ሰዋስው ☘☘☘☘
Open in Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
Show more1 161
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
1 161
❤ ከዚህም በኋላ አገሪቱን ማጥፋትን ስለ አባ ዮሐንስ ይተው ዘንድ መልሱን ለመኰንኑ ንጉሡ ጽፎ ደብዳቤዋን ወደ ደመናው ወረወራት የተሰበሰቡትም እያዩ እጅ ተቀበለችውና ወደ ደመናው ገባች ወዲያውኑ አባ ዮሐንስ በዚያች ደመና ወደበዓቱ ተመለሰና በማግሥቱ ያቺን ደብዳቤ ለመኰንኑ ሰጠው በላይዋም የንጉሡ ፊርማውና ማኅተሙ አለ በአያትና በአነበባት ጊዜ ደነገጠ አደነቀም ስለ አገሪቱ ድኅነትም እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ አገሩ ተመለሰ። የንጉግሥ ዘመድ የሆነች የከበረች ሴት ዜናውን በሰማች ጊዜ ከደዌዋ ይፈውሳት ዘንድ ወደርሱ መጣች በጸሎቱም ተፈወሰች።
❤ ከዚህም በኋላ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ በሞተ ጊዜ መናፍቁ መርቅያን ነገሠ። ቅዱስ አባ ዲዮስቆሮስንም አሠቃየው። የቀናች ሃይማኖትን ስለመለወጡ አባ ዮሐንስ እየዘለፈና እየረገመው ወደ ርሱ ደብዳቤ ላከ ከጥቂት ወራትም በኋላ እግዚአብሔር ቀሠፈው። ለእርሱም ዕድሜው መቶ ሃያ አምስት ዓመት ሲሆነው ዕረፍቱ እንደደረሰ አወቀ እየጸለየም ግምባሩን በምድር አስነክቶ ሰገደ ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ ከመቃብሩም ቊጥር የሌላቸው ድንቆች የሆነ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 21 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለኪ ማርያም እምነ። ዘሰመናይናኪ ጸወነ። ሶበ እምርኁቅ ርእየ ዘጽላሎትኪ ስነ። ለቢሶ ዳዊት ልብሰ ክብር ዘየሐይድ ዐይነ። ቅድመ ታቦተ ሕግ ኀለየ ወዓዲ ዘፈነ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ አርኬ የኅዳር 21።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ዕግትዋ ለጽዮን ወሕቀፍዋ። ወተናገሩ በውስተ ማኅፈዲሃ። ደዩ ልበክሙ ውስተ ኃይላ"። መዝ 47፥12። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 23፥1-ፍ.ም።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "እስመ ሐረያ እግዚአብሔር ለጽዮን። ወአብደራ ከመ ትኩኖ ማኅደሮ። ዛት ይዕቲ ምዕራፍየ ለዓለም"። መዝ 131፥13-14። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 6፥12-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥5-11 እና የሐዋ ሥራ 7፥44-59። የሚነበበው ወንጌል # ማቴ 21፥42-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጽዮን ማርያም በዓልና የጾም ጊዜ ። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ኅዳር ፳፩ (21) ቀን።
❤ እንኳን ለእናታች ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ታቦተ ጽዮን የፊልስጥኤማውያን ጣዖት ዳጎንን ለሰባበረችበት (ታሪኩ በመጽሐፍ ቅዱስ # 1ኛሳሙ 5)፣ ወደ ኢትዮጵያ ገብታ አክሱም ለመጀመርያ ጊዜ ለከበረችበትና ታቦተ ጽዮን ከነበረችበት ድንኳን ወጥታ ማንም ካህን ሳይሸከማት በተአምራት አብርሃና አጽብሓ ወዳሠሩላት ቤተ መቅደስ ራሷ በመንፈስ ቅዱስ ገብታ ለተገኘች ለዓመታዊ መታሰቢያ በዓልና ለኢትዮጽያዊው ጻድቅ ለአቡነ ተወልደ መድኅን ለበዓላቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሮሜ አገር ከሆነ ተአምራት ከሚያደርግ (ከገባሬ መንክራት) ከቅዱስ ጎርጎርዮስ ዕረፍት፣ ከእስክድርያ ሃምሳ አራተኛ ሊቀ ጳጳስ ከአባ ቆዝሞስ ዕረፍት ከእስሙናይ አገር ሰማዕታት ከእልፍዮስ፣ ከዘኬዎስ፣ ከሮማኖስ፣ ከዮሐንስ፣ ከፊቅጦርና ይስሐቅ ከመታሰቢያቸው፣ ከብርሌና ከብርጭቆ ሠሪዎች ልጅ ከሆነ ከአስዩጥ ሀገር ከቅዱስ አባት ከአባ ዮሐንስ ዕረፍትና፣ ጫብሬ ከምትባል ከአገር ድልበት ከቅድስት ዲቦራ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዕለቱ አንገርናሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ዓይ ይእቲ ዛቲ እንተ ታስተርኢ እምርኁቅ ከመ ማኅቶት ብርህት ከመ ፀሐይ ሙሴኒ ርእያ ሀገር ቅድስት ዕዝራኒ ተናገራ ዳዊት ዘመራ"፡፡ ትርጉም፦ ይህች እንደ መብራት ከሩቅ የምትታየው ማን ናት? ሙሴ ያያት ቅድስት ሀገር ዕዝራ የተናገረላት ዳዊት የዘመረላት፡፡
+ + +
❤ በዚች ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የበዓልዋ መታሰቢ ነው። በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ የሮሜ አገር የሆነ ገባሬ መንክራት ቅዱስ ጎርጎርዮስ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት የቀናች ሃይማኖትንም ተምሮ እውነተኛ ክርስቲያን ሆነ። ከዚህም በኋላ የዚህን ዓለም ኃላፊነት የማታልፍ የመንግሥተ ሰማያትንም ኑሮ አሰበ ኀሳቡንም ሁሉ ስለ ነፍሱ ድኅነት አደረገ።
❤ የዚያችም አገር ኤጲስቆጶስ በኤጲስቆጶስነት ሥራ ይረዳው ዘንድ ለመነው እርሱ ግን አልፈቀደም ከውዳሴ ከንቱ የሚሸሽ ሁኗልና ወደ ገዳምም ገብቶ ጽኑዕ የሆነ ተጋድሎንም መጋደል ጀመረ። የዚችም አገር ኤጲስቆጶስ በዐረፈ ጊዜ ኤጲስቆጶስ የሚያደርጉት ፈልገው አጡ ስለዚህም ተሰብስበው ሳሉ የመለኮትንም ነገር የሚናገር ጎርጎርዮስ ከእርሳቸው ጋር ሳለ ገዳማዊ ጎርጎርዮስን ፈልጋችሁ በእናንተ ላይ ሹሙት የሚል ቃል ከሰማይ ወደ እነርሱ መጣ። በበረሀም ውስጥ በፈለጉት ጊዜ አላገኙትም እየፈለጉትም ብዙ ቀን ኖሩ እርሱ ግን በአቅራቢያቸው ይኖር ነበር። ባላገኙትም ጊዜ በአንድ ምክር ተስማምተው በሌለበት ወንጌል ይዘው በላያቸው ኤጲስቆጶስነት ሾሙት ስሙንም የመለኮትን ነገር በሚናገር በጎርጎርዮስ ስም ጎርጎርዮስ ብለው ሰየሙት።
❤ ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ተገልጦ "ተነሥተህ ወደ እነርሱ ሒድ እነሆ በላያቸው ኤጲስቆጶስነት ሹመውልሃልና ይህም ከእግዚአብሔር የሆነ ነው" አለው። ያን ጊዜም ወደ እነርሱ ወረደ የአምላክን ትእዛዝ መተላለፍ ፈርቷልና በአዩትም ጊዜ ወጥተው በታላቅ ክብር ተቀበሉት የሹመቱንም ሥርዓት ፈጸሙ። እግዚአብሔርም ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ተአምራትን በእጆቹ ገለጠ ስለዚህ ገባሬ መንክራት ጎርጎርዮስ ተብሎ ተጠራ።
❤ ከብዙዎች ተአምራቱም አንዲቱ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ ከእርሷም ብዙ ዓሣዎችን የሚያጠምዱባት ታናሽ ባሕር ነበረቻቸው አንዱም አንዱ የኔ ናት በማለት እርስ በርሳቸው ተጣሉ ስለዚችም ባሕር በመካከላቸው ይፈርድ ዘንድ ወደ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ለመሔድ ተስማሙ እርሱም ከሁለት ተካፈሉ ብሎ አዘዛቸው እንዳዘዛቸውም ባልተስማሙ ጊዜ ስለዚች ባሕር እግዚአብሔርን ለመነው በዚያንም ጊዜ ባሕሪቱ ደርቃ የምትታረስ ምድር ሆነች ስለሚደረጉ ድንቆች ተአምራቴ ዜናው በሁሉ አገር ተሰማ በጎ አገልግሎቱንም ከፈጸመ በኋላ በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ቅዱስ አባት በገባሬ መክራት ጎርጎርዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ የብርሌና የብልጭቆ ሠሪዎች ልጅ አባ ዮሐንስ፦ ይህንም ቅዱስ በወለዱት ጊዜ በበጎ ተግሣጽ አሳደገውታል የጥርብ ሥራንም አስተማሩት ከጥቂት ዘመናትም በኋላ አባቱና እናቱ ዐረፉ። ያን ጊዜ ወደ ቅዱስ ኢስድሮስና ወደ አባ ባይሞን ዘንድ ሒዶ መነኰሰ በጾምና በጸሎት በገድል ሁሉ ተጠምዶ ተጋደለ ዜናውም በራቀ ገዳማት ሁሉ ተሰማ።
❤ ከዚህም በኋላ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጠለት ወደ አገሩ ሒዶ ወገኖቹን የጽድቅን ጎዳና ይመራቸው ዘንድ አዘዘው። ቅዱስ ቊርባንንም ሳይቀበል ከበዓቱ የማይወጣ ሆነ። በአንዲት ዕለትም ሁለት ቅዱሳን አረጋውያን አባ አብዢልና አባ ብሶይ ወደርሱ መጡ ገና ወደርሱ ሳይቀርቡ ከሩቅ ሳለ ስማቸውን በመጥራት ሳያውቃቸው አባቶቼ ለመምጣታችሁ ሰላምታ ይገባል ብሎ ተናገረ እጅግም አደነቁት አባ ሲኖዳም ከግብጽ አገር እየመጣ ብዙ ጊዜ ይጎበኘው ነበር።
❤ የከዳተኞችም ጠብ በግብጽ አገር ላይ በተነሳ ጊዜ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ የላከው የጦር መኰንን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መጣ። በጸሎቱም ይረዳው ዘንድ ለመነው ቅዱስ ዮሐንስም መስቀሉን አንሥቶ መኰንኑን "አይዞህ አትዘን አንተ ጠላቶችህን ድል ታደርጋለህና"፧ አለው እንደ ቃሉም ሆነ። ዳግመኛም በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ላይ ጠላት በተነሣበት ጊዜ ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ላከ እርሱም "አትዘን ጠላትህን ታሸንፋለህ" አለው ያን ጊዜም ጠላቶቹን አሸነፈ።
❤ ከዚህም በኋላ በእነዚያ ወራት ንጉሥ ቴዎዶስዮስ የርኵሰትን ሥራ ስለ ሠሩ የአስዩጥን ሰዎች እንዲገድላቸው ሀገራቸውንም እንዲአጠፉ አዘዘ። ንጉሡም የላከው መኰንን ሳይደርስ የእግዚአብሔር መልአክ ይህን ነገር ለአባ ዮሐንስ አሳወቀው የአገርም ሰዎች የንጉሡን ትእዛዝ በሰሙ ጊዜ ወደ አባ ዮሐንስ ገዳም ወጥተው ስለ መጥፋታቸው በፊቱ አለቀሱ አባ ዮሐንስም "አትጨነቁ አይዟችሁ እግዚአብሔር ያድናችኋላና" አላቸው። መኰንኑም በመጣ ጊዜ ከእርሱ በረከትን ይቀበል ዘንድ ወደ አባ ዮሐንስ ደረሰ አባ ዮሐንስም ንጉሡ ያዘወውን ሁሉ ነገረው መኰንኑም ሰምቶ ደነገጠ ለቅድስናውም ተገዢ ሆነ ለመኰንኑም ርኵስ መንፈስ ያደረበት የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረው ያድንለት ዘንድ ቅዱስ ዮሐንስን ለመነው በዚያንም ጊዜ ዘይትን ቀብቶ አዳነው።
❤ ከዚህም በኋላ የአስዩጥ ሰዎችን መገደላቸውን እንዲተው ወደ ንጉሥ ይጽፍለት ዘንድ መኰንኑን አባ ዮሐንስ ለመነው መኰንኑም ጽፎ ለአባ ዮሐንስ ሰጠው አባ ዮሐንስም ተቀብሎ ወደ ዋሻው ገባ ወደ ጌታችንም ጸለየ ብርህት ደመናም መጣች ተሸክማም ወደ ንጉሡ አደሰገችው ያን ጊዜም ንጉሥ ከማዕድ ላይ ነበረ ያንንም ደብዳቤ ከወደላይ ጣለለት ንጉሡም አንሥቶ በአነበበው ጊዜ ከመኰንኑ የተጻፈ እንደሆነ በመካከላቸው በአለ ምልክት ተሸፎ አገኘው የተጻፈውም ቃሉ ስለ አባ ዮሐንስ ልመና ሀገሪቱን ማጥፋትን እንዲተው የሚል ነበር ቀና ባለ ጊዜም ደመና አየ ንጉሡም አደነቀ።
1 161
20/3/2015 ዓ.ም
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ የቅዳሴ የሚባል ምስባክ
መዝ ፹፫፥፮
እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ፤
ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል፤
ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን።
#ትርጕም፦
የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና፤
ከኃይል ወደኃይል ይሄዳል፤
የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ሰላም ለአንያኖስ ዘተጰጰሰ ቅድመ እምኀበ ማርቆስ"። ትርጉም፦ ከቅዱስ ማርቆስ ዘንድ አስቀድሞ ጵጵስናን ለተሾመ ለአንያኖስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ "ሰላም ለአንያኖስ በኀብለ ሃይማኖት ዘተስሕበ። ላዕለ እስክንድርያ እማርቆስ ከመ ይሠየም አበ። ኄረ ከዊኖ ወአኮ ዓሳበ። እምአፈ ተኵላት መሠጠ ሶበ መርዔቶ ዓቀበ። ዕሴተ ትጉሐን ኖሎት በሰማይ ረከበ"። ትርጉም፦ በእስክንድርያ በማርቆስ ወንበር ላይ አባትን ኾኖ ይሾም ዘንድ በሃይማኖት ገመድ የተሳበ ለኾነ ለቅዱስ አንያኖስ ሰላምታ ይገባል፤ ምንደኛን ያይደለ መልካም እረኛን መኾን ከነጣቂ ተኵሎች መንጋውን በጠበቀ ጊዜ የትጉሃን ዕረኞችን ዋጋ በማይ አገኘ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 20።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ኅዳር ፳ (20) ቀን።
❤ እንኳን በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ እጅ ጵጵስና ለተሾመው ለእስክንድርያ ሁለተኛ ሊቀ ጳጳስ ለቅዱስ አባት ለአባ አንያኖስ ለዕረፍት በዓልና ለሠራዊት አለቃ ለከበረ ለሰማዕት ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተ ክርስቲያኑ ለከበረችበት በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ አንያኖስ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ አረማውያን ናቸዉ እርሱም ጫማ ሰፊ ነበር ቅዱስ ወንጌላዊ ማርቆስ ወደ እስክንድርያ አገር መጀመርያ በገባ ጊዜ እግሩን ተደናቅፎ ጫማው ተቆረጠ እንዲሰፋለትም ወደ ጫማ ሰፊ አንያኖስ ዘንድ ሔደና ጫማውን ሰጠው መስፋትም በጀመረ ጊዜ መስፊያው ጣቱን ወጋው በዮናኒም ቋንቋ "አቴኦስ" አለ ትርጓሜውም አንድ እግዚአብሔር ማለት ነው። ቅዱስ ማርቆስም የእግዚአብሔርን ስም ሲጠራ በሰማ ጊዜ ደስ ብሎት የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰገነው።
❤ ከዚህም በኋላ አፈር አንሥቶ በምራቁ ጭቃ አድርጎ በአንያኖስ ጣት ላይ አደረገውና በዚያን ጊዜ አዳነው አንያኖስም ከዚህ ድንቅ ምልክት የተነሣ አደነቀ ቅዱስ ማርቆስንም ወደ ቤቱ ወሰደው ስለ ሥራው ስለ አምልኮቱም የመጣውም ከወዴየት ቦታ እንደሆነ ጠየቀው። ቅዱስ ማርቆስም ከብሉያትና ከሐዲሳት መጻሕፍት የአንድ እግዚአብሔርን ህልውና ስለ ዓለም ሁሉ ድኅነት የወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን መከራ መስቀልንም ተቀብሎ ስለመሞቱ ስለ ትንሣኤውና ስለዕርገቱ ዳግመኛም ለፍርድ ስለ መምጣቱ ይነግረው ጀመረ። የአንያኖስ ልቡ ብሩህ ሁኖለት በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ከቤተሰብ ሁሉ ጋር ተጠምቀ። የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ በላያቸ ወረደ አዘውትሮ በመጠመድ የሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስን ትምህርት የሚሰማ ሆነ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ሕጓንና ሥርዓቷንም ተማረ።
❤ ቅዱስ ማርቆስም ወደ ሌሎች አገሮች ሒዶ ለማስተማር በፈለገ ጊዜ እጆቹን በአንያኖስ ላይ ጭኖ በግብጽ አገር ለወገኖቹ ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ሊቀ ጵጵስና ሾመው እርሱም ብዙዎችን አስተምሮ አጠመቃቸው በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው ቤቱንም ቤተ ክርስቲያን አደረጋት እርሷም በስተምራብ ከእስክድርያ ከተማ ውጭ ያለች ዛሬ የሰማዕት ቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሁና የታወቀች ናት።
❤ ይህ የተመሰገነ አባት አንያኖስም በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ዐሥራ ሁለት ዓመት አገልግሎ በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አባ አንያኖስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 20 ስንክሳር።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኀይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን"። መዝ 83፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 1፥5-12፣ 1ኛ ጴጥ 5፥1-8 እና የሐዋ ሥራ 20፥20-31። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 10፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ አንያኖስ የዕረፍት በዓልና የነቢያት (የገና) ጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በዕለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማቴ. 10፥1-16 "ወጸውዖሙ ለ፲ወ፪ ሐዋርያት" -"ዐሥራ፡ሁለቱን፡ደቀ፡መዛሙርቱን፡ወደ፡እርሱ፡ጠርቶ፥እንዲያወጧቸው፡በርኩሳን፡መናፍስት፡ላይ፡
ደዌንና፡ሕማምንም፡ሁሉ፡እንዲፈውሱ፡ሥልጣን፡ሰጣቸው። የዐሥራ፡ሁለቱም፡ሐዋርያት፡ስም፡ይህ፡ነው፤መጀመሪያው፡ጴጥሮስ፡የተባለው፡ስምዖን፡ወንድሙ፡እንድርያስም፥የዘብዴዎስ፡ልጅ፡ያዕቆብም፡ወንድሙ፡ዮሐንስም፥ ፊልጶስም፡በርተሎሜዎስም፥ቶማስም፡ቀራጩ፡ማቴዎስም፥የእልፍዮስ፡ልጅ፡ያዕቆብም፡ታዴዎስም፡
የተባለው፡ልብድዮስ፥ ቀነናዊውም፡ስምዖን፡ደግሞም፡አሳልፎ፡የሰጠው፡የአስቆሮቱ፡ይሁዳ። እነዚህን፡ዐሥራ፡ሁለቱን፡ኢየሱስ፡ላካቸው፥አዘዛቸውም፥እንዲህም፡አለ፦በአሕዛብ፡መንገድ፡አትሂዱ፥ወደሳምራውያንም፡ከተማ፡አትግቡ፤ ይልቅስ፡የእስራኤል፡ቤት፡ወደሚሆኑ፡ወደጠፉት፡በጎች፡ሂዱ፡እንጂ። ሄዳችኹም፦መንግሥተ፡ሰማያት፡ቀርባለች፡ብላችሄ፡ስበኩ። ድውዮችን፡ፈውሱ፤ሙታንን፡አስነሡ፤ለምጻሞችን፡አንጹ፤አጋንንትን፡አውጡ፤በከንቱ፡ተቀበላችሁ፥በከንቱ፡ስጡ። ወርቅ፡ወይም፡ብር፡ወይም፡ናስ፡በመቀነታችሁ፥ወይም፡ለመንገድ፡ከረጢት፡ወይም፡ኹለት፡እጀ፡ጠባብ፡ወይም፡ጫማ፡ወይም፡በትር፡አታግኙ፤ለሠራተኛ፡ምግቡ፡ይገባዋልና። በምትገቡባትም፡በማናቸዪቱም፡ከተማ፡ወይም፡መንደር፥በዚያ፡የሚገባው፡ማን፡እንደ፡ኾነ፡በጥንቃቄ፡
መርምሩ፤እስክትወጡም፡ድረስ፡በዚያ፡ተቀመጡ። ወደ፡ቤትም፡ስትገቡ፡ሰላምታ፡ስጡ፤ ቤቱም፡የሚገባው፡ቢሆን፡ሰላማችሁ፡ይድረስለት፤ባይገባው፡ግን፡ሰላማችሁ፡ይመለስላችሁ። ከማይቀበሏችሁም፡ቃላችሁንም፡ከማይሰሙ፡ሁሉ፥ከዚያ፡ቤት፡ወይም፡ከዚያች፡ከተማ፡ስትወጡ፡የእግራችሁን፡ትቢያ፡አራግፉ። እውነት፡እላችኋለሁ፥በፍርድ፡ቀን፡ከዚያች፡ከተማ፡ይልቅ፡ለሰዶምና፡ለገሞራ፡አገር፡ይቀልላቸዋል። እንሆ፥እኔ፡እንደ፡በጎች፡በተኵላዎች፡መካከል፡እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ፥እንደ፡እባብ፡ልባሞች፡እንደ፡ርግብም፡የዋሆች፡ሁኑ።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
19/03/2015 ዓ.ም (፲፱/፫/፳፻፲፭ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ሕጉ ለእግዚአብሔር ንጹሕ ወይመይጣ ለነፍስ።
ስምዑ ለእግዚአብሔር እሙን ወያጠብብ ሕፃናተ።
ኩነኔሁ ለእግዚአብሔር ርቱዕ ወያስተፌሥሕ ልበ። መዝ. 18፥7
🕯 ትርጉም
የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን ይመልሳል።
የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን አዋቂዎች ያደርጋል።
የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው፤ ልብን ደስ ያሰኛል።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ዮሐ. 15:17-26፡ "ወዘንተ እኤዝዘክሙ ከመ ትትፋቀሩ" - "እርስ፡በእርሳችሁ፡እንድትዋደዱ፡ይህን፡አዛችኋለሁ። ዓለም፡ቢጠላችሁ፡ከእናንተ፡በፊት፡እኔን፡እንደ፡ጠላኝ፡ዕወቁ። ከዓለምስ፡ብትኾኑ፡ዓለም፡የራሱ፡የሆነውን፡ይወድ፡ነበር፤ነገር፡ግን፥እኔ፡ከዓለም፡መረጥኋችሁ፡እንጂ፡ከዓለም፡ስላይደላችሁ፡ስለዚህ፡ዓለም፡ይጠላችኋል። ባሪያ፡ከጌታው፡አይበልጥም፡ብዬ፡የነገርኋችሁን፡ቃል፡አስቡ።እኔን፡አሳደውኝ፡እንደ፡ሆኑ፡እናንተን፡ደግሞ፡ያሳድዷችኋል፤ቃሌን፡ጠብቀው፡እንደ፡ሆኑ፡ቃላችሁን፡ደግሞ፡ይጠብቃሉ። ዳሩ፡ግን፡የላከኝን፡አያውቁምና፡ይህን፡ሁሉ፡ሰለ፡ስሜ፡ያደርጉባችኋል። እኔ፡መጥቼ፡ባልነገርኋቸውስ፡ኃጥያት፡ባልሆነባቸውም፡ነበር፤አሁን፡ግን፡ለኃጥያታቸው፡ምክንያት፡የላቸውም። እኔን፡የሚጠላ፡አባቴን፡ደግሞ፡ይጠላል። ሌላ፡ሰው፡ያላደረገውን፡ሥራ፡በመካከላቸው፡ባላደረግሁ፥ኃጥያት፡ባልሆነባቸውም፡ነበር፤አሁን፡ግን፡እኔንም፡አባቴንም፡አይተውማል፡ጠልተውማል። ነገር፡ግን፥በሕጋቸው።በከንቱ፡ጠሉኝ፡ተብሎ፡የተጻፈው፡ቃል፡ይፈጸም፡ዘንድ፡ነው። ዳሩ፡ግን፡እኔ፡ከአብ፡ዘንድ፡የምልክላችሁ፡አጽናኝ፡እርሱም፡ከአብ፡የሚወጣ፡የእውነት፡መንፈስ፡በመጣ፡ጊዜ፥እርሱ፡ስለ፡እኔ፡ይመሰክራል።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
19/3/2015 ዓ.ም (፲፱/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ጽልአ በአመፃ ይፀልዑኒ።
ዕቀባ ለነፍስየ ወአድኅና።
ወኢይትኀፈር እስመ ኪያከ ተወከልኩ፡፡ መዝ. 24፥19
🕯 ትርጉም
የግፍም ጥል ጠልተውኛል።
ነፍሴን ጠብቅና አድነኝ።
አንተን ታምኛለኹና አልፈር።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ሰላም ለቴዎፍሎስ ሰማዕት ዘፈጸመ ገድሎ በሃይማኖት"። ትርጉም፦ ገድሉን በሃይማኖት የፈጸመ ለኾነ ለሰማዕት ቴዎፍሎስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ "ሰላም ለቴዎፍሎስ መናኔ ክብሩ ወዓለሙ። ወለጰጥሪቃ ብጽዕት እንተ ሐመት በሕማሙ። ዓዲ ሰላም ለደማሊስ ወልዶሙ። ዘእንበለ ያእምር ምንተኒ ሰምየ አቡሁ ወእሙ። በእንተ ክርስቶስ ዘተክዕወ ደሙ"። ትርጉም፦ በርሱ መከራ መቀበል ለታመመችንእድ ክብርት ለኾነች ለጰጥሪቃና ዓለምን ከክብሩ ጋር ለናቀው ለቴዎፍሎስ ሰላምታ ይገባል፤ ዳግመኛም አባቱንና እናቱን መጥራት ሳያውቅ ስለ ክርስቶስ ደሙ ለፈሰሰ ለልጃቸው ለደማሊስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ)የኅዳር 19።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ኅዳር ፲፱ (19) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ለዓለም ብርሃን ለሆኑት እመቤታችን ዕጣን እየሰጠቻቸው ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር ላጠኑት ለአቡነ ዮሴፍ ዘእንጂፋት ለልደታቸው በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አባ ዮሴፍ ዘእንጂፋት፦ አባታቸው ንጉሡ ዐፄ ዳዊት እናታቸው ዳግም ሞገሳ ይባላሉ፡፡ ትውልድ ሀገራቸው ወሎ መቄት እንጂፋ ነው፡፡ አባታችን አባ ዮሴፍ ኅዳር 19 ቀን ሲወለዱ በርካታ ሙታን ተነሥተዋል፡፡ ይህም ቅዱስ ያዩትና የሰሙት እስቲያደንቁት ድረስ በአባቱ ቤት ሳለ የዚህን ዓለም ጥበብ ሁሉ ተማረ የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት ተረጐመ ከዚህም በኋላ ዲቁና ሾሙት።
❤ የነፍሱንም ድኅነት እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ ብርሃናዊ መልአኩን ቅዱስ ሚካኤልን ላከለትና "ዮሴፍ ሆይ ይህን ኃላፊውን ዓለም ትወድዋለህን አስጸያፊ አይደለምን በውስጡም ያለ ሁሉ" አለው። ከዚያችም ጊዜ ጀምሮ እርሱ የመረጠውን መንገድ ይመራው ዘንድ እግዚአብሔር እየለመነ ጾምና ጸሎትን ጀመረ።
❤ ከወለቃ አውራጃም ስሙ አባ ዘካርያስ የሚባል ነበረ እርሱም ለዮሴፍ ዘመዱ የሆነ በጭልታም ዮሴፍን ወስዶ የምንኵስና ልብስ አለበሰው። ወደትግራይ ምድርም ወስደውና በዚያ ተግባረ እድ ለምንኵስና ሥራ የሚገባ ጽሕፈትን ስፌትን ተማረ።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ በረሀ ዱር ገብተው የእንጨት ፍሬ እየበሉ ከዝኆኖች ከአንበሶችና ከዘንዶዎች እየተፈተኑ በየአይነቱ በሆነ ተጋድሎ በመድከም ኖሩ። በጽድቃቸውም ኃይል ብዙ ተአምራትን አደረጉ አባ ናትናኤልም የጋለ ምንቸት በመሐል እጁ ይዞ በመነኰሳቱ ፊት ዞረ። አባ ዮሴፍም የሚያበስሉበት ማሰሮ በተሰበረ ጊዜ ወጡ ሳይፈስ አገናኝቶ እንደ ቀድሞው አደረገው። ገብረ ኄርም ሕዝባዊ ሲሆን በሞተ ጊዜ ሊአጠምቁት ሲሉ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ኤጲስቆጶስነት ሹሞኛልና እኔ በእጄ አጠምቃችኋለሁ" አላቸው። እሊህም ቅዱሳን የትሩፋታቸውንና የጽድቃቸውን የአማረ ሥራቸውን አሳዩ።
❤ ከዚህም በኋላ አባ ዮሴፍን ወደ ጳጳስ ወሰዱትና ቅስና ተሾመ። አባ ዘካርያስም በዐረፈ ጊዜ አባ ዮሴፍ ወደ ሌላ ገዳም ሒዶ ሳይቀመጥ ቁሞ አርባ መዓልትም አርባ ሌሊት ጾመ። ከድካም ጽናትም በወደቀ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል አነሣው። ሁለተኛም ከገደል አፋፍ እጁን ዘርግቶ ሳይሰበስብ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ቆመ። ሰይጣንም መጥቶ ወደ ቆላ ወረወረው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ተቀብሎ ወደ መቆሚያው መለሰው። ደግሞም ከደንጊያ ወሻ ውስጥ ገብቶ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ያለ መብልና ያለ መጠጥ ኖረ። ሰይጣናትም ወደርሱ እየመጡ በየራሳቸው ምትሐት በማሳየት ያስፈራሩት ነበር መላእክትም ያበረቱትና ያጸኑታል። ናላው በአፍንጫው እስቲፈስ ድረስ በየእልፍ እልፍ እየሰገደ ኖረ።
❤ ከዚያም የትራይን አውራጃዎች ሁሉ ዞረ። ወደ ሰሜንም ምድር ተሻግሮ ከቅዱስ ያሬድ መቃብር ገባ በደጃፉም ላይ ተቀርጾ አግኝቶ አንቀጸ ብርሃን ተማረ። ሲመለስም ሽፍቶች አግኝተውት በደንጊያ ወገሩት በበትርም ደበደቡት በጦርም ወግተው ጥለውት ሔዱ። አምላክን የወለደች እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም ወደርሱ መጥታ አዳነችው። አንዲት ቀንም የሴት በድን አግኝቶ በላይዋ ባማተበ ጊዜ ተነሣች።
❤ ወደ ኢየሩሳሌምም ሦስት ጊዜ ሒዶ ከከበሩ ቦታዎች ተባርኳል ወደ አባቶቻችን ሐዋርያት መቃብም እስከ አገረ ባርቶስና ሕንደኬ ደረሰ። ውኃው ከመላበት ወንዝም በሚደርስ ጊዜ በላዩ አማትቦ እንደ የብስ በእግሩ እየረገጠ ይሻገረዋል። አንበሶችና ነብሮች ይከተሉታል ምግብ በአጡ ጊዜ ድንጊያውን ባርኮ ሥጋ አድርጎ ይሰጣቸዋል።
❤ ከዚህ በኋላም ወደ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ገዳም ደብረ ሊባኖስ ሔደ። ከአባ ተወልደ መድኅንም እጅ አሰሰኬማ ተቀበለ። አባ ተወልደ መድኅንም ሊፈትነው ወዶ ሰባት የጽድ ቅርንጫፍ ሰብሮ ትከለው ብሎ ሰጠው በተከላቸውም ጊዜ ወዲያውኑ በቅለው አደጉ እስከ ዛሬም አሉ። ብዙዎችም ወደርሱ መጥተው በእርሱ እጅ መነኰሱ እግዚአብሔር አብና አምላክን በወለደች በእመቤታችን ድንግል ማርያም ስም በአነፃቸው አብያተ ክርስቲያን በአንድነት ኖሩ።
❤ በአንዲት ዕለትም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕጣንን ሰጠችውና ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋራ የአሸናፊ የእግዚአብሔርን መንበር አጠነ። ብዙ ጊዜም ወደርሱ ሐዋርያት እየመጡ ይባርኩታል። በአንዲት ዕለትም ነብር ከእናቱ እጅ ሕፃንን ነጥቆ ወሰደ በአባ ዮሴፍም ስም በአማጸነችው ጊዜ በሦስተኛው ቀን መለሰላት።
❤ ለልጆቹም ገንዘብም ሆነ የእንስሳ ጥሪት እንዳያደርጉ ሥጋ እንዳይበሉ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ ትሕትናን ቅንነትን እንዲማሩ ከንቱ ነገር ቧልትን እንዳይናገሩ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዳይስቁ ይህ ሁሉና የመሳሰለውን ሥርዓትን ሠራላቸው።
❤ ከዚህም በኋላም ሩጫውን በፈጸመ ጊዜ ግንቦት19 ቀን በሰላም በፍቅር ዐረፈ ደብረ ታቦር ብሎ በሰየማት ቤተ ክርስቲያንም ተቀበረ ከእርሱም ቊጥር የሌላቸው ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሴፍ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑረሰ ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት19 ስንክሳር።
https://t.me/Eotcw
