና ስለወለደችው አንድ ልጅዋ ምንኛ ታለቅስ ይሆን? #ያዕቆብ ያለቀሰው የልጁን #የዮሴፍን ልብስ በእጁ ይዞ ነበር፡፡ #ድንግል_ማርያም ግን የልጅዋን ልብስ ይዛ እንዳታለቅስ ልብሱን ቀድደው ተካፍለውታል ፣ በቀሚሱም ላይ ዕጣ ተጣጥለዋል፡፡ የእርስዋ ኀዘን #ከያዕቆብ ኀዘን ይበረታል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ‹‹እርሱ ተሰቀለ እንጂ እርስዋ ምን ሆነች? አንተ ብትቆነጠጥ እናትን ያማታል ወይ?› እያሉ ሊፈላሰፉ ይሞክራሉ፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ‹የልጅ ስቃይ ለእናት ምንዋ እንደሆነ እናቶቻችሁን ሒዱና ጠይቁ› ከማለት በቀር ምን እንመልሳለን? የሱ መከራ ለእርስዋ ምንም አይደለም የሚለው አመለካከት የሰይጣን የራሱ አስተሳሰብ እንደሆነ #መጽሐፍ_ቅዱስ ያስረዳናል፡፡ ታስታውሱ ከሆነ #ጻድቁ_ኢዮብ ዐሥር ልጆቹ በአንድ ጊዜ መሞታቸው ሲነገረው አምላኩን ባለመሳደቡ ሰይጣን አፍሮ ነበር፡፡ #በኢዮብ ጥንካሬ ደስ ያለው ፈጣሪም ሰይጣንን ‹‹ባሪያዬን ኢዮብን አየኸው?›› ብሎ ቢጠይቀው ‹‹ቁርበት ስለ ቁርበት ነው ፤ በሰውነቱ መከራ ብታመጣበት ይክድሃል›› አለ፡፡ በሰይጣን አስተሳሰብ አንድ አባት ልጆቹ ቢሞቱም እንኳን የራሱ ሰውነት እስካልተነካ ድረስ ዘልቆ አይሰማውም ፣ ሕሊናውንም አይፈትነውም፡፡ ኢዮብስ ልጆቹ የመሞታቸውን ዜና ሰማ እንጂ አሟሟታቸውን አላየም፡፡ ልጅዋ ሲሰቃይ ያየች #ድንግል_ማርያም ‹እስዋ ምንም አልሆነችም› የሚል ሰው ሃሳቡ ሰይጣን ከተናገረው በምን ይለያል?

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ኢያቄም ወሐና ወለዱ ሰማየ ሰማዮሙኒ አስረቀት ፀሐየ ቅ.ያሬድ እንኳን ለእመቤታችን ፳፻፳፱ኛ አመት የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ!!!!! ፠ ሰላም ለልደትኪ እማኅፀነ ድክምት ሥጋ ድኅረ ኀለፋ ውርዙት ወድኅረ ትክቶ ኃደጋ #ልደታለማርያም እመቤታችን በነገረ ማርያም ላይ የምትወዳቸውን በዓላት ስጠዘረዝር ከሁሉም አብልጣ የምትወደው በዓሏ እንደሆነ የተናገረችለት በዓል በዓለ ልደቷን ነው፡፡ ለዚህም እንደምክንያት የጠቀሰችው ከጨለማ ወደ ብርሃን ከጠባብ ወደ ሰፊ የወጣሁበት እንዲሁም ደሞ እናትና አባቴ በዚያች መካንነት እንደ ኃጢያት በሚቆጠርበት ዘመን በሁሉ ዘንድ መጠለላትን እና መገለልን የእኔ ልደት አርቋልና ከሁሉ በዓላቶቹ እወደዋለው ብላለች፡፡ #ግንቦትልደታለምንበተለየመልኩበደጅይከበራል?? ይህ የግንቦት ልደታ በዓል ከሌሎቹ በዓላት በተለየ መልኩ በደጅ ነው የሚከበረው ይህም ቅድስት ሐና እመቤታችንን በጸነሰች ጊዜ የአጎቷ ልጅ አርፎ ለለቅሶ ሂዳ አስከሬኑን እየዞረች በምታለቅስ ጊዜ ጥላዋ አስክሬኑ ላይ ቢያርፍ ከሞተበት ተነስቷል ይህንን ያዩ እኩያን አይሁድ በማኅጸን ሁኖ እንዲህ ያደረገ ልጅ ሲወለድማ እንደ ዳዊት እንደ ሰሎሞን ቀጥቅጦ ይገዛናል ብሎ በክፋት በቅድስት ሐና ላይ በተነሱባት ጊዜ በስደት ወደ ሊባኖስ ተራራ ሂዳ #ሰማይን በዚያ ወልዳታለች እኛም ከቤት በመውጣት የምናከብረው ይህንን ምሳሌ በማድረግ ነው፡፡ ከአቆራሪተ መዐት ከሰዐሊተ ምህረት እመቤታችን ረድኤቷን በረከቷን ያሳድርብን

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለማርቆስ ለማርያም ዕጓላ። ዘሰሐብዎ በአህባል ውስተ ዐፀደ ላሕም ከመ ዳቤላ። አመ አውዕዮቶ ፈቃዱ ለእሳት በነበልባላ። ዝናም ወአስሐትያ አጥፍኡ ማዕበላ። መብረቅኒ ለሥጋሁ ከለላ"። ትርጉም፦ በላም በረት ውስጥ እንደ ወይፈን በገመድ የሳቡት ለኾነ ለማርያም ልጅ ለቅዱስ ማርቆስ ሰላምታ ይገባል፤ ርሱን በእሳቲቱ ላንቃ (ወላፈን) ለማቃጠል በወደዱ ጊዜ ውርጭ እና ዝናብ ማዕበሏን አጠፋ፤ መብረቅም ሥጋውን ጋረዳት። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሚያዝያ 30። @Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ እንኳን ለትንሣኤ ሦስተኛ ሳምንት ለኤማሁስ መንገደኞች መታሰቢያ ቀን በሰላም አደረሰን። + + + ❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ "ወበእሑድ ሰንበት ጌሠት ማርያም መግደላዊት በጽባሕ ኀበ መቃብር እንዘ ዓዲ ጽልመት ወረከበት ዕብነ ዕቱተ እምአፈ መቃብር ወበጽሐት ኀበ ስምዖን ጴጥሮስ ወኀበ ካልዕ ረድዕ ዘያፈቅሮ ኢየሱስ ወትቤሎሙ ነሥእዎ ለእግዚእየ እምውስተ መቃብር ወኢየአምር ኀበ ወሰድዎ እንዘ ይረውጹ ክልኤሆሙ ኅቡረ በድሮ ለጴጥሮስ ዝኩ ካልዕ ረድእ ዘያፈቅሮ ኢየሱስ"። ትርጉም፦ በእሑድ ሰንበትም ማርያም መግደላዊት ገና ጨለማ ሳለ ገሥግሣ ወደ መቃብር ደንጊያውንም ከመቃብሩ አፍ ተነሥቶ አገኘች ፈጥናም ወደ ስምዖን ጴጥሮስ ኢየሱስ ይወደው ወደ ነበረው ወደ ሁለተኛው ደቀ መዝሙር ደረሰች፤ ጌታዬን ከመቃብር የወሰዱበትን አላውቅም አለቻቸው ጴጥሮስም ያ ሁለተኛውም ደቀ መዝሙር ወጡና ወደ መቃብር ሄዱ ሁለቱም በአንድነት ሲሮጡ ያ ሌላው ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን ቀድሞት ወደ መቃብር ደረሰ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ይእዜ እትነሣእ ይቤ እግዚአብሔር። እሬሲ መድኀኒት ወአግህድ ቦቱ። ቃለ እግዚአብሔር ቃል ንጹሕ"። መዝ 11 የሚነበቡት መልእክታት 2ኛ ቆሮ 5፥11-ፍ.ም፣ 2ኛ ጴጥ 3፥14-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 21፥31-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 24፥13-33። መልካም የቅዱስ የማርቆስ የዕረፍት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። @Eotcw

❤ ሌሊት ሲሆንም ይገድሉት ዘንድ እስከሚሰበሰቡ ድረስ ወደ እስር ቤት አስገቡት፡፡ መንፈቀ ሌሊት ሲሆንም በሮች ተዘግተው ጠባቂዎችም ተኝተው ሳሉ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ የእግዚአብሔር መልአክም "የግብጽን አገራት ሁሉ የምታረጋጋ የእግዚአብሔር አገልጋይ ማርቆስ ሆይ ስምህ በሰማይ ባለ የሕይወት መጽሐፍ ተጽፏል ከሐዋርያት ቁጥርም ተቆጥሮአል፤ መታሰቢያህም አይረሳም፤ በምድርም ስፍር ቁጥር የሌላትን ሥልጣን፣ ጸጋ ኃይል እነሆ ሰጥቶሃልና፤ ነፍስህ በሰማይ ይሆናል ሥጋህም በመሬት አይጠፋም" አለው፡፡ ❤ ቅዱስ ማርቆስም ይህን ምሳሌ በተመለከተ ጊዜ እጆቹን ወደ ሰማይ አነሣ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከፊትህ አልጣልኸኝም፣ ከቅዱሳን ማኀበርም ደምረኸኛልና አመሰግንሃለሁ፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እለምንሃለሁ ነፍሴን በሰማይ ተቀበላት፤ ከፊትህም አትተወኝ" አለ፡፡ ይህን በተናገረ ጊዜ ጌታችን አዳኝ ከሆነው ከሕማሙ በፊት በመቃብርም ከመጨመሩ አስቀድሞ በሐዋርያት መካከል እንደነበረ ሆኖ ታየው፡፡ "የመረጥሁህ ማርቆስ ሆየ ሰላሜ ከአንተ ጋር ይሁን፤ በወንጌል አስተማርሁህ፤ እነሆመ መከራን ከመቀበሌ አስቀድሞ ከጓደኞችህ ከሐዋርያት ጋር አንደሆንሁት በአርአያ ተገለጥኩልህ፤ ከእነርሱ ምንም ጉድለት እንዳይኖርብህ" አለው፡፡ ቅዱስ ማርቆስም "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከጸጋህ ታላቅነት የተነሣ አመሰግንሃለሁ፤ በሥጋህ አንደነበርህ ሁነህ አንዳይህ የተገባኝ አድርገኸኛልና” አለው "ስለተቀደሰው ስምህ መከራን እቀበል ዘንድ ትዕግሥትን አድለኸኛልና" ጌታችንም ሰላምን ሰጠውና በታላቅ ምስጋና ወደ ሰማይ አረገ ፡፡ ሲነገም የአገሩ ሰዎች ተሰበሰቡ፤ ከእስር ቤትም አወጡት በሰንሰለትም አሰሩት፤ ዳግመኛም በላሞች ቦታ እንደፍየል እንጐትተው እያሉ በከተማው ጐተቱት፡፡ ❤ ብፁዕ ማርቆስም ምስጋናን አቀረበ በሰማይ ተገለጠ፡፡ በየአገሩ ከጎተቱት በኋላም ደሙ በየመንገዱና በየአደባባይዋ ሞላ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ነፍሴን በእጅህ ሰጠሁ" አለ፡፡ ይህን ከተናገረ በኋላም ሚያዝያ 30 ቀን ዐረፈ፡፡ ሁሉም አረማውያን ቅዱስ ማርቆስ አንዳረፈ በተመለከቱ ጊዜም ሥጋውን በእሳት ያቃጥሉት ዘንድ አውበካልዮን በምትባል ቦታ ጽኑ እሳትን አነደዱ፡፡ በእግዚአብሔር ፈቃድም ጨለማና ቀዝቃዛ ነፋስ ሆነ፤ ፀሐይም ብርሃኑን ሰወረ፡፡ በዚች ዕለትም እስከ ምሽት ድረስ መብረቅ፣ ነጎድጓድ፣ ዝናምና ብርድም ሆነ፤ ከአገሩ ሰዎች ከሽማግሌዎች ብዙዎች ወደቁ ከእነርሱም ብዙዎቹ ሞቱ ያን ጊዜ ፈሩ ሂደወም ከአገሩ ሰዎች የቅዱሱን ሥጋ አኖሩት፤ የተዘባበቱበትም አሉ “ ታላቁ አምላክ ሆይ የዚህን ሰው ነፍስ ተቀበላት በዚች ዕለት የልደቱ ዕለት ናትና” አሉ፡፡ ምዕመናን ወንዶች ደረሱና የቅዱሱን ሥጋ ከእሳቱ ወሰዱት ጸሎት ወደሚጸለይበት ቦተም አደረሱት በእርሱ ላይም ተሳሉ፣ ምስጋናንም አቀረቡ እንደ ሥርዓታቸውም እንደ አገሩ ሰዎች ገነዙት በቆፈሩለት መቃብርም ቀበሩት፡፡ መታሰቢያውንም በደስታ፣ በምሥጋና አብዝተው አደረጉ፣ አበዙ በአገሩ መሠረታዊ ቦታም አስቀመጡት፡፡ ❤ የሰማዕታት መጀመሪያ በግብጽ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰ የወንጌላዊው የቅዱስ ማርቆስ ዕረፍቱ በሚያዝያ ወር መጨረሻ በ30 ሠላሳኛው ቀን ዕለቱመ ሰኞ ጠዋት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ በተገለጸ 68 ዓ.ም ወደ ሰማይ ባረገ በ35 ዓ.ም በታላቋ አገር በእስክንድርያ ሆነ ፡፡ ከሐዋርያውና ከወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን፡፡ በጸሎቱ ይማረን!፡፡ ምንጭ፦ ገድለ ሐዋርያት ፤ ስንክሳር ፤ ክብረ ቅዱስ ማርቆስ ከሚለው መጽሐፍ። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7 ወይም መዝ 115፥6-7። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ10፥1-19 ወይም ሉቃ 10፥1-12። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። @Eotcw

❤ ቅዱስ ማርቆስ በኢየሩሳሌም የእናቱ የማርያም ቤት የደቀ መዛሙርቱ መገናኛና መሰባሰቢያ ስለነበር ደቀመዛሙርቱን የበለጠ እንዲያውቃቸውና እንዲቀርባቸው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ከማድረጉም በላየ በተለይም ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ባለው የጠበቀ ዝምድናና ቀረቤታ ለቅዱስ ጴጥሮስ የሃይማኖት ልጅ በመሆንና ለአገለግሎቱም ፍጹም መንፈሳዊና እውነተኛ የክርስቶስ ምስክር ለመሆን በቅቷል፡፡ ቅዱስ ማርቆስ በልጅነቱ በኢየሩሳሌም ለመኖር በመታደሉ በዚያም ዘመን ይሰጥ የነበረውን ትምህርት የማግኘት ዕድል ገጥሞት ነበርና የዕብራይስጥ፣ የላቲንና የግሪክ ቋንቋዎችን ያውቅ ነበር፡፡ ❤ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌልን መስበክ የጀመረው ገና በወጣትነቱ ነበር በመጀመሪያ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አብሮ ያስተምር ነበር፡፡ በግብረ ሐዋርያት አንደተገለጸው ቅዱስ ማርቆስ ከቅድስ ጳውሎስና ከቅድስ በርናባስ ጋር ይሰበክ ነበር፡፡ ከዚያም በፊት ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በኢየሩሳሌምና በይሁዳ አስተምሮአል፡፡ ❤ ቅዱስ ማርቆስ ንጹሕና ድንግል መሆኑን መልካምነቱንና ትምህርቱን ተመልክቶ ቅዱስ ጴጥሮስ ለግብጽና ለአካባቢዋ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አድርጎ ሾመው፡፡ በግብጽ አገሮች በሎኒያ፣ በመርቅያ፣ በጣውንቄ፣ በበርቃ ለመጀመሪያ አስተማረ እርሱ ነው፡፡ ወንጌልን አስተማራቸው፡፡ አዳኝ በሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንንም አስተማራቸው፡፡ ሁሉም የዚያች አገር ሰዎች ልቡናቸው የደነደነ ነበሩ በርኵሰት ሁሉ የተሞሉ አማልክትንም ያመልኩ ነበር፡፡ ሰይጣንን በማምለክም ይኖሩ ነበር፡፡ በየቦታው በየመንገዱም ሁሉ ምኩራቦችን የአማልክትን ቤት ይሠሩ ነበር፡፡ መድኃኒትን፣ ዝሙትንም ያደርጉ ሕጻናትን ይገድሉ በደማቸው መድኃኒትን ያደርጉ ነበር፡፡ ❤ ቅዱስ ማርቆስም ወደ ሐዋርያት በሄደ ጊዜ አስቀድሞ በርቃ ደረሰ፡፡ ዘመዶቹ ከእነርሱ ወገን ናቸውና፡፡ እግዚአብሔርን ቃልም አስተማራቸው በመካከላቸው ብዙ ተአምራትን አደረገ፤ በሽተኞችን ፈወሳቸው ለምጻሞችንም አነጻቸው፤ በእርሱ ላይ በአደረው ጸጋም አጋንንትን አስወጣ፤ ብዙዎችም በትምህርቱ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ አምላኮቻቸውንም (ጣዖቶቻቸውንም) ሰባበሩ፤ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስምም አጠመቃቸው፡፡ ❤ በዚያ ቦታም ወደ እስክንድርያ ይሄድ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ተገለጠለት፡፡ በዚያም መልካም ተዘራባት ይኸውም የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ወንጌላዊው ብፁዕ ቅዱስ ማርቆስም ለጦርነት እንደተዘጋጀ ጎልማሳ ሆነ ወንድሞቹንም ሰላም አላቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚያ ቦታ ቅዱስ ወንጌልን አስተምር ዘንድ ወደ እስክንድርያ እንድሄድ አዝዞኛል" አላቸው፡፡ እነርሱም ሸኙት በመርከብም ተሳፍሮ ወደ እስክንድርያ ሄደ በደረሰ ጊዜም ወደ ከተማው በር ገባ የጫማው ማሠሪያም ተቆረጠ "በቅንነትም መንገድ ፈጠነች" አለ በዚያም ከከተማው መግቢያ ጫማ ሰፊ ነበር፡፡ ቅዱስ ማርቆስም እንዲሰፋለት ለርሱ ሰጠው ሲሰፋም ጣቱን ወግቶ ሰነጠቀው ከእርሱም ደም ፈሰሰ በዩናኒም ቋንቋ "ኢታስታያስ" አለ ትርጓሜው አንድ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ማርቆስም "ስሙን የምትጠራው አውቀኸው ነውን" አለው "እንጠራዋለን እንጂ አናውቀውም" አለ፡፡ ቅዱስ ማርቆስ በጣቶቹ ላይ መራቅ ጨመረና አፈር ወሰደ ያን ጫማ ሰፊ ቀባው "በሕያው አግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ስም አጅህ ትፈወስ" አለው፡፡ ስለዚህም ተፈወሰች ጫማ ሰፊውም በሥልጣኑ በቃሉ ያደረገውን ድንቅ ተአምር በተመለከተ ጊዜ "የቸሩ አምላክ አገልጋይ ሆይ እለምንሃለሁ ዛሬ ውጣና በቤቴ ዕረፍ በአንድነትም እንመገብ መልካም ነገርን አድርገህልኛልና" አለው፡፡ ❤ ብፁዕ ቅዱስ ማርቆስም ተደሰተ፡፡ "እግዚአብሔር ሰማያዊት የምትሆን ሕይወት ኀብስትን ይስጥህም" አለው፡፡ ጫማ ሰፊውም ሐዋርያውም እየተደሰተ ወደ ቤቱ አስገባው፡፡ ሐዋርያውም እየተደሰተ ወደ ቤቱ ገባለት። "የእግዚአብሔር በረከት በዚህ ቤት ይኑር" አለ፡፡ ወንድሞች በአንድነት ጸለዩ ከጸሎት በኋላም ተቀመጡና ደስ እያላቸው ተመገቡ፡፡ ጫማ ሰፊውም ቅዱስ ማርቆስን "አባት ሆይ እለምንሃለሁ ይህንን የምትለው እንዴት ነው፤ ይህ ስምስ ምንድን ነው ይህ እንደዚህ የሚቻለው ነው" አለው፡፡ ቅዱስ ማርቆስም "እኔ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ነኝ" አለው፡፡ ጫማ ሰፊውም "እኔ ላየው እሻለሁ" አለው፡፡ ቅዱስ ማርቆስም "እኔ አሳይሃለሁ" አለው፡፡ ቅዱስ ማርቆስም የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ ነው እያለ የወንጌሉን መጀመሪያ አስተማረው፡፡ በትንቢት ስለ እርሱ የተናገሩትንም ከመጻሕፍት ተናገረ፡፡ ጫማ ሰፊውም "እኔ የምትለውን ይህን መጽሐፍ እለምንሃለሁ ከረጅም ዘመን ጀምሮ የግብጻውያን ልጆች እንደማይማሩበት አልሰማህምን" አለው ቅዱስ ማርቆስ እንዲህ በማለት የእግዚአብሔርን ነገር ይነግረው ዘንድ አስቀደመ "የዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ዘንድ ናት" አለው ጫማ ሰፊውም የቅዱስን ነገር በሰማ ጊዜ በእግዚአብሔር አመነ ለእርሱም አመለከተው ከእርሱም ኃይላትን ተአምራትን አየ እርሱ ቤተሰቡ፣ ከአገሩ ሰዎችም ብዙዎቹ ተጠመቁ፡፡ የጫማ ሰፊው ስምም አንያኖስ ይባላል፡፡ ያን ጊዜም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ምዕመናን በዙ፡፡ የአገሩ ሰዎች በሰሙ ጊዜም "ይህ የገሊላ ሰው ከዚህ አገር ደርሷል፤ የአማልክትን እጅ መንሻ ለውጧል፤ እንዳይመለኩ ከልክሏል" አሉ ሊገሉትም ፈለጉት ይጥሉት ዘንድም በእርሱ ላይ ፍለጋን አበዙ ብፁዕ ማርቆስ ይህን በተረዳ ጊዜ አስተማራቸውና አንኖስንም ኤጲስ ቆጾስነት ሾመላቸው ሦስት ካህናትንም ሾመላቸው ስማቸውም ወልዮስ፣ መሪደስና በሪሞስ ይባላል፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮም ሰባት ዲያቆናትን አንድ ላይ አሥራ አንድ ሰዎችን ሾመላቸው፡፡ ❤ ቅዱስ ማርቆስም ወደ ብርቃ ወጣ ለዓመታትም በእርሷ ተቀመጠ፡፡ በሁሉም አገራት ኤጲስቆጶሳትን፣ ካህናትን ሾሞላቸው ወደ እስክንድርያም ተመለሰ፡፡ በእግዚአብሔር በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም ጸጋና ማመን በዛባት የላም ቦታ በሚባለው በባሕሩ ዳር ካለው ቦታም ቤተ ክርስቲያን ሠሩ ከዚያ ቦታ ከዓለቱ ሥርም ታላቅ ድንጋይ ቁራጭ ነበር፡፡ ጻድቁም ስለ ምዕመናን መልካም ሃይማኖት እግዚአብሔርን አመሰገነ ብዙ ዘመን በቆየ ጊዜም ክርስቲያኖች በዙ አማልክትንም ተዘባበቱባቸው፤ አረማውያንንም ናቋቸው፡፡ አረማውያንም ቅዱስ ማርቆስ እንደሆነ ወደ አገራቸው እንደ ደረሰ ተረዱ፡፡ ከሰሙት ተአምራት ብዛት የተነሳ ልቡናቸው በቁጣ ተሞላ እርሱ ሕመምተኞችን ይፈውስ፣ ለምጻሞችንም ያነጻ፣ ደንቆሮዎችንም እንዲሰሙ፣ እውራንንም እንዲያዩ ያደርጋል መልካም ተስፋንም ያስተምራቸው ነበር ይይዙት ዘንድም ፈለጉት፤ በየቤታቸውም ጥርሳቸውን ያፋጩ ነበር፤ በአማልክቱ ምኵራብም "እኛ ለዚህ ጠንቋይ ተሸነፍን" እያሉ ጮኹ፡፡ ምዕመናን የሚያከብሩት ዕለት ሰንበት የተባረከው የፋሲካ በዓልም በሰንበት ቀን ሆነ፤ ይህም ዕለት ሚያዝያ 17 ቀን ነው፡፡ ❤ በዚያች ዕለትም በእነርሱ ዘንድ የሰራቢስ የልደቱ ቀን ነበር፡፡ ያማረች ዕለትን አገኙ ሰላዮችን ላኩና ያዙት፡፡ እርሱን የቅዳሴ ጸሎት ሳይፈጽምም በሰንሰለት አሠሩት በላሞች ቦታ እንጐትተው እያሉም እንደ አውራ ፍየል በየመንገዱ ጐተቱት፡፡ ቅዱስ ማርቆስም በጐተቱት ጊዜ አግዚአብሔርን አመሰገነው፡፡ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በተቀደሰው ስምህ መከራን እንድቀበለ አዘጋጅተኸኛልና አመሰግንሃለሁ” አለ፡፡ ሥጋውም በየመሬቱ ተቆራረጠ ደሙም በየዐለቱ ፈሰሰ፡፡

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ሚያዝያ ፴ (30) ቀን። ❤ እንኳን ለሐዋርያው ለወንጌላዊው ለእስክድርያ ሊቃነ ጳጳሳት አለቃ (መጀመርያ) ከሰባ ሁለቱ አርድእት ለአንዱ ለሆነው ለቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ "ሰላም ለማርቆስ ዜናዊ ወንጌለ ጽድቅ ሰባኪ ለእለ በግብጽ ኖላዊ። ትርጉም፦ በግብጽ ላሉ ምዕመናን ጠባቂን ለኾነ የጽድቅ ወንጌል የሚያስተምር ለኾነው ለባምሥራቹ ለቅዱስ ማርቆስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ ሐዋርያው ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ፦ የቅዱስ ማርቆስ ወላጆች ስም የአባቱ ስም ቅዱስ አርሰጡጳውሎስ ሲሆን የእናቱ ስም ቅድስት ማርያም ይባላል፡፡ አባቱ ባለፀጋና ያላገባ ነበር የአባቱ ስም ስምዖን ይባል ነበር፡፡ ስምዖንም አርስጡጳውሎስን እንዲያገባ ይገፋፋው ነበር፡፡ አንድ ቀን ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ በቤቷ እንግዶችን የምትቀበልና የምታስተናግድ ማርያም የተባለችውን የወንጌላዊ የቅዱስ ማርቆስ እናት አገኘ ፡፡ እሱም እሷም ሳያስቡት ባዩት ሕልምና በመፈክረ ሕልም (በሕልም ፈቺዎች) በተነገራቸው መሠረት ተገናኝተው የትዳር ሕይወትን መሠረቱ፡፡ ❤ አርስጡጳውሎስ ከከበረውና በባለጸግነቱ ከታወቀው ከአባቱ ካገኘው ሀብት ለነዳያን የሚመጸውት፣ ዐሥራት በኩራት የሚያወጣና ወደ እግዚአብሔርም ዘወትር የሚጸልይ ደግ አባት ነበር፡፡ እሱም የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስ ዘመድ የአክስት ልጅ እንደሆነና ቅዱስ ጳውሎስም በመልአክቱ የጠቀሰው እሱን እንደሆነ አንዳንድ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ "አብሮ ከእኔ ጋር የታሰረ አርስጥሮኮስ የበርናባስም የወንድሙ ልጅ ማርቆስ ኢዮስጦስም የተባለ ኢያሱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል" ቈላስይስ 4፥10 ነገር ግን አንዳንድ የግሪክ፣ የላቲን፣ የግእዝና የኮኘት ትርጉሞች "የበርናባስ የወንድሙ ልጅ" የሚለውን ሐረግ አይጠቅሱም ይህም ምንአልባት አንዳንድ የግሪክ ቃላት ከአንድ በላይ ትርጉም ስላላቸው ይሆናል፡፡ ❤ የቅዱስ ማርቆስ እናት ማርያም ተብለው ከተጠሩት ብዙ ቅዱሳት አንስት መካከል አንዷ ናት፡፡ ቤቷ በኢየሩሳሌም እንደነበረና ምዕመናንም በቤቷ በጸሎት ይሰበሰቡ እንደነበር በሐዋ 12-12-17 በሰፊው ተገልጾአል፡፡ ይህም በጥንት ወይም በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ ካሉት መንፈሳውያኑ ሴቶች (ቅዱሳት አንስት) ከፈተኛ ቦታ ያላት እንደነበር ያመለክታል። በዚያን ጊዜ የነበሩ ምዕመናን በአንድነት በክርስቶስ ስም ይሰባሰቡ ስለነበር ክርስቲያን የሚለውን ስም ያገኙትም በዚሁ ወቅት ነበር፡፡ "በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፤ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርቱም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ"፡፡ ሐዋ 11-26 ❤ የቅዱስ ማርቆስ እናት የማርያም ቤት የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ለጸሎት የሚሰበሰቡበት ነበር፡፡ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት በጽርሐ ጽዮን ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ እንደተገለጸላቸውና መንፈስ ቅዱስን እንደላከላቸው በቅዳሴ ዲዮስቆሮስ እንዲህ ተጽፏል "አመ ሣልስት ዕለት ተንሥአ እሙታን ወቦአ ኀበ ሀለው አርዳኢሁ ጉቡአን ወአስተርእዮሙ በጽርሐ ጽዮን … ወበ ፶ ዕለት ፈነወሎሙ መንፈሰ ቅዱስ ከመ ዘእሳት ወተናገሩ በነገረ ኩሉ በሐውርት … በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ የተሰበሰቡ ደቀ መዛሙርት ባሉበት ገባ በጽርሐ ጽዮንም ታያቸው …በ50ኛው ቀንም በእሳት አምሳል መንፈስ ቅዱስን ሰደደላቸው በአገሩ ቋንቋ ሁሉ ተናገሩ" ❤ በኢየሩሳሌም ውስጥ የማርያም ቤት የሐዋርያት መገናኛና መሰባሰቢያ ነበር፡፡ ስለዚህም የማርቆስ እናት የማርያም ቤት የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ኀብረት መለያ ሆኖ ይታወቃል፡፡ ❤ ቅዱስ ማርቆስ የተወለደው በአባቱ ወገን ከነገደ ይሁዳ ሲሆን የተወለደበት ቦታ ከአምስቱ የምዕራብ ከተሞች አንዷ በሆነችው በሊቢያ በሲርኔ ይኸውም አብራይሮሎስ በተባለች ትንሽ መንደር ተወለደ፡፡ ትውልዱ ዕብራዊ ቤተሰቦቹም ይኖሩበት የነበረው በሰሜን አፍሪካ በጥንታዊቱ ፔንዲፓሊስ ሲሪኒካ (ቀሪና) በተባለችው በዛሬው ሊቢያ ምዕራባዊ ጠረፍ በተቆረቆረችው ደማቅ ከተማ ስለነበር ቅዱስ ማርቆስ አፍሪካዊ ነው የሚባለውም ለዚህ ነው የሚሉ አሉ፡፡ ሉሌ መላኩ ቤተክርስቲያንህን እወቅ። ❤ ቅዱስ ማርቆስ ሰኔ 3 ቀን በዕለተ ረቡዕ ተጸንሶ መጋቢት 3 ቀን በዕለተ ዐርብ ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ተወለደ፡፡ ❤ የቅዱስ ማርቆስ የስሙ ትርጓሜ ማርቆስ ማለት ንህብ ማለት ነው ንብ ከሁሉ እንዲቀስም አስቀድሞ ከክርስቶስ በኋላም ከሐዋርያት ተምሮአልና፡፡ አንድም አንበሳ ማለት ነው አንበሳ ለላሕም ጌታው እንደሆነ እንዲሰብረው እርሱም አምልኮተ ላሕምን ከግብጽ አጥፍቷልና፡፡ አንድም ካህን ልዑክ ማለት ነው፡፡ ብሥራተ ማሪ ማርቆስ ይላል የተደራረበ ቀለም ነው፡፡ ሁሉም ካህን ማለት ነው፡፡ እመልአክተ ሲኖዲቆስ ባለ ጊዜ መልእክትም ሲኖዲቆስም ክታብ ማለት እንደሆነ ….። ❤ የቅዱስ ማርቆስ ሁለተኛ ስሙ ዮሐንስ ይባላል። "ባስተዋለም ጊዜ እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለ ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ" ሐዋ12፥12 ❤ የቅዱስ ማርቆስ ተክለ ቁመናና መልክ እንዲሁም አለባበሱን እንዲህ በማለት ተጠቅሷል፡፡ "የግብጽና የኢትዮጵያ ኮከብ ብፁዕና ቅዱስ ማርቆስ መልኩ ቀይ ቅንድቦቹም ከበድ ያሉ ዓይኖቹም እንደሰማያዊ ኀብር የጠሩ ቁመቱ ረጅም ከአንገቱም ስር ስርጉድ የሆነ እንደ ነቢዩ ኤልሳዕ ራሰ በራህ የሆነ ቀሚስ (ልባልባውም) በወገቡ የሆነ የግብጽና የኢትዮጵያ አባት የቅዱስ ማርቆስ ምልክቱ ይኸ ነበር፡፡ ❤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ሥጋዊ በሚሰብክበት ጊዜ ቅዱስ ማርቆስ ወጣት ነበር፡፡ ልቦናው የቀና እንደሆነም አውቆ ከሰባ ሁለቱ አርድእት የመጀመሪያ አድርጐ መረጠው ከዚህ በኋላ የክርስቶስ ደቀመዝሙር ሆኖ ጌታ ወንጌልን ሲያስተምር፤ ተአምራት ሲያደርግ ያስተውል ነበር ፡፡ በምሴተ ሐሙስ በአይሁድ ሲያዝና መከራን ሲቀበል ቅዱስ ማርቆስ በኢየሩሳሌም መንገድ ላየ ሆኖ በርቀት ድርጊቱን ይከታተለ ነበር፡፡ በወንጌሉም እንዲህ ተብሎ የተጻፈው ስለ አርሱ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ "ዕርቃኑን በነጠላ የሸፈነ አንድ ጐበዝ ይከተለው ነበር ጎበዛዝቱም ያዙት፤ እርሱ ግን ነጠላውን ትቶ ዕራቁቱን ሸሸ"፡፡ ማር14-51-52 ❤ ቅዱስ ማርቆስ በቤቱ መጻፊያ ይዞ የጌታን ተአምራት ይጽፍ ነበር፡፡ የግሞ ሊናሮስ የሚባል አገልጋዩን ጌታን እንዲከተልና የሚያደርገውንም ተአምራት እንዲጽፍ ያደርግ ነበር ፡፡ "ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በዓለ ፋሲካን ሲያከብር ተከተሉት" የተባለውም ቅዱስ ማርቆስን እንደሆነ እንዲህ ተጽፍል፤ "ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ላከ እነዲህም አላቸው ወደ ከተማ ሂዱ ማድጋ ውሃ የተሸከመ ሰውም ያገኛችኋል ተከተሉት የሚገባበትንም የቤቱን ጌታ መምህሩ፣ ከደቀመዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ወዴት ነው ይላል በሉት፡፡ እርሱም በደርብ ላይ ያለውነ የተሰናዳና የተነጠፈ ታላቅ አዳራሽ ያሳያችኋል፣ በዚህም አሰናዱልን፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ወጡ ወደ ከተማም ሄደው እንዳላቸው አገኙ ፋሲካም አሰናዱ” ማር 14፥13-15፤ ሉቃ 22፥10-12።