ሰዋስው ☘☘☘☘
Open in Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
Show more1 161
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ኅዳር ፲ (10) ቀን።
❤ እንኳን ለሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት ለበዓላቸው መታሰቢያና ለሃምሳ ቅዱሳት ንጹሐት መነኰሳይያት ደናግልና ለእናታቸው ለነበረች ለቅድስት ሶፍያ በዑልያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ በእስክድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት በድሜጥሮስ ዘመን ስለ ጾም ሥርዓት ቅዱሳት ሊቃነ ጳጳሳትና የኤጲስ ቆጶሳት የአንድነት ጉባኤ ከተደረገበት (የቅዱስ ዲሜጥሮስን ቀመር፡አቡሻህርን በሁሉም ዘንድ እንዲጠቀሙበት በጉባኤ ወሰኑ)፣ ከጳውሎስና ከሦስት ሰማዕታት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ ቅዱሳት ንጹሐት መነኰሳይያት ደናግል እናታቸው ቅድስት ሶፍያ፦ እሊህም ቅዱሳት ከተለያዩ አገሮችና ቦታዎች ሲሆኑ መለኮታዊ ፍቅር በአንድነት ሰበሰባቸው የምንኲስናንም ልብስ ለበሱ ይኸውም የመላእክት ልብስ ነው። በሮሜ አገር ከአሉ ገዳማትም በአንዱ የሚኖሩ ሆኑ ቅድስት ሶፍያም በእነርሱ ላይ እመ ምኔት ሆነች።
❤ እርሷም ጸጋንና ዕውቀትን የተመላች ናት የቅዱሳን መነኰሳትን ገድል በማንበብ እየጾሙ እየጸለዩ በምድር ላይ እንደ መላእክት እስከ ሆኑ ድረስ መንፈሳዊ ዕድገትን አሳደገቻቸው ከእነርሱም በአንድ ገዳም ውስጥ ሰባ ዓመት ያህል የኖሩ አሉ ከውስጣቸውም ልጅ እግሮች የሆኑ አሉ።
❤ ከሀዲ ንጉሥ ዑልያኖስም ከፋርስ ንጉሥ ከሳቦር ጋር ሊዋጋ በሮሀ ሀገር በኩል በሚያልፍ ጊዜ እርሱ ሳቦር ሊወጋው ወደርሱ እንደሚመጣ ሰምቷልና አልፎ ሲሔድም በውስጡ እሊህ ደናግል ያሉበትን ገዳም አይቶ "ይህ ምንድን ነው" ብሎ ጠየቀ ሰዎችም "ይህ የደናግሎች ገዳም ነው" አሉት።
❤ በዚያንም ጊዜ ወደዚያ ገዳም ገብተው ደናግሎችን እንዲገድሏቸው በገዳሙ ውስጥም ያለ ገንዘባቸውን ሁሉ እንዲዘርፉ ወታደሮቹን አዘዘ ወታደሮችም ገብተው እሊያን ደናግል በሰይፍ ገደሏቸው ገዳሙንም አጠፉ የገዳሙን ገንዘብ ሁሉንም ዘረፉ።
❤ ከሀዲውን ንጉሥ ግን ስለ መንጋዎቹ በቀል እግዚአብሔር ተበቀለው ይህም እንዲህ ነው ያጠፋው ዘንድ ሰማዕት መርቆሬዎስን አዘዘው መርቆሬዎስም በአካለ ነፍስ ሒዶ በጦር ወጋውና በክፉ አሟሟት ሙቶ ወደ ዘላለም ሥቃይ ሔደ። እሊህ ቅዱሳት ደናግል ግን ወደ ዘላለም ተድላ ደስታ ገቡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ደናግላንና በእናታቸው በቅድስት ሶፍያ ጸሎት ይማረን በረከታቸው ከእኛ ጋራ ትኑ ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ በዚችም ዕለት በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት በድሜጥሮስ ዘመን ስለ ጾም ሥርዓት ቅዱሳን ሊቃነ ጳጳሳትና የኤጲስቆጶሳት የአንድነት ስብሰባ ተደረገ። በዚህም የአንድነት ጉባኤ የመሰብሰባቸው ምክንያት እንዲህ ነው የክርስቲያን ወገኖች በጥር ዐሥራ አንድ ቀን በከበረች በጥምቀት በዓል ተጠምቀው በማግሥቱ የከበረች የአርባ ቀንን ጾም መጾም ይጀምራሉ እስከ የካቲት ሃያ ሁለት ቀንም ጾመው ጾምን ይፈታሉ።
❤ ከዚህም በኋላ በመጋቢት በሃያ ሦስት የሕማማትን ሰሞን መጾም ይጀምራሉ በዚህም ወር በሀያ ሰባት የስቅለቱን በዓል ያከብራሉ በሃያ ዘጠኝም ክብር ይግባውና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የትንሣኤውን በዓል ያክብሩ ነበር።
❤ ይህ ድሜጥሮስም በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ሁኖ በተሾመ ጊዜ በእርሻ የሚተዳደር መጻሕፍትን የማያውቅ ጨዋ ሰው ሲሆን እግዚአብሔር በመለኮታዊ ስጦታው ልቡን ብሩህ አድርጎለት የብሉይንና የሐዲስ መጻሕፍትን የቤተ ክርስቲያንንም ሕግ አወቀ ከእርሳቸውም ብዙዎችን ተረጎመ።
❤ ከዚህም በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ባሕረ ሐሳብ የተባለ የዘመን ቁጥርን ጻፈ ይህም ክብር ይግባውና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አጽዋማትና በዓላቶቹ የሚታወቁበት እሊህም የከበረች የአርባ ቀን ጾም የሆሣዕና ዑደት ስቅለቱ ትንሣኤው በአርባ ቀን ዕርገቱ ከትንሣኤውም በኋላ በኀምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ የወረደበት ናቸው። ይህንንም ጽፎ ወደ ሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ፊቅጦር ላከ ሁለተኛም ወደ አንጾኪያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ መክሲሞስ ላከ ዳግመኛም ወደ ኢየሩሳሌም አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ አጋብዮስ ላከ እነርሱም በአነበቧት ጊዜ እጅግ ደስ ተሰኙባት።
❤ የሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ፊቅጦርም በሮሜ አገሮች ሁሉ ያሉትን ኤጲስቆጶሳቶቹን አዋቂዎችን ብዙዎች ሊቃውንትንም ሰበሰባቸው ይህንንም የዘመን ቁጥር አስነበበላቸው እጅግ በጣም ጥሩ ሁኖ አግኝተውት ደስ ተሸኙበት በደስታም ተቀበሉት አባዝተውም በመጻፍ ለሁሉ አገሮች ላኩት እስከዚች ዕለትም ጸንቶ ተሠርቶ ኖረ። ከዚህም በኋላ ልዩ ሦስት የሆነ አንድ እግዚአብሔርን ፈጽሞ እያመሰገኑት ወደየሀገራቸው ገቡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ሥርዓትን በሰሩልን አባቶች ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 10 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለደናግል እምተደልዎ ወእምተሐውዞ። ለወልደ ማርያም ድንግል እንዘ ይተልዋ ግዕዞ። ሶበ ዑልያኖስ ቀተሎን ለእሎን በተጋዕዞ። እግዚአብሔር መስተበቅል ለመርቆሬዎስ አዘዞ። በቀለ ደሞን በኲናት ይርግዞ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 10።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ። ወኮነኒ ጽዕለተ። ለበስኩ ሠቀ ወኮንክዎሙ ነገረ"። መዝ 68፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 2፥1-12 ወይም ቲቶ 2፥1-9፣ 1ኛ ጴጥ 3፥1-7 እና የሐዋ ሥራ 17፥34-30። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 25፥1-14። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው። መልካም የሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ልክ የዛሬ 103 ዓመት ኅዳር 9 በዚህች ቀን
(1912) ታላቁ ኢትዮዽያዊ ምሑር፤ የሊቆች ሁሉ ሊቅ፤ ደግና ሐዋርያዊ አባት ሊቀ ሊቃውንት የኔታ አካለ ወልድ ዐርፈዋል።
❤ ሊቃውንት የቀለም ቀንድ ሲሏቸው አፄ ቴዎድሮስ ደግሞ፦ "ይማሯል እንደ አካልዬ፤ ይዋጉዋል እንደ ገብርየ"። ብለው ፎክረውላቸዋል።
❤ የቦሩ ሜዳው ኮከብ ይልቁኑ ለወሎ ሕዝብ ትልቅ አባት ነበሩ።
❤ በኢየሩሳሌሙ ጉባኤም እንዳኮሩን አንዘነጋም።
የሊቁ አካለ ወልድ በረከታቸው ይደርብን።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ ጥንቃቄ ለመላው ኦርቶዶክሳዊ❗️
#ሁሉም ኦርቶዶክስ_ሸር_ያድርግ!!!
❤ የቀበሌ መታወቂያ ጉዳይ ❗️
❤ ታግዶ የቆየው የመታወቂያ እድሳት ከዚህ ከህዳር ወር ጀምሮ መሰጠት የተጀመረ መሆኑን ተከትሎ መታወቂያ ለማሳደስ የሚሄዱ የከተማዋ ነዋሪዎች ከታች የምትመለከቱትን ፎርም አስቀድመው እንዲሞሉ በመደረግ ላይ ይገኛል።
❤ በሚሞላው ፎርም ላይ ከተካተቱት መጠይቆች አንደኛው " ሃይማኖት " የሚለው ነው። አብዛኛው ኦርቶዶክሳዊ ባለማስተዋልና ትኩረት ባለመስጠት በዚህ መጠይቅ ሥር "ክርስቲያን" የሚለውን መጠሪያ መጠቀም ልምድ አድርጎት ይታያል።
❤ ሆኖም በዚህ ወቅት እንደ ወል ስም እያገለገለ በሚገኘው ስም መጠቀም ከኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር ጋር ተያይዞ በቀጣይ ትልቅ ፈተና ይዞ የሚመጣ መሆኑን በማስተዋል ሐይማኖት በሚለው መጠይቅ ሥር " ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ " የሚለውን የሃማኖታችንን መጠሪያ ለይቶ በአግባቡ መሙላት ይገባዋል።
❤ በክርስትና ስም የሚጠቀሙ ሌሎች የሃይማኖት ድርጅቶች በመኖራቸውና ይህም የኦርቶዶክሳውያን ቁጥር የተዛባና የተሳሳተ እንዲሆን ያደርጋል።
❤ በአሁኑ ወቅት እየተስተዋለ እንዳለው ኦርቶዶክሳውያን ከሀገሪቱ ፖለቲካዊ ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እየተገፉና እየተገለሉ እንዲሄዱ በማድረግ ቁጥራቸውን በማዛባትና ዝቅ አድርጎ በማሳየት ፍላጎታቸውን ለማሳካት ለሚፈልጉ አካላት ምቹ ሁኔታ መፍጠር አይገባም።
❤ በተለይም በዕድሜ የገፉና የቀለም ትምህርት ያልቆጠሩ ወገኖቻችንን በማሳወቅ "ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ" የሚለውን የሃይማኖታችንን መጠሪያ በአግባቡ እንዲሞሉ ማድረግ ከእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ የሚጠበቅ ተግባር ነው።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ማኅበረ በኵር እለ በኒቅያ ተጋብኡ፤ በኒቅያ ቃለ ሃይማኖት ወሰኑ ወሠርዑ፤ እንበለ ሕጸት ሥላሴ አርትዑ"። ትርጉም፦ በኒቅያ የተሰበሰቡ የኵር ጌታ ማኅበር፤ በኒቅያ የሃይማኖትን ቃል ወስነው ሥርዐትን (ቀኖናን) ሠሩ፤ ያለ አካላት ጕድለትም ሦስትነትን አቅናኑ። ሊቁ ቅዱስ በድጓው ያሬድ።
+ + +
❤ "ሰላም ለ፫፻፲ወ፰ ርቱዓነ ሃይማኖት ሠራዕያን ሕግ እለ በሥላሴ ዘውግ እለ ይውኅዝ እምከናፍሪሆሙ አንቅዕት ወአፍላግ እለ አጽንዕዋ ለቤተ ክርስቲያን በብዙኅ መናስግ"። ትርጉም፦ ቤተ ክርስቲንን በብዙዎች ቊልፎች (መቀርቀሪያዎች) ያጸኗት ለኾኑ፤ ከከንፈሮቻቸው ምንጮችና የወንዞች ፈሳሽ የሚፈስስ፤ በሥላሴ ተወጋጋኞች (ተባባሪዎች) ለኾኑ ሕግን ለደነገጉ ሃይማኖታቸው ለቀና ለሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ ሊቃውንት ሰላምታ ይገባል። ሊቀ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
https://t.me/Eotcw
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ዮሐ. 10:25-ፍ፡ም፡ "ወአውሥአ እግዚእ ኢየሱስ" - "ኢየሱስም፡መለሰላቸው፥እንዲህ፡ሲል፦ ነገርዃችሁ፡አታምኑምም፡እኔ፡በአባቴ፡ስም፡የማደርገው፡ሥራ፡ይህ፡ስለ፡እኔ፡ይመሰክራል፤
እናንተ፡ግን፡እንደነገርኋችሁ፡ከበጎቼ፡ስላልሆናችሁ፡አታምኑም። በጎቼ፡ድምፄን፡ይሰማሉ፡እኔም፡አውቃቸዋለሁ፡ይከተሉኝማል፤ እኔም፡የዘለዓለም፡ሕይወትን፡እሰጣቸዋለሁ፥ለዘለዓለምም፡አይጠፉም፥ከእጄም፡ማንም፡አይነጥቃቸውም። የሰጠኝ፡አባቴ፡ከዅሉ፡ይበልጣል፥ከአባቴም፡እጅ፡ሊነጥቃቸው፡ማንም፡አይችልም። እኔና፡አብ፡አንድ፡ነን። አይሁድ፡ሊወግሩት፡ደግመው፡ድንጋይ፡አነሡ። ኢየሱስ፦ከአባቴ፡ብዙ፡መልካም፡ሥራ፡አሳየዃችሁ፤ከእነርሱ፡ስለ፡ማናቸው፡ሥራ፡ትወግሩኛላችሁ? ብሎ፡መለሰላቸው። አይሁድም፦ስለ፡መልካም፡ሥራ፡አንወግርህም፤ስለ፡ስድብ፤አንተም፡ሰው፡ስትሆን፡ራስህን፡አምላክ፡ስለ፡ማድረግህ፡ነው፡እንጂ፡ብለው፡መለሱለት። ኢየሱስም፡እንዲህ፡ብሎ፡መለሰላቸው፦እኔ፦አማልክት፡ናችሁ፡አልሁ፡ተብሎ፡በሕጋችሁ፡የተጻፈ፡አይደለምን?መጽሐፉ፡ሊሻር፡አይቻልምና፡እነዚያን፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡የመጣላቸውን፡አማልክት፡ካላቸው፥ የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ነኝ፡ስላልሁ፡እናንተ፡አብ፡የቀደሰውን፡ወደ፡ዓለምም፡የላከውን፦ትሳደባለህ፡ትሉታላችሁን? እኔ፡የአባቴን፡ሥራ፡ባላደርግ፡አትመኑኝ፤ ባደርገው፡ግን፥እኔን፡ስንኳ፡ባታምኑ፡አብ፡በእኔ፡እንደ፡ሆነ፡እኔም፡በአብ፡እንደ፡ሆንሁ፡ታውቁና፡ታስተውሉ፡ዘንድ፡ሥራውን፡እመኑ። እንግዲህ፡ደግመው፡ሊይዙት፡ፈለጉ፤ከእጃቸውም፡ወጣ። ዮሐንስም፡በመጀመሪያ፡ያጠምቅበት፡ወደነበረው፡ስፍራ፡ወደዮርዳኖስ፡ማዶ፡እንደ፡ገና፡ሄደ፡በዚያም፡ኖረ።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
9/3/2015 ዓ.ም
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ወነበቡ ዓመፃ ውስተ ዓርያም ።
ወአንበሩ ውስተ ሰማይ አፉሆሙ።
ወአንሶሰወ ውስተ ምድር ልሳኖሙ፡፡ መዝ 72:8
🕯 ትርጉም
ከፍ ከፍ ብለውም በዐመፃ ተናገሩ።
አፋቸውን በሰማይ አኖሩ።
አንደበታቸውም በምድር ውስጥ ተመላለሰ።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማቴ. 18:12-23 "ምንት ትብሉ እመቦ ብእሲ" - "ምን፡ይመስላችኋል? ላንድ፡ሰው፡መቶ፡በጎች፡ቢኖሩት፡ከእነርሱም፡አንዱ፡ቢባዝን፥ዘጠና፡ዘጠኙን፡በተራራ፡ትቶ፡ሄዶም፡የባዘነውን፡አይፈልግምን? ቢያገኘውም፥እውነት፡እላችኋለሁ፥ካልባዘኑቱ፡ከዘጠና፡ዘጠኙ፡ይልቅ፡በርሱ፡ደስ፡ይለዋል። እንደዚሁ፡ከነዚህ፡ከታናናሾቹ፡አንዱ፡እንዲጠፋ፡በሰማያት፡ያለው፡አባታችሁ፡ፈቃድ፡አይደለም። ወንድምህም፡ቢበድልህ፥ሄደህ፡አንተና፡እርሱ፡ብቻችሁን፡ሆናችሁ፡ውቀሰው። ቢሰማህ፥ወንድምህን፡ገንዘብ፡አደረግኸው። ባይሰማህ፡ግን፥በሁለት፡ወይም፡በሦስት፡ምስክር፡አፍ፡ነገር፡ሁሉ፡እንዲጸና፥ዳግመኛ፡አንድ፡ወይም፡ሁለት፡ከአንተ፡ጋራ፡ውሰድ፤ እነርሱንም፡ ባይሰማ፥ለቤተ፡ክርስቲያን፡ንገራት፤ደግሞም፡ቤተ፡ክርስቲያንን፡ባይሰማት፥እንደ፡አረመኔና፡ እንደ፡ቀራጭ፡ይሁንልህ። እውነት፡እላችኋለሁ፥በምድር፡የምታስሩት፡ሁሉ፡በሰማይ፡የታሰረ፡ይሆናል፥ በምድርም፡የምትፈቱት፡ሁሉ፡በሰማይ፡የተፈታ፡ይሆናል። ደግሞ፡እላችዃለኹ፥ከእናንተ፡ኹለቱ፡በምድር፡በማናቸውም፡በሚለምኑት፡ነገር፡ዅሉ፡ቢስማሙ፡በሰማያት፡ካለው፡ከአባቴ፡ዘንድ፡ይደረግላቸዋል። ሁለት፡ወይም፡ሦስት፡በስሜ፡በሚሰበሰቡበት፡በዚያ፡በመካከላቸው፡እሆናለሁና። በዚያን፡ጊዜ፡ጴጥሮስ፡ወደ፡እርሱ፡ቀርቦ፦ጌታ፡ሆይ፥ወንድሜ፡ቢበድለኝ፡ስንት፡ጊዜ፡ልተውለት፧እስከ፡ሰባት፡ጊዜን? አለው። ኢየሱስ፡እንዲህ፡አለው፦እስከ፡ሰባ፡ጊዜ፡ሰባት፡እንጂ፡እስከ፡ሰባት፡ጊዜ፡አልልህም። ስለዚህ፥መንግሥተ፡ሰማያት፡ባሮቹን፡ሊቈጣጠር፡የወደደን፡ንጉሥ፡ትመስላለች።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
9/3/2015 ዓ.ም
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ንጉሥሰ ይትፌሣሕ በእግዚአብሔር።
ወይከብር ኵሉ ዘይምሕል ኪያሁ።
እስመ ይትፈጸም አፍ ዘይነብብ ዐመፃ፡፡ መዝ. 62÷11
🕯 ትርጉም
ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል።
በእርሱ የሚምል ሁሉ ይከብራል።
ሐሰትን የሚናገር አፍ ይዘጋልና።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯1 161
❤ በዚያም ወራት ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ ጸሐፊ የሚሆነውና የሚረዳው ብልህ ሰው ፈለገ ስለ አባ ይስሐቅም ነገሩት እርሱም መልክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ይጽፍለትም ዘንድ ደብዳቤ ሰጠው እርሱ ግን አባ ይስሐቅ እያወቀ ጽሕፈቱን አበላሸ ሊቀ ጳጳሳቱ እንዲተወውና ወደ አስቄጥስ ገዳም እንዲመለስ ነበር የዚህን ዓለም ክብር ይጠላልና። ሊቀ ጳጳሳቱም እንዲተወውና እንዲአሰናብተው አውቆ ማበላሸቱን በአወቀ ጊዜ "በጥሩ ጽፈሃል ከዚህም እንድትሔድ እኔ አልተውህም" አለው አባ ይስሐቅም እንደማይለቀው አውቆ የሚያውቀውን ሁሉ ጥበቡን ያማረ ጽሕፈቱንም ገለጠለት ሊቀ ጳጳሳቱም በእርሱ እጅግ ደስ አለው።
❤ ከጥቂት ወራትም በኋላ አባ ይስሐቅ ወደ አስቄጥስ ገዳም ተመለሰ አባ ዮሐንስም የሚያርፍበት ቀን በደረሰ ጊዜ ስለርሱ ሊቀ ጵጵስና የሚሾም ማን እንደሆነ ያስረዳው ዘንድ ክብር ይግባውና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው ጌታም በራይ "ከአንተ በኋላ ለዚች ሹመት የሚጠቅም ረዳትህ ይስሐቅ ነው" አለው።
❤ ከዚህም በኋላ ሕዝቡን ጠራቸውና ከእርሱ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት ሁኖ የሚሾም ረዳቱ ይስሐቅ እንደሆነ አስረዳቸው ከዚህም በኋላ አባ ዮሐንስ በዐረፈ ጊዜ ይህን ቅዱስ አባ ይስሐቅን ይዘው በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾሙት በዘመኑም ቤተ ክርስቲያን ብርሃን ሆነች ብዙዎች አብያተ ክርስቲያንንም አደሳቸው ይልቁንም የወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስን ቤተ ክርስቲያን አሳምሮ አደሳት የሊቀ ጵጵስናውንም ቤት አደሰ።
❤ ይህንም አባት ብዙ ችግርና መከራ ደርሶበታል በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ መንበርም ሰባት ዓመት ተኩል ኑሮ ኅዳር 9 ቀን በሰላም ዐረፈ። በዚህም ቅዱስ አባት በመጽሐፈ ገድሉ ከእሑድ ቀን በቀር ሊቀ ጳጳሳት እንዳይሾም የሚያዝ ጽሑፍ አለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሊቀ ጳጳሳት በአባ ይስሐቅ ጸሎት ይመረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 9 ስንክሳር።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ንጉሥሰ ይትፌሣሕ በእግዚአብሔር። ወይከብር ኲሉ ዘይምሕል ኪያሁ። እስመ ይትፈጸም አፍ ዘይነብብ ዐመፃ"። መዝ62፥11። የሚበበው ወንጌል ማቴ 18፥12-23።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወነበቡ ዓመፃ ውስተ ዓርያም። ወአንበሩ ውስተ አፉሆሙ። ወአንሶሰወ ውስተ ምድር ልሳኖሙ"። መዝ 72፥8-9። የሚነበቡት መልዕክታት ቈላ 2፥5-13፣ 2ኛ ዮሐ 1፥6-12፣ የሐዋ ሥራ 15፥22-30። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ10፥25-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የሠለስቱ ምዕት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ኅዳር ፱ (9) ቀን።
❤ እንኳን ሃይማኖት ላቀኑ ለአባቶቻችን ለሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ (ሠለስቱ ምዕት) ኤጲስቆጶሳት ከሃዲ አርዮስን በ325 ዓ.ም በኒቅያ ጉባኤ በጻድቁ ንጉሥ በቈስጠንጢኖስ ዘመን አውግዘው ለለዩበት ቀን ለበዓላቸው መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከእስክድርያ አርባ አንደኛ ሊቀ ጳጳስ ከቅዱስ አባት አባ ይስሐቅ እግዚአብሔር አምላክ ዕረፍት ረድኤት በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ "ሠለስቱ ምዕት ዐሠርቱ ወሰመንቱ ሃይማኖተ እለ ከሠቱ መጋብያነ ምሥጢር ለመንፈስ ቅዱስ ቤቱ፣ በሲኖዶሶሙ ጥቅመ ኃጢአት ነሠቱ፣ ዐላውያን አእትቱ"። ትርጉም፦ የመንፈስ ቅዱስ ማደርያው ሃይማኖታዊ ምስጢርን የሚመግቡ፣ ሃይማኖትን ገልጠው ያብራሩ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ሊቃውንት፣ በጉባኤያቸው የኑፋቄ ሕንጻን አፈረሱ መንናፍቃንንም አስወገዱ። ሊቁ ቅዱስ በድጓው ያሬድ።
+ + +
❤ በዚችም ቀን ዳግመኛ የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት የኤጲስቆጶሳት ስብሰባ በኒቅያ ከተማ በጻድቅ ንጉሥ በቈስጠንጢኖስ ዘመን ሆነ። ከእርሳቸውም ጋራ አራቱ ሊቃነ ጳጳሳት አሉ እሊህም አባ እለእስክንድሮስ የእስክንድርያ፣ አባ ዮናክንዲኖስ ከሮሜ አገር፣ አባ ሶል ጴጥሮስ የቊስጥንጥንያና የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ኤዎስጣቴዎስ ናቸው። ስብሰባቸውም የሆነበት ምክንያት በእስክንድርያ አገር ቄስ ሁኖ ስለ ነበረው ስለ አርዮስ ነው። እርሱ ስቶ የክብር ባለቤት ወልድን በመለኮቱ ፍጡር ነው በማለቱ ነው።
❤ ከእሊህሜ ቅዱሳን ተጋዳዮች አባቶች ከውስጣቸው እንደ ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ በሽተኞችን የሚፈውሱ ድንቆች ተአምራትን የሚያደርጉ አሉ ብዙ ዘመናትም ስለ ቀናች ሃይማኖት የተሠቃዩ አሉ። ከእርሳቸውም የእጃቸውንና የእግራቸውን ጥፍሮች ያወለቋቸው አሉ ዳግመኛም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን የቆረጧቸው አሉ። ጥርሶቻቸውን የሰበሩአቸውና ጎናቸውን የሠነጠቋቸውም አሉ።
❤ ከውስጣቸውም ስሙ ቶማስ የሚባል የአገረ መርዓስ ኤጲስቆጶስ አለ ከሀድያንም ሃያ ሁለት ዓመት አሥረው ርኅራኄ የለውን ሥቃይ አሠቃዩት በየዓመቱም ወደርሱ በመግባት ከሕዋሳቱ አንዱን ይቆርጣሉ እንዲህም በማድረግ እጆቹን፣ እግሮቹን፣ ከንፈሮቹን፣ አፍንጫውንና ጆሮዎቹንም ቆርጠው ጨረሱ። ጥርሶቹንም ሰበሩ በእሳትም ተለብልቦ እንደ ጠቆረ ግንድ አደረጉት የርሱ ወገኖችም እንደሞተ አስበው እንደ ሌሎች ሰማዕታት በየዓመቱ መታሰቢያውን አደረጉ።
❤ እሊህ አባቶችም ወደ ኒቅያ ከተማ በደረሱ ጊዜ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ታላቅና ሰፊ የሆነ መሰብሰቢያ አዳራሽ አዘጋጁላቸው በውስጡም ለየአንዳንዳቸው ወንበርን አኖረ የእርሱንም ወንበር ከእርነርሱ ወንበሮች ዝቅተኛ አደረገ መሳለምን በመርዓስ ኤጲስቆጶስ በቅዱስ ቶማስ ጀመረ ሰገደለት ሕዋሳቶቹ ከተቆረጡበት ላይ ተሳልመው። እንዲሁም አባቶችን ሁሉንም ተሳለማቸው። ከዚህም በኋላ በትረ መንግሥቱን ሰይፋን ቀለበቱን ሰጣቸውና እንዲህ አላቸው "እነሆ አሁን በካህናት ሁሉና በመንግሥት ላይ ሃይማኖቱ እንደናንተ የቀና ከሆነ ታኖሩት ዘንድ ሃይማኖቱ የቀና ካልሆነ ግን ከምእመናን ለይታችሁ ታሳድዱት ዘንድ ሥልጣንን ሰጠኋችሁ"።
❤ እነርሱም ሕግንና ሥርዓትን ሠሩ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመካከላቸው ይቀመጥ ነበር ልቡናቸው በመንፈስ ቅዱስ የበራላቸው ሰዎች አይተውታልና በሚቆጥሩአቸው ጊዜ ግን ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ቊጥር ሁነው ያገኙአቸዋል።
❤ ከዚህም በኋላ ለካህናትና ለሕዝባውያን ለነገሥታት ለመሳፍንት ለሚገዙና ለሚሽጡ ነጋዴዎች፣ ለድኆችም፣ ለሽማግሎችና ለጎልማሶች፣ ለሙት ልጆችም ለወንድና ለሴት ሥርዓትን ሠሩ።
❤ ከዚህም በኋላ ወልድ በመለኮቱ ከአብ ጋር ትክክል እንደሆነ እያስረዱ የቀናች ሃይማኖትን አስተማሩ የተረገመ አርዮስንና በረከሰች ትምህርቱ የሚያምነውን አውግዘው ለዩ።
❤ የሠሩዋት ያስተማሩዋትም የሃይማኖት ትምህርት ይቺ ናት እንዲህ ብለው "ሁሉን በያዘ ሰማይና ምድርን የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም እናምናለን። ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ የተፈጠረ ያይደለ የተወለደ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል። ሁሉ በርሱ የሆነ ያለ እርሱ ግን ምንም ምን የሆነ የሌለ በሰማይም ያለ በምድርም ያለ። ስለእኛ ስለ ሰው ስለ መዳናችን ከሰማ ወረደ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ፈጽሞ ሰው ሆነ። ሰው ሁኖ በጰንጤናዊ ጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ ታመመ ሞተ ተቀበረም በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ። በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ዳግመኛም ሕያዋንንና ሙታንን ይገዛ ዘንድ በጌትነት ይመጣል ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም"።
❤ ከዚህም በኋላ የመንፈስ ቅዱስ ጠላት ስለሚሆን ስለመቅዶንዮስ በቊስጥንጥንያ ከተማ መቶ ሃምሳው የኤጲስቆጶሳት በተሰበሰቡ ጊዜ ከዚህ የቀረውን ሠሩ። እንዲህ አሉ "ጌታ ማሕያዊ በሚሆን ከአብ በሠረፀ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና ከወልድ ጋር በነቢያት የተናገረ። ከሁሉ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰብዋት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እናምናለን። ኃጢአትን ለማስተሥረይ በአንዲት ጥምቀትም እናምናለን። የሙታንንም መነሣት የሚመጣውንም ሕይወት ተስፋ እናደርጋለን"።
❤ እሊህም አባቶቻችን ይችን ሃይማኖት ትምህርት ምዕመናን ሁሉ በቀንም በሌሊትም በጸሎታቸው ጊዜ እንዲአነቡዋት በቅዳሴም ጊዜ እንዲጸልዩባት አዘዙ ወንዶችና ሴቶች፣ ሽማግሎችና ልጆች፣ አገልጋዮችም ሁሉ እንዲማሩዋት አዘዙ። ሠርተው ወስነው ለቤተ ክርስቲያን የሃይማኖትን ፋና ከአስቆሙላት በኋላ ወደ አገራቸው በፍቅር አንድነት ተመለሱ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሠለስቱ ምዕት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ አባ ይስሐቅ፦ ይህም አባት በእስክንድርያ አገር ከተሾሙ መካከል ለአባቶች ሊቀ ጳጳሳት አርባ ዘጠነኛው ነው። ይህም ቅዱስ ቡርልስ ከሚባል አገር ነው ወላጆቹም እግዚአብሔርን የሚፈሩ እጅግም ባለጸጎች ናቸው ከረጅም ዘመንም በኋላ ይህን ቅዱስ በወለዱት ጊዜ በታላቅ ደስታ ደስ ተሰኙበት።
❤ ከዚህም በኋላ ያጠምቀው ዘንድ ወደ ኤጲስቆጶሱም በአቀረቡት ጊዜ ኤጲስቆጶሱም ሲያጠምቀው በሕፃኑ ራስ ላይ የብርሃን መስቀልን አየ በዚያንም ጊዜ የሕፃኑን እጅ ይዞ በራሱ ላይ አኖረ። እንዲህም ብሎ ትንቢት ተናገረት "ይህ ሕፃን በእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ላይ ይሾማል" አባቱንም እንዲህ አለው "ይህን ልጅ ጠብቀው እርሱ ለእግዚአብሔር የተመረጠ መሣሪያ ይሆናል"።
❤ ጥቂትም በአደገ ጊዜ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርትና ጽሕፈትን አስተማሩት የቅዱሳንንም ዜና የሚያነብ ሆነ ወላጆቹንም ትቶ ወደ አስቆጥስ ገዳም ሔደ በአበ ምኔቱ በአባ ዘካርያስም ዘንድ መነኲሶ በገድል ተጠመደ። በአንዲትም ዕለት አንድ ጻድቅ ሰው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አየው በእርሱም ላይ "ይስሐቅ በክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ይሾም ዘንድ አለው" ብሎ ትንቢት ተናገረ።
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ኅዳር_፮ - ፰ #ተዝካረ_አበው_ዘዋልድባ_ ( #ኅዳር ፱ #መግደፊያ፤ #ኅዳር 24 #የሱባኤው ማብቂያ።
❤ ይህ ሱባኤም ሆነ ዝክር በዓለም ላይ በዋልድባ/ዋሊ/ ብቻ ነው የሚደረገው፨
የ160 ቀናት ሱባዔ (4ት ሱባኤ (4x40/)፤
❤ ከሰኔ 16-21 በዋልድባ ገዳም ያሉ ምዕመናን ከገዳሙ ይወጣሉ፤ በአንጻሩ ደግሞ ከገዳሙ ለተለያዩ ጉዳዮች ወጥተው የነበሩ አባቶች ወደ በኣታቸው ይሰባሰባሉ፤.
❤ ከሰኔ 21- ነሐሴ 16 በበኣታቸው ሆነው ሱባኤውን ይጀምራሉ፤
❤ ከነሐሴ 16 ጀምሮ አብዛኞቹ በዓታቸውን ለቅቀው በገዳሙ ውስጥ በሚገኙ ዋሻዎች፣ ፍርክታዎች፣ ገደላ ገደሎች፣ …. መንነው ሱባኤውን ይይዛሉ፡፡
❤ እጅግ በጣም አስቸኳይ ጉዳይ ያጋጠማቸውና ለተልእኮ የሚፈለጉ አባቶችና አርድዕት "አመ ሰዱሱ ለመስከረም" (መስከረም 6፤ የአቡነ ሳሙኤል በዓለ ፍልሰት ላይ) አባቶች ፈቅደውና ጸሎት አድርገውላቸው መውጣት ይችላሉ፤ ግን ኅርመቱ እስከሚያልቅ እስከ ኅዳር 24 ተመልሰው ወደ ገዳሙ መግባት አይችሉም፤
❤ ተዝካረ አበው ዘዋልድባ፦ በኢትዮጵያ በብቸኝነት ጌታችን በመሠረተው በዚህ ታላቅ ገዳም በዋልድባ ብቻ ከሚደረጉ ሥርዐቶች መካከል አንዱና ከቀድሞ አባቶች ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው መካከል፤ ከሰኔ ፳፩ - ኅዳር ፳፬ ድረስ (ለ160 የሱባኤ ቀናት)፤ የወጣ ሳይገባ፥ የገባ ሳይወጣ (መርፌም ቢኾን የቤተ ክርስቲያን መገልገያም ቢሆን ከሱባዔው በፊት ወደ ገዳሙ ካልገባ ሱባዔው እስኪያልቅ ጥቅም ላይ አይውልም)፤ በዕቃ ቤት እስከ ኅዳር 6 ይከርማሉ፤
❤ ሱባኤው የ160 ቀናት ሲሆን፤ ከ140 ቀናት በኋ ላከኅዳር ፮-፰፥ ለ3ት ቀና፤ በስም የሚታወቁም የማይታወቁም፤ በገሃድ የኖሩም በስውር የኖሩም፤ …. የአርጋብ ጸዓድዒድ ቅዱሳን አበው ዘገዳመ ዋሊ ዝክራቸው ነው፡፡ ተዝካረ አበው የሚደረገው ማይ ለበጣ በተባለው ቦታ ብቻ ነው፤ ስለዚህም በዋልድባ አብረንታንትና በሥሩ ያሉ በሱባኤ የቆዩ አባቶች በማኅበር ደረጃ ወደ ማይለበጣ ይሰበሰባሉ፡፡
፠ ከኅዳር 6-8 ተዝካሩ የሚደረገው #ገመሎ_ በተባለውና ቀድሞ የዋልድባ አባቶች (ቋርፍ በዋልድባ ገዳም ከመጀመሩ በፊት ይመገቡት የነበረውን) እጅግ በጣም መራራ የኾነውንና ከመሬት ተቆፍሮ የሚወጣውን፤ ሁሉም የዋልድባ አበው ይመገባሉ (በዓለም ያለን ግን አንድ ፍሬ ቴምር የሚያህለውን ለመመገብ እንኳን እጅግ በጣም ነው የሚከብደን!!)፡፡
❤ #በኅዳር ፱ በእህልና በከብት ይገደፋል፤ ግድፍት ምግብም እስከ ገና ጾም መግቢያ ኅዳር 14 ድረስ ይበላል፡፡ መልሰው ከኅዳር ፱ ጀምረው ደግሞ እስከ ኅዳር ፳፬ ወደ ሱባዔ ገብተው በ፳ወ፬ቱ ካህናተ ሰማይ ትልቁ ሱባዔ ያበቃል፤ ነገር ግን እህል መቅመስ የማይፈልጉ አባቶች ወደ ማይለበጣ ሳይመጡ ሱባኤያቸውን ኅዳር ፳፬ ይጨርሳሉ፤ የፈለገ በኅዳር ፳፬ ወደ ማይለበጣ መጥቶ በእህል ብቻ ይገድፋል፤ ያልፈለገ ግን ከሱባዔ ወደ ሱባዔ በመሸጋገር አያይዞ የገናን ጾም እስከ ገና ጾሞ፤ የገና በዓል ዕለት ወደ ማይለበጣ መጥቶ ይገድፋል፡፡ ዓመት እስከ ዓመት ደግሞ ኅርመተኛ የሆኑና እንጀራ የማይቀምሱም አሉ፡፡
❤ ከኅዳር ፳፬ ጀምሮ ወደ ዋልድባ ገዳም መግባት መውጣት ይፈቀዳል፤ ነግር ግን በ160 ቀናት (ከሰኔ 21- ኅዳር 24 ከቀባሪ በስተቀር መግባት መውጣት አይቻልም፥ ውግዝ ነው)፨
❤ ለእነዚህም ለዋልድባ አርግብ ፀዓድዒድ ቅዱሳን አበው መልክእ ተደርሶላቸዋል፤ እነሆ ከመልክኡ አንዱ እንዲህ ይላል፤
+ + +
❤ "ሰላም ለዝክረ ስምክሙ ለዘይሴኒ እምወይን፤
ወእምነ ሐሊብ ጣዕሙ እንተ ይሠምዮ ልሣን፡፡
አበው ቀደምት ዘአብረንታንት ቅዱሳን፤
እለ ሕገክሙ ዘእንበለ ፍሬ ምኑን፤
ከመ ኢያብኡ እክለ በዛቲ መካን"፡፡
❤ የአበው ጸሎት ምሕረት ያውርድ፤
የአበው እንባ የነደደውን እሳት ያብርድ፤
የአበው አምላክ የአበውን ኀዘን፥ ልቅሶ፥ ስደት፥ መከራ ተመልክቶ ፍርዱን ይስጥ፡፡
የአበው አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ፡፡
❤ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ከአርጋብ ጸዓድዒድ ቅዱሳን አበው አንድነት፥ ከአቡነ ሳሙኤል ልጅነት፥ ከገዳመ ዋሊ ረድኤት በረከት ይክፈለን፥ ከቅድስቲቷ እምነት አያናውጸን። ምንጭ፦ ዋልድባ WALDIBA WALI ገጽ።
https://t.me/Eotcw
